*ምን ነበረ?*
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)
፡
ምን ነበረ ማፍቀር ምን ነበረ መውደድ፣
አብሮ ሰጥሞ መጓዝ መክነፍ በአንድ መንገድ፣
፡
ምን ነበር መናፈቅ ምንድነው ትዝታ፣
እያሰቡ መኖር ሁሌም በትውስታ፣
የሗሌት መመለስ ዳክሮ ጠዋት ማታ፣
፡
ምላስ ላይ ከሞተ ምላስ ላይ ተወልዶ፣
አንጀት ካላራሰ ከልብ ላይ ወርዶ፣
፡
አካል ካላሳየው ካልኖረው ህይወቱ፣
ነፍስ ካልዘራበት ወዲያ ካ'ንደበቱ፣
ፍቅር ቃል ከሆነ እውነት ማፍቀር ከንቱ፣
፡
ምን ነበር መጣመር ምን ነበር አንድነት፣
በጎጆ ስር መኖር ከሁለት ሶስትነት፣
አንሶ ተወዳጅቶ ደርሶ እጥፍ መብዛት፣
ካ'ንድ ወንዝ ተጨልፎ በጋራ መዋኘት፣
፡
ምን ነበረ?
፡
ልብን ቅስምን ስብሮ ለራቀ ወዳጁ፣
ማንባት ምን ነበረ እንዲመለስ ደጁ፣
፡
መፀፀት ራስ መውቀስ መማፀን ይቅርታ፣
ሰው ወዶ ሰው ማጣት የሰፈነ ለታ፣
፡
ይሄስ ለምንድነው ቆይ ለምንስ ሲባል፣
ራስን በፍቅር ማሰር በራስ ፍም መቃጠል፣
፡
ማን ማንን መሰለ ማንስ ለማን ኖረ፣
አንዱ ላ'ንዱ ማለት አረ ምን ነበረ?፣
ነሐሴ 29/12/09....ሰኞ 3:51 ማታ
@yeneta
@getem
@getem
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)
፡
ምን ነበረ ማፍቀር ምን ነበረ መውደድ፣
አብሮ ሰጥሞ መጓዝ መክነፍ በአንድ መንገድ፣
፡
ምን ነበር መናፈቅ ምንድነው ትዝታ፣
እያሰቡ መኖር ሁሌም በትውስታ፣
የሗሌት መመለስ ዳክሮ ጠዋት ማታ፣
፡
ምላስ ላይ ከሞተ ምላስ ላይ ተወልዶ፣
አንጀት ካላራሰ ከልብ ላይ ወርዶ፣
፡
አካል ካላሳየው ካልኖረው ህይወቱ፣
ነፍስ ካልዘራበት ወዲያ ካ'ንደበቱ፣
ፍቅር ቃል ከሆነ እውነት ማፍቀር ከንቱ፣
፡
ምን ነበር መጣመር ምን ነበር አንድነት፣
በጎጆ ስር መኖር ከሁለት ሶስትነት፣
አንሶ ተወዳጅቶ ደርሶ እጥፍ መብዛት፣
ካ'ንድ ወንዝ ተጨልፎ በጋራ መዋኘት፣
፡
ምን ነበረ?
፡
ልብን ቅስምን ስብሮ ለራቀ ወዳጁ፣
ማንባት ምን ነበረ እንዲመለስ ደጁ፣
፡
መፀፀት ራስ መውቀስ መማፀን ይቅርታ፣
ሰው ወዶ ሰው ማጣት የሰፈነ ለታ፣
፡
ይሄስ ለምንድነው ቆይ ለምንስ ሲባል፣
ራስን በፍቅር ማሰር በራስ ፍም መቃጠል፣
፡
ማን ማንን መሰለ ማንስ ለማን ኖረ፣
አንዱ ላ'ንዱ ማለት አረ ምን ነበረ?፣
ነሐሴ 29/12/09....ሰኞ 3:51 ማታ
@yeneta
@getem
@getem
* ኑ .ዛ . ዜ .***
ጌታ ሆይ....
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ሚስቴን እንዳያይዋት፤
ህይወቷን በሙሉ ቤት ዘግተህ አቆያት።
እነዛ ከዋክብት ፣ አብረቅራቂ አይኖቿን
የማታ ብርሀን ፣ የቀን መኩሪያዎቿን
በሌላ ተማርከው ፣ግራ እንዳይገባቸው
መአቱን አውርደህ ድርግምግም አርጋቸው።
...............................................
ገጣባ አርገህ ተወው ፣ ያንን ሐር ጸጉሯን
ሌላ ከሚያይብኝ ፣;ትቅር ባዶ ቅሏን::
..............
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ቀጥ ብሎ የቆመ ፣ ያን ሰልካካ አፍንጫ
ከርክመህ ጣልልኝ ፣ በያዝከው መቁረጫ
ያንን የሚያሰጎመጅ ፣ ያን እንጆሪ ከንፈር
ፍቀድልኝና.....
ወስላታ ሳይቀምሰው ከ'ኔ ጋር ይቀበር::
....................
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
እነዛ ጡቶቿን ፣ እንደጦር የሰሉ
ኪንታሮት አክለው ፣ የት ሄዱ? ይባሉ
ያንን ችቦ ወገብ ፣ ቀጥኖ የተሰቀለው
ወጥረህ ወጥረህ ፣ ከበሮ አሳክለው::
.
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ጀግና የሚያሳድድ ፣ ያን ኩሩ ዳሌዋን
ድንገት ንሳትና ፣ ትፈልግ ሁዋላዋን።
በማታ በማታ.....
ወጣ ብሎ መግባት ፣ ሁሉ እንዳያምራቸው
እግሮቿን አልምሸህ ፣ መሄድ ይሳናቸው::
..................
ኡፍፍፍ....
እንዲያውም ወፍ አርጋት ፣ በአየር ትመላለስ
ወንድ አንኩዋኩቶ አይጥራት....
ጎጆዋን በዛፍ ላይ ፣ በስንጥር ትቀልስ።
በቃ....
በፍቅር ጎዳና ፣ ሌላ ከሚመራት
ፈቃድህ ከሆነ …
ሳትሞት በቁሟ ፣ ከ'ኔ ጋር ቅበራት።
.
.
አምላኬ....
መቼም መሄዴ ነው...
ጊዜዬን ጨርሼ ፣ መሰናበቴ ነው
ብቻ አደራህን...ብቻ አደራህን...
ከሞትኩኝ በሁዋላ ፣ ማንም እንዳይነካት
ማንም ተመኝቶ ፣ በልቡ እነዳይለካት።
........
በቃ አልፈልግማ ፣ በቃ እንዳያዩብኝ
ከህመሜ ይበልጥ ፣ አልጋ ላይ ከጣለኝ
ከሞትኩኝ በሁዋላ .....
የሌላ ስትሆን ፣ ማሰቡ ነው 'ሚያመኝ::
ጌታ ሆይ....
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ሚስቴን እንዳያይዋት፤
ህይወቷን በሙሉ ቤት ዘግተህ አቆያት።
እነዛ ከዋክብት ፣ አብረቅራቂ አይኖቿን
የማታ ብርሀን ፣ የቀን መኩሪያዎቿን
በሌላ ተማርከው ፣ግራ እንዳይገባቸው
መአቱን አውርደህ ድርግምግም አርጋቸው።
...............................................
ገጣባ አርገህ ተወው ፣ ያንን ሐር ጸጉሯን
ሌላ ከሚያይብኝ ፣;ትቅር ባዶ ቅሏን::
..............
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ቀጥ ብሎ የቆመ ፣ ያን ሰልካካ አፍንጫ
ከርክመህ ጣልልኝ ፣ በያዝከው መቁረጫ
ያንን የሚያሰጎመጅ ፣ ያን እንጆሪ ከንፈር
ፍቀድልኝና.....
ወስላታ ሳይቀምሰው ከ'ኔ ጋር ይቀበር::
....................
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
እነዛ ጡቶቿን ፣ እንደጦር የሰሉ
ኪንታሮት አክለው ፣ የት ሄዱ? ይባሉ
ያንን ችቦ ወገብ ፣ ቀጥኖ የተሰቀለው
ወጥረህ ወጥረህ ፣ ከበሮ አሳክለው::
.
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ጀግና የሚያሳድድ ፣ ያን ኩሩ ዳሌዋን
ድንገት ንሳትና ፣ ትፈልግ ሁዋላዋን።
በማታ በማታ.....
ወጣ ብሎ መግባት ፣ ሁሉ እንዳያምራቸው
እግሮቿን አልምሸህ ፣ መሄድ ይሳናቸው::
..................
ኡፍፍፍ....
እንዲያውም ወፍ አርጋት ፣ በአየር ትመላለስ
ወንድ አንኩዋኩቶ አይጥራት....
ጎጆዋን በዛፍ ላይ ፣ በስንጥር ትቀልስ።
በቃ....
በፍቅር ጎዳና ፣ ሌላ ከሚመራት
ፈቃድህ ከሆነ …
ሳትሞት በቁሟ ፣ ከ'ኔ ጋር ቅበራት።
.
.
አምላኬ....
መቼም መሄዴ ነው...
ጊዜዬን ጨርሼ ፣ መሰናበቴ ነው
ብቻ አደራህን...ብቻ አደራህን...
ከሞትኩኝ በሁዋላ ፣ ማንም እንዳይነካት
ማንም ተመኝቶ ፣ በልቡ እነዳይለካት።
........
በቃ አልፈልግማ ፣ በቃ እንዳያዩብኝ
ከህመሜ ይበልጥ ፣ አልጋ ላይ ከጣለኝ
ከሞትኩኝ በሁዋላ .....
የሌላ ስትሆን ፣ ማሰቡ ነው 'ሚያመኝ::
Hafa:
።።።።ሩብ ጉዳይ ማለት?።።።።
የተቀጣጠርነው ዘጠኝ ሰዐት ነበር
በሰዐቱ ጉድለት
በልቤ ልብ ምት
አንቺ ስትመጪ ሩብ ጨመርሽበት!
ሰዐቱ ልክ ነው.....
ዘጠኝ ከሩብ እውነት!
በነበረን ጊዜ
በሠላሳው ደቂቅ..
ሠላሳ ጉዳዬን አውርቼ ሳልጨርስ
ሩብ ጉዳይ ድርስ!
የማይረባ ሰዐት የልብ የማያደርስ
ሩብ ጉዳይ ይላል...
ጉዳይ ሩብ ሳይደርስ
ሰዕቱ ተሣስቷል
ወይ ሆን ብሎ ዋሽቷል
እኔ አንቺን ማወራሽ ስንት ጉዳይ እያለ
ሩብ ጉዳይ ብሎ ማንን አታለለ?
ምክንያቱስ ምንድነው?
እንድትሄጅ ብሎ ነው?
ነገር ፍለጋ ነው?
ወይስ ተሳስቶ ነው?
የራሱ ጉዳይ ነው!
ብዬ አልተወው ነገር
በሰዐቱ ውሸት አንቺም ተታለሻል
ሩብ ጉዳይ ሚለው
እውነቱን መስሎሻል
ልትሄጅ ተነስተሻል።
✍ሀ.ገ.መ
@getem
@getem
።።።።ሩብ ጉዳይ ማለት?።።።።
የተቀጣጠርነው ዘጠኝ ሰዐት ነበር
በሰዐቱ ጉድለት
በልቤ ልብ ምት
አንቺ ስትመጪ ሩብ ጨመርሽበት!
ሰዐቱ ልክ ነው.....
ዘጠኝ ከሩብ እውነት!
በነበረን ጊዜ
በሠላሳው ደቂቅ..
ሠላሳ ጉዳዬን አውርቼ ሳልጨርስ
ሩብ ጉዳይ ድርስ!
የማይረባ ሰዐት የልብ የማያደርስ
ሩብ ጉዳይ ይላል...
ጉዳይ ሩብ ሳይደርስ
ሰዕቱ ተሣስቷል
ወይ ሆን ብሎ ዋሽቷል
እኔ አንቺን ማወራሽ ስንት ጉዳይ እያለ
ሩብ ጉዳይ ብሎ ማንን አታለለ?
ምክንያቱስ ምንድነው?
እንድትሄጅ ብሎ ነው?
ነገር ፍለጋ ነው?
ወይስ ተሳስቶ ነው?
የራሱ ጉዳይ ነው!
ብዬ አልተወው ነገር
በሰዐቱ ውሸት አንቺም ተታለሻል
ሩብ ጉዳይ ሚለው
እውነቱን መስሎሻል
ልትሄጅ ተነስተሻል።
✍ሀ.ገ.መ
@getem
@getem
Fikre @:
❤️ቅኔ ሁነሽብኝ❤️
:
ቅኔ ሁነሽብኝ
ያልተፈታ ሚስትር;
አልገባህ ብሎኛል
አንች ያደረግሽኝ
የሆንሽልኝ ነገር;
*
አላውቅም እንዳልል
*
ተምሬ ነበረ
ቅኔ ከመምህሬ;
በፍቅርሽ ተይዠ
ሄጀ ተነክሬ;
እጆቸን እግሮቸን
መላው ሠውነቴን
ተይዠ ታስሬ;
እንዴት ይገባኛል
ትምህርትስ ተምሬ;
በታላላቅ ሠወች
ምክር ተመክሬ;
"የቀን እንጅ ....
የሠው የለው ጀግና"
ሲሉ ሰምቻለሁ;
የእኔም ቀን አስክተደርስ
አጠብቃታለሁ;
*
ለአንች ሲዘንብልሽ
እኔ ጋም ሲያካፋ;
እንዲሁ አኖራለሁ
ፈጣሪ አስኪያሳየኝ
እች ቀንም አልፋ;
*
የሆንኩትን ሁለ
እንድትሆኝ አልፈቅድም
ተማሪ ተብለሽ ግን ከተፈረደብሽ ;
እምልልሻለሁ አልጠፋም ከጎንሽ;
አስረዳሻለሁኝ የደረሰብኝን
ሆኘ እንደመምህርሽ;
ተፃፈ"በፍቅረዬሀንስ አባይ"
30/12/2009
ባህር ዳር
@getem
@getem
@getem
❤️ቅኔ ሁነሽብኝ❤️
:
ቅኔ ሁነሽብኝ
ያልተፈታ ሚስትር;
አልገባህ ብሎኛል
አንች ያደረግሽኝ
የሆንሽልኝ ነገር;
*
አላውቅም እንዳልል
*
ተምሬ ነበረ
ቅኔ ከመምህሬ;
በፍቅርሽ ተይዠ
ሄጀ ተነክሬ;
እጆቸን እግሮቸን
መላው ሠውነቴን
ተይዠ ታስሬ;
እንዴት ይገባኛል
ትምህርትስ ተምሬ;
በታላላቅ ሠወች
ምክር ተመክሬ;
"የቀን እንጅ ....
የሠው የለው ጀግና"
ሲሉ ሰምቻለሁ;
የእኔም ቀን አስክተደርስ
አጠብቃታለሁ;
*
ለአንች ሲዘንብልሽ
እኔ ጋም ሲያካፋ;
እንዲሁ አኖራለሁ
ፈጣሪ አስኪያሳየኝ
እች ቀንም አልፋ;
*
የሆንኩትን ሁለ
እንድትሆኝ አልፈቅድም
ተማሪ ተብለሽ ግን ከተፈረደብሽ ;
እምልልሻለሁ አልጠፋም ከጎንሽ;
አስረዳሻለሁኝ የደረሰብኝን
ሆኘ እንደመምህርሽ;
ተፃፈ"በፍቅረዬሀንስ አባይ"
30/12/2009
ባህር ዳር
@getem
@getem
@getem
አቤል አልማዝ ቸብቸብ አርጉላት:
.፡....እንባ 'ና ሣቅ፡.፡.፡.፡
ከሩቅ ይሠማኛል የቅኔ ፊደላት
ባ'ንዱ ደግፍ የሚል ባ'ንዱ ግን ግደላት
ከሩቅ ይሠማኛል ዜማ አልባ ዘፈኖች
ግጥም የማያውቁ የዘመን ዘፋኞች
ከሩቅ ይሠማኛል የሤት እንጉርጉሮ
ካ'ገር የበረረ የናፍቆት እሮሮ
ከሩቅ ይሠማኛል ለጆሮዬ አይሎ
ስጋ እየከተፈ ሲበላ ዘልዝሎ
ደሞ ይነግረኛል ረሀብ ይጠራኛል
ስጋ ከሚበላው አካፍለኝ ይለኛል
ከሩቅ ይሠማኛል የሀገሬ ጩኸት
የሚሠማኝ አጣው ለኔ የሚሟገት
ስትል ስትል ስትል ስትል ስትል
ስ....?......ል........ስ....ን.....ል...
የታፈነ ጩኸት የታፈነውን ህልም
አቤል አልማዝ
@getem
@getem
.፡....እንባ 'ና ሣቅ፡.፡.፡.፡
ከሩቅ ይሠማኛል የቅኔ ፊደላት
ባ'ንዱ ደግፍ የሚል ባ'ንዱ ግን ግደላት
ከሩቅ ይሠማኛል ዜማ አልባ ዘፈኖች
ግጥም የማያውቁ የዘመን ዘፋኞች
ከሩቅ ይሠማኛል የሤት እንጉርጉሮ
ካ'ገር የበረረ የናፍቆት እሮሮ
ከሩቅ ይሠማኛል ለጆሮዬ አይሎ
ስጋ እየከተፈ ሲበላ ዘልዝሎ
ደሞ ይነግረኛል ረሀብ ይጠራኛል
ስጋ ከሚበላው አካፍለኝ ይለኛል
ከሩቅ ይሠማኛል የሀገሬ ጩኸት
የሚሠማኝ አጣው ለኔ የሚሟገት
ስትል ስትል ስትል ስትል ስትል
ስ....?......ል........ስ....ን.....ል...
የታፈነ ጩኸት የታፈነውን ህልም
አቤል አልማዝ
@getem
@getem
Yougin:
(ባዶ)ከደጃች ዮኒ ብላታ
ከወደድከኝ ከምር ዝለልና አሣየኝ ብለሽ ያልሽኝ እለት
ጉልበቴ እሥኪከዳኝ አንቺን ለማሥደሠት
እንጠለጠላለዉ ዉጣ ካልሽኝ ቤት
ዳግሞ በሌላቀን ከዘፈኑ ተርታ የመደብሽኝ እንደዉ
አይኔ ንዲሁ ያድራል ላንቺ ማይገባ ወዲያ ጣል አያልኩኝ ግጥሙን ሥሞግተዉ
እሩጥና ልይህ የሚሉት ቃሎችሽ ከጆሮዬ ሲደርሥ
እፈተለካለሁ ከመሮጫዉ ትራክ መሀረብ በጥሼ ባንዲራሽን ልለብሥ
እራሥህን ሆንህ ካላየሁህ ብለሽ የወተወትሽ ለታ
ያኔ ነው ሥጋቴ
የእኔነት ክብር ያላገኘው እርሥቴ
ከማንነት ክራር ተበጥሶ ወድቋል የህይወት ጅማቴ
ማን ተብሎ ሊሠጥ ባዶ ቅል ኔነቴ
(ባዶ)ከደጃች ዮኒ ብላታ
ከወደድከኝ ከምር ዝለልና አሣየኝ ብለሽ ያልሽኝ እለት
ጉልበቴ እሥኪከዳኝ አንቺን ለማሥደሠት
እንጠለጠላለዉ ዉጣ ካልሽኝ ቤት
ዳግሞ በሌላቀን ከዘፈኑ ተርታ የመደብሽኝ እንደዉ
አይኔ ንዲሁ ያድራል ላንቺ ማይገባ ወዲያ ጣል አያልኩኝ ግጥሙን ሥሞግተዉ
እሩጥና ልይህ የሚሉት ቃሎችሽ ከጆሮዬ ሲደርሥ
እፈተለካለሁ ከመሮጫዉ ትራክ መሀረብ በጥሼ ባንዲራሽን ልለብሥ
እራሥህን ሆንህ ካላየሁህ ብለሽ የወተወትሽ ለታ
ያኔ ነው ሥጋቴ
የእኔነት ክብር ያላገኘው እርሥቴ
ከማንነት ክራር ተበጥሶ ወድቋል የህይወት ጅማቴ
ማን ተብሎ ሊሠጥ ባዶ ቅል ኔነቴ