ኃጢአት ለመስራት የጨከነ ልብ ጽድቅን ለመስራት ለምን ይፈራል? ኃጢአትን ለማድረግ የሚያወጣ የሚያወርድ አእምሮ ጽድቅን ስለመስራት ማሰብን ለምን ይታክታል? አስቦ ኃጢአት ሰርቶ ሳያስቡ ጽድቅ መስራት እንደምን ያለ ነው? ስለዚህ ጽድቅ ስለመሥራት ዕለት ዕለት ማሰብ አለብን።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍4🥰3
"አባት ላም ይሰጣል፤ ልጅ አጓት ይነሳል።"
በብዙዎቻችን የሕይወት መስመር ውስጥ የሚጸጽተንና ተመልሰን ዕድሉን ብናገኝ እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል የምናስባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ልጅ እያለን እናታችን ስታዘን እያኮረፍንና እየተኮሳተርን "ገረድ መሰልኩሽ እንዴ" እያልን ትእዛዟን ተላልፈናል። ዛሬ ላይ ኾነን ግን ልጅ ወልዶ ያየው ይቅርና ለእናት ገረድነት የሚያንስባት እንደኾነ ያልወለደም ያውቀዋል።
ያ እርሷን በማበሳጨት ያሳለፍናቸው እድሜዎች ዛሬ ላይ እናታችንን ሕመም ላይ እንደጣላት ስናይ የፈሰሰውን ውሃ ለማፈስ እንታትራለን። በእርግጥ አሁንም ከገባን የፈሰሰውን ማፈሱ ጥቅም አለው። ሌላ ብስጭት ፈሶ ሌላ ሕመም በእናታችን አይጨመርምና።
ከአባታችን አብራክ በመከፈላችን ከእናታችን ማኅጸን በመውጣታችን ምክንያት ቆሻሻችንን ሲያጸዱ፣ ክብር እየነፈግናቸው ለእኛ እና ስለእኛ ደፋ ቀና ሲሉ እያየን የርኅራኄ ጠብታ በልቡናችን ያለመንጠቡ ያሳዝናል።
የኹላችን አባትና እናት እግዚአብሔርስ ለእኛ ከምድራውያን እናትና አባት በላይ ያላደረገልን ምን አለ? ከመላእክት አልቆ ፈጥሮናል። በአርአያውና በአምሳሉ አበጅቶናል። ከፍጥረታት ኹሉ እኛን "እጅግ መልካም ፍጥረት" አደረገን። የምናስብ፣ የምንናገር፣ የምንኖር (ሕያዋን) አደረገን። አጓት ምስጋናን በልቡናችን አስበን በአንደበታችን እንድንናገር የበቃን ፍጥረቱ አደረገን። ታዲያ ለምንድን ነው እስከዛሬ አጓት ምስጋናን ያላቀረብንለት? እርሱ እኮ የሚቃጠል መሥዋዕትን ሳይሆን የተሰበረ መንፈስን ይወዳል።
የተሰበረ መንፈስ ምንድን ነው? በትሕትና፣ በፍቅር በምስጋና የተሞላ ልቡና ነው። እርሱ እግዚአብሔር ትሑታንን ይወዳል። ትሑታንም ለእርሱ ለእግዚአብሔር ሳያቋርጡ የምስጋና መስዋዕት ይሰዉለታል። ይህም የተፈጠሩበት ዓለማ ነውና ሳይዘነጉና ሳይታክቱ ስባሔ ያቀርቡለታል። ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነውና የተፈጠርነው።
ስለዚህ ተወዳጆች ላሙን ለሰጠን አባት አጓትን አንንሳው። አናመሰግነው ዘንድ ያጎደለብን አንዳች ነገር የለምና።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
መስከረም ፳ ፳፻፲፭
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#share

👏3
ውዳሴ ማርያም የሚጸልይና የማይጸልይ
የእመቤታችንን ውዳሴ ማርያም የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በየዕለቱ የሚጸልይ ሰው የእናት አባቱን ርስት የወረሰ ይመስላል።
የሰባቱን ዕለት ውዳሴ ማርያም በእድሜዋ ልክ በየዕለቱ የሚጸልይ ደግሞ የዘመዶቹን ጨምሮ የወረሰ ይመስላል።
እመቤታችንን ሳያመሰግን የሚውል ሰው ምን ይመስላል ቢሉ
ከሰው ቤት ድግስ ተጠርቶ ሂዶ በር ላይ ሲደርስ ውኃ ተደፍቶበት፥ ተቆጥቶ የሚመለስ፤ እንቅፋት እየመታው እየወደቀ እየተነሣ እየተሰበረ የሚሄድ ይመስላል።
ያ ሰው ካለመብላቱ በላይ እየተሰበረ እንደሄደ እመቤታችንን የማያመሰግንም በመከራ ሥጋ ላይ መከራ ነፍስ ይጸናበታል። በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ይጨመርበታል።
እኛ ግን፦ “አማንኬ ይደልወኪ አስተብፅዖ እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ -የከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ብፅዕት መባል በእውነት ይገባሻል" እንላታለን።
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
👇join👇

❤6👍3🔥1
ከዐውደ ምሕረቱ የምሕረት ወንጌል ከሚሰበክበት፤
ኹለት ካለህ መጽውት ወንጌሉ ቢልበት፤
ከዐውደ ምሕረቱ ስር ኹለት ሱሪ ያለው ሲሰማ ያ ድሃ፤
አንዱን ሱሪ ሰጥቶ ለሌላኛው ድሃ፤
ገነትን ወረሰ ኾነ ባለጸጋ ጠጣ የሕይወት ውሃ።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
መስከረም ፳፫ ፳፻፲፭ ዓም
https://t.me/getseseb
ኹለት ካለህ መጽውት ወንጌሉ ቢልበት፤
ከዐውደ ምሕረቱ ስር ኹለት ሱሪ ያለው ሲሰማ ያ ድሃ፤
አንዱን ሱሪ ሰጥቶ ለሌላኛው ድሃ፤
ገነትን ወረሰ ኾነ ባለጸጋ ጠጣ የሕይወት ውሃ።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
መስከረም ፳፫ ፳፻፲፭ ዓም
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
❤4
Watch "ሰአሊ ለነ ቅድስት|አዲስ ስብከት|New Ethiopian Orthodox Tewahdo Preaching 2021|Endalikachewu Neway|መ/ር እንዳልክ ንዋይ" on YouTube
https://youtu.be/13NcT_FwF7I
https://youtu.be/13NcT_FwF7I
YouTube
ሰአሊ ለነ ቅድስት|አዲስ ስብከት|New Ethiopian Orthodox Tewahdo Preaching 2021|Endalikachewu Neway|መ/ር እንዳልክ ንዋይ
❤2
"የመዳንሽ ቀን ዛሬ ነው። ልጄ አሁን ያለሽበት ሕይወት የጨለመ ነው። ጨለማን ደግሞ ከብርሃን ሌላ የሚያሸንፈው ኃይል ከቶ የለም። አሁን አንቺ ከብርሃን ፊት ቆመሻል። ወደ እርሷ ተመለሺ" አሉ መልሰው አንድ ሰው ብቻ በሚያስተኛው የቆርቆሮ ቤት ውስጥ ያሉት ሰው። በመካከላቸው ትንሽ ጸጥታ ኾነ። የሌሊቱ ነፋስ እንደበግ እረኛ የሚያፏጭ ይመስላል፤ ዛፎቹን በኃይሉ ያንገላታል።
"ድንግል ማርያም የዓለምን ብርሃን የወለደች እውነተኛ ብርሃን ናት። ወደ እርሷ የጨለመባቸው መጥተው ይበራላቸዋል። ወደእርሷ የተዳደፉት መጥተው ይነጻሉ እንጂ የተዳደፉትን አትጠየፍም። በማንኛውም ኃጢአት የቆሸሹ ሰዎችን አጥባ ንጹሐን ታደርጋቸዋለች። የሕይወት ውኃን የወለደች የሕይወት ውኃ ምንጭ ናትና። እርሷ ለሙት ልጆች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ኹሉ የመስቀል ስር ስጦታ እናት ናት። ወደ እርሷ ማን በሥልጣኑ ይቀርባል? እርሷ ለኹሉ በርኅራኄ የቀረበች ናት እንጂ። ኹልጊዜ የጠፉ ልጆቿን እጆቿን ዘርግታ ትፈልጋቸዋለች ትጠብቃቸዋለች። ለዓመታት ያነባሽው ዕንባ አዛኝቷን አስነብቷታል። ነፍስሽን አጥበሽ ወደ ልጇ ማኅበር ትገቢ ዘንድ ፍቃዷ ነው። ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለኹላችንም ጭምር እንጂ። እየሰማሽኝ ነው ልጄ?" አሉ እንደእርጎ በረጋው ድምጻቸው። ........
|የማርያማዊት ሌሊት ከሚለው ጽሑፍ የተቀነጨበ|
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
"ድንግል ማርያም የዓለምን ብርሃን የወለደች እውነተኛ ብርሃን ናት። ወደ እርሷ የጨለመባቸው መጥተው ይበራላቸዋል። ወደእርሷ የተዳደፉት መጥተው ይነጻሉ እንጂ የተዳደፉትን አትጠየፍም። በማንኛውም ኃጢአት የቆሸሹ ሰዎችን አጥባ ንጹሐን ታደርጋቸዋለች። የሕይወት ውኃን የወለደች የሕይወት ውኃ ምንጭ ናትና። እርሷ ለሙት ልጆች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ኹሉ የመስቀል ስር ስጦታ እናት ናት። ወደ እርሷ ማን በሥልጣኑ ይቀርባል? እርሷ ለኹሉ በርኅራኄ የቀረበች ናት እንጂ። ኹልጊዜ የጠፉ ልጆቿን እጆቿን ዘርግታ ትፈልጋቸዋለች ትጠብቃቸዋለች። ለዓመታት ያነባሽው ዕንባ አዛኝቷን አስነብቷታል። ነፍስሽን አጥበሽ ወደ ልጇ ማኅበር ትገቢ ዘንድ ፍቃዷ ነው። ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለኹላችንም ጭምር እንጂ። እየሰማሽኝ ነው ልጄ?" አሉ እንደእርጎ በረጋው ድምጻቸው። ........
|የማርያማዊት ሌሊት ከሚለው ጽሑፍ የተቀነጨበ|
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍5❤3
ሀ
ሀ ብሂል ሀልዎቱ ለእግዚአብሔር እምቅድም ዓለም። "ሀ" ማለት የእግዚአብሔር መኖር ከዓለም በፊት ነው። እርሱ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር ከማበጀቱ በፊት ነበረ። እርሱ እግዚአብሔር በደረታቸው የሚሳቡ በክንፋቸው የሚበሩ በእግራቸው የሚሽከረከሩ ፍጥረታትን ከመፍጠሩ በፊት ነበረ። እርሱ እግዚአብሔር ሰው ዘመናትን ይቆጥርባቸው ዘንድ ከፈጠራቸው ከፀሐይ ከጨረቃ ከከዋክብት አስቀድሞ ነበረ። ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብትንም ሳይፈጥር ያመሽና ያነጋም ነበረ። እርሱ እግዚአብሔር አዝርዕትን አትክልትን ዕፅዋትን በምድር ላይ እንዲበቅሉ ከማዘዙ በፊት ነበረ። እርሱ እግዚአብሔር ውሃን ከሦስት ከፍሎ ጠፈረን ከመፍጠሩ በምድር ላይ አብሕርትን ከማደላደሉ በፊት ነበረ። እርሱ እግዚአብሔር "ብርሃን ይኹን" ብሎ ብርሃንን ከመፍጠሩ በፊት ነበረ። እርሱ እግዚአብሔር ሰማይን ያለምሰሶ ምድርን ያለመሠረት ከማጽናቱ በፊት ነበረ።
ኹሉን በጥበቡ ፈጠረ። እርሱ ከኹሉም ነገር በላይ ኹሉም ነው። በእርሱ ፊቱ ኹሉም ነገር ምንም ነው።
ኹሉን ያስገኘ እግዚአብሔርን ይዘን ኹሉን የምናጣበት ምክንያት ምንድን ነው? በእርግጥም ኹሉን የያዘውን አልያዝነውም። ስለዚህ በማጣት (በኃጢአት) ውስጥ እንኖራለን። ችግሮች ኹሉ ከላይ ኾነው ሲኮረኩሙን እንጂ ከችግሮች በላይ ኾነን ከኖርን ስንት ዘመናት አልፈዋል?
እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው። ዘለዓለማዊነት የባሕርይው ነው። በእርሱ ዘለዓለማዊነት በእርሱ ምሉዕነት ውስጥ ውስንነት የለም። ስለዚህ አባ አባት የምንልበትን የልጅነት ጸጋ ሰጥቶናልና አምነን በጸሎት እንለምነው። አምነን በጸሎት የምንለምነውን ይሰጠናልና።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
መስከረም ፳፱ ፳፻፲፭ ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#share #like
"ወአንቢበክሙ አንትሙ ለዘኢያንበበ አይድኡ እናንተ አንብባችሁ ላላነበበው ንገሩ"
ቴሌግራም፦ https://t.me/getseseb
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100086220856701

❤4👍4🥰1
ያልመለስነው ጥያቄ
መድረሻውን ለማያውቅ መንገደኛ ስለመድረሻው ቢነግሩት አይሰማም። ለዚህ ነው "ይቅር ካላልህ ገነትም ይቅርብህ" የሚለውን የቅዱስ ኤፍሬም አረጋዊን ቃል ሲሰማ ይቅርብኛ የሚለው። ምናልባት ይህንን ስንሰማ "ያመዋል እንዴ? እንዴት ገነት ይቅርብኝ ይላል?" እንል ይሆናል። በእርግጥም በአንደበታችን አልተናገርነው ይኾናል እንጂ "ገነት ይቅርብኝ" ካልን ሰነባብተናል።
ገነት ምንድን ናት? መገኛዋ ወዴት ነው? በገነት ውስጥ ምን አለ? ምን የተሻለ ነገር አለ? ይህንን ጥያቄ ያለመለሰ ሰው እየኖርኩ ነው ቢል መድረሻውን ከማያውቅ መንገደኛ የባሰ ከንቱ ለመኾኑ ጥርጥር የለውም።
አንድ ሯጭ ምን ያኽል ሜትር እና በምን ምክንያት እንደሚሮጥ አስቀድሞ ያውቃል። ስለዚህም እንዴት መሮጥ እንዳለበት በትጋት ተራራውን እየወጣ ቁልቁለቱን እየወረደ፣ ኮረኮንቹን እየረጋገጠ፣ ላብ እንደዝናም እያበሰበሰው፣ ሳንባውን በአፉ እስኪተፋ ድረስ እየደከመው፣ ልቡ እንደቡሄ ጅራፍ እየጮኸች ይለማመዳል።
ይህን የሚያደርገው ጥያቄዎቹን ስለመለሰ ነው። የሚሮጠው ለምን፣ እንዴት፣ እስከ የት የሚለውን ተረድቷል። መንፈሳዊ ሕይወትም እንዲሁ ነው። እኛ ግን ያልመለስነው ጥያቄ ስላለን ተጋድሎአችን እንደድር ሳስቶ በቀላሉ ይበጠሳል።
ለመኾኑ ገነት ምንድን ናት? መገኛዋ ወዴት ነው? በገነት ውስጥ ምን አለ? ምን የተሻለ ነገር አለ?
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
መስከረም ፴ ፳፻፲፭ ዓም

👏3👍2❤1🔥1
ብትሰጠኝ ኖሮ
ትናንት አራት ኪሎ አካባቢ ካለ አንድ ፎቶ ቤት ጉርድ ፎቶ ለመነሣት ሄድኩ። ወደ ቤቱ ዘልቄ ከፊት ያለውን ደረጃ ወጣሁና ፎቶ ከሚያነሳው ቀይ ወጣት ጋር ተገናኘኹ።
"ጉርድ ነው?" አለኝ
"አዎ አራት በአራት (4×4)" አልኩት።
ሁለት ሴቶች ሊነሱ ይሁን ሰራተኞች ይሁኑ ባላውቅም ነበሩ። "አራት በአራት?" አሉ።
እኔም "አዎ አራት በአራት" ብዬ መለስኩ። በውስጤ አራት በአራት የሚባል የለም እንዴ አልኩኝ።
"አስቸኳይ ነው?" ልጁ ነው።
"አይ አይደለም....... ኖርማል ነው.... መቼ ይደርሳል"
" እ ነገ ጠዋት ሁለት ሰዓት ይደርስልሀል። መጥተህ መውሰድ ትችላለህ"
ሁለት ጊዜ በካሜራው ቀጭ ቀጭ አደረገና ገጼን ወሰደ። ደረሰኜን ተቀብዬ ወደ ቤቴ ሄድኩ።
መሽቶ ነጋ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከአርባ አምስት ሲል ፎቶ ቤት ደረስኩ።
" እንዴት አደራችሁ"
"እግዚአብሔር ይመስገን።"
"ፎቶ" ብዬ ደረሰኜን ሰጠኋቸው።
"ጉርድ ነው?"
"አዎ"
አንዲት ሴት መጣችና ደረሰኙን አየት አድርጋ ፎቶዬን ሰጠችኝ።
" ይሄ አራት በአራት ነው?"
"አይ ሦስት በአራት"
"እኔ እኮ አራት በአራት ነው ያዘዝኩት"
"እናንተ በትክክል አታዳምጡም ነበር" አለችና "ምን ያደርግልሀል" አለችኝ።
"ልመዘገብበት"
" እና ሦስት በአራት እኮ ነው ታዲያ መመዝገቢያ"
" የታዘዝኩት አራት በአራት ወይም ፓስፖርት ሳይዝ ተብዬ ነው" አልኩአት።
"ምንም ልዩነት የለውም እኮ ደግሞ የሚሻለው ይሄ ነው። አራት በአራቱ ትንሽ ወደ ጎን ሾጠጥ ይልብሀል። ወይም ሁለት በአራት ይሁንልህ እሱም ግን ወደ ታች ረዘም ይላል"
የምትለው ሊገባኝ አልቻለም። የምፈልገውን ለምን እንደፈለግሁት እኔ ባውቅም የማልፈልገውን እንድፈልገው እያወራች ነው። ዝም ብዬ እየሰማኋት ነው።
" አራት በአራቱን እንሰራልሀለን። ይህ ለሌላ ጊዜ እንዲጠቅምህ ዐሥራ አምስት ብር ክፈልና ውሰደው።" አለችኝ።
ምንም መልስ አልሰጠኋትም። ትናንት ሠላሳ ብር የከፈልኩ ቢሆንም ዐሥራ አምስት ብር ጨምሬ መውሰድ ብችልም ውስጤ ባልከፍላት ሦስት በአራት አድርጋ የሰራችውን ምን ልታደርገው ነው ብዬ ማሰብ ጀመርሁ።
እንደእውነቱ ከሆነ ፎቶውን መልሰው አይሰሩበትም። መጣል ወይም ማቃጠል ነው ያላቸው አማራጭ። በራሳቸው ስህተት ነው የከሰሩት ግን ኪሳራቸውን በእኔ ዐሥራ አምስት ብር ካላካካሱት ጥቅም ያገኙ አይመስላቸውም። ሳስበው በነጻ የተበላሸውን(ተሳስተው ሦስት በአራት አድርገው ያወጡትን) ፎቶ ለእኔ በመስጠትና ፎቶውን በመጣል መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
መልስ ሳልሰጣት ዝም ብዬ አየኋት። "በቃ ቁጭ በልና ጠብቀኝ አራት በአራት አድርጌ ላውጣልህ" አለችኝና ቁጭ አልኹ። ሀሳቤ ግን አሁንም ይሄዳል። ይጓዛል። ይጠይቃል።
ቆይ ትናንት ሠላሳ ብር ያስከፈሉኝን ፎቶ ዛሬ በዐሥራ አምስት ብር ውሰድ የምትለኝ ስለሚያዋጣት ነው? ወይስ ከከሰረ አይቀር ጥቂትም ቢሆን ያስገባ ብላ? እንደዛስ ቢሆን ለእኔ እንዲሁ ብትሰጠኝ ኪሳራው ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ እንደመጣል ከሆነ ለምን አልሰጠችኝም? እንዲሁ ፎቶውን ብትሰጠኝ ኖሮ ደግና ሩኅሩኅ እንደኾነች እንዳስብና በጎ ነገር ስላደረገችልኝ ሁልጊዜ እሷ ጋር ለመነሳት እንዳስብ ታደርገኝ ነበር።
ፎቶውን ብትሰጠኝ ኖሮ ቀድሜ የከፈልኳት ሠላሳ ብር እንዳለ ኾኖ ለበጎነቷ ተጨማሪ ዐሥራ አምስት ብሩንም ልሰጣት እችል ነበር።
አንዳንድ ሰው አላጋጠማችሁም? እርሱ ካልበላው ምግቡ መሬት ላይ ቢደፋ የሚመርጥ። እርሱ ካለበሰው ልብሱ ቢቀዳደድ ደስ የሚለው። ምግቡ በመደፋቱ ልብሱም በመቀደዱ የሚያገኘው አንዳች ጥቅም የለም። እንደውም ጥላቻን ስግብግብነት ይዘራል።
አንተ ጋር መጥቶ የማይጠቅምን ነገር ሌላው ጋር ሲሄድ ግን እጅግ አስፈላጊ የኾነን ነገር በደስታ የማትሰጥ ከኾነ አንተ በእርግጥም ስግብግብ ነህ ማለት ነው።
ባስ ውስጥ ወጣትና ጤነኛ ኾነህ ሳለ ቀድመህ ወንበር ስለያዝክ የሰባ ዓመት አዛውንት፣ እርጉዝ ሴት፣ የታመመ ሰው ቆሞ ሲሄድ እያየህ ከተመቸህና ቦታ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ካልሆንክ አንተ በእርግጥም አእምሮህን ያጣህ እብድ ነህ ማለት ነው።
የማይጠቅመንን ነገር ከሚጠቅማቸው ነፍገን ስንት ምርቃት አለፈን ስንት መርገምስ ደረሰን?
ለእኛ ኢምንት የኾነው ነገር ለሌላው ብዙኅ ሊኾን ይችላልና የምር ደግ እንሁን።
ዲያቆን ሳሙኤልበላቸው
ጥቅምት ፩ ፳፻፲፭ ዓም

❤9👍5🔥1
❖ነፍሳችሁን አሽትቷት❖
አንድ ሰው ሽንት ቤት ውስጥ ገብቶ ተጨማልቆ እንካ ውሃ ታጠብበት ሲሉት "ኤጭ ጀመረው ደግሞ..... እእእይ.... ተመልሼ እኮ እቆሽሻለሁ አልፈልግም" ይላል?
በፍጹም እንዲያውም ብዙ ውሃና መጥፎ ጠረኑን ደስ በሚያሰኝ መአዛ የሚቀይርለት ሳሙና እንዲሰጡት ይለምናል እንጂ።
ተወዳጆች ሆይ ኃጢአት ማለት ከሽንት ቤት ጽዳጅ በላይ የሚያቆሽሸንና የሚያገማን ነገር ነው።
ንስሐ ደግሞ ንጹሕ እና ጽዱ እንዲሁም ከናርዶስ ሽቱ በላይ እንድናውድ የሚያደርገን ውሃና ሳሙና ነው።
እናም ተወዳጆች ንስሐ እየገባን ነው? ከኾነ ንጹሕና የግሩም መአዛ ባለቤቶች ነን። ንስሐ እየገባን ካልኾነና ድጋሚ ስለምንበድል መንጻት አያስፈልገንም እያልን ከኾነ ግን ከሽንት ቤቱ በላይ ቆሻሾችና መጥፎ ሽታ የምንሸት መኾናችንን እንወቅ።
ካላመናችኹኝ በልቡናችሁ አፍንጫ ነፍሳችሁን አሽትቷት።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
ጥቅምት ፫ ፳፻፲፭ ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#share #like
"ወአንቢበክሙ አንትሙ ለዘኢያንበበ አይድኡ እናንተ አንብባችሁ ላላነበበው ንገሩ"
ቴሌግራም፦ https://t.me/getseseb
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100086220856701
አንድ ሰው ሽንት ቤት ውስጥ ገብቶ ተጨማልቆ እንካ ውሃ ታጠብበት ሲሉት "ኤጭ ጀመረው ደግሞ..... እእእይ.... ተመልሼ እኮ እቆሽሻለሁ አልፈልግም" ይላል?
በፍጹም እንዲያውም ብዙ ውሃና መጥፎ ጠረኑን ደስ በሚያሰኝ መአዛ የሚቀይርለት ሳሙና እንዲሰጡት ይለምናል እንጂ።
ተወዳጆች ሆይ ኃጢአት ማለት ከሽንት ቤት ጽዳጅ በላይ የሚያቆሽሸንና የሚያገማን ነገር ነው።
ንስሐ ደግሞ ንጹሕ እና ጽዱ እንዲሁም ከናርዶስ ሽቱ በላይ እንድናውድ የሚያደርገን ውሃና ሳሙና ነው።
እናም ተወዳጆች ንስሐ እየገባን ነው? ከኾነ ንጹሕና የግሩም መአዛ ባለቤቶች ነን። ንስሐ እየገባን ካልኾነና ድጋሚ ስለምንበድል መንጻት አያስፈልገንም እያልን ከኾነ ግን ከሽንት ቤቱ በላይ ቆሻሾችና መጥፎ ሽታ የምንሸት መኾናችንን እንወቅ።
ካላመናችኹኝ በልቡናችሁ አፍንጫ ነፍሳችሁን አሽትቷት።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
ጥቅምት ፫ ፳፻፲፭ ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#share #like
"ወአንቢበክሙ አንትሙ ለዘኢያንበበ አይድኡ እናንተ አንብባችሁ ላላነበበው ንገሩ"
ቴሌግራም፦ https://t.me/getseseb
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100086220856701
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
❤7🥰4🔥2
ብዙ መጥራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ። ሲታዩ ግን ተስፋ የሚያስቆርጡና የእግዚአብሔርን ከሃሊነት እንድንጠራጠር የሚያደርጉ ይመስላሉ። ትልቁ ችግር እዚህ ጋር ነው። የተሰበቀውን የዲያብሎስን ማንኛውም እና በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣውን ውጊያ ማሸነፍ እንደማንችልና በቅዱሳን መላእክት እንደምንጠበቅ፣ እንደምንረዳ እንዘነጋለን። ይህ ማለት በዲያብሎስ ቅኝ ግዛት ውስጥ ያለጥርጥር ወድቀናል ማለት ነው።
እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ማመን ያለብን ዲያብሎስ አይደለም እግዚአብሔርን ቅዱሳን መላእክትን እንኳ የማሸነፍ ምንም ዓይነት ብርታት እንደሌለው ነው።
ስለዚህ በ40 እና በ80 ቀናችን የሥላሴን ልጅነት የተቀበልን ክርስትያኖች ኹላችን ያለምንም ፍርሃት ስራችንን እንስራ። አሁን እየሰራን ሳይሆን እያወራን ነውና። የተሰጠን ተልእኮ አለ። ይኸውም የክርስቶስን ወንጌል ማወቅ፣ መኖርና ማሳወቅ ነው።
የእግዚአብሔርን የወንጌሉን መንግሥት አምነን ማሳመን የዜግነት ግዴታችን ነው።
"ነዋ ወንጌለ መንግሥቱ ለእግዚአብሔር" የማለት ውዴታና ግዴታ አለብን። ያለዚያ ከሰማያዊው ዜግነት የሚያስወጣንን መንገድ በገዛ እጃችን ጀምረናል ማለት ነው።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ማመን ያለብን ዲያብሎስ አይደለም እግዚአብሔርን ቅዱሳን መላእክትን እንኳ የማሸነፍ ምንም ዓይነት ብርታት እንደሌለው ነው።
ስለዚህ በ40 እና በ80 ቀናችን የሥላሴን ልጅነት የተቀበልን ክርስትያኖች ኹላችን ያለምንም ፍርሃት ስራችንን እንስራ። አሁን እየሰራን ሳይሆን እያወራን ነውና። የተሰጠን ተልእኮ አለ። ይኸውም የክርስቶስን ወንጌል ማወቅ፣ መኖርና ማሳወቅ ነው።
የእግዚአብሔርን የወንጌሉን መንግሥት አምነን ማሳመን የዜግነት ግዴታችን ነው።
"ነዋ ወንጌለ መንግሥቱ ለእግዚአብሔር" የማለት ውዴታና ግዴታ አለብን። ያለዚያ ከሰማያዊው ዜግነት የሚያስወጣንን መንገድ በገዛ እጃችን ጀምረናል ማለት ነው።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍7🔥1
✟ "ዕዳሽ ገና"✟
"ቆማጣ ውብ የኾነች መልከ መልካም ሴት ልጅ ወለደና ቤተ ዘመዱ ተሰብስቦ ስም ሲያወጣ "አማረች፣ ተዋበች፣ ውብነሽ፣ አበራሽ" ትባል በማለት ሲከራከር አባት ሰምቶ ልቡ በሐዘን ተነካ ቀጠል አድርጎ "ዕዳሽ ገና" ትባል አለ ይባላል።"
ይህን ድንቅ ጽሑፍ ሥነ ምግባር በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ነው ያገኘኹት።
ይህ አባት ከቤተ ዘመዱ በላይ በተወለደችው ውብ ልጅት ከማንም በላይ እንደሚደሰት ሳይታለም የተፈታ ነው። እንኳን ውብና መልከ መልካም ኾና ይቅርና የአብራኩ ክፋይ ፉንጋ እንኳ ብትኾን አባት በልጅቱ መወለድ የእውነት ይደሰታል።
አሁን የመጣ ደስታ ግን ቀጣይ የሚመጣ መከራን ከጋረደ ሕይወት ዕውር ዕውርን እንደሚመራው መኾኑ አይቀርም። ልጅቱ ሴት እና መልከ መልካም መኾኗ በረከት እንዳለው ኹሉ ሴት እና መልከ መልካም መኾኗም የኋላ ኋላ መከራ ማምጣቱ የሚጠበቅ ነው። እሱ ደግሞ አባት ነው እርሷ የዐይኑ ማረፊያ ስስቱ። ለዚህ ነው "ዕዳሽ ገና" ትባል ሲል የሰየማት።
በእርግጥ ዕዳው ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለእርሱም መኾኑ ግልጥ ነው። አባት ነው ቆርሶ ማጉረሱ፣ ቀዶ ማልበሱ እንዳለ ኾኖ ከክፋትና ከክፉዎች ሁሉ ሊጠብቃት ከጉማሬ ቆዳ በላይ የጠነከረ ጋሻ መኾን ያሻዋል። ስሟ የእርሷ መጠሪያ ኾነ እንጂ ስሟን ሲጠራ "ዕዳዬ ገና" እያለ ለራሱ የሚሰማው ይመስለኛል።
ብዙዎቻችን በዛሬ ትንሽ ደስታ የዛሬንና የነገን ትልቅ ደስታን እያጣን ነው። ለምሳሌ እንቅልፍ አንዲት ባለሙያ ከምትሰራው ጣፋጭ ወጥ ይልቅ ይጣፍጠናል። እናም ይህን "ጣፋጭ" እንቅልፍ "ሺ ዓመት አይኖር" እያልን እንለጥጠዋለን። ነገር ግን "ሺ ዓመት አይኖር" እያልን ዘለዓለም እየሞትን ወይም የዘለዓለም ሞትን ገንዘብ እያደረግን መኾኑን ልብ አንልም።
አባ ዮሐንስ ዘሰዋስው እንዲህ ይላል" ንቁ ዐይን አእምሮን ንጹሕ ያደርጋል የበዛ እንቅልፍ ግን ነፍስን ያደነዝዛል።" ስንቶቻችን እንሆን ነፍሳችን የደነዘዘው?
በየሚዲያውም ቁጭ ብለን የምንጋተውም "ለሽ እንበል" ነው። ተግቶ ስለመተኛት እንጂ ተግቶ ስለመሥራትና ስኬታማ ስለመኾን አይነገሩንም። አቅዶ ስለመስረቅ እንጂ አቅዶ ባለጸጋ ስለመኾን አያስተምሩንም። ስለመበቀል እንጂ ምሕረት ስለማድረግ አይሰብኩንም። ድንግልናን ከጋብቻ በፊት በዝሙት ስለማጣት እንጂ ስለድንግልና ስለንጽሕና ስለጋብቻ ቅዱስነት አያስረዱንም።
ዐይን የሥጋ፤ አእምሮ የነፍስ ገንዘብ ናቸው። በአፍህ የገባ እንጀራ ሆድህ ላይ እንዲቀመጥ በዐይንህ የገባው ነገርም አእምሮህ ላይ ይቀመጣል። አእምሮህ ደግሞ አንተን የሚቆጣጠርህ ፍጥረት ነው። ይህ ማለት አሁን በሕይወትህ የምታደርጋቸው ነገሮች መጥፎም ይሁን መልካም በሥጋህ (በአምስቱ የስሜት ሕዋሳትህ) ለአእመሮህ (ለነፍስህ) የመገብከውን ነው።
ወዳጄ በሕይወትህ መንፈሳዊ፣ ነፍሳዊ፣ ሥጋዊ መልካም ለውጥ በየቀኑ እያመጣህ ካልሆነ "ዕዳህ ገና" አንተ ነህ።
እታለም ዛሬም ስትዘባነኚና በእርድና መንፈስ ስትሸቀረቀሪ የምታሳልፊ ከኾነ አንቺ "ዕዳሽ ገና" ነሽ።
ከመካከላችን ግራዋ የሚጣፍጠው ማን ነው? ለፍየል ግን ተመራጭ ምግቧ ነው። እንቅልፍም ለሰነፎች ከማር ከወተት የሚመርጡት ምግባቸው ነው። ለትጉሆች ግን ከግራዋ በላይ ይመራቸዋል። ግራዋ ለፍየል የጣፈጣት ባሕሪው ጣፋጭ ስለኾነ አይደለም የፍየሏ ምላስ እንጂ። እንቅልፍም የሚጣፍጠን ጣፋጭ ስለኾነ አይደለም ሰነፎች ስለኾንን እንጂ።
እንግዲህ ምን እንጠብቃለን? በነግህ እንንቃ ውዳሴ ማርያም እንድገም። አእምሯችን ንጹሕ፣ ቀናችን ብሩህ፣ ሕልማችን እውን፣ ሥራችን ሥሙር ይኾናል።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
ጥቅምት ፲፮ ፳፻፲፭ ዓም

👏3👍2🔥1
ጌታችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ ሲመጣ ስለሰዎች ኃጢአት እኛን ለምሥክርነት አይጠይቀንምና የሰዎችን ኃጢአት መዘከር አቁመን የራስችንን ኃጢአት እየዘከረን በዕንባ በንስሐ ልንጸዳ ግድ ይለናል።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍2🥰2
ሳይንስ እና አቦ ሰጥ
ከመቼ ጀምሮ እንደኾነ አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር ሳይንሳዊ ካልኾነ ወይም በሳይንስ ካልተደገፈ እንዳንቀበለው አእምሮአችን በዚህ መንገድ ተሰርቷል/ እየተሰራ ነው። ስለዚህ ነገሩ ሳይንሳዊ ካልኾነ "ምንድን ነው ዝም ብለህ በአቦ ሰጥ የምትጓዘው?" ትባላለህ።
የዚህን ትርጉም ስንመለከተው ለምሳሌ "ጸበል (የተቀደሰ እርጥበት ያለው አፈር) ተቀብቶ መዳን ሳይንሳዊ አይደለም። ስለዚህ ተቀባይነት አይኖረውም።" ሲሉ ይደመጣል።
እኔ እምለው ከኮኮናት የተሰራ ሎሽን ለሰውነት ከበጀ ደብረ ሊባኖስ ያለው እምነት( ጸበል (የተቀደሰ አፈር) ደዌ የማያድንበትን ምክንያት ለምን በሳይንስ አስደግፈው አይነግሩንም?
ወዳጄ እጅ እግርህ ሲያብጥ ውሃ በጨው አሙቀህ ጠዋት ማታ ታጥበህ ከዳንኽ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት የቅዱስ ገብርኤል ጠበል ከካንሰር ማዳን እንዴት አይችልም ብለህ ታስባለህ?
የኾነው እና እየኾነ ያለውን ነገር በሳይንስ አልተደገፈምና አንቀበለውም ከተባለ የማይኾንበትንም መንገድ በሳይንስ አስደግፈው ይንገሩን።
አቦ ሰጥ ያሉት ነገር ከሳይንስ በላይ እንደኾነ የግድ ማወቅ አለብን። አንድ ወንድ ሱሪው ቢረዝመው "ይህማ ሱሪ አይደለም" አይልም። በሳይንስ ዓይን መንፈሳዊው ነገር የረቀቀ ስለኾነ "አቦ ሰጥ" ማለት ኢሳይንሳዊ ነው።

🤩2❤1🔥1
አንድ ብሎ ማቆም እውቀት አይደለም። ሁለት ሦስት እያሉ መቀጠል ያስፈልጋል። አንድ ባለምሳር ትልቅ ዛፍን ለመቁረጥ የተሳለ መጥረቢያ መያዙ ብቻ አይጠቅመውም። ግንዱ ላይ በጣም ብዙ ጊዜ ምሳሩን ማሳረፍ አለበት።
መጽሐፍም እንዲሁ ነው መደጋገም፣ ዕለት ዕለት መነበብ መቀጠል አለበት።
አእምሮን መግዘር የሚችሉ ከምሳር ይልቅ ስለት ያላቸው መጻሕፍት አሉ።
ስል የኾነው ምሳር ዛፉን ለመቁረጥ በተደጋጋሚ በላዩ እንዳረፈበት፤ እኛም መጻሕፍትን በየቀኑ አእምሮአችን ላይ ማስፈር ይኖርብናል።
አንድ ብለህ ከጀመርኽ ኹለት ብለህ ቀጥል።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
መጽሐፍም እንዲሁ ነው መደጋገም፣ ዕለት ዕለት መነበብ መቀጠል አለበት።
አእምሮን መግዘር የሚችሉ ከምሳር ይልቅ ስለት ያላቸው መጻሕፍት አሉ።
ስል የኾነው ምሳር ዛፉን ለመቁረጥ በተደጋጋሚ በላዩ እንዳረፈበት፤ እኛም መጻሕፍትን በየቀኑ አእምሮአችን ላይ ማስፈር ይኖርብናል።
አንድ ብለህ ከጀመርኽ ኹለት ብለህ ቀጥል።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
Telegram
ገጸ ሰብእ
ከትናንት ብንዘገይም ከነገ እንቀድማለን!
https://t.me/getseseb
https://t.me/getseseb
👍7🔥1
❖እስካላቋረጥን አሸናፊዎች ነን❖
እኛ በምናውቀው ሩጫ የአንድ ሯጭ አሸናፊነት የሚወሰነው ሯጮቹን ኹሉ በመቅደሙ ላይ ነው። በመንፈሳዊ ሕይወት ግን እንዲህ የለም። ትግል እንጂ ፉክክር የለም። አንድ ሯጭ በሩጫ ቢሉ በአየር ጠባይ አካሉ ቢዝል መሮጥ ቢያቅተው ሩጫውን አቋርጦ እስካልወጣ ድረስ ደረጃ አይነፈገውም። በእግሩ እየዳኸም ቢሆን ሩጫውን መጨረስ ይችላል። በመንፈሳዊ ሕይወትም እንዲህ ነው። የምንቀድመው የለም። ደረጃችን ግን በሩጫችን ጊዜ በሚገጥመን ትግል፣ መከራ ይወሰናል።
አሸናፊነታችን ዙሩን በመጨረሳችን ከኾነ ወደቅን ብለን ከመሙ መውጣት ምን ይሉታል?
የንጽሕና አየራችን በኃጢአት ወበቅ ተመትቶ ብንዝል፤ በየጊዜው በተለያየ መንገድና መጠን የሰይጣን ጾር እየወጋን ቢያዳክመን፤ ብንፍገመገምም ብንወድቅም እንኳ እስካላቋረጥን ድረስ አሸናፊዎች ነን። ምክንያቱም የሚቀድመንም የምንቀድመውም የለም። መከራውን አልፈን መደረሳችን ድል ያቀዳጀናልና።
ሰይጣን አንድን ሰው የሚያሸንፍበት ኃይል የለውም። የሌለውን ኃይል ግን ከሰውየው ይቀበላል። ሰውየው እንዲያሸንፈው እስካልፈቀደለት፤ እጁን እስካልሰጠ ድረስ ሰይጣን ሊያሸንፈው አይችልም። የሰይጣን ድርሻ እስከጥግ መፈተን ነው። እስከ ጥግ ሲፈትን እጅ ከሰጠን አሸናፊነቱን ይወስዳል።
ምናልባት በተለያዩ የኃጢአት መሰናክሎች እየተሰነካከልን ይሆናል፤ ምናልባት በጎ ነገር ለማድረግ መንፈሳችን ዝሎ ይሆናል፤ ምናልባት መንፈሳዊ ሰው ለመኾን እየፈለግንና እየሞከርን ከሳምንት ያለፈ መንፈሳዊ ኾኖ መቆየት ተስኖን ይሆናል፤ ብቻ በመንፈሳዊው መም በምንሮጥበት ጊዜ ደክመን፣ ተሰላችተን ቢሆን እንኳ በእንብርክካችን እንዳኽ። ሩጫቸውን የጨረሱ ቅዱሳን ማበረታቻ ሰጥተው እንድንሮጥ ያደርጉናልና። በእጃቸው ደግፈው በጸሎታቸው ያድሱናል።
ከቻልን እንብረር፤ መብረር ካልቻልን እንሩጥ፤ መሮጥ ካልቻን ዱብ ዱብ እንበል፤ ዱብ ዱብ ማለት ካልቻልን እንራመድ፤ መራመድ ካልቻልን እንንቀሳቀስ በፍጹም እንዳንቆም።

❤4👏4🔥1🥰1
❖ታዘብከኝ❖
አንድ እኅታችን ትምህርቷን ጨርሳ ስራ ፍለጋ ላይ ነች። ስራ ግን አልተገኘም። ስለዚኽ ኹሉን ማድረግ ወደ ሚችል ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ጸለየች። ስራ ስጠኝ ብላ። ልመናዋን ባቀረበች በጥቂት ጊዜ ውስጥ "3 ሺህ" ብር ደሞዝ ያለው ስራ ማስታወቂያ ይወጣና። የትምህርት ማስረጃዋን ታስገባለች። ጸሎቴ ተሰማ ብላ። ነገር ግን እንዳሰበችው አልሆነም። ወደቀች። ይህን ጊዜ እግዚአብሔርን "ታዘብኩኽ" አለችው። ቀን አልፎ ቀን ተተካ። ሌላ የ"7 ሺህ" ብር ደሞዝ ያለው የስራ ማስታወቂያ ይወጣል። አሁንም እንደጓጓች ይህን አታስመልጠኝ እያለች የትምህርት ማስረጃዋን ታስገበለች። እግዚአብሔር የሚሰማት አልኾነም። ይህም ስራ አመለጣት አጣችው። አሁን እጅግ ከፍቷታል ያንን ቃል ደግማ "ታዘብኩኽ" አለችው፤ እግዚአብሔርን። አሳይቶ እንደነሳት ነው የተረዳችው። ዳግመኛም ከቀናት በኋላ ከ"10 ሺህ" ብር ደሞዝ በላይ ያለው የስራ ማስታወቂያ ይወጣል። አሁን ግን እምቢ አለች። ቤተ ሰቦቿ ጓደኞቿ ቢሏት ቢሰሯት ፈጽሞ እምቢኝ አለች። "በ3ሺ እና በ7ሺ ያላገኘሁትን ስራማ አይሰጠኝም" ብላ እግዚአብሔርን በማኩረፍ ጸናች። ጓደኞቿ የትምህርት ማስረጃዋን ወስደው እርሷ ሳታውቅ ያስገቡላታል። ባላወቀቸውና ባላሰበቸው መንገድ ከ10 ሺ ብር በላ ደሞዝ ያለው ስራ ለእርሷ ይሆናል። ከመስሪያ ቤቱ ተደውሎ ይነገራታል። ማመን ቢያቅታትም በመጨረሻ ወደ እግዚአብሔር ቀና ብላ "ታዘብከኝ" አለችው።
ይህ ታሪክ እውነተኛ ታሪክ ነው። በብዙዎቻችን ሕይወት ውስጥ ይህን መሰል ታሪክ ተደርጎም ያውቃል። እግዚአብሔርን አምነን፣ ፈልገን ከጠየቅነው በኋላ እርሱ የወደደውን እንዲሰጠን ሳይሆን እኛ ያሰብነውን ካልሰጠን እንላለን። በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ከእናንተ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብ ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታዎችን መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? " ይለናል። ማቴ ፯፥፱-፲፩።
እግዚአብሔር ለሚለምኑት የሚለምኑትን ብቻ ሳይኾን የሚሰጠው ከሚለምኑት አብልጦ ነው። ፈያታዊ ዘየማን በዕለተ ምጽአት በመንግሥቱ እንዲያስበው ጠየቀ፤ ጌታችን ግን የጠየቀው ዕለት በገነት ከእርሱ ጋር እንዲኾን ፈቀደለት። የደሙን ማኅተም ሰጠው። ከአዳም ቀድሞ ገነት ገባ።
መጻጉዕ ደቀ መዛሙርቱን አዝዞ አልያም እርሱ ተሸክሞ ወደ መጠመቂያው እንዲወስደው ጠየቀ፤ ጌታችን ግን አልጋኽን "ተሸክመኽ ሂድ" ብሎ አዳነው።
እንግዲህ እግዚአብሔር እንዳይታዘበን ከለመንነው በኋላ እርሱን እንጠብቅ። የሚሰጠንንም በጸጋ እንቀበል።
የክርስቶስን ምሥጢር እንደናገር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ እንዲከፍትልኝ በመልካም እንድኖር ስለእኔ ደግሞ ጸልዩ።
ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
መጋቢት 23 2014 ዓ.ም ዘተጽሕፈ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በድጋሚ የተለቀቀ

👍4🥰2❤1
ይህስ በነግህ የመጣ የጽድቅ ጥሪ ነው። ይህስ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው። ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
እንግዲህ ምን እንላለን? 97% በመናፍቃን ለተከበበው ለሆሳዕናው ፀሐይ ለሆመቾ ቅድስት ሥላሴ የአቅሜን እንዳላደርግ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
አንድ ውዳሴ ማርያም ገዝቼ ለመዳን የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
https://t.me/getseseb
እንግዲህ ምን እንላለን? 97% በመናፍቃን ለተከበበው ለሆሳዕናው ፀሐይ ለሆመቾ ቅድስት ሥላሴ የአቅሜን እንዳላደርግ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
አንድ ውዳሴ ማርያም ገዝቼ ለመዳን የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
https://t.me/getseseb
✟እግዚአብሔር ያውቃል✟
ዲያብሎስ የነጋችንን አያውቅም። እንዲሁ እኛም ስለነጋችን አናውቅም። እግዚአብሔር ግን ያውቃል።
ዲያብሎስ ስለትናንታችን ያውቃል። እኛም ስለትናንታችን እናውቃለን። እግዚአብሔር ግን ትናንታችንንም ዛሬአችንንም ነጋችንንም ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛም ከዲያብሎስም በላይ ያውቃል። ዲያብሎስ ከትናንት ታሪኮቻችን ላያውቃቸው የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉት። ስለትናንታችን ያውቃል ስንል ከእኛ እኩል ያውቃል ማለታችን አይደለም። ስለዚህ ስለራሳችን ባለን እውቀት እንበልጠዋለን ማለት ነው። ታዲያ ከእግዚአብሔር ይልቅ ዲያብሎስን የምንፈራው ለምንድን ነው?
ብዙዎቻችን "እግዚአብሔር ያስተካክልልኛል፤ ያሳካልኛል" ከማለት ይልቅ "ሰይጣን ያሰነካክለኛል፤ ያበላሽብኛል" ማለት ይቀናናል። ሰይጣን ከትናንት ታሪካችን ተነሥቶ ነጋችንን በሊኾን ይችላል ገምቶ ነው ፈተና የሚቀምረው። ይህ ማለት የሰይጣን ዕውቀት ግምታዊ እንጂ ፍጹም አይደለም። ሊኾንም ላይኾንም ይችላል ላይ የረገጠ ያልጸና ዕውቀት ነው። የእግዚአብሔር ግን ይለያል። እግዚአብሔር ትናንትን "ይቅር በለኝ" ሲሉት ሙሉ በሙሉ ይቅር የሚልና ዛሬን የሚያኖር ስለነገ ደግሞ ብሩህ ተስፋ የሚሰጥ አምላክ ነው።
ትናንት ዘማውያን፣ ትናንት ዘፋኞች፣ ትናንት ሌቦች፣ ትናንት ሱሰኞች፣ ትናንት ሰካራሞች፣ ትናንት ወስላቶች፣ ትናንት ለመንፈሳዊ ስራ ከበረዶ ይልቅ የቀዘቀዝን ለኀጢአት ደግሞ የምንፋጠን ኾነን ሊኾን ይችላል። እሊህ ኹሉ ከተራራ የገዘፉ ኀጢአቶቻችን ግን በእግዚአብሔር ምሕረት ፊት ኢምንት ናቸው።
እግዚአብሔር ራሳችንን ከምንወደው በላይ ያፈቅረናል። እግዚአብሔር ራሳችንን ከምንከባከበው በላይ ይሳሳልናል። ካህኑ ጋር ሄደን ንስሐ እንግባ። ይህን ብቻ ነው እግዚአብሔር የሚፈልገው። የእኛን በንስሐ መመለስ ብቻ።
ዛሬ ካለንበት ጨለማ በብርሃኑ የሚሞላን ብርሃናችን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ብርሃንን መቃወም የሚችል ጨለማ የለም። እግዚአብሔርን ከወደድነውና ከእርሱ ጋር መኖር ከፈለግን ያበራልናል። ከገባንበት ጨለማ ያወጣናል። ይኽ ብቻ አይደለም።
እግዚአብሔር ስለነጋችን ከማንም በላይ ያውቃል። ነጋችንን ያለማንም እርዳታ ያስተካክላል። እግዚአብሔርን መቃወም የሚችል ሰማያዊም ኾነ ምድራዊ ኀይል የለም። ሰይጣን ተመቸውም አልተመቸውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ካለ በፍጹም ሊያሸንፈን አይችልም። እግዚአብሔር ደግሞ ከእኛ ጋር የሚኾነው በንስሐ በር ወደ እርሱ ስንገባ ነው። በንስሐ ውኃ ቤታችንን አጽድተን ስንቀበለው በልባችን በክብር ስናስተናግደውና ስናነግሠው ነው።
ዲያቆን ሳሙኤል በላቸው
"የምወዳችሁ ወንድሞቼ! ስለአእምሯችን ሕጸጽ ጸልዩልን። ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ፤ ተስፋችንም ይኽ ብቻ ነው።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።"
ሃይ.አበው ዘቴዎዶስዮስ

🥰2