ኮሮናና ናፍቆት፤
✍ ✍ ✍
በዚህ ቀውጢ ጊዜ …
ብቻዬን ቁጭ ብዬ - ያስታወስኩሽ ለታ፥
የቁንጅናሽ ጥቅል - ዓይኔ ላይ ሲፈታ፥
መራቅሽ ሲያደክመኝ፥
ከማልወጣው አቀበት - የርቀት ኮረብታ፥
ህዝቤን አስጨንቆ - አንቺን ስላሳጣኝ!
ኮሮና የሚባል ከምድር እንዲጠፋ - ልቤ ተመኘልሽ፥
ውዴ መጥተሽልኝ፥
አቅፌ ልስምሽ - ስናፍቅ መሸልሽ፤
❤️ ❤️
በዚያ የወሸባ እለት፥
እያሰብኩሽ መሸ - ለብቻዬ ሁኜ፥
ያን እለት ማታ - ከሰማይ ጽልማሞት፥
ከኮከቦች ድርድር - ያንቺን ምስል ስዬ፥
የኔና አንቺን ነገር - ለጨረቃ አውርቼ፥
የፍቅር ብሶቴን - ሰምታኝ ስታበቃ፥
እሷም ጨክናበኝ - ባትመልስ ጨረቃ…🌙
አንገቴን ሰብሬ...
የህዋውን አምላክ - አጥብቄ ጠየኩት፥🙏
ይሄን ደዌ ኣንሳ - ምህረት አውርድ አልኩት፤
መራራቅን ረቶ - ፍቅራችን እንዲበልጥ፥
የምናቤን ሠላም- በገሐድ እንዲገልጥ፥
ማይነጥፍ እዝነቱን - ፈውሱን ተማጸንኩት፥
የእረፍታችንን ቀን - እንዲያቀርብ ጠየኩት፤
እናም ውዴ - አንቺን በሆዴ ይዤ - እንዳቀረከርኩኝ...
"ከቆንጆ ቀን ጋራ የኔን ቆንጆ አምጣ!" - እያልኩኝ፥
ብቻዬን ለመንኩኝ... 🙏🙏🙏
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ/
ግንቦት/2012)
@EliasGebru
@getem
@getem
✍ ✍ ✍
በዚህ ቀውጢ ጊዜ …
ብቻዬን ቁጭ ብዬ - ያስታወስኩሽ ለታ፥
የቁንጅናሽ ጥቅል - ዓይኔ ላይ ሲፈታ፥
መራቅሽ ሲያደክመኝ፥
ከማልወጣው አቀበት - የርቀት ኮረብታ፥
ህዝቤን አስጨንቆ - አንቺን ስላሳጣኝ!
ኮሮና የሚባል ከምድር እንዲጠፋ - ልቤ ተመኘልሽ፥
ውዴ መጥተሽልኝ፥
አቅፌ ልስምሽ - ስናፍቅ መሸልሽ፤
❤️ ❤️
በዚያ የወሸባ እለት፥
እያሰብኩሽ መሸ - ለብቻዬ ሁኜ፥
ያን እለት ማታ - ከሰማይ ጽልማሞት፥
ከኮከቦች ድርድር - ያንቺን ምስል ስዬ፥
የኔና አንቺን ነገር - ለጨረቃ አውርቼ፥
የፍቅር ብሶቴን - ሰምታኝ ስታበቃ፥
እሷም ጨክናበኝ - ባትመልስ ጨረቃ…🌙
አንገቴን ሰብሬ...
የህዋውን አምላክ - አጥብቄ ጠየኩት፥🙏
ይሄን ደዌ ኣንሳ - ምህረት አውርድ አልኩት፤
መራራቅን ረቶ - ፍቅራችን እንዲበልጥ፥
የምናቤን ሠላም- በገሐድ እንዲገልጥ፥
ማይነጥፍ እዝነቱን - ፈውሱን ተማጸንኩት፥
የእረፍታችንን ቀን - እንዲያቀርብ ጠየኩት፤
እናም ውዴ - አንቺን በሆዴ ይዤ - እንዳቀረከርኩኝ...
"ከቆንጆ ቀን ጋራ የኔን ቆንጆ አምጣ!" - እያልኩኝ፥
ብቻዬን ለመንኩኝ... 🙏🙏🙏
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ/
ግንቦት/2012)
@EliasGebru
@getem
@getem
እርሾ
ብርሃን ከሌለ ጨለማው ላይነጋ
ሊጡ እንጀራ ላይሆን ጋጋሪው ቢተጋ
ምነው የአባይ እርሾ ጣና ተዘነጋ
✍ @sanaanaf
13/07/12
@getem
@getem
@yega_mastawesha
ብርሃን ከሌለ ጨለማው ላይነጋ
ሊጡ እንጀራ ላይሆን ጋጋሪው ቢተጋ
ምነው የአባይ እርሾ ጣና ተዘነጋ
✍ @sanaanaf
13/07/12
@getem
@getem
@yega_mastawesha
መርሳትን መርሳት ፪
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።።።።።።።።
እኔማ አልችልበት፥
አድሮ ነገር መርሳት፥ በትንታ ቆጥሬ
እኖራለሁ እንጂ፥
ሀቄን በማተቤ፥
ኪዳኔን በልቤ ባንጀቴ ቋጥር።
ወረድኩኝ ተረተር ፥
ወንዙን ተሻገርኩት ፥ አቀበትም ወጣሁ
ከተራራ ጀርባ
ብቀልስም ጎጆ…
መጣህ በሀሳቤ ፥ የሚያስረሳኝ አጣሁ።
(ሀገሬንም ተውኳት
እናቴን ራቅኋት፥
ሄድኩኝ ተሰድጄ ፥ ፍቅርህን ልሻገር
ሰውነት ከነሳኝ፥
ሰው ሰው ካልሸተተ ፥ ምን ያደርጋል ሀገር።)
ከቤታችን በታች፥
ካለችው ግራር ስር ፥ ትዝታ ዘርተናል
ሳናርም ሳናጭድ፥
እንደብኩን አራሽ፥
"ለወፍ ሲሳይ ትተን ፥ ፍቅርን በትነናል።
አልችልበት እኔ፥
በልቤ ያለን ቅጽ ፥
ገንጥሎ መጣሉን ፥ እንዳይበጀኝ ሳውቀው
ከዘመን ምድጃ፥
የከሰመን እውነት ፥
እያርገበገብኩኝ
ላላያይዘው ነው፥ ትዝታ እምሞቀው።
አንተማ ልባም ነህ፥
ከትዝታህ መስኖ ፥ ወረት አጠብቅም
ወፍ ከበላው አዝርት፥
ጎታ ሙሉ ምርትን ፥ ፈጽሞ አትናፍቅም።
በትላንት ትዝታ፥
የዳነን በሽታ ፥ ደግሞ ልታስገረሽ
የዛሬ ስንዴህን፥
በማብሰልሰል ካፊያ፥ በዋግ ልታስጠረሽ
አትለፋም እንደኔ።
ታውቀዋለህና፥
እንዳይበጅህ ከቶ
ከሌለ ሰው ገላ ፥ ማደርን ከቅፉ
ነገላይ ለመድረስ ፥ በትላንት ጎዳና መደነቃቀፉ።
እኔ ግን እንዲህ ነኝ፥
"ያለፈውን ልርሳው" ፥ እያልኩኝ ስነሳ
"ምን ነበር ምረሳው? "
በሚል ዝንጋዔ ፥ መልሼ ሳነሳ
ይኼው አለሁ ዛሬም፥
ልረሳህ እያልኩኝ ፥ መርሳቴን ስረሳ።
@getem
@getem
@getem
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።።።።።።።።
እኔማ አልችልበት፥
አድሮ ነገር መርሳት፥ በትንታ ቆጥሬ
እኖራለሁ እንጂ፥
ሀቄን በማተቤ፥
ኪዳኔን በልቤ ባንጀቴ ቋጥር።
ወረድኩኝ ተረተር ፥
ወንዙን ተሻገርኩት ፥ አቀበትም ወጣሁ
ከተራራ ጀርባ
ብቀልስም ጎጆ…
መጣህ በሀሳቤ ፥ የሚያስረሳኝ አጣሁ።
(ሀገሬንም ተውኳት
እናቴን ራቅኋት፥
ሄድኩኝ ተሰድጄ ፥ ፍቅርህን ልሻገር
ሰውነት ከነሳኝ፥
ሰው ሰው ካልሸተተ ፥ ምን ያደርጋል ሀገር።)
ከቤታችን በታች፥
ካለችው ግራር ስር ፥ ትዝታ ዘርተናል
ሳናርም ሳናጭድ፥
እንደብኩን አራሽ፥
"ለወፍ ሲሳይ ትተን ፥ ፍቅርን በትነናል።
አልችልበት እኔ፥
በልቤ ያለን ቅጽ ፥
ገንጥሎ መጣሉን ፥ እንዳይበጀኝ ሳውቀው
ከዘመን ምድጃ፥
የከሰመን እውነት ፥
እያርገበገብኩኝ
ላላያይዘው ነው፥ ትዝታ እምሞቀው።
አንተማ ልባም ነህ፥
ከትዝታህ መስኖ ፥ ወረት አጠብቅም
ወፍ ከበላው አዝርት፥
ጎታ ሙሉ ምርትን ፥ ፈጽሞ አትናፍቅም።
በትላንት ትዝታ፥
የዳነን በሽታ ፥ ደግሞ ልታስገረሽ
የዛሬ ስንዴህን፥
በማብሰልሰል ካፊያ፥ በዋግ ልታስጠረሽ
አትለፋም እንደኔ።
ታውቀዋለህና፥
እንዳይበጅህ ከቶ
ከሌለ ሰው ገላ ፥ ማደርን ከቅፉ
ነገላይ ለመድረስ ፥ በትላንት ጎዳና መደነቃቀፉ።
እኔ ግን እንዲህ ነኝ፥
"ያለፈውን ልርሳው" ፥ እያልኩኝ ስነሳ
"ምን ነበር ምረሳው? "
በሚል ዝንጋዔ ፥ መልሼ ሳነሳ
ይኼው አለሁ ዛሬም፥
ልረሳህ እያልኩኝ ፥ መርሳቴን ስረሳ።
@getem
@getem
@getem
#ዝም #ዝም
ሆድ ከሀገር ይሰፋል~ በሚሉባት ሀገር
አፍ ከአለም መስፋቱን ~ለማን እንናገር ?
ለማን እንናገር ~ እኮ ለማ እንማው
አፍ ባጋለው ሐገር~ምጣድ ነው
ሚሰማው
#ሰማ #ሰማ #ብለን
በቶሎ ተጋግረን ~ በጊዜ እንዳንወጣ
በሰማ ምጣድ ላይ ~ የሚያሰፋ መጣ
የሚያሰፋው መጣ ~ሊጡን አንጠልጥሎ
ማልዶ ሊማግድህ ~ ነፃ ላውጣህ ብሎ
ተናገር ይልሀል ~ አስከብር መብትህን
እንዳሻህ ተጠቀም ~ ሰብአዊነትህን
#እኔ ግን #እላለሁ
በንግግር ብቃት ~ እልፎች ቢጀግኑም
አንድ ሺህ ምላሶች ~አንድ ጆሮ አይሆኑም
በምላስ ተስቦ ~ ከሰነባበተ
ጆሮን ይከልላል ~ አፍ ከተከፈተ
#እኔ #ጠይቃለሁ
የወል ጥያቄህ ላይ
ያለ ሀሳብ ተኝተው ~ ሠው ለሚያንተርሱ
መናገር አይደል ወይ ~ ዝም ማለት ራሱ
#እኔ #ሞግታለሁ
ሐሳብን በመግለፅ ~ በመናገር አለም
ዝም የማለት መብቱን~የሚያስከብር የለም
#እኔ #እጠቁማለሁ
በነፃነት ጥላ ~ ግብሩ የተከለለ
በመናገር መብት ውስጥ~ዝም የማለት አለ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@getem
@getem
@getem
ሆድ ከሀገር ይሰፋል~ በሚሉባት ሀገር
አፍ ከአለም መስፋቱን ~ለማን እንናገር ?
ለማን እንናገር ~ እኮ ለማ እንማው
አፍ ባጋለው ሐገር~ምጣድ ነው
ሚሰማው
#ሰማ #ሰማ #ብለን
በቶሎ ተጋግረን ~ በጊዜ እንዳንወጣ
በሰማ ምጣድ ላይ ~ የሚያሰፋ መጣ
የሚያሰፋው መጣ ~ሊጡን አንጠልጥሎ
ማልዶ ሊማግድህ ~ ነፃ ላውጣህ ብሎ
ተናገር ይልሀል ~ አስከብር መብትህን
እንዳሻህ ተጠቀም ~ ሰብአዊነትህን
#እኔ ግን #እላለሁ
በንግግር ብቃት ~ እልፎች ቢጀግኑም
አንድ ሺህ ምላሶች ~አንድ ጆሮ አይሆኑም
በምላስ ተስቦ ~ ከሰነባበተ
ጆሮን ይከልላል ~ አፍ ከተከፈተ
#እኔ #ጠይቃለሁ
የወል ጥያቄህ ላይ
ያለ ሀሳብ ተኝተው ~ ሠው ለሚያንተርሱ
መናገር አይደል ወይ ~ ዝም ማለት ራሱ
#እኔ #ሞግታለሁ
ሐሳብን በመግለፅ ~ በመናገር አለም
ዝም የማለት መብቱን~የሚያስከብር የለም
#እኔ #እጠቁማለሁ
በነፃነት ጥላ ~ ግብሩ የተከለለ
በመናገር መብት ውስጥ~ዝም የማለት አለ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@getem
@getem
@getem
የኮሮና መዳኒት
ሰሜን ደቡብ ~ ምስራቅ ምዕራቡ
ከኮሮና ፀድቶ ~ ሰላም ይሁን ልቡ
ክፉ አይንኳው ~ ወገን ባለው ይተጋገዝ
ያለው ለሌለው ~ ያለቺውን ያግዝ
በብሄር በጎሳ ~ አይከለል ድንበር
በሽታው አይመርጥም ~ ሀይማኖት ቋንቋና ዘር
ስማኝ ወገኔ ~ ጊዜ በጣም ከፍቷል
ያለን ስናሸሽ ~ ሞት በርላይ ቆሟል
መፍራት አያስፈልግ ~ መጨነቅ አብዝቶ
ዋናው መጠንቀቅነው ~ መልክቱን ሰምቶ
እጅታጠቡ ሲባል ~ እንደቀልድ ስንቆጥረው
ማክስ አድርጉ ሲባል ~ ስንል መታፈንነው
ምክሮቹን ስንንቅ ~ አይንካንም ብለን
እየበዛ ሲሄድ ~ መግቢያ እናጣለን
አውቀን ስንንቀው ~ አላወቁም ብሎ
እየከፋ መቶቷል ~ እያደር ውሎ
የቻይና በሽታ ~ የአውሮፓ ነው ሲባል
ሁሉንም ነካክትቷል ~ ሁሉን ይገላል
መዳኒት የለው ~ ብር አይገድበው
ቴክኖሎጂ እንኳን ~ ችሎ አላሸነፈው
አገራት ቢሮጡ ~ ቀን ማታ ሳይመርጡ
ፈጣሪን ካልያዙ ~ ምንም አያመጡ
ጥያቄው እኛ ጋር ~ መልሱም እኛ ጋራ
በጣም ቀላል ነው ~ ቢመስለን ተራራ
አምላክን መለመን ~ በንፁህ ልቡ ሆኖ
መዳኒቱ ለእግዜር ~ መገዛትነው ታምኖ
19/09/2012
@cokabu
@getem
@getem
ዳዳ coffee
ሰሜን ደቡብ ~ ምስራቅ ምዕራቡ
ከኮሮና ፀድቶ ~ ሰላም ይሁን ልቡ
ክፉ አይንኳው ~ ወገን ባለው ይተጋገዝ
ያለው ለሌለው ~ ያለቺውን ያግዝ
በብሄር በጎሳ ~ አይከለል ድንበር
በሽታው አይመርጥም ~ ሀይማኖት ቋንቋና ዘር
ስማኝ ወገኔ ~ ጊዜ በጣም ከፍቷል
ያለን ስናሸሽ ~ ሞት በርላይ ቆሟል
መፍራት አያስፈልግ ~ መጨነቅ አብዝቶ
ዋናው መጠንቀቅነው ~ መልክቱን ሰምቶ
እጅታጠቡ ሲባል ~ እንደቀልድ ስንቆጥረው
ማክስ አድርጉ ሲባል ~ ስንል መታፈንነው
ምክሮቹን ስንንቅ ~ አይንካንም ብለን
እየበዛ ሲሄድ ~ መግቢያ እናጣለን
አውቀን ስንንቀው ~ አላወቁም ብሎ
እየከፋ መቶቷል ~ እያደር ውሎ
የቻይና በሽታ ~ የአውሮፓ ነው ሲባል
ሁሉንም ነካክትቷል ~ ሁሉን ይገላል
መዳኒት የለው ~ ብር አይገድበው
ቴክኖሎጂ እንኳን ~ ችሎ አላሸነፈው
አገራት ቢሮጡ ~ ቀን ማታ ሳይመርጡ
ፈጣሪን ካልያዙ ~ ምንም አያመጡ
ጥያቄው እኛ ጋር ~ መልሱም እኛ ጋራ
በጣም ቀላል ነው ~ ቢመስለን ተራራ
አምላክን መለመን ~ በንፁህ ልቡ ሆኖ
መዳኒቱ ለእግዜር ~ መገዛትነው ታምኖ
19/09/2012
@cokabu
@getem
@getem
ዳዳ coffee
#እንቆቅልሽ_ቅኔ
.
ጫጫታ
ኳኳታ
በወረሰው አለም
ከዝምታ ልቆ ነፍስን የሚቀጣ ምንም ህመም የለም
.
እያለች
አይኖቿን ጨፍና ከራሷ ስታመልጥ
በምናቧ አለም ማደሪያዋን ስትረግጥ
.
ታያለች...
የመብራት ብልጭታ
የጠርሙስ ኳኳታ
የጠጪ ድንፋታ
የሙዚቃ ጩኸት የደናሽ ጋጋታ
ሁሉ እየታወሰ ነፍሷን ሲያስገርማት
ደግሞ ትነቃለች ታያለች ባዶ ድስት
ሞልቶ የጎደለ ልክ እንደ 'ርሷ አይነት
.
ደግሞ ትቃኛለች የቤቷን ሠውነት
እዚያ ማዶ ፍራሽ ዘመን ያደቀቀው
የነተበ አልጋ ልብስ የተቀዳደደ
ርቃን ሠውነትን ማልበስ የለመደ
.
ደግሞ ሣጥን መሣይ
ስሩን ምስጥ የበላው
ገላን መሸፈኛ ጥቂት ጨርቅ የያዘ
ሌላ ግብር ያለው ወገብ የሚያሳርፍ እየወዘወዘ
.
ደግሞ ስኒ ነኝ ባይ መልኩን የዘነጋ
ከጀበናው ጋራ ዘውትር የሚያወጋ
.
ዝ ብ ር ቅ ር ቅ ያለ ቤት
ልክ እንደ ርሷ ዓይነት
.
ታያለች ባዶ ውስጥ
ለራስ የሚገለጥ
.
ድንገት ሣታስበው ከዐይኗ እንባ ይፈሳል
በደረቀ ጉንጯን ወንዝ ሆኖ ያርሳል
.
ተሠማት ኳኳታ ሳንቃዋ ሲከፈት
ሰዓቷን አየችው ተሠዓቱ ይላል
ለካስ ትንሳኤ ነው ልጇ ፊቷ ቆሟል
.
እንባዋን በራፊ እየጠራረገች
ፈ ገ ግ ትላለች
በጣም ያስገርማል መሣቅ ትችላለች
.
ዐይኖቹን በስስት ትመለከትና 'ልጄ' ትለዋለች
'እማዬ' ይላታል በጨለመ ቀኗ ብርሃን ያሳያታል
ስለ ተማሪ ቤት ይተርክላታል
እያገላበጠ ደግሞ ይስማታል
መኖር ያስመኛታል
.
ደግሞ ይጠይቃል የማያልቅ ጥያቄ
ርሷም ትለዋለች ልጄ ምን አውቄ
'እማዬ ' ይላታል
ትለዋለች 'ልጄ'
እንቆቅልሽ ስልሽ በይኝ ምን አውቄ
እኔ ልጠይቅሽ ጥያቄ አርቅቄ
.
እንቅቅልሽ
ምን አውቅልህ
ዐይኗን ተኩላ ገበያ ምትወጣ
ብሎ ይጠይቃታል
ድንግጥ ትላለች
ልቧ ይሸበራል ፍርሃት ትወርሳለች
እንጃ ! ትለዋለች
በቃ ካላወቅሽው ሌላ ልጠይቅሽ
.
እንቆቅልሽ
ምነ አውቅልህ ልጄ
ፀጉሯን አበጥራ ገበያ ምትወጣ
ብሎ ይጠይቃል
ዐይኗ እንባ አቅርሮ ነፍሷ ይጨነቃል
ርሱ መቼ ገባው መልሺ ይላታል
.
በውስጧ ትለላለች
ዐይኖቿን ተኩላ ገበያ ምትወጣ
ፀጉሯን አበጥራ ገበያ ምትወጣ
ከቶ ከኔ ውጪ ሌላ ማን ሊመጣ
ትላለች በውስጧ
በልጇ እንቆቅልሽ ታይቷት መገለጧ
ዝም ትለዋለች
ደግሞ ዐይኑን ታያለች
.........//..........
በሔለን ፋንታሁን
፲፮-፱-፳፻፲፪ ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
.
ጫጫታ
ኳኳታ
በወረሰው አለም
ከዝምታ ልቆ ነፍስን የሚቀጣ ምንም ህመም የለም
.
እያለች
አይኖቿን ጨፍና ከራሷ ስታመልጥ
በምናቧ አለም ማደሪያዋን ስትረግጥ
.
ታያለች...
የመብራት ብልጭታ
የጠርሙስ ኳኳታ
የጠጪ ድንፋታ
የሙዚቃ ጩኸት የደናሽ ጋጋታ
ሁሉ እየታወሰ ነፍሷን ሲያስገርማት
ደግሞ ትነቃለች ታያለች ባዶ ድስት
ሞልቶ የጎደለ ልክ እንደ 'ርሷ አይነት
.
ደግሞ ትቃኛለች የቤቷን ሠውነት
እዚያ ማዶ ፍራሽ ዘመን ያደቀቀው
የነተበ አልጋ ልብስ የተቀዳደደ
ርቃን ሠውነትን ማልበስ የለመደ
.
ደግሞ ሣጥን መሣይ
ስሩን ምስጥ የበላው
ገላን መሸፈኛ ጥቂት ጨርቅ የያዘ
ሌላ ግብር ያለው ወገብ የሚያሳርፍ እየወዘወዘ
.
ደግሞ ስኒ ነኝ ባይ መልኩን የዘነጋ
ከጀበናው ጋራ ዘውትር የሚያወጋ
.
ዝ ብ ር ቅ ር ቅ ያለ ቤት
ልክ እንደ ርሷ ዓይነት
.
ታያለች ባዶ ውስጥ
ለራስ የሚገለጥ
.
ድንገት ሣታስበው ከዐይኗ እንባ ይፈሳል
በደረቀ ጉንጯን ወንዝ ሆኖ ያርሳል
.
ተሠማት ኳኳታ ሳንቃዋ ሲከፈት
ሰዓቷን አየችው ተሠዓቱ ይላል
ለካስ ትንሳኤ ነው ልጇ ፊቷ ቆሟል
.
እንባዋን በራፊ እየጠራረገች
ፈ ገ ግ ትላለች
በጣም ያስገርማል መሣቅ ትችላለች
.
ዐይኖቹን በስስት ትመለከትና 'ልጄ' ትለዋለች
'እማዬ' ይላታል በጨለመ ቀኗ ብርሃን ያሳያታል
ስለ ተማሪ ቤት ይተርክላታል
እያገላበጠ ደግሞ ይስማታል
መኖር ያስመኛታል
.
ደግሞ ይጠይቃል የማያልቅ ጥያቄ
ርሷም ትለዋለች ልጄ ምን አውቄ
'እማዬ ' ይላታል
ትለዋለች 'ልጄ'
እንቆቅልሽ ስልሽ በይኝ ምን አውቄ
እኔ ልጠይቅሽ ጥያቄ አርቅቄ
.
እንቅቅልሽ
ምን አውቅልህ
ዐይኗን ተኩላ ገበያ ምትወጣ
ብሎ ይጠይቃታል
ድንግጥ ትላለች
ልቧ ይሸበራል ፍርሃት ትወርሳለች
እንጃ ! ትለዋለች
በቃ ካላወቅሽው ሌላ ልጠይቅሽ
.
እንቆቅልሽ
ምነ አውቅልህ ልጄ
ፀጉሯን አበጥራ ገበያ ምትወጣ
ብሎ ይጠይቃል
ዐይኗ እንባ አቅርሮ ነፍሷ ይጨነቃል
ርሱ መቼ ገባው መልሺ ይላታል
.
በውስጧ ትለላለች
ዐይኖቿን ተኩላ ገበያ ምትወጣ
ፀጉሯን አበጥራ ገበያ ምትወጣ
ከቶ ከኔ ውጪ ሌላ ማን ሊመጣ
ትላለች በውስጧ
በልጇ እንቆቅልሽ ታይቷት መገለጧ
ዝም ትለዋለች
ደግሞ ዐይኑን ታያለች
.........//..........
በሔለን ፋንታሁን
፲፮-፱-፳፻፲፪ ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Tadesse)
እንደምን አደራቹ?
በአካባቢያችን ላይ እንዲኹም በእንቅስቃሴዎቻችን መኻከል ምናገኛቸዉ ''መስማት የተሳናቸዉ'' ሰዎች ምን ያህል ሊነግሩን 'ሚፈልጒትን ነገር እንረዳቸኋለን?
መልካም ቀን!
ግንቦት/ 2012
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
@Mykeyonthestreet
በአካባቢያችን ላይ እንዲኹም በእንቅስቃሴዎቻችን መኻከል ምናገኛቸዉ ''መስማት የተሳናቸዉ'' ሰዎች ምን ያህል ሊነግሩን 'ሚፈልጒትን ነገር እንረዳቸኋለን?
መልካም ቀን!
ግንቦት/ 2012
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
@Mykeyonthestreet
የኗሪ ታዛቢ!
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።
ተይ በሏት ይችን ሰው፥ ምከሯት ትታረም
አጀብ አያሰኝም ፥ጅብ ካህያ መክረም!¡
ታግሼው ነው እንጂ!
እስስት አመልሽን ፥ ስታግለበልቢኝ
ፈርቼሽ አይደለም ፥ እንዳሻሽ ስትገልቢኝ።
ተቻችሎ መክረም!
አንቺ ትብሺ አንተ ፥
በሚል የጋራ ሀሳብ ፥ ፍቅር ካላሰረን
ቤታችን ፈረሰ፥ አውላላ ላይ ቀረን።
እወቂበት በቃ!
ማን የገነባውን ፥ ማን አፍርሶ ያልፋል
በመቻቻል ሲሆን ፥ የኔም ልብ ይሰፋል።
መቼስ ምን ይደረግ!
ጊዜ ላይቀይርሽ !
ታጥቦ ጭቃ አመልሽ ፥ ቀኔን እያስረጀው
(ትኖሪያለሽ እንጂ)
ባኗኗሪነት ነው ፥ እድሜዬን ምፈጀው።
@getem
@getem
@getem
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።
ተይ በሏት ይችን ሰው፥ ምከሯት ትታረም
አጀብ አያሰኝም ፥ጅብ ካህያ መክረም!¡
ታግሼው ነው እንጂ!
እስስት አመልሽን ፥ ስታግለበልቢኝ
ፈርቼሽ አይደለም ፥ እንዳሻሽ ስትገልቢኝ።
ተቻችሎ መክረም!
አንቺ ትብሺ አንተ ፥
በሚል የጋራ ሀሳብ ፥ ፍቅር ካላሰረን
ቤታችን ፈረሰ፥ አውላላ ላይ ቀረን።
እወቂበት በቃ!
ማን የገነባውን ፥ ማን አፍርሶ ያልፋል
በመቻቻል ሲሆን ፥ የኔም ልብ ይሰፋል።
መቼስ ምን ይደረግ!
ጊዜ ላይቀይርሽ !
ታጥቦ ጭቃ አመልሽ ፥ ቀኔን እያስረጀው
(ትኖሪያለሽ እንጂ)
ባኗኗሪነት ነው ፥ እድሜዬን ምፈጀው።
@getem
@getem
@getem
#ቀሽም_ብይን
ምሩቅ ጥበብ ሰሪ
የሸራ ቀበኛ ፥ የቀለም ቀማሪ
ጠቢባን ጠበብቶች
የቀለም አባቶች
የብሩሽ አርበኛ ፥ የኪነት ገማቾች
በዘመን የቆሙት
ከትውልዱ ወጥተው ፥ የሚተዛዘቡት
አልያ ....ዘመን አልፈው
በነጠረ ስራ....
ከኛ ጀምበር ጥላ ፥ በሞገስ የቆሙት
መናኛም.....ሆኑ ...ዝነኛ
ትሁትም ....ሆኑ ....ጉረኛ
እርቃን አፍቃሪዎች!
ምስል ደጋሚዎች!
ምጡቅ አሳቢዎች!
ብቻ.....ሰአሊ የሆኑ
ሸራ የወጠሩ ፥ ብሩሽ የዘገኑ
ሁለት ግዜ ነው.... የሚስሉ
ሁለት ግዜ ነው ....የሚያጤኑ
#አንድ...
በረጅም ግዜ ተመስጦ ...በጥቂት ግዜ መቃኘት
የሚፈለገውን ውበት ፥ ተኩሮ በማየት
በህሊና ችንካር ሸራ
ያኔ ነው ፥ የጥበብ ሽል ፥ ፅንሱ የሚዘራ
#ሁለት...
እንግዲህ በሀሳብ ፥ ምስሉ እንደታያቸው
በውን አለም ሸራ ...ይጫራል ንድፋቸው
አይን እና እጆቻቸው ፥ እኩል እስከቻሉ
የግል አይናቸውን ፥ ለሰው ይቸራሉ
ያዩትን ...ለማውረድ
ፅንፉን ለማዋደደ
ጣጥረው..
ጫጭረው...
ሞንጭረው...
የለቀለቁትን.... አቅመ ጥበብ ቅይጥ
ጋለሪ እያገባ ...ወዳጅ እንዲያቋምጥ
ሁለቴ ተረግዞ...ሁለቴ ይማጣል
አፍቃሪው በርትቶ....
ወላድ ለመጠየቅ ...አውደርይ ይወጣል
በዚህ ኩናቴ ውስጥ...
አንዳቹም ሰአሊ
ልጁን የሰቀለ ፥ በቤት በጋለሪ
እስኪያረጅ ...እስኪሸጥ
ማንጠልጠል ይወዳል ፥ ጭንቁን እንደ ትሪ
የብሩሹ አጣጣል ፥ ቀለም ስብጥሩ
የመልእክቱ ምጥቀት ፥ ብራና ሚስጥሩ
ገለፃው......ውብቱ
ጨረሩ ....ሙቀቱ
ሺህ ግዜ ፥ እልፍ አመት
እኛን ቢገርመንም...
ቢያጅበንም ...ደርሶ
የሁለቴ ምጥ ነው
ዘመን የሚሻገር ፥ በቀለማት ርሶ
አየሽልኝ ውዴ....
እንዲህ ያለውን ሰው
ወሮታው ሲዘከር ስላንጠለጠለ
በምናቤ ጓዳ...
የማይከስም ምስልን...ራሴ ላስጠለለ
አፍቃሪነት ዳሩ...
ከጠቢብም በላይ ...ጥበብ እንዳዘለ
ምስክሬ ነፍሴ
ባገኘው ወረቀ....አንቺን እንደሳለ
ምን ይሆን መስፈርቱ
ማነው የሚረዳ...
አይኔ በከደነ ፥ ገፅታሽ ሲቀዳ
ምስልሽ ሲንቀራወዝ ...በህልሜ ሰሌዳ
በውኔም በወረቀት ፥ ሲብስ በግድግዳ
የብዙ ብዙን ምጥ....አዕላፈ ውልጃ
ከሁለት ግልግል...ካንድ ተኩል ውርጃ
ለማመዛዘኛ....ቢጠፋ ብልሀቱ
ተደብቄ ኖርኩኝ ፥ የመልክሽ ሎሬቱ ።
✍ አብርሀም_ተክሉ ( መርዕድ)
@Abrham_teklu
@getem
@getem
ምሩቅ ጥበብ ሰሪ
የሸራ ቀበኛ ፥ የቀለም ቀማሪ
ጠቢባን ጠበብቶች
የቀለም አባቶች
የብሩሽ አርበኛ ፥ የኪነት ገማቾች
በዘመን የቆሙት
ከትውልዱ ወጥተው ፥ የሚተዛዘቡት
አልያ ....ዘመን አልፈው
በነጠረ ስራ....
ከኛ ጀምበር ጥላ ፥ በሞገስ የቆሙት
መናኛም.....ሆኑ ...ዝነኛ
ትሁትም ....ሆኑ ....ጉረኛ
እርቃን አፍቃሪዎች!
ምስል ደጋሚዎች!
ምጡቅ አሳቢዎች!
ብቻ.....ሰአሊ የሆኑ
ሸራ የወጠሩ ፥ ብሩሽ የዘገኑ
ሁለት ግዜ ነው.... የሚስሉ
ሁለት ግዜ ነው ....የሚያጤኑ
#አንድ...
በረጅም ግዜ ተመስጦ ...በጥቂት ግዜ መቃኘት
የሚፈለገውን ውበት ፥ ተኩሮ በማየት
በህሊና ችንካር ሸራ
ያኔ ነው ፥ የጥበብ ሽል ፥ ፅንሱ የሚዘራ
#ሁለት...
እንግዲህ በሀሳብ ፥ ምስሉ እንደታያቸው
በውን አለም ሸራ ...ይጫራል ንድፋቸው
አይን እና እጆቻቸው ፥ እኩል እስከቻሉ
የግል አይናቸውን ፥ ለሰው ይቸራሉ
ያዩትን ...ለማውረድ
ፅንፉን ለማዋደደ
ጣጥረው..
ጫጭረው...
ሞንጭረው...
የለቀለቁትን.... አቅመ ጥበብ ቅይጥ
ጋለሪ እያገባ ...ወዳጅ እንዲያቋምጥ
ሁለቴ ተረግዞ...ሁለቴ ይማጣል
አፍቃሪው በርትቶ....
ወላድ ለመጠየቅ ...አውደርይ ይወጣል
በዚህ ኩናቴ ውስጥ...
አንዳቹም ሰአሊ
ልጁን የሰቀለ ፥ በቤት በጋለሪ
እስኪያረጅ ...እስኪሸጥ
ማንጠልጠል ይወዳል ፥ ጭንቁን እንደ ትሪ
የብሩሹ አጣጣል ፥ ቀለም ስብጥሩ
የመልእክቱ ምጥቀት ፥ ብራና ሚስጥሩ
ገለፃው......ውብቱ
ጨረሩ ....ሙቀቱ
ሺህ ግዜ ፥ እልፍ አመት
እኛን ቢገርመንም...
ቢያጅበንም ...ደርሶ
የሁለቴ ምጥ ነው
ዘመን የሚሻገር ፥ በቀለማት ርሶ
አየሽልኝ ውዴ....
እንዲህ ያለውን ሰው
ወሮታው ሲዘከር ስላንጠለጠለ
በምናቤ ጓዳ...
የማይከስም ምስልን...ራሴ ላስጠለለ
አፍቃሪነት ዳሩ...
ከጠቢብም በላይ ...ጥበብ እንዳዘለ
ምስክሬ ነፍሴ
ባገኘው ወረቀ....አንቺን እንደሳለ
ምን ይሆን መስፈርቱ
ማነው የሚረዳ...
አይኔ በከደነ ፥ ገፅታሽ ሲቀዳ
ምስልሽ ሲንቀራወዝ ...በህልሜ ሰሌዳ
በውኔም በወረቀት ፥ ሲብስ በግድግዳ
የብዙ ብዙን ምጥ....አዕላፈ ውልጃ
ከሁለት ግልግል...ካንድ ተኩል ውርጃ
ለማመዛዘኛ....ቢጠፋ ብልሀቱ
ተደብቄ ኖርኩኝ ፥ የመልክሽ ሎሬቱ ።
✍ አብርሀም_ተክሉ ( መርዕድ)
@Abrham_teklu
@getem
@getem
#ልጅነትና_እውቀት
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ከእለታት አንድ ቀን
ጦርነት ሁሉ አልቆ፥ ሰላም የሚሰፍን
ይመስለኝ ነበረ
ትልልቅ ሰው ሁሉ
ሚስጥር የሚደብቅ፥ ገመና የሚሸፍን።
.
ይመስለኝ ነበረ
ቤተስኪያን ሂያጅ ሁሉ፥ እውነት የሚናገር
ሰው የመሬት ዜጋ
መሬትም የሰው ልጅ፥ ሁሉም የራስ ሃገር፡፡
.
ይመስለኝ ነበረ
የታመመ ሁሉ ፥ ታክሞ የሚድን
የተራበ ጠግቦ
የምስጋና ንፋስ፥ ምድርን የሚከድን።
.
ይመስሉኝ ነበረ
አብረው ያየኋቸው፥ ከልብ ሚዋደዱ
‘ሚዋደዱ ሁሉ
የማይለያዩ፥ የማይከዳዱ።
ሰው በሙሉ መልካም
ያጠፋ እንኳን ቢኖር፥ ወዲያው የሚቀጣ
መጥፎው ተወግዶ
ደግ የሚነግስበት፥ ዘመን የሚመጣ።
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ማደግ ደስ የሚያሰኝ
ለሚራበሽ አለም፥ መድሃኒት የማስገኝ
በመኖሬ ምክንያት
የሌላውን ህይወት፥ ሳሻሽል የምገኝ፡፡
.
.
ይመስለኝ ነበረ....።
.
.
የዋህ ልጅነቴን
አደግሁና አየሁት፥ ትዝብቴ አሳቀቀኝ
ሃሳቤን ቢያውቁብኝ
መሳቂያ መሆኔን፥ ማን አስጠነቀቀኝ?
.
አደግሁና ጀመርኩ
በያደባባዩ፥ መካሰስ መወንጀል
ባከማቸሁት ላይ
ነጥቆ ማከማቸት፥ ያማኜን መከጀል።
በሰው ሰራሽ ድንበር
በሰው ሰራሽ ቀንበር፥ ቡድን እየሰራሁ
እንደ ሰኔ መሬት
እየተሸናሸንኩ፥ መባላት ከዘራሁ
ማነው ያስተማረኝ
ታቦት ሰርቆ መሸጥ፥ ክህነቴን ጥዬ
ማነው የነገረኝ
ሸንግሎ ማሳደር፥ የእግዜር ሰው ነኝ ብዬ?
የሚል ጥያቄ አለኝ
ለዚያ ልጅነቴ፥ ለዛሬው ማደጌ
ማን ያብራራልኛል
በሽታ መፍጠሬን፥ መድሃኒት ፈልጌ?
መሳሪያ ፈልስፌ
ጠብ-መንጃ መሸጤን፥ ለጦር ማስታጠቄን
ማን ይመልስልኝ
የማደግ ክፋቴን፥ የልጅነት ሃቄን?
.
አለም አኬልዳማ
በእድሜዬ እሾህ ማሳ፥ ደማምቼ ባለፍኩ
አደግሁና ገባኝ
ሌላው ምን አገባኝ.. ራሴን ካተረፍኩ?
#Haileleul_Aph
@getem
@getem
@getem
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ከእለታት አንድ ቀን
ጦርነት ሁሉ አልቆ፥ ሰላም የሚሰፍን
ይመስለኝ ነበረ
ትልልቅ ሰው ሁሉ
ሚስጥር የሚደብቅ፥ ገመና የሚሸፍን።
.
ይመስለኝ ነበረ
ቤተስኪያን ሂያጅ ሁሉ፥ እውነት የሚናገር
ሰው የመሬት ዜጋ
መሬትም የሰው ልጅ፥ ሁሉም የራስ ሃገር፡፡
.
ይመስለኝ ነበረ
የታመመ ሁሉ ፥ ታክሞ የሚድን
የተራበ ጠግቦ
የምስጋና ንፋስ፥ ምድርን የሚከድን።
.
ይመስሉኝ ነበረ
አብረው ያየኋቸው፥ ከልብ ሚዋደዱ
‘ሚዋደዱ ሁሉ
የማይለያዩ፥ የማይከዳዱ።
ሰው በሙሉ መልካም
ያጠፋ እንኳን ቢኖር፥ ወዲያው የሚቀጣ
መጥፎው ተወግዶ
ደግ የሚነግስበት፥ ዘመን የሚመጣ።
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ማደግ ደስ የሚያሰኝ
ለሚራበሽ አለም፥ መድሃኒት የማስገኝ
በመኖሬ ምክንያት
የሌላውን ህይወት፥ ሳሻሽል የምገኝ፡፡
.
.
ይመስለኝ ነበረ....።
.
.
የዋህ ልጅነቴን
አደግሁና አየሁት፥ ትዝብቴ አሳቀቀኝ
ሃሳቤን ቢያውቁብኝ
መሳቂያ መሆኔን፥ ማን አስጠነቀቀኝ?
.
አደግሁና ጀመርኩ
በያደባባዩ፥ መካሰስ መወንጀል
ባከማቸሁት ላይ
ነጥቆ ማከማቸት፥ ያማኜን መከጀል።
በሰው ሰራሽ ድንበር
በሰው ሰራሽ ቀንበር፥ ቡድን እየሰራሁ
እንደ ሰኔ መሬት
እየተሸናሸንኩ፥ መባላት ከዘራሁ
ማነው ያስተማረኝ
ታቦት ሰርቆ መሸጥ፥ ክህነቴን ጥዬ
ማነው የነገረኝ
ሸንግሎ ማሳደር፥ የእግዜር ሰው ነኝ ብዬ?
የሚል ጥያቄ አለኝ
ለዚያ ልጅነቴ፥ ለዛሬው ማደጌ
ማን ያብራራልኛል
በሽታ መፍጠሬን፥ መድሃኒት ፈልጌ?
መሳሪያ ፈልስፌ
ጠብ-መንጃ መሸጤን፥ ለጦር ማስታጠቄን
ማን ይመልስልኝ
የማደግ ክፋቴን፥ የልጅነት ሃቄን?
.
አለም አኬልዳማ
በእድሜዬ እሾህ ማሳ፥ ደማምቼ ባለፍኩ
አደግሁና ገባኝ
ሌላው ምን አገባኝ.. ራሴን ካተረፍኩ?
#Haileleul_Aph
@getem
@getem
@getem
ሴባስቶፖል
"""""''"""""""'
እቴ የለፉሁልሽ
እጉያዬ አድርጌሽ ፥ልሰክን ከቀልቤ፤
አንዴ ነው የተኮሰው
የፍቅሩን ወላፈን፥ ሴባስቶፖል ልቤ!
አንዴ ያፈቀረ
አንዴ እቀባብሎ፥ አንዴ ይተኩሳል፤
እድል ስትዞርበት
ሺ ባዙቃ ብዪዝ ፥ሺ ባዙቃ ይከሽፋል!
የኔ ግን ሌላ ነው
እድልና ፍቅር አብረው ቢተኮሱ፤
በአንድ የፍቅር ረመጥ፥
ድባቅሽ ተመትቶ፥
ልብሽ ተማረከ፥ ከተተሽ ከእቅፉ!
እንዲያ ነው አላማው፤
እንዲህ ነው ኢላማው!
ከእምነት የተኮሱት
በእውነት አቀባብለው፥የልብ መምቻ ሲሆን፤
ኢላማ አይስትም
ከሽፎ አይቀርም ባዶ፥ የፍቅር ሴባስቶፖል!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
"""""''"""""""'
እቴ የለፉሁልሽ
እጉያዬ አድርጌሽ ፥ልሰክን ከቀልቤ፤
አንዴ ነው የተኮሰው
የፍቅሩን ወላፈን፥ ሴባስቶፖል ልቤ!
አንዴ ያፈቀረ
አንዴ እቀባብሎ፥ አንዴ ይተኩሳል፤
እድል ስትዞርበት
ሺ ባዙቃ ብዪዝ ፥ሺ ባዙቃ ይከሽፋል!
የኔ ግን ሌላ ነው
እድልና ፍቅር አብረው ቢተኮሱ፤
በአንድ የፍቅር ረመጥ፥
ድባቅሽ ተመትቶ፥
ልብሽ ተማረከ፥ ከተተሽ ከእቅፉ!
እንዲያ ነው አላማው፤
እንዲህ ነው ኢላማው!
ከእምነት የተኮሱት
በእውነት አቀባብለው፥የልብ መምቻ ሲሆን፤
ኢላማ አይስትም
ከሽፎ አይቀርም ባዶ፥ የፍቅር ሴባስቶፖል!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
የሙፍቲያችን ዱዓ...
***
ያረቢ ያመናን - በራህመትህ እያት፥
ጀሊሉ አደራህን - አገሬን ጠብቃት!
🙏🙏🙏
ከኮሮና ደዌ፥
ከእምቦጭ ወረራ፥
ከግብጽ ድንፋታ፥
ከከፋፋይ ዛቻ፥
ወንድም ከሚያጋድል፥
የርስ በርስ ጥላቻ፤
ጀሊሉ ጠብቃት።
... 🙏🙏🙏
ከኢኮኖሚ ድቀት፥
ከሴራ ዘመቻ፥
ምርጫን ካስታከከ፥
ከስልጣን ሽኩቻ፥
ከማይደማመጥ፥
ከሚል እኔ ብቻ፤
ጀሊሉ ጠብቃት።
... 🙏🙏🙏
ከአንበጣ መንጋ፥
ከመኪና አደጋ፥
ከህጻናት ርሃብ፥
አንገት ከሚያስደፋው፥
ከስደት አለንጋ፥
...
ጌታዬ አደራህን!
ከፊቷ አለና፥
ብዙ አይነት ፈተና፥
ጀሊሉ ጠብቃት፥
ይህቺ ምስኪን አገር፥
ካላንተ ማን አላት?
....🙏🙏🙏
(አሜን በሉ፤)
#ጁምዓሙባረክ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ )
@EliasGebru
@getem
@getem
***
ያረቢ ያመናን - በራህመትህ እያት፥
ጀሊሉ አደራህን - አገሬን ጠብቃት!
🙏🙏🙏
ከኮሮና ደዌ፥
ከእምቦጭ ወረራ፥
ከግብጽ ድንፋታ፥
ከከፋፋይ ዛቻ፥
ወንድም ከሚያጋድል፥
የርስ በርስ ጥላቻ፤
ጀሊሉ ጠብቃት።
... 🙏🙏🙏
ከኢኮኖሚ ድቀት፥
ከሴራ ዘመቻ፥
ምርጫን ካስታከከ፥
ከስልጣን ሽኩቻ፥
ከማይደማመጥ፥
ከሚል እኔ ብቻ፤
ጀሊሉ ጠብቃት።
... 🙏🙏🙏
ከአንበጣ መንጋ፥
ከመኪና አደጋ፥
ከህጻናት ርሃብ፥
አንገት ከሚያስደፋው፥
ከስደት አለንጋ፥
...
ጌታዬ አደራህን!
ከፊቷ አለና፥
ብዙ አይነት ፈተና፥
ጀሊሉ ጠብቃት፥
ይህቺ ምስኪን አገር፥
ካላንተ ማን አላት?
....🙏🙏🙏
(አሜን በሉ፤)
#ጁምዓሙባረክ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ )
@EliasGebru
@getem
@getem