ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
(ባዶ ፍቺ)
ምራቅ የዋጥኩብሽ፣
የሰላም መንገዴ ፣
ምንም ቢሆን ምንም፣
የሥጋ ዘመዴ ፣
የልቤን ስብራት የጠገንሽ፣
መቋሚያ ግንዴ ሆነሽ ፣
ታሪኬን የለወጥሽልኝ ፣
ኑሮ በዘዴን ያስተማርሽኝ ።
አንቺ እኮ ነሽ ጥበብ ፣
የዓለምን ድብቅ ሚሥጥር፣
አንድበአንድ ያሳየሽኝ።
አዎን የኔ ጥበብ ፣
የስሜቴ ብቸኛ ተጋሪ፣
የውስጤን ችግር አውቀሽ፣
ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ አማካሪ ፣
ለእድገቴ ጎዳና ፣
ከጎኔ የምትሆኚ፣
አይዞሽ ብለሽ ሁሌም፣
እኔን ምታፅናኚ ፣
ምንጊዜም ታጋሽ ፣
ቶሎ ማትሰለቺ ፣
እስኪ እናወራ እውነት ፣
ማን አለ እንደ አንቺ ???
ከወደኩበት ባታነሺኝ፣
ነበርኩ ባዶ ፍቺ።
✍️ ቤዚቾ

@getem
@getem
@getem
..................ሴት...........

እዪ መስታወት በማለዳ:
ፈግጊ ፊቱ፡ ፊትሽ ትዋል ተስፋን ወልዳ፡፡
ሁኚ መስታወት አንፀባርቂ:
ንፁህና ገፅ አዋቂ፡፡
እዪ መብራት በጨለማ:
በድቅድቁ ተስፋሽ አይቀማ፡፡
ሁኚ መብራት ባለጨረር፡
ብርሀን ለቀሽ ፅልመት ይወረር፡፡
እዪ ውሀ እርጋታውን:
ደግነቱን፡
ዝም ማለቱን።
ሁኚ ውሀ ሩህሩህ አርኪ:
ለሰው ፈሰሽ ሰውን ባርኪ፡፡
እዪ ንፋስ፡አቅጣጫውን፡
ብልሀቱን፡
ብልጥነቱን፡፡
ሁኚ ንፋስ የቀደመች ውል ጠቋሚ፡
ያዘመመች ወደመልካም፡ መልካም ሰሚ፡፡
እዪ አፈር ለም ማልማቱን፡
ሁኚ አፈር ባለ እንቁ:
ለሰው እህት ሁኚው ብርቁ፡፡
እዪ ጠፈር ኮከብ ሀብቱን፡
ሁኚ ጠፈር ባለ ሚስጥር፡
ባለ ጥበብ ዝሪ ፍቅር፡፡
እዪ እነሱን፡ ሁኚ እነሱን፡፡
ተነጠቂ በልህቀት:
ተመንጠቂ በሰው'ነት።
ለሀዋም መልካሚቷ:
ለአዳማን እናቲቷ፡፡
ውሰጂ ዘር ስጪኝ ፍሬ፡
ልወድስሽ በከንፈሬ፡፡
ፊቴ ይብራ ፊትሽን ሲያይ፡
መንፈሳችን አይለያይ፡፡
ሰርክ ለምለም አስቢልኝ፡
በጎ ውለሽ ቸር አምሺልኝ፡፡
እዪ ሰማይ፡
ሁኚ ሰናይ፡፡
የሚስኪናን ማረፊያችን፡
የብቻነት መጠጊያችን፡፡
እዪ መስታወት፤ ሁኚ ውሀ፡
እዪ አፈር፤ ሁኚ ንፋስ፡
እዪ መብራት፤ ሁኚ ጠፈር፡፡
ምን ተስኖሽ፡ ምን ነስተሸኝ፡
ኩራቴ ነሽ ለእኔ ያለሽኝ።
ሴት፡፡

ርብቃ ሲሳይ
ተፃፈ:- 20/07/2011
ወልድያ፤ኢትዮጵያ


@getem
@getem
@getem
ክቡራትና ክቡራን ወድ የግጥም ብቻ ወዳጆች ለምንሰራው ጥናት እንዲረዳን ማህበራዊ ምልከታችሁን እንድትቸሩኝ ስል ለእናንተ እጠይቃለሁ!
 
 ጥያቄውም:- ''ስለሽመና'' ሙያ የተፃፉ መፅሃፍትን የተሰሩ ዘጋቢ ቪዲዮችን እንዲሁም እርሶ ስለሙያው የሚያውቁትን ከስር በሚገኘው ሊንክ ላይ እንዲያጋሩኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ።

በዚህ ይላኩልኝ @Mykey21
#ድንጋይ

እነርሱ ድንጋዩን ትውልድ ወገሩበት ፣
እኛም በተራችን ጥበብ አኖርንበት፡፡

ግን፤

የመግደል ማሻሩ ቢለያይም ውሉ፣
ጠቢብና ጠባብ ድንጋዩ ስር አሉ፡፡



@abiye12


@getem
@getem
@getem
"ደሃ አይጣላ ከውሃ"
አንዲት ሴት ነበረች የቤት ሰራተኛ
ቀን ስትደክም ውላ ሌትም የማትተኛ
ኑሮዋ ሆነና የአርባ ቀን ዕድሏ
ልጅ እያጠባች ነው የተለያት ባሏ
ላንድ ልጇ ስትል በነፃ እየሰራች
ደሞዟን ሳትል ነው ለፍታ ያሳደገች
እንደወጣ ቢቀር ያ ባሏ ያ ጎበዝ
ስትረግም ትኖራለች ያሻገረውን ወንዝ
ለራሷ ምትቀምሰው ምትልሰው ሳይኖራት
ምን ልታጠባ ነው የምትወለደው ሲሏት
ልጅ ስህተት አይደለም ከመጣ በኋላ
ብላ ተስፋ ቆርጣ ሄደች ዳግም ጥላ
ሀገር ጥላ ጠፍታ ተሰዳ በሩቁ
ትኑር ትሙት እንኳን አንዳቸው ሳያውቁ
ስንት ዘመን አልፎ ናፍቃ ብትመለስ
ይኸው ፊት አስነሳት የታቀፈችው ነፍስ
ምናለ ብትተው የባሏን እሮሮ
ያሻገረው ወንዝ መርገም በእንጉርጉሮ
ወንዙን አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
ከሀገር ሀገር ስትዞር ተሸክማ ጓዟን
ስንት አሳር አይታለች ለማሳደግ ልጇን
እረፍት እንኳን ሳታውቅ በነፃ እየሰራች
ወዟን አራግፋ ነው ለፍታ ያሳደገች
ታዲያ አንድ ቀን ጠዋት ማለዳ ተነስታ
ቅጠል ጠርጋ መጥታ ሳታርፍ እንኳን ለአፍታ
ልጇን በአንቀልባ አዝላ ውሀ ልትቀዳ
ከለመደችው ወንዝ መሸት ሲል ወርዳ
ጎንበስ ባለችበት በድካም ስሜቷ
አመለጣት ልጇ የዕድሏ ሀብቷ
ደራሽ ወሰደባት የት ገባ ፀሎቷ
የምትወደው ልጇ ሆነ የውሃ ሽታ
ምንያደርግላታል ብታለቅስ ብትረግመው
ከውሃ ተጣልታ የትም ለማትደርሰው
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ደሃ አይጣል ከውሃ
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ዳዊት ፅጌ

@getem
@getem
@getem
👍1
#ውሎ

ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ...
እስኒከር ተጫምታ ...
ቲሸርት በቁምጣ ....አዘንጧት ፈክታ
አጭር ፍሪዝ ፀጉሯን
አለፍ አለፍ... ብላ ብራውን ቀብታ
ቅሪላ ለማልፋት ....ኳስ ሜዳ ተገኝታ
ሹሌ ሲሏት ሹሌ...
ቴዘር ሲሏት ቴዘር
እንዳማራት ውላ ....ባማራት ስታድር
ሲሻትኝ በቴስታ....በደም የምትነክር
#ወንዳ_ወንድ_ሴት_ልጅ....
በሴት ተክለ ገላ...ያባቷ ዘረመል ...ለወንድ ሲያሾራት
የሰፈሯ ወንዶች ....ለጉድ ነው ሲወዷት
ሴት ወንድማቸውን....አይሹም ሊከፋት...
ልክ....እንደ ብርቅዬ....
#ሙድና ወንድነት...ባዲስ ቃና ጣዕም..ከፍቅሯ ሲቀዳ
ሽር ብትን....እንጂ ...
በሰፈር....በሜዳ
በፊቷ ለመቅሸም
መሰገጥ አይቃጣም ...ምርጥዬ እና አራዳ ።

#ሴት...እንዲሁም ሴት ናት....
ከጥንቱ ሲፈጥራት
እሬት...እሬት ያለ ...በኮሶ የታሸ...የሰለቸ ኑሮ
ሳያጩ...ሳይቋጩ......ከመአት ተምሮ
ለሆነች ሽራፊ ለደቂቃ ውሎ
...#ሀይ...#ባይ.....ለማለቱም... ሴት ያገኘ ግዜ
#ስሜቱ_ግልፅ_ነው
እለቱን ላበራ...በእንስቶች ፀጋ… ያለም ድንዛዜ
እናም ይችን ፍጥረት...ስጦታው ሳያንሳት
ዳግም አክሎባት
በወንድ አረማመድ ፥ ከወንዶቹ ጀማ ፥ እግሯ ሲወክላት
ድድ ማስጫው ዙሪያ....ካሉት ወንዶች ጋራ ፥ ባንድነት ስናያት
#በተመስጦ_አይኔ.......
መምጣቷን ወድጄ....አመጣጧን ስታዘብ
ከወንዶቹ ግንባር ....ይህ ነው #የሚነበብ
ሰላም ከማለቷ....
ውሀ የሚጠብሰው፥ አፈ ጮሌው ጀለስ
ምላሱ ይሰንፋል
ቀደም ቀደም ሲል ፥ ሾርኒዋን ፍራቻ ፥ ከማሸሞር ያርፋል
ፀበኛውም ጓዴ....
ይመችሽ እያለ.....ቴስታዋን ይሸሻል
የቀለደች...እንደው...
የከበበው ጀማ " #ዋህ " ብሎ ይፈርሳል
ካራዳነት ሰፈር...
እያመቻመቹ...በጓደኝነት መስክ ...ዘመን ይታረሳል
ልርሳህ...ቢሉት እንኳ..........ይህ መቼ ይረሳል
እድሜ ለሰጠው ሰው ....እንዳጀብ ይወሳል።

በዚህ...በኛ ሰፈር....
ከቤቴ....ፊት ለፊት
የለመድኳት ... #ቆንጆ......
ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ....አርቃኝ ከጎጆ
ከሰፈሬ ወንዶች....ከጀማው ከትሜ
ስትስቅ...ስቄላት
ስትነሳ....ቆሜ
ድፍረት ለለበሰው ...ውበቷ ታምሜ
በለት እየናረ .... ተሸርፎ አልቆ ቅስሜ
አይኖቼን ...አንብባ ፥ መውደዴ እስኪገባት
ካራዶች ጉባኤ....ከድንጋዩ አግዳሚ
የሷ ጋሻ ጃግሬ....የፍቅሯ ታማሚ...
እኖራለሁ እንጂ.....ሰርክ ስከተላት
ወንዳ ወንድ ውቤን ....ፍቅሬን ስመግባት
ደፍሬም...አልደፍር....
አፍሬም...አላፍራት..
ሳፈቅራትኝ ልኑር....እኔን ሳስለምዳት ።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
እውነትና ንጋት እያደር ይነጋል
የአበው አባባል ብርሀን ያበራል
እውነት እውነት ሆኖ ከተረጋገጠ
ፀሀይም መውጣቷ መንጋቱም አልቀረ
ውሸት ሀሰት ሆኖ ከጨለመ ቀኑ
ብርሀን አይታይ ዝንታለሙን ሁሉ።

ሶቅራጠስ

@getem
@getem
@getem
(በታመነ መንግስቴ)

አዛን አለ ሀረር
ጎንደር ይቀደሳል?
ኢሉ አባቦራ ላይ"ኢትዮጵያ" የሚለው ስምሽ ይወደሳል?
በአርያም አንች አለሽ
በጀነት ፣በገነት?
በየደማችን ነው ዛርና መንፈሱ
የኢትዮጵያዊነት?
አክሱም ፅዮን ጫፍላይ
ሠንደቅሽ ተተክሎ?
ወሎየ ሲመርቅ
ዘይር ጀባ ብሎ?

አክሊልሽ ጋምቤላ
በወርቅ ሲሰራ?
ሽናሻ ይፈታል ሰይጣን ያሰረውን
ጠልፎ 'ሚጥል ሴራ?
ክበሪልኝማ ራስ ደጀንሽ ላይ
ከፍፍፍፍ ወደ ማማ?
ልክሽ ዛግዌ ናት አክሱም ላሊበላ
ልዩ ነሽ እማማ?

እመኝኝ እናቴ ሰው ይሞታል እንጅ
የአንች አይቀርም ቃልሽ?
ያለውን አይረሳም በጨነቀሽ ጊዜ
ዘርጊልኝ የሚልሽ?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


@getem
@getem
@getem
የእስክሽር ሱሰኛ

እስክትሽሪ ዘፍነሽ እስክሽር ላስቆምሽኝ
የድምፅሽን ውበት ሌት ተቀን አትንሺኝ

አንቺው ባለቅኔ አንቺው ሰው አሻሪ
እንባ ነው ጉልበትሽ ወደሽ ስታፈቅሪ
እኔም ያንቺ አድማጭ የእስክሽር ሱሰኛ
ድምፅሽን ካልሰማው እንቅልፍ ባይኔ አይዞር ለሊቱን አልተኛ

እናምልሽ አንቺ ቃልሽን አክባሪ
ባይገጥምሽ ጓደኛ ለቀለበት ኗሪ
ድምፅሽን ለአንድ አፍታ ሰምቶሽ የወደደ
አንድ ልብ አለልሽ ከውሸት አለም ርቆ ወቶ የተሰደደ
በሙዚቃም ሀይል
መከዳትን ዘፍነሽ ነፍስ የዘራሽበት
እስክሽር ላፈቅርሽ በልብሽ ላይ ልዝመት

ባትረሺው ትዝታን በልብሽ ተስሎ
ቢተውሽ ነካክቶ ፍቅርን ተመስሎ
በድምፅሽ ለሻረው የእስክሽር ሱሰኛ
በይ ቶሎ ዳኝለት ሰላም ውሎ ይተኛ
ቃልሽ ላይነካ ፍፁም የነበረ
እስክትሽሪ ረስቶሽ ወድያው የተሰበረ
ለእግዜሩ ሰላምታ ምን ቢኮራ ላንቺ
ብዙ አይኖች አሉ የሚያዩ ወዳንቺ

ልካስሽ ለማለት ያልኩት ፈራ ተባ
ጉዳትሽን ሳስብ ነው መሆኑን ጉልበትሽ የስብራት እንባ

ማልቀስ እና ውበት ፣ ቃላትን ቢነሱኝ ፣ ከድምፅሽ ባንድምታ
የእስክሽር ሱሰኛ አስባለኝ ዝምታ።

ተፃፈ በአኒታ
@getem
@getem
@getem
@getem
(እንደ ፈንድሻ ተበተኑ )
ጊዜ ላይ ሳይቆሙ
ለስራ እያቅማሙ
ከራሳቸው አልፈዉ ፣
ሀገርን አስጠቆሩ ፣
በእኩይ ምግባራቸው ፣
ህፀፅ ተነከሩ ፣
ህይወት ምን ትሁን ምን ፣
ሚስጥር ገመናዋን ፣
ሳያጠኑ ፣
ፍሬያቸውን አጥተው፣
ለፈንድሻ አምሳል ደርሰው
ተበተኑ።

✍️ ቤዚቾ

@getem
@getem
@getem
እንደ ቀልድ ፈገግ (በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ፣ ሳቄ ይቀድመኛል።
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ፣ ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው!
እየሳቁ ውሎ ፣ እየሳቁ ማደር።
ውሸት ነው አትመኝ....
እዚህ ሀዘን የለም ፤ ሳቅ ነው የተረፈን
ህመም ለቆ ይሔዳል
"አመመኝ አመመኝ" ፣ በሚል አንድ ዘፈን።
.......
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? ፣ እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ፣ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ።
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ፣ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ፣ ምኔ እንደታመመ?
አያስቅም ታዲያ?!


@getem
@getem
1👍1
#ዛሬ አለም አቀፍ የራድዮ ቀን ነው ! የሸገሯን መዓዛ አለማመስገን ንፍጉነት ነው! መልካም የስራ ዘመን! ለሸገር ራድዮና ለጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ !


ማሪንጌ ቻ! !!!!!

ኧረ ሸገር ሸገር ፤ ሸገር ባውቶብሱ ፣
የመርካቶ ልጆች ፤
ሸ ከርተፍ እያሉ ፣ ከምኔው ደረሱ ።
ታምር አይደለም ወይ ፤ እንደ ሰማይ መና ፤
ሽበት ክብር ሲሆን ፤ እድሜና ቁመና ።
አስናቀ አስናቀ፤ አስናቀ ቢሉሽ ፤
ኬሬዳሽ በያቸው ፤አይስማ ጆሮሽ ፤
ቼ በይው ፤
ፈረሱን አቤ ነው ብለሽ ።
በደርባባው ዛትሽ ፤ በሁለመናሽ ፤
እንደ እቴጌ ማርዳ ፤ ያምራል ከራማሽ ፤
እድሜ ይቀጥላል ፤ ውብ አንደበትሽ ፤
መአዛ ማር ዘነብ ፤ መኣዛ ጥንቅሽ ።
ማሪንጌ ቻ ፤
ማሪንጌ ቻ ዘመናችን ይመር እንደ ማ'ዛ ብሩ ፤ እንደ አበበ በልቻ ።
ማሪንጌ ቻ! !!!

((( ጃ ኖ )))

መታፈር በከንፈር! !!!!! ያውም ደግሞ ልክ እንደ መኣዛ
ብሩ! !!!!


እናንት የጦቢያ እህቶቼ ሆይ! !!!!ከሴትነት ላይ የሰከነ
እውቀት ሲጨመርበት በዚያ ላይ ያደጉበትን ማህበረሰብ
ለዛና ወዘና ሳይለቁ የሚከወን ጋዜጠኝነት ከህዝባዊ
ሃላፊነት ጋር ተዋህዶ ሲገኝ ግዙፍ ከራማ ይሆንና ላገሩ
ለወንዙ የምትከብዱ እመቤታትና ወይዛዝርት አድርጎ
በጦቢያ ሰማይ ላይ ያነግሳችሃል! !! እንዲህም ያለ ነገር
በዚህች መአዛ ብሩ በምትባል የሸገር ራዲዮ ፊት አውራሪ
፤ ጦቢያዊት ደርባባ ሴት ዘንድ ሲፈጸም አይተናልና ደርባባ
እህትና እናት ያልነሳሃን ያገሬ ሰማይ በረካ ሁንልኝ እንጅ
ሌላ ምን እልሃለሁ! !!!

@Nagayta
@getem
@getem
👍1
ለጁምኣ መዳረሻ
💛


ሀገሬ

(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)

አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት
ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ።
ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነጻነት።
በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነጻነት።
አገሬ ሃብት ነው።
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ።
ጠጁ ነው ወለላ ከኮኛክ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ።
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ።
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ !
ምነው ! ለምን ! እንዴት !
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ !
አሻፈረኝ እምቢ !
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ።
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት
ካያት ከቅደመ አያት የተረካከቡት
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ብጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ገነት ነው አገሬ።
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ
እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ።


ኮሎኝ ጀርመን 1959 ዓ.ም

@getem
@getem
@Nagayta
1
Audio
#ዝክረ_ቫለንቲኖ

በሮማኖች...አገር
ይሄውልሽ #ውዴ...በፊት ድሮ ድሮ
ሴት ሴቱን ሲከተል ፥ በዘቡ ተማሮ
ንጉስ... #ክላውዲዎስ
ለክተት ዘመቻ....
#ልጄን #ሚስቴን...በሚል ስስት እያነቀው
እንዴት ነው ጦረኛ ፥ ላገር የሚወድቀው ?
ብሎ ስለራደ...
ተባእቱን ሁላ.... ከተራክቦ አገደ
አሻፈረኝ ያለ .. #ሰማዕቱ_ቄስም
በንጉሱ ፈቃድ ስለተናደደ
#እስከተቀላበት...ህይወቱ እስካለፈ
በሚስጥር ፥ ስንቱን ጥንድ ፥ አጋብቶት አረፈ
እናም ዛሬ ዛሬ.......ባገርሽ ፣ ባገሬ
ቀይ....ቀዩ #ነገር ......እየተማገደ
ቫለንቲኖን ማሰብ ....ስለተለመደ
ምን ከኔ ባትኖሪ...
የት እንደሆንሽ እንኳን ፥ ባይጠረጠርም
ግራ ጎኔን #ለራት...ለደስታው ባልቀጥርም
እስክትመጪ ድረስ
#በቀይ ደምቄ........ቤቴን አሸብርቄ
አንቺ መናፈቄ
አስቤሽ መዝለቄ
በ ከማን አንሼ...እንዲያው ለነገሩ
ከማላውቀው አገር ፥ የነበሩት አባት ፥ እንዲህ ሲዘከሩ
ለማላውቅሽ አንቺ
#happy_valentine ...
የተባለ ምኞት ፥ ምኑ ላይ ነው #ነውሩ?

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

" #Happy_valentine_my_Love "
( #ባለሽበት_ቦታ)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
2👍1
ከፍቅር ደሴት ዳር
©ሲራክ
ሰኔ ሰላሳ ነው ያገኘውሽ እለት
ፍቅርሽን በልቤ ያነጋገስኩበት
አንቺ የኔ ውሃ
የኔ ድንቅ አምሃ
ከዶቅማው ዛፍ ስር
የከተብነው ፍቅር
ከመስኩ ቦርቀን ያሸትነው ትዝታ
ከወንዙ ዳርዳርታ በውኃው ድንፋታ
የቀማመርንበት
ጅምሩ ፍቅራችን ህይወት የዘራበት
ዛሬ ነው ቀናችን
አሁን ነው ጊዜያችን
ዘመናትን አልፎ ጅምሩን ያፀናው
እንደ ንስር በሮ ከልብሽ ያረፈው
አንቺ የኔ ውሃ
የኔ ድንቅ አምሃ
ከክፉ እንቅልፉ ያነቃሽው ልቤ
በአስኳላው ወኔ ያገኘሽ ምናቤ
ነይ እንሂድ ብሏል ከሀይቁ ዳርዳርታ
ብቅ በይ ይልሻል ሲመሽ ወደ ማታ
ሀይቁን ዳር አፅድቼ
መንፈሴን አፅንቼ
እጠብቅሻለሁ ስጋጃ ዘርግቼ
ሻማዬን አብርቼ
ከፍቅር ደሴት ዳር
በሀሴት ተሳክረን ስንበር እንድናድር
__________°°°°°°______________
ሲራክ @siraaq
መልካም የፍቅረኛሞች ቀን
መልካም ቫላንታይን
መልካም ባላንጣይን

@getem
@getem
@getem
@getem
Audio
እንዴት ነህ ፈጣሪ
(በረከት በላይነህ)

@getem
@getem
@getem