ጌታችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ ሲመጣ ስለሰዎች ኃጢአት እኛን ለምሥክርነት አይጠይቀንምና የሰዎችን ኃጢአት መዘከር አቁመን የራስችንን ኃጢአት እየዘከረን በዕንባ በንስሐ ልንጸዳ ግድ ይለናል።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍2🥰2
ሳይንስ እና አቦ ሰጥ
ከመቼ ጀምሮ እንደኾነ አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር ሳይንሳዊ ካልኾነ ወይም በሳይንስ ካልተደገፈ እንዳንቀበለው አእምሮአችን በዚህ መንገድ ተሰርቷል/ እየተሰራ ነው። ስለዚህ ነገሩ ሳይንሳዊ ካልኾነ "ምንድን ነው ዝም ብለህ በአቦ ሰጥ የምትጓዘው?" ትባላለህ።
የዚህን ትርጉም ስንመለከተው ለምሳሌ "ጸበል (የተቀደሰ እርጥበት ያለው አፈር) ተቀብቶ መዳን ሳይንሳዊ አይደለም። ስለዚህ ተቀባይነት አይኖረውም።" ሲሉ ይደመጣል።
እኔ እምለው ከኮኮናት የተሰራ ሎሽን ለሰውነት ከበጀ ደብረ ሊባኖስ ያለው እምነት( ጸበል (የተቀደሰ አፈር) ደዌ የማያድንበትን ምክንያት ለምን በሳይንስ አስደግፈው አይነግሩንም?
ወዳጄ እጅ እግርህ ሲያብጥ ውሃ በጨው አሙቀህ ጠዋት ማታ ታጥበህ ከዳንኽ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት የቅዱስ ገብርኤል ጠበል ከካንሰር ማዳን እንዴት አይችልም ብለህ ታስባለህ?
የኾነው እና እየኾነ ያለውን ነገር በሳይንስ አልተደገፈምና አንቀበለውም ከተባለ የማይኾንበትንም መንገድ በሳይንስ አስደግፈው ይንገሩን።
አቦ ሰጥ ያሉት ነገር ከሳይንስ በላይ እንደኾነ የግድ ማወቅ አለብን። አንድ ወንድ ሱሪው ቢረዝመው "ይህማ ሱሪ አይደለም" አይልም። በሳይንስ ዓይን መንፈሳዊው ነገር የረቀቀ ስለኾነ "አቦ ሰጥ" ማለት ኢሳይንሳዊ ነው።

🤩2❤1🔥1
አንድ ብሎ ማቆም እውቀት አይደለም። ሁለት ሦስት እያሉ መቀጠል ያስፈልጋል። አንድ ባለምሳር ትልቅ ዛፍን ለመቁረጥ የተሳለ መጥረቢያ መያዙ ብቻ አይጠቅመውም። ግንዱ ላይ በጣም ብዙ ጊዜ ምሳሩን ማሳረፍ አለበት።
መጽሐፍም እንዲሁ ነው መደጋገም፣ ዕለት ዕለት መነበብ መቀጠል አለበት።
አእምሮን መግዘር የሚችሉ ከምሳር ይልቅ ስለት ያላቸው መጻሕፍት አሉ።
ስል የኾነው ምሳር ዛፉን ለመቁረጥ በተደጋጋሚ በላዩ እንዳረፈበት፤ እኛም መጻሕፍትን በየቀኑ አእምሮአችን ላይ ማስፈር ይኖርብናል።
አንድ ብለህ ከጀመርኽ ኹለት ብለህ ቀጥል።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
መጽሐፍም እንዲሁ ነው መደጋገም፣ ዕለት ዕለት መነበብ መቀጠል አለበት።
አእምሮን መግዘር የሚችሉ ከምሳር ይልቅ ስለት ያላቸው መጻሕፍት አሉ።
ስል የኾነው ምሳር ዛፉን ለመቁረጥ በተደጋጋሚ በላዩ እንዳረፈበት፤ እኛም መጻሕፍትን በየቀኑ አእምሮአችን ላይ ማስፈር ይኖርብናል።
አንድ ብለህ ከጀመርኽ ኹለት ብለህ ቀጥል።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍7🔥1
❖እስካላቋረጥን አሸናፊዎች ነን❖
እኛ በምናውቀው ሩጫ የአንድ ሯጭ አሸናፊነት የሚወሰነው ሯጮቹን ኹሉ በመቅደሙ ላይ ነው። በመንፈሳዊ ሕይወት ግን እንዲህ የለም። ትግል እንጂ ፉክክር የለም። አንድ ሯጭ በሩጫ ቢሉ በአየር ጠባይ አካሉ ቢዝል መሮጥ ቢያቅተው ሩጫውን አቋርጦ እስካልወጣ ድረስ ደረጃ አይነፈገውም። በእግሩ እየዳኸም ቢሆን ሩጫውን መጨረስ ይችላል። በመንፈሳዊ ሕይወትም እንዲህ ነው። የምንቀድመው የለም። ደረጃችን ግን በሩጫችን ጊዜ በሚገጥመን ትግል፣ መከራ ይወሰናል።
አሸናፊነታችን ዙሩን በመጨረሳችን ከኾነ ወደቅን ብለን ከመሙ መውጣት ምን ይሉታል?
የንጽሕና አየራችን በኃጢአት ወበቅ ተመትቶ ብንዝል፤ በየጊዜው በተለያየ መንገድና መጠን የሰይጣን ጾር እየወጋን ቢያዳክመን፤ ብንፍገመገምም ብንወድቅም እንኳ እስካላቋረጥን ድረስ አሸናፊዎች ነን። ምክንያቱም የሚቀድመንም የምንቀድመውም የለም። መከራውን አልፈን መደረሳችን ድል ያቀዳጀናልና።
ሰይጣን አንድን ሰው የሚያሸንፍበት ኃይል የለውም። የሌለውን ኃይል ግን ከሰውየው ይቀበላል። ሰውየው እንዲያሸንፈው እስካልፈቀደለት፤ እጁን እስካልሰጠ ድረስ ሰይጣን ሊያሸንፈው አይችልም። የሰይጣን ድርሻ እስከጥግ መፈተን ነው። እስከ ጥግ ሲፈትን እጅ ከሰጠን አሸናፊነቱን ይወስዳል።
ምናልባት በተለያዩ የኃጢአት መሰናክሎች እየተሰነካከልን ይሆናል፤ ምናልባት በጎ ነገር ለማድረግ መንፈሳችን ዝሎ ይሆናል፤ ምናልባት መንፈሳዊ ሰው ለመኾን እየፈለግንና እየሞከርን ከሳምንት ያለፈ መንፈሳዊ ኾኖ መቆየት ተስኖን ይሆናል፤ ብቻ በመንፈሳዊው መም በምንሮጥበት ጊዜ ደክመን፣ ተሰላችተን ቢሆን እንኳ በእንብርክካችን እንዳኽ። ሩጫቸውን የጨረሱ ቅዱሳን ማበረታቻ ሰጥተው እንድንሮጥ ያደርጉናልና። በእጃቸው ደግፈው በጸሎታቸው ያድሱናል።
ከቻልን እንብረር፤ መብረር ካልቻልን እንሩጥ፤ መሮጥ ካልቻን ዱብ ዱብ እንበል፤ ዱብ ዱብ ማለት ካልቻልን እንራመድ፤ መራመድ ካልቻልን እንንቀሳቀስ በፍጹም እንዳንቆም።

❤4👏4🔥1🥰1
❖ታዘብከኝ❖
አንድ እኅታችን ትምህርቷን ጨርሳ ስራ ፍለጋ ላይ ነች። ስራ ግን አልተገኘም። ስለዚኽ ኹሉን ማድረግ ወደ ሚችል ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ጸለየች። ስራ ስጠኝ ብላ። ልመናዋን ባቀረበች በጥቂት ጊዜ ውስጥ "3 ሺህ" ብር ደሞዝ ያለው ስራ ማስታወቂያ ይወጣና። የትምህርት ማስረጃዋን ታስገባለች። ጸሎቴ ተሰማ ብላ። ነገር ግን እንዳሰበችው አልሆነም። ወደቀች። ይህን ጊዜ እግዚአብሔርን "ታዘብኩኽ" አለችው። ቀን አልፎ ቀን ተተካ። ሌላ የ"7 ሺህ" ብር ደሞዝ ያለው የስራ ማስታወቂያ ይወጣል። አሁንም እንደጓጓች ይህን አታስመልጠኝ እያለች የትምህርት ማስረጃዋን ታስገበለች። እግዚአብሔር የሚሰማት አልኾነም። ይህም ስራ አመለጣት አጣችው። አሁን እጅግ ከፍቷታል ያንን ቃል ደግማ "ታዘብኩኽ" አለችው፤ እግዚአብሔርን። አሳይቶ እንደነሳት ነው የተረዳችው። ዳግመኛም ከቀናት በኋላ ከ"10 ሺህ" ብር ደሞዝ በላይ ያለው የስራ ማስታወቂያ ይወጣል። አሁን ግን እምቢ አለች። ቤተ ሰቦቿ ጓደኞቿ ቢሏት ቢሰሯት ፈጽሞ እምቢኝ አለች። "በ3ሺ እና በ7ሺ ያላገኘሁትን ስራማ አይሰጠኝም" ብላ እግዚአብሔርን በማኩረፍ ጸናች። ጓደኞቿ የትምህርት ማስረጃዋን ወስደው እርሷ ሳታውቅ ያስገቡላታል። ባላወቀቸውና ባላሰበቸው መንገድ ከ10 ሺ ብር በላ ደሞዝ ያለው ስራ ለእርሷ ይሆናል። ከመስሪያ ቤቱ ተደውሎ ይነገራታል። ማመን ቢያቅታትም በመጨረሻ ወደ እግዚአብሔር ቀና ብላ "ታዘብከኝ" አለችው።
ይህ ታሪክ እውነተኛ ታሪክ ነው። በብዙዎቻችን ሕይወት ውስጥ ይህን መሰል ታሪክ ተደርጎም ያውቃል። እግዚአብሔርን አምነን፣ ፈልገን ከጠየቅነው በኋላ እርሱ የወደደውን እንዲሰጠን ሳይሆን እኛ ያሰብነውን ካልሰጠን እንላለን። በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ከእናንተ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብ ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታዎችን መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? " ይለናል። ማቴ ፯፥፱-፲፩።
እግዚአብሔር ለሚለምኑት የሚለምኑትን ብቻ ሳይኾን የሚሰጠው ከሚለምኑት አብልጦ ነው። ፈያታዊ ዘየማን በዕለተ ምጽአት በመንግሥቱ እንዲያስበው ጠየቀ፤ ጌታችን ግን የጠየቀው ዕለት በገነት ከእርሱ ጋር እንዲኾን ፈቀደለት። የደሙን ማኅተም ሰጠው። ከአዳም ቀድሞ ገነት ገባ።
መጻጉዕ ደቀ መዛሙርቱን አዝዞ አልያም እርሱ ተሸክሞ ወደ መጠመቂያው እንዲወስደው ጠየቀ፤ ጌታችን ግን አልጋኽን "ተሸክመኽ ሂድ" ብሎ አዳነው።
እንግዲህ እግዚአብሔር እንዳይታዘበን ከለመንነው በኋላ እርሱን እንጠብቅ። የሚሰጠንንም በጸጋ እንቀበል።
የክርስቶስን ምሥጢር እንደናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ እንዲከፍትልኝ በመልካም እንድኖር ስለእኔ ደግሞ ጸልዩ።
ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
መጋቢት 23 2014 ዓ.ም ዘተጽሕፈ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በድጋሚ የተለቀቀ

👍4🥰2❤1
ይህስ በነግህ የመጣ የጽድቅ ጥሪ ነው። ይህስ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው። ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
እንግዲህ ምን እንላለን? 97% በመናፍቃን ለተከበበው ለሆሳዕናው ፀሐይ ለሆመቾ ቅድስት ሥላሴ የአቅሜን እንዳላደርግ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
አንድ ውዳሴ ማርያም ገዝቼ ለመዳን የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
https://t.me/getseseb
እንግዲህ ምን እንላለን? 97% በመናፍቃን ለተከበበው ለሆሳዕናው ፀሐይ ለሆመቾ ቅድስት ሥላሴ የአቅሜን እንዳላደርግ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
አንድ ውዳሴ ማርያም ገዝቼ ለመዳን የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
https://t.me/getseseb
✟እግዚአብሔር ያውቃል✟
ዲያብሎስ የነጋችንን አያውቅም። እንዲሁ እኛም ስለነጋችን አናውቅም። እግዚአብሔር ግን ያውቃል።
ዲያብሎስ ስለትናንታችን ያውቃል። እኛም ስለትናንታችን እናውቃለን። እግዚአብሔር ግን ትናንታችንንም ዛሬአችንንም ነጋችንንም ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛም ከዲያብሎስም በላይ ያውቃል። ዲያብሎስ ከትናንት ታሪኮቻችን ላያውቃቸው የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉት። ስለትናንታችን ያውቃል ስንል ከእኛ እኩል ያውቃል ማለታችን አይደለም። ስለዚህ ስለራሳችን ባለን እውቀት እንበልጠዋለን ማለት ነው። ታዲያ ከእግዚአብሔር ይልቅ ዲያብሎስን የምንፈራው ለምንድን ነው?
ብዙዎቻችን "እግዚአብሔር ያስተካክልልኛል፤ ያሳካልኛል" ከማለት ይልቅ "ሰይጣን ያሰነካክለኛል፤ ያበላሽብኛል" ማለት ይቀናናል። ሰይጣን ከትናንት ታሪካችን ተነሥቶ ነጋችንን በሊኾን ይችላል ገምቶ ነው ፈተና የሚቀምረው። ይህ ማለት የሰይጣን ዕውቀት ግምታዊ እንጂ ፍጹም አይደለም። ሊኾንም ላይኾንም ይችላል ላይ የረገጠ ያልጸና ዕውቀት ነው። የእግዚአብሔር ግን ይለያል። እግዚአብሔር ትናንትን "ይቅር በለኝ" ሲሉት ሙሉ በሙሉ ይቅር የሚልና ዛሬን የሚያኖር ስለነገ ደግሞ ብሩህ ተስፋ የሚሰጥ አምላክ ነው።
ትናንት ዘማውያን፣ ትናንት ዘፋኞች፣ ትናንት ሌቦች፣ ትናንት ሱሰኞች፣ ትናንት ሰካራሞች፣ ትናንት ወስላቶች፣ ትናንት ለመንፈሳዊ ስራ ከበረዶ ይልቅ የቀዘቀዝን ለኀጢአት ደግሞ የምንፋጠን ኾነን ሊኾን ይችላል። እሊህ ኹሉ ከተራራ የገዘፉ ኀጢአቶቻችን ግን በእግዚአብሔር ምሕረት ፊት ኢምንት ናቸው።
እግዚአብሔር ራሳችንን ከምንወደው በላይ ያፈቅረናል። እግዚአብሔር ራሳችንን ከምንከባከበው በላይ ይሳሳልናል። ካህኑ ጋር ሄደን ንስሐ እንግባ። ይህን ብቻ ነው እግዚአብሔር የሚፈልገው። የእኛን በንስሐ መመለስ ብቻ።
ዛሬ ካለንበት ጨለማ በብርሃኑ የሚሞላን ብርሃናችን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ብርሃንን መቃወም የሚችል ጨለማ የለም። እግዚአብሔርን ከወደድነውና ከእርሱ ጋር መኖር ከፈለግን ያበራልናል። ከገባንበት ጨለማ ያወጣናል። ይኽ ብቻ አይደለም።
እግዚአብሔር ስለነጋችን ከማንም በላይ ያውቃል። ነጋችንን ያለማንም እርዳታ ያስተካክላል። እግዚአብሔርን መቃወም የሚችል ሰማያዊም ኾነ ምድራዊ ኀይል የለም። ሰይጣን ተመቸውም አልተመቸውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ካለ በፍጹም ሊያሸንፈን አይችልም። እግዚአብሔር ደግሞ ከእኛ ጋር የሚኾነው በንስሐ በር ወደ እርሱ ስንገባ ነው። በንስሐ ውኃ ቤታችንን አጽድተን ስንቀበለው በልባችን በክብር ስናስተናግደውና ስናነግሠው ነው።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ

🥰2
✟ነገን ለምን፧✟
ነገ አይነጋም ብለን አናስብም። ነገ እንደምንሞትም አንገምትም። "ነገ እንገናኝ" ብለን ግን እንቃጠራለን፨
አውቀነውም ይኹን ሳናውቀው ነገ ላይ ህልው የመኾን ጥልቅ ፍላጎት አለን። ነገር ግን ነገ ላይ ለመኖር ምንም ዓይነት ሥልጣን የለንም። ነገ ላይ ማድረስ የሚችል ሥሉስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፨
እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ፤ ስለነገ የምናወራው በእግዚአብሔር ላይ ባለን ጥልቅ መደገፍ ነው፧ ወይስ የመኖር ፍላጎት ስላለን፧ ነገ መኖር የምንፈልገው መኖር ስለሚያስደስተን ነው፧ ወይስ ነገ ላይ የምናርማቸው ነገሮች ስላሉ፧ ቆይ ግን ለምንድን ነው ነገ የምንኖረው፧ ከዛሬ ምን የተሻለ ነገር እናደርጋለን፧ ዛሬን በቆሻሻነት ኖረን ነገን ለመኖር የምንፈልገው ለምንድን ነው፧
ነገን የሚሰጠን ትናንት ያኖረን ዛሬን የሰጠን እግዚአብሔር ነው። ስለኹለት ነገር ነገን ይሰጠናል፥
፩ኛ ዛሬን በመልካምነት፣ በንጽሕና፣ በጸሎት፣ በምስጋና በአጠቃላይ በእግዚአብሔር ሀሳብ፣ ፍላጎትና ፈቃድ ከኖርን ነገም ከዚህ በላይ እንድንተገብርና ከክብር ወደ ላቀ ክብር እንድንሸጋገር፨
፪ኛ ዛሬን በኀጢአት፣ በከንቱነት፣ ከእግዚአብሔር ፈቃድና ሀሳብ ውጪ ከኖርን በይቅርታ ተመልሰን ነገ በእግዚአብሔር ፍላጎት እንድንኖር ነው፨
ትናንትን በኀጢአት አሳልፈን ሳለ ዛሬን የሰጠን ይቅር ሊለን ነው። በኀይሉ፣ በሞገሱ፣ በክብሩ፣ በጸጋው ሊሞላን ነው። መኖራችን ጥቅም ባይኖረው ኖሮ ዛሬን ባላየናት ነበር። የሰጠንን ዛሬ ከተጠቀምን የሌለችንን ነገ ይሰጠናል። የሰጠንን ዛሬን ካልተጠቀምንም ነገን እንድንጠቀም ስለፍጹም ፍቅሩ ነገን ይሰጠናል፨
በዛሬ ከታመንን በነገ ይሾመናል።
ዛሬ በጸሎት እንታመን። ዛሬ በምስጋና እንታመን። ዛሬ በምጽዋት እንታመን። ዛሬ በንጽሕና እንታመን። ዛሬ በንስሐ እንታመን። ዛሬ በማንበብ እንታመን። ዛሬ በጎ ቃላትን በመናገር እንታመን።....
✢ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው✢

❤3👍1
✟ "ዕዳሽ ገና"✟
"ቆማጣ ውብ የኾነች መልከ መልካም ሴት ልጅ ወለደና ቤተ ዘመዱ ተሰብስቦ ስም ሲያወጣ "አማረች፣ ተዋበች፣ ውብነሽ፣ አበራሽ" ትባል በማለት ሲከራከር አባት ሰምቶ ልቡ በሐዘን ተነካ ቀጠል አድርጎ "ዕዳሽ ገና" ትባል አለ ይባላል።"
ይህን ድንቅ ጽሑፍ ሥነ ምግባር በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ነው ያገኘኹት።
ይህ አባት ከቤተ ዘመዱ በላይ በተወለደችው ውብ ልጅት ከማንም በላይ እንደሚደሰት ሳይታለም የተፈታ ነው። እንኳን ውብና መልከ መልካም ኾና ይቅርና የአብራኩ ክፋይ ፉንጋ እንኳ ብትኾን አባት በልጅቱ መወለድ የእውነት ይደሰታል።
አሁን የመጣ ደስታ ግን ቀጣይ የሚመጣ መከራን ከጋረደ ሕይወት ዕውር ዕውርን እንደሚመራው መኾኑ አይቀርም። ልጅቱ ሴት እና መልከ መልካም መኾኗ በረከት እንዳለው ኹሉ ሴት እና መልከ መልካም መኾኗም የኋላ ኋላ መከራ ማምጣቱ የሚጠበቅ ነው። እሱ ደግሞ አባት ነው እርሷ የዐይኑ ማረፊያ ስስቱ። ለዚህ ነው "ዕዳሽ ገና" ትባል ሲል የሰየማት።
በእርግጥ ዕዳው ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለእርሱም መኾኑ ግልጥ ነው። አባት ነው ቆርሶ ማጉረሱ፣ ቀዶ ማልበሱ እንዳለ ኾኖ ከክፋትና ከክፉዎች ሁሉ ሊጠብቃት ከጉማሬ ቆዳ በላይ የጠነከረ ጋሻ መኾን ያሻዋል። ስሟ የእርሷ መጠሪያ ኾነ እንጂ ስሟን ሲጠራ "ዕዳዬ ገና" እያለ ለራሱ የሚሰማው ይመስለኛል።
ብዙዎቻችን በዛሬ ትንሽ ደስታ የዛሬንና የነገን ትልቅ ደስታን እያጣን ነው። ለምሳሌ እንቅልፍ አንዲት ባለሙያ ከምትሰራው ጣፋጭ ወጥ ይልቅ ይጣፍጠናል። እናም ይህን "ጣፋጭ" እንቅልፍ "ሺ ዓመት አይኖር" እያልን እንለጥጠዋለን። ነገር ግን "ሺ ዓመት አይኖር" እያልን ዘለዓለም እየሞትን ወይም የዘለዓለም ሞትን ገንዘብ እያደረግን መኾኑን ልብ አንልም።
አባ ዮሐንስ ዘሰዋስው እንዲህ ይላል" ንቁ ዐይን አእምሮን ንጹሕ ያደርጋል የበዛ እንቅልፍ ግን ነፍስን ያደነዝዛል።" ስንቶቻችን እንሆን ነፍሳችን የደነዘዘው?
በየሚዲያውም ቁጭ ብለን የምንጋተውም "ለሽ እንበል" ነው። ተግቶ ስለመተኛት እንጂ ተግቶ ስለመሥራትና ስኬታማ ስለመኾን አይነገሩንም። አቅዶ ስለመስረቅ እንጂ አቅዶ ባለጸጋ ስለመኾን አያስተምሩንም። ስለመበቀል እንጂ ምሕረት ስለማድረግ አይሰብኩንም። ድንግልናን ከጋብቻ በፊት በዝሙት ስለማጣት እንጂ ስለድንግልና ስለንጽሕና ስለጋብቻ ቅዱስነት አያስረዱንም።
ዐይን የሥጋ፤ አእምሮ የነፍስ ገንዘብ ናቸው። በአፍህ የገባ እንጀራ ሆድህ ላይ እንዲቀመጥ በዐይንህ የገባው ነገርም አእምሮህ ላይ ይቀመጣል። አእምሮህ ደግሞ አንተን የሚቆጣጠርህ ፍጥረት ነው። ይህ ማለት አሁን በሕይወትህ የምታደርጋቸው ነገሮች መጥፎም ይሁን መልካም በሥጋህ (በአምስቱ የስሜት ሕዋሳትህ) ለአእመሮህ (ለነፍስህ) የመገብከውን ነው።
ወዳጄ በሕይወትህ መንፈሳዊ፣ ነፍሳዊ፣ ሥጋዊ መልካም ለውጥ በየቀኑ እያመጣህ ካልሆነ "ዕዳህ ገና" አንተ ነህ።
እታለም ዛሬም ስትዘባነኚና በእርድና መንፈስ ስትሸቀረቀሪ የምታሳልፊ ከኾነ አንቺ "ዕዳሽ ገና" ነሽ።
ከመካከላችን ግራዋ የሚጣፍጠው ማን ነው? ለፍየል ግን ተመራጭ ምግቧ ነው። እንቅልፍም ለሰነፎች ከማር ከወተት የሚመርጡት ምግባቸው ነው። ለትጉሆች ግን ከግራዋ በላይ ይመራቸዋል። ግራዋ ለፍየል የጣፈጣት ባሕሪው ጣፋጭ ስለኾነ አይደለም የፍየሏ ምላስ እንጂ። እንቅልፍም የሚጣፍጠን ጣፋጭ ስለኾነ አይደለም ሰነፎች ስለኾንን እንጂ።
እንግዲህ ምን እንጠብቃለን? በነግህ እንንቃ ውዳሴ ማርያም እንድገም። አእምሯችን ንጹሕ፣ ቀናችን ብሩህ፣ ሕልማችን እውን፣ ሥራችን ሥሙር ይኾናል።

"አባት ላም ይሰጣል፤ ልጅ አጓት ይነሳል።"
በብዙዎቻችን የሕይወት መስመር ውስጥ የሚጸጽተንና ተመልሰን ዕድሉን ብናገኝ እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል የምናስባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ልጅ እያለን እናታችን ስታዘን እያኮረፍንና እየተኮሳተርን "ገረድ መሰልኩሽ እንዴ" እያልን ትእዛዟን ተላልፈናል። ዛሬ ላይ ኾነን ግን ልጅ ወልዶ ያየው ይቅርና ለእናት ገረድነት የሚያንስባት እንደኾነ ያልወለደም ያውቀዋል።
ያ እርሷን በማበሳጨት ያሳለፍናቸው እድሜዎች ዛሬ ላይ እናታችንን ሕመም ላይ እንደጣላት ስናይ የፈሰሰውን ውሃ ለማፈስ እንታትራለን። በእርግጥ አሁንም ከገባን የፈሰሰውን ማፈሱ ጥቅም አለው። ሌላ ብስጭት ፈሶ ሌላ ሕመም በእናታችን አይጨመርምና።
ከአባታችን አብራክ በመከፈላችን ከእናታችን ማኅጸን በመውጣታችን ምክንያት ቆሻሻችንን ሲያጸዱ፣ ክብር እየነፈግናቸው ለእኛ እና ስለእኛ ደፋ ቀና ሲሉ እያየን የርኅራኄ ጠብታ በልቡናችን ያለመንጠቡ ያሳዝናል።
የኹላችን አባትና እናት እግዚአብሔርስ ለእኛ ከምድራውያን እናትና አባት በላይ ያላደረገልን ምን አለ? ከመላእክት አልቆ ፈጥሮናል። በአርአያውና በአምሳሉ አበጅቶናል። ከፍጥረታት ኹሉ እኛን "እጅግ መልካም ፍጥረት" አደረገን። የምናስብ፣ የምንናገር፣ የምንኖር (ሕያዋን) አደረገን። አጓት ምስጋናን በልቡናችን አስበን በአንደበታችን እንድንናገር የበቃን ፍጥረቱ አደረገን። ታዲያ ለምንድን ነው እስከዛሬ አጓት ምስጋናን ያላቀረብንለት? እርሱ እኮ የሚቃጠል መሥዋዕትን ሳይሆን የተሰበረ መንፈስን ይወዳል።
የተሰበረ መንፈስ ምንድን ነው? በትሕትና፣ በፍቅር በምስጋና የተሞላ ልቡና ነው። እርሱ እግዚአብሔር ትሑታንን ይወዳል። ትሑታንም ለእርሱ ለእግዚአብሔር ሳያቋርጡ የምስጋና መስዋዕት ይሰዉለታል። ይህም የተፈጠሩበት ዓለማ ነውና ሳይዘነጉና ሳይታክቱ
ምስጋና ያቀርቡለታል። ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነውና የተፈጠርነው።
ስለዚህ ተወዳጆች ላሙን ለሰጠን አባት አጓትን አንንሳው። አናመሰግነው ዘንድ ያጎደለብን አንዳች ነገር የለምና።

❤1👍1
+++ «ለመተኛት ወደ አልጋህ ባመራህ በቀረብህ ጊዜ አልጋዬ፡ ምን አልባት በዚህ ሌሊት ለእኔ መቃብሬ ልትኾኚ ይኾን ይኾናል፤ በጊዜአዊው ዕንቅልፍ ፈንታ በዚህ ሌሊት ያኛው እንቅልፍ (ሞት) ይመጣብኝም እንደ ኾነ አላውቀውም በላት ።
ስለዚህ ነጻ እግሮች እያሉህ ከመልካም ሥራ በኋላ ሩጥ፤ ከታሠሩ መፈታት በማይችሉበት ማሰሪያ ከመታሠራቸው በፊት፡፡ የእጆችህ ጣቶችም እስካሉህ ድረስ ሞት ከመምጣቱ በፊት በጸሎት ፊትህንና መላ ሰውነትህን በተእምርተ መስቀል አማትብ፡፡ ዐይኖች እስካሉህ ድረስ በአቧራ ከመሽፈናቸው በፊት በአንብዕ(በእንባ) ምላቸው።
ሰው ሆይ ከዚህ ዓለም መለየትህን አስብ፣ እንዲህም በል፡- እነሆ የታዘዘ መልአክ ከበር ቆሞአል (ደርሶአል)፣ እኔንም ይከተለኛል። ለምን ሊል ዘሊል እኾናለሁ? መመለሻ የሌለው ዘለዓለማዊ መንገድ አለ፡፡
መለኮት ደግነት የተነሣ የሰውን ልብ የሚገዛውና ነፍስን ወደ ሕይወት የሚመራት የመጀመሪያው ትምህርት ተዘክሮተ ሞት ነው።.ተዘክሮተ ሞት በሰይጣን እጅግ በብዙ ይጠላል፡፡ እርሱም ከሰው ተዘክሮን ለመንቀል በሙሉ ኃይሉ መሞከርን አይተዉም፡፡ የሚቻለውስ ቢኾን በምድራዊ ሕይወት አሳብ ተብትቦ ተዘክሮተ ሞትን ከሰው ልብ (አእምሮ) ለማስወገድ ምድራዊ መንግሥታትን ለሰው በሰጠው ነበር፡፡ አታላዩ ሰይጣን ተዘክሮተ ሞት በሰው ሁልጊዜም ካለ፣ አሳቡ ለአሁኑ ሕይወት መታለሎች የተጣበቀ ኾኖ እንደማይቀር አልያም የሰይጣን ማታለሎች ሰውን ሊቀርቡት እንደማይችሉ ያውቃል፡፡"
#ማር_ይስሐቅ_ሶርያዊ

❤4👍2
"በየዕለቱ ከአምላኬ ጋር የማወጋው ነገር አለኝና ያለማቋረጥ ከቀን ውሎዬ ውስጥ ሰርቄ ከልጅነት እስከ እርግናዬ ድረስ በተመስጦ ኖርኹ"
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
@getseseb
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
@getseseb
👍4🔥2
✢መጀመሪያ የሌለው እግዚአብሔር መጀመሪያ ላላቸው ችግሮቻችን ኹሉ መፍትሔ ነው።✢
አንድ ሰው ሱሰኛ ቢኾን ሱስ የጀመረበት የመጀመሪያ ዕለትና አጋጣሚ አለው። ይኽ ብቻ አይደለም። ሱስ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት የኾነው ሰውና በሱስ ወጥመድ ያጠመደችው ዕፅም ትኹን መጠጥ፥ ማየትም ትኹን መስማት፥ ማሰብም ትኹን መዳሰስ ...... ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጋት የተጠቀማት ያቺ መጀመሪያ አላት።
እስኪ በዝምታ ኾነን፤ ዕያወቀን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት አርግዘናቸው ልንገላገላቸው ያልቻልናቸው ችግሮቻችንን ስህተቶቻችንን በአጠቃላይ ወደ መልካም ልንቀይራቸው የምንፈልጋቸውን ጠባዮቻችንን ሥራዎቻችንን ለአፍታ ልብ እንበላቸው እናስተውላቸው። ኹሉም መነሻ አላቸው። መድረሻም አላቸው። ኹሉም አድራሻቸው ይታወቃል።
አድራሻው የሚታወቅ ወንጀለኛ ከፖሊስ አያመልጥም። የትም ይኹን፤ አድራሻው እስከታወቀ ድረስ በቁጥጥር ስር መዋሉ አይጠረጠርም።
ተወዳጆች እግዚአብሔር የእያንዳንዳችንን የኃጢአቶቻችንን አድራሻ ያውቃል። ምን ቀን፣ በምን ምክንያት፣ እንዴት ኀጢአት ውስጥ እንደተዘፈቅን ያውቃል።
የኀጢአቶቻችንን መነሻ ምክንያት ጠንቅቆ ያውቃል።
ተወዳጆች እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው። ማንኛውም ፍጥረት በእግዚአብሔር ከመፈጠሩ በፊት ህልውና አልነበረውም። ስለዚህ በሚታየውም በማይታየውም ዓለም ውስጥ የሚኖር ኹሉ ከእግዚአብሔር በታች ነው። እኛም ኀጢአቶቻችንም ጭምር።
እውነት ነው ኀጢአትን እግዚአብሔር አልፈጠራትም። ሰው ዕፀ በለስ በልቶ አመጣት እንጂ። ኀጢአት የእኛ ያለመታዘዝ የሥራችን ውጤት ናት። ስለዚህ እኛ ከእግዚአብሔር በታች ከኾንን ኀጢአትም ከእግዚአብሔር በታች ናት። ይኽ ብቻ አይደለም። ኀጢአት ከእኛም በታች ናት።
ችግሩ "ለሰይጣን አትስጠው ሥልጣን" እንደተባለ በገዛ እጃችን በራሳችን ላይ አነገሥናት እንጂ ከእኛ አትበልጥም።
"ለሰማይ ምሰሶ የለው ለባዕድ ሥር የለው" ነው ነገሩ።
እኛ ግን በተለያየ ምክንያት ሥልጣን ስለሰጠናቸው ኀጢአቶቻችን እንደ ጥቅምት ብርድ እጅና እግራችንን አሳስረው አስቀመጡን። ስለዚህ ተስፋ የሚባል ነገር ማየት አልቻልንም።
መፍትሔው ግን አንድ ነው። መጀመሪያ የሌለው እግዚአብሔር መጀመሪያ ላላቸው ችግሮቻችን ኹሉ መፍትሔ ነው። ሐኪሙ እርሱ ነው። መድኃኒቱም ራሱ ነው።
ለሐኪም ይነግሩታል። እስኪ በጣም ታመን ሐኪም ቤት የሄድንበትን ጊዜ እናስታውስ። የቱ ጋር እንደሚያመን፣ እንዴት እንዳመመን፣ ከመቼ ጀምሮ የሕመም ስሜት እንደተሰማን ቅልስልስልስ እያልን "ዶክተርዬ" ብለን እያቆላመጥን መሬት ኾነን በታላቅ ትሕትናና ልመና ይፈውሰንም አይፈውሰንም ምንም ማረጋገጫ በሌለን.... ምድራዊ ሐኪምን እንደሚያድነን አምነን ሕመማችንን እንናገራለን።
ምነው ታዲያ እግዚአብሔርን በብስጭት እንናገረዋለን? ምነው ታዲያ በጥርጣሬ እንለምነዋለን? ምነው ታዲያ የሚያዝልንን የነፍስ መድኃኒቶች ጾም፣ ጸሎት፣ ንስሐ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ እንስታጉላለን? የታይፎድ መድኃኒት አይቋረጥም እያልን የምንሽቆጠቆጥ እኛ ለነፍሳችን መድኃኒት ምነው ፊት ነሣነው!
አሁን ላለንበት የመከራ ሕይወት እግዚአብሔር ተጠያቂ አይደለም። አንድ ታማሚ ሐኪሙ ያዘዘውን መድኃኒት ሳይወስድ ሐኪሙ አላዳነኝም ማለት አይችልም። መጀመሪያ እግዚአብሔር ጋር አቀራረባችንን እናስተካክለው። ልመናችን በትሕትና ይኹና። ከዚያ የታዘዘልንን መድኃኒት በሰዓቱ እንውሰድ። ያለጥርጥር መጀመሪያ ያላቸው ኀጢቶቻችን መጀመሪያ በሌለው ፈጣሪያችን ይቅር ይባላሉ።

❤2🥰2👏2🔥1🎉1🤩1
✢ፎርሜሽናችንን እናስተካክል✢
በእግር ኳሱ ዓለም በአንድ ቡድን ዐሥራ አንድ ተጨዋቾች ቢጫወቱም በዓለማችን የምናውቃቸው ታላላቅ የሚባሉ የእግር ኳስ ተጨዋቾች ያሉባቸው ቡድኖች ግን ተጋጣሚያቸውን ኹል ጊዜ እንዳሰጉ ነው።
ለአንዱ፤ ለዚያ ጎበዝ ለተባለው ተጨዋች ሲባል የቡድኑ አሰላለፍ (formation) ይቀየራል። ይስተካከላል። ምክንያቱም የጎበዙ ተጨዋች መኖር ለቡድኑ አሸናፊነት አስፈላጊ ስለኾነ። ማንም ይኽንን አይቃወምም።
የሚገርመው ግን ኳስ ተጨዋቹን ያመነውን ያኽል እንኳ በሕይወታችን ሰልፍ ላይ እግዚአብሔርን አለማመናችን ነው። በኑሯችን ስንትና ስንት ግጥሚያ ነው ያለብን? ስንትና ስንት የውድድር ሜዳዎች ነው የሚያጋጥሙን? በእሊኽ ኹሉ የሕይወት ግጥሚያዎቻችን የእግዚአብሔር መኖር አስፈላጊ ነው። በሕይወት ጨዋታ የጨዋታ ብልጫም አሸናፊነትም የምናገኘው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሲኾን ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሲኾን የኳስ ቁጥጥራችን ይጨምራል። ኳሱን ከመረቡ በቀላሉ ማገናኘት ያስችለናል።
ጥያቄው እኛ ለእግዚአብሔር የሚመች አሰላለፍ ተሰልፈናል ወይ ነው?
ድል እንፈልጋለን የድል ፎርሜሽን ግን አልሰራንም።
የምንውልበት ቦታ፣ የምንመለከታቸው ነገሮች፣ የምንሰማቸው ድምፆች፣ የምናስባቸው ሀሳቦች፣ የምናደርጋቸው ድርጊቶች እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳይሰለፍና እንዳይረዳን የሚያደርጉ ስለኾኑ መደሰት የለ፥ ዕረፍት የለ፥ ሰላም የለ፥ ተስፋ የለ፥ እንዲኹ ስንጨነቅ አሸናፊነትን እንደናፈቅን መሽቶ ይነጋል።
ማሸነፍ ከኾነ የምንፈልገው የኀጢአት፣ የዕንቅልፍ፣ የስንፍና ፎርሜሽናችንን ወደ ጽድቅ፣ ወደ ጸሎት፣ ወደ ንባብ፣ ወደ ጾም፣ ወደ ንስሐ ፎርሜሽን እንቀየር ፤ ለእግዚአብሔር የሚመች አሰላለፍ እንሰለፍ።
ያን ጊዜ የጨዋታ ብልጫውም፣ ግቡም፣ ኮከብ ጎል አግቢነቱም፣ ዋንጫውም የእኛው ይኾናል።
፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡..፡

❤3🥰2👏1
✢ወይ ካለው ተወለድ ወይ ካለው ተጠጋ✢
የድሃ ምሬት እንዲህ ነው፤"ወይ ካለው ተወለድ ወይ ካለው ተጠጋ"።
ሀብታም የመኾን ጥሙ የሚቆርጥለት ከሀብታም በመወለድ አልያም ከሀብታም በመጠጋት እንደኾነ ስለሚያስብ።
ሰው የደኸየበትን ነገር ይፈልጋል። በገንዘብ ከኾነ የደኸየው ገንዘብ ይፈልጋል።
አሁን እኛ የደኸየንበት ነገር ምንድን ነው? የምንፈልገው ሀብት ምንድን ነው?
ገንዘብ ነው? ሰላም ነው? ከሱስ መውጣት ነው? እውነተኛ ወዳጅ ነው? ቤት ነው? ንብረት ነው? ዕውቀት ነው? ጥበብ ነው? ምንድን ነው የምንፈልገው?
እኛ እኮ ካለው ተወልደናል። በዐርባ እና በሰማንያ ቀናችን ኹሉ የእርሱ ከኾነ ከባለጸጋው ከእግዚአብሔር በጥምቀት ተወልደናል። የአባታችን የኾነ ኹሉ የእኛ ነው።
ባለጸግነት ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ነው።
ሰላም በማን ነው? በእግዚአብሔር ነው።
ችግሮችን የመቋቋምና የማሸነፍ ኀይል ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ነው።
ያለጥርጥር ኹሉን መቻል ኀይልን በሚሰጠን በእግዚአብሔር ነው።
ታዲያ ለምንድን ነው በሥጋም፣ በነፍስም፣ በመንፈስም የደኸየነው?
የወለደንን እግዚአብሔር ተወልደን ስለራቅነው ነው። በጸጋ ልጆቹ ነን ግን እንደአባት አልቀረብነውም።
ልጆች ሳለን ልብስ ቢያስፈልገን አባታችንን "ልብስ ካልገዛህ" ብለን ግድ እንለዋለን። ልብሱን እስኪገዛልን ድረስ በጩኸትም በዕንባም በመለማመጥም ዕረፍት እንነሣዋለን። ልመናችንን የምናቆመው ልብሱን የገዛ ዕለት ነው።
እግዚአብሔር አባታችን ነው ካለን፤ አሁን አልፋታ ብሎ የተጋባንን ክፉ ሥራችንን ለምን ያኽል ጊዜ እንዲያስወግድልን ለምንነው? እንዴት ባለጩኸት ጠራነው? እንዴትስ ብለን በዕንባ ተማጸንነው?
ሊቁ አምብሮስ እንዲህ ይላል "ዕንባ ይቀበላል እንጂ አይለምንም"
አባታችን እግዚአብሔር ከገባንበት የኀጢአት ሱስ እስኪያወጣን ድረስ በዕንባ ጩኸት እንጠጋው። በምስጋና እንጠጋው።
መቼም አባት ነው በደስታችን ጊዜም በምስጋና እንጠጋው።
ካለው ከእግዚአብሔር ተወልደናል ካለው ከአባታችን ከእግዚአብሔር መጠጋት ይቀረናል።
በዕንባ በምስጋና እንጠጋው።

❤4🔥1
✢እግዚአብሔር በእኛ አይለካም✢
አንድን ወታደር "ልጅህ ፈሪ ነው? ደፋር?" ተብሎ ቢጠየቅ " እንዴ የኔ ልጅማ ወንዱ አንበሳው" ብለው ይመልሳል። ምክንያቱም ልጁን በልጁ አቅም ሳይኾን በራሱ ዐይን ስላየው ነው። ልጁ እኮ ዕልም ያለ ፈሪ ሊኾን ይችላል። ግን የእርሱ ጀግንነት በዘር ወደ ልጁ እንደሄደ ስለሚያስብ የልጁን ፈሪነት ለመቀበል ይቸግረዋል።
እንዲህ ያለ አመለካከት ሳናውቀው እግዚአብሔርንም በእኛው ልክ የመለካትና የማየት በሽታ አምጥቶብናል። ይኽ በጣም አደገኛ ነገር ነው።
አንዳንዶቻችን የኾነ ነገር የማይሳካ ወይም የተበላሸ፣ያለቀለት፣ የደቀቀለት ሲመስለን " እንግዲህማ ምን አዲስ ነገር ይመጣል? እግዚአብሔር ረስቶኛል። አሁንማ ረፍዷል።" እንላለን።
ይኽንን ስንል ቅንጣት እንኳ ኀፍረትም ፍርሃትም አይሰማንም።
ለእግዚአብሔር ረፍዷል ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር አርፍዷልስ ትርጉሙ ምንድን ነው?
እኛ ተጋድመን ቅዳሴ እንደሚረፍድብን እግዚአብሔር የሚያረፍድ ነው እንዴ የሚመስለን?
ቆይ ምን ለማለት ፈልገን ነው?
በቦታ እንኳ ካየነው አንድ ሰው የሚያረፍደው በተመሳሳይ ሰዓት በአንድ ቦታ መገኘት ባለመቻሉ ምክንያት ካለበት ቦታ ወደሌላኛው ቦታ በሚሄድበት ጊዜ ነው።
እና እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ አለና ነው የሚያረፍደው? ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የኾኑለትን አምላክ ነው በመከራችን ቦታ የለኽም የምንለው?
ማርፈድ እኮ ከጊዜ በኋላ ለተፈጠሩ በጊዜ ውስጥ ለሚኖሩ ለፍጡራን የሚቀጽል ነው። ታዲያ ጊዜን የፈጠረውን አባታችንን ነው አርፍደሃል የምንለው?
እግዚአብሔር አይዘገይም። አይቀርምም። የሚሰራበት የራሱ የኾነ ጊዜ አለው።
ያለጊዜዋ የተቀጠፈች ፍሬ ኹሉ ትመራለች። ሕመምም ትኾናለች። የእግዚአብሔርን ጊዜ ሳትጠብቅ የምትሰራ ስራ ኹሉ ትጠፋለች። ታጠፋለችም።
የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ጊዜ እንጠብቅ።

👍4🔥1