#ያንቺው_ደቂቅ
:
:
ከቅዱስ ተራራ እንደመነጨ ኩልል ብሎ እንደጠራ
እንደ ጎበዝ ገበሬ ዘር እልፍ አላፍ የሚያፈራ
ልክ እንደ ፀደይ ሰማይ
ወለል ብሎ እንደሚታይ
ልዩ ስሜት እንከን የለሽ ያደባባይ ጥዑም ሚስጥር
ጨቅላ እፃናት የሚረዱት እሷ ለኔ አላት ፍቅር።
:
:
ጨቅላ እፃናት ሚገባቸው ሰሙም ወርቁም ማያሻማ
ለልብ ሀሴት መጠንሰሻ ሳትናገር የሚሰማ
ሁሉ ፈጥኖ የሚረዳው ግልፅ ስሜት ቀላል ቅኔ
ላዋቂው ሰው ላስተዋዩ ተሰወረ ምነው ከኔ።
:
:
የፍቅርን ታንኳ ቀዝፋ ከኔ ዘንዳ ስትመጣ
እንደ እፃን ስትቦርቅ በደስታ ጮቤ ረግጣ
ምትይዝ ምትለቀው ጠፍቷት ጥርሷ ሳይከደን አምሽቶ
ከርታታ ዓይኗ ሲስለመለም በእንቅልፍ አጀብ ተረቶ
ደረት ክንዴን ተንተርሳ ሰላም እንቅልፍ ተኝታለች
ከ አንዴም አንድ ሺህ ግዜ ፍቅሬ አንተነህ ብላኛለች።
:
:
ያ ፍም ስሜት ነበልባሉ ባይኗ ዘልቆ የሚያወራው
ቀልብ የሚስብ እጅግ ደማቅ እንደ ሩቢ የሚያበራው
ዋጋ ተመን የማይሰፍረው የከበረው ከቀይ እንቁ
የቀለም ቀንድ ከሆንኩት ሰው ምነው ከኔ መደበቁ።
:
:
ለኔ ያላት ጥልቅ ፍቅር ልብ ዘልቆ የሚያረካ
ንዋይ ከቶ የማይገዛው ባለም ሚዛን የማይለካ
መሰረቱ ወለል ጣራው የታነፀ በፅኑ ቃል
እንደሆነ እንኳን ሊቁ ደቂቁም ሰው በደንብ ያውቃል።
:
:
ሸክላ ፈራሽ ገላን ቀርቶ ነብሷን ለኔ አትሰስትም
እኔ ካለው አጠገቧ ግራዋውም አይመራትም
መታያዋም መደበቂያ እኔ እንደሆንኩ ህዝብ ያወራል
ልቤ ብቻ ከእውነታው ላይተያይ ተሰውሯል።
:
:
ቀን ከሌሊት ቢያዳምጡት በማይጠገብ አንደበቷ
እማሬውም ፍካሬውም አቻ ፍቺ የቃላቷ
እኔ ብቻ ሆኜ ሳለው የሷ ድርሰት ነፀብራቁ
ታዲያ ምነው ከእውነታው ልባም ልቤ መራራቁ።
:
:
የጭንቀቷ ማራገፊያ ወደቧ ነው ዓይኔን መሳም
አንገቴ ስር ስትወሸቅ ይሰማታል ልዩ ሰላም።
ዘቢብ ስሜት የማይነጥፍ ቀን ሲገፋ ውሎ ሲያድር
ደርሶ ሚስጥር ሆኖብኛል የሚታየው ገሀድ ፍቅር።
:
:
ሌላን ነገር ለመረዳት ቅፅበት እንኳን ማይወስድብኝ
ግልፁ ፍቅሯ ለምን ይሆን እንዲ ስውር የሆነበኝ።
ልጅ አዋቂው የተረዳው ያደባባይ ግልብ ነገር
ባለ ማዕረግ የሆንኩት ሰው እንዴት እኔ ልደናገር?
እያልኩ ሁሌ ደጋግሜ እኔው እኔን ጠይቄያለው
ቀለም ቁጥር አመክንዮ አይገልፃትም አውቄያለው።
:
:
ለካ ፍቅርን ለመረዳት ሊቅ ደቂቅን አያካትም
ስሜት ስሌት የሆነበት መቼም ቢሆን አያውቃትም።
ለኔ ካለት ፍቅር ጋራም የገባኝን ሳነፃፅር
የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ኢምንት ነው የሚያሳፍር።
እናም ለምን እንዳልገባኝ ደጋግሜ ሳውጠነጥን
ስሌት እንጂ ስሜት የለኝ የሷን ፍቅር የሚመጥን።
ጠቢቧ ሴት አስተዋዩዋ ረቂቋ የኔ አፍቃሪ
ለሌላ ሰው የቀለም ቀንድ ላንቺ ደቂቅ ነኝ ተማሪ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu
@getem
@getem
@getem
:
:
ከቅዱስ ተራራ እንደመነጨ ኩልል ብሎ እንደጠራ
እንደ ጎበዝ ገበሬ ዘር እልፍ አላፍ የሚያፈራ
ልክ እንደ ፀደይ ሰማይ
ወለል ብሎ እንደሚታይ
ልዩ ስሜት እንከን የለሽ ያደባባይ ጥዑም ሚስጥር
ጨቅላ እፃናት የሚረዱት እሷ ለኔ አላት ፍቅር።
:
:
ጨቅላ እፃናት ሚገባቸው ሰሙም ወርቁም ማያሻማ
ለልብ ሀሴት መጠንሰሻ ሳትናገር የሚሰማ
ሁሉ ፈጥኖ የሚረዳው ግልፅ ስሜት ቀላል ቅኔ
ላዋቂው ሰው ላስተዋዩ ተሰወረ ምነው ከኔ።
:
:
የፍቅርን ታንኳ ቀዝፋ ከኔ ዘንዳ ስትመጣ
እንደ እፃን ስትቦርቅ በደስታ ጮቤ ረግጣ
ምትይዝ ምትለቀው ጠፍቷት ጥርሷ ሳይከደን አምሽቶ
ከርታታ ዓይኗ ሲስለመለም በእንቅልፍ አጀብ ተረቶ
ደረት ክንዴን ተንተርሳ ሰላም እንቅልፍ ተኝታለች
ከ አንዴም አንድ ሺህ ግዜ ፍቅሬ አንተነህ ብላኛለች።
:
:
ያ ፍም ስሜት ነበልባሉ ባይኗ ዘልቆ የሚያወራው
ቀልብ የሚስብ እጅግ ደማቅ እንደ ሩቢ የሚያበራው
ዋጋ ተመን የማይሰፍረው የከበረው ከቀይ እንቁ
የቀለም ቀንድ ከሆንኩት ሰው ምነው ከኔ መደበቁ።
:
:
ለኔ ያላት ጥልቅ ፍቅር ልብ ዘልቆ የሚያረካ
ንዋይ ከቶ የማይገዛው ባለም ሚዛን የማይለካ
መሰረቱ ወለል ጣራው የታነፀ በፅኑ ቃል
እንደሆነ እንኳን ሊቁ ደቂቁም ሰው በደንብ ያውቃል።
:
:
ሸክላ ፈራሽ ገላን ቀርቶ ነብሷን ለኔ አትሰስትም
እኔ ካለው አጠገቧ ግራዋውም አይመራትም
መታያዋም መደበቂያ እኔ እንደሆንኩ ህዝብ ያወራል
ልቤ ብቻ ከእውነታው ላይተያይ ተሰውሯል።
:
:
ቀን ከሌሊት ቢያዳምጡት በማይጠገብ አንደበቷ
እማሬውም ፍካሬውም አቻ ፍቺ የቃላቷ
እኔ ብቻ ሆኜ ሳለው የሷ ድርሰት ነፀብራቁ
ታዲያ ምነው ከእውነታው ልባም ልቤ መራራቁ።
:
:
የጭንቀቷ ማራገፊያ ወደቧ ነው ዓይኔን መሳም
አንገቴ ስር ስትወሸቅ ይሰማታል ልዩ ሰላም።
ዘቢብ ስሜት የማይነጥፍ ቀን ሲገፋ ውሎ ሲያድር
ደርሶ ሚስጥር ሆኖብኛል የሚታየው ገሀድ ፍቅር።
:
:
ሌላን ነገር ለመረዳት ቅፅበት እንኳን ማይወስድብኝ
ግልፁ ፍቅሯ ለምን ይሆን እንዲ ስውር የሆነበኝ።
ልጅ አዋቂው የተረዳው ያደባባይ ግልብ ነገር
ባለ ማዕረግ የሆንኩት ሰው እንዴት እኔ ልደናገር?
እያልኩ ሁሌ ደጋግሜ እኔው እኔን ጠይቄያለው
ቀለም ቁጥር አመክንዮ አይገልፃትም አውቄያለው።
:
:
ለካ ፍቅርን ለመረዳት ሊቅ ደቂቅን አያካትም
ስሜት ስሌት የሆነበት መቼም ቢሆን አያውቃትም።
ለኔ ካለት ፍቅር ጋራም የገባኝን ሳነፃፅር
የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ኢምንት ነው የሚያሳፍር።
እናም ለምን እንዳልገባኝ ደጋግሜ ሳውጠነጥን
ስሌት እንጂ ስሜት የለኝ የሷን ፍቅር የሚመጥን።
ጠቢቧ ሴት አስተዋዩዋ ረቂቋ የኔ አፍቃሪ
ለሌላ ሰው የቀለም ቀንድ ላንቺ ደቂቅ ነኝ ተማሪ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu
@getem
@getem
@getem
👍1
ቆንጂት
"""""""""
መች ተራው ሊነካት
በጥበብ ተፈጥራ በጥበብ የምትኖር
ይቺ ስመ ቆንጂት
እንዲው በደፈናው ያወቃት ማን ነበር?
ውስጠቷን ገላልጦ ካልፈተሻት በቀር
ስለ እሷ ማን ይንገር?
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
በጥበብ ያልኖረ
እንዲው እሚንገላወድ ከአላፊ አግዳሚ፤
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
ቁንጅናን የማያውቅ
አይናዋጅ ያለበት ሁሉን አቅፎ ሳሚ።
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
አድርባይ ሴረኛ
የክፋትን ዳና ተከትሎ ተጓዥ
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
ሀቅ እውነትን ጥሎ
የውሸት ካራ መዛዥ እውነትን አመርቃዥ።
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
ስሜት የጋለበው
ስክነት የጠፋበት ከሁሉ በራሪ፤
ይኸው የሱ ሆነች
ከወተት ከረጋው ከፍቅር አሳሪ።
እናማ ሰዓሊው
ብሩሹን አቅልሞ
ከዘረጋው ሸራ ጥበብ የቀመረው፤
ድንገት ትቷት ሄዶ
ሰዓሊው ቀረበት ኖረች ከገጠመው።
ምንም ማረግ አይቻልም
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
"""""""""
መች ተራው ሊነካት
በጥበብ ተፈጥራ በጥበብ የምትኖር
ይቺ ስመ ቆንጂት
እንዲው በደፈናው ያወቃት ማን ነበር?
ውስጠቷን ገላልጦ ካልፈተሻት በቀር
ስለ እሷ ማን ይንገር?
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
በጥበብ ያልኖረ
እንዲው እሚንገላወድ ከአላፊ አግዳሚ፤
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
ቁንጅናን የማያውቅ
አይናዋጅ ያለበት ሁሉን አቅፎ ሳሚ።
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
አድርባይ ሴረኛ
የክፋትን ዳና ተከትሎ ተጓዥ
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
ሀቅ እውነትን ጥሎ
የውሸት ካራ መዛዥ እውነትን አመርቃዥ።
ድሮንስ ማን ሊያውቃት?
ስሜት የጋለበው
ስክነት የጠፋበት ከሁሉ በራሪ፤
ይኸው የሱ ሆነች
ከወተት ከረጋው ከፍቅር አሳሪ።
እናማ ሰዓሊው
ብሩሹን አቅልሞ
ከዘረጋው ሸራ ጥበብ የቀመረው፤
ድንገት ትቷት ሄዶ
ሰዓሊው ቀረበት ኖረች ከገጠመው።
ምንም ማረግ አይቻልም
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
(ባዶ ፍቺ)
ምራቅ የዋጥኩብሽ፣
የሰላም መንገዴ ፣
ምንም ቢሆን ምንም፣
የሥጋ ዘመዴ ፣
የልቤን ስብራት የጠገንሽ፣
መቋሚያ ግንዴ ሆነሽ ፣
ታሪኬን የለወጥሽልኝ ፣
ኑሮ በዘዴን ያስተማርሽኝ ።
አንቺ እኮ ነሽ ጥበብ ፣
የዓለምን ድብቅ ሚሥጥር፣
አንድበአንድ ያሳየሽኝ።
አዎን የኔ ጥበብ ፣
የስሜቴ ብቸኛ ተጋሪ፣
የውስጤን ችግር አውቀሽ፣
ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ አማካሪ ፣
ለእድገቴ ጎዳና ፣
ከጎኔ የምትሆኚ፣
አይዞሽ ብለሽ ሁሌም፣
እኔን ምታፅናኚ ፣
ምንጊዜም ታጋሽ ፣
ቶሎ ማትሰለቺ ፣
እስኪ እናወራ እውነት ፣
ማን አለ እንደ አንቺ ???
ከወደኩበት ባታነሺኝ፣
ነበርኩ ባዶ ፍቺ።
✍️ ቤዚቾ
@getem
@getem
@getem
ምራቅ የዋጥኩብሽ፣
የሰላም መንገዴ ፣
ምንም ቢሆን ምንም፣
የሥጋ ዘመዴ ፣
የልቤን ስብራት የጠገንሽ፣
መቋሚያ ግንዴ ሆነሽ ፣
ታሪኬን የለወጥሽልኝ ፣
ኑሮ በዘዴን ያስተማርሽኝ ።
አንቺ እኮ ነሽ ጥበብ ፣
የዓለምን ድብቅ ሚሥጥር፣
አንድበአንድ ያሳየሽኝ።
አዎን የኔ ጥበብ ፣
የስሜቴ ብቸኛ ተጋሪ፣
የውስጤን ችግር አውቀሽ፣
ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ አማካሪ ፣
ለእድገቴ ጎዳና ፣
ከጎኔ የምትሆኚ፣
አይዞሽ ብለሽ ሁሌም፣
እኔን ምታፅናኚ ፣
ምንጊዜም ታጋሽ ፣
ቶሎ ማትሰለቺ ፣
እስኪ እናወራ እውነት ፣
ማን አለ እንደ አንቺ ???
ከወደኩበት ባታነሺኝ፣
ነበርኩ ባዶ ፍቺ።
✍️ ቤዚቾ
@getem
@getem
@getem
..................ሴት...........
እዪ መስታወት በማለዳ:
ፈግጊ ፊቱ፡ ፊትሽ ትዋል ተስፋን ወልዳ፡፡
ሁኚ መስታወት አንፀባርቂ:
ንፁህና ገፅ አዋቂ፡፡
እዪ መብራት በጨለማ:
በድቅድቁ ተስፋሽ አይቀማ፡፡
ሁኚ መብራት ባለጨረር፡
ብርሀን ለቀሽ ፅልመት ይወረር፡፡
እዪ ውሀ እርጋታውን:
ደግነቱን፡
ዝም ማለቱን።
ሁኚ ውሀ ሩህሩህ አርኪ:
ለሰው ፈሰሽ ሰውን ባርኪ፡፡
እዪ ንፋስ፡አቅጣጫውን፡
ብልሀቱን፡
ብልጥነቱን፡፡
ሁኚ ንፋስ የቀደመች ውል ጠቋሚ፡
ያዘመመች ወደመልካም፡ መልካም ሰሚ፡፡
እዪ አፈር ለም ማልማቱን፡
ሁኚ አፈር ባለ እንቁ:
ለሰው እህት ሁኚው ብርቁ፡፡
እዪ ጠፈር ኮከብ ሀብቱን፡
ሁኚ ጠፈር ባለ ሚስጥር፡
ባለ ጥበብ ዝሪ ፍቅር፡፡
እዪ እነሱን፡ ሁኚ እነሱን፡፡
ተነጠቂ በልህቀት:
ተመንጠቂ በሰው'ነት።
ለሀዋም መልካሚቷ:
ለአዳማን እናቲቷ፡፡
ውሰጂ ዘር ስጪኝ ፍሬ፡
ልወድስሽ በከንፈሬ፡፡
ፊቴ ይብራ ፊትሽን ሲያይ፡
መንፈሳችን አይለያይ፡፡
ሰርክ ለምለም አስቢልኝ፡
በጎ ውለሽ ቸር አምሺልኝ፡፡
እዪ ሰማይ፡
ሁኚ ሰናይ፡፡
የሚስኪናን ማረፊያችን፡
የብቻነት መጠጊያችን፡፡
እዪ መስታወት፤ ሁኚ ውሀ፡
እዪ አፈር፤ ሁኚ ንፋስ፡
እዪ መብራት፤ ሁኚ ጠፈር፡፡
ምን ተስኖሽ፡ ምን ነስተሸኝ፡
ኩራቴ ነሽ ለእኔ ያለሽኝ።
ሴት፡፡
✍ ርብቃ ሲሳይ
ተፃፈ:- 20/07/2011
ወልድያ፤ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
እዪ መስታወት በማለዳ:
ፈግጊ ፊቱ፡ ፊትሽ ትዋል ተስፋን ወልዳ፡፡
ሁኚ መስታወት አንፀባርቂ:
ንፁህና ገፅ አዋቂ፡፡
እዪ መብራት በጨለማ:
በድቅድቁ ተስፋሽ አይቀማ፡፡
ሁኚ መብራት ባለጨረር፡
ብርሀን ለቀሽ ፅልመት ይወረር፡፡
እዪ ውሀ እርጋታውን:
ደግነቱን፡
ዝም ማለቱን።
ሁኚ ውሀ ሩህሩህ አርኪ:
ለሰው ፈሰሽ ሰውን ባርኪ፡፡
እዪ ንፋስ፡አቅጣጫውን፡
ብልሀቱን፡
ብልጥነቱን፡፡
ሁኚ ንፋስ የቀደመች ውል ጠቋሚ፡
ያዘመመች ወደመልካም፡ መልካም ሰሚ፡፡
እዪ አፈር ለም ማልማቱን፡
ሁኚ አፈር ባለ እንቁ:
ለሰው እህት ሁኚው ብርቁ፡፡
እዪ ጠፈር ኮከብ ሀብቱን፡
ሁኚ ጠፈር ባለ ሚስጥር፡
ባለ ጥበብ ዝሪ ፍቅር፡፡
እዪ እነሱን፡ ሁኚ እነሱን፡፡
ተነጠቂ በልህቀት:
ተመንጠቂ በሰው'ነት።
ለሀዋም መልካሚቷ:
ለአዳማን እናቲቷ፡፡
ውሰጂ ዘር ስጪኝ ፍሬ፡
ልወድስሽ በከንፈሬ፡፡
ፊቴ ይብራ ፊትሽን ሲያይ፡
መንፈሳችን አይለያይ፡፡
ሰርክ ለምለም አስቢልኝ፡
በጎ ውለሽ ቸር አምሺልኝ፡፡
እዪ ሰማይ፡
ሁኚ ሰናይ፡፡
የሚስኪናን ማረፊያችን፡
የብቻነት መጠጊያችን፡፡
እዪ መስታወት፤ ሁኚ ውሀ፡
እዪ አፈር፤ ሁኚ ንፋስ፡
እዪ መብራት፤ ሁኚ ጠፈር፡፡
ምን ተስኖሽ፡ ምን ነስተሸኝ፡
ኩራቴ ነሽ ለእኔ ያለሽኝ።
ሴት፡፡
✍ ርብቃ ሲሳይ
ተፃፈ:- 20/07/2011
ወልድያ፤ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
"ደሃ አይጣላ ከውሃ"
አንዲት ሴት ነበረች የቤት ሰራተኛ
ቀን ስትደክም ውላ ሌትም የማትተኛ
ኑሮዋ ሆነና የአርባ ቀን ዕድሏ
ልጅ እያጠባች ነው የተለያት ባሏ
ላንድ ልጇ ስትል በነፃ እየሰራች
ደሞዟን ሳትል ነው ለፍታ ያሳደገች
እንደወጣ ቢቀር ያ ባሏ ያ ጎበዝ
ስትረግም ትኖራለች ያሻገረውን ወንዝ
ለራሷ ምትቀምሰው ምትልሰው ሳይኖራት
ምን ልታጠባ ነው የምትወለደው ሲሏት
ልጅ ስህተት አይደለም ከመጣ በኋላ
ብላ ተስፋ ቆርጣ ሄደች ዳግም ጥላ
ሀገር ጥላ ጠፍታ ተሰዳ በሩቁ
ትኑር ትሙት እንኳን አንዳቸው ሳያውቁ
ስንት ዘመን አልፎ ናፍቃ ብትመለስ
ይኸው ፊት አስነሳት የታቀፈችው ነፍስ
ምናለ ብትተው የባሏን እሮሮ
ያሻገረው ወንዝ መርገም በእንጉርጉሮ
ወንዙን አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
ከሀገር ሀገር ስትዞር ተሸክማ ጓዟን
ስንት አሳር አይታለች ለማሳደግ ልጇን
እረፍት እንኳን ሳታውቅ በነፃ እየሰራች
ወዟን አራግፋ ነው ለፍታ ያሳደገች
ታዲያ አንድ ቀን ጠዋት ማለዳ ተነስታ
ቅጠል ጠርጋ መጥታ ሳታርፍ እንኳን ለአፍታ
ልጇን በአንቀልባ አዝላ ውሀ ልትቀዳ
ከለመደችው ወንዝ መሸት ሲል ወርዳ
ጎንበስ ባለችበት በድካም ስሜቷ
አመለጣት ልጇ የዕድሏ ሀብቷ
ደራሽ ወሰደባት የት ገባ ፀሎቷ
የምትወደው ልጇ ሆነ የውሃ ሽታ
ምንያደርግላታል ብታለቅስ ብትረግመው
ከውሃ ተጣልታ የትም ለማትደርሰው
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ደሃ አይጣል ከውሃ
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ዳዊት ፅጌ
@getem
@getem
@getem
አንዲት ሴት ነበረች የቤት ሰራተኛ
ቀን ስትደክም ውላ ሌትም የማትተኛ
ኑሮዋ ሆነና የአርባ ቀን ዕድሏ
ልጅ እያጠባች ነው የተለያት ባሏ
ላንድ ልጇ ስትል በነፃ እየሰራች
ደሞዟን ሳትል ነው ለፍታ ያሳደገች
እንደወጣ ቢቀር ያ ባሏ ያ ጎበዝ
ስትረግም ትኖራለች ያሻገረውን ወንዝ
ለራሷ ምትቀምሰው ምትልሰው ሳይኖራት
ምን ልታጠባ ነው የምትወለደው ሲሏት
ልጅ ስህተት አይደለም ከመጣ በኋላ
ብላ ተስፋ ቆርጣ ሄደች ዳግም ጥላ
ሀገር ጥላ ጠፍታ ተሰዳ በሩቁ
ትኑር ትሙት እንኳን አንዳቸው ሳያውቁ
ስንት ዘመን አልፎ ናፍቃ ብትመለስ
ይኸው ፊት አስነሳት የታቀፈችው ነፍስ
ምናለ ብትተው የባሏን እሮሮ
ያሻገረው ወንዝ መርገም በእንጉርጉሮ
ወንዙን አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
ከሀገር ሀገር ስትዞር ተሸክማ ጓዟን
ስንት አሳር አይታለች ለማሳደግ ልጇን
እረፍት እንኳን ሳታውቅ በነፃ እየሰራች
ወዟን አራግፋ ነው ለፍታ ያሳደገች
ታዲያ አንድ ቀን ጠዋት ማለዳ ተነስታ
ቅጠል ጠርጋ መጥታ ሳታርፍ እንኳን ለአፍታ
ልጇን በአንቀልባ አዝላ ውሀ ልትቀዳ
ከለመደችው ወንዝ መሸት ሲል ወርዳ
ጎንበስ ባለችበት በድካም ስሜቷ
አመለጣት ልጇ የዕድሏ ሀብቷ
ደራሽ ወሰደባት የት ገባ ፀሎቷ
የምትወደው ልጇ ሆነ የውሃ ሽታ
ምንያደርግላታል ብታለቅስ ብትረግመው
ከውሃ ተጣልታ የትም ለማትደርሰው
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
እሷም አለችው ብላ ጠጋ 'ላንተም አለ በጋ'
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ደሃ አይጣል ከውሃ
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ደሃ አይጣላ ከውሃ
ዳዊት ፅጌ
@getem
@getem
@getem
👍1
#ውሎ
ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ...
እስኒከር ተጫምታ ...
ቲሸርት በቁምጣ ....አዘንጧት ፈክታ
አጭር ፍሪዝ ፀጉሯን
አለፍ አለፍ... ብላ ብራውን ቀብታ
ቅሪላ ለማልፋት ....ኳስ ሜዳ ተገኝታ
ሹሌ ሲሏት ሹሌ...
ቴዘር ሲሏት ቴዘር
እንዳማራት ውላ ....ባማራት ስታድር
ሲሻትኝ በቴስታ....በደም የምትነክር
#ወንዳ_ወንድ_ሴት_ልጅ....
በሴት ተክለ ገላ...ያባቷ ዘረመል ...ለወንድ ሲያሾራት
የሰፈሯ ወንዶች ....ለጉድ ነው ሲወዷት
ሴት ወንድማቸውን....አይሹም ሊከፋት...
ልክ....እንደ ብርቅዬ....
#ሙድና ወንድነት...ባዲስ ቃና ጣዕም..ከፍቅሯ ሲቀዳ
ሽር ብትን....እንጂ ...
በሰፈር....በሜዳ
በፊቷ ለመቅሸም
መሰገጥ አይቃጣም ...ምርጥዬ እና አራዳ ።
#ሴት...እንዲሁም ሴት ናት....
ከጥንቱ ሲፈጥራት
እሬት...እሬት ያለ ...በኮሶ የታሸ...የሰለቸ ኑሮ
ሳያጩ...ሳይቋጩ......ከመአት ተምሮ
ለሆነች ሽራፊ ለደቂቃ ውሎ
...#ሀይ...#ባይ.....ለማለቱም... ሴት ያገኘ ግዜ
#ስሜቱ_ግልፅ_ነው
እለቱን ላበራ...በእንስቶች ፀጋ… ያለም ድንዛዜ
እናም ይችን ፍጥረት...ስጦታው ሳያንሳት
ዳግም አክሎባት
በወንድ አረማመድ ፥ ከወንዶቹ ጀማ ፥ እግሯ ሲወክላት
ድድ ማስጫው ዙሪያ....ካሉት ወንዶች ጋራ ፥ ባንድነት ስናያት
#በተመስጦ_አይኔ.......
መምጣቷን ወድጄ....አመጣጧን ስታዘብ
ከወንዶቹ ግንባር ....ይህ ነው #የሚነበብ
ሰላም ከማለቷ....
ውሀ የሚጠብሰው፥ አፈ ጮሌው ጀለስ
ምላሱ ይሰንፋል
ቀደም ቀደም ሲል ፥ ሾርኒዋን ፍራቻ ፥ ከማሸሞር ያርፋል
ፀበኛውም ጓዴ....
ይመችሽ እያለ.....ቴስታዋን ይሸሻል
የቀለደች...እንደው...
የከበበው ጀማ " #ዋህ " ብሎ ይፈርሳል
ካራዳነት ሰፈር...
እያመቻመቹ...በጓደኝነት መስክ ...ዘመን ይታረሳል
ልርሳህ...ቢሉት እንኳ..........ይህ መቼ ይረሳል
እድሜ ለሰጠው ሰው ....እንዳጀብ ይወሳል።
በዚህ...በኛ ሰፈር....
ከቤቴ....ፊት ለፊት
የለመድኳት ... #ቆንጆ......
ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ....አርቃኝ ከጎጆ
ከሰፈሬ ወንዶች....ከጀማው ከትሜ
ስትስቅ...ስቄላት
ስትነሳ....ቆሜ
ድፍረት ለለበሰው ...ውበቷ ታምሜ
በለት እየናረ .... ተሸርፎ አልቆ ቅስሜ
አይኖቼን ...አንብባ ፥ መውደዴ እስኪገባት
ካራዶች ጉባኤ....ከድንጋዩ አግዳሚ
የሷ ጋሻ ጃግሬ....የፍቅሯ ታማሚ...
እኖራለሁ እንጂ.....ሰርክ ስከተላት
ወንዳ ወንድ ውቤን ....ፍቅሬን ስመግባት
ደፍሬም...አልደፍር....
አፍሬም...አላፍራት..
ሳፈቅራትኝ ልኑር....እኔን ሳስለምዳት ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
@getem
ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ...
እስኒከር ተጫምታ ...
ቲሸርት በቁምጣ ....አዘንጧት ፈክታ
አጭር ፍሪዝ ፀጉሯን
አለፍ አለፍ... ብላ ብራውን ቀብታ
ቅሪላ ለማልፋት ....ኳስ ሜዳ ተገኝታ
ሹሌ ሲሏት ሹሌ...
ቴዘር ሲሏት ቴዘር
እንዳማራት ውላ ....ባማራት ስታድር
ሲሻትኝ በቴስታ....በደም የምትነክር
#ወንዳ_ወንድ_ሴት_ልጅ....
በሴት ተክለ ገላ...ያባቷ ዘረመል ...ለወንድ ሲያሾራት
የሰፈሯ ወንዶች ....ለጉድ ነው ሲወዷት
ሴት ወንድማቸውን....አይሹም ሊከፋት...
ልክ....እንደ ብርቅዬ....
#ሙድና ወንድነት...ባዲስ ቃና ጣዕም..ከፍቅሯ ሲቀዳ
ሽር ብትን....እንጂ ...
በሰፈር....በሜዳ
በፊቷ ለመቅሸም
መሰገጥ አይቃጣም ...ምርጥዬ እና አራዳ ።
#ሴት...እንዲሁም ሴት ናት....
ከጥንቱ ሲፈጥራት
እሬት...እሬት ያለ ...በኮሶ የታሸ...የሰለቸ ኑሮ
ሳያጩ...ሳይቋጩ......ከመአት ተምሮ
ለሆነች ሽራፊ ለደቂቃ ውሎ
...#ሀይ...#ባይ.....ለማለቱም... ሴት ያገኘ ግዜ
#ስሜቱ_ግልፅ_ነው
እለቱን ላበራ...በእንስቶች ፀጋ… ያለም ድንዛዜ
እናም ይችን ፍጥረት...ስጦታው ሳያንሳት
ዳግም አክሎባት
በወንድ አረማመድ ፥ ከወንዶቹ ጀማ ፥ እግሯ ሲወክላት
ድድ ማስጫው ዙሪያ....ካሉት ወንዶች ጋራ ፥ ባንድነት ስናያት
#በተመስጦ_አይኔ.......
መምጣቷን ወድጄ....አመጣጧን ስታዘብ
ከወንዶቹ ግንባር ....ይህ ነው #የሚነበብ
ሰላም ከማለቷ....
ውሀ የሚጠብሰው፥ አፈ ጮሌው ጀለስ
ምላሱ ይሰንፋል
ቀደም ቀደም ሲል ፥ ሾርኒዋን ፍራቻ ፥ ከማሸሞር ያርፋል
ፀበኛውም ጓዴ....
ይመችሽ እያለ.....ቴስታዋን ይሸሻል
የቀለደች...እንደው...
የከበበው ጀማ " #ዋህ " ብሎ ይፈርሳል
ካራዳነት ሰፈር...
እያመቻመቹ...በጓደኝነት መስክ ...ዘመን ይታረሳል
ልርሳህ...ቢሉት እንኳ..........ይህ መቼ ይረሳል
እድሜ ለሰጠው ሰው ....እንዳጀብ ይወሳል።
በዚህ...በኛ ሰፈር....
ከቤቴ....ፊት ለፊት
የለመድኳት ... #ቆንጆ......
ወንዳ ወንድ ሴት ልጅ....አርቃኝ ከጎጆ
ከሰፈሬ ወንዶች....ከጀማው ከትሜ
ስትስቅ...ስቄላት
ስትነሳ....ቆሜ
ድፍረት ለለበሰው ...ውበቷ ታምሜ
በለት እየናረ .... ተሸርፎ አልቆ ቅስሜ
አይኖቼን ...አንብባ ፥ መውደዴ እስኪገባት
ካራዶች ጉባኤ....ከድንጋዩ አግዳሚ
የሷ ጋሻ ጃግሬ....የፍቅሯ ታማሚ...
እኖራለሁ እንጂ.....ሰርክ ስከተላት
ወንዳ ወንድ ውቤን ....ፍቅሬን ስመግባት
ደፍሬም...አልደፍር....
አፍሬም...አላፍራት..
ሳፈቅራትኝ ልኑር....እኔን ሳስለምዳት ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
@getem
✍(በታመነ መንግስቴ)
አዛን አለ ሀረር
ጎንደር ይቀደሳል?
ኢሉ አባቦራ ላይ"ኢትዮጵያ" የሚለው ስምሽ ይወደሳል?
በአርያም አንች አለሽ
በጀነት ፣በገነት?
በየደማችን ነው ዛርና መንፈሱ
የኢትዮጵያዊነት?
አክሱም ፅዮን ጫፍላይ
ሠንደቅሽ ተተክሎ?
ወሎየ ሲመርቅ
ዘይር ጀባ ብሎ?
አክሊልሽ ጋምቤላ
በወርቅ ሲሰራ?
ሽናሻ ይፈታል ሰይጣን ያሰረውን
ጠልፎ 'ሚጥል ሴራ?
ክበሪልኝማ ራስ ደጀንሽ ላይ
ከፍፍፍፍ ወደ ማማ?
ልክሽ ዛግዌ ናት አክሱም ላሊበላ
ልዩ ነሽ እማማ?
እመኝኝ እናቴ ሰው ይሞታል እንጅ
የአንች አይቀርም ቃልሽ?
ያለውን አይረሳም በጨነቀሽ ጊዜ
ዘርጊልኝ የሚልሽ?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@getem
@getem
@getem
አዛን አለ ሀረር
ጎንደር ይቀደሳል?
ኢሉ አባቦራ ላይ"ኢትዮጵያ" የሚለው ስምሽ ይወደሳል?
በአርያም አንች አለሽ
በጀነት ፣በገነት?
በየደማችን ነው ዛርና መንፈሱ
የኢትዮጵያዊነት?
አክሱም ፅዮን ጫፍላይ
ሠንደቅሽ ተተክሎ?
ወሎየ ሲመርቅ
ዘይር ጀባ ብሎ?
አክሊልሽ ጋምቤላ
በወርቅ ሲሰራ?
ሽናሻ ይፈታል ሰይጣን ያሰረውን
ጠልፎ 'ሚጥል ሴራ?
ክበሪልኝማ ራስ ደጀንሽ ላይ
ከፍፍፍፍ ወደ ማማ?
ልክሽ ዛግዌ ናት አክሱም ላሊበላ
ልዩ ነሽ እማማ?
እመኝኝ እናቴ ሰው ይሞታል እንጅ
የአንች አይቀርም ቃልሽ?
ያለውን አይረሳም በጨነቀሽ ጊዜ
ዘርጊልኝ የሚልሽ?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@getem
@getem
@getem
የእስክሽር ሱሰኛ
።
እስክትሽሪ ዘፍነሽ እስክሽር ላስቆምሽኝ
የድምፅሽን ውበት ሌት ተቀን አትንሺኝ
።
አንቺው ባለቅኔ አንቺው ሰው አሻሪ
እንባ ነው ጉልበትሽ ወደሽ ስታፈቅሪ
እኔም ያንቺ አድማጭ የእስክሽር ሱሰኛ
ድምፅሽን ካልሰማው እንቅልፍ ባይኔ አይዞር ለሊቱን አልተኛ
።
እናምልሽ አንቺ ቃልሽን አክባሪ
ባይገጥምሽ ጓደኛ ለቀለበት ኗሪ
ድምፅሽን ለአንድ አፍታ ሰምቶሽ የወደደ
አንድ ልብ አለልሽ ከውሸት አለም ርቆ ወቶ የተሰደደ
በሙዚቃም ሀይል
መከዳትን ዘፍነሽ ነፍስ የዘራሽበት
እስክሽር ላፈቅርሽ በልብሽ ላይ ልዝመት
።
ባትረሺው ትዝታን በልብሽ ተስሎ
ቢተውሽ ነካክቶ ፍቅርን ተመስሎ
በድምፅሽ ለሻረው የእስክሽር ሱሰኛ
በይ ቶሎ ዳኝለት ሰላም ውሎ ይተኛ
ቃልሽ ላይነካ ፍፁም የነበረ
እስክትሽሪ ረስቶሽ ወድያው የተሰበረ
ለእግዜሩ ሰላምታ ምን ቢኮራ ላንቺ
ብዙ አይኖች አሉ የሚያዩ ወዳንቺ
።
ልካስሽ ለማለት ያልኩት ፈራ ተባ
ጉዳትሽን ሳስብ ነው መሆኑን ጉልበትሽ የስብራት እንባ
።
ማልቀስ እና ውበት ፣ ቃላትን ቢነሱኝ ፣ ከድምፅሽ ባንድምታ
የእስክሽር ሱሰኛ አስባለኝ ዝምታ።
ተፃፈ በአኒታ
@getem
@getem
@getem
@getem
።
እስክትሽሪ ዘፍነሽ እስክሽር ላስቆምሽኝ
የድምፅሽን ውበት ሌት ተቀን አትንሺኝ
።
አንቺው ባለቅኔ አንቺው ሰው አሻሪ
እንባ ነው ጉልበትሽ ወደሽ ስታፈቅሪ
እኔም ያንቺ አድማጭ የእስክሽር ሱሰኛ
ድምፅሽን ካልሰማው እንቅልፍ ባይኔ አይዞር ለሊቱን አልተኛ
።
እናምልሽ አንቺ ቃልሽን አክባሪ
ባይገጥምሽ ጓደኛ ለቀለበት ኗሪ
ድምፅሽን ለአንድ አፍታ ሰምቶሽ የወደደ
አንድ ልብ አለልሽ ከውሸት አለም ርቆ ወቶ የተሰደደ
በሙዚቃም ሀይል
መከዳትን ዘፍነሽ ነፍስ የዘራሽበት
እስክሽር ላፈቅርሽ በልብሽ ላይ ልዝመት
።
ባትረሺው ትዝታን በልብሽ ተስሎ
ቢተውሽ ነካክቶ ፍቅርን ተመስሎ
በድምፅሽ ለሻረው የእስክሽር ሱሰኛ
በይ ቶሎ ዳኝለት ሰላም ውሎ ይተኛ
ቃልሽ ላይነካ ፍፁም የነበረ
እስክትሽሪ ረስቶሽ ወድያው የተሰበረ
ለእግዜሩ ሰላምታ ምን ቢኮራ ላንቺ
ብዙ አይኖች አሉ የሚያዩ ወዳንቺ
።
ልካስሽ ለማለት ያልኩት ፈራ ተባ
ጉዳትሽን ሳስብ ነው መሆኑን ጉልበትሽ የስብራት እንባ
።
ማልቀስ እና ውበት ፣ ቃላትን ቢነሱኝ ፣ ከድምፅሽ ባንድምታ
የእስክሽር ሱሰኛ አስባለኝ ዝምታ።
ተፃፈ በአኒታ
@getem
@getem
@getem
@getem
እንደ ቀልድ ፈገግ (በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ፣ ሳቄ ይቀድመኛል።
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ፣ ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው!
እየሳቁ ውሎ ፣ እየሳቁ ማደር።
ውሸት ነው አትመኝ....
እዚህ ሀዘን የለም ፤ ሳቅ ነው የተረፈን
ህመም ለቆ ይሔዳል
"አመመኝ አመመኝ" ፣ በሚል አንድ ዘፈን።
.......
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? ፣ እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ፣ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ።
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ፣ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ፣ ምኔ እንደታመመ?
አያስቅም ታዲያ?!
@getem
@getem
.
.
አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ፣ ሳቄ ይቀድመኛል።
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ፣ ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው!
እየሳቁ ውሎ ፣ እየሳቁ ማደር።
ውሸት ነው አትመኝ....
እዚህ ሀዘን የለም ፤ ሳቅ ነው የተረፈን
ህመም ለቆ ይሔዳል
"አመመኝ አመመኝ" ፣ በሚል አንድ ዘፈን።
.......
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? ፣ እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ፣ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ።
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ፣ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ፣ ምኔ እንደታመመ?
አያስቅም ታዲያ?!
@getem
@getem
❤1👍1
#ዛሬ አለም አቀፍ የራድዮ ቀን ነው ! የሸገሯን መዓዛ አለማመስገን ንፍጉነት ነው! መልካም የስራ ዘመን! ለሸገር ራድዮና ለጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ !
ማሪንጌ ቻ! !!!!!
ኧረ ሸገር ሸገር ፤ ሸገር ባውቶብሱ ፣
የመርካቶ ልጆች ፤
ሸ ከርተፍ እያሉ ፣ ከምኔው ደረሱ ።
ታምር አይደለም ወይ ፤ እንደ ሰማይ መና ፤
ሽበት ክብር ሲሆን ፤ እድሜና ቁመና ።
አስናቀ አስናቀ፤ አስናቀ ቢሉሽ ፤
ኬሬዳሽ በያቸው ፤አይስማ ጆሮሽ ፤
ቼ በይው ፤
ፈረሱን አቤ ነው ብለሽ ።
በደርባባው ዛትሽ ፤ በሁለመናሽ ፤
እንደ እቴጌ ማርዳ ፤ ያምራል ከራማሽ ፤
እድሜ ይቀጥላል ፤ ውብ አንደበትሽ ፤
መአዛ ማር ዘነብ ፤ መኣዛ ጥንቅሽ ።
ማሪንጌ ቻ ፤
ማሪንጌ ቻ ዘመናችን ይመር እንደ ማ'ዛ ብሩ ፤ እንደ አበበ በልቻ ።
ማሪንጌ ቻ! !!!
((( ጃ ኖ )))
መታፈር በከንፈር! !!!!! ያውም ደግሞ ልክ እንደ መኣዛ
ብሩ! !!!!
እናንት የጦቢያ እህቶቼ ሆይ! !!!!ከሴትነት ላይ የሰከነ
እውቀት ሲጨመርበት በዚያ ላይ ያደጉበትን ማህበረሰብ
ለዛና ወዘና ሳይለቁ የሚከወን ጋዜጠኝነት ከህዝባዊ
ሃላፊነት ጋር ተዋህዶ ሲገኝ ግዙፍ ከራማ ይሆንና ላገሩ
ለወንዙ የምትከብዱ እመቤታትና ወይዛዝርት አድርጎ
በጦቢያ ሰማይ ላይ ያነግሳችሃል! !! እንዲህም ያለ ነገር
በዚህች መአዛ ብሩ በምትባል የሸገር ራዲዮ ፊት አውራሪ
፤ ጦቢያዊት ደርባባ ሴት ዘንድ ሲፈጸም አይተናልና ደርባባ
እህትና እናት ያልነሳሃን ያገሬ ሰማይ በረካ ሁንልኝ እንጅ
ሌላ ምን እልሃለሁ! !!!
@Nagayta
@getem
@getem
ማሪንጌ ቻ! !!!!!
ኧረ ሸገር ሸገር ፤ ሸገር ባውቶብሱ ፣
የመርካቶ ልጆች ፤
ሸ ከርተፍ እያሉ ፣ ከምኔው ደረሱ ።
ታምር አይደለም ወይ ፤ እንደ ሰማይ መና ፤
ሽበት ክብር ሲሆን ፤ እድሜና ቁመና ።
አስናቀ አስናቀ፤ አስናቀ ቢሉሽ ፤
ኬሬዳሽ በያቸው ፤አይስማ ጆሮሽ ፤
ቼ በይው ፤
ፈረሱን አቤ ነው ብለሽ ።
በደርባባው ዛትሽ ፤ በሁለመናሽ ፤
እንደ እቴጌ ማርዳ ፤ ያምራል ከራማሽ ፤
እድሜ ይቀጥላል ፤ ውብ አንደበትሽ ፤
መአዛ ማር ዘነብ ፤ መኣዛ ጥንቅሽ ።
ማሪንጌ ቻ ፤
ማሪንጌ ቻ ዘመናችን ይመር እንደ ማ'ዛ ብሩ ፤ እንደ አበበ በልቻ ።
ማሪንጌ ቻ! !!!
((( ጃ ኖ )))
መታፈር በከንፈር! !!!!! ያውም ደግሞ ልክ እንደ መኣዛ
ብሩ! !!!!
እናንት የጦቢያ እህቶቼ ሆይ! !!!!ከሴትነት ላይ የሰከነ
እውቀት ሲጨመርበት በዚያ ላይ ያደጉበትን ማህበረሰብ
ለዛና ወዘና ሳይለቁ የሚከወን ጋዜጠኝነት ከህዝባዊ
ሃላፊነት ጋር ተዋህዶ ሲገኝ ግዙፍ ከራማ ይሆንና ላገሩ
ለወንዙ የምትከብዱ እመቤታትና ወይዛዝርት አድርጎ
በጦቢያ ሰማይ ላይ ያነግሳችሃል! !! እንዲህም ያለ ነገር
በዚህች መአዛ ብሩ በምትባል የሸገር ራዲዮ ፊት አውራሪ
፤ ጦቢያዊት ደርባባ ሴት ዘንድ ሲፈጸም አይተናልና ደርባባ
እህትና እናት ያልነሳሃን ያገሬ ሰማይ በረካ ሁንልኝ እንጅ
ሌላ ምን እልሃለሁ! !!!
@Nagayta
@getem
@getem
👍1
ለጁምኣ መዳረሻ
💛
ሀገሬ
(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)
አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት
ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ።
ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነጻነት።
በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነጻነት።
አገሬ ሃብት ነው።
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ።
ጠጁ ነው ወለላ ከኮኛክ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ።
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ።
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ !
ምነው ! ለምን ! እንዴት !
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ !
አሻፈረኝ እምቢ !
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ።
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት
ካያት ከቅደመ አያት የተረካከቡት
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ብጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ገነት ነው አገሬ።
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ
እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ።
ኮሎኝ ጀርመን 1959 ዓ.ም
@getem
@getem
@Nagayta
💛
ሀገሬ
(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)
አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት
ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ።
ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነጻነት።
በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነጻነት።
አገሬ ሃብት ነው።
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ።
ጠጁ ነው ወለላ ከኮኛክ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ።
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ።
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ !
ምነው ! ለምን ! እንዴት !
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ !
አሻፈረኝ እምቢ !
መቅደስ ነው አገሬ፣
አድባር ነው አገሬ።
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት
ካያት ከቅደመ አያት የተረካከቡት
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ብጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ገነት ነው አገሬ።
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ
እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ።
ኮሎኝ ጀርመን 1959 ዓ.ም
@getem
@getem
@Nagayta
❤1