ግጥም ብቻ 📘
68.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
172 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
" አትቆርጥም "

ብቸኝነት ይብቃህ ሂድ ካንዷ ተጠጋ
ላንተ ዓይነቱ ፈጥሯል ቆንጆ ጉብል ሸጋ
ብሎ የጠቆመኝ
ድፍረቱን የሰጠኝ
የተኛውን ልቤ ቀስቅሶት ሲጉላላ
አትቆርጥም ይለኛል አዝግኖኝ ከኋላ ።

አ/ሀኪም
@venue13
@getem
@getem
ያልተፃፈበት ወረቀት
(መነሻ ሃሳብ Robert Frost The Road not taken )
.
ሁለት ወረቀቶች
በድንኳን መዝገቤ፤ አትሮንሴ ላይ ያኖርኩ
አንዲት ብዕር ስዬ
በመቋሚያ ድጋፍ፤ መቅረዝ ለኩሼ ቆምኩ፡፡
አንዱ ላይ አፈጠጥኩ፤ እስከ ግርጌ ህዳጉ
ሌላውንም አየሁ
እድል እኩል ሲያደርግ፤ የማማረጥ ወጉ፡፡
.
ቀዳሚው ባዶ ነጭ
ያልተረጋገጠ፤ በብዕር ጫፍ አርማ
ሁለተኛው ክትቡ
የተዥጎረጎረ፤ በስንክሳር ፊርማ፡፡
.
እኒህ ወረቀቶች፤
አትሮንሴ ላይ ያሉ፤ በመኖሬ ድንኳን
በዛሬው አቋቋም
አንዱን ለሌላ ቀን፤ ባስቀምጠው እንኳን
ሁለቱም ያው ናቸው!!
የተፃፈበቱ
ነጭ ጥንተ ስራው፤ የነጠፈ ሽሉ
ያልተፃፈበት ላይ
ብዕሬ ቢጓዝበት፤ ይመሳሰላሉ፡፡
.
መጨረሻቸው አንድ፤ መምረጡ ሲያስቸግር
ከመንታ መንገዶች
ባንደኛው ላይ እንዲያልፍ፤ የተራማጅ እግር
ኮቴዎች ላጥናና
በመረዳት ልቁም፤ መድረሻዬን ልስራ?
ወይስ ባዲስ ጥርጊያ
ፈለጌ ላይ ላኑር፤ የግሮቼን አሻራ?
.
በዘመናት ልኬት
ትዝታው ሲተረክ፤ የደረስኩት ገድል
ልዩነት ቢፈጥርም
አዲሱን መርጬ፤ ቀዳሚን ስበድል
የውሳኔ ሃሳቤ
ከንባብ ተቀድቶ፤ ነባር ነው ካልኩት ገፅ
ባዶው ወረቀት ላይ
ተደርጎ ይፃፋል፤ የመጀመሪያ አንቀፅ፡፡
...


by
haileluel

@getem
@getem
////-------/////

የማይነጋ ሕልም ሳልም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የማይድን በሽታ ሳክም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም፡፡

#ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ጃን!!!ጥላ!!!!!


ሞኝ ሰው ሞኝ ነው፤
ቅዠቱን ሚያክም፤ ህልሙን አጠፋፍቶ፤
ጭጋግ ባየ ቁጥር፤
ጃንጥላየን ይላል፤
የህልሙን ደመኛ፤ አለቱን ረስቶ።


((( ጃ ኖ ))


ሸጋ ሸጊቱ ሀሙስ! !!!!

@balmbaras
@getem
*ዛሬ ልጠይቅሽ*
~~~...~~~

በግማሽ አካሌ ፊትሽ ቀርቤያለው
የጎደለውን ፓርት መሙላት ፈልጌያለው
የወሰድሽው ልቤን ብዬ መጥቻለው
ያንቺን ልብ ስጪኝ ወይ የኔን መልሺው
................. .......... .ልልሽ ወስኛለው
ሙሉ ሳልሆን መኖር በጣሙን ከብዶኛል
በጉድለት መዋሉ እጅጉን ደክሞኛል
ያላንቺ መወሰን በቃ እኔ አቅቶኛል
እና ዛሬ ወሰንኩ በድጋሚ ልቅረብ ፊትሽ
በተስፋ የተሞላ እጄን ልዘርጋልሽ
ዛሬ ለቫላንታይን እስኪ ልጠይቅሽ
በፍቅረኛሞች ቀን ፍቅርን ላቅርብልሽ...


((-ዮናታን አሰፋ))

ለቫለንታይን የተፃፈ

@getem
@getem
@yab1964
አበቦቼ ነገ የባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ( አያ ሙሌ ) የተወለደበት ቀን ነው የሱን ግጥሞች በሱ ዙሪያ የተፃፉ ነገሮችን ጀባ እያላችሁን.....👇👇👇

@balmbaras

@Lula_al_greeko


ዛሬና ነገን የሱን ስራዎች እያነበብን አያ ሙሌን እንዘክራለን🙏🙏
 ~~~~ሀገርሽ~~~~
ቀጠሮ መቃጠር ያንን ትልቅ ነገር እሱን እረስቼ፣
የመፈለግ ጉጉት የማግኘትን ድምፀት በልቤ ሰምቼ፣
ከኔነት ከተማ ከአንቺነት ሀገር አማካይ ላይ ያለ፣
የእኔ ሀገር ያልሆነ ያንቺም ያልተባለ፣
መቃጠሪያ የሚሆን ባዕድ ሀገር የሆነ፣
መፈለጌን ትቼ አንቺን ተከተልኩኝ ተስፋዬ መከነ፣
ስከተልሽ,,,,,,,,,,,ስከተልሽ፣
የእኔን መከተል ፍቀጂ አትፍቀጂ እሱን ሳልጠይቅሽ፣
መሄዴን መንጎዴን እሱን ብቻ እያየሁ ገባሁኝ ሀገርሽ፣
የሀገርሽ ስሙ "አንቺ" እንደሚባል ሰማሁኝ ሲያወሩ፣
የቀዬሽም ሰዎች ስምሽን ያነሱታል በዘፈን መዝሙሩ፣
ሳለ ስንት ጉዳይ ሳለ ስንት ነገር፣
ተከትሎ መግባት "አንቺ" ብሎ ሀገር፣
እናም ሀገርሽ ላይ ሰውን ሁሉ ንቆ ወደ ታች ማሳያ አለ ትልቅ ማማ፣
ዞር ሲባል ደሞ "አንቺ" ሀገር የሚል ያ ሰንደቅ አላማ፣
ሰንደቅ ዓላማው ላይ አንቺና ባዶ ምስል ቆመው ይታያሉ፣
አንቺን አንቺን ያሉ፣
መንጎድ መንጎድ ብቻ እንደተወደዱ በልባቸው ያመኑ፣
በዛ ምስል ፋንታ ሰርክ አንተ፣
ሰርክ እሱ ሰርክ እኔ እየተባባሉ፣
በባዶ ምስሉ ላይ ሚስት የናፈቃቸው ባሎች የሚባሉ፣
ተራቸውን ይዘው ወቅት እየጠበቁ ሁሌ ይተካካሉ፣
@yosef
@getem
@getem
አበቦቼ ነገ የባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ( አያ ሙሌ ) የተወለደበት ቀን ነው የሱን ግጥሞች በሱ ዙሪያ የተፃፉ ነገሮችን ጀባ እያላችሁን.....👇👇👇

@balmbaras

@Lula_al_greeko


ዛሬና ነገን የሱን ስራዎች እያነበብን አያ ሙሌን እንዘክራለን🙏🙏
...ንሳማ ጎበዝ ... ንሳ ተነስነስ ...
ከስፍርህ ጎለህ ከሰው አትነስ
ንሳማ ጎበዝ ... ንሳ አታደግድግ ...
ወገብን ጠበቅ ... ባንጀት ድርብ ድግ ...
እንኳን እቁቡ ... እድሩ ፈርሶ ...
የወላድ ማህፀን ... በዋይታ ታርሶ ...
አማንስ ቢሆን ... ለተቀመጠ ...
እያላመጠ ... እየገላመጠ ...
እየተርመጠመጠ ... እየተዳመጠ
እድሜውን ይፈጃል እንጂ በከንቱ ...
ማን ይለዋል አንቱ ...
ንሳማ ጎበዝ ... ንሳ ተነስነስ ...
ከስፍርህ ጎለህ ከሰው አትነስ!!!!!


((( ሙሉጌታ ተስፋዬ )))

@Balmbaras
@getem
እናት!!!!!!!!!!!!!!!!!!!



መንገደኛው ልጇ፤
መንገድ የገባሁ ቀን፤
እናቴ ስትሸኘኝ፤
እመየ ስትሸኘኝ፤ ራሴን አሻሽታ!!!!
እንደውሃ ሽታ!!!እንደውሃ ሽታ!!!!
ከመንገድ ላይ ቀረ፤ የያዘኝ በሽታ!!!!!

(((ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ))(


@Balmbaras
@getem
ድጋሚ ልሰበር
====//====
በፍቅር ታምሜ ገና ሳላገግም
የተሰበረውን ልቤንም ሳልገጥም
ምንም ሳላስበው ሌላ ሳላስቀድም
ወደሩቅም ሳልሄድ ወዴትም ሳልደክም
ደሞ ፍቅር ያዘኝ ካንዲት መልከመልካም
ልቤን ወስዳው ሄደች ያለምንም ጥቀም
የተሰበረው ልብም ገና ሳያገግም
መልሶ ሊሰበር በከንቱ ሊደክም
በተስፋ ሄደና አለ አልመለስም
አላመንኩም ነበር መጀመርያ ግዜ
ያለምንም መስፈርት እኔ አንቺን መውደዴ
ስላንቺ ያለ እረፍት ቀን ማታ ማሰቤ
አይንሽን ሳላየው ስቀር መናፈቄ
ግን ሲቆይ አወኩት ባንቺ መረታቴ
በመልካም ባህሪሽ እኔ መሸነፌ
በግሩም ጠረንሽ ፍፁም መማረኬ
ቆይቶ ነው የገባኝ ያላንቺ መጉደሌ
......እና የተረዳው እለታ.....
ልነግርሽ ወሰንኩ ልቤ እንደተረታ
በጣሙን ፈራሁ ፍፁም ልቤ መታ
በቃ ምን ልበልሽ ፍቅሬ ልክ አጣ
አይምሮዬ ዞረ ምለው ሁላ ጠፋ
በልቤ ያለውን የነገርኩሽ ለታ
ትንሽ ቀሎኝ ነበር የማታ የማታ
መልስሽ ግን ከበደኝ ለሊቱ ሲነጋ
ኩራት መስሎኝ ነበር ልክ መጀመርያ
ተስፋ ያለኝ መስሎኝ ቀኑ መሽቶ ነጋ
...................ግን....................
ተሳስቼ ነበር አንቺን መጠበቄ
የማገኝሽ መስሎኝ በሀሳብ መቅዘፌ
ፍቅረኛ ይኖረኛል ብዬ መደምደሜ
የምቶጂኝ መስሎኝ ፍፁም መባከኔ
............አልገመትኩም ነበር..........
አልገመትኩም ነበር ልቤ እንደሚሰበር
ያልተሻለው ጎኔ ከአልጋ እንደሚቀር...

((-ዮናታን አሰፋ))


@getem
@getem
@yab1964
ብርዕ – በደም ዕንባ / ሙሉጌታ ተስፋዬ




በኔው ‘ኔ ጥራና
በኔው ‘ኔ ጥራና
ባፅሜ ቀሰም ብርዕ
በህይወት ማቅለሚያው
ጠርቤ ስለቁጥ
የኑሮን ሽቁጥቁጥ
የራሴ ጉልቻ … አንገቴ አለ ዘምበል
የደም ወዜ ጠለል … እንባዬ አለ ከምበል
በሞት ሞት ጣረሞት … <በልቤ ልብ በል!>
ሥጋት አንድውጋት
ነፍሴን ሲሰንጋት
በቅኔ እንቆቅልሽ … ቁልቁል ተቆልፌ
በእምነት … እምም እመ-እዝነት
በህልም ዓለም ሽምጥ ግልቢያ ተሰልፌ
ለሥጋ ታርቄ
ለገላ መርቄ
እርቃኔን ወጥቼ – ግቤኔን አስጥቼ
የጎኔን ጨረስኩት – ሆዴን ስሸነግል
ለነገ ራሴ ስንቅ – ልቃንጣዬ አገልግል።
ካምና ከታች አምናው
የጉልበት የጤናው
ቢታይ ሁለንተናው – <ሁሉ> ሁለመናው
የልቤ ልብ በል – ለልቤ ሲጠናው
ብቻ ላይኔ ብቻ – ላይኔ ለብረቱ – ላይኔ ብቻ ቀናው!
ለታይታ ለዝናው …
በሰው ፊት በሸንጎ ለወግ ማ’ርግ ዝናው!!


አዎ! በኔው ‘ኔ ጥራና
በኔው ‘ኔ ብራና
በብርዔ ስለቁጥ
የኑሮን ሽቁጥቁጥ
ደም እንባ – ደም እንባ – እንበለ እንባ ደም
ሕይወት እንጉርጉሮ – በአትም አይታደም።


(ለሚንቁኝ – ለማያውቁኝ)
29/7/84


@balmbaras
@getem
ዛሬ ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ የተወለደበት ቀን ነው !!!!

የሱን ግጥሞች ቅኔዎች ስለሱ የተፃፈ ነገር ካላቹ እያካፈላችሁን @balmbaras እኛም ስለሱ የተፃፋ የሱን ግጥምና ቅኔዎች እያስነበብናቹ....ጁምኣን እሱን በመዘከር አናሳልፋለን አያ ሙሌን ለማያውቀው ሰው በዚህ አጋጣሚ በትንሹም ቢሆን ስለሱ የሆነ ነገር ያውቃል ብለን እናስባለን



አበቦቼ ሸጋ ጁምኣ !!!

@balmbaras
እ – ህ – ህ… ወ – ፍ – ዬ . . . ኡ – ሁ – ሁ… ወ
– ፊ – ቱ . . .
ከሚለው የአበበ ተካ ዘፈን ጋር ለአመታት የከረመው ፍቅሬ
ሰሞኑን አገርሽቶ (ምን እንደቀሰቀሰው ባይታወቅም)
እንደገና እንደ አዲስ ከወፍዬ ጋር እየዘመርኩ፣
እያፏጨሁ… አብሬያት አለሜን እየቀጨሁ… የግጥሙን
ርቀት… የጥበቡን ጥልቀት ሳብሰለስል… ፍቅርና ወፍ፣
ወፍና ጎጆ፣ ጎጆና ሰው፣ ሰውና እምነት፣ እምነትና
ተፈጥሮ፣ ተፈጥሮና ህይወት ምናምን እያልኩ ማደበላለቅ
ሲያምረኝ… ሲያመራምረኝና ሲመረምረኝ… ገጣሚው
ባይኔ ላይ ይዋልል ገባ… ስምም፣ ክብርም፣ ብርም
ተነፍጎት ያለፈው ሙሉጌታ ተስፋዬ… ሰላማዊ እረፍት
ሙሌዋዋዋ… በዚሁ ዋዋዋ ልበል እንጂ !
ድምጻዊ አበበ ተካ በአንድ ወቅት የሙዚቃውን ገበያ
የተቆጣጠረ… በቅንጣት ዝና የከበረ… ዘፈኖቹ
እንደጣፋጭ ቡና እየተደጋገሙ የተጣጣሙለት ምርጥ
ዘፋኝ እንደነበር የ1988ቱን የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል እና
የአቤን ሽልማት (እንዲሁም ለቅሶውን…) ማስታወስ
ብቻውን በቂ ነው፡፡ ቆይ ግን አቤ የት ገባ? በቃ
እልምምም?!… “ያ ሱዳን ፈናኒ” እያለ ቼቺኒያን
እንዳላቀናት እንዲህ ድምጹ ጥፍት?…. ኧረ አቤ አንተ
ያቀናሃት ቼቺኒያ ዛሬ ራሷን የቻለች አገር ሆና ምግብም፣
ጥበብም፣ ህይወትም፣ ሞትም እየተቸበቸበባት ነውና
እንዳቀናሃት ካለህበት መጥተህ አቃናት ብያለሁ
እግረመንገዴን . . .
እና እንደዚያ አቧራ ያጨሰ የነ ወፍዬ ዘፈን አልበም
መላው ግጥሞቹ (ከአንድ ዘፈን በስተቀር) የሙሌ
እንደሆኑ ሳስብ ያለዋዛ እንዳልተወደዱ ገባኝ… አበበ ተካ
ከዚህ አልበሙ በፊት የቀደመ አልበም ነበረው እምብዛም
አይታወቅም… እናም ለአበበ ዝና ሌሎች በርካታ ተጨማሪ
ተዛማጅ ጥበቦች ቢኖሩም ቅሉ የሙሌ ጣፋጭ ግጥም
የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ማንም አይክድም!
*
ማነው ደግሞ ያ ድሮ ጥርሰ ወርቅ የነበረው አሁን ግን
ጥርሱ ሃጫ በረዶ የሚመስለው ዘፋኝ?… ያ ነዋ የጥቁር
ውሃው ልጅ?… ታምራት ደስታ አትሉኝም!… ታምራት ደስታ
የቱ?… ብንባል ብዙዎቻችን ታምራት “ሃኪሜ ነሽ” ነዋ
ብለን እንደምንመልስ ጥርጥር የለኝም… ለምን ቢባል
ታምራትን ካለመታወቅ ወደ መታወቅ ከከተፋ ቤት ወደ
አደባባይ ይዛ የወጣች ዘፈን ሃኪሜ ነሽ ናትና !




♫ . . . ሐኪሜ ነሽ መድሃኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እመ እምነቴ
ሐኪሜ ነሽ መዳኒቴ
እኔ አዳም
ብሞት አንቺንስ አልከዳም . . . ♫


♫ . . . አንቺን የመሰለ ሌላ ሰው ቢኖርም
ላይን ይሞላል እንጂ ለነፍስ አይዘምርም
ጠረንሽን ለምጄ እንደ ናርዶስ ሽቶ
ሌሊቱ እንዴት ይንጋ ቀኑስ እንዴት መሽቶ . . . ♫


የዚህም ግጥም ጌታ የታሜ ባለውለታ አሁንም ሙሌ
ነውና ክብር ለሙሌ . . .


@balmbaras
@getem
♫ . . . አደራ ልጄን አደራ
ሆዴን ልጄን አደራ . . . ♫


የሚለውን የብጽአት ስዩም ዘፈን ያደመጠ፣ የወለደና እና
የከበደ ዘፈኑን ሲሰማ ወይም የብጽአትን በእንባ የተሞላ
አዘፋፈን ሲያይ ልጁን ብሎም እናቱን እያሰበ በፍቅር
እንደሚቃጠል ዘፈኑን ያደመጠ ቢፈርድ ይሻለኛል. . .


♫ . . . ወልደህ እየው ብሎ ወላጅ የመረቀው
ለልጅ ሲንሰፈሰፍ ያኔ ነው የሚያውቀው
እርብትብት ከንፈሩ ያንገቱ ስር ሽታ
ከሞትም ያድናል እንኳን ከበሽታ . . . ♫


♫ . . . ባልማዝና በእንቁ በከበረ ድንጋይ
አሽቆጥቁጬ አኑሬሽ በሆንኩሽ አገልጋይ
ምናለ ለእምዬ ውሃ ሸጬስ ባድር
ማን ውጪ እንዳይለኝ ካገርና ከእድር . . . ♫


ይህን የመሰለ መቼም ሊደመጥ የሚችል ዘፈን እንዲሁም
ሌሎች የአንድ ሙሉ አልበም የብጽአት ዘፈኖች የሙሌ
ናቸውና አሁንም ክብር ለሙሌ!… የፀደኒያ ገብረማርቆስ፣
የሃና ሸንቁጤ፣ የመሰረት ሌላም ሌላም… እያሉ መዘርዘር
ይቻላል…


እንደው ወፍዬ ኮርኩሮኝ አነሳሁት እንጂ እጅግ የበዙትን
የባለቅኔውን የዘፈን ግጥሞች እዚህ ዘርዝሬ
አልዘልቀውም… ምናልባት እየቆራረጥን በተለያየ ግዜ
መነካካት የቻልን እንደሆን እንጂ!… ግና የዚህ ሁሉ ጥበብ
ባለቤት የሆነ ታላቅ ሰው እንደምንምና እንደማንም
ተዘንግቶ ሲቀር ማየት በ’ርግጥ ያማል፡፡ ስንዱ አበበ
እጅግ የበዛ ክብርና ምስጋና ይግባትና የተወሰኑትን
ስራዎቹን ሰብስባ “የባለቅኔ ምህላ”ን አሳትማልናለች…
“ጉኖዬ” አክብሮታዊ ምስጋናዬ ባለሽበት ይድረስሽ…
ላሁኑ የዘፈን ስራዎቹ ላይ ብቻ ነኝና ስንዱ በመጽሐፉ −
ደብዳቤ ለ“ሲኦል”− ስትል ስለ ሙሌ ከጻፈችው ትንሽ
ልቆንጥር…

@Balmbaras
@getem
# የእብድ_ሰው_ፀሎት
.
አነስታይንም አለ ...
:
"ማሰብ የተሳነው፣ ያበደ ሰው ማለት
ግብሩ ተመሳሳይ፣ ሁሌም እለት ተለት።
ዘወትር ያንኑ ፣ ደጋግሞ... ደጋግሞ
የተለየ ውጤት ፣ የሚጠብቅ ቆሞ።"


እኔ ግን የዋሁ፣ ምክር የማልሰማው
እግዜሩን ልለምን፣ ወጥቼ ከማማው፣
የአነስታይንን ቃል፣ ጠቅሼ አስቀድሜ
አቤቱ እሷን ስጠኝ፣ አልኩት ደጋግሜ።
:
በወሩ አንቺን ሰጠኝ፣ ፅኑ እምነቴን አይቶ
አሊያም እልህ ይዞት፣ ሳይንቲስቱን ጠልቶ።
------------------------//------------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
*ግዜ ነው ስቃዩ*
=======//========
መታሰር መገረፍ አይደለም ስቃዩ
በቤት ውስጥ ታፍኖ ዘመን ማስቆጠሩ
በየቀኑ ሶስቴ ባለንጋ መላጡ
ያለምግብ ውሀ ቀናት መቆየቱ
አይደለም ስቃዩ
~~~~~~~~~~~~~~
አፍቅሮ ማጣትም አይደለም ስቃዩ
ልብ እየፈለገ ጨክኖ መራቁ
አእምሮ ያለረፍት ቀን ማታ ማሰቡ
ፍቅርን ለመናገር ሲጨነቅ ማደሩ
አይደለም ስቃዩ
~~~~~~~~~~~~~~~~
በህመም መንገላታቱም አይደለም ስቃዩ
በበሽታ ታሞ ብዙ ማቃሰቱ
እጅጉን ደካክሞ በአልጋ መውደቁ
እጥንት ተሰብሮ ጥርስ ማስነከሱ
አይደለም ስቃዩ
~~~~~~~~~~~~~~~
ቤተሰብ በሞት ማጣት አይደለም ስቃዩ
ፍፁሙን አምርሮ ደም እንባ ማልቀሱ
በሀዘን ተጎድቶ ልብ መሰበሩ
መለየትን ጠልቶ መቅረብን መፍራቱ
አይደለም ስቃዩ
~~~~~~~~~~~~~~~
ያቺ የታሰርንባት የተገረፍንባት
ያቺ ያፈቀርንባት እና ያጣንባት
ያቺ የታመምንባትና የቆሰልንባት
ያቺኛዋ ግዜ በሞት ያጣንባት
ያቺ ሰአት ያ ቀን ነው ስቃዩ
አዎ ግዜ ሲሄድ ነው ስቃዩ
ግዜው ሲነጉድ ነው ስቃዩ
ማያልፍ ሚመስለው ቀኑ ነው ቁስሉ
ሰአቱ ነው ህመሙ ግዜ ነው ስቃዩ::
~~~~~~~•••••••~~~~~~~~
*************


((-ዮናታን አሰፋ))



@getem
@getem
@yab1964
​​እናት +251-912-176-635 ወይዘሮ ሙሉ አብርሃ

ታማሚ +251-920-667-623 አማኑኤል ፍቃደ
0173072831300 ሙሉ አብርሃ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

+14692315220 ዳግማዊት ውጪ ላላችሁ ኢትዮጵያዊያን

መርዳት እንኳን ባንችል ሼር በማረግና ደዉሎ እግዜአብሄር ይማርክ ማለት ትልቅ ነገር ነው
“. . . ይህንን ይሁን ብዬ ጓዶቼን ፈትቼ፣ ህዝቤን አምኜ፣
ችሎታዬን ለዘፋኞች ልስጥ አልኩና ተነሳሁ፡፡ ገበያው
እጅግ የደራ ከመሆኑ የተነሳ እንኳን ሌላ ነገርሽን ከዓይንሽ
ላይ ኩልሽን ሊሰርቁሽ የሚችሉ ሰዎች የበዙበት ሆነ፡፡
ይህን ትልቅ የገበያ ስፍራ ለመቀላቀል ስንት አሳር
እንደቆጠርኩ ዛሬም ሳስበው ይዘገንነኛል፡፡ በቃ
የስልጣናቸው የመጨረሻ ዳር ድንበር አሁን ትዝ አለኝ!
“የኢኮኖሚው ባለቤት የፖለቲካውም ዋና ባለቤት”
እንደሆነ ሁሉ የስራው ባለቤቶች ነጋዴዎች ብቻ ሆኑ፡፡


. . . “እኔ እበላ − እኔ እበላ” እያሉ ከሚሻሙት ጋር
ለጨው ለበርበሬ፣ ለውሎ ላዳሩ እንኳ ብዬ አብሬያቸው
ለመቆየት አቃተኝ፡፡ ይልቅ ጠጋ ያሉኝ ጋር በማርያም
መንገድ፣ በማተብ በክርስትና ለየግል ተነጋግረን፣ ቀኑን
አሳምረን፣ ዱአ አድርገን፣ ተፈጥሮንና ፈጣሪን ሳይቀር
እያፋጠጥን አብረን ጎጆ ልንወጣ ሰርተን ፈረንካው ሲገኝ
አይኔን ለማየት እንኳ ይፀየፋሉ፡፡ አልፈው ተርፈው
ብኩርናዬን ሳይቀር እንድሸጥላቸው ሁሉ ጠየቁኝ፡፡


. . . ስሚ ʻንጂ አንድ ቀን “ያንተን የተለያዩ ዘፈኖች
መደዳውን ዛሬ አራት በኤፍ ኤም ሰማሁ ብለሽ” በልብሽ
ያጨበጨብሽልኝን ዕለት አስታውሼ ምን ትዝ አለኝ
መሰለሽ! ያወጣሁላቸው ስሞች! ታምራት ሃኪሜ ነሽ፣
መሰረት ጉምጉም፣ ፀደኒያ ገዴ፣ ብፅአት ገዳዬ፣ ሸህ
አብዱ ሃዋብስል ኧረ ስንቱን አድምቄዋለሁ አያ! ምንስ
ቢሆን ሙሉጌታ ተስፋዬ ወዲ ሀለቃይ! ተጋዳላይ ነኝ’ኮ! …
” (የባለቅኔ ምህላ፣ ገፅ 133)


እስቲ ደጋግመን እናንብበውና ከባለቅኔ ምህላ ጋር ደግሞ
እንመለሳለን… የቻላችሁ አንብቡትማ!… ዛሬም በርካታ
ሙሌዎች በዙሪያችን ይኖራሉና ክብር ለጥበበኞች. . .
ነጃ ይበለን እያልን በሃና ሸንቁጤ ዘፈን (በሙሌ ግጥም)
እንሰነባበት . . .


@balmbaras
@getem