ግጥም ፍለጋ እና ሌሎችም...
223 subscribers
3 photos
12 links
በዚህ ቻናል እጅግ ደስ ደስ የሚሉ ግጥሞች ፣ አስተማሪ ፅሁፎች ፣ ጥቅሶች ፣ አዝናኝ ፎቶዎች እና የመዝናኛ ጥያቄዎች ከአስደሳች ሽልማቶች ጋር ያገኛሉ

ግጥሞች
ፎቶዎታች
አስታማሪ ፅሁፎች ካሎት በ @wendeTheII ያድርሱኝ
Download Telegram
Forwarded from Liul-Z-ማርያም
➤ሰው_አለበት_ልቤ😍😍


ገጣሚ ሲሳይ አሰፋ/የኔታ


🗣አንባቢ Santaye ፪
(@Santuka)

ትዝ አለህ የኔ ባል😘
ከዋክብት ሲወጡ ሰአት ለኛ አይመርጡም
ዛሬ ግን ከፍቷቸው በሰአት አሎጡም😔
ብቻዬን ያላንተ አይተውኝ ስቆዝም
ገብቷቸው ነው መሰል አይተውኝ አሉ ዝም

💔💔😍

Join us👇👇👇👇
@Axelym
@Axelym
@Axelym
የጥበብ አይኖች
መካሪ ሀሳቦች ጥበብ ናቸው
የፈልጉት ሀሳብ በፈለጉት መንገድ
እዚህ ይገኛል ።ሀሳበዎን ለማካፈል በዘህ ሊንክ
ይጠቀሙ @sam2127
https://t.me/TIBEBnegni
ልጠብቅሽ ፈለኩ

መምጣት አለመምጣት
ሁለት ምርጫ ኑሮሽ፡
አንደኛውን መርጠሽ
ሌላውን ስትሸሽ፡
ፈለኩ.....ቃልሽን መወሰን፡
ሀሳብሽን ማስከን፡
አለመምጣት ይውደቅ
መምጣት እንዲፀድቅ፡
ልክ እንደ ፈጣሪሽ
መምጣትሽን ላርቅቅ፡
ወሳኝም አይጠፋም
ተቀባይ እንደዛው፡
በሀሳብ ቢደናቀር
የሰው ሀሳብ ከሰው፡
ይሉኝታ ቢከፈን
የሀሳብ ጎዶሎ እቃ፡
ጉዳት ያመጣ እንጂ
የመመራት እጣ
አያስተነፍስም የመወሰን ሲቃ፡
በይ መምጣትሽም ይቅር
ተፈለግሽም ቅሪ፡
ባትመጪ እንኳን ከቶ
አደለሁም'ና የጥበቃ ፈሪ፡
የመምጣትሽን ቃል
ውሳኔሽን ጠበኩ፡
ባትመጪ እንኳን ከቶ
ልጠብቅሽ ፈለኩ።

ሚኪ
Forwarded from Liul-Z-ማርያም
🚶‍♂ሂድ እንዳትመለስ🙅‍♀



Santa_¥e

ከሄድክ አትመለስ ሀዘኔ ላንተው ነው😒
ሁሉንም አይተኸው ሁሉንም ጠግበኸው
ደስታ ሲርቅህ....
ከመስጠቱ ሲሰንፍ ሲሰበሰብ እጅህ
ያጣህ ለት ሲክድህ ያመንከው ወዳጅህ🤔

...

ለማንኛውም አስተያየት( @Santuka )😍


@Axelym
@Axelym
@Axelym
በላይ በቀለ ወያ
.
ገላሽ ገላ አይመርጥም ፣ ከሁሉ ይጋደማል
ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል
ከሴት ክብርሽ ይልቅ ፣ ስሜትሽ ይቀድማል።
።።።
ነግሬሽ ነበረ፡፡
ጭን ከሰማይ ቢገዝፍ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል
ምን ተራራ ቢመስል...
ጡትም አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡
ነግሬሽ ነበረ....
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯ የአምላክ ነው ፣ እንደ እናት ስታስብ!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ክብረቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ.
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
።።።።።
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
ሴት ክብሯን ስታጣ ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
።።።።
ነግሬሽ ነበረ
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ስሜት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።
።።።
ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።
።።።
ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይተኛታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!

ለሌሎች አሪፍ ግጥሞች ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇

@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
ለምን አስፈለገ??🤔🤔🤔

SantaYe
......&......
🎤Santa¥e

😍😍😍😜
.
ብሩህ ውብ አይኖችህ እኔኑ እያስተዋሉ
የመጀመሪያህ መሆኔን ሌሎች እንደሌሉ
ስትነግረኝ አምኜህ ልቤ ራሴን ታርቆት
ውሸት እንደምጠላ እንደማቶድ ስርቆት......


07/07/2012

#Really_I_want_to_hear_his_answer
(whyyy?)

@Axelym
@Axelym
@Axelym
ፀሐይ ያሸንፋል
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ተይ ይነጋል ስልሽ ፣ አይነጋም ብለሽኝ
በጨለማዬ ላይ ፣ ጨለማ ሆነሽኝ
እንደተለየሽኝ
የምኖርለትን ፣ አንድ ምክንያት ሳጣ
ተስፋዬ ተሟጣ
ወይ ታንቄ ልሞት ፣ ወይ መርዝ ልጠጣ
ወይ መርዝ ልገዛ ፣ ወይ ገመድ ላመጣ
ከቤት እንደወጣሁ ፣ በሀገር ፀሐይ ወጣ ።
ጨለማ ተነነ ፣ ፅልመት ረገፈ
ጊዜ ተአምረኛው
እርግብና እባብ ፣ እያስተቃቀፈ
ያሳየኝ ጀመረ ፣ መኖር እስኪያሳሳኝ
ተአምር ስመለከት
ሞቴ ተዘነጋኝ ፣ መሔድሽ ተረሳኝ።
።።።
ተይ ይነጋል ስልሽ ፣ አይነጋም ብለሽኝ
በጨለማዬ ላይ ፣ ጨለማ አልብሰሽኝ
ተስፋ አስቆርጠሽኝ
እንደተለየሽኝ
ሰማይና ምድሩ ፣ ተሞልቶ በተስፋ
ተስፋ የቆረጠ
ድምፁን ሚያሰማበት ፣ አደባባይ ጠፋ
የተስፋ መፈክር
የለውጥ መፈክር
የሚያሰሙ ህዝቦች ፣ ባደባባይ ሞልተው
መንገዶች በሙሉ ፣ በተስፋ ተዘግተው
ጊዜ ተአምረኛው
አይሆንም ያልሽውን ፣ ሲሆን እያሳየኝ
ለህይወት እስክጓጓ ፣ ከሞት ሊያዘገየኝ
በተስፋ አነሳኝ
መሔድሽ ተረሳኝ።
።።።።
ተይ ይነጋል ስልሽ ፣ አይነጋም ብለሽኝ
በጨለመ ቀን ላይ ፣ ፅልመት አልብሰሽኝ
ስትሔጂ ጥለሽኝ
በሀገር ፀሐይ ወጣ ፣ ፅልመቶች ጠፉ
አይሆኑም ያልሻቸው ፣ እየሆኑ አለፉ
በጎች ከተኩላ ጋር ፣ አብረው ተሰማሩ
የታወሩ አህዮች
በጅቦች ተመርተው ፣ መንገድ ተሻገሩ
ታምርና ትንግርት ፣ በሀገሩ ገነነ
አሸባሪ ያሉት ፣ አሻጋሪ ሆነ
ጊዜ ተአምረኛው
ከቶ አይነጋም ስትይ ፣ ሺህ ፀሀይ ታቅፎ
ከባንዲራው መሀል
ያሉትን ኮከቦች ፣ ከላዩ አራግፎ
በፀሐዮች ተካ
ይገርማል አንችዬ
ፀሐይ ስትወጣ ፣ ኮከብ የለም ለካ።
ለካንስ ለካንስ
ፀሐይን ለማያውቅ ፣ ኮከብ ነው ፀሐዩ
ለካንስ ለካንስ
ፀሐይ የጠፋበት ፣ ኮከብ ነው ወካዩ።
።።
ብቻ ምን አለፋሽ
አይነጋም ብለሽኝ ፣ ከሔድሽ በኋላ
የናፈቀን ፀሐይ ፣ እንደአሸን ፈላ
እንደሾላ ፍሬ ፣ ብርሐን ረገፈ
መንጋቱን ሳልነግርሽ
ተአምር እያየሁ
መሔድሽ ተረስቶኝ ፣ ብዙ ቀን አለፈ።
።።።
እርግጥ ነው
እውነት ነው
ዛሬም ባደባባይ ፣ ሰዎች ይሞታሉ
ሰው ባልሆኑ ሰዎች ፣ እየተገደሉ።
ነገር ግን ነገር ግን
በኗሩ ልብ ውስጥ ፣ ሟች አለ በፀጋ
አንዳንድ ሰው አለ
እራሱን ሚያጨልም ፣ ሀገር እንዲነጋ።
(መስዋትነት ነው ፣ የብርሐን ዋጋ)
።።።።
እርግጥ ነው
እውነት ነው
መብራትና ውሐ ፣ አሁንም ይጠፋል
ነገር ግን
ነገር ግን
ቀን የወጣ ፀሐይ ፣ መሽቶም ያሸንፋል።
ውሃ ባትኖርም
እድፍ አልያዘንም ፣ የለብንም ድካም
የፍቅርን ያህል
አያነፃም ውሐ ፣ ጥም ቆርጦ አያረካም።

ለሌሎች እጅግ ደስ የሚሉ ግጥሞች ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇
@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII

@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII

@getemTheII
@getemTheII
@getemTheII
እኛነታችንን በደንብ አናውቀውም፡ ግን እኛ እኔ በሚል አጥር ውስጥ ተተብትበናል። መኖር እንመኛለን ግን የሌላው አለመኖር አያሳስበንም፡ መራብ አንፈልግም የሌሎች እርሀብ ግን አያመንም፡ ሰላም እንፈልጋለን ግን የሌሎች ሰላም እናናጋለን፡ መደሰት እንወዳለን
ግን ሌሎች እንዲያለቅሱ ምክኒያቶች ነን። በእውነት ምኑም ነገር አልገባንም፡ ብኩኖች ብቻ ነን ፡ ሸክላነታችን ያልገባን ፡ ነገን ለመኖር ዋስትና የሌለን ከንቱዎች፡ አፈርን ካፈር ለመለየት የምንዳክር ቂሎች ፡
ስጋችን የተለቀ ፣አስተሳሰባችን ያልታረቀ ፣ አካሄዳችን እና ምግባራችን የተናቀ ምስቅልቅሎች፡ ምኑም ነገር አልገባንም። ለክብርና ለዝና ፡ ለሀብትና አድሮ አመድ ለሚሆን ስጋችን ባሪያዎች የሆንን፤ የምንፈልገው አይገባንም ፡ የሚያስፈልገን አይታየንም፡ የውስጣችንን ባዶነት በጩህትና ባለባበስ ለመሸፈን የምንዋትት አሳዛኞች፡ ከፈጣሪ ትዛዝ ይልቅ የፍላጎታችን ባሪያወች ፡ ከፍርቅር ይልቅ የጥላቻ ፈረሶች ፡ የሰውነት ክብራችንን ያጣን፣ ጥጋብ ምንሆነውን ያሳጣን ፣ ከቁጣው መቅሰፍት ያልወጣን
ጅሎች ሆነናል ፡፡ የምንናገረውን አናቅም፡ የምናምነውን እሱን አንሰማውም፡ የቃል ሰዎች ብቻ ነን፡ ፡
ሀጢታችን በፊታችን የተገለጠ ነው፡ ግን ክብራችን ይመስለናል ፡፡ እምናደርገውን አናስተውልም ፣ እየሆነ ያለው ሁሉ አይገባንም፡፡ የፈጣሪ እዳ አለብን ፡ እጃችን ባዶ ነው ፡ ለዛውም የተጨማለቀ ። አልገባንም ሀጢያታችን በዝቷል ፡ ውጤቱንም እያየነው ነው ፡፡ ከሩጫችን ረጋ እንበል፣እናስተውል ፣እንመለስ፣ ሰው እንሁን ፣ አስተሳሰባችንን ከሰውነት ሚዛን አናስወጣው ፡፡ አልረፈደም እንፀልይ ፡ የፈጠረን አምላክ ለይቅርታ የታመነ ነው።


ሰላም፣ ፍቅር፣ ጤንነት ፡ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን !

Samuel Adane

❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
****ፍፃሜዉ****

የሚሽከረከሩ አለምን በገንዘብ
አድምቀው ያበዙ ተፈጥሮን በጥበብ ፣
-
ያገር ተወካዮች የአለማት መሪ ፣
ጎዳና የሚኖር በልቶ ፍርፋሪ ፣
-
ኑሮ ያቆሰለው ያገር ወንደላጤ፣
የተጎሳቆለ ምስኪን የኔ ቢጤ ፣
-
ጠቢብ ስአሊያን ድንቅ ሙዚቀኛ ፣
ሽጋ መልከ መልካም ታዋቂ ዝነኛ ፣
-
የኔ አይነት አመዳም ባሪያ መልከ ጥፉ ፣
እውቅ ባለሀብቶች
ሚሊዮን ተርቦ ቢሊዮን ያቀፉ ፣
አንቱ የተባሉ በስም የገዘፉ ፣
ይኖራሉ በአለም እንዲህ ተለያይተው ፣
ምድርና ሰማይ ቤታቸውን ሰርተው ።
-
ይሄ ሁሉ አዳም አንድ ሆኖ ደሙ ፣
ስጋው አፈር ሲለብስ
ሲለይ ከአለሙ ፣
መአረጉ ቀርቶ
ሁሉም በአንድ ላይ ሬሳ ነው ስሙ ።

ሳሙኤል አዳነ
@Sam2127

🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
ትዝብት

በመዋደድ መንፈስ
ስቀን የኖርናቸው፡ ውብ ቀኖች አለፉ
ስንስቅ የሳቁልን
አጃቢዎቻችን ከጎናችን ጠፉ
አንችም ጥለሽኝ ሄድሽ
ሥሌት ነው መንገድሽ፡ የልብሽ ላይ ቁልፉ
ትዝታ ቀሪ ነው
ቃል ያስተ ሳሰረው
ቀን ቆጥሮ ከሄደ፡ ትዝብት ነው ትርፉ

ሳሙኤል አዳነ
@sam2127

❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
ንዴት😒....እልህ🤨....ናፍቆት🙂


ምንም ያህል ንሮ_እልህና ንዴት
ደርሶ ቢያላውሰው🤨
ከራስ ስስት በላይ_ነፍስ ጥግ ድረስ
ያፈቀሩትን ሰው😍
ከቶ አለመናፈቅ የሚችለው ማነው?

ገጣሚ እዩኤል ደርብ

🎤 @santuka
...

ምክንያቱም ፍቅሬ
በፍቅር መንገድ ላይ እኔ ራሴን ሳውቀው
የታገለኝ ነበር ከጀግንነት አንሶ
ከስሬ ሚወድቀው😊

🤔እንዴት ለመረታት እኔው ተፋልሜ
ራሴን ጣልኩልህ
ከሚል ጥያቄ ስር ተወላጅ ዜማ ነው
የሚሰማኝ እልህ🙄

@Axelym
@Axelym
@Axelym