ሲመሽ
____
ሚደምነው ለኔ ፥ ሚጨልመው ለአንቺ፣
ሚያነቅፈኚ እኔ፥ የምትደሚው አንቺ፣
ገና ሳላውቅ መንጋት
ገና ሳላውቅ ማለም፣
ሲነጋ እንዲታወቅ
ይመሽ ጀመረ ይበልጥ እንድደመም፣
በድንግዝግዝ ሰማይ፥ መማሩን ለሚችል፣
መሽቶበት ለሚውል፥
ወገግ ሲል ማዬት ፥ምን ያህልስ ደስ ይል፣
___
ግዕዝ ሙላት
By @geez_mulat
@getem
@getem
@paappii
____
ሚደምነው ለኔ ፥ ሚጨልመው ለአንቺ፣
ሚያነቅፈኚ እኔ፥ የምትደሚው አንቺ፣
ገና ሳላውቅ መንጋት
ገና ሳላውቅ ማለም፣
ሲነጋ እንዲታወቅ
ይመሽ ጀመረ ይበልጥ እንድደመም፣
በድንግዝግዝ ሰማይ፥ መማሩን ለሚችል፣
መሽቶበት ለሚውል፥
ወገግ ሲል ማዬት ፥ምን ያህልስ ደስ ይል፣
___
ግዕዝ ሙላት
By @geez_mulat
@getem
@getem
@paappii
የእኔ የምለው የለም !!
......................
እባክሽን ውዴ ፣ናፈቅሽኝ ነይልኝ፣
አይኔ እንቅልፍ አምሮታል፣ጎኔም ይረፍልኝ፣
እኔ ያንቺ አፍቃሪ፣አሳዛኝ ከርታታ፣
ደክሞኝ እንዳልተኛ፣ናፍቆቴ በረታ፣
አይኔ ከፎቶሽ ላይ፣ላይነሳ ተተክሎ፣
ልቤ ላይመለስ፣ወዳንቺ ኮብልሎ፣
ነይልኝ የኔ ናፍቆት፣አካሌ አይውቀስሽ፣
ደክሞት እንዳይተኛ፣ምክንያት አያርግሽ፣
አቺም ሰው ነሽና ፣ይግባሽ መናፈቄ፣
ፍቅሬን በመናፈቅ ፣አይገደብ ሳቄ፣
ከዚህ በላይ መውደድ ፣ፍቅሬ ለማበድ ነው፣
አንቺን ሲናፍቅ ነው፡ ቀኑም የሚመሸው፣
ተሰራልኝ እንጂ ፣እንደሰው አካላት
የኔ የምለው የለም ለራሴ ነው ያልኩት።
ገጣሚ _አዩ
ለአዲዬ
@getem
@getem
@getem
......................
እባክሽን ውዴ ፣ናፈቅሽኝ ነይልኝ፣
አይኔ እንቅልፍ አምሮታል፣ጎኔም ይረፍልኝ፣
እኔ ያንቺ አፍቃሪ፣አሳዛኝ ከርታታ፣
ደክሞኝ እንዳልተኛ፣ናፍቆቴ በረታ፣
አይኔ ከፎቶሽ ላይ፣ላይነሳ ተተክሎ፣
ልቤ ላይመለስ፣ወዳንቺ ኮብልሎ፣
ነይልኝ የኔ ናፍቆት፣አካሌ አይውቀስሽ፣
ደክሞት እንዳይተኛ፣ምክንያት አያርግሽ፣
አቺም ሰው ነሽና ፣ይግባሽ መናፈቄ፣
ፍቅሬን በመናፈቅ ፣አይገደብ ሳቄ፣
ከዚህ በላይ መውደድ ፣ፍቅሬ ለማበድ ነው፣
አንቺን ሲናፍቅ ነው፡ ቀኑም የሚመሸው፣
ተሰራልኝ እንጂ ፣እንደሰው አካላት
የኔ የምለው የለም ለራሴ ነው ያልኩት።
ገጣሚ _አዩ
ለአዲዬ
@getem
@getem
@getem
#ያንቺው_ደቂቅ
:
:
ከቅዱስ ተራራ እንደመነጨ ኩልል ብሎ እንደጠራ፤
እንደ ጎበዝ ገበሬ ዘር እልፍ አላፍት የሚያፈራ፤
ልክ እንደ ፀደይ ሰማይ፤
ወለል ብሎ እንደሚታይ፤
ልዩ ስሜት እንከን የለሽ ያደባባይ ጥዑም ሚስጥር፤
ጨቅላ እፃናት የሚረዱት እሷ ለኔ አላት ፍቅር።
:
:
ጨቅላ እፃናት ሚገባቸው ሰሙም ወርቁም ማያሻማ፤
ለልብ ሀሴት መጠንሰሻ ሳትናገር የሚሰማ፤
ሁሉ ፈጥኖ የሚረዳው ግልፅ ስሜት ቀላል ቅኔ፤
ላዋቂው ሰው ላስተዋዩ ተሰወረ ምነው ከኔ።
:
:
የፍቅርን ታንኳ ቀዝፋ ከኔ ዘንዳ ስትመጣ፤
እንደ እፃን ስትቦርቅ በደስታ ጮቤ ረግጣ፤
ምትይዝ ምትለቀው ጠፍቷት ጥርሷ ሳይከደን አምሽቶ፤
ከርታታ ዓይኗ ሲስለመለም በእንቅልፍ አጀብ ተረቶ፤
ደረት ክንዴን ተንተርሳ ሰላም እንቅልፍ ተኝታለች፤
ከ አንዴም አንድ ሺህ ግዜ ፍቅሬ አንተነህ ብላኛለች።
:
:
ያ ፍም ስሜት ነበልባሉ ባይኗ ዘልቆ የሚያወራው፤
ቀልብ የሚስብ እጅግ ደማቅ እንደ ሩቢ የሚያበራው፤
ዋጋ ተመን የማይሰፍረው የከበረው ከቀይ እንቁ፤
የቀለም ቀንድ ከሆንኩት ሰው ምነው ከኔ መደበቁ?
:
:
ለኔ ያላት ጥልቅ ፍቅር ልብ ዘልቆ የሚያረካ፤
ንዋይ ከቶ የማይገዛው ባለም ሚዛን የማይለካ፤
መሰረቱ ወለል ጣራው የታነፀ በፅኑ ቃል፤
እንደሆነ እንኳን ሊቁ ደቂቁም ሰው በደንብ ያውቃል።
:
:
ሸክላ ፈራሽ ገላን ቀርቶ ነብሷን ለኔ አትሰስትም፤
እኔ ካለው አጠገቧ ግራዋውም አይመራትም፤
መታያዋም መደበቂያ እኔ እንደሆንኩ ህዝብ ያወራል፤
ልቤ ብቻ ከእውነታው ላይተያይ ተሰውሯል።
:
:
ቀን ከሌሊት ቢያዳምጡት በማይጠገብ አንደበቷ፤
እማሬውም ፍካሬውም አቻ ፍቺ የቃላቷ፤
እኔ ብቻ ሆኜ ሳለው የሷ ድርሰት ነፀብራቁ፤
ታዲያ ምነው ከእውነታው ልባም ልቤ መራራቁ።
:
:
የጭንቀቷ ማራገፊያ ወደቧ ነው ዓይኔን መሳም፤
አንገቴ ስር ስትወሸቅ ይሰማታል ልዩ ሰላም፤
ዘቢብ ስሜት የማይነጥፍ ቀን ሲገፋ ውሎ ሲያድር፤
ደርሶ ሚስጥር ሆኖብኛል የሚታየው ገሀድ ፍቅር።
:
:
ሌላን ነገር ለመረዳት ቅፅበት እንኳን ማይወስድብኝ፤
ግልፁ ፍቅሯ ለምን ይሆን እንዲ ስውር የሆነበኝ?
ልጅ አዋቂው የተረዳው ያደባባይ ግልብ ነገር፤
ባለ ማዕረግ የሆንኩት ሰው እንዴት እኔ ልደናገር?
እያልኩ ሁሌ ደጋግሜ እኔው እኔን ጠይቄያለው፤
ቀለም ቁጥር አመክንዮ አይገልፃትም አውቄያለው።
:
:
ለካ ፍቅርን ለመረዳት ሊቅ ደቂቅን አያካትም፤
ስሜት ስሌት የሆነበት መቼም ቢሆን አያውቃትም።
ለኔ ካለት ፍቅር ጋራም የገባኝን ሳነፃፅር፤
የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ኢምንት ነው የሚያሳፍር።
እናም ለምን እንዳልገባኝ ደጋግሜ ሳውጠነጥን፤
ስሌት እንጂ ስሜት የለኝ የሷን ፍቅር የሚመጥን።
ጠቢቧ ሴት አስተዋዩዋ ረቂቋ የኔ አፍቃሪ፤
ለሌላ ሰው የቀለም ቀንድ ላንቺ ደቂቅ ነኝ ተማሪ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
:
:
ከቅዱስ ተራራ እንደመነጨ ኩልል ብሎ እንደጠራ፤
እንደ ጎበዝ ገበሬ ዘር እልፍ አላፍት የሚያፈራ፤
ልክ እንደ ፀደይ ሰማይ፤
ወለል ብሎ እንደሚታይ፤
ልዩ ስሜት እንከን የለሽ ያደባባይ ጥዑም ሚስጥር፤
ጨቅላ እፃናት የሚረዱት እሷ ለኔ አላት ፍቅር።
:
:
ጨቅላ እፃናት ሚገባቸው ሰሙም ወርቁም ማያሻማ፤
ለልብ ሀሴት መጠንሰሻ ሳትናገር የሚሰማ፤
ሁሉ ፈጥኖ የሚረዳው ግልፅ ስሜት ቀላል ቅኔ፤
ላዋቂው ሰው ላስተዋዩ ተሰወረ ምነው ከኔ።
:
:
የፍቅርን ታንኳ ቀዝፋ ከኔ ዘንዳ ስትመጣ፤
እንደ እፃን ስትቦርቅ በደስታ ጮቤ ረግጣ፤
ምትይዝ ምትለቀው ጠፍቷት ጥርሷ ሳይከደን አምሽቶ፤
ከርታታ ዓይኗ ሲስለመለም በእንቅልፍ አጀብ ተረቶ፤
ደረት ክንዴን ተንተርሳ ሰላም እንቅልፍ ተኝታለች፤
ከ አንዴም አንድ ሺህ ግዜ ፍቅሬ አንተነህ ብላኛለች።
:
:
ያ ፍም ስሜት ነበልባሉ ባይኗ ዘልቆ የሚያወራው፤
ቀልብ የሚስብ እጅግ ደማቅ እንደ ሩቢ የሚያበራው፤
ዋጋ ተመን የማይሰፍረው የከበረው ከቀይ እንቁ፤
የቀለም ቀንድ ከሆንኩት ሰው ምነው ከኔ መደበቁ?
:
:
ለኔ ያላት ጥልቅ ፍቅር ልብ ዘልቆ የሚያረካ፤
ንዋይ ከቶ የማይገዛው ባለም ሚዛን የማይለካ፤
መሰረቱ ወለል ጣራው የታነፀ በፅኑ ቃል፤
እንደሆነ እንኳን ሊቁ ደቂቁም ሰው በደንብ ያውቃል።
:
:
ሸክላ ፈራሽ ገላን ቀርቶ ነብሷን ለኔ አትሰስትም፤
እኔ ካለው አጠገቧ ግራዋውም አይመራትም፤
መታያዋም መደበቂያ እኔ እንደሆንኩ ህዝብ ያወራል፤
ልቤ ብቻ ከእውነታው ላይተያይ ተሰውሯል።
:
:
ቀን ከሌሊት ቢያዳምጡት በማይጠገብ አንደበቷ፤
እማሬውም ፍካሬውም አቻ ፍቺ የቃላቷ፤
እኔ ብቻ ሆኜ ሳለው የሷ ድርሰት ነፀብራቁ፤
ታዲያ ምነው ከእውነታው ልባም ልቤ መራራቁ።
:
:
የጭንቀቷ ማራገፊያ ወደቧ ነው ዓይኔን መሳም፤
አንገቴ ስር ስትወሸቅ ይሰማታል ልዩ ሰላም፤
ዘቢብ ስሜት የማይነጥፍ ቀን ሲገፋ ውሎ ሲያድር፤
ደርሶ ሚስጥር ሆኖብኛል የሚታየው ገሀድ ፍቅር።
:
:
ሌላን ነገር ለመረዳት ቅፅበት እንኳን ማይወስድብኝ፤
ግልፁ ፍቅሯ ለምን ይሆን እንዲ ስውር የሆነበኝ?
ልጅ አዋቂው የተረዳው ያደባባይ ግልብ ነገር፤
ባለ ማዕረግ የሆንኩት ሰው እንዴት እኔ ልደናገር?
እያልኩ ሁሌ ደጋግሜ እኔው እኔን ጠይቄያለው፤
ቀለም ቁጥር አመክንዮ አይገልፃትም አውቄያለው።
:
:
ለካ ፍቅርን ለመረዳት ሊቅ ደቂቅን አያካትም፤
ስሜት ስሌት የሆነበት መቼም ቢሆን አያውቃትም።
ለኔ ካለት ፍቅር ጋራም የገባኝን ሳነፃፅር፤
የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ኢምንት ነው የሚያሳፍር።
እናም ለምን እንዳልገባኝ ደጋግሜ ሳውጠነጥን፤
ስሌት እንጂ ስሜት የለኝ የሷን ፍቅር የሚመጥን።
ጠቢቧ ሴት አስተዋዩዋ ረቂቋ የኔ አፍቃሪ፤
ለሌላ ሰው የቀለም ቀንድ ላንቺ ደቂቅ ነኝ ተማሪ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
አውቃለሁ አልነገርኩሽም
አሞኝ ባዝን ምን ብከፋ
ከሞላ ሰው ከዚህ ሁሉ!
ሚያስታምመኝ ሰው ቢጠፋ
ሳቄን ለምደሽ ሳቅ ብነፍግሽ
ተቀየመ! ያንች መልስሽ
ግን አይደለ ሀቅ እውነታው!
የሳቀ ሁሉ አይደል ደስታው!
በራሁ ባለው ፈገግታዬ
ታጭቆ አለ ትዝታዬ
ስብራቴ ሰው ማጣቴ
አስመሳዩ እኔነቴ
አለው የሚለኝ ወዳጅ ባጣ
ዘውትር ድዴ ደጅ ሲሰጣ
አንድም በመናፈቅ!
አንድም በፍርሀት
ስትኖር ነፍሴ በስቅላት
አውቃለሁ አልነገርኩሽም!!
ልቤን ስሰጥ ጥሩ ላልኩት
ሳይሆን ሲቀር እንዳሰብኩት
ስሰባበር ዶቃ ሆኜ
እንዲያነሳኝ ሰው ለምኜ
ስንቴ እንዳፈርኩ በፍጥረቴ
ታውቀዋለች እመቤቴ
በ ኪሩቤል አሰፋ
@Ebuh_bhr
@getem
@getem
@getem
አሞኝ ባዝን ምን ብከፋ
ከሞላ ሰው ከዚህ ሁሉ!
ሚያስታምመኝ ሰው ቢጠፋ
ሳቄን ለምደሽ ሳቅ ብነፍግሽ
ተቀየመ! ያንች መልስሽ
ግን አይደለ ሀቅ እውነታው!
የሳቀ ሁሉ አይደል ደስታው!
በራሁ ባለው ፈገግታዬ
ታጭቆ አለ ትዝታዬ
ስብራቴ ሰው ማጣቴ
አስመሳዩ እኔነቴ
አለው የሚለኝ ወዳጅ ባጣ
ዘውትር ድዴ ደጅ ሲሰጣ
አንድም በመናፈቅ!
አንድም በፍርሀት
ስትኖር ነፍሴ በስቅላት
አውቃለሁ አልነገርኩሽም!!
ልቤን ስሰጥ ጥሩ ላልኩት
ሳይሆን ሲቀር እንዳሰብኩት
ስሰባበር ዶቃ ሆኜ
እንዲያነሳኝ ሰው ለምኜ
ስንቴ እንዳፈርኩ በፍጥረቴ
ታውቀዋለች እመቤቴ
በ ኪሩቤል አሰፋ
@Ebuh_bhr
@getem
@getem
@getem
. ዝም አትበል ግታ
ከፂዎን አዳራሽ የህግ ታቦቴን
የለም ሚጋርዳት የቃል ኪዳን ቤቴን
እያልክ የፃፍክልን ያቺ የቃልህ ርዕሷ
ፈርሷል በጠላት ሰይፍ የክብር መቅደሷ
በቀስተ ዳመና ዎቶ ተዘርግቶ ይነጠፍ ልባሷ
አለምም እንድትድን ተዳኝታ በሷ
ብዙ ሰው ይሞታል ድንገት በወጣበት
አንስቶ ቀባሪ አልቃሽ በለለበት
ፈጥነን እዳንመጣ አንተ ወዳለህበት
በጠላት ታጥረናል አቅምን ስጠን ጉልበት
ዝም አትበል ጌታ ይዘርጉ እጆችህ
ሲሞቱ እያየህ አማኝ ልጆችህ
በቃልህ ፀንተው አንተን እየጠበቁ
በጠላት ሰይፍ ታርደው ስቶች አለቁ
@getem
@getem
@getem
By @Habtishe01
ከፂዎን አዳራሽ የህግ ታቦቴን
የለም ሚጋርዳት የቃል ኪዳን ቤቴን
እያልክ የፃፍክልን ያቺ የቃልህ ርዕሷ
ፈርሷል በጠላት ሰይፍ የክብር መቅደሷ
በቀስተ ዳመና ዎቶ ተዘርግቶ ይነጠፍ ልባሷ
አለምም እንድትድን ተዳኝታ በሷ
ብዙ ሰው ይሞታል ድንገት በወጣበት
አንስቶ ቀባሪ አልቃሽ በለለበት
ፈጥነን እዳንመጣ አንተ ወዳለህበት
በጠላት ታጥረናል አቅምን ስጠን ጉልበት
ዝም አትበል ጌታ ይዘርጉ እጆችህ
ሲሞቱ እያየህ አማኝ ልጆችህ
በቃልህ ፀንተው አንተን እየጠበቁ
በጠላት ሰይፍ ታርደው ስቶች አለቁ
@getem
@getem
@getem
By @Habtishe01
"ኦሪዮን"!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ያቺ የኔ ናርዶስ ፣ የነፍስያ ከርቤ
አትራቂው በሏት፣
ጠረኗን ልመገብ ፣ ላሽትታት ቀርቤ፡፡
ከዘመናት ደዌ፣
ከአልጋ ቁራኝ ፣ተርትሮ ሚያ´ስነሳ
ላረጀ ጎልማሳ፣
ልጅነት አድሎ ፣ እርጅና ሚነሳ
የጨመተ ልብን፣
በብርሀን ፍጥነት ፣ ዝማሜ ሚሞላ
አላት አንዳች ሚስጥር ፣ አላት አንዳች መላ፡፡
ልፈልጋት ወጣሁ፣ ልቤ ተራመደ
እግሬ ግን ምን ነካው፣
ከርምጃ ታግዶ፣ ምነው ተጋመደ ?
ከርምጃዬ ጋራ ፣ ፍልሚያ ተጋጥሜ
አሰስኩት ሰፈሯን፣
የአባቷን አጥር ፣ ዙሪያ ተጠምጥሜ፡፡
የለችም አጣኋት፣
ርቋል ከመንደሩ ፣ ጠረኗም አይሸትም
ድምጿም አይሰማ፣ ማንም አይጠራትም
(በስውር ወጥታለች፣ ማንም አላያትም፡፡
አላት መከተሚያ ፣ ስትሆን ብቻዋን
ለነጠላ ነፍሷ ፣ ስትፈልግ አቻዋን፡፡
ከቤቷ በታች ነው፣ ያ ሽንጣም አሸንዳ
ወገቧን ይመስላል፣
ከተራራው ጥጋት ፣ ቁልቁል ሲከነዳ!
ከፈፋው ላይ ወርዶ፣ አሸዋው ላይ ያርፋል
አለትን ከመሬት ፣ አስሮ ይጋረፋል!!
ያቻትና አየኋት፣
ወራጅ ወንዙ መሀል ፣ ድንጋይ ላይ ቆማለች
ያችን ክንፋም ኮከብ፣ ኦሪዮንን መስላለች፡፡
ፀጉሯን ነሰነሰው ፣ ያ ዜመኛ ንፋስ
ጠረኗን ላከልኝ ፣ ለኔ ስስ እስትንፋስ
ደሞ ዝቅ አለና ፣ ደረቷን ገለጠው
መንቶ ጡቷ ማሀል፣ ዐይኔን አስቀመጠው
"ሸርቧ ሸርተት አለ ፣ መለሰችው በጇ
አክናዷን አየሁት ፣ ሲገለጥ ግዳጇ!"
ንፋሱ ይነፍሳል፣
እየደረደረ ፣ ለቀሚሷ ዜማ
ያካሏን ትርምስ ፣ ፍጥረት እንዲሰማ፡፡
አያታለሁ እኔ
እኔን አታየኝም!
ከወንዙ ዳር ያለ ፣ ዛፍ ላይ ተንጠልጥዬ
በንፋሱ ዜማ፣
በአካሏ ቅኝት ፣ በምርኮ ተጥዬ!
ተራመደች ደግሞ፣ ……
ከለምለሙ ሳር ላይ ፣ ተንጋላ አረፈችው
ፈረሰኛ ልቤን፣ ሌጣውን ጫነችው
በሰመመን ከድና ፣ አዐይኗን ጨፈነችው፡፡
ዐይኔ ካይኗ ቀረ ፣ እዛው ተሰንቅሮ
ከሷ ተወዳጀ ፣ ከኔ ተቃቅሮ፡፡
ንፋሱ ያዜመል ፣ ይቀኛል አሁንም
ከሷ ትንፋሽ በቀር ፣ አይሰማም ምንም!!!
(የልብ ጆሮዎች፣ በምርኮ ሲወድቁ
ሁሉን ነገር ንቀው፣
ገዢን በማድመጥ ነው፣ ነፍስን የሚያፀድቁ፡፡)
አእዋፍ አያዜሙም፣ ቀትር ነው ለነሱ
የእጸዋት ቅጠሎች፣
አይወድቁም ከዛፉ ፣ ከምድር አይነሱ፡፡
በቃ በዚህ ቅጽበት
የሚሰማው ቅኔ ፣ የሶስታችን ቋንቋ
የንፋሱ ዜማ፣
ያካሏ ዳንስ እና ፣ የኔ ነፍስ ጭንቋ፡፡
ድንገት ብታየኝስ ፣ ቅኘቷን ብታቆም
ብዬ ፈርቼ ነው፣
ፍለፊቷ ሄጄ ፣ ቀርቢያት የማልቆም፡፡
ብቻ!
እድሜ ለዛ ንፋስ!
ምን አጎደለብኝ፣
አካሏን አስቃኝቶ
ጠረኗን አሽቶቶ
ፈውስ መግቦኛል ፣ በጄ'ኳ ባልነካት
መንፈሷ ደርሶኛል ፣ ባካለም ባይልካት!
ዐይኔን አልነቀልኩም፣ ከዐይኖቿ ጓዳ
አንገቴን አሳረፍኩ ፣ ከደረቷ ሜዳ
እኔም ልክ እንደሷ አይኔን ከድኛለሁ
ግን አልተከለልኩም፣
ካለሁባት ዓለም፣
በጥፍ የምታምር፣ ሌላ ዓለም አያለሁ፡፡
አይኖቼን ከድኜ ፣ ዓለምን ካየኋት!
መንቃትስ ለምኔ ፣ ዐይን ገልጦ መሄድ
እኔን ካለተሳነኝ፣
የፍቅሯን አውድማ ፣ እሸሮሮ ማሄድ!!
ዓለም ደና ሰንብች፣
የብቻዬን ገነት ፣ ከሷ ጋር ልኑራት
ጭለማን አናይም፣ አለች የኔ መብራት
እንተኛ ዘላለም ፣ እንቅለፍ እንዳትነሱን
በኔና በሷ አለም፡
ሁሌም ቀን ነውና፤
ቢመሸም ቢነጋም ፣ እንዳትቀሰቅሱን !!
By Dagim hiwot
@getem
@getem
@paappii
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ያቺ የኔ ናርዶስ ፣ የነፍስያ ከርቤ
አትራቂው በሏት፣
ጠረኗን ልመገብ ፣ ላሽትታት ቀርቤ፡፡
ከዘመናት ደዌ፣
ከአልጋ ቁራኝ ፣ተርትሮ ሚያ´ስነሳ
ላረጀ ጎልማሳ፣
ልጅነት አድሎ ፣ እርጅና ሚነሳ
የጨመተ ልብን፣
በብርሀን ፍጥነት ፣ ዝማሜ ሚሞላ
አላት አንዳች ሚስጥር ፣ አላት አንዳች መላ፡፡
ልፈልጋት ወጣሁ፣ ልቤ ተራመደ
እግሬ ግን ምን ነካው፣
ከርምጃ ታግዶ፣ ምነው ተጋመደ ?
ከርምጃዬ ጋራ ፣ ፍልሚያ ተጋጥሜ
አሰስኩት ሰፈሯን፣
የአባቷን አጥር ፣ ዙሪያ ተጠምጥሜ፡፡
የለችም አጣኋት፣
ርቋል ከመንደሩ ፣ ጠረኗም አይሸትም
ድምጿም አይሰማ፣ ማንም አይጠራትም
(በስውር ወጥታለች፣ ማንም አላያትም፡፡
አላት መከተሚያ ፣ ስትሆን ብቻዋን
ለነጠላ ነፍሷ ፣ ስትፈልግ አቻዋን፡፡
ከቤቷ በታች ነው፣ ያ ሽንጣም አሸንዳ
ወገቧን ይመስላል፣
ከተራራው ጥጋት ፣ ቁልቁል ሲከነዳ!
ከፈፋው ላይ ወርዶ፣ አሸዋው ላይ ያርፋል
አለትን ከመሬት ፣ አስሮ ይጋረፋል!!
ያቻትና አየኋት፣
ወራጅ ወንዙ መሀል ፣ ድንጋይ ላይ ቆማለች
ያችን ክንፋም ኮከብ፣ ኦሪዮንን መስላለች፡፡
ፀጉሯን ነሰነሰው ፣ ያ ዜመኛ ንፋስ
ጠረኗን ላከልኝ ፣ ለኔ ስስ እስትንፋስ
ደሞ ዝቅ አለና ፣ ደረቷን ገለጠው
መንቶ ጡቷ ማሀል፣ ዐይኔን አስቀመጠው
"ሸርቧ ሸርተት አለ ፣ መለሰችው በጇ
አክናዷን አየሁት ፣ ሲገለጥ ግዳጇ!"
ንፋሱ ይነፍሳል፣
እየደረደረ ፣ ለቀሚሷ ዜማ
ያካሏን ትርምስ ፣ ፍጥረት እንዲሰማ፡፡
አያታለሁ እኔ
እኔን አታየኝም!
ከወንዙ ዳር ያለ ፣ ዛፍ ላይ ተንጠልጥዬ
በንፋሱ ዜማ፣
በአካሏ ቅኝት ፣ በምርኮ ተጥዬ!
ተራመደች ደግሞ፣ ……
ከለምለሙ ሳር ላይ ፣ ተንጋላ አረፈችው
ፈረሰኛ ልቤን፣ ሌጣውን ጫነችው
በሰመመን ከድና ፣ አዐይኗን ጨፈነችው፡፡
ዐይኔ ካይኗ ቀረ ፣ እዛው ተሰንቅሮ
ከሷ ተወዳጀ ፣ ከኔ ተቃቅሮ፡፡
ንፋሱ ያዜመል ፣ ይቀኛል አሁንም
ከሷ ትንፋሽ በቀር ፣ አይሰማም ምንም!!!
(የልብ ጆሮዎች፣ በምርኮ ሲወድቁ
ሁሉን ነገር ንቀው፣
ገዢን በማድመጥ ነው፣ ነፍስን የሚያፀድቁ፡፡)
አእዋፍ አያዜሙም፣ ቀትር ነው ለነሱ
የእጸዋት ቅጠሎች፣
አይወድቁም ከዛፉ ፣ ከምድር አይነሱ፡፡
በቃ በዚህ ቅጽበት
የሚሰማው ቅኔ ፣ የሶስታችን ቋንቋ
የንፋሱ ዜማ፣
ያካሏ ዳንስ እና ፣ የኔ ነፍስ ጭንቋ፡፡
ድንገት ብታየኝስ ፣ ቅኘቷን ብታቆም
ብዬ ፈርቼ ነው፣
ፍለፊቷ ሄጄ ፣ ቀርቢያት የማልቆም፡፡
ብቻ!
እድሜ ለዛ ንፋስ!
ምን አጎደለብኝ፣
አካሏን አስቃኝቶ
ጠረኗን አሽቶቶ
ፈውስ መግቦኛል ፣ በጄ'ኳ ባልነካት
መንፈሷ ደርሶኛል ፣ ባካለም ባይልካት!
ዐይኔን አልነቀልኩም፣ ከዐይኖቿ ጓዳ
አንገቴን አሳረፍኩ ፣ ከደረቷ ሜዳ
እኔም ልክ እንደሷ አይኔን ከድኛለሁ
ግን አልተከለልኩም፣
ካለሁባት ዓለም፣
በጥፍ የምታምር፣ ሌላ ዓለም አያለሁ፡፡
አይኖቼን ከድኜ ፣ ዓለምን ካየኋት!
መንቃትስ ለምኔ ፣ ዐይን ገልጦ መሄድ
እኔን ካለተሳነኝ፣
የፍቅሯን አውድማ ፣ እሸሮሮ ማሄድ!!
ዓለም ደና ሰንብች፣
የብቻዬን ገነት ፣ ከሷ ጋር ልኑራት
ጭለማን አናይም፣ አለች የኔ መብራት
እንተኛ ዘላለም ፣ እንቅለፍ እንዳትነሱን
በኔና በሷ አለም፡
ሁሌም ቀን ነውና፤
ቢመሸም ቢነጋም ፣ እንዳትቀሰቅሱን !!
By Dagim hiwot
@getem
@getem
@paappii
አጉብጠን ጋላቢ፣
ከሂዎት ቀንጫቢ፣
ከብርድ ላይ ላቢ፣
ከደርቅ ጡት ጠቢ፣
ሆንን ለጦቢያይቱ
ገዳይና አሳቢ፣
እስከመቼ እንሁን ደረቅ ዘር ደራቢ፣
_
የሆነች ሀገር ትናፍቀኛለች
__
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat ^^
@getem
@getem
@getem
ከሂዎት ቀንጫቢ፣
ከብርድ ላይ ላቢ፣
ከደርቅ ጡት ጠቢ፣
ሆንን ለጦቢያይቱ
ገዳይና አሳቢ፣
እስከመቼ እንሁን ደረቅ ዘር ደራቢ፣
_
የሆነች ሀገር ትናፍቀኛለች
__
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat ^^
@getem
@getem
@getem
በሽተኛ አፍቃሪ
እሱ:- ውዴ ፍቅሬ ሆዴ ዛሬ ምን ሁነሻል
እንደተለመደው ዛሬንም አሞሻል?
እኔ:- አላመመኝሞ
እሱ:-ታዲያ ምን ሁነሻል?
አፍሽ ለመናገር ያሰበ ይመስላል
ልታወሪ ስትይ ጉሮሮሽ ያንቅሻል
አይኖችሽም ሊያዩኝ የፈሩኝ ይመስላል
እባክሽ ንገሪኝ ልቤ ተረብሿል
እኔ:-እ.....ምን መሰለህ
ዛሬ የመጣሁት እውነቱን ልነግርህ
ከሆዴ ያለውን ሁሉን ላጫውትህ
ነውና እንዳታቋርጠኝ አዳምጠኝ ዝምብለህ
እንደሚታወቀው ከተዋወቅን አንስቶ ሁልጊዜ ያመኛል
ያጥወለውለኛል ሆዴን ይቆርጠኛል
ብዙ ብዙ ነገር ያደራርገኛል
ግን እውነቱን ልንገርህ
መስሜትን ትሻለህ
በቃ ውሸቴን ነው ታምሜ አላውቅም
ራሴን ደና ነኝ ሆዴን አያመኝም
በተገናኘን ቀን.....
ብርድብርድ ብሎኛል እያልኩ ማስመሰሌ
ስለሚገኝ ነው ከቅፍህ ሰላሜ
የውሸት መንቀጥቀጤ እንዲያ መንዘርዘሬ
ስለቴ ሁኖ ነው በቅፍህ መኖሬ
እንድታቅፈኝ 'ኮነው እንዲያ እንዲ መሆኔ
ደሞ በሌላ ቀን......
ዛሬ ደና አድለው ራሴን አሞኛል
መቆምም አልቻልኩም በጣም አዙሮኛል
ላንተ ባይገባህም እኔ ግን ያንን ስል
ማለቴ ነበረ ግንባሬን ብትስመኝ በ1ዴ ይሻለኛል
ደሞ በሌላ ቀን.......
መራመድ አቃተኝ ጉልበቴ ታመመ
እግሬ እምቢ ብሎኛል አልላወስ አለ
ልቤ ግን ነበረ እዘለኝ እያለ
አንተ ግን
እየገባህ ይሆን ወይ እየጠረጠርክ
ራሴን አመመኝ ስልህም እየሳምክ
ብርድ ብርድ ብሎኛል ስልህም እያቀፍክ
መራመድ አልቻልኩም ስልህም እያዘልክ
ይህን ሁሉ እያ'ረክ አብረን ቆይተናል
በሽተኛ አፍቃሪህ ያሰበችው ሁሉ ተሰካክቶላታል
ካላደፈረሰው የውሸት ህመሜ
ስለምወድህ 'ኮ ነው የዋሸሁ አለሜ
ብዙ ስለዋሸህ
ይቅርታ እባክህ
እሱ :-በመገረም በፈገግታ እያያት
የኔ በሽተኛ.. ብሎ አቀፋት
By @Meswatttt
@getem
@getem
@getem
እሱ:- ውዴ ፍቅሬ ሆዴ ዛሬ ምን ሁነሻል
እንደተለመደው ዛሬንም አሞሻል?
እኔ:- አላመመኝሞ
እሱ:-ታዲያ ምን ሁነሻል?
አፍሽ ለመናገር ያሰበ ይመስላል
ልታወሪ ስትይ ጉሮሮሽ ያንቅሻል
አይኖችሽም ሊያዩኝ የፈሩኝ ይመስላል
እባክሽ ንገሪኝ ልቤ ተረብሿል
እኔ:-እ.....ምን መሰለህ
ዛሬ የመጣሁት እውነቱን ልነግርህ
ከሆዴ ያለውን ሁሉን ላጫውትህ
ነውና እንዳታቋርጠኝ አዳምጠኝ ዝምብለህ
እንደሚታወቀው ከተዋወቅን አንስቶ ሁልጊዜ ያመኛል
ያጥወለውለኛል ሆዴን ይቆርጠኛል
ብዙ ብዙ ነገር ያደራርገኛል
ግን እውነቱን ልንገርህ
መስሜትን ትሻለህ
በቃ ውሸቴን ነው ታምሜ አላውቅም
ራሴን ደና ነኝ ሆዴን አያመኝም
በተገናኘን ቀን.....
ብርድብርድ ብሎኛል እያልኩ ማስመሰሌ
ስለሚገኝ ነው ከቅፍህ ሰላሜ
የውሸት መንቀጥቀጤ እንዲያ መንዘርዘሬ
ስለቴ ሁኖ ነው በቅፍህ መኖሬ
እንድታቅፈኝ 'ኮነው እንዲያ እንዲ መሆኔ
ደሞ በሌላ ቀን......
ዛሬ ደና አድለው ራሴን አሞኛል
መቆምም አልቻልኩም በጣም አዙሮኛል
ላንተ ባይገባህም እኔ ግን ያንን ስል
ማለቴ ነበረ ግንባሬን ብትስመኝ በ1ዴ ይሻለኛል
ደሞ በሌላ ቀን.......
መራመድ አቃተኝ ጉልበቴ ታመመ
እግሬ እምቢ ብሎኛል አልላወስ አለ
ልቤ ግን ነበረ እዘለኝ እያለ
አንተ ግን
እየገባህ ይሆን ወይ እየጠረጠርክ
ራሴን አመመኝ ስልህም እየሳምክ
ብርድ ብርድ ብሎኛል ስልህም እያቀፍክ
መራመድ አልቻልኩም ስልህም እያዘልክ
ይህን ሁሉ እያ'ረክ አብረን ቆይተናል
በሽተኛ አፍቃሪህ ያሰበችው ሁሉ ተሰካክቶላታል
ካላደፈረሰው የውሸት ህመሜ
ስለምወድህ 'ኮ ነው የዋሸሁ አለሜ
ብዙ ስለዋሸህ
ይቅርታ እባክህ
እሱ :-በመገረም በፈገግታ እያያት
የኔ በሽተኛ.. ብሎ አቀፋት
By @Meswatttt
@getem
@getem
@getem
#ወረኛ_ነው_እያልሽ
:
:
የቤቴን ገመና ዘራብኝ አውጥቶ፣
ያሽሟጡብኝ ጀመር ሀገር ሁሉ ሰምቶ።
አደባባይ ወጣ ጉዴን አዳረሰው፣
በምላሱ ስለት ገመናዬን ማሰው።
፡
፡
አጋሬ ነው ብዬ ሁሉንም ብነግረው የልቤን ዘርዝሬ፣
ሹክ ቱስ እያለ ያደባባይ ሚስጥር ሆነብኝ ሚስጥሬ።
በ'ኔና አንተ ይቅር ብዬ የነገርኩትን የጓዳዬን እውነት፣
ከ እንቅልፉ ተነስቶ አፉን አሟሸበት።
፡
፡
እንዲ እንዲ እያልሽ ላየሺው ሰው ሁሉ፣
የኔን ወረኛነት ትሰብኪያለሽ አሉ።
፡
፡
እውነቱ ግን እየው እውነቱን ግን ስሚ፣
ከቆሰልሽም ቁሰይ ከደማሽም ድሚ።
፡
፡
የኛኑ ገመና አውጥቼ አልበተንኩም፣
እንዲ ናትም ብዬ ለማንም አላልኩም።
ግን የሚያሳዝነው ማስተዋል ተስኖሽ እንደ ቸኮለ ጅብ ቀንድ እንደሚነክሰው፣
ተናግረሽ አረፍሺው ወሬ ሰምቶ ቢያድር በቃኝ ለማይል ሰው።
፡
፡
እኔን ያማሽ መስሎሽ የምላስሽን በትር፣
ወረኛ ነው እያልሽ በምሽት በቀትር፣
እየሰነዘርሺው ልክ ላንቺው ቢጤ ወሬን አሰንቆ አሽሙር ለሚጠጣ፣
እድሜ ላንቺ ፍቅሬ የቤታችን ጓዳ አደባባይ ወጣ።
፡
፡
እውነቱ ግን እየው እውነቱን ግን ስሚ፣
ከቆሰልሽም ቁሰይ ከደማሽም ድሚ።
፡
፡
ያሳብሽ ከረጢት የሚስጥርሽ ዋሻ የስሜትሽ ማህደር፣
ቢከፋሽ ቢለማሽ ሁሉን ሚሸክፈው አንድ ልቤ ነበር።
ምን ቢለበልበኝ ካንቺ አይበልጥም ብዬ በቻልኩት እሳቱን፣
ዳሩ ምን ይረባል ባደባባይ ደገስሽ ደጅ ጥደሽ ድስቱን።
ከጀማሽ መካከል ሚገስፅ ሚቆጣሽ ተይ የሚልሽ ጠፋ፣
ሀሜት ነው ቅኝቱ ቱልቱላሽ ሲነፋ።
፡
፡
የሚገርመው ነገር ካለስም ስም ሰተሽ ብትለጥፊብኝም፣
ላንቺ ይብላኝ እንጂ አምተሺኛል ብዬ እኔስ አልከፋኝም።
ይባስ ደስ ብሎኛል ክበሪልኝ ፍቅሬ፣
አይደለሁም እንጂ ወረኛ እንኳ ብሆን ወሬን ያስተማርሺኝ የወሬ መምህሬ፣
አንቺ መሆንሽን ባደባባይ ቆመሽ መስክረሻል ዛሬ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
:
:
የቤቴን ገመና ዘራብኝ አውጥቶ፣
ያሽሟጡብኝ ጀመር ሀገር ሁሉ ሰምቶ።
አደባባይ ወጣ ጉዴን አዳረሰው፣
በምላሱ ስለት ገመናዬን ማሰው።
፡
፡
አጋሬ ነው ብዬ ሁሉንም ብነግረው የልቤን ዘርዝሬ፣
ሹክ ቱስ እያለ ያደባባይ ሚስጥር ሆነብኝ ሚስጥሬ።
በ'ኔና አንተ ይቅር ብዬ የነገርኩትን የጓዳዬን እውነት፣
ከ እንቅልፉ ተነስቶ አፉን አሟሸበት።
፡
፡
እንዲ እንዲ እያልሽ ላየሺው ሰው ሁሉ፣
የኔን ወረኛነት ትሰብኪያለሽ አሉ።
፡
፡
እውነቱ ግን እየው እውነቱን ግን ስሚ፣
ከቆሰልሽም ቁሰይ ከደማሽም ድሚ።
፡
፡
የኛኑ ገመና አውጥቼ አልበተንኩም፣
እንዲ ናትም ብዬ ለማንም አላልኩም።
ግን የሚያሳዝነው ማስተዋል ተስኖሽ እንደ ቸኮለ ጅብ ቀንድ እንደሚነክሰው፣
ተናግረሽ አረፍሺው ወሬ ሰምቶ ቢያድር በቃኝ ለማይል ሰው።
፡
፡
እኔን ያማሽ መስሎሽ የምላስሽን በትር፣
ወረኛ ነው እያልሽ በምሽት በቀትር፣
እየሰነዘርሺው ልክ ላንቺው ቢጤ ወሬን አሰንቆ አሽሙር ለሚጠጣ፣
እድሜ ላንቺ ፍቅሬ የቤታችን ጓዳ አደባባይ ወጣ።
፡
፡
እውነቱ ግን እየው እውነቱን ግን ስሚ፣
ከቆሰልሽም ቁሰይ ከደማሽም ድሚ።
፡
፡
ያሳብሽ ከረጢት የሚስጥርሽ ዋሻ የስሜትሽ ማህደር፣
ቢከፋሽ ቢለማሽ ሁሉን ሚሸክፈው አንድ ልቤ ነበር።
ምን ቢለበልበኝ ካንቺ አይበልጥም ብዬ በቻልኩት እሳቱን፣
ዳሩ ምን ይረባል ባደባባይ ደገስሽ ደጅ ጥደሽ ድስቱን።
ከጀማሽ መካከል ሚገስፅ ሚቆጣሽ ተይ የሚልሽ ጠፋ፣
ሀሜት ነው ቅኝቱ ቱልቱላሽ ሲነፋ።
፡
፡
የሚገርመው ነገር ካለስም ስም ሰተሽ ብትለጥፊብኝም፣
ላንቺ ይብላኝ እንጂ አምተሺኛል ብዬ እኔስ አልከፋኝም።
ይባስ ደስ ብሎኛል ክበሪልኝ ፍቅሬ፣
አይደለሁም እንጂ ወረኛ እንኳ ብሆን ወሬን ያስተማርሺኝ የወሬ መምህሬ፣
አንቺ መሆንሽን ባደባባይ ቆመሽ መስክረሻል ዛሬ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
ልሂድ ባልሽኝ ቁጥር
ስንቴ አንቺን ልሸኝሽ
በር ድረስ ወጣሁ
ሸኝቼሽ ስመለስ
አንቺን ነው ማገኘው
እራሴን እያጣሁ
እንዴት አትይኝም...
እንደዘበት መርሳት
ላይችል አቅፎ ሰንበር
እንዴት ሄድሽ ልበል
ትዝታሽ ጠብቆ እየከፈተልኝ በር
ግን ግን ....
የሚለኝ አይጠፍም
ስትሄድ ሸኝቷት አያዝናል እንዴ ደግሞ
መኖር ይባላል ወይ
ካቀፉት ገላ ስር ልብ ሲሸሽ ቀድሞ
አየሽ የኔን ህይወት
ከዕለት ለት እያደር
ቢጠጥርም ከአለት
ከመሄድሽ በላይ
ትዝታን መርሳት ነው
አንቺ የለሽም ማለት
አትጠራጠሪ
የሚሆነው ሁሉ
ስለሆነ አይደለም
በአንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም
የኔ ያልሆነን ነው
አግኝቼ የማጣው
ያለፍኩትን ታሪክ
ባሻገረኝ ድልድይ
ዘወር ብዬ ሳየው
በእርሱ ፍቃድ እንጂ
በምኞቴ አይደለም
ዛሬ የሚለየው
አዎን እመኛለሁ
የተመኘሁትን አንቺን አግኝቻለሁ
ያገኘሁትንም አንቺን አጥቻለሁ
ባጣሁት ነገር ላይ
ፈፅሞ አልከፋም
ለምን እከፋለሁ
እንኳን የኔ ያልኩሽ
አግኝቼ ላጣሁሽ
እኔ እንኳን እራሴ
የራሴው አይደለሁ
ያ ደግሞ ምንድን ነው
የሚሆነው ሁሉ ስለ ሆነ አይደለም
በአንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም
የኔ ያልሆነን ነው
አግኝቼ የማጣው
@getem
@getem
@paappii
By #Abel man
ስንቴ አንቺን ልሸኝሽ
በር ድረስ ወጣሁ
ሸኝቼሽ ስመለስ
አንቺን ነው ማገኘው
እራሴን እያጣሁ
እንዴት አትይኝም...
እንደዘበት መርሳት
ላይችል አቅፎ ሰንበር
እንዴት ሄድሽ ልበል
ትዝታሽ ጠብቆ እየከፈተልኝ በር
ግን ግን ....
የሚለኝ አይጠፍም
ስትሄድ ሸኝቷት አያዝናል እንዴ ደግሞ
መኖር ይባላል ወይ
ካቀፉት ገላ ስር ልብ ሲሸሽ ቀድሞ
አየሽ የኔን ህይወት
ከዕለት ለት እያደር
ቢጠጥርም ከአለት
ከመሄድሽ በላይ
ትዝታን መርሳት ነው
አንቺ የለሽም ማለት
አትጠራጠሪ
የሚሆነው ሁሉ
ስለሆነ አይደለም
በአንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም
የኔ ያልሆነን ነው
አግኝቼ የማጣው
ያለፍኩትን ታሪክ
ባሻገረኝ ድልድይ
ዘወር ብዬ ሳየው
በእርሱ ፍቃድ እንጂ
በምኞቴ አይደለም
ዛሬ የሚለየው
አዎን እመኛለሁ
የተመኘሁትን አንቺን አግኝቻለሁ
ያገኘሁትንም አንቺን አጥቻለሁ
ባጣሁት ነገር ላይ
ፈፅሞ አልከፋም
ለምን እከፋለሁ
እንኳን የኔ ያልኩሽ
አግኝቼ ላጣሁሽ
እኔ እንኳን እራሴ
የራሴው አይደለሁ
ያ ደግሞ ምንድን ነው
የሚሆነው ሁሉ ስለ ሆነ አይደለም
በአንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም
የኔ ያልሆነን ነው
አግኝቼ የማጣው
@getem
@getem
@paappii
By #Abel man
እዩ ኬር የቤት እቃዎችን ጥገና
--------------------------------------
- የፍሪጅ
- የልብስ ማጠቢያ
- የኦቭን
- የማይክሮ ዌቭ
ከበቂ የወረቀት ዋስትና ጋር የጥገና አገልግሎት እንሰጣለን።
#ለደረሰኙ ጭንቅ አይበሎት።
+251974716100
+251922919247 ይደውሉ
https://t.me/eyucare
--------------------------------------
- የፍሪጅ
- የልብስ ማጠቢያ
- የኦቭን
- የማይክሮ ዌቭ
ከበቂ የወረቀት ዋስትና ጋር የጥገና አገልግሎት እንሰጣለን።
#ለደረሰኙ ጭንቅ አይበሎት።
+251974716100
+251922919247 ይደውሉ
https://t.me/eyucare
የቃል ጦር መማዘዝ፣
ለማይፀና ጫጉላ፣
በሰለለ ፍቅር፣
እንደማምሻ ጥላ፣
እርምን ላያወጡ፣
ደጋግሞ መጋደል፣
ይሰለቻል አይደል?
ሐገር በመረቀው፣
በኔና አንተ ምላሽ፣
ፈገግታችን ታይታ፣
ሳቃችን ሰው ሰራሽ።
ወይ አልተናበብን፣
ገመና አልከተትን፣
ያንዳችንን ሕልፈት፣
ሌላችን አልሞትን።
ዘፍነው ላጣመሩን፣
የውሸት ብንስቅም፣
ከአልባሳችን ማዶ፣
ተያይተን አናውቅም።
የት የያዘን ፍቅር?
የት የገባን መውደድ?
ዘመን ሊያሻግረን፣
በመሳሳብ መንገድ?
ከገላህ የሚተርፍ፣
ቢኖር ያጠናሁት፣
ላንተ ያለኝን ስስት፣
ዛሬ ባላጣሁት።
ከማማሬ ማዶ፣
ነፍስህ ብታይ ነፍሴን፣
ልብህ ባልቋመጠ፣
ሽሽት እስትንፋሴን።
እርምን ላያወጡ ፣
ደጋግሞ መጋደል፣
ይሰለቻል አይደል?
በማዕዶት ያየህ
14/07/2015 ዓ.ም.
@getem
@getem
@paappii
ለማይፀና ጫጉላ፣
በሰለለ ፍቅር፣
እንደማምሻ ጥላ፣
እርምን ላያወጡ፣
ደጋግሞ መጋደል፣
ይሰለቻል አይደል?
ሐገር በመረቀው፣
በኔና አንተ ምላሽ፣
ፈገግታችን ታይታ፣
ሳቃችን ሰው ሰራሽ።
ወይ አልተናበብን፣
ገመና አልከተትን፣
ያንዳችንን ሕልፈት፣
ሌላችን አልሞትን።
ዘፍነው ላጣመሩን፣
የውሸት ብንስቅም፣
ከአልባሳችን ማዶ፣
ተያይተን አናውቅም።
የት የያዘን ፍቅር?
የት የገባን መውደድ?
ዘመን ሊያሻግረን፣
በመሳሳብ መንገድ?
ከገላህ የሚተርፍ፣
ቢኖር ያጠናሁት፣
ላንተ ያለኝን ስስት፣
ዛሬ ባላጣሁት።
ከማማሬ ማዶ፣
ነፍስህ ብታይ ነፍሴን፣
ልብህ ባልቋመጠ፣
ሽሽት እስትንፋሴን።
እርምን ላያወጡ ፣
ደጋግሞ መጋደል፣
ይሰለቻል አይደል?
በማዕዶት ያየህ
14/07/2015 ዓ.ም.
@getem
@getem
@paappii
ሰው ፈለኩኝ ሰው አጣሁኝ
ልጠጋው ስል ከእኔ ይርቃል
ከሰው ጋራ ሰው ለመሆን
ሰው መሆንን ይጠይቃል
በሰው ደጃፍ አንጋጠጥኩኝ
ተዘግቶብኝ የእውነት በር
እስከዛሬ ስፈልገው
ለካ ያጣሁት እኔን ነበር።
*
*
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@getem
ልጠጋው ስል ከእኔ ይርቃል
ከሰው ጋራ ሰው ለመሆን
ሰው መሆንን ይጠይቃል
በሰው ደጃፍ አንጋጠጥኩኝ
ተዘግቶብኝ የእውነት በር
እስከዛሬ ስፈልገው
ለካ ያጣሁት እኔን ነበር።
*
*
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@getem