ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጋሞ!!!!!


ከቃጫው ገመድ ላይ ፤ ውብ ፍቅሩን ጠምጥሞ፤
በሰፊ ትከሻው፤
ጦቢያ የምትባል ያባቶቹን ኪዳን ሃገር ተሸክሞ፤
ሩቅ ነው ምናቡ፤
ሩቅ ነው መንገዱ፣ ዳርቻ የለውም እንደ አባያ ጫሞ፤
ወዘናው ሙሉ ነው፤
አፉ ይጣፍጣል፤
ብእሩ ይሰላል እንደ ጨንቻው ሰንደቅ እንደ አሰፋ ጫቦ፤
ጨንቻ ሚካኤል ላይ፤
ሳየው ደስ ይለኛል በአረንጓዴ አፈር ላይ በአዝመራ ታጅቦ፤
ልክ እንደተራራው፤
እንደ ጨንቻ ዳገት ወደ ላይ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ተሹሞ፤
ቃሉን የማይሽረው፤
የባንዲራው ጌታ ፤
የጦቢያ ባለሟል እንደምነው ዶርዜ እንደምነው ጋሞ???

(( ጃ ኖ ))💚💛

@getem
@getem
ከእኔነት ያመጸ ፤ ክብርን የሚያስረሳ ፤ ፍቅር ባንች ሞልቶ፤
በጀምበር መግቢያ ላይ፤
በጥርጊያው መንገድ ላይ፤
መንገዱ ሲከዳኝ የጉልበቴ ስፍር መቀነቱ ላልቶ፤
እምወድሽዋ፤
የመንገዴን ጥመት ፤ ጎንበስ ብሎ ማቅናት አትሰለችም ከቶ።

((( ጃ ኖ ))💚💛

@getem
@getem
@Nagayta
""""የሴት ህልም""""
.......መኮንን አልማው ገበይ.....
..............
በሃካል እርቀሽኝ
በሰው አሳማሽኝ!
ኑሮዬን ለብቻ ስገፋው እያዩ
"ብቸኛው" ይሉኛል ከሰው እየለዩ!
እውነት ከተባለ
ብቻነት የት አለ?
'ያሣብ ሰረገላ ከስንቱ እያዋለ!
በርግጥ
በፍቅር ለመዋደቅ
ግድ ቢልም መተዋወቅ
ግን የትኛውም ወንድ
ሳታውቀው ሳያውቃት
በልቡ የሚሥላት
በአዕምሮው የሚያሥባት
ከነፍሱ የማትሾልክ
አለች የሴት መላክ!
"
አሁን እኔ እንኳን
ከዓለም ህዝብ መሃል ፣ ሰው 'ብቸኛው'ሚለኝ
ኮሮና እንዳለበት ፣ ደፍሮ ሠው ባይቀርበኝ
ብመሥልም ብቸኛ...
ገልጠው ባያዩኝ እንጂ ፣ እንደ እትም ደብዳቤ
ቢፈትሹኝ ኖሮ ፣ እንደተጎዘጎዝሽ አንቺ አለሽ በልቤ!


የካቲት 06/2012 ዓ.ም
(በፍቅረኛሞች ቀን ብቻቸውን ሢያሣልፉ አይተን ፍቅረኛ አልባ መሥለው እንዳይታዩን)

@getem
@getem
@getem
ፍተቅስርፋ(ልዑል ኃይሌ)
ችንካርሽን አየሁት
በፍቅር መስቀል ላይ የተሠቀልሽበት፤
ሠንበርሽን አየሁት
በአይሁድ አፍቃሪ የተገረፍሽበት፤
ደምሽን አየሁት
ቁስልሽን አየሁት አየሁት ያንቺ ዕንባ፤
ጀምበር አዘቅዝቃ
ሕመምሽ ሊቀበር ቁስልሽ አፈር ገባ፤
በ3ኛው መዓልት
ከመከዳት ፍቅር ከሞት ስትነሺ፤
ትንሳኤሽ ናፋቂ
እየጠበቅኩሽ ነው እስክትመለሺ፤
.
ያለፍሽበት መንገድ
ትዝታው ምን ቢያምም ባይሽርም ጠባሳው፤
አሻግረሽ ተመልከች
ተስፋ ነው ትልቅ ስንቅ ትላንት የሚያስረሳው፤
.
ተራመጅ ወደ'ኔ
እየጠበቅኩሽ ነው በናፍቆት ውብ ተስፋ፤
ወደ ኋላ እትሂጂ
የትላንቱ ዕንባሽ ይዞኝ እንዳይጠፋ፤
ደግሞ እንዳይመልሰኝ
ከተሠቀልኩበት የትላንት ችንካሬ የትላንት ግርፋት፤
ወደ ነገ ምሪኝ
በጥዑም ፍቅራችን ዛሬን እንለፋት፤
.
ተመልከች ዙሪያሽን!
ከከተማው ሁሉ
ከወጪ ወራጁ ካላፊ ካ'ግዳሚው፤
ይበዛል ይበልጣል ቁስል ተሸካሚው፤
ግን ዕድሜ ለጥርሱ
ሸፍኖ ያልፈዋል ሐቅ እንዳላወቀ፤
እንዲህ ነው በኛ ዓለም
ጀምበር እየወጣ ጀምበር የጠለቀ፤
.
ተመልከች ዙሪያሽን!
ከጀምበር ተማሪ
እንደሚፈራረቅ መጥለቅና መንጋት፤
ትላንትሽን ጣዪ ዛሬን ውብ አድርጊያት፤
.
እንፍጠር ውብ ዓለም
እንፍጠር ውብ መንደር፤
ተዋድደን እንዋል
ተዋድደን እንደር፤
.
ይግረመው ዓለሙ
በችንከር በክህደት ሲሰቅለን የኖረ፤
ፍቅር ላሠብንለት
ለምላሽ ስንቅ ብሎ ክህደት ለሠፈረ፤
.
ዙሪያሽን ተመልከች!
ሻማው ይታይሻል?
ይታይሻል ክብሪት? 'ሳት እየለኮሰ፤
ፅልመት ለመግፈፍ ነው
ራሱን አቃጥሎ ከክር የደረሠ፤
ፍቅር እንደዚህ ነው
ፅልመትን ለመግፈፍ
ለሠው ብርሃን ሲሉ ራስን ማቃጠል፤
አንጀትን በጥሰው
ለጨለመበት ሠው ብርሃንን መቀጠል፤
.
እኔም ክብሪት ሆኜ ስደርስ ከልብሽ በር፤
ከክርሽ ላይ ሳልደርስ ስለምን ልሰበር፤
አታጥፊኝ በንፋስ አታጥፊኝ በእሣት፤
ከመጥፋቴ በፊት
ቢያንስ
ያንቺን ብርሃንነት ከፅልመቱ ላንሳት
የካቲት 5, 2012 ዓ.ም.
ትቀመጥ!...
@getem
@getem
@getem
1👍1
(እ............ህ............ህ)
....
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*************
ሰማሽው ይህን ድምጽ?
ሙታንን ሚጠራ
መርገምትን ሚቀራ።
ሰይጥኖ ከሸይጣን ጽድቅትን የጠላ
ከሲኦል እልፍኝ ላይ ግብር እሚያበላ።

ጥርምስ ክርስስ ጭርስስ
ድፍርስ ትርምስ ግርስስ።
ፍጥረቱ የሆነ
ቅላጼው በአንቺታሽ ላይወድቅ የገነነ።

እርኩሳን ያላቁት
አውሬያት ያነቁት።
በርባኖስ ባልባሱ በጽልመት ያስጌጠው
ጭቃ ያጨቀቀው ጭምሉቁ የዋጠው።
ግርጥት አትሮንስ ላይ
ለመልካ ሣጥናኤል ልሳኔ እሚቀኝ
በእብደትሽ ምታብጂው ድመጸቴ ደነቀኝ።

ድምጸቴ ደነቀኝ

ልዝብ ቅርፍፍ ዝልጉስ
ቅፍድድ ብግር ኩስስ
መጫሚያው የሆነ
ኧረ እንዴት ሁኖ ነው
ኧረ እንዴት ኩኖ ነው
ካንቺነትሽ ሲደርስ
አምሮ የተካነ።

ንገሪኝ እመዋ

ስርጌዋ ስሬዋ
ስሜዋ ውቅሬዋ
ክርሜዋ ግርሜዋ።

በፍቅርሽ አጽዋማት
በይሁን ቁርጥማት
በከንፈርሽ ጥማት

ዝንተ ዓለም ስትለብሺኝ
ምነው ያልጸየፍሽኝ
ምነው ያልገደፍሽኝ

ንገሪኝ ግርሜዋ

ንግርት ልፋፌሽ ምንድ ነው
ሰበብ ምክንያት የትሽ ነው።

አንዳንድ ቀንማ
አንዳንድ ቀንማ
ያሰኛል ውሽማ
ብዬ ባልኩሽ ለታ
አ...ቤ....ት..... ድምጽህ ያልሽኝ እውነት ነው በባታ ።

ንገሪኝ ስሬዋ

አምሳል ምስራቼ
መለኮት ምራቼ
የጎደልኩብሽ ለት
ሙሉ ነህ እያልሽኝ ነፍሴን ምታርሻት
እጅ እጅ ምትል ቀልዴን ሳቅ እምትለውሻት
ካለማመን ማመን ማመንን የቸርሻት ።

ነፍሴን የት አረገሻት
ስሜን መች ገባሻት

ብዬ ሳሰላስል
በሕማምሽ ሳስል
ቀኖና ያጀበው አርሟዊ ቀልብሽ
ድገንቱን ተሰቦኝ በመለኮት ኃይልሽ
ሁሉን ነገር ትቼ ሁሉን ነገር ሆንኩሽ

ለምን እዳትይኝ
ስታብጂኝ አበድኩሽ ።
እ............ህ............ህ
.
.
.
ተጻፈ:-06/06/2012 ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
1
..........በትዝታዬ ስም ......
ይህን ህዝብ አውቀዋለው
ያከበረኝ የተቀበለኝ የመገበኝ እና የተንከባከበኝ ነው
ይኛውን አላውቀውም
የናቀኝ ያሳደደኝ ያስራበኝ እና ያንገላታኝ ነው
በማውቃት የልደት እና የትንሳዬ ትዝታዬ እምላለው
ያኛው
ከደጉ አለማደጉን
ከቀናው አለመዋሉን
በማውቃት ሸግዬ ትዝታዬ ስም እምላለው
ደግሞም ሳስታውሰው
የልደት ቀን ድግስ እንግድነቴን
ያከበረልኝ ይህ ህዝብ
የአምላክ ፍቅር ለብሶ
ቋንቋዬን ሊናገር ፍርሀቱን ጥሶ
በቀረበኝ ቁጥር ቀርቤው ወድጄዋለው
ደግሞ በትንሳዬው
ኮሾኮሾታ የገደለብኝን የመዋደድ ጥበብ
በዛ በሀሴት ለት
እንደ እህት አይቶ
ሲያከብረኝ እንደ እናት ለይቶ
ሊቀርበኝ ያቀረበኝን ይህን ህዝብ አውቀዋለው

ልቡ ገራገር ነው
የትኩስ ጥጥ ውበት በላዩ የደፋ
ቃላቱ ቁጥብ ነው
ያልፈራ ያልደፈረ ለማንም ያልከፋ
ሀሳቡ ግልፅ ነው
ሊገፋኝ የጠበበ ሊወደኝ የሰፋ
ይህን ህዝብ አውቀዋለው
እርሱ ጠምጦት እኔን አጠጥቷል
ማዕዱን አብልቶ የሚበላው አቷል
ይህ ህዝብ
የፍቅር ልደት ነው
የሩህሩህ ትንሳኤ
ባለቸኝ ሸግዬ ትዝታ እምላለው
ይህ ይህዝብ
እረፍትን የሚወድ
ከእውነት የሚወለድ
ይህ ህዝብ
ከሰላም ነው።

,,,,,ርብቃ ሲሳይ...


@getem
@getem
@getem
👍1
Audio
# _ያማል
(ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ)

@getem
@getem
@getem
👍1
ቀርቼ ከ........

መኖርስ ኖሪያለሁ ሁሉንም አይቼ
ከፅድቁም ከርኩሱም ሄደዋል እግሮቼ
ፍቅርንም ጥላቻን ሁሉንም ጎብኝቼ
በሁለቱም ዛቢያ ሳንዟብብ ከርሜ
ከአንደኛው ስሞላ ከሌላኛው ስጎል
ከጎደለው ስዉል ከሞላዉ ሳቃልል
ከዚህም ከዛም ሳልሆን ቀረሁኝ ከመሀል

(እምነት ዋለልኝ)


@getem
@getem
@getem
👍1
🌹ካገባች በኋላ

ሌላ ወንድ አቀፋት የሚል መርዶ ሽሽት
ሌላ ሴት እያቀፍኩ በያንዳንዷ ምሽት
እሷ ናት እላለሁ
(የኔ እብደት ሲገርመኝ ይባስ የሴቶቹ)
ፍቅር የሰለቻቸው ፍቅርን የሰለቹ
እሷ ናችሁ ስላልኩ "እሷ ነን" እያሉ
እኔ እንዳነሳቸው ራሳቸውን ጣሉ


(አሌክስ አብርሀም)


@getem
@getem
@getem
❤️ለትውስታ

ተላለፉ ሲለን
**

ከመረዋው ውግረት
ከቃጭሉ ዋይታ እኩል ብንሰማም
በአንድ ደውል ድምፅ
ግለ ህሊናችን አንድ ላይ ቢደቃም
ተላለፉ ሲለን
ፊትና ኃላ እንጂ እኩል አንነቃም።

ይስማዕከ ወርቁ
ከ "የወንድ ምጥ" የግጥም መድብል


@getem
@getem
@beppa_19
ከስካሩ ጀርባ

በጌሾና በብቅል ከዛለ ሰውነት
ከደከመ ምላስ በመቆም ለእውነት
ከኮልታፋው አፍ ውስጥ ምራቅ ከመረረው
ከሰከረ ሰው ነው ንፁህ ዕውነት ያለው!

ተረት እንደሆነው ተውሶ ከአበው ቃል
ሆድ ያባውነን ሁሉ ብቅል ያወጣዋል
ከሰካራም ሃሳብ ከስካሩ ማህደር
እኔ የተረዳሁት ኅቡዕ ቁምነገር
በገፈ ይጠጣ ሁሉም በገፋ ይስከር
ለእውነት የምትቆም ሀገር ለመፍጠር!

@Eromaa
የካቲት 2012

@getem
@getem
@getem
የፍቅር ፀብ
( በላይ በቀለ ወያ )

ባብሮነታችን ውስጥ
ጥላቻ ባይኖርም - መናናቅ ነበረ
በመናናቃችን
መለያየት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ
አብሮ መብላት ቀረ
አብሮ መዋል ቀረ
አብሮ ማደር ቀረ
ቀረ
ቀረ
ቀረ
ሁሉም ነገር ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ
በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ
እንኳን ተለያየን - እንኳን አብረን በላን
እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣለን፡፡
ባብሮነታችን ልክ
መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ
አሁን የሚታየኝ
ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ፡፡
እንኳን ተለያየን!

( በላይ በቀለ ወያ )

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
@getem
👍1
ሰው የሚሉት ስንኝ ከወዴት ነው ያለ
(በመልአኩ ስብሐት ባይህ)
.
.
.
የዕለት ዝግም ጉዞ
የሌት ጭምት ፉዞ።
ግርጣታሙ ወዝዞ
ግፍልታሙ ቀዝዞ።
ባልታለበ ወተት
ባልተላመ ልመት
ባልታለቀ እልቀት።
ላሚቷ ተጥላ
እናትነት አዝላ።
ጡር አይሉት በደል
ጋራ አይሉት ደለል።
ውሉ ባልታወቀ
ስሩ ባልዘለቀ።
የዘመን እንቅፋት
የግፍፍት ክርፋት።
ያ ክርትት ገጣሚ
ያ ብኩን ገጣሚ
እድሜ የታደለው፣
እርሷን አገኝ ብሎ
እራሱን የጣለው።
በስንኙ ቁጥረት
በብዛኔው ዝረት።
ሕይወት ትልሟ አጠረ
እንደ ጉም በነነ፣
ሰው በሚሉት ፍጥረት
ኑረቷ ተነነ።
እያለ ሲከትብ
ጆሮ የተነሳው፤
ያድኩም ጦማሪ
የኔም ያንቺም ሰው ነው።
እና እኔም ፈለግሽ
ከአዝርእትሽ ዘርሽ
አድምጪኝ ልንገርሽ።
ላሚቷ ሀገር ናት
መውደቂያዋን ያጣች፣
ወተት በሚሉት ህዝብ
ተልባ የነጣች።
ላሚቷ ሀገር ናት
የጠነዛ ሙጃ ጎራሽ ያላመሏ
ሲነትብ የሚውል አንቦግቧጊ ምስሏ።
ላሚቷ ሀገር ናት
በሬ መሪ ሹማ
ጊደሯን ምታስርብ፣
በፍጥረቶቿ ግብር
እያደር ምትረግብ።
ላሚቷ ሀገር ናት
ፀዳል መና አፍርታ
ሲቃ አተላ ተጋች፣
የሳማትን ገፍታ ያለባትን አንጋች።
ላሚቷ ሀገር ናት
የሰለለች ብርቱ
በናኑርሽ ብሂል ምትውል ከበረቱ።
ላሚቷ ሀገር ናት
የሰንበት ቡራኬ
የልግስነት ትርጉም፣
የጥጣኖች ቀሰም
የፈሳሾች ዓለም።
ላሚቱ መስጠት ናት
የቅንነት ጥጋት።
ውለታን እማጥፍ
የመጣፈጥ ሰፈፍ።
እናም ብሎም ሲሆን
ጠቢቡን ስንመዝን፣
ሰውነትም እውነት
እውነትነት እምነት።
መሆኑን ስንቀምር።
ለፋፊው ክቡር ነው
በእኔ ብቻ አንባቢ እኛነት የጫረው።
ያ ክርትት ገጣሚ
ያ ብኩን ገጣሚ
የኔም የአንተም ሰው ነው።
..........................................
ሀገርም ሰውነት
የጉድለታት ሙሌት፣
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰውም ሀገርነት።

@getem
@getem
@getem
👍1
Audio
#ቀን_መሸኛ_ቅኔ
(ከመስፍን ወንደሰን)
@getem
@getem
@getem
@getem
ቀን ያበደ ለታ
ተፈጥሮ በድንገት ዛብ በለቀቀበት
በዞረባት ግዜ በዞረባት መሬት
ዶሮ ሲአንቀላፉ በጓጉንቸር ጩኸት
በዘጠኝ ይነጋል ቀኑ ያበደለት
ጊዜ ቀስቱ ሲዝል ሲረግብ ደጋኑ
ቋጠሮው ሲላላ የፈጥሮ ውሉ
ሳያልቅ ለሊቱ እነደ ጭንጋፍ ሁሉ
በዘጠኝ ይነጋል እብድ ቀን ላመሉ
ጠብ በመተቃቀፍ
ቁጣ በፈገግታ
ፍቅር በንክሻ
ሰላምታ በቴስታ
ሀዘን በዳንኪራ
ጋብቻ በዋይታ
የሚሆነው ቀርቶ
የማይሆን ይሆናል ቀን ያበደታ ለታ ።
(በጌትነት እንየው እውቀትን ፍለጋ መድብል)

@getem
@getem
@getem
ኩርኩም
እልፍ ኩርኩሞችን
የቀመሱ ራሶች
ዳሳሽ እጆች እንጂ
አይሹም ትራሶች ።


(የወንድ ምጥ በይስማእከ ወርቁ)

@getem
@getem
@getem
👍1
ሀገርህ ናት በቃ
[ነብዩ መኮንን]
.
ይቺን ናት ኢትዬጰያ
ሀገርህ ናት በቃ!!
በዚች ንፍቀ-ክበብ
አይምሽ እንጂ መሽቶ፥ ማታው ከጠረቃ
የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ

ይቺው ናት ዓለምህ፥ ብቻዋን የተኛች -ከዓለም ተደብቃ
አኪሯ ቀዝቅዞ "ያንቀላፋች ውቢት" ያንተው የክት ዕቃ

ምን ትሆን እንግዲህ- ሀገርህ ናት እሷ-ልቧን አታውልቃት - አትጨቅጭቃት በቃ
አብረህ አንቀላፋ- ወይ አብረሀት ንቃ!!
.
@getem
@getem
@getem
@getem