ግጥም ብቻ 📘
68.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
172 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
መሃል ሸዋ ላይ ራስ ሆቴል እንገናኝና የሸዋን ቀበሌ መረባ
እንበልበት! !!


መረባ አትይም ወይ ፤
ከምትወዘወዥ እንዳበደ ጥጃ ፤
መረባ አይደለም ወይ ፤
ጀምበር ሳይዘቀዝቅ የሚያወጣው ሃጃ ።
እንጃ! !!!

((( ጃ ኖ )))

@Balmbaras
@getem


ረቡዕ ሚያዝያ
3 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ከ 30 ጀምሮ
በራስ ሆቴል አዳራሽ ተቃጥረናል፡፡
©ጦቢያግጥምንበጃዝ


((( አበቦቼ እንዳትቀሩ )))
እንደ ቀልድ ፈገግ...
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ፣ ሳቄ ይቀድመኛል።
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ፣ ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው!
እየሳቁ ውሎ ፣ እየሳቁ ማደር።
ውሸት ነው አትመኝ....
እዚህ ሀዘን የለም ሳቅ ነው የተረፈን
ስላቅ ነው ትርጉሙ...
ሀገር ለቆ ሄዶ፣
"ሀገሬን ሀገሬን" ፣ ብሎ እንደመዝፈን።
............................................
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? ፣ እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ፣ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ።
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ፣ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ፣ ምኔ እንደታመመ?
...........................................
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ
ቂቂቂቂቂቂቁ......ልነግርሽ እኮ ነው
ምን ብዬ ልንገርሽ?....
ልነግርሽ ያልሁትን ፣ ሳቄ እያፈነው።




@getem
@getem
@lula_al_greeko
 ~~~~መለያት ማለት~~~~

ይሀው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ
ያዩሽ ሰዎች ሁለ ከ እቅፌ ጉያ
ዛሬም ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድተዋለች ብለው ክንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ አለም ፈጠነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፈቀር እንጂ፤
ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው

ለኔና ላቺኮ መለያየት ማለት፤
በሩቅ መፋቀር ነው የላመተያየት
የለመተያየት መፋቀር ማለት፤
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሂውት
ዘወትር ዘወትር ምን አልባት፤
ምን አልባት እያለች የምትኖር ሂውት
በተሰፋዋ ማሃል ጥቂት ደስታ አላት
በተስፋችን ማሃል መፋቀሩ ካለ
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንትያያለን
ብለሽ ነገሪያቸው
ልቦናው ተጣብቋል በያቸው
እንጂ በኛ ማሃል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመታያየት
በሩቅ መስማማት በደምፅ አልባ ቃላት

@Zerusoutlying
@getem
@getem
ምኞት እሹሩሩ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የምኞቴን ስእል፣ ከግንባሬ አንስቼ
ብብቴ ስር ደበቅሁ
በስውር ጎምዥቼሽ፣ ስንት ዘመን ማቀቅሁ
ሳትቀጥሪኝ ቁጭ ብዬ፣ አንቺን እየጠበቅሁ።

By bewuketu siyum

@getem
@getem
@paappii
ሞቶ መውለድ
(ታምራት ሚሊዮን)
..
በልጅነቴ ነው....
እናቴ ከመቅደስ..ስዕል ይዛ መጣች
ስዕሉን ለመስቀል..
የሚስማሩን አናት..በመዶሻ መታች
..
ስዕሉ ላይ ያለው...
በመዶሻ ብረት..በተመታ ሚስማር
የተቸነከረ፣እግሩ የቆሰለ..ቀላ ያለ ሰው ነው..።
..
እናቴን ጠየኳት..
"ስሚኝ እናቴ ሆይ..ይሄ ያማረ ሰው
እዛ እንጨቱ ላይ ሚስማር ያጣበቀው....
እዚህ ግድግዳ ላይ ሚስማር የሰቀለው
ሚስማር የገደለው...
ዘመዳችን ይሆን??..ቆይ ይሄ ሰው ማነው??።
..
በችግር ጊዜአችን..
ጥሎን ሞተ ያልሽው..አባቴ እንዳይሆን!!"
..
የምስሉን ሰው ባርምሞ እያየች
በእጇ እየሳበችኝ..እናቴ መለሰች...።
"ወዲህ ናልኝ ልጄ..ዘመድ ላስተዋውቅህ...
ሞቶ የወለደህ እሱ ነው አባትህ...."
......
ስለ ጠፋው ሳይሆን..ስለዚኛው አባት
እናቴ አስረዳችኝ...
እሷ እንዳለችኝ..የማይጠፋ ጥሎኝ
ሚስጥሩ የከበደ
ሞቶ ማኖር 'ሚችል..ለካስ አባት አለኝ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
...ዝንብ ነኝ...

👉ዋሲሁን ሀይሉ

ልክ ነሽ ህይወቴ
በሞላ አበባ አዛባን ማለቴ
ወርቅ እየወረወርኩ
ድንጋይ እየመረጥኩ
ለሸሸኝ ጥንባንሳ
እንደ ርግብ እየበረርኩ
ሰላምን ከለመንኩ
እንደ ነብ አበባ ከልቀሰምኩኝ
የሸሸኝን ትቼ ጎኔን ካላየሁኝ
አለሜ ስደቢኝ
እውነትም ዝንብ ነኝ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
…ገዘተኝ…

👉…ዋሲሁን ሀይሉ

ሀሳብሽን ጥለሽ የተጓዝሽው ጉዞ
መንገዱ እንዲቃና በምርቃቴ ታግዞ
…እንደ ዶሮ ጀርባ አጥሮ ተቀንሶ
ጨርቅ እንዲሆንልሽ ለጉዞ ለስልሶ
የተሸከምሽውን ከባድ ሸክም ጣዪ
የሰው ልብ ትተሽ መንገድሽን እዪ
ጉልበት አንዲሆንሽ…
ሌላ ስንቅ ያዢ የኔን ልብ አትብዪ
:
ሰማሽኝ…?
የማሰብ አድማሴ የቀልቤ ዳርጥጉ
የካሮት እንዳይሆን መስፋት ማደጉ
ልቀቂው ያንን ዳር ያንን ሰፊ ቦታ
ልክ እንደ ቀደመው ይሁን አይረታ
:
የፍቅር ቅኔ ዘርፌ
መውደድሽን ተደግፌ
ካላማረ የፍቅሬ ዝማሬ
በኢሮስሽ ዞሬ
ምህዋሩን ተሽከርክሬ
ከቅኔ ማህሌቱ ካልከተምኩ
ያንቺን ልብ ካልከፈትኩ
ንገሪው ይሄንን ሞኝ
ብነግረው ላይሰማኝ
ለራሱ ምሎ ልቤ ገዘተኝ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
እንባ! !!!!!


የኢትዮጲያ ልጆች ፤ እናንተ ሁላችሁ ፤
አባቴን ላኩልኝ ፤
የእንባየን ወረታ ፤
በላይኛው ሃገር ታገኙታላችሁ ።


((ይህ ነፍስ የሚያደፈርስ እንባ የአንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ
እንባ ነው ። ሰውየው ሰርቆ ወይም ቀጥፎ አይደለም
የሚንገላታው ። የተከዳው ሙሴ ነው እሱ ።)))


@Balmbaras
@getem
በየጁዎች ኪታብ!!!!!!


በወልዮቹ ቤት፣
ሃራ ጥጋ ጥጉን፣ ስንት ዱኣ ሞልቶ፣
ዳንዮል አወል ቤት፣
ኑ ብሉኝ እያለ፣
የቂሷው ሰደቃ፣ ኢልሙ ተፈትፍቶ፣
አደረ ይሉኛል፣
የሸሆቼን ኪታብ፣ የሚቀራው ጠፍቶ።


እኒያ ደጋጎቹ፣
ልቡናቸው ፀሃይ፣
እንደዘምዘም ውሃ፣ ቀልባቸው ጡሃራ፣
ዘይሩኝ የሚያሰኝ፣
እንደ መዲና በር፣ እንደመካ ጎራ፣
አይናቸው ብርቅ ነው፣
አሻግሮ ይፈታል፣ የርዚቁን ኢሻራ፣
እነሱ አልነበሩ፣
የኒያው ባለሟል፣ የሂማው ሙሽራ፤
ጁምኣው ይደምቃል፤
ቀኑ ይሞሸራል፤ ስማቸው ሲጠራ።


ሸጋ የጁምኣ ቀን!!!!!!


ሸጋ የጁምኣ ቀን!!!!!


ሸጋ የጁምኣ ቀን!!!!!!



((( ጃ ኖ ))

@Balmbaras
@getem
።በላይ በቀለ ወያ።

ስንት አመታት ሙሉ
ማፍቀሬን ነግሪያት ፣ ጠልታኝ ስብሰለሰል
ድንገት እሺ አለችኝ
ልቧን የቀየረው ፣ አብይ ነው መሰል።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
feeling የራስሽ
...ጉዳይ!!
---------------------------
ከ'ምነቴ፣ ከ'ውነቴ
ሸሽተሽ ከገነቴ፣

ዓርያም እሚያወጣን
የፍቅርን ቅዳሴ
የዕርገቱን እጣን፣
ብትሄጂም እረግጠሽ
ከወረብ፣ ዝማሜ
ዳንኪራውን መርጠሽ፤
...
ምላሴን ለእርግማን አላንቀሳቅስም
በሃገሬ ባህል ሙት አይወቀስም።

--------------------//------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getwm
@getem
@lula_al_greeko
#ይታየኛል
:
:
ሴት ከሆን ማናግር ስልክ ተደውሎ
አናትሽ ላይ ወቶ የሆነ ዛር ዘሎ
ምትደውለው ማናት?
የት ነውስ ምታውቃት?
ደርሶ ቁጥርክን ለምንስ ሰጠሀት?
አምጣው ስልኩን በቃ!! እንደውም ላዋራት!!
ሁሌ ባልሺኝ ቁጥር አላማርርሽም
አሁንስ ሰለቸሺኝ መቼም አልልሽም።
:
:
ሁለታችን ሆነን ስናቀና መንገድ
በፊት ከማታውቂያት ወይ ወዳጅ ወይ ዘመድ
ድንገት ስንገናኝ ከሁሉ አስቀድመሽ
እኔ ባለቤቱ አንቺ ግን ምኑ ነሽ?
ባልሺም ጊዜ ከቶ አልነደድኩብሽም
ለሰው ይምሰል እንጂ ለኔ ግን በፍፁም ጨቅጫቃ አይደለሽም።
:
:
ስልኬን ስትነካኪ ካየሽ የሴት ፎቶ
ቁጣሽ ግሎ ንሮ ወዲያው ደምሽ ፈልቶ
ባይንሽ ቂጥ እያየሽ የጥያቄ ውርጅብኝ
ገና አንዱን ሳልመልስ ስላዘነብሺብኝ
ጭራሽ አይከፋኝም
አዎንታዊነቱ እኔን አይጠፋኝም።
:
:
እቤታችን ሆነን ተቃቅፈን በደስታ
እየተሳሳቅን ፊልም ያየንም ለታ
አንዲቷን ተዋናይት እንደው ሳላስበው
ያልኩሽ እንደሆነ በጣም ነው ምታምረው
ከባጡም ከቆጡም ሰበቦች ደርድረሽ
እየገላመጥሺኝ ቻናሉን ቀይረሽ
ሌላ ሌላ ነገር ስትከፍቺብኝም
ጨቅጫቃነት መስሎ እኔን አይሰማኝም።
:
:
አንዳች ጉዳይ ገጥሞኝ
ከደጅ ውዬ ማታ እቤቴ ስመጣ
እየቀየጥሺብኝ ሰላምታና ቁጣ
ከማን ጋር የት ገብተክ ከማን ጋር የት ወጣ
ከማን ጋራ ምን በልተ ምንስ ደግሞ ጠጣ
ብለሺኛል ብዬ አልበሳጭ እኔ
የልብሽ ነው እንጂ የአፍሽ ለምኔ።
:
:
የሚገርመው ነገር ...
ዘንድሮ ሰው ሁሉ የት ገባ የት ወጣ ጭቅጭቅ መስሎታል
"ቅናት" ካሉት ቅኔ ሰሙን ብቻ አንግቦ ወርቁን ዘንግቶታል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ ...
ገብቶኛል ድብቁ
ጌጥ ሆኖኛል ወርቁ።
:
:
እንዲ አረግሺኝ ብዬ እንዲያም አልሺኝ ብዬ
አላፈገፍግም ፍቅራችንን ጥዬ።
:
:
እንደውም የኔ ውድ
በየቀኑ ቅኚ በየቀኑ በዪኝ እጅግ ደስ ይለኛል
ከቅናትሽ ጀርባ ፍቅርሽ ይታየኛል
"ቅናት" ሚሉት ቅኔ ወርቁ በርቶልኛል።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu
@getem
@getem
ትቀሪያለሽ ብዬ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
ትቀሪያለሽ እያልኩ
ታረፍጃለሽ እያልኩ ፣ ብዙ ጊዜ አለፈ
ገጣሚው በውሉ
ፍቅረኛው ቀርታበት
"ትመጫለሽ የሚል ፣ እልፍ ግጥም ፃፈ።
እኔ ግጥም ጠፋኝ ፣
ቀድመሽ ስትገኚ ፣ ራቀ ከልቤ ሀሴት
ለገጣሚ ደግሞ
ፍቅረኛ አትሆንም ፣ቀጥራ የማትቀር ሴት።
።።
እናም እልሻለሁ
ቅሪብኝ ልቅርብሽ ፣ ልቤ እያፈቀረሽ
ምኑን ገጣሚ ሆንኩ
ትመጣለች ካላልኩ ፣ ቀጥረሽኝ ካልቀረሽ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
ሸጋ ቅዳሜ ይሁንልን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!


ከጀርባችን ባለከራማውና ጅንኑ የጦሳ ተራራን ተደግፈን፣
የአልጋ ወራሽን ቤተመንግስት (መርሆ ግቢን) ተንተርሰን፣
ከፊታችን ደግሞ የዱኣውን ሪጋ ( መንደር) አረብ ገንዳን
ተመርኩዘን ቅዳሜን ለማሸብረቅ በሉባንጃና በብርጉዱ
ሽታ ታጥነን በቄጤማው ጉዛጓዝ ላይ ብንሰየም ምን
ይለናል???? ምንም!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!


በቅዳሜ ሰማይ እንኳን የወሎ ሰው ጦሳ እንኳን በጅ ብሎ
በሃድራው መኪና ይሳፈራል !!!!!!!!


በመኪናው መንገድ ጎማው ሸተተኝ፣
የሃድራው መኪና መጣ መሰለኝ።


አለች አሉ ጃኖ ባለመንዙማዋ። እንግዳሳ!!!!!!!!!



ሽብርቅርቅ፣ድምቅምቅ፣ፍልቅልቅ፣ ያለ ቅዳሜ
ይሁንላችሁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!


@Balmbaras
@getem
እስክስ ቅዳሜ! !!!!!!


ከሰኞ እስከ አርብ ፤
ባለቃ በምንዝር ፣ ታምሜ ተምሜ ፤
የምታከምብሽ ፤
የቀኑ ባለሟል፤ እንዴት ነሽ ቅዳሜ! !!!!!!

(( ጃ ኖ ))

@balmbaras
@getem
------------------------------
ሞልቶልን ስንፈስክ ፥ በቅቤ እና ስጋ
ለነዳያንን እንስጥ ፥ እንዲሆነን ዋጋ።
ፈጥነን አለን እንበል፥ እንድረስላቸው
ፃሙን አስፈትተን ፥ ፃም እናሲዛቸው።
--------------------------------
( በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@lula_al_greeko