ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እውነትና ንጋት እያደር ይነጋል
የአበው አባባል ብርሀን ያበራል
እውነት እውነት ሆኖ ከተረጋገጠ
ፀሀይም መውጣቷ መንጋቱም አልቀረ
ውሸት ሀሰት ሆኖ ከጨለመ ቀኑ
ብርሀን አይታይ ዝንታለሙን ሁሉ።

ሶቅራጠስ

@getem
@getem
@getem
(በታመነ መንግስቴ)

አዛን አለ ሀረር
ጎንደር ይቀደሳል?
ኢሉ አባቦራ ላይ"ኢትዮጵያ" የሚለው ስምሽ ይወደሳል?
በአርያም አንች አለሽ
በጀነት ፣በገነት?
በየደማችን ነው ዛርና መንፈሱ
የኢትዮጵያዊነት?
አክሱም ፅዮን ጫፍላይ
ሠንደቅሽ ተተክሎ?
ወሎየ ሲመርቅ
ዘይር ጀባ ብሎ?

አክሊልሽ ጋምቤላ
በወርቅ ሲሰራ?
ሽናሻ ይፈታል ሰይጣን ያሰረውን
ጠልፎ 'ሚጥል ሴራ?
ክበሪልኝማ ራስ ደጀንሽ ላይ
ከፍፍፍፍ ወደ ማማ?
ልክሽ ዛግዌ ናት አክሱም ላሊበላ
ልዩ ነሽ እማማ?

እመኝኝ እናቴ ሰው ይሞታል እንጅ
የአንች አይቀርም ቃልሽ?
ያለውን አይረሳም በጨነቀሽ ጊዜ
ዘርጊልኝ የሚልሽ?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


@getem
@getem
@getem
የእስክሽር ሱሰኛ

እስክትሽሪ ዘፍነሽ እስክሽር ላስቆምሽኝ
የድምፅሽን ውበት ሌት ተቀን አትንሺኝ

አንቺው ባለቅኔ አንቺው ሰው አሻሪ
እንባ ነው ጉልበትሽ ወደሽ ስታፈቅሪ
እኔም ያንቺ አድማጭ የእስክሽር ሱሰኛ
ድምፅሽን ካልሰማው እንቅልፍ ባይኔ አይዞር ለሊቱን አልተኛ

እናምልሽ አንቺ ቃልሽን አክባሪ
ባይገጥምሽ ጓደኛ ለቀለበት ኗሪ
ድምፅሽን ለአንድ አፍታ ሰምቶሽ የወደደ
አንድ ልብ አለልሽ ከውሸት አለም ርቆ ወቶ የተሰደደ
በሙዚቃም ሀይል
መከዳትን ዘፍነሽ ነፍስ የዘራሽበት
እስክሽር ላፈቅርሽ በልብሽ ላይ ልዝመት

ባትረሺው ትዝታን በልብሽ ተስሎ
ቢተውሽ ነካክቶ ፍቅርን ተመስሎ
በድምፅሽ ለሻረው የእስክሽር ሱሰኛ
በይ ቶሎ ዳኝለት ሰላም ውሎ ይተኛ
ቃልሽ ላይነካ ፍፁም የነበረ
እስክትሽሪ ረስቶሽ ወድያው የተሰበረ
ለእግዜሩ ሰላምታ ምን ቢኮራ ላንቺ
ብዙ አይኖች አሉ የሚያዩ ወዳንቺ

ልካስሽ ለማለት ያልኩት ፈራ ተባ
ጉዳትሽን ሳስብ ነው መሆኑን ጉልበትሽ የስብራት እንባ

ማልቀስ እና ውበት ፣ ቃላትን ቢነሱኝ ፣ ከድምፅሽ ባንድምታ
የእስክሽር ሱሰኛ አስባለኝ ዝምታ።

ተፃፈ በአኒታ
@getem
@getem
@getem
@getem
(እንደ ፈንድሻ ተበተኑ )
ጊዜ ላይ ሳይቆሙ
ለስራ እያቅማሙ
ከራሳቸው አልፈዉ ፣
ሀገርን አስጠቆሩ ፣
በእኩይ ምግባራቸው ፣
ህፀፅ ተነከሩ ፣
ህይወት ምን ትሁን ምን ፣
ሚስጥር ገመናዋን ፣
ሳያጠኑ ፣
ፍሬያቸውን አጥተው፣
ለፈንድሻ አምሳል ደርሰው
ተበተኑ።

✍️ ቤዚቾ

@getem
@getem
@getem
እንደ ቀልድ ፈገግ (በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ፣ ሳቄ ይቀድመኛል።
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ፣ ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው!
እየሳቁ ውሎ ፣ እየሳቁ ማደር።
ውሸት ነው አትመኝ....
እዚህ ሀዘን የለም ፤ ሳቅ ነው የተረፈን
ህመም ለቆ ይሔዳል
"አመመኝ አመመኝ" ፣ በሚል አንድ ዘፈን።
.......
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? ፣ እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ፣ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ።
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ፣ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ፣ ምኔ እንደታመመ?
አያስቅም ታዲያ?!


@getem
@getem
1👍1
#ዛሬ አለም አቀፍ የራድዮ ቀን ነው ! የሸገሯን መዓዛ አለማመስገን ንፍጉነት ነው! መልካም የስራ ዘመን! ለሸገር ራድዮና ለጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ !


ማሪንጌ ቻ! !!!!!

ኧረ ሸገር ሸገር ፤ ሸገር ባውቶብሱ ፣
የመርካቶ ልጆች ፤
ሸ ከርተፍ እያሉ ፣ ከምኔው ደረሱ ።
ታምር አይደለም ወይ ፤ እንደ ሰማይ መና ፤
ሽበት ክብር ሲሆን ፤ እድሜና ቁመና ።
አስናቀ አስናቀ፤ አስናቀ ቢሉሽ ፤
ኬሬዳሽ በያቸው ፤አይስማ ጆሮሽ ፤
ቼ በይው ፤
ፈረሱን አቤ ነው ብለሽ ።
በደርባባው ዛትሽ ፤ በሁለመናሽ ፤
እንደ እቴጌ ማርዳ ፤ ያምራል ከራማሽ ፤
እድሜ ይቀጥላል ፤ ውብ አንደበትሽ ፤
መአዛ ማር ዘነብ ፤ መኣዛ ጥንቅሽ ።
ማሪንጌ ቻ ፤
ማሪንጌ ቻ ዘመናችን ይመር እንደ ማ'ዛ ብሩ ፤ እንደ አበበ በልቻ ።
ማሪንጌ ቻ! !!!

((( ጃ ኖ )))

መታፈር በከንፈር! !!!!! ያውም ደግሞ ልክ እንደ መኣዛ
ብሩ! !!!!


እናንት የጦቢያ እህቶቼ ሆይ! !!!!ከሴትነት ላይ የሰከነ
እውቀት ሲጨመርበት በዚያ ላይ ያደጉበትን ማህበረሰብ
ለዛና ወዘና ሳይለቁ የሚከወን ጋዜጠኝነት ከህዝባዊ
ሃላፊነት ጋር ተዋህዶ ሲገኝ ግዙፍ ከራማ ይሆንና ላገሩ
ለወንዙ የምትከብዱ እመቤታትና ወይዛዝርት አድርጎ
በጦቢያ ሰማይ ላይ ያነግሳችሃል! !! እንዲህም ያለ ነገር
በዚህች መአዛ ብሩ በምትባል የሸገር ራዲዮ ፊት አውራሪ
፤ ጦቢያዊት ደርባባ ሴት ዘንድ ሲፈጸም አይተናልና ደርባባ
እህትና እናት ያልነሳሃን ያገሬ ሰማይ በረካ ሁንልኝ እንጅ
ሌላ ምን እልሃለሁ! !!!

@Nagayta
@getem
@getem
👍1
ለጁምኣ መዳረሻ
💛


ሀገሬ

(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)

አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት
ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ።
ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነጻነት።
በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነጻነት።
አገሬ ሃብት ነው።
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ።
ጠጁ ነው ወለላ ከኮኛክ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ።
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ።
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ !
ምነው ! ለምን ! እንዴት !
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ !
አሻፈረኝ እምቢ !
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ።
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት
ካያት ከቅደመ አያት የተረካከቡት
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ብጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ገነት ነው አገሬ።
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ
እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ።


ኮሎኝ ጀርመን 1959 ዓ.ም

@getem
@getem
@Nagayta
1
Audio
#ዝክረ_ቫለንቲኖ

በሮማኖች...አገር
ይሄውልሽ #ውዴ...በፊት ድሮ ድሮ
ሴት ሴቱን ሲከተል ፥ በዘቡ ተማሮ
ንጉስ... #ክላውዲዎስ
ለክተት ዘመቻ....
#ልጄን #ሚስቴን...በሚል ስስት እያነቀው
እንዴት ነው ጦረኛ ፥ ላገር የሚወድቀው ?
ብሎ ስለራደ...
ተባእቱን ሁላ.... ከተራክቦ አገደ
አሻፈረኝ ያለ .. #ሰማዕቱ_ቄስም
በንጉሱ ፈቃድ ስለተናደደ
#እስከተቀላበት...ህይወቱ እስካለፈ
በሚስጥር ፥ ስንቱን ጥንድ ፥ አጋብቶት አረፈ
እናም ዛሬ ዛሬ.......ባገርሽ ፣ ባገሬ
ቀይ....ቀዩ #ነገር ......እየተማገደ
ቫለንቲኖን ማሰብ ....ስለተለመደ
ምን ከኔ ባትኖሪ...
የት እንደሆንሽ እንኳን ፥ ባይጠረጠርም
ግራ ጎኔን #ለራት...ለደስታው ባልቀጥርም
እስክትመጪ ድረስ
#በቀይ ደምቄ........ቤቴን አሸብርቄ
አንቺ መናፈቄ
አስቤሽ መዝለቄ
በ ከማን አንሼ...እንዲያው ለነገሩ
ከማላውቀው አገር ፥ የነበሩት አባት ፥ እንዲህ ሲዘከሩ
ለማላውቅሽ አንቺ
#happy_valentine ...
የተባለ ምኞት ፥ ምኑ ላይ ነው #ነውሩ?

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

" #Happy_valentine_my_Love "
( #ባለሽበት_ቦታ)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
2👍1
ከፍቅር ደሴት ዳር
©ሲራክ
ሰኔ ሰላሳ ነው ያገኘውሽ እለት
ፍቅርሽን በልቤ ያነጋገስኩበት
አንቺ የኔ ውሃ
የኔ ድንቅ አምሃ
ከዶቅማው ዛፍ ስር
የከተብነው ፍቅር
ከመስኩ ቦርቀን ያሸትነው ትዝታ
ከወንዙ ዳርዳርታ በውኃው ድንፋታ
የቀማመርንበት
ጅምሩ ፍቅራችን ህይወት የዘራበት
ዛሬ ነው ቀናችን
አሁን ነው ጊዜያችን
ዘመናትን አልፎ ጅምሩን ያፀናው
እንደ ንስር በሮ ከልብሽ ያረፈው
አንቺ የኔ ውሃ
የኔ ድንቅ አምሃ
ከክፉ እንቅልፉ ያነቃሽው ልቤ
በአስኳላው ወኔ ያገኘሽ ምናቤ
ነይ እንሂድ ብሏል ከሀይቁ ዳርዳርታ
ብቅ በይ ይልሻል ሲመሽ ወደ ማታ
ሀይቁን ዳር አፅድቼ
መንፈሴን አፅንቼ
እጠብቅሻለሁ ስጋጃ ዘርግቼ
ሻማዬን አብርቼ
ከፍቅር ደሴት ዳር
በሀሴት ተሳክረን ስንበር እንድናድር
__________°°°°°°______________
ሲራክ @siraaq
መልካም የፍቅረኛሞች ቀን
መልካም ቫላንታይን
መልካም ባላንጣይን

@getem
@getem
@getem
@getem
Audio
እንዴት ነህ ፈጣሪ
(በረከት በላይነህ)

@getem
@getem
@getem
#እኖርልሻለሁ !
(© በርናባስ ከበደ)
-
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እኖርልሻለሁ፡፡

እንደ ጥዑም ቡና ፡ እንደሚያውድ እጣን
እንደ ትሁት ምላስ ፡ አባራሪ ሰይጣን፣
እንደ ዋሽንት ድምፅ ፡ እንደሚሰጥ ሀሴት
ሥነ-ሥርዐት እንዳላት ፡ አመለ-ሸጋ ሴት፣
እንደሚያምር ሸማ ፡ በሰዎች ገላ ላይ
እንደነዚ ሁሉ ፡ ከነዚህም በላይ፣
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እኖርልሻለሁ፡፡

ላንቺ ያለኝን ፍቅር -
ቃሌን ከሰማሽው ፡ ካየሽው መውደዴን
በይ አድምጭኝ ደሞ -
የበላኝን ነገር ፡ ያንጀቴን የሆዴን ፡፡

ሸሽቶ ካልበረረ -
ታጥቆ ካልዘመተ ፡ ዱር ወድቆ ካልቀረ
ጀግና አይባልም ወይ?
ቃል አልበላም ብሎ : ጦሙን ውሎ ያደረ?!
አይባልም ወይ ጀግና : እያለች ህይወቱ
ነፋስ ጎርፉን ችሎ : የፀናው በ’ምነቱ፡፡

እውነቴን እኮ ነው! …
እንዲያውም… እንዲያውም… ሞትማ ረፍት ነው!!
እረፍት እኮ ነው ሞት -
እርግፍ አርጎ መተው : ላንድዬው ግልግል
መኖር ግና ውጊያ : ከራስ ጋራ ትግል!
ከራስ አቋም ሙግት : ከራስ ሃሳብ ግጥሚያ
ተኩስ አቁም የሌለው : የዘላለም ፍልሚያ፡፡

ስለዚ’ ምክንያት : እነሆተ ቅኔ
አንድም ለዘመኔ፣ አንድም ለወገኔ፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እኖርልሻለሁ!!››
-
-
-
የሌሎች አገልጋይ : ብሆንም ምንደኛ
ወረቀት ያሰረኝ : የወር ደሞዝተኛ፣
የኮርኒስ አይጥና : ባለግዜ አለቃ
የሚጨፍሩብኝ : በመንታ ፈረቃ፣
ሀገር የምቀልብ : ላቤን ጥጄ በድስት
ሶስት ጨቅላ ልጆች : አንድ ትልቅ መንግስት፣…
ሳልሰስት እውቀቴን
ሳልቆጥብ ጉልበቴን፣
ካመት እስከ ዓመት : በትጋት በመዝለቅ
ደረጃና ደሞዝ : እድገት ስጠባበቅ፣…
ዛሬን እንዳይርበኝ : ቤሳቤስቲን ጥለው
ለነገ እንዳይተርፈኝ : በእርከን ከልለው፣
በትዝብት እያዩኝ
መፅውተው ሲሸኙኝ፣….
ሐዘኔ ቢመርም
ቅስሜ ቢሰበርም፣
ዘንድሮም እናዳምናው
ያው እንደካቻምናው …
ከእለት እንጀራ ጋር ፡ ቀጥላለች ህይወት
ግን ኣላማርርም -
ይሁን ተመስገን ነው ፡ እሱስ ማን አየበት?!
እላለሁ ‹ተመስገን!› -
ፀሎት እና ትጋት : ተስፋ ሲያመረቃኝ
አሜን!... ይሁን አሜን! ...
እኔም ሰው ቀጥሬ : ለመታማት ያብቃኝ|!!!
-
-
-
እንደ ጥዑም ቡና ፡ እንደሚያውድ እጣን
እንደ ትሁት ምላስ ፡ አባራሪ ሰይጣን፣
እንደ ዋሽንት ድምፅ ፡ እንደሚሰጥ ሀሴት
ሥነ-ሥርዐት እንዳላት ፡ አመለ-ሸጋ ሴት፣
እንደሚያምር ሸማ ፡ በሰዎች ገላ ላይ
እንደነዚ ሁሉ ፡ ከነዚህም በላይ፣
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እኖርልሻለሁ፡፡
-
-
-
አፈሯን ቢቅሙት ፡ ስኳር ጣፋጭ ነገር
ሳትሰስት በምትቸር ፡ በዚች ለምለም ሀገር፣
ብልጥግና እንዲሆን -
ኢንዱስትሪ እንዲያብብ ፡ በሚል ቃል ከለላ
ገበሬው ተገፍቶ ፡ ፊት ሲቆም ደላላ፣…
ወረት ፋሽን ጠልፎት -
ሰው ህልሙን እረስቶ ፡ ከቅዠት ሲፋቀር
ደመና ብርቅ ሆኖ -
ሰማይ ከንፈር ሳይገጥም ፡ እንደሳቀ ሲቀር፣…
ንፋስ እንዳጣፋው : የጎረምሳ ከንፈር
መሬት ሲሰነጠቅ : አለት ሲፈረፈር፣…
መጤ ነህ ተብሎ : ወገን ዱር ሲሰደድ
ከምርጥ ሰው ይልቅ : ምርጥ ዘር ሲወደድ፣…
ከሰማይ በራሪ : ከአንበጣ በቀር
ተዘዋውሮ መብላት : ዘበት ሆኖ ሲቀር፣…
ወተት አልሰጥ ብለው : ላሞች ሲለግሙ
ጥጆቹም እንደሰው : ‘አርብ-ሮብ’ ሲፆሙ፣…
ይህ ሁሉ ሲደረግ ፡ በብርሃን በግላጭ
ቢሰነጥቀኝም ፡ ቁጭት እንደ ምላጭ፣
“ዘራፍ ወንዱ!” ብዬ
ሞፈር ጅራፍ ጥዬ፣
ቁራሽ ዳቦ አልጎርስም ፡ ነጥቄ እንደ ሽፍታ
እርሜን ከምበላ -
ትብያ ሆኜ ልቅር ፡ ልሙት ዛሬ ማታ !!!

ዋጥ አርጌው እንጅ ፡ ቢቸግረኝ መላው
ንገረኝ ካልሽማ -
ብሶት መች ይጠፋል ፡ በሆድ የማብላላው፡፡

ይኸው በኛ ቀዬ -
መሬቱም እንደ ሰው ፡ እጅ መንሻ ለምዶ
አለማዳበርያ : ሣር አይበቅልም ሰርዶ !!
ይሁን!... ምንም አይደል -
ምርቱ ተትረፍርፎ : ጎተራ ከሞላ
ግን ውለታ አያውቅም -
ደሞ ለከርሞውም ፡ ይጠብቃል ሌላ!

ከገብሱ፣ ከስንዴው፣
ከጤፍ፣ ከሽምብራው ፡ እኩሉ ተሽጦ
እሽግ ማዳበርያ ፡ ኹኖ ተለውጦ፣
ስልቅጥ ያረገዋል ፡ አፈር ላንድ ‘ራቱ
ሰው “ጭሰኛ” ሆነ ፡ የገዛ መሬቱ !!!

አየሽልኝ አይደል?
እንዲ ነው ኑሮዬ ፡ ነገር አኳኋኔ
መተከዝ ምን ሊበጅ -
ችግሬ ላይ ስስቅ ፡ ፈክቶ ያልፋል ቀኔ፡፡
አኮቴት ነው ለአፌ -
ስተኛም ‹ተመስገን!› : ስነቃም ‹ተመስገን!›
የነገን የከርሞን : እርሱ ያውቃል መገን!!

አይጨክን አንድዬ : ባይዘልቅም ከጓዳ
ራዕይ ያሳየኛል : በሕልሜ ሰሌዳ!
አያለሁ በሕልሜ -
“ኩልል ያለ ውሃ : ከቧንቧ ስቀዳ
ሞፈር ወድያ ጥዬ : ትራክተር ስነዳ፣…
ግልገል አውሮፕላን -
ማሳዬ ገላ ላይ : ፀረ-ተባይ ሲረጭ
አረም እና ችጋር : በአጭሩ ሲቀጭ፣…
ፈረንጅ አሰልፌ : ስሸጥ ዳማከሴ
አንቱታ እና አክብሮት : ሲሆን ቡና ቁርሴ፣ …”
ኣያለሁ ዘለለት -
ሲባትል የዋለ : ጎኔን ሳሳርፈው
ምናል ለልጄ ሲል -
ሕልሜን እውን አርጎት : በስምሽ በፃፈው፡፡
-
-
-
እንደ ጥዑም ቡና ፡ እንደሚያውድ እጣን
እንደ ትሁት ምላስ ፡ አባራሪ ሰይጣን፣
እንደ ዋሽንት ድምፅ ፡ እንደሚሰጥ ሀሴት
ሥነ-ሥርዐት እንዳላት ፡ አመለ-ሸጋ ሴት፣
እንደሚያምር ሸማ ፡ በሰዎች ገላ ላይ
እንደነዚ ሁሉ ፡ ከነዚህም በላይ፣
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እኖርልሻለሁ፡፡
-
-
-
በክርስቶስ በኩል : ከዛም በሃዋርያት
በተሰጠው ሹመት : ቅዱስ ስነ-ሥርዓት፣
ካህኑ ሲያስተምር : ወንጌል መፅሃፍ ገልጦ
ምእመኑ እየሰማ : ፊት ለፊት ተቀምጦ፣
“አንድ ሰው ወደቀ…”
“ተቀሰፈ” ሲባል : በሃጥያት ተረታ
ሁሉም በአንድነት
እልልታን ያሰማል : በመተከዝ ፈንታ!

አሁን አሁንማ …
ይህን ሰሞንማ : ጭራሽ ብሶበታል
በአንድ እግር ያስቻለው : ተመስጦውን አቷል
ማንጎላጀት ቀርቶ ፡ አንጥፎ ተኝቷል!!

በአንቀጽ፣ በምዕራፍ
በየፀሎቱ ጫፍ
ጎሸም የሚያረገው ፡ ቀስቃሽ ይፈልጋል
በ‹አባት ሆይ!› ጀምሮ ፡ በ‹አሜን!› እስኪያሳርግ : አሥር ግዜ ያዛጋል፡፡

አዝማምያውን አይተን
ይህን ተመልክተን ፡ ለነገው ስንፈራ
ደሞ አዲሶች መጡ -
ተሸክመው ወስደው ፡ ሊያደርጉት ጭፍራ!!
ተስፋ የሚሸጡ ፡ ቅብዓት ነጋዴዎች
ሃሰተኛ ነብያት ፡ “የእግዚአብሔር ሰዎች”፣
በየመንገዱ ዳር -
የፈውስ የታምራት ፡ ድንኳን እየጣሉ
ይህ ምስኪን ህዝብሽን -
ቀኑን ይሰርቁታል ፡ “ይነጋል” እያሉ፡፡
“ይነጋል” እያሉ ፡ ይሰርቁታል ዓይኑን
“ይነጋል” እያሉ ፡ ይሰርቁታል ልቡን …
እስኪ እግዜር ይሁነው ፡ ይመልሰው ቀልቡን
እኔም ልቅሶው ይብቃኝ ፡ ስጭኝ መሃረቡን፡፡

ኢትዮጵያዬ እናቴ
ባፈርሽ ላይ ኑሬ : ካለቀረ መሞቴ
እነሆ ምኞቴ ፡ የዘመን ፀሎቴ!

ከትላንት እስከ ጥንት -
ሲሻው በሎሌው ላይ ፡ ሲሻው በመኳንንት
አድሮ ሚያስጨንቅሽ ፡ የአየር አጋንንት
ሰላሳ ክንድ ይራቅ -
ይውደቅ ይንፈራፈር ፡ ይሙት ትንፋሽ ይጣ
ሶስት ጊዜ ጩሆ ፡ ከግዛትሽ ይውጣ !!!
-
-
-
እንደ ጥዑም ቡና ፡ እንደሚያውድ እጣን
እንደ ትሁት ምላስ ፡ አባራሪ ሰይጣን፣
እንደ ዋሽንት ድምፅ ፡ እንደሚሰጥ ሀሴት
ሥነ-ሥርዐት እንዳላት ፡ አመለ-ሸጋ ሴት፣
እንደሚያምር ሸማ ፡ በሰዎች ገላ ላይ
እንደነዚ ሁሉ ፡ ከነዚህም በላይ፣
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እኖርልሻለሁ፡፡
-
-
-
እንደ ለውዝ ቆሎ : እንደ ጦር ማስቲካ
የመንገድ ዳር ሸቀጥ : ሲሆን ፖለቲካ፣
“ቀኝ ዘመም” ያልነው : አ
1
ድሮ ሲሆን ግራ
ከሊቅ እስከ ደቂቅ : ሲተነትን ሴራ፣…
ሹመት በዘር ገመድ -
በጎሳ በነገድ፣ ሲዋረስ እንደ ርስት
“ሙሴያችሁ ነኝ’’ ሲለን -
በትሩን የያዘው : ባለጊዜው መንግሥት፣…
ቀን ሰው እያነሳ : ቀን ሰው እየጣለ
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ …
እኔ ኩሩው ልጅሽ : በጣት የማይዘግኑኝ
ትንታግ የሳት ቋያ : እማያዳፍኑኝ፣
ባይኖረኝም ፓርቲ : የለት ውሎ መግቢያ
ምርጫ ምልክቱ : አርማው ማራገብያ፣
ቼ! ብዬ ማዘምተው : ባልመለምል ቡድን
አንዱን ረግጦ ሚገል : አንዱን ወድቆ እሚያድን፣
ጭቁኑ ላይ ቆሜ -
ጭንቁን አፋፍሜ : ድልን ባልጎነጭ
ግንባሬ ላብ እንጂ : ስልጣን ባያመነጭ፣
እንዴት ዝም ልበል -
ጆሮ ዳባ ብዬ : እስከመቼ ልዝለቅ
ፊት ለፊቴ እያየሁ -
በታሪክ ውትፍትፍ : ወገን ሲተላለቅ!

እናማ …
የቤትሽ ቅናት ቢበላኝ : ልቤ በሃዘን ቢደማ…
ጠቅል ብራና ይዤ : ወጣሁኝና ከማማ፣
ገድልሽን አንቀፅ በአንቀፅ : ከዳር እስከ ዳር ነዛሁት
እንኳንስ አፈር መሬቱን : ሰማዩን ጭምር ገዛሁት፡፡
በዘመን ጀርባ ታክኬ
የኋሊት ኋሊት ተጉዤ
ከዮቶር ሃረግ መዝዤ፣…
የዋሾ ምላሱ እስቲያንቀው : ነገርኩት ገናናው ሥሜን
ወአክሱም ወላሊበላ : አሀዱ ኢትዮጵያ አሜን!!!!
-
-
-
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እኖርልሻለሁ፡፡
-
ሞትማ ረፍት ነው -
እርግፍ አርጎ መተው : ላንድዬው ግልግል
መኖር ግና ውጊያ : ከራስ ጋራ ትግል!
ከራስ አቋም ሙግት : ከራስ ሃሳብ ግጥሚያ
ተኩስ አቁም የሌለው : የዘላለም ፍልሚያ፡፡
-
-
-
እንደ ጥዑም ቡና
እንደሚያውድ እጣን
እንደ ትሁት ምላስ : አባራሪ ሰይጣን፣
እንደ ዋሽንት ድምፅ ፡ እንደሚሰጥ ሀሴት
ሥነ-ሥርዐት እንዳላት ፡ አመለ-ሸጋ ሴት፣
እንደሚያምር ሸማ ፡ በሰዎች ገላ ላይ
እንደነዚ ሁሉ ፡ ከነዚህም በላይ፣
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፡ እኔ እ ወ ድ ሻ ለ ሁ
እንኳን መሞት ቀርቶ ፡ እ ኖ ር ል ሻ ለ ሁ!!!
------------------//------------------------
(© በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@getem
1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጋሞ!!!!!


ከቃጫው ገመድ ላይ ፤ ውብ ፍቅሩን ጠምጥሞ፤
በሰፊ ትከሻው፤
ጦቢያ የምትባል ያባቶቹን ኪዳን ሃገር ተሸክሞ፤
ሩቅ ነው ምናቡ፤
ሩቅ ነው መንገዱ፣ ዳርቻ የለውም እንደ አባያ ጫሞ፤
ወዘናው ሙሉ ነው፤
አፉ ይጣፍጣል፤
ብእሩ ይሰላል እንደ ጨንቻው ሰንደቅ እንደ አሰፋ ጫቦ፤
ጨንቻ ሚካኤል ላይ፤
ሳየው ደስ ይለኛል በአረንጓዴ አፈር ላይ በአዝመራ ታጅቦ፤
ልክ እንደተራራው፤
እንደ ጨንቻ ዳገት ወደ ላይ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ተሹሞ፤
ቃሉን የማይሽረው፤
የባንዲራው ጌታ ፤
የጦቢያ ባለሟል እንደምነው ዶርዜ እንደምነው ጋሞ???

(( ጃ ኖ ))💚💛

@getem
@getem