ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ቀርቼ ከ........

መኖርስ ኖሪያለሁ ሁሉንም አይቼ
ከፅድቁም ከርኩሱም ሄደዋል እግሮቼ
ፍቅርንም ጥላቻን ሁሉንም ጎብኝቼ
በሁለቱም ዛቢያ ሳንዟብብ ከርሜ
ከአንደኛው ስሞላ ከሌላኛው ስጎል
ከጎደለው ስዉል ከሞላዉ ሳቃልል
ከዚህም ከዛም ሳልሆን ቀረሁኝ ከመሀል

(እምነት ዋለልኝ)


@getem
@getem
@getem
👍1
🌹ካገባች በኋላ

ሌላ ወንድ አቀፋት የሚል መርዶ ሽሽት
ሌላ ሴት እያቀፍኩ በያንዳንዷ ምሽት
እሷ ናት እላለሁ
(የኔ እብደት ሲገርመኝ ይባስ የሴቶቹ)
ፍቅር የሰለቻቸው ፍቅርን የሰለቹ
እሷ ናችሁ ስላልኩ "እሷ ነን" እያሉ
እኔ እንዳነሳቸው ራሳቸውን ጣሉ


(አሌክስ አብርሀም)


@getem
@getem
@getem
❤️ለትውስታ

ተላለፉ ሲለን
**

ከመረዋው ውግረት
ከቃጭሉ ዋይታ እኩል ብንሰማም
በአንድ ደውል ድምፅ
ግለ ህሊናችን አንድ ላይ ቢደቃም
ተላለፉ ሲለን
ፊትና ኃላ እንጂ እኩል አንነቃም።

ይስማዕከ ወርቁ
ከ "የወንድ ምጥ" የግጥም መድብል


@getem
@getem
@beppa_19
ከስካሩ ጀርባ

በጌሾና በብቅል ከዛለ ሰውነት
ከደከመ ምላስ በመቆም ለእውነት
ከኮልታፋው አፍ ውስጥ ምራቅ ከመረረው
ከሰከረ ሰው ነው ንፁህ ዕውነት ያለው!

ተረት እንደሆነው ተውሶ ከአበው ቃል
ሆድ ያባውነን ሁሉ ብቅል ያወጣዋል
ከሰካራም ሃሳብ ከስካሩ ማህደር
እኔ የተረዳሁት ኅቡዕ ቁምነገር
በገፈ ይጠጣ ሁሉም በገፋ ይስከር
ለእውነት የምትቆም ሀገር ለመፍጠር!

@Eromaa
የካቲት 2012

@getem
@getem
@getem
የፍቅር ፀብ
( በላይ በቀለ ወያ )

ባብሮነታችን ውስጥ
ጥላቻ ባይኖርም - መናናቅ ነበረ
በመናናቃችን
መለያየት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ
አብሮ መብላት ቀረ
አብሮ መዋል ቀረ
አብሮ ማደር ቀረ
ቀረ
ቀረ
ቀረ
ሁሉም ነገር ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ
በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ
እንኳን ተለያየን - እንኳን አብረን በላን
እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣለን፡፡
ባብሮነታችን ልክ
መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ
አሁን የሚታየኝ
ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ፡፡
እንኳን ተለያየን!

( በላይ በቀለ ወያ )

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
@getem
👍1
ሰው የሚሉት ስንኝ ከወዴት ነው ያለ
(በመልአኩ ስብሐት ባይህ)
.
.
.
የዕለት ዝግም ጉዞ
የሌት ጭምት ፉዞ።
ግርጣታሙ ወዝዞ
ግፍልታሙ ቀዝዞ።
ባልታለበ ወተት
ባልተላመ ልመት
ባልታለቀ እልቀት።
ላሚቷ ተጥላ
እናትነት አዝላ።
ጡር አይሉት በደል
ጋራ አይሉት ደለል።
ውሉ ባልታወቀ
ስሩ ባልዘለቀ።
የዘመን እንቅፋት
የግፍፍት ክርፋት።
ያ ክርትት ገጣሚ
ያ ብኩን ገጣሚ
እድሜ የታደለው፣
እርሷን አገኝ ብሎ
እራሱን የጣለው።
በስንኙ ቁጥረት
በብዛኔው ዝረት።
ሕይወት ትልሟ አጠረ
እንደ ጉም በነነ፣
ሰው በሚሉት ፍጥረት
ኑረቷ ተነነ።
እያለ ሲከትብ
ጆሮ የተነሳው፤
ያድኩም ጦማሪ
የኔም ያንቺም ሰው ነው።
እና እኔም ፈለግሽ
ከአዝርእትሽ ዘርሽ
አድምጪኝ ልንገርሽ።
ላሚቷ ሀገር ናት
መውደቂያዋን ያጣች፣
ወተት በሚሉት ህዝብ
ተልባ የነጣች።
ላሚቷ ሀገር ናት
የጠነዛ ሙጃ ጎራሽ ያላመሏ
ሲነትብ የሚውል አንቦግቧጊ ምስሏ።
ላሚቷ ሀገር ናት
በሬ መሪ ሹማ
ጊደሯን ምታስርብ፣
በፍጥረቶቿ ግብር
እያደር ምትረግብ።
ላሚቷ ሀገር ናት
ፀዳል መና አፍርታ
ሲቃ አተላ ተጋች፣
የሳማትን ገፍታ ያለባትን አንጋች።
ላሚቷ ሀገር ናት
የሰለለች ብርቱ
በናኑርሽ ብሂል ምትውል ከበረቱ።
ላሚቷ ሀገር ናት
የሰንበት ቡራኬ
የልግስነት ትርጉም፣
የጥጣኖች ቀሰም
የፈሳሾች ዓለም።
ላሚቱ መስጠት ናት
የቅንነት ጥጋት።
ውለታን እማጥፍ
የመጣፈጥ ሰፈፍ።
እናም ብሎም ሲሆን
ጠቢቡን ስንመዝን፣
ሰውነትም እውነት
እውነትነት እምነት።
መሆኑን ስንቀምር።
ለፋፊው ክቡር ነው
በእኔ ብቻ አንባቢ እኛነት የጫረው።
ያ ክርትት ገጣሚ
ያ ብኩን ገጣሚ
የኔም የአንተም ሰው ነው።
..........................................
ሀገርም ሰውነት
የጉድለታት ሙሌት፣
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰውም ሀገርነት።

@getem
@getem
@getem
👍1
Audio
#ቀን_መሸኛ_ቅኔ
(ከመስፍን ወንደሰን)
@getem
@getem
@getem
@getem
ቀን ያበደ ለታ
ተፈጥሮ በድንገት ዛብ በለቀቀበት
በዞረባት ግዜ በዞረባት መሬት
ዶሮ ሲአንቀላፉ በጓጉንቸር ጩኸት
በዘጠኝ ይነጋል ቀኑ ያበደለት
ጊዜ ቀስቱ ሲዝል ሲረግብ ደጋኑ
ቋጠሮው ሲላላ የፈጥሮ ውሉ
ሳያልቅ ለሊቱ እነደ ጭንጋፍ ሁሉ
በዘጠኝ ይነጋል እብድ ቀን ላመሉ
ጠብ በመተቃቀፍ
ቁጣ በፈገግታ
ፍቅር በንክሻ
ሰላምታ በቴስታ
ሀዘን በዳንኪራ
ጋብቻ በዋይታ
የሚሆነው ቀርቶ
የማይሆን ይሆናል ቀን ያበደታ ለታ ።
(በጌትነት እንየው እውቀትን ፍለጋ መድብል)

@getem
@getem
@getem
ኩርኩም
እልፍ ኩርኩሞችን
የቀመሱ ራሶች
ዳሳሽ እጆች እንጂ
አይሹም ትራሶች ።


(የወንድ ምጥ በይስማእከ ወርቁ)

@getem
@getem
@getem
👍1
ሀገርህ ናት በቃ
[ነብዩ መኮንን]
.
ይቺን ናት ኢትዬጰያ
ሀገርህ ናት በቃ!!
በዚች ንፍቀ-ክበብ
አይምሽ እንጂ መሽቶ፥ ማታው ከጠረቃ
የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ

ይቺው ናት ዓለምህ፥ ብቻዋን የተኛች -ከዓለም ተደብቃ
አኪሯ ቀዝቅዞ "ያንቀላፋች ውቢት" ያንተው የክት ዕቃ

ምን ትሆን እንግዲህ- ሀገርህ ናት እሷ-ልቧን አታውልቃት - አትጨቅጭቃት በቃ
አብረህ አንቀላፋ- ወይ አብረሀት ንቃ!!
.
@getem
@getem
@getem
@getem
አትምጣ ብለሺኝ
(ዶ.ር በድሉ ዋቅጅራ)

ከነብስሽ ተሙዋግተሽ፣
ከራስሽ ተጣልተሽ፣
ህመም ነህ ብለሺኝ፤
ካለም ተቆራርጠሽ፣
ሱባኤ ተቀምጠሽ፣
ሀጥያት አድርገሽኝ፣
ደጅሽን ቆልፈሽ፣
መብራትሽን አጥፍተሽ፣
አትምጣ ብለሽኝ፣ ትጠብቂኛለሽ።
.
@getem
@getem
@getem
1
ይቀረኛል
(ይስማዕከ ወርቁ)
.
ጎጆዬን ልሠራ ሐረግ ስመዝ ኖሬ
ማገር ስቆርጥላት የትም ዞሬ ዞሬ
ራሴን ልችል ነው እያልኩ ከችግር
ቆላ ደጋ ስግር
ለካስ ይቀረኛል አብሮ የሚያማግር
ውሃ የሚያቃጥን ተስፋ የሚያጋግር።
.
@getem
@getem
@getem
ጠላቴን ስመርቅ

በስልጣን ከፍ ከፍ
በዝና ከፍ ከፍ
በሀብትም ከፍ ከፍ
ወደላይ ከፍ ከፍ
ከፍ ከፍ.... ከፍ ከፍ
ከዛ የወደቅህ ዕለት አጥንትህ እንዳይተርፍ::

ገጣሚ ታገል ሰይፉ
@getem
@getem
@getem
@getem
የሟች ሀገር እውነት
.
ልጄ!
‹‹ሀገር ማለት ሰው ነው!›› ፣ያሉህን ተቀበል
ሰው በሞተ ቁጥር ፣ ‹‹ሀገሬ ሞተች›› በል።

(በላይ በቀለ ወያ)

@getem
@getem
@getem
እየደሙ መዋብ!?!
(መላኩ አላምረው)
...
እንዲህ ናት ሀገሬ ...
ገነት ሆና ሳለ፡ የሲኦል አበጋዝ: ሚፈራረቅባት፤
የበቀል ደም እና፡ የተስፋ አበባ፡ አብሮ ‹ሚፈካባት› !
.
በአንድ በኩል የልጇ፡ ደም እየፈሰሰ፡ በዓይኗ ስታነባ፤
ደስታዋን ሊመልስ፡ ምድሯ ያበቅላል፡ የተስፋ አበባ!
...
ደም እየፈሰሰ፡ ሀገር ተተብትባ፡ በሰማንያ ጣጣ፤
ይኸውና ደግሞ፡ አደይ አፈንድቶ፡ አዲስ ዓመት መጣ!
...
.
መቼም አስገራሚ፡ የማትመረመር፡ ቅኔ ናት ምድሪቷ፤
አካሏ እየደማ፡ ለአልቃሽ ዓይኗ ደስታ፡ አበባ ነው ቤቷ!
.
@getem
@getem
@getem
👍1
ያገረሸ ፍቅር
.
የሰማይ
አሞራ
ላዋይህ
ችግሬን፡፡
ብረር ሒድ ንገራት”.
ከትልቁ
ዛፍ
ሥር፣
ዱሮ በልጅነት
ከተጫወትንበት
ከትልቁ ዛፍ ሥር አታጣትም ፍቅሬን።
ብረር
ሒድ ንገራት፣
ንገር መናፈቄን።
.
(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)
.
@getem
@getem
@getem
@getem
ውሸት ነው💞💞
(ኤፍሬም ስዩም)
.
ፍቅሬ አንዳንድ ግዜ አመሌን የማጣው
በንፁህ ጨዋታሽ የምነጫነጨው
በጥርስሽ ብርሀን ፊቴን የማጠቁረው
ምነው ሆዴ ስትይ ብወድሽ የምለው
እውነት እንዳይመስልሽ አይደለም ውሸት ነው።
.
ደግሞም አንዳንድ ቀን
እኔ አንቺ አብረን ሆነን
የምለይሽ በሰመመን።
ከሰመመን መልሰሽኝ
ምንው ሆዴ ስትይኝ
ሀሳብ የከተተኝ
ፍቅርሽ ነው ያልኩትኝ
እውነት ይሁን ውሸት እኔንም አልገባኝ።
.
ሌላም በሌላ ቀን አዱኛ ስተርፈን
አድባር ሲቀርበን ፍቅር በልተን
ፍቅር ሰርተን እንዳበቃን
ታፈቅረኛለህ ስትይኝ ከእኔ በላይ ያልኩትኝ
በእውኔ አይሆንም በህልሜ መሰለኝ።
.
ደግሞም ሌላ ጊዜ
ከሀገር ምድር ተገልለን
እኔ ባንቺ አንቺ በእኔ ተጠልለን
ምሽት ደርሶ ሲለያየን
ጀንበር ዘቀዘቀችች መለየት ሊሆን ነው
ነግቶ እስከማይሽ ናፍቆት ብዙ ነው
ብዬ ያወራሁሽ እኔ ልሙት ብዬሽ
እውነት እውነት ስልሽ
እውነት እንዳይመስልሽ
ውሸት ነው ልንገርሽ
በፈጠረሽ አምላክ ይሄን ሁሉ እውነት
አሁን የነገርኩሽ እራሱ ውሸቱን እውነት
እንዳይመስልሽ።
.
እውነት ግን አለሜ
ውሸት ይመስልሻል አንቺን ባላፈቅር
ይሄ ሁሉ ይወራል ውሸቴን ነው ተብሎስ
ከወደዱት ሌላ ለጠላት ይፃፋል
እውነቱን ልንገርሽ ሊፃፍም ይችላል
እውነት ነው ብሎ ማታለል ይቀላል።
.
እኔ ግን ልንገርሽ
እውነት ነው ስልሽ
እውነት እንዳይመስልሽ
ውሸት እንዳይመስልሽ........
.
@getem
@getem
@getem
መሰላል
.
መሰላል ለመውጣት
አለው ትልቅ ብልሀት።
የላዩን ጨብጦ፤
የታቹን ረግጦ፣
ወደላይ መመልከት
እጆችን ዘርግቶ በሀይል መንጠራራት።
ጨብጦ መጎተት የላዩን፣
ላይ ታች እንዲሆን።
አንድ በአንድ እየረገጡ
መሰላል የወጡ፣
ብልሆች የማይጣደፉ
ሞልተዋል በያፋፉ።
ዘርግተው የጨበጡትን መርገጥ
የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ፡፡
ሲወርዱ ግን ያስፈራል
የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡
😊😊😊
.
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፣ እንጉርጉሮ፣ 1967)

@getem
@getem
@getem
›‹ላያስማማ›‹

ይማግ ይማግና:
ሊዋጥ ተዘጋጅቶ:ሲሄድ እንደቆየ፤
ይጋት ይጋትና:
ሊተፋ ተሟግቶ:ሲመጣ ዘገየ፡፡

……ርብቃ ሲሳይ…
ሚያዚያ,2008


@getem
@getem
@getem