ገጸ ሰብእ
427 subscribers
105 photos
1 file
232 links
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
Download Telegram
መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡

መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

“እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ”
የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
"ራስህን ከቤተክርስቲያን ፈጽሞ አትለይ። የትኛውም ተቋም የቤተክርስቲያንን ያህል ሥልጣን የለውም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን ድኅነትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መጠጊያህ ናት።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/getseseb
6
ገጸ ሰብእ pinned «"ራስህን ከቤተክርስቲያን ፈጽሞ አትለይ። የትኛውም ተቋም የቤተክርስቲያንን ያህል ሥልጣን የለውም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን ድኅነትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መጠጊያህ ናት።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ https://t.me/getseseb»
አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቆአልና፤
ከሰው ልጆችም መተማመን ጎድሎአልና፤
እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤
በሽንገላ ከንፈር ኹለት ልብ ኾነው ይናገራሉ።"
መዝ ፲፩፥፩-፪
@getseseb
😢3
🥰12
ለኢትዮጵያ ያድርገው

(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕ. 37)
----------
1፤ የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ።

2፤ በእነርሱም አንጻር በዙሪያቸው አሳለፈኝ፤ እነሆም፥ በሸለቆው ፊት እጅግ ብዙ ነበሩ፥ እነሆም፥ እጅግ ደርቀው ነበር።

3፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ። እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁ።

4፤ እርሱም እንዲህ አለኝ። በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው። እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።

5፤ ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ትንፋሽን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ።

6፤ ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

7፤ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፤ ስናገርም ድምፅ ሆነ፥ እነሆም፥ መናወጥ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ።

8፤ እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ትንፋሽ ግን አልነበረባቸውም።

9፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው በል አለኝ።

10፤ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።

11፤ እርሱም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ። አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።

12፤ ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ።

13፤ ሕዝቤ ሆይ፥ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

14፤ መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ እንዳደረግሁም ታውቃላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ለኢትዮጵያ
አንድ ሰው

https://t.me/getseseb
👍21
ለምንድን ነው ግን እግዚአብሔር አዲስ ዓመት የሰጠን? ለምን እስትንፋሳችን ቀጥ አላለም? ነገን ለማየት የሚያስችል ምን ንጹሕ ማንነት አለን? ተኝተን ስንነቃ መስከረም አንድ ለምን ኾነ? አዲስ ዓመት ለምን ተባለ? ምክንያት ምክንያት ምክንያቱ ምንድን ነው? ከዚኽ ቀደም በተሰጡን ዓመታት ያለሰራናቸውን መልካም ነገሮች፤ ያልኖርነው የንጽሕና ሕይወት እንኖር ዘንድ የሚያስችል ዕድል አይደለምን?

ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!

ሳሙኤል በላቸው (ዲ/ን)
Join👉 @getseseb
https://t.me/getseseb
8👍2🔥2
ትናንት አልፎ ዛሬ ተሰጥቶናል። ነገ ግን ትናንትን ባሳለፈን ዛሬን በሰጠን በአምላካችን እጅ ላይ ናት። ስለዚህ ልንሰራ የምንችለው ዛሬን ነው። የዛሬ ስራችን ግን በአምላካችን ቸርነት ለሚሰጠን ነገ ትልቅ ጥቅም ነው።
ዛሬ የንስሐ ቀን ተሰጥቶናል፤ በመንፈሳዊ ሕይወታችንም በሥጋዊ ሕይወታችንም የሰራናቸውን ስህተቶችና ያልሰራናቸውን መልካም ነገሮች የምናድስበት።
ትናንት ያበላሸነውን አእምሯችንን፤ ያላጠራነውን አመለካከታችንን፤ ያላነጻነውን ሀሳባችንን ዛሬ እናክመውና ነገን በተስፋ እንጠባበቅ።

ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!

ሳሙኤል በላቸው | ዲያቆን
@getseseb
#share
6🔥1
"ተስፋ አትቁረጪ፡፡ ኦሎምፒያስ ሆይ ! እውነተኛውና እጅግ ክፉው ነገር አንድ ብቻ ነው፤ እውነተኛ ፈተና አንድና አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ኃጢአት ነው፡፡ እንዲህ ብዬ አሰምቼ መንገሬንም መቼም መች አላቋርጥም፡፡

ሌሎች ነገሮች ግን - ለምሳሌ ሴራዎች፣ ጥላቻዎች፣ ማጭበርበሮች፣ ሐሜቶች፣ ስድቦች፣ ወቀሳዎች፣ የራስ ያልኾነን ነገር የእኔ ነው ብሎ መያዝ፣ ስደት፣ ስል የኾነ የጠላት ጎራዴ፣ የጉድጓድ ውስጥ የኾኑ አደጋዎች፣ ከዓለም ኹሉ የሚመጣ ውጊያ፣ እንዲሁም አንቺ ልትጠሪው የምትችዪ ሌላም ኹሉ ነገር - እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም፡፡

የእነዚህ ነገሮች ክብደታቸው ምንም ይኹን ምን ሐላፊያን ናቸው፤ የሚጠፉ ናቸው፤ ሟች ሰውነታችንን ሊጎዱ ቢችሉም እንኳን መንፈሳዊው ማንንታችንን ግን ምንም ሊያደርጉ የማይችሉ ናቸው፡፡

ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስም ከዚህ ዓለም ሕይወት ጋር ተያይዘው የሚገኙ ደስታዎችም ኾኑ ኀዘኖች ምናምንቴነትን ሊናገር ወድዶ እውነቱን በአንዲት አረፍተ ነገር ገልጦታል፤ እንዲህ ሲል፡-“የሚታዩ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸውና” /2ኛ ቆሮ.4፥18/፡፡

ታዲያ እንደ ፈሳሽ ውኃ የሚያልፉ ጊዜያዊ ነገሮችን የምትፈሪው ስለ ምንድን ነው?

ወደ ኦሎምፒያስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
7👍1😢1
Forwarded from 🎚የዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት መወያያ🎚
"እነሆ የአብነት ጊዜ ደረሰ"
ልዩ የትምህርት ዕድል ለወጣቶች
ይደውሉ ይመዝገቡ
096567318ዐ / 0939019363
👍42
Forwarded from Yordanos
የእምነት ሕይወት
በገበያ ላይ

የብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የምንጊዜም ወርቃማ
ብሒሎች

፩. የንስሀ አባት ማለት እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት ሰው ማለት ነው፡፡

፪. ኃጢአት ከበጎ ነገር በተቃራኒ መስራት ብቻ አይደለም። በጎውን አውቆ አለመስራትም ኃጢአት ነው።

፫. ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃሜውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ፡፡

፬. ሊቅ በሊቅነቱ ቢያስተምርህ ሊቅ ትሆናለህ ሊቅ በሕይወቱ ቢያስተምርህ ግን ክርስቲያን ትሆናለህ።

፭. አንተ ሐሳብህን ልትመራው እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን እንዲመራህ ቦታ አትስጠው፥ እውነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚመራ ነዉ።

፮. ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።

፯. በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።

ከመጽሐፉ የተወሰደ
አዘጋጅ:- ዲ/ን ዮርዳኖስ ፍሬው
አሳታሚና አከፋፋይ:- ሀሁ መጻሕፍት መደብር
ስልክ:- 0911006705
🙏3
እጮኛሞች "በሐዘንም በደስታም አንለያይም!" ማለት ወጋቸው ነው። እናትም ልጇን ስትልክ "ጎሽ የኔ ልጅ እንዳትፈራ!" ብላ ለልጇ ድፍረትንና ተስፋን መስጠት ልማዷ ነው።
ኹሉም በያለበት የደኅንነት ቃል ይገባል። ግን በሐዘን የተለያዩ እጮኛሞችም፤ ልጇን ልካ መኪና ሲበላባት ያልሰማች እናትም እናውቃለን። በመከራህ ቀን የወዳጆችህ የ"እረዳሃለሁ"፣ የ"ከጎንህ ነኝ" ቃል ሊታጠፍ ይችላል።
የማይታበል ቃል ግን እዚህ አለ፤ የማይጠፋ ኪዳን ግን በዚህ አለ " በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።"
(መዝሙረ ዳዊት 50:15)

ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው

https://t.me/deaconsamuelbelachew
👍5🥰1
ሰው ወደ ናፍቆቱ ይሳባል። ሰው ለናፍቆቱ ዋጋ ይከፍላል። ሰው ከናፍቆቱ ጋር ጊዜ ያጠፋል።
እንዲያስታውሷችሁ የምትፈልጓቸው ሰዎች እያስታወሷችሁ ካልኾነ ከእናንተ አንድ ነገር ጎድሎ ይኾናል።
እንዲወዷችሁ የምትፈልጓቸው ሰዎች እየወደዷችሁ ካልኾነ አንድ ነገር ጎድሎአችሁ ይኾናል።
እርሱም
በሕይወታችሁ ሰዎች ከእናንተ የሚናፍቁት የሚስማማቸው ምን ነገር አላችሁ? እናንተን እንዲያስታውሱ እንዲወዱ  የሚያደርጋቸው መልካም ነገር ምንድን ነው?
ይህን ጥያቄ መመለስ ካልቻልን ከሰዎች ጋር አብሮ መቀጠል በጣም ከባድ ይኾናል።
ነገር ግን መልካም ነገር ኖሮአችሁ አላስታውስ ካልዋችሁ በቃ ተዉአቸው ወይ እናንተ ለእነርሱ ወይ እነርሱ ለእናንተ የተገቡ አይደሉም ማለት ነው። ወደሚገቧችሁና ወደምትገቧቸው ሂዱ።
ጌታችን ኢየሱስም ያደረገው ይህንን ነው።
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1:11 እንዲህ ተጽፏል "የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤"

ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው

#share
https://t.me/deaconsamuelbelachew
8👍2
ዘወትር እሑድ በአካል በገዳማችን በመገኘት ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ይማሩ !