ፍቅሬን በግጥም 💞
5.4K subscribers
59 photos
21 videos
2 files
78 links
✍️ለምን ወደድኩህ/ሽ?
እንጃ።🤷‍♀️
✍️ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ?
እንጃ🤷‍♀️
✍️እንዴት ማረከኝ/ሺኝ?
እንጃ🤷‍♀️

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟

👉comet ena malt yemet felguti ngr kal
@Erazatube_bot
Download Telegram
❤️❤️ትርታዬ❤️❤️

አንቺ የኔ ቆንጆ የኔ ማር ወለላ፣
ማሬ ማሬ ስለው እንዲያው ያንቺን ገላ፣
ይስበኝ ጀመረ ከፊትም ከኀላ።

ምን ይሔ ይገርማል ለምንስ ደነቀሽ፣
ማሬ የሚለው ቃል ለፍቅርሽ ካነሰሽ፣
ምንም እልሻለሁ ትርታዬ አንቺ ነሽ።

አንቺ የኔ ቆንጆ የልቤ ትርታ፣
ሁሌ አስብሻለሁ በጠዋት በማታ።

ትርታዬ ስልሽ ውሸት እንዳይመስልሽ፣
እጅሽ አምጪና አዳምጪ ከፈለግሽ፣
የኔ ትርታዬ ሁልጊዜም አንቺው ነሽ።

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
በፍቅር መንገድ ውስጥ ስትሆን ስሜትህን ገርተህ ልብህ የሚፈልገውን አለማድረግ አይታሰብም.....ፍቅር ይመራሃል አንተም ሳታወላውል ትከተለዋለህ በቃ እንደዛ ነው የሚሆነው.............እና አላውቅም በብዙ ነገር ደካማ ነኝ ግን አንተን መውደድ ሚደክመኝ አይመስለኝም...
#.... 🦋
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
❤️የፍቅር ቃል

ልቤንም በሀሴት
መንፈሴን በደስታ
ሞልቻት ህይወቴን
በሳቅ በፈገግታ
እንደ እፃን ቦርቄ
ተጫውቼ ስቄ
ደግሞ እንደ ፈንዲሻ
ፈንድቼ ፈንድቄ
ከተሰጠኝ እድሜ
አንድ የምጨምረው
ጥርሶችሽ ተከፍተው
ፈገግታሽን ሳይ ነው

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
እናም . . .ስለኔ እያሰብክ ከሆነ ምናልባት እኔም ስላንተ እያሰብኩ ይሆናል . . .😒
💚💛❤️
...ሰውም_ፍቅርም_ከንቱ ***
.
.
አፍቅሮ መፈቀር መታደል ነበረ
ግን ይሆናል ያልኩት ሳይሆንልኝ ቀረ
ብዙም አልተከፋው ብዙም አልተጨነኩ
ሰው ሁሉ ወረተኛ መሆኑን ግን አወኩ
አውቄ ፈተሽኩት እራሴን ቀርቤ
ለዚ ዘመን ፍቅር ለካ አይሆንም ልቤ።
💚💛❤️
#.... 🦋
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
#ማፍቀር እኮ ሀጥያት አይደለም

ነገር ግን በፍቅር ስም በሰው ስሜት
ላይ መጫወት ትልቅ ሀጥያት ነው!

#ወዳጄ
እውነተኛ ፍቅር እኮ ለምትወደው ሰው ምንም
ሳትሰስት እራስህን አሳልፈህ መስጠት እንጂይ
በማስመሰል ተጀምሮ በጥላቻ የሚደመደም አይደለም፤

ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር ስሜት
ሳይሆን ዘልአለማዊ መተሳሰብ ነው።

#.... 🦋
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
፨እጠብቅሻለሁ፨
አሞሽ ነው ተኝተሽ
ስጣራ ዝም ያልሽ
እማ ልደግፍሽ
እጄን ያዢ ተነሽ
ወይ በይኝ ስጠራሽ
ልጄ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
በጣም ነው የራበኝ
ልጥባ ጡትሽን ስጪኝ
በለጋው እድሜዬ ሜዳ ላይ አጣይኝ
እርቃ ሄዳለች በቃ ተዋት አሉኝ
አሰማም ሞታለች ሰዎች ሁሉ ሲሉኝ
አልገባኝም እኔ እማ እስኪ አስረጂኝ
ምን ማለት ነው ሞት?
ተኝቶ መነሳት?
ወይስ በዛው መቅረት?
አስረጂኝ ልወቀው
ሸሽቶኛል ሁሉም ሰው
እንዳትቆይብኝ እጠብቅቫለሁ
እማ የኔ ውዷ ከልብ ወድሻለሁ

#.... 🦋
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
🙇ስማ ስሚ🙇‍♀
💖💖💖
የደመቀች ፀሀይ ውበቷ ቢጣራም
ፀሀይ ካልጠለቀች ጨረቃ አታበራም
አዕላፍ ቢመስሉም በቁጥር ቢልቁም
ጨረቃም ካልጠፋች ከዋክብት አይደምቁም
ህይወትም እንዲህ ነች...
እንሰጋለን እንጂ በችግር ሲጨልም
ካልጨለመ በቀር ብርሃን አናይም
።።።።።።።።።።።//።።።።።።።።።።
#.... 🦋
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
በማን ልመስልሽ

አንች ተጎሳቁለሽ እኔን ሀይል አልብሰሽ
አንቺ አመድ መስለሽ እኔን ወርቅ አድርገሽ
አንቺ አጎንብሰሽ እኔን ቀና አድርገሽ
አንቺ ሳትማሪ እኔን አስተምረሽ
እማ ምን አድርጌ አንችን ላስደስትሽ
❤️❤️ እማ❤️❤️
የሚያምሩት አይኖችሽ ማየት ያስቸገረው
እኔን ለማሳደግ ጢስ ለጢስ ሲሄድ ነው
ያ እሜያምረው ደምግባት ውበቱ የጠፋው
እኔን ለማሳደግ እላይ እታች ሲል ነው
ታድያ ምን ልበልሽ ለዚህ ጣፋጭ ፈቅርሽ
ከ ቃላት በላይ ነው ለኔ ሁሌም ፍቅርሽ

እራዛ

የሚስማማ join & share
👇👇👇
#.... 🦋
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
ሰላም ለዚህ ቻናል ወዳጆች የውስጥን ስሜት ቃላት አሰባጥረን ስሜትን ከስሜታችሁ አዋህደን አቤት የልቤን አወራህ እስክትሉ ድረስ ሀሳባችሁ ሀሳባችን እስኪመስላችሁ ድረስ የልባችሁን በግጥም ,በወግ ,በቀልድ
እንተነፍስላቹሀለን፡፡ ቃላችን እውን ነውና ይቀላቀሉን ይወዱናል፡፡

እራዛ
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
       ❤️🩵❤️🩵❤️🩵
          ማነው የተረዳኝ
ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ
እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ።
ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ
አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ።
እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ
ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ።
እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው
የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው
መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው
ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው
ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው
የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው?
እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ
እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ
ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ
ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ።
አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው
አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው
እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
😡 ገላሽን አጫርተሽ 👍

ጭንሽን ለሁሉም ገልጠሽ ስታበቂ
እንባሽ ምርኩዝ ላይሆን አትነፋረቂ

ካጣሁሽ አልኖርም
      ያለሽም ሰው ሁሉ በፍፁም ያላንች
ሊቀየር ይችላል ለሀለሉም ስትከፍች

እንዳያታልልሽ ይሄ ግብዝ አለም
ጭን ስላለ ብቻ ካገኙት
       መጋደም ሴትነት አይደለም

ገላሽ ከለመደ ካገኘው ሰው ሁሉ ከሆነ ሚጋራ
ጣፋጭሽን መጠው የትም ይጥሉሻል ልክ እንደ ሸንኮራ

ማይገባሽ ቦታ
ማይመጥንሽ ቦታ በፍፁም አትቁሚ
ጆሮ ተሰቶሻል ትሰሚ እንደሁ ስሚ  🎤

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤
#ሄደች_መሰለኝ

በፊት ገና ድሮ እሷን እንዳወኳት
ሳልነግራት ደፍሬ እኔ እንዳፈቀርኳት
በፍርሃት ተውጬ ስሜቴን ደብቄ
ለራሴው ሳወራ ሀሳቤን አምቄ
በጥላዋ ስኖር በፍቅሯ ከለላ
በረረች መሰለኝ ሄደች ወደሌላ

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
🔣🔣🔣🔣🔣🔣⭕️🔣🔣🔣🔣🔣🔣

        "ምን ያክል ነው ፍቅርሽ
               ብለህ ብጠይቀኝ

ምን ያክል ልበልህ
ምኑን አውቀዋለሁ፣
እኔ አምላክ አይደለሁ፣

ብቻ ግን 🔣🔣

ማንም ጓደኛዋን ከምትወደው በላይ፣
ማንም ፍቅረኛዋን ከምታፈቅረዉ በላይ፣
ውስጤን ገዝተከዋል ቦታ አለህ ልቤ ላይ፡፡
🔣🔣🔣🔣🔣🔣❤️🔣🔣🔣🔣🔣🔣
ብታምንም ባታምንም፣
እውነቱን ልንገርህ ፍቅሬ አንተን አልዋሽም፣
እስከ ዘላለሙ እኔ አላፈቅርህም፣
እንደ ሞኝ አፍቃሪ
የዘላለሜ ነህ ብዬ አልደልልህም፣
ምክንያቱም...
ዘላለም የሚኖር ሠው ተፈጥሮ አያውቅም፡፡
አንተም
እኔም
ሁሉም
ማንም ቢሆን ማንም፣
ዘላለም አፍቅሮ ዘላለም አይኖሮም፡፡
ግን...
እስከ'ድሜዬ ክልል እስከ ሂወቴ ጫፍ፣
መቼም አይሰለቸኝ
አንተና ፍቅርህን አዝያችሁ ብከንፍ፡፡

   አፈቅርሃለሁ 💖    ➡️ትላንትም
                                   ➡️ ዛሬም
                                     ➡️ ነገም
አስካለው በምድር ፣ከዛም በኋላ ❤️

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
Forwarded from 𝖊𝖗𝖆𝖟𝖆 𝖋𝖎𝖑
👋ሰላም 👋ሰላም
     ውድ የቻናላችን ተከታዮች በሙሉ
         ዛሬ ለኔ ልዩ ቀን ነው
       ምክንያቱም በጣም የምወደው ከጓደኛ ልደቱ ነው
05/06/2016E.C.
             መልካም ልደት በሉኝ
        👑👑🎂🎂🎂🎂👑👑
  
#ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ
              🇪🇹
#ፍቅር_ያሸንፋል🇪🇹

መልካም ምኞታቹን
እዚህ ላይ ግለፁልኝ
      📥 👉
@mamewolf

ስለ መጡ እናመሰግናለን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


  ✦_ @getemi _✦
Forwarded from 𝖊𝖗𝖆𝖟𝖆 𝖋𝖎𝖑
የኔ ወድ ልደትሽ እኮ ዛሬ ነው
የኔ ተወዳጅ እህቴ 😘 ፈጣሪ ከሠጠኝ ልዩ ስጦታ 💝አንዷ እና ልዩዋ ነሽ። ዛሬ ደግሞ አንች ወደዚህ ምድር የመጣሽበት 😁ልዩዋ ቀን 05/06/2016 ናት እናም እንኳን ለውቧ የልደት ቀንሽ በሠላም  አደረሠሽ እህቴ 🌟🎂🎉Ĥ🎉🎊🎂B🎉🎊🍰🍯🍮🍭🍬🍧Ď🌟🎂🎉🎊🍰🍬🍧🎂🎉

  
     
         
             
                
                    
እንኳን ተወለድሽልኝ ነፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ አመት ኑሪልኝ የኔ ውድ ፈጣሪ እንዳገናኘን ሁሉም አይለያየን እ
🎉🎉🎉HBD🎉🎉🎉
🎉🎉🎉 HBD🎉🎉🎉
🎉🎉🎉  HBD🎂🎂🎂🎂
👉      እራዛ
👉      ኢክራም
HBD TO YOU🎂🎂🎂🎂🎂🎂

  ✦_
@getemi _✦
።።።።።።አጠይቁኝ ይቅር💔።።።።።።

ለምን ሆነ አትበሉኝ አጠይቁኝ ይቅር
ሁሉን ብነግራችሁ ላይገባችሁ ነገር😕
እንዴት አትበሉ ለማወቅ ጓጉታችሁ
ነገሩን ብታውቁ ምንም ላይጠቅማችሁ
አጠይቁኝ እኔን ትላንትስ ብላችሁ
ታሪኬን የዃሊት እያስታወሳችሁ😡
የት ነበርሽ አትበሉ አታብዙ ጥያቄ
የትስ እንደነበርኩ እኔ የት አውቄ
ምላሼን በመሻት ጥያቄ አታብዙ
ዃላ ብነግራችሁ ብዙ ነው መዘዙ
አታድሙት ቁስሌን በሾክ ወጋግታችሁ
የማያባራ ደም ጉድ እንዳይሰራችሁ😔
ዝምታዬ ጎልቶ ስሜት ካልሰጣችሁ🙍‍♂
አላደክምም ራሴን አንዱም ላይገባችሁ🤦‍♀

ስለዚህ እባካችሁ።።።።።።።

አጠይቁኝ ይቅር የለኝም መልሳችሁ።🤷‍♂🤷‍♀

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
ለካ አረሳሁሽም
""""""""""""""""""""


መስሎኝ ነበር
የረሳሁሽ ያወጣሁሽ ከህይወቴ ፣
የጠላሁሽ ችዬ ያራቅኩሽ ከእኔነቴ ፣

መስሎኝ ነበር
የሄድሽበት የእግርሽ ዳና የተፋቀ ፣
የፈገግታሽ ምስል ከልቤ የራቀ ፣

እኔስ ብዬ ነበር
እረስቼሻለው ከሀገሩም የለሽም ፣
ለምጄው ነው እንጂ ለካ አረሳሁሽም ።

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
መንቃት እፈራለሁ
"""""" """"""''"""

እወድሻለሁና

ፈገግታና ሳቅሽ ፣
ኩርፊያ ቁም ነገርሽ ፣
ሁሉሽ የሚያስደስት ፣
ጠረንሽ የሚስብ እንደ ከርቤ ማዕጥንት ፣
አብረሺኝ ስትሆኚ አለም እንደ ኩታ ፣
ደስታን እንደ ጃኖ ደርቦ እንደወጣ ፣
ሁሉ እንደሞላለት ፣
ነው ምሆነው እውነት ።

ፀሊም መልኬ በርቶ ፣
ጉልበቴ በርትቶ ፣
አለምን በእጄ የያዝኩት ሲመስለኝ ፣
መንቃት እፈራለሁ ካንቺ እንዳይነጥለኝ ።

ደስታዬን ስትሰጪኝ ነጥቀሽ ከእምባዬ፣
ህልም ነው ሚመስለኝ ባልነቃ ደስታዬ ፣
መንቃት እፈራለሁ ከሰጠሽኝ አለም ፣
ህልም ነው ሚመስለኝ ህልም ግን አይደለም ።

ሁሌ...... አብረሽኝ..........ሁኚ

#በረከትዘውዱ

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
#አወይ_ጥርሷ



ዓይኖቿ ጥለውኝ ገና ሳልነሳ፤
ከንፈሯ ደገመኝ አቤት የኔ አበሳ።


እኔን ማለት ትታ፤
ጭራሽ በሱ ፈንታ፤
ከንፈሯን አሽሽታ፤
ሳቀችብኝ ልጅት መሬት ስወድቅ አይታ።


እኔስ...
ካ'ይኗ ከከንፈሯ እመሬት ከጣለኝ፤
የጥርሷ ድርድር ነው ይበልጥ ያቃጠለኝ።

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ