ፍቅሬን በግጥም 💞
5.19K subscribers
68 photos
22 videos
2 files
84 links
✍️ለምን ወደድኩህ/ሽ?
እንጃ።🤷‍♀️
✍️ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ?
እንጃ🤷‍♀️
✍️እንዴት ማረከኝ/ሺኝ?
እንጃ🤷‍♀️

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟

👉comet ena malt yemet felguti ngr kal
@Erazatube_bot
Download Telegram
ስላንተ እየፃፍኩ አንተን ስተውንህ ፣
ደግሞም በሸራዬ ስሞነጫጭርህ ፣
በልቤ ዞፋን ላይ በክብር ሳነግስህ ፣
ዜማና ቅኝቴ በድምፄ ስቃኝህ ፣
የፍቅር ቀማሪ ደራሲ ኦንኩልህ ።
እኔ ብቻ ማይህ የግሌ ጋለሪ
ብሎም እደ ጥበብ እንደ ሸክላ ሰሪ
ሁሌም የማድስህ እኔ ያንተ አፍቃሪ ።
ትወናዬን የሚያዬ አልሻም አድናቂ
ሙዚቃዬን ሰሚ እንዳይመጣ አርቃቂ
ለመስማት ለማየት እኔ አለሁኝ በቂ ።
በእራሴ ዓለም ያኖርኩ ሸሽጌ፣
እኔነቴን ሰጠው ከእራስ እስከ እግርጌ ፣
እንዳሻህ ሁንበት በነፍስ በስጋዬ፣
ስትፈልግ እየሳክ እያልክም እዬዬ ።
ግና አደራህን ውዴ ይህንን አትዘንጋ፣
ይህን የፃፍኩልህ በህልም አለም ጣጣ፣
እውን መስሎ ደግሞ ፍለጋ እንዳትወጣ፣
ብሎም ቅዠትህ ነኝ በህልም ምመጣ።  

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
♥️መብቴ መሰለኝ🥰
         ~~~~

ውብ አስተያየትሽ እጅግ ካማለለኝ🙄

ቁጥቡ  ፈገግታሽ  እኔን  ከገደለኝ😁

ወደድኩሽ ማለት መብቴ መሰለኝ🤔

ምንጨነቀሽ አንቺን እኔን ደስ ካለኝ🤷‍♂

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
ከሰው መሃል
ምን አይኔ ላይ ጣለሽ👀
ላይመለስ ልቤ በቃ ተከተለሽ🚶‍♂
እሰይምሽ እጠራሽ ቸገርኝ
ለቆንጆ ሚሆን ቆንጆ ቃል አጠረኝ
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አይኖችሽን አይቼ ሳገግም አንደበትሽ ይገለኛል ዳግም♥️

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
አንድ ጥያቄ አለኝ? | I Have A Question


Single ሆኖ መኖር ወይም መቆየት ምን ችግር አለው?

ሰዎች ፍቅረኛ ስለኖራቸው አንተም/አንቺም ይኑርሽ ማለት አይደለም። አንዳንዴ ዳር ሆኖ ሮማንስ ማየትም የአለም ሌላኛው ገፅታዋ ነው ላንተ/ላንቺ ሚሆንሽን Save ማረግ ደሞ ያንቺ/ያንተ ፋንታ ይሆናል ማለት ነው።

አንዳንዴ ሌሎችን በማየት ብቻ ወይም ጓደኞቻችን አረጉት ብለን ከገባንበት በኃላ በተለያዩ ምክንያቶች ግንኙነቱ ለመቆም ይገደዳል ስለዚ ዘሎ ከመግባት በፊት ማስተዋልና አርቆ ማሰብ አጭር ግኙኘነት እድሜ እንዲኖራቸው ያግዛል ብላ እቺ ቻናል ታምናለች።
​​💝ምንም ብንራራቅ
ስፍራችን---------ቢለያይ
ሁሉ ጊዜ በአከል ምንም ባንተያይ


አንተም ካለህበት  እኔም ካለሁበት
ሳያግደን መንገድ ሳያገደን  ርቀት
እየተገናኘን በእምነት ቀለበት
ተሳስሮም ልባችን በፍቅር መቀነት
 
እመነኝ ሆዴ እንዋደዳለን
ይሔ ቀን አብቅቶ ነገን እናያለን።


━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
​​ለምን እንደማልጠላሽ ባላውቅም
    የምወድሽ ልጠላሽ ባለመቻሌ ነው

ለኔ መኖር ማለት አንቺ ነሽ መሞትስ ማን መሰለሽ ? መኖር አንቺ ከሆንሽ መሞት እንዴት ሌላ ይሆናል  መሞትም መኖርም አንቺ ነሽ
አለም ለኔ ትልቅ ት/ት ቤት ነች አንቺ ደግሞ እኔን እንድታስተምሪ የተመደብሽ ልዩ አስተማሪ ነሽ የሒወቴ አስተማሪ በጣም ነው ምወድሽ
  በጣም እንደምታፈቅሪኝ አውቃለው ለዛም ደስ ይለኛል መፈቀር ብርቅ ሆኖብኝ አይደለም ባንቺ መፈቀሬ ግን ብርቅ ያደርገዋል፡፡
የኔ ፍቅር ❤️ አንቺ ማለት ለኔ መግለፅ የማልችልሽ ባዶ መስመሬ ነሽ
አንቺን ሳስብ ብዙ ነገር እረስቻለው እራሴንም ችምር
መናፈቅ ማለት እሩቅ ያለን ብቻ ሳይሆን በእቅፍ ያሉትንም ነው
ሁሌም ጠዋት ስነሳ ጥሩ እድል እንዳለኝ አምናለሁ፣ ምክንያቱ ደግሞ ራሴን ነው የምሆነው፣ማንነት ሁሌም ስኬት ነው ብቻውን ነዋ የተፈጠረው፡፡

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲             
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
​​ለምን ቀሰቀስሽኝ፣
ህይወት ልትዘርቢኝ ወይስ ልትገዪኝ፣
ከወጋሽኝ ወዲያ ይማርህ ልትዪኝ፣
ንገሪኝ በይ ልስማሽ ዛሬ ምኔ ታየሽ፣
ኮስማናው ገላዬ ቆይ ምኑ አማረሽ፣
የገረጣው ፊቴ ይሄ አመድ ለባሽ፣
የደከመው እግሬ ካንቺ ርቆ ሲሸሽ፣
የዛለው ጉልበት መክኖ ስለፍቅርሽ፣
እንዲ ተጎድቼ ለምን ትመጫለሽ፣
ለምን ቀሰቀስሽኝ ቆይ ዛሬ ምን ታየሽ፣


━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
❤️

#ምኗ_ነው?
:
:
:
ምኗን ነው ግን የወደድከው
አልፎ አልፎ ይለኛል ሰው፤
እንዲ ብሎ ሚጠይቀኝ
የሆነ ብቃት እንዳነሰው፤
መጠይቁ ያሳብቃል፤
የልቡ ዓይን ያልበራለት
ወትሮስ ፍቅርን እንዴት ያውቃል።
:
:
ብዙ ማዕረግ ብዙ ገድል
የቀለም ቀንድ ጥልቅ ሀሳቡ፤
እስካልበራ እውር ልቡ፤
ፍቅር ወርሶ እስካልቋጨው፤
ሰው አይሆንም የምድር ጨው።
:
:
ሆነሽልኝ ዝርግፍ ጌጤ
ወርቀዘቦ ተክህኖ፤
አዋቂው ሰው ለጋ ሆኖ፤
እንዲያ ብሎ ሲጠይቀኝ
ያደርገኛል ደርሶ ብግን፤
የሚጠላው ምኗ ነው ግን?

#እራ_ፊል

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
"አንተ.. በጣም
ውሸታም ነህ አስመሳይ፣
ይነጥለኝ ካንተጋ
አይንህንም ሳያሳይ"፣

ልልህ እያቃጣኝ
የገዛ ውሸቴ ያግደኛል ደርሶ፣
ምን አፍ አለኝ እና
አንተን የምናገር ደሞ ከኔብሶ።


━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
ቅርአለኝ
.
አብረን ሳንዘልቅ ክረምትን፣
አስታውሰን ሳንስቅ ትናንትን፣
ሳናጌጥ በሱፍ በቬሎ፣
ሳንጨፍር ድንኳን ተጥሎ፣
በዘመድ አዝማድ ምርቃት፣
ትዳር ጣእሟን ስናቃት፣
ሳምንታት አመታት ሳንቆጥር፣
እኔና አንተን መሳይ ሳንፈጥር፣
ከጎንህ ተኝቼ ሳልነቃ፣
እንዲሁ በዋዛ ተለያየን በቃ¿


━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
የክረምት ዶፍ ዝናብ ገላሽን ካራሰው
ሽቅብ እወጣለሁ
ደመናን ላፈርሰው ።
ንፋስ በክንፎቹ ጉንጭሽን ቢዳብስ
ስታገል አድራለሁ አየር ሳበሰብስ
ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ያለኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ

መብረር ያሰኘሽ 'ለት ክንፋም ልሁን ልክነፍ
ውሃ ያሰኘሽ 'ለት ወንዝ ውቅያኖስ ልጥለፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።

ስቀና እንዲህ ነኝ !

#ዘሩባቤል

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
Forwarded from ❤ Erza bot
የ90ዎቹ ሙዚቃ አድናቂዎች ቻናል Join በማለት ይቀላቀሉን።
👇
https://t.me/+JcWeEF28Q-plZWZk
አደራ ጠርጥሪኝ

ስምሽን ስሰማ እንባ አይኔን ካሞቀኝ
ስላንቺ ሳወራ ሳግ ደርሶ ካነቀኝ
ፀሀይ ከበረደኝ ሳቅ ከኔ ከራቀ
መከፋት ደስታየን ከእኔ ከሰረቀ

              አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

በእብዶች መካከል ደህና ከተሰኘሁ
በዝናብ ሲርሱ ደርቄ ከታየሁ
በትልቅ ሰው ለቅሶ ሳቄ ካመለጠኝ
ሀገር ባሳቀ ቀልድ እንባ ካጠመቀኝ

              አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ከጨረቃ ጋራ ሳወጋ ካመሸሁ
ከሚያውቁሽ ከሚያውቁኝ ከራሴ ከሸሸሁ
አለም ከደበተኝ ከከረፋኝ ሀገር
በሆነ ባልሆነው ካለኝ ነገር ነገር

               አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ይሄው አሁን እንኳ
ስላንቺ እየፃፍኩኝ ላብ ሞልቷል ግንባሬ
ቁጭ ብየ ራሱ ልሩጥ ይላል እግሬ

እኔ እወድሻለሁ ማለቱን ትቻለሁ
በስምሽ መማሉን ረስቼዋለሁ
ለምን ለምን ለምን
ለምን አንቺን ብቻ ለምን ከሰው መርጦ
የሚያርበተብተኝ
የሚያብሰከስከኝ ከሌላው አብልጦ
                        ....ማለቱን ካበዛሁ

               አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

አወ ናፍቀሽኛል አልክድም ወድቄ
ዝም ብለሽ ነይልኝ አታብዢ ጥያቄ
መልሴ ሁኝኝና
ከወደቅኩበት ጥግ ነይ ፈልገሽ አንሺኝ
መራቅሽ አሞኛል በመቅረብ ፈውሺኝ

አደራ......

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
ስንት ጊዜ ይፈጃል ምን ያህል አመታት
ስንት ሰዉ ይበቃል ትዝታን ለመርሳት

ምን የሚሉት ጂኒ ካንተ ጋር አሰረኝ
የትኛዉ መለኮት በፍቅርህ ጠፈረኝ

በየትኛዉ ጥበብ በየትኛዉ ዘዴ
በየትኛዉ ብልሀት አወከዉ የሆዴን

እንጃ................
ጊዜም መልሱ ጠፋበት መሰለኝ
ካንተ ጋር ይነጉዳል ጥያቄ እያጫረኝ

ስንት ዘመን ቀረኝ
ስንት እድሜ ይተርፈኝ
መቼ ያሳርፈኝ

ትዝታህ ጠቢቡ
ትዝታህ ብልሁ

ትዝታህ ብልጥ ወዳጅ
እያሳሳቀ ነዉ አብሮ ሚያሳቅቀኝ
እያጫወተ ነዉ እድሜዬን የቀጨኝ

ወይ እሱ ይተወኝ ወይ አንተ ደግመህ ና
ትዝታህን ዉሰድ እኔን መልስና።

ትዝታ ወልዴ


━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
💔 ልቤ ምን አጠፋ💔

እኔስ መስሎኝ ነበር  ካንጀት ያፍርከኝ
ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ
መውደዴን ነግሮህ  የሆዴን አውጥቼ
መዋል ማድር አልችል  ካንተ ተለይቼ
ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ
ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ?


ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ
ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ
ያንተው ህመምተኛ  ባይተዋር ሆኛለሁ
ህመምተኛ አደርኸኝ ለማን እሆናለሁ


እንግዲህ  ኑሮዬ በዱር በገደል ነው
ከሰው መኖር አልችል  ልቤ ካንተ ጋር ነው
አልበላም  አልጠጣም  ልድረቅ ልሁን እንጨት
የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣



አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣
ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ
ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል
የጊዜው  ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል
ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ  ይፈርዳል 💔


━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
አትሂድብኝ

አንተን ሳገኝ . . .

ከሠማዩ ጥጋት ይመስለኛል የቆምኩ
ከሁሉ በልጬ ዓለምን የጨበጥኩ፤
እኔ ፀሐይ ሆኜ አንተ ውብ ጨረቃ
ሌት ከቀን ስንቦርቅ ህይወታችን ደምቃ፤
ከዛም ይሰማኛል በልቤ ደስታ
በሐሴት መሞላት የፍቅር እርካታ፤

አንተን ሳጣ . . .

ከባህር ጠለል ስር ልክ እንደተጣልኩኝ
መኖር ያቅተኛል ሁሉም ጨላልሞብኝ፤
እንባዬ ገንፍሎ በዝቶብኝ ትካዜ
እሸበራለሁኝ በናፍቆት አባዜ፤
ወዘናዬ ጠፍቶ ውበቴ ተገፎ
በአጥንቴ እቀራለሁ ስጋዬ ተራግፎ      

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

😍😍😍ደስ ትይኛለሽ😀😀😀
""""""""'"''"'""""
ያቺ የመጀመሪያ ቀን ገና ሳይሽ ውዴ፣
ሳላስበው መተሽ ስትቆሚ ከፊቴ፣
ደስ ብለሽኛል ልንገርሽ በሞቴ፣
........
አይኖችሽ ተኩለው ልብ ይሰርቃሉ፣
አፍንጫሽ ቀጥ ብሎ ሌላ ያስንቃሉ ፣
ውበት ሰጥተውሻል ጥርስሽ መደርደሩ፣
ፈገግ ስትይ ዲንፕልሽ ማማሩ፣
ይሄ ሁሉ ነገር አሁን የማደንቀው፣
እውነቱን ስነግርሽ ደስ ስላልሽኝ ነው፣
ፀጉርሽን ስትለቂው እጅግ ያምርብሻል፣
አጠር ያለም ቢሆን ሌላው ቀንቶብሻል፣
አተኩሬ ሳየው የአንገትሽን ውበት፣
ጌጣጌጡ ይበልጥ ሆነውሻል ድምቀት፣
ውዴ ስለውበትሽ ብዙ ነገር ምለው፣
ደስ ትይኛለሽ ምክንያቱ ይሄ ነው፣
........ .
ወገብሽ መቅጠኑ ቀሚስ ሳመሩ፣
የዳሌሽ ስፋቱ አቤት ማስገረሙ፣
ቁመትሽ ሎጋ ነው ሰንደቅ ያሰቅላል፣
ይሄ ሁሉ ውበት ምን ይሰራልሻል፣
ሁለት ብትሆኚ ይበልጥ ያምርብሻል፣
እኔ ግን እውነቱን ስነግርሽ፣
የእግዜርን ጥበብ ማድነቄ ነው ስልሽ እመኚኝ እባክሽ፣
...........
ውበትሽ ልዮ ነው እርከን የሌለበት፣
ደም ግባትሽ ይስባል ምንም አይወጣለት፣
ይበልጥ ለግሶሻል ውበት ላንቺ አብልጦ፣
አብዝቶ ሰቶሻል እግዜር ላንቺ አድልቶ፣
ግን እኔ.................
ይሄ ሁሉ ነገር አሁን የምነግርሽ፣
ደስ ስላልሽኝ ነው ፍቅር እንዳይመስልሽ፤
😜😜👍አለቀ😆😆👌

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
❤️💙💕💕❤️💛

አፍቅሬሽ ከልቤ ያኔ ስጠይቅሽ
አሻፈረኝ ያልሽው ብር የለህም ብለሽ
እድሜ ላንቺ ውዴ አሁን ብር ይዣለው
አሁን ስንት ገባሽ ይሀው ልገዛሽ ነው..

💘💘❤️‍🔥❤️‍🔥💝💝❣️❤️‍🩹🤍

-------------------------------------------
@getemi
@getemi
@getemi
♡ ㅤ  ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲            
ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ  ˢʰᵃʳᵉ
----------------------------------------