"ወደድኩህ " ያልሽኝ ቀን
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሸኝቼሽ ስመለስ
ያልሽኝን እያሰብሁ ፣ አልፌው ሰፈሬን
አልፌው መንደሬን
ላልፋት ስል ሀገሬን
ድንበር ጠባቂዎች ፣ በሰደፍ ግንባሬን
ነርተው ዘረሩኝ ፣ ከሀሳቤ አነቁኝ
ወደት ነው ምትሔደው ፣ በማለት ጠየቁኝ
ወዴት ልበላቸው
ተደቅነውብኝ ፣ ፍርጃና ጠብመንጃ
ያልሽኝ ተዘነጋኝ ፣ ምን እንዳልሽኝ እንጃ
።።።።
ብቻ ሰምቻለሁ
ብቻ ግን አውቃለሁ
" ወደ ተለየ አለም
ፍቅር ይወስዳል" ይላል ፣ ያፍቃሪ አፍ መፍቻ
እዚ እንዳይሆን ብቻ 😂
@getem
@getem
@lula_al_greeko
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሸኝቼሽ ስመለስ
ያልሽኝን እያሰብሁ ፣ አልፌው ሰፈሬን
አልፌው መንደሬን
ላልፋት ስል ሀገሬን
ድንበር ጠባቂዎች ፣ በሰደፍ ግንባሬን
ነርተው ዘረሩኝ ፣ ከሀሳቤ አነቁኝ
ወደት ነው ምትሔደው ፣ በማለት ጠየቁኝ
ወዴት ልበላቸው
ተደቅነውብኝ ፣ ፍርጃና ጠብመንጃ
ያልሽኝ ተዘነጋኝ ፣ ምን እንዳልሽኝ እንጃ
።።።።
ብቻ ሰምቻለሁ
ብቻ ግን አውቃለሁ
" ወደ ተለየ አለም
ፍቅር ይወስዳል" ይላል ፣ ያፍቃሪ አፍ መፍቻ
እዚ እንዳይሆን ብቻ 😂
@getem
@getem
@lula_al_greeko
+++ያለ ፍቅር ባዶ+++
እኛ ምንኖርባት ይህች ቧልተኛ አለም፣
ከፍቅር በስተቀር የሚበጀን የለም፣
ብጥብጥ ረብሻ፣
ሰው ሲጠቀምበት ሰላም ማደፍረሻ፣
ሰው ከሰው ሲባላ ሲቧጨቅ ሲባጠስ፣
ክብር ሚገኝ መስሎት ሰላም በማደፍረስ፣
ፍቅርን ረግጠው በጥላቻ ሊያልፉ፣
ዘር በሚሉት ሰበብ ሰውን እየገፋ፣
ወንድሙ ተመቶ ወድቆ እያየ ሰው፣
እህቱ ተደፍራ ቆሞ የሚስቀው፣
የሰው መሰረቱ ፍቅር የቱ ጋር ነው?
ሰውነቱን ረስቶ ለሰው ማሰብ ትቶ፣
ያለውን በመተው የሰው ተመኝቶ፣
ወገኑን ሲያጠቃ ከምኞት ተጋብቶ፣
እንዲሁም አንዳንዱ በበቀል ተሞልቶ፣
እህቱን ይደፍራል ወንድሙን ይገላል፣
በእብሪት ተሞልቶ ከፍቅር ተጣልቶ፣
ሀገርም ከሀገራት እየተቧጨቁ፣
በአሜሪካ ዛቻ በነ ራሺያ ዘመቻ
ሰው እያሳቀቁ፣
ጥላቻን አፈሩ ፍቅርን እያራቁ፣
እንግዲህ ወዳጄ አለም ተበላሸች፣
ፍቅርን አጥፍታ ጥላቻ አነገሰች፣
ሰውን አለያይታ በዘር ከፋፈለች፣
በዘሮቹ መሀል ጥላቻን ጠብ አርጋ ህዝብን አጋደለች፣
ይህች አለም ከንቱ ያለ ፍቅር ባዶ፣
ይህው ህዝብ አለቀ ነዶ እንደ ማገዶ።
//ነብያት ወንድወሰን //
@getem
@getem
እኛ ምንኖርባት ይህች ቧልተኛ አለም፣
ከፍቅር በስተቀር የሚበጀን የለም፣
ብጥብጥ ረብሻ፣
ሰው ሲጠቀምበት ሰላም ማደፍረሻ፣
ሰው ከሰው ሲባላ ሲቧጨቅ ሲባጠስ፣
ክብር ሚገኝ መስሎት ሰላም በማደፍረስ፣
ፍቅርን ረግጠው በጥላቻ ሊያልፉ፣
ዘር በሚሉት ሰበብ ሰውን እየገፋ፣
ወንድሙ ተመቶ ወድቆ እያየ ሰው፣
እህቱ ተደፍራ ቆሞ የሚስቀው፣
የሰው መሰረቱ ፍቅር የቱ ጋር ነው?
ሰውነቱን ረስቶ ለሰው ማሰብ ትቶ፣
ያለውን በመተው የሰው ተመኝቶ፣
ወገኑን ሲያጠቃ ከምኞት ተጋብቶ፣
እንዲሁም አንዳንዱ በበቀል ተሞልቶ፣
እህቱን ይደፍራል ወንድሙን ይገላል፣
በእብሪት ተሞልቶ ከፍቅር ተጣልቶ፣
ሀገርም ከሀገራት እየተቧጨቁ፣
በአሜሪካ ዛቻ በነ ራሺያ ዘመቻ
ሰው እያሳቀቁ፣
ጥላቻን አፈሩ ፍቅርን እያራቁ፣
እንግዲህ ወዳጄ አለም ተበላሸች፣
ፍቅርን አጥፍታ ጥላቻ አነገሰች፣
ሰውን አለያይታ በዘር ከፋፈለች፣
በዘሮቹ መሀል ጥላቻን ጠብ አርጋ ህዝብን አጋደለች፣
ይህች አለም ከንቱ ያለ ፍቅር ባዶ፣
ይህው ህዝብ አለቀ ነዶ እንደ ማገዶ።
//ነብያት ወንድወሰን //
@getem
@getem
እገጥማለሁ እንጂ....
ግጥም እገጥማለሁ፤
ነገር እገጥማለሁ፤
ግጣም እገጥማለሁ፤
....እገጣጥማለሁ.....
ከዚህ ወድያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ።
((( ጃ ኖ )))
@Balmbaras
@getem
ግጥም እገጥማለሁ፤
ነገር እገጥማለሁ፤
ግጣም እገጥማለሁ፤
....እገጣጥማለሁ.....
ከዚህ ወድያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ።
((( ጃ ኖ )))
@Balmbaras
@getem
ድምፅህ መረዋ ነው ስራህ የማይረሳ
ስሜትን ኮርኩሮ ከወንበር ሚያስነሳ
#ካንቺ_አይበልጥም.......
ብለህ ስታዜም ስትል #ሰሊናዬ .......
ስንቱን ሰው ላፅናናው ስንቱን አባብዬ
በመሄድህ ዜና ስንቱ ሰው ደቀቀ
ስንቱ ሐዘን በላው ስንቱ ሰው ደረቀ
እኔም ደንግጫለሁ አንጀቴ ታጠፈ
ለህመሜ መግለጫ ዕንባዬ ተረፈ
#Rest_In_peace_ታሜ
@Getem
ስሜትን ኮርኩሮ ከወንበር ሚያስነሳ
#ካንቺ_አይበልጥም.......
ብለህ ስታዜም ስትል #ሰሊናዬ .......
ስንቱን ሰው ላፅናናው ስንቱን አባብዬ
በመሄድህ ዜና ስንቱ ሰው ደቀቀ
ስንቱ ሐዘን በላው ስንቱ ሰው ደረቀ
እኔም ደንግጫለሁ አንጀቴ ታጠፈ
ለህመሜ መግለጫ ዕንባዬ ተረፈ
#Rest_In_peace_ታሜ
@Getem
ሰው እያለ አጠገባችን ፤
መልካም ስሙን ፣ መጥራት ሲያመን
<< ሰው ካልሞተ ፣ ወይ ካልሄደ
አይነሳም >> እንላለን።
እንዲህ እያልን ፣
አበባውን ቀጥፈን ጥለን
አበባ እናስቀምጣለን።
((( ነብይ መኮንን )))
@balambaras
@getem
መልካም ስሙን ፣ መጥራት ሲያመን
<< ሰው ካልሞተ ፣ ወይ ካልሄደ
አይነሳም >> እንላለን።
እንዲህ እያልን ፣
አበባውን ቀጥፈን ጥለን
አበባ እናስቀምጣለን።
((( ነብይ መኮንን )))
@balambaras
@getem
ሞት አያምም!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
………………………………
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለ
መኖር እንጂ የበደለ
መኖር እንጂ ፣ ያቆሰለ
ምት አያምም ከገደለ!!!
@lula_al_greeko
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
………………………………
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለ
መኖር እንጂ የበደለ
መኖር እንጂ ፣ ያቆሰለ
ምት አያምም ከገደለ!!!
@lula_al_greeko
@getem
@getem
"አዎ ነኝ"
የችግር አለንጋ አካሌን ባያነፍር
ፈገግታዬ ጠፍቶ ለፅልመት ባያብር
.
.
ጉልበቴን አቅፌ አንገቴን ባልደፋ
ብሶቴን ባክመው በምናልባት ተስፋ
ደንታ ቢስ ነች አሉ ማሰብ የተሳናት
ሰው አድርጎ ፈጥሮ ቸልታ የሞላት
.
.
አዎ ደንታ ቢስ ነኝ።
የመከራ ጥይት በላዬ ቢዘንብም
አያሌ ፈተና ፊቴ ቢደንቀም
አንድ ላይ ተባብሮ ዙሪያዬን ቢከብም
.
ፍፁም እጅ አልሰጥም
አዎ እጅ አልሰጥም
መኖርም አንዴ ነው መሞትም አንዴ ነው
የፈተና ድልድይ ማለፍያው ፅናት ነው
ብለህ ንገራቸው
ምትወጥን በልኩ ነፍሷን ሳታሳርር
መንገድ በሌለበት መንገድ ምትፈጥር
ተስፋ ባልታየበት ተስፋ ምታዋቅር ህይወትን በጥበብ አቅላ ምትኖር
ነች ብለህ አስረዳቸው ።
.
.
አለም ዋዣቂ ናት ግራ ሆነች ሲሉ የምትገኝ በቀኝ
ደርሼ ላልይዛት የትካዜ ሾተል ለምን ይሸንቁረኝ?
.
.
ችግር የሚገፋው እራስን በመግደል ከሆነ ብይኑ
.
አዎ ደንታ ቢስ ነኝ
ማሰብ የተሳነኝ
.
.
በሀሳብ ትካዜ ናላዬን ባዞርም
በዋይታ በለቅሶ አይኔን ባሳዝንም
አልፌ አልወጣ ከተሾመው አጥር
ፈጣሪ በቃሉ የፃፈውን አልሽር።
(ሙና ሀበሻዊት)
Join 👇👇
@getem
@getem
@munihabeshawt
የችግር አለንጋ አካሌን ባያነፍር
ፈገግታዬ ጠፍቶ ለፅልመት ባያብር
.
.
ጉልበቴን አቅፌ አንገቴን ባልደፋ
ብሶቴን ባክመው በምናልባት ተስፋ
ደንታ ቢስ ነች አሉ ማሰብ የተሳናት
ሰው አድርጎ ፈጥሮ ቸልታ የሞላት
.
.
አዎ ደንታ ቢስ ነኝ።
የመከራ ጥይት በላዬ ቢዘንብም
አያሌ ፈተና ፊቴ ቢደንቀም
አንድ ላይ ተባብሮ ዙሪያዬን ቢከብም
.
ፍፁም እጅ አልሰጥም
አዎ እጅ አልሰጥም
መኖርም አንዴ ነው መሞትም አንዴ ነው
የፈተና ድልድይ ማለፍያው ፅናት ነው
ብለህ ንገራቸው
ምትወጥን በልኩ ነፍሷን ሳታሳርር
መንገድ በሌለበት መንገድ ምትፈጥር
ተስፋ ባልታየበት ተስፋ ምታዋቅር ህይወትን በጥበብ አቅላ ምትኖር
ነች ብለህ አስረዳቸው ።
.
.
አለም ዋዣቂ ናት ግራ ሆነች ሲሉ የምትገኝ በቀኝ
ደርሼ ላልይዛት የትካዜ ሾተል ለምን ይሸንቁረኝ?
.
.
ችግር የሚገፋው እራስን በመግደል ከሆነ ብይኑ
.
አዎ ደንታ ቢስ ነኝ
ማሰብ የተሳነኝ
.
.
በሀሳብ ትካዜ ናላዬን ባዞርም
በዋይታ በለቅሶ አይኔን ባሳዝንም
አልፌ አልወጣ ከተሾመው አጥር
ፈጣሪ በቃሉ የፃፈውን አልሽር።
(ሙና ሀበሻዊት)
Join 👇👇
@getem
@getem
@munihabeshawt
አትግጠም አትበሉኝ!!!!!
አትደንስ በሉኝ፣
አትጨፍር በሉኝ፣
አትፎክር በሉኝ፣
አትሸልል በሉኝ፣
አትጀርጅር በሉኝ፣
አትናገር በሉኝ፣
አትቁም፣
አትሂድ፣
አትነሳ በሉኝ፣ በሉኝ እንዳሻችሁ፣
ግን!!!!!
ግን!!!!!!
አትግጠም አትበሉኝ፣
አትግጠም አትግጠም፣ አትበሉኝ ሁላችሁ፣
በነጻነት ጠኔ፣
ግጥም'ጥም ብዬ፣ እንዳልሞትባችሁ።
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
አትደንስ በሉኝ፣
አትጨፍር በሉኝ፣
አትፎክር በሉኝ፣
አትሸልል በሉኝ፣
አትጀርጅር በሉኝ፣
አትናገር በሉኝ፣
አትቁም፣
አትሂድ፣
አትነሳ በሉኝ፣ በሉኝ እንዳሻችሁ፣
ግን!!!!!
ግን!!!!!!
አትግጠም አትበሉኝ፣
አትግጠም አትግጠም፣ አትበሉኝ ሁላችሁ፣
በነጻነት ጠኔ፣
ግጥም'ጥም ብዬ፣ እንዳልሞትባችሁ።
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
ነጃ በለን ነጃ!!!!
እስቲ በጁምኣው፤
ጨዋታው ይቅርብኝ፤
እኔም ብላቴናው፤
ሶላቴን ልፈጥም፤
ብዬ ዱኣ ላድርግ፤ """ነጃ በለን ነጃ፤"""
አውቃለሁ አውቃለሁ፤
ከሞት ይጋርዳል፤
በልኣ ይሸፍናል፤ ያንተ መጋረጃ።
ነጃ በለን ነጃ!!!!!!
(((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
መልካም ጁምኣ!!!!!!!!
እስቲ በጁምኣው፤
ጨዋታው ይቅርብኝ፤
እኔም ብላቴናው፤
ሶላቴን ልፈጥም፤
ብዬ ዱኣ ላድርግ፤ """ነጃ በለን ነጃ፤"""
አውቃለሁ አውቃለሁ፤
ከሞት ይጋርዳል፤
በልኣ ይሸፍናል፤ ያንተ መጋረጃ።
ነጃ በለን ነጃ!!!!!!
(((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
መልካም ጁምኣ!!!!!!!!
ወልዲያ በጁምኣ!!!!
በሸህ ዳና ቱፍታ ፤
በነ አውገረድ ቱፍታ ፤
በከረሞች ኪታብ ፤ መልኳ ተበጅቶ ፤
ስንቱ ተረገመ፤
የሸሆቹን ሃገር ፤ ወልዲያን ነካክቶ ።
ወረሃቡል ብሎ ፤
የእነነየ ምላስ እሳት እየተፋ ፤
ወልዲያን የነካ ፤
ጣይ እንዳየ ጭጋግ ብን ብሎ ጠፋ ።
አቦ በጁምኣው ፤
በጡሃራው ሰማይ መለይካ በዞረው ፤
የወልዲያን ጠላት ፤
ከሰማይ አፍርጦ አንዳች ይዘርረው ።
ወላሂ! !!!ይኸው ነው! !!!
((( ጃ ኖ )))
@Balmbaras
@getem
በሸህ ዳና ቱፍታ ፤
በነ አውገረድ ቱፍታ ፤
በከረሞች ኪታብ ፤ መልኳ ተበጅቶ ፤
ስንቱ ተረገመ፤
የሸሆቹን ሃገር ፤ ወልዲያን ነካክቶ ።
ወረሃቡል ብሎ ፤
የእነነየ ምላስ እሳት እየተፋ ፤
ወልዲያን የነካ ፤
ጣይ እንዳየ ጭጋግ ብን ብሎ ጠፋ ።
አቦ በጁምኣው ፤
በጡሃራው ሰማይ መለይካ በዞረው ፤
የወልዲያን ጠላት ፤
ከሰማይ አፍርጦ አንዳች ይዘርረው ።
ወላሂ! !!!ይኸው ነው! !!!
((( ጃ ኖ )))
@Balmbaras
@getem
በላይኛው ቀርሳ፣
በታችኛው አውሳ፣
እየተናጠረች፣
በሽንሽን ቀሚሷ፣
ድረስልኝ ብላ፣ ጁምኣ ልካብኝ፣
እረግ ነገ ደግሞ፣
ባቲ አጣሪ ገንዳ፣ ቀጭን ሀጃ አለብኝ፣
አውሳ በር፣
አግኝቸሽ በነበር!!!
አጣሪ ገንዳ፣
ሙቸልሽ ነበረ፣ በሃድራ ስነዳ።
ገንደድዩ፣
መገን እንሶሱላ፣መገን ቀጠናዩ።
ይኸው ደሞ ዛሬ፣
በቀርሳ ብርቱካን፣ ደብዳቤሽ ተጣፈ፣
ጥርስሽ ውልብ አለኝ፣
እንደትርሙብሌ፣እየተሰለፈ።
አለብኝ ፣
አለብኝ፣
ባቲ ያሉ ጊዜ ፣
ሸጋና ደም ግባት፣ ከተፍ እሚልብኝ።
ቅዳሜ በሸጋ፣
ቅዳሜን በሙና፣
ብቅ ያለች እንደሆን፣ በሃድራው መኪና፣
እንደ አፋር ምንሽር፣አምራ ተሽሞንሙና።
መስፈሪያው ባቲ ነው፣ ዛትና ቁመና።
እንደ ብርቱካኑ፣ እንደ ማር ወለላ፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ፣
የጠየመ ከንፈር፣ የመከከ ገላ፣
ቀርሳ ላይ ተጋግሮ፣ ባቲ ላይ ሲበላ።
ዘለቀች ልጅቱ፣
ደሞ ጀማመረች፣
በደመነው ሰማይ፣ ብርድ እያባረረች፣
ሀድራ ተሟሙቃ፣ ቡና እየካደመች፣
እኔን የማይበርደኝ፣ ባቴን ነው እያለች።
ከመንዙማ መሃል፣
መደዱን ጎንጉና፣ ተቀኘችላችሁ፣
" ባቴን ተረከዜን፣ ላኩልኝ ብያችሁ፣
ምነው ባቴን ብቻ፣ታስቀሩታላችሁ። "
ቅዳሜና ናፍቆት፣ ሃድራና ዝየራ፣
እንዴት ይጣፍጣል፣ከባቲዎች ጋራ።
አሳ በራ ጊቴ፣
አውቶብስ የሚቴ፣
ቡርቃ ተረከዜ፣
ሃውሳ መቀነቴ፣
እንደ አጀብ፣ ይቀልጣል ቅዳሜና ባቴ።
ያች የሀድራ ሹፌር፣
ድረስልኝ ብላኝ፣ ልካለች ከባቲ፣
ባቲና ቅዳሜ፣ቅዳሜና አሽኩቲ፣
ሀድራና መቀነት፣ ጀምኣና አርቲ፣
እየጎዘጎዘች፣ ድረሱልኝ ካለች፣
መገን ድረሱላት፣ ሀጃ ታወጣለች፣
ቅዳሜም ይቀልጣል፣ ባቲም ትነዳለች።
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!!!
በታችኛው አውሳ፣
እየተናጠረች፣
በሽንሽን ቀሚሷ፣
ድረስልኝ ብላ፣ ጁምኣ ልካብኝ፣
እረግ ነገ ደግሞ፣
ባቲ አጣሪ ገንዳ፣ ቀጭን ሀጃ አለብኝ፣
አውሳ በር፣
አግኝቸሽ በነበር!!!
አጣሪ ገንዳ፣
ሙቸልሽ ነበረ፣ በሃድራ ስነዳ።
ገንደድዩ፣
መገን እንሶሱላ፣መገን ቀጠናዩ።
ይኸው ደሞ ዛሬ፣
በቀርሳ ብርቱካን፣ ደብዳቤሽ ተጣፈ፣
ጥርስሽ ውልብ አለኝ፣
እንደትርሙብሌ፣እየተሰለፈ።
አለብኝ ፣
አለብኝ፣
ባቲ ያሉ ጊዜ ፣
ሸጋና ደም ግባት፣ ከተፍ እሚልብኝ።
ቅዳሜ በሸጋ፣
ቅዳሜን በሙና፣
ብቅ ያለች እንደሆን፣ በሃድራው መኪና፣
እንደ አፋር ምንሽር፣አምራ ተሽሞንሙና።
መስፈሪያው ባቲ ነው፣ ዛትና ቁመና።
እንደ ብርቱካኑ፣ እንደ ማር ወለላ፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ፣
የጠየመ ከንፈር፣ የመከከ ገላ፣
ቀርሳ ላይ ተጋግሮ፣ ባቲ ላይ ሲበላ።
ዘለቀች ልጅቱ፣
ደሞ ጀማመረች፣
በደመነው ሰማይ፣ ብርድ እያባረረች፣
ሀድራ ተሟሙቃ፣ ቡና እየካደመች፣
እኔን የማይበርደኝ፣ ባቴን ነው እያለች።
ከመንዙማ መሃል፣
መደዱን ጎንጉና፣ ተቀኘችላችሁ፣
" ባቴን ተረከዜን፣ ላኩልኝ ብያችሁ፣
ምነው ባቴን ብቻ፣ታስቀሩታላችሁ። "
ቅዳሜና ናፍቆት፣ ሃድራና ዝየራ፣
እንዴት ይጣፍጣል፣ከባቲዎች ጋራ።
አሳ በራ ጊቴ፣
አውቶብስ የሚቴ፣
ቡርቃ ተረከዜ፣
ሃውሳ መቀነቴ፣
እንደ አጀብ፣ ይቀልጣል ቅዳሜና ባቴ።
ያች የሀድራ ሹፌር፣
ድረስልኝ ብላኝ፣ ልካለች ከባቲ፣
ባቲና ቅዳሜ፣ቅዳሜና አሽኩቲ፣
ሀድራና መቀነት፣ ጀምኣና አርቲ፣
እየጎዘጎዘች፣ ድረሱልኝ ካለች፣
መገን ድረሱላት፣ ሀጃ ታወጣለች፣
ቅዳሜም ይቀልጣል፣ ባቲም ትነዳለች።
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!!!
* ትዝታሽ*
ተሳልሽና በምናቤ አለም ፤
ከራሴው ሰርቄ የትዝታን ቀለም ፤
.
.
ያልነበር በነበር ለራሴ ነግሬ ፤
ቀለሙን ሳልሰስት እንዳሻሽ ሰፍሬ ፤
.
.
ስሥልሽ ስቀባሽ ሳጠፋ ሳደምቅሽ ፤
ያልነበር ማንነት በነበር ስኩልሽ ፤
ትዝታ ወርቅ ነው ወርቅ ቅብ አንቺ ነሽ ፤
ትዝታን ልንገርሽ
ቀለሙን ደባልቄ ብሩሼን ነከርኩኝ ፤
ፀጉርሽን ጎንጉኜ ግንባርሽን ሳልኩኝ ፤
.
.
ሽብሽብ የማያውቀው ፊት ግንባርሽማ ፤
ባዳ መሆንሽን ሰምቶ እንዳልሰማ ፤
.
.
ጥፋቱም የኔው ነው ጥፋቴን አመንኩኝ ፤
የሳልኩትን ግንባር ለመውቀስ አልቻልኩኝ ፤
.
.
አይንሽ በማየቱ ፤
ጆሮሽ በመስማቱ፤
ጥርስሽ በመሳቁ፤
ልብሽ በማወቁ ፤
ተወቃሽም ሆነው ለፍርድ ከበቁ ፤
ክሱን አንስቻለው ይግባኝ ይጠይቁ ፤
.
.
አፍሽ ነው ጠላቴ ዝምታን ሚነግረኝ፤
እለማወቄ ነው ብሩሽ ያላስጣለኝ ፤
.
.
ግና
ስዕሉም ደብዝዞ ውጥር ሸራው ነትባል ፤
ከሰአሊው መዳፍ ቀለሙም ጠብ ይላል ፤
ጠብ ጠብ ጠብ ጠብ ጠብ ይላል ፤
●●●●●●●//●●●●●●●
@AcubeZ
@getem
@getem
ተሳልሽና በምናቤ አለም ፤
ከራሴው ሰርቄ የትዝታን ቀለም ፤
.
.
ያልነበር በነበር ለራሴ ነግሬ ፤
ቀለሙን ሳልሰስት እንዳሻሽ ሰፍሬ ፤
.
.
ስሥልሽ ስቀባሽ ሳጠፋ ሳደምቅሽ ፤
ያልነበር ማንነት በነበር ስኩልሽ ፤
ትዝታ ወርቅ ነው ወርቅ ቅብ አንቺ ነሽ ፤
ትዝታን ልንገርሽ
ቀለሙን ደባልቄ ብሩሼን ነከርኩኝ ፤
ፀጉርሽን ጎንጉኜ ግንባርሽን ሳልኩኝ ፤
.
.
ሽብሽብ የማያውቀው ፊት ግንባርሽማ ፤
ባዳ መሆንሽን ሰምቶ እንዳልሰማ ፤
.
.
ጥፋቱም የኔው ነው ጥፋቴን አመንኩኝ ፤
የሳልኩትን ግንባር ለመውቀስ አልቻልኩኝ ፤
.
.
አይንሽ በማየቱ ፤
ጆሮሽ በመስማቱ፤
ጥርስሽ በመሳቁ፤
ልብሽ በማወቁ ፤
ተወቃሽም ሆነው ለፍርድ ከበቁ ፤
ክሱን አንስቻለው ይግባኝ ይጠይቁ ፤
.
.
አፍሽ ነው ጠላቴ ዝምታን ሚነግረኝ፤
እለማወቄ ነው ብሩሽ ያላስጣለኝ ፤
.
.
ግና
ስዕሉም ደብዝዞ ውጥር ሸራው ነትባል ፤
ከሰአሊው መዳፍ ቀለሙም ጠብ ይላል ፤
ጠብ ጠብ ጠብ ጠብ ጠብ ይላል ፤
●●●●●●●//●●●●●●●
@AcubeZ
@getem
@getem
# ልኬት_እና_ስኬት
:
‹‹አሥር ጊዜ ለካ፤ አንድ ጊዜ ቁረጥ!››
ይለኛል ወገኔ፣
ደጋግሞ መለካት፣ ጊዜ ማባከን ነው!
እለዋለሁ እኔ፡፡
:
:
‘ቤት’ በኩል ለክቼ፣ በየት በኩል ልቁረጥ?
ሃሳቤ ሃሳብ ወልዶ፣ እያደር ሲለጠጥ፡፡
:
ፋታ በማይሰጠው፣ በዚህ ዘመን ኩነት
ለማሞቅ ያኖሩት፣ ተ’ኖ በሚያልቅበት
ማነው ወተት ጥዶ፣ የሚወጣ ዙረት??
:
ሥፍር የሌላቸው፣ መሥፈሪያዎች በዝተው
መሥፈር የሚችሉ፣ ሙያተኞች ጠፍተው፤
ስህተት ቢደጋገም፣ ከውነት ጫፍ ላይውሉ
ሲለኩ መኖር ነው ፣ የመታሪ እድሉ።
:
ቆሞ ከማመንታት፣ በመንታ መንገድ ላይ
በቀን በጨለማ ፣ በዝናብ በፀሃይ፤
ፍፃሜው ቢያስፈራም፣ ውሳኔው ቢመርም
ተሳስቶ መታረም ፣ ሳይሻል አይቀርም፡፡
:
:
‹‹አሥር ጊዜ ለካ፤ አንድ ጊዜ ቁረጥ፡፡››
ይለኛል ወገኔ፣
አንድ ጊዜ ለካ፤ ወድያውኑ ቁረጥ!
እለዋለሁ እኔ፡፡
----------------------//-----------------------
( በርናባስ ከበደ ፣ ፊደልና ቅኔ ፣ የ14 ገጣሚያን ስብስብ መድብል
፣ 2009 ዓ.ም)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
:
‹‹አሥር ጊዜ ለካ፤ አንድ ጊዜ ቁረጥ!››
ይለኛል ወገኔ፣
ደጋግሞ መለካት፣ ጊዜ ማባከን ነው!
እለዋለሁ እኔ፡፡
:
:
‘ቤት’ በኩል ለክቼ፣ በየት በኩል ልቁረጥ?
ሃሳቤ ሃሳብ ወልዶ፣ እያደር ሲለጠጥ፡፡
:
ፋታ በማይሰጠው፣ በዚህ ዘመን ኩነት
ለማሞቅ ያኖሩት፣ ተ’ኖ በሚያልቅበት
ማነው ወተት ጥዶ፣ የሚወጣ ዙረት??
:
ሥፍር የሌላቸው፣ መሥፈሪያዎች በዝተው
መሥፈር የሚችሉ፣ ሙያተኞች ጠፍተው፤
ስህተት ቢደጋገም፣ ከውነት ጫፍ ላይውሉ
ሲለኩ መኖር ነው ፣ የመታሪ እድሉ።
:
ቆሞ ከማመንታት፣ በመንታ መንገድ ላይ
በቀን በጨለማ ፣ በዝናብ በፀሃይ፤
ፍፃሜው ቢያስፈራም፣ ውሳኔው ቢመርም
ተሳስቶ መታረም ፣ ሳይሻል አይቀርም፡፡
:
:
‹‹አሥር ጊዜ ለካ፤ አንድ ጊዜ ቁረጥ፡፡››
ይለኛል ወገኔ፣
አንድ ጊዜ ለካ፤ ወድያውኑ ቁረጥ!
እለዋለሁ እኔ፡፡
----------------------//-----------------------
( በርናባስ ከበደ ፣ ፊደልና ቅኔ ፣ የ14 ገጣሚያን ስብስብ መድብል
፣ 2009 ዓ.ም)
@getem
@getem
@lula_al_greeko