ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የስሌት #ጋብቻ
#አንቺ
ሽማግሌ አዘጋጅ ብለሽ ተናግረሻል
ምን አለው ይሉኛል ብለሽ ተጨንቀሻል
#እኔ
ከቀየው መርጬ
በቂ ሽማግሌ አዘጋጅቻለሁ
የሌለኝ ነገር
ለራሴ አለኝ ብዬ በቃል ሸምድጃለሁ
#እነሱ
ቤተዘመድ መጥቶ
ምን አለው ለማለት ማልዶ ይሰለፋል
ሽማግሌ ከቦ
ምን አለው ለሚባል
የወላጅ ጥያቄ የሐሰት መልስ ይፅፋል
#ውዴ #አትጨነቂ
ያንቺ ብቻ አይደለም የሀገር ነው ችግሩ
እኛም ቤት ብትመጪ ይሔው ነው ነገሩ
#አምና
የታናሽ እህቴ
የልጅነት ፍቅሯ አመት በአል አስታኮ
በፍቅር መርቀን
ፈቅደን እንድንሰጠው ሽማግሌ ልኮ
#መልስ #ሲጠባበቅ
በዚህ ወገን ሆኜ እኔም ጠይቄያለሁ
ማይደርስብኝ መስሎኝ ምን አለው ብያለሁ
በሴት ወገን ስንሆን የወንዱን ባናውቅም
ምን አለው ተብሎ ሰው አይጠየቅም
ሀቅ ተዟዙሮ
ቦታ ተቀያይሮ
የትናንት ተቀባይ ከነገ ወዲያ ይልካል
በሴቷ ጠይቆ በወንድ ይጠየቃል
ሸፋፍነነው እንጂ
ደፍረን ከጠራነው ነገሩ ያሳስባል
በንግድ አጠያየቅ
ምን አለው አይደለም ስንት አለው ነው ሚባል
ባንክ ቤት ስንት አለው በጥሬው ያኖረው
ስንት መኪና አለው የሚያሽከረክረው
ስንት ካሬ መሬት ካርታ የወጣለት
ስንት ክፍል ቪላ የተንጣለለለት
በልጅ የደም ቀለም የሌለንን ስንስል
ልጅ የምንድር ሳይሆን ገዢ ነው ምንመስል
የመመኘት ቀመር
የማዟዟር ብዜት በዘመን ሲጣፋ
ምን አለው ነው እንጂ
ከዬት አመጣው የሚል ሽማግሌ ጠፋ
#እኔ #ምለው ?
የማካፈል ስሌት ዞሮ የመጣ ‘ለት
ምን ያህል ይዘናል ምን አለው ለማለት
#ይልቅ
እግዚአብሔር አድሎት
በጥላቻ ዘመን የሰው ልጅ ሲፋቀር
አፍቃሪ ልብና
ሁሉም ነገር አለው ከሀብት በስተቀር
ሀቁን እያወቅነው ውጠን ከማባበል
ምን አለውን ትተን ምን የለውም እንበል
=====||=====
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@beppa_19
1
#የሐገር #ፍቅር #ስሜት
አረንጓዴ ቢጫ
ቀይ ቀለም ካየ ብእሩን ያነሳል
ገጣሚ አይናፋር ነው
አንገት ይደፋና ስንኝ ይቀልሳል
* * *
ካድሬ ግን ደፋር ነው
ካድሬ ፈጣጣ ነው መች አይቶ ይለቃል
በሰው ሀገር ገብቶ ኮኮብ ይጠይቃል
ከሙሉቀን ሰ•

\💚መልካም💛 ቀን❤️\

@getem
@getem
@beppa_19
( ነቃበል)
ጀምበሯ ሳትጠልቅ ፣ የወደቀን አንሳ፤
ህልምህ እንዲሰምር ፣ መስጠትን አትርሳ፤
አላካፍል ብለህ ፣ ብቻህን አትብላ፤
ገሀነምንሽተህ ፣ ፅድቅህን አትጥላ፤
ቤዚቾ

@getem
@getem
🙏 50 % @ ( ) 🙏


ነገር ለማመስጠር ፤ ማንም ቢጣጣርም
በተቀደደው ልክ ፤ መበርገዱ አይቀርም

@getem
@getem
@getem

አምደማሪያም ጠይብ (ፊዳው)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
(በjo)

በፀጥታ ላይ ትዝታ
በትዝታ ላይ መኝታ...
በነበር ላይ እንሆናለን
በባዶ ሜዳ እንከብራለን።

አይ እኛ........

ፀጥ ብሎ መኝታ
ከዛም ተስፋ ማድረግ፤
እረብሻን ቀስቅሶ
በአንዱ እንባ ላይ ማደግ፤
ነበር እንጂ ያለን
መች ደረሰ ላሁን፤
ቀደምት ታሪካችን
መች ጠቀመን አሁን፤

አዎን መች ጠፍቶናል.........

ደግሞም ተስፋ ማድረግ
አልጋ ላይ ተኝቶ፤
የህልም እንጀራን ማኘክ።

ግና ከዚህ ሁሉ......

ነበር ሳይሆን ለሁን፣
ግዜው ክፉ ሳይሆን፣
ፀሀይቱም ሳትጠልቅ፣
ጨረቃም ሳትለቅ........
በድቅድቅ ጨለማ
እንደሚበራ ኮከብ
አሁን ነው መፈንጠቅ.......




ተፃፈ በ @Mak_bale
29.5.2012

@getem
@getem
@getem
👍1
ደጋሽ ነጋሽ
በምድር እንፋሎት ዶሮ ወጥ አበሰልኩ
በጨረቃዋ ፍም ድፎ ዳቦ ጋገርኩ
መአልቱ ሲነጋ የህልሜን ቀን ደገስኩ
✧✧✧✧✧✧✧✧
ሲራክ @siraaq

@getem
@getem
@getem
@getem
ፈላጊው ሲፈለግ
©ሲራክ
እንባዬን አድርቆ ውስጤን ያቆሰለ
እልፍ አመት ያኖረኝ ያ ፍቅርሽ የታለ?

ሲራክ @siraaq
#
@getem
@getem
@getem
@getem
#ሹ ክ ሹ ክ ታ
እንቺ
የኔ ኮልታፋ
በለሌሊቱ ሰማይ
ከፀጥታው በላይ
በመሸው አለም ላይ
የኛ ሹክሹክታ ነው ሚሰማው ባለም ላይ
በጣፋጭ አንደበት
በኮልታፋው አፍሽ ስትንሾካሾኪ
#አፈቅልሀለሁ ብለሽ ፍቅርሽን ስትሰብኪ
ሌሊቴን በኮልታፋው አፍሽ ከቶ ስታፈኪ
      ሰይጣን ተላካፊው ከቶ ግርም ሲለው
      ደግሞ በዚ ምሽት ደሞ የምን ፍቅር ነው
      ጥያቄ ሲያበዛ መግቢያ መውጫው
        ሰይጣንስ ቢጠፋው
      ሚለክፈውን ጉብል አንቺ ስታስቆሚው
      #አፈቅልሀለሁ ስትይኝ
      ከቶ ሚቃጠለው
ከፀበል ቀጥሎ የኔ ኮልተረፋ ናት ለሰይጣን መፍትሄው
    አቦ ተኮላተፊልኝ
አፍሽ ሲኮላተፍ
የኔ ልብ ይመታል
ቃል ስታጣምሚ
ሀሴቴ ይመጣል
ወልከፍ ስትይልኝ
ጥርሴ ይፈለቀለቃል
የማላቀው ስሜት እንዲህ ሹክ በላት ይለኛል
ፍቅሌ
አቅልሻለሁ ሁሌ
ተኮላተፍኩ እንዴ
አወየው እድሌ
አንደበትሽ
ከኔ ስለሆነ ነው
አሁንማ
ትናጋሽ የኔም ነው

                             ተፃፈ በብላቴናው ብዕር

@getem
@getem
@getem
@getem
አንፃር
ፍቅር የዘላለም ደቂቃ
መሰልቸት የደቂቃ ዘላለም
አኗኗሩ እንጂ
ጊዜ ሩቅ አይደለም
ህይወት አላጠረም።
####////////////####
#የምድር ዘላለም
ዲበኩሉ ጌታ
@getem
@getem
@getem
@siraaq
ላንቺ ስል...
(በላይ በቀለ ወያ)


<<እንጀራ እወዳለሁ >> ፥ ስትዪኝ ሰምቼ
አንቺን ደስ እንዲልሽ ፥ አብሲቱን ጠጥቼ
ሞቼልሽ ነበረ ፥ ኩፍታ አብዝቼ😂
ደግሞ እንደገና…
<<ማፍቀር መታደል ነው>> ፥ ስትይ ሰማሁና
አንቺን እረስቼ ፤ ሌላ አፈቀርኩልሽ
ምን ማልሆነው አለ ፥ አንቺን ደስ እንዲልሽ?!😂
።።።
@getem
@getem
#jeko
1
ኤዶማዊ ውበት
©ሲራክ
ኤዶማዊት ውበት ፍኖተ ገሞራ
እንዲህም አላየው ውበት ከዚያ ጎራ
ከእሱዋ ኒቄጥራ .....
በአውደ ሲመቱ መርቆ ቢፈጥራት
ከስምም ስም መርጦ ኢትዮጵያዊት አላት
______°°°________°°°________
ስጦታነቷ ለኔዋ ለኤዶሜ ትሁንልኝ
ሲራክ @siraaq
----
@getem
@getem
@getem
👍1
አጥብቆ ተመልካች
/በዕውቀቱ ስዩም/
*--------------*
አይሽ አይሽና
አበባ ከንፈሯ
አበባ ከንፈሯ
ከንፈሯ እንዴት ያምራል!
እንኳን የኔን ገላ ንቦችን ይጠራል
እያልኩ አስባልሁ
ከንፈርሽን አያለሁ።
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አበባ ከንፈሯ
አበባ ከንፈሯ
ትንሽ አብጧል መሰል
ማነው የቀጠፋት?
ተስማ ነውንጂ መቼም ንብ አይነድፋት
እያልኩ አስባለሁ
ከንፈርሽን አያለሁ።
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይደለም ከንፈሯ
አይኔ ነው ያበጠው
አይቶ ያታለለ
ከንፈሯን ያሳየኝ ቅል እያሳከለ
እያልኩ አስባለሁ
ከንፈርሽን አያለሁ።
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይኔን እንቃለሁ
ከፊቴ የማየው
ከንፈር ይሁን ግንባር
እንዴት ብዬ አውቃለሁ?
እያልኩ አስባለሁ።
~~~~~~~~~~~

@getem
@getem
@beppa_19
1
በግራሽ -እቀፊኝ
== == == == ጋሻው ለኔ
ውዴ ሆይ ነይልኝ እንኩዋን ደህና መጣሽ
በጣም በርዶኝ ነበር ካጠገቤ ሳጣሽ
በይ እቅፍ አድርጊኝ ግራ እጅሽን ዘርጊ
ባይሆን ቀኝ እጅሽን ትንሽ ወደዛ አርጊ
ኡፍፍ...
በቀኝ መታቀፍ
እንዴት ነው የሚቀፍ?
እባክሽን ውዴ.....ያልኩሽን ሰምተሻል?
ቀኝሽን አርቂው ግራሽ ነው የሚሻል
በቀኝ እጅሽማ
ለስንቱ ጎረምሳ ሰላምታ ሰጥተሻል
የሰው ከጃይ ሁሉ የዘየረሽ መስሎ
ሲያልፍ አይቸዋለሁ ከመዳፍሽ መሃል ምኞት ቀልቡን ጥሎ::
ምን ይህ ብቻ ውዴ?
ከታሪክ ገፅ ላይ ብታተኩሪ አንዴ
ስንት ገራሚ እውነት ታገኝ የለም እንዴ
የያኔው ባለቀን :ለምዶበት ማቀንቀን
በቀኝ እጄ ሳቅፍህ _
መንገድህ ይቀናል እያለ ሲያሞቀኝ:
ውሎ ሳያድር ነው በቀኝ ሽብር መላ በወጠምሻ ክንዱ ጎኔን ያደቀቀኝ:
ይሄኛውስ ቢሆን በእሱ የተተካው
ላክምልህ በሚል ከንቱ ፖለቲካው
ለስንቴ መሰለሽ_
እየተደበቀ ቁስሌን የሚነካው
ታዲያ በዚህ ዘመን_
እነዚህን ሁሉ የቀኝ አቀንቃኞች ከልቡ እያመነ
በተናገሩት ቃል እየተማመነ
ከቤቱ የወጣ ቀኝ አውለኝ እያለ
ከአውላላ ሜዳ ላይ ቀረ እንደዋለለ::
እናልሽ ፍቅሬ ሆይ ይሄ ተሞክሮ
ልቤ ውስጥ ተቁዋጥሮ
እንኩዋንስ በቀኝ እጅ ልቀፍህ ተብዬ
"ቀ" የሚባል ፊደል ሲያልፍ በጆሮዬ
ቀማኛ
ቀበኛ
ቀጣፊ
ቀሳፊ...
የሚል የ"ቀ" ውላጅ
የክፉ አሳብ ጉማጅ
ባሳቤ እየመጣ
ጤናና ሰላሜን ባንዴ ነው የማጣ::
ስለዚህ ህይወቴ ከገባሽ ጭንቀቴ
በግራሽ እቀፊኝ አድምጭኝ በሞቴ
በግራ ጡትሽ ስር ካለው ትንሽ ኮዳ
ልብ የሚሉት ጉዋዳ:
እኔ ጠጋ ስልሽ ነፍሴ ከነፍስሽ ጋር
ሽርክና መፍጠርዋን በድንገት ሲረዳ:
ምን ያህል ጋሎን ደም ባንዴ እንደሚቀዳ:
የፍቅሬ ማእበል የልብሽን ባህር ስንቴ እንደሚንጠው:
ሽጉጥ ልበልና በደንብ ላዳምጠው:
ከግራ አጥንቶችሽ እስኪ ልበል ልክክ
ለመቁጠር እንድችል የትርታሽን ልክ!!
ትር… ትር… ትር ……………

@getem
@getem
@beppa_19
👍1
" ብልጡ ፍቅርሽ ሲያጃጅለኝ የጫርኩት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
**************************
የውበት ዳርቻ
የአድማሷን መባቻ።
አንቺን የእኔን ጠሀይ
የተድላዬን ሰማይ።
ልስልሽ ፈለጌ
ምስልሽን አጣሁት
ከምስሌ አድርጌ።
ከስብዕናሽ ጠለል ከሀሳብሽ ከፍታ
አየሁኝ በሳቅሽ ጨረቃ ተከፍታ።
ጨረቃ ጨረቃ
ጨረቃ ጨረቃ
ያቺ ድንቡል ቦቃ
አንቺ ስትቦዢ ይሆን ምትነቃ?
አንቺ እንደሁ አትቦዢ
ከቶ አደበዝዢ
በመውደድሽ ሸጠሽ ታደርጊያለሽ ገዢ።
ያውም በሠላሳ
ያውም በሠላሳ
ክደሸ ስታበቂኝ ምንም እማልመስልሽ
በገደልሽኝ ቁጥር ሳትሞች ምሞትልሽ
በገፋሽኝ ቁጥር ሳትወድቂ ማነሳሽ
በሸጥሽኝ መጠን ልክ ለመክሰር ምገዛሽ
ይሁዳ ነሽ አንቺ እኔ ደግሞ ጌታሽ።
.
.
.
ተጻፈ:-፳፩/፱/፳፻፲፩ ዓ.ም
@getem
@getem
@poem_with_mela
የመከራ ስላቅ
©ሲራክ
እንባዬን በስላቅ ገንቡና ከትሩት
ወይ መብራት ስሩበት ሲሻችሁ ዋኙበት
በደም እዤ ምራቅ....
ሳቅ ደስታችሁ ይድመቅ..
ደሜ ዥረት ሆኖ ታጠቡት ገላችሁን
አጥንቴን አውጡና ስሩት አጥራችሁን
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን.....
በህልማችሁ ይሁን
-------------//-------------
ሲራክ @siraaq
_____°°°°°____
@getem
@getem
@getem
@getem
የውልሽ አለሜ
በህይወት ሰንሰለት፣
ከእለታት በአንድ ቀን
ከድኩም ልቤ ጋር ፣
ከደጅ ተቀምጠን
ጨረቃን እያየን፣
ኮኮብ ስንቆጥር
ከሰማይ ሰሌዳ
የተሳለን ውበት ፣
ድምቀት ስንቀምር
ተገልፃልን ነበር ፣
አንድ ግሩም ታምር
ታምሩ እንዲህ ነበር፣
የወረደው ሚስጥር
ከአፈቃሪ ልቤ ጋር፣
ኩኩብ ስንቀጥር
ደምቃ በወጣችው፣
በጠፏ ጨረቀ፣ ውበት ተደንቄ
ከገሀዱ አለም ፣
በምናቡ ሀሳብ ፣ ወዲያ ተደብቄ
በአንቺ ርሀብ ፉርጎ
በትዝታ ሀዲድ ፣በመናፈቅ ባቡር ፣
ከህላዌው ደጀፍ
ከሰማየ ሰማይ ፣ ከልዕሉ መንበር
ከደመናው በላይ ፣
ከመናፍስቱ ዘንድ ፣ወዲይ ሂጄ ነበር
በአማልክቱ ዓለም
በሰማያት ጉዞ ፣በደመናው ፈረስ
………ታድያ እዛ ስደርስ
ከአርያም እልፍኝ
.
.
.
.
.
.

















.
በቅርቡ ይጠብቁ በማለዳ ስንኝ የግጥም መድብል

Join and share..........👇👇
@getem
@getem
@getem
@getem
ቴዲ /የጠረፍ

እነሱ /ይላሉ/:- ቃል አዉጣ ....ቃል አዉጣ
.....እኔ ያንቺ ድንጉጥ ከየት ብዬ ላምጣ
እነሱ/ይላሉ/ :- ተናገር ስለ እምነት
እኔ ያንቺ አገልጋይ ቡዙ ሰዉ አያለዉ.
ሳስስ ያንቺን አይነት
እነሱ /ይላሉ/:- አስተምር በመንፈስ
እኔ ተለጉሜ አንቺን አስባለዉ
ካለሁበት ስርቅ ከቆኩምኩበት ስፈርስ
.........
እንዲዉ ሳይገናኝ የአማኙ መንጋ
እነሱ ለጮሁት ዝም ያልኩት ሰዉዬ ልሳኔ ተዘጋ.....
/በጌታ ስም/

🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂

....... ብቻ.........
ያየዉሽን ያህል
ያሰብኩሽን ያህል ልነካሽ ወደ ላይ በተሳብኩኝ ቁጥር
እንጃባቱ ሰይጣን ይወድቃል እግሬ ስር
/ወጋዉት/

........ብቻ .....
የናፍቆቴን ያህል
የፍቅርሽን ያህል እያየዉሽ ስስቅ
የፃድቃን አይነቶች አዳራሹን ጥቅጥቅ
/ አንድ ሰዉ ጮሆ አሜን ይበል እስኪ /
.......................
እዚህ
ከልቤ ክፋይ ዉስጥ ጌታ እንቺን ፅፎ
ድዊ እጥል ጀመር ነገሬ ሁሉ ላይ አይንሽ ተለጥፎ
.......
የአይንሽ አኳኃን .... አነሳስ አጣጣል
እመኚዉ ፀጋ ነዉ ታሪክ ይለዉጣል
እርኩስ መናፍስትን ይገለባብጣል



በእየሱስ ስም

@a0Teddy ቴዲ/ የጠረፍ

@getem
@getem
@getem
በስንኝ ቋጠሮ ትንሿ ስራዬ፡
ለስናን ወጣቶች ትድረስ ደብዳቤዬ።
ዝናሸ ተነገረ መሠረትሽ ጸና በጮቄ ተራራ፡
አባዛዥ ጊወርጊስ የትዉልዴ ስፍራ፡፡
ህሊናውን ገዝቶ ለተመለከተዉ የአባጅሜን ጫካ፡
አስታው ኮሸሽሌው ጅባራው ሲፈካ
ዝንጀሮው ቀበሮው በውስጡ ሲያስካካ፡
በአእዋፍ ዝማሬ መንፈሱ ሲረካ፡
ይመስላል የወጡ ለበአለ ፋሲካ።
ቀበሮው ዝንጀሮው
ጅቡና አሳማው
ነብሩና ሚዳቆው
ሁሉም በየመንጋው
አስከ ልጅ ልጃቸው
ቁሩንና ዋዕዩን በህብረት ተላምደው
ረሀቡን ታግሰው
ምድራቸውን ምሰው
አደን ወጥተው ወርደው
ይኖራሉ ውስጥሽ አንቺን ጥግ አድርገው
በአንቺ ተጠልለው ።
ይች የስናን ቆንጆ የጮቄ ተራራ
በአገር በቀል ዛፎች በአስታ በጅባራ
በአምጃ በኮሶ ብትሞሸር አምራ
ያበራ ጀመረ ውበቷ እንደ ጮራ።
የጮቄ ተራራ አምላክ የመረጠሽ
አዕዋፍ አራዊት በነገድ በጎሣ የተጠለሉብሽ
ህሙማን ልጆችሽ
ከብዙ ደዌያት የተፈወሱብሽ
መፍትሔ በሖነው ቅዱሱ ፀበልሽ
ቅዱሳን ሰዎቹ የሚፀልዩልሽ
የውኀ ምንጮችን ከቦታሽ አፍልቀሽ
ከጮቄ እስከ ካይሮ ውኀሽን ገብረሽ
የፍጡራኑ አምላክ በጥበብ ያጸናሽ
የስንቱን ውኀ ፅምዕ በምንጭሽ አረካሽ።
አንቺ የጅሜ ቆንጆ
ጥናቱን አርቅቆ አዋጁን አውጆ
መጣ ወደ ቦታሸ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከወንዝሽ
ሊሠራ የጥናቱን ጎጆ።
ከጮቄ ተራራ ጎዴብ ሙጋ ተምዝግ አኩርፈው
ቢወርዱ
እምቁ ሀብትሽን ከፊት እየነዱ
ጣና በለስ ጊቤን ተሳልመው ሲወረዱ
በኩራት በንቃት እየተራመዱ
አባይ በአጠመደው የውህደት ወጥመድ ገብተው
ተማገዱ።
ከርሰ ቀላያትን በደለል አጥግበው
ግርማ ሞገሰ ሆነው
ዳር ድንበሩን ቃኝተው
አቧራና ትቢያን ከእግራቸው አራግፈው
የልምላሜን ካባ ደርበው ደራርበው
ምድረ ኢትዮጵያን ዙረው ተዟዙረው
ከላይ ከአርያም ደመናውን ጠቅሰው
ዝናም ተቀብለው
ከልምላሜ ፅዋ ሕዝቡን አጠጥተው
ሁሌም ይኖራሉ ለዘለአለም ነግሠው።
አንት ወጣቱ ትውልድ ባህልህን ጠብቅ
ውጭ ውጩን አትናፍቅ
ቅድሚያ ማንነትህን እራስህን እወቅ
ወዳጅ ዘመድህን ሀገርህን እወቅ
ከዐቢይ እስከ ደቂቅ
ፍፁም አንተነትህን ከውስጥህ አታርቅ
ከሽሙጥ ከንፈር ከሀሰትም እራቅ
ሀሠትንም ጥላት ከእውነት ጋርም ታረቅ
ለሰማዩ ቤትህ ሰንቅህንም ሰንቅ
የፀሎት ሰንሰለት ወገብህ ላይ ታጠቅ
በትንሣኤ ጊዜ ትሳለማት ዘንዳ የጌታን
አምደወርቅ።
የሐሠት አለቆች የሐሠት ሠራዊት
አውነትን ገነዙት
ይዘው በሰንሰለት
እንደ በግ አረዱት
አንገቱን ቆረጡት
በሾተልም ወጉት
ፍላፃም ላኩበት
ለሁለት ከፈሉት
በስለት በለቱት
አንጀቱንም ሳቡት
እንደ ማግ ጎተቱት
በጋለ ብረት ላይ እንደ ሰንዴ ቆሉት
በእሳት አበሰሉት
አድርቀውም ፈጩት
በነፋስ አዘሩት
ከገፀ ምድር ላይ እውነትን ለማጥፍት።
የግፍ ፅዋዕ ሞላች
ልታፈስ ደረሰች
ነፃነቷን ሻተች
የሙት ልጇን ጠራች
ሲቃ ባነቀው ድምፅ ልጄ ልጄ እያለች
ደም የቀላቀለ እንባን እያነባች
እውነት እውነት ብላ የሙት ልጇን ጠራች።

ጸሀፊ እና ገጣሚ፦ አብርሃም ታደገ ሽፈራው፤
አንድነታችን ሀይላችን ነው!
አስተያይት ጎባጣን ያቀናል እና በራችሁን ክፈቱ፤፤፤

@getem
@getem
@beppa_19
#ያንቺው_ደቂቅ
:
:
ከቅዱስ ተራራ እንደመነጨ ኩልል ብሎ እንደጠራ
እንደ ጎበዝ ገበሬ ዘር እልፍ አላፍ የሚያፈራ
ልክ እንደ ፀደይ ሰማይ
ወለል ብሎ እንደሚታይ
ልዩ ስሜት እንከን የለሽ ያደባባይ ጥዑም ሚስጥር
ጨቅላ እፃናት የሚረዱት እሷ ለኔ አላት ፍቅር።
:
:
ጨቅላ እፃናት ሚገባቸው ሰሙም ወርቁም ማያሻማ
ለልብ ሀሴት መጠንሰሻ ሳትናገር የሚሰማ
ሁሉ ፈጥኖ የሚረዳው ግልፅ ስሜት ቀላል ቅኔ
ላዋቂው ሰው ላስተዋዩ ተሰወረ ምነው ከኔ።
:
:
የፍቅርን ታንኳ ቀዝፋ ከኔ ዘንዳ ስትመጣ
እንደ እፃን ስትቦርቅ በደስታ ጮቤ ረግጣ
ምትይዝ ምትለቀው ጠፍቷት ጥርሷ ሳይከደን አምሽቶ
ከርታታ ዓይኗ ሲስለመለም በእንቅልፍ አጀብ ተረቶ
ደረት ክንዴን ተንተርሳ ሰላም እንቅልፍ ተኝታለች
ከ አንዴም አንድ ሺህ ግዜ ፍቅሬ አንተነህ ብላኛለች።
:
:
ያ ፍም ስሜት ነበልባሉ ባይኗ ዘልቆ የሚያወራው
ቀልብ የሚስብ እጅግ ደማቅ እንደ ሩቢ የሚያበራው
ዋጋ ተመን የማይሰፍረው የከበረው ከቀይ እንቁ
የቀለም ቀንድ ከሆንኩት ሰው ምነው ከኔ መደበቁ።
:
:
ለኔ ያላት ጥልቅ ፍቅር ልብ ዘልቆ የሚያረካ
ንዋይ ከቶ የማይገዛው ባለም ሚዛን የማይለካ
መሰረቱ ወለል ጣራው የታነፀ በፅኑ ቃል
እንደሆነ እንኳን ሊቁ ደቂቁም ሰው በደንብ ያውቃል።
:
:
ሸክላ ፈራሽ ገላን ቀርቶ ነብሷን ለኔ አትሰስትም
እኔ ካለው አጠገቧ ግራዋውም አይመራትም
መታያዋም መደበቂያ እኔ እንደሆንኩ ህዝብ ያወራል
ልቤ ብቻ ከእውነታው ላይተያይ ተሰውሯል።
:
:
ቀን ከሌሊት ቢያዳምጡት በማይጠገብ አንደበቷ
እማሬውም ፍካሬውም አቻ ፍቺ የቃላቷ
እኔ ብቻ ሆኜ ሳለው የሷ ድርሰት ነፀብራቁ
ታዲያ ምነው ከእውነታው ልባም ልቤ መራራቁ።
:
:
የጭንቀቷ ማራገፊያ ወደቧ ነው ዓይኔን መሳም
አንገቴ ስር ስትወሸቅ ይሰማታል ልዩ ሰላም።
ዘቢብ ስሜት የማይነጥፍ ቀን ሲገፋ ውሎ ሲያድር
ደርሶ ሚስጥር ሆኖብኛል የሚታየው ገሀድ ፍቅር።
:
:
ሌላን ነገር ለመረዳት ቅፅበት እንኳን ማይወስድብኝ
ግልፁ ፍቅሯ ለምን ይሆን እንዲ ስውር የሆነበኝ።
ልጅ አዋቂው የተረዳው ያደባባይ ግልብ ነገር
ባለ ማዕረግ የሆንኩት ሰው እንዴት እኔ ልደናገር?
እያልኩ ሁሌ ደጋግሜ እኔው እኔን ጠይቄያለው
ቀለም ቁጥር አመክንዮ አይገልፃትም አውቄያለው።
:
:
ለካ ፍቅርን ለመረዳት ሊቅ ደቂቅን አያካትም
ስሜት ስሌት የሆነበት መቼም ቢሆን አያውቃትም።
ለኔ ካለት ፍቅር ጋራም የገባኝን ሳነፃፅር
የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ኢምንት ነው የሚያሳፍር።
እናም ለምን እንዳልገባኝ ደጋግሜ ሳውጠነጥን
ስሌት እንጂ ስሜት የለኝ የሷን ፍቅር የሚመጥን።
ጠቢቧ ሴት አስተዋዩዋ ረቂቋ የኔ አፍቃሪ
ለሌላ ሰው የቀለም ቀንድ ላንቺ ደቂቅ ነኝ ተማሪ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu

@getem
@getem
@getem
👍1
ሥዕሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ #አሥለው ሥጥታ ያበርክቱ
🎂ለ ልደት🎂
❤️ለፍቅረኛ❤️
👨‍⚖ለሰርግ 👰
🧑‍🎓ለምርቃት👨‍🎓
በ +251934039346
ወይም @cher46 ማዘዝ ይቻላል ።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህን እድል ይጠቀሙበት!
#ሥዕል_ብቻ

@seiloch
@seiloch
👍1