ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የምናቧ ፍቅሬ
ማንን ልሁን ካልሺኝ
መሆን ከቻልሺልኝ ምናቤን ሁኚልኝ
በብዕሬ የፃፍኳት ድርሰቴ  ላይ የማቃት አንድ ሴቲት አለች
በምናቤ ያለች
በምናቤ የኖረች
ግን
ይሄን ምፅፍልሽ
አንቺም
ከአለም የሌለሽ የምናቤ አለም ሰው
አንቺም ህይወት አልባ ረቂቅ ፍቅሬነሽ
       
                         ተፃፈ በብላቴናው ብዕር
@getem
@getem
@getem
#አዎ ~ባላ'ገር~ነህ!!!

የደመናን እንባ
የናፈቁ አይኖችህ
ሽቅብ ወደ ሰማይ ዘውትር ሲዋትቱ
ከደረቀ መሬት
ትግል የገጠሙ
ሻካራ እጆችህ ሞፈር ሲጎትቱ
ከበሬ ተጣምደህ
አፈር ስትገፋ ቀንበር ስትሸከም
ያኔ ነው የገባኝ
የህይወትህ ምሬት ለኔ ያንተ መድከም፡፡

ግና ከተሜው ሰው
የባላገር ትርጉም ያልገባው ምፃጉ
ለስም አልባ ስሙ
መሆንህን እረስቶ ክብርና ማረጉ
አርሰህ ባጎረስከው
ውለታቢስ ሆዱ ለባእዳን ሰግዶ
ባላገር ይልሀል
በመዘመን ብሂል እርሱ ሀገሩን ክዶ፡፡

አዎ ባላ'ገር ነህ
ሀገር ስላለህ ነው ባላ'ገር ምትባል
እውነትም ይሄ ስም
ከማንም በላቀ ለክብርህ ይገባል፡፡

ስለዚህ ለነሱ
ለከተሜው ጭሶች ባላገር ለናቁ
ሀገር እያላቸው
ሀገር አልባ ሆነው ሀገር ለናፈቁ
ባላ'ገር ነህና
ይበሉህ ባላገር ሀገርን እስኪያውቁ፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

((ሸጋ ሐሙስ))

@getem
@getem
@beppa_19
👍1
የሠቆቃ ጊዜ የሠቆቃ ዘመን፣
ዘንቦ ማያባራ ቢጸለይ ቢለመን።
ሠሚ ያጣ ጬኸት፣
እንቅልፍ አልባ ሌሊት፣
ኗሪ አልባ ወና ቤት፣
ጸደይ የለሽ ክረምት፣
ትንሣኤ አልባ ሥቅለት፣



አምላክ ዛሬ ይብቃን፤ በዝቷል ሠቆቃችን፣
ሥንሥም መነከሥ፤ ወርቅ ሥንሠፍር ጠጠር ሆኗል ምላሻችን።
#fb

@getem
@getem
@getem
ልበ ዱሪቆን
-------#በሲራክ----------

አለሜ......
በአፍላነት እድሜ ገና በልጅነት
የደወርነው ፍቅር ደርሰው ያልፈተሉት
የትዝታ መንጋ ልባችን ያዘለው
ማደግ ያልዘነጋው
አርያም ባይሰማው ይህን አይነት ፍቅር
ህቡዕ ነው ልንገርሽ የኔና አንቺስ ነገር
እዚህ ከኛ ልብ ውስጥ ንዴት አሸልቧል
ያልወለድነው ፍቅር ልባችን አርግዟል
የኔም የአንቺ አንደበት ዝምታውን መርጧል
ይሁን ይሁን ልቀበለው
ያ ልባችን አማን አለው
.
ትዝ ይልሻል
በማሪያም ዕለት ከንግስ መልስ
ከሜዳው ላይ ከአፀዱ ስር ምሽት ሳይደርስ
ተቀምጠን ተጠጋግተን በፍንደቃ ስናወጋ
ተሰምቶኛል አንዳች እውነት ከሙቀትሽ የላብ ቀጋ
.
ያ ልብሽ ደጋ ነው በማፍቀር የናኘ
የኔ ልብ ቆላ ነው አንቺን የተመኘ
ምክኒያቱ ይህ ነው የልበ ዱሪቆን
ልባችን ተማምኖ አንደበት ቢከዳን
በቃ ተፈጥረን ነው እሳት ውሃ ሆነን
.
ደግሞ ጊዜው ቢተም
ምሽት ደርሶ ቢጨላልም
ከውብ አይንሽ ቅሬታሽን አነባለው
ክንድሽ ሲያቅፈኝ ጭንቀትሽን እረዳለው
.
በሌላ ቀን ተነፋፍቀን ስንገናኝ
ትንፋሽሽ ነው ማፍቀርሽን የሚያወጋኝ
እርግብ ሆነሽ እኔ ቁራ
ተራርቀን ባንድ ጣራ
እሳት ስሆን አንቺ ውሃ
ያልታደልኩሽ የኔ አምሃ
.
ዱሪቆን ነው በቃ እንቅር
እኔና አንቺ አንናገር
በሀሳብ መንገድ እንሳፈር
በልባችን እንፋቀር
አርግዚኝ በተስፋ ልብሽ ከኔ አይሽሽ
ልታገስሽ እኔም በተስፋ ላርግዝሽ
.
በማሪያም ዕለት ከንግስ መልስ
ከሜዳው ላይ ከአፀዱ ስር ምሽት ሳይደርስ
ተቀምጠን ተጠጋግተን በፍንደቃ ስናወጋ
ተሰምቶኛል አንዳች እውነት ከሙቀትሽ የላብ ቀጋ
-------------//---------------
ሲራክ @siraaq
#
@getem
@getem
@getem
👍1
"ካለፈ በኋላ.."
""""""""""""
((ዮሐንስ ፍቃዴ))
ፀጉር ቆራጮቹ
ፀጉሩን እየተቹ
'ምነው እቴ ፀጉሩን...'
ብለው እያወሩ፤ ሊያሙት ተመቻቹ
የልብስ ነጋዴ...
'ልብሱን ባ'መት እንኳ አይቀይርም እንዴ?'
ብለው በአንድነት፤ ተንጫጩበት አንዴ
ደሞ የገነባው፤ ጫማ አምራች ፋብሪካ
'ምናይነት ነፈዝ ነው ብራንድ የማይለካ
እግሩን ካዲስ ጫማ የማያነካካ
ከዘመኑ ጋራ የማይለካካ
ም'ናይነት አፈር ነው እግሩ አፈር የነካ'
ብሎ ይዘልፈዋል...
ጫማውን ለመሸጥ እግሩን ይሰድበዋል
"""""""""""""""""""
ክብር የማይገባው ፍቅር የማይገባው
እውነት ባየ ቁጥር የሚንገበገበው..
'እዩት ይሄ ከንቱ..
ተሸክሞ ሲዞር ባንዲራ ባንገቱ
እዩት ማስጠላቱ ...
ክንዱ ላይ ያሰረው የሸማ ጥለቱ'
ብሎ ያሳጣዋል፤ ክብር ያልገባው ጅል
አማረብኝ ብሎ፤ የሚያምረውን ሊጥል
'እሱም ብሎ ደሞ፤ ጀግና ባለ ቅኔ
ደሞ እሱን ብሎ ሊቅ፤ አረ ለሱስ መጥኔ..
ዝም ብየ ባወራ... አልበልጠውም እኔ?'
ይሉታል አንዳንዶች
ከባድ የሚያቀሉ የቀለሉ ሰዎች
""""""""""""""""""
'እዩት ያን ከርፋፋ..
ቅኔ ነው እያለ ቅሌቱን ሲተፋ
እዩት ይሄን ክርፍፍ..
ህይወቱን እንደ ጅል፤ ቅኔ ብሎ ሊዘርፍ
ያውና ያ አስመሳይ...
ደሞ እንደገጣሚ ይዞ ተመሳሳይ
እዩት ይጃጃላል
ሲሉ የሰማውን ቅኔ በሉት ይላል
የሰው ነገር ሰምቶ ሊቀኝ ይከጅላል'
እያሉ ይሉታል..
ይሉታል.. ይሉታል...
ገ'ለው ያድኑታል.. ሰቅለው ያወርዱታል
"""""""""""""""""""
እሱ ግን..
የሚሉትን ሁሉ ሰምቶ እያሳለፈ
እሱ እየረገፈ ቅኔ እየዘረፈ
በመንገዱ አለፈ..
'ብቻ ግን የሱ ልብ፤ አለው መቀነቻ
ቅኔ እየዘረፉ፤ ቅኔ መሆን ብቻ!'
እሱ ግን አለፈ..
እንደተቆለፈ!
""""""""""""""""
ካለፈ በኋላ፤ ሁሉም ገረማቸው
የሄደበት መንገድ፤ ሰው መሰለባቸው
ካለፈ በኋላ፤ ሁሉም ጨነቃቸው
የዘረፈው ቅኔ፤ ሰው ሆኖ ታያቸው
ካለፈ በኋላ፤ ሁሉም ተገረሙ
ወደ ተነሳበት፤ ሄዱ እያዘገሙ
ካረፈ በኋላ፤ ሁሉም ተናደዱ
ላያገኙት ነገር፤ ሊፈልጉት ሄዱ
=+++-+++-+++=

@getem
@getem
@getem
ቄሳር አፈረሰ !!!!!


የቄሳር ለቄሳር ፤
የእግዚሃርን ለእግዜር ፤
ነበር ኪዳናችን ፤
ቄሳር አፈረሰ ፤
ይኸው ቃሉን በላ ፤
ልቀድስ እያለ ገባ መቅደሳችን ፤
ካህን ባገር ጠፍቶ ፤
ፍቱን ፍቱን ማለት ሆኗል ጸሎታችን ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ጁምኣ!💚

@Nagayta
@getem
@getem
#አያስታውቅም_ወይ

በከረረ ጥፊ ፥ ጆሮዬ ሲናጋ
በቡጢና ጡጫ ፥ ገላዬ ሲለጋ
በበላዬ ሰፍረሽ ፥ ልክ እንደ ግመሬ
መላወሻ ባጣ ፥ መሬት ተዘርሬ
#ኡ.... #ኡ.....ብዬ ጮኬ
ጎረቤት አውኬ
በሰለለ ድምፄ የተደናገጡ
#ተግተልትለው መጡ
ከወረደው መአት ፥ ከጭን ሰው ሊያወጡ
ከመቅፅበት ግና ፥ ቤታችን ሲደርሱ
ገላዬን አሳፍሮ ፥ገላሽ መገንደሱ
ከበላይሽ ሆኜ ፥ ቢማትሩ ግዜ
#በእግዜር ተዋት አሉኝ
#ማሪው እንደማለት
ተራዱኝ ያልኳቸው ፥ ቦታዬን በማየት
ዳሩ...ምን ያድርጉ
ባይገባቸው እንጂ ፥ ቦታዬና ቦታሽ
ያስታውቅ ነበር ፥ አንቺ እንዳልተመታሽ ።

#ተበላው ( 😔😔😔 )

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!

መገን ተርቲበኛ!!!!!


አገር ሲዞር ውሎ፤
አህሪቡ የሚለው ፤ ተቀባይ ስላጣ፤
አንበጣ እንኳን በአቅሙ፤
ወሎ ድረስ ዘልቆ፤
ቡና አጠጡኝ ብሎ፤ ይኸው ዛሬ መጣ።
ቡና አጠጡኝ ብሎ፤ ከመጣ ደጃችን፤
አህሪቡ ነው እንጅ፤ ወትሮም ልማዳችን፥
እንኳን ወዳጅና፤
ጠላት ይማርካል ፤ የተርቲብ ቡናችን።

(( ጃ ኖ))💚💛❤️

ሸጋ ቅዳሜ!

@getem
@getem
@Nagayta
#የስሌት #ጋብቻ
#አንቺ
ሽማግሌ አዘጋጅ ብለሽ ተናግረሻል
ምን አለው ይሉኛል ብለሽ ተጨንቀሻል
#እኔ
ከቀየው መርጬ
በቂ ሽማግሌ አዘጋጅቻለሁ
የሌለኝ ነገር
ለራሴ አለኝ ብዬ በቃል ሸምድጃለሁ
#እነሱ
ቤተዘመድ መጥቶ
ምን አለው ለማለት ማልዶ ይሰለፋል
ሽማግሌ ከቦ
ምን አለው ለሚባል
የወላጅ ጥያቄ የሐሰት መልስ ይፅፋል
#ውዴ #አትጨነቂ
ያንቺ ብቻ አይደለም የሀገር ነው ችግሩ
እኛም ቤት ብትመጪ ይሔው ነው ነገሩ
#አምና
የታናሽ እህቴ
የልጅነት ፍቅሯ አመት በአል አስታኮ
በፍቅር መርቀን
ፈቅደን እንድንሰጠው ሽማግሌ ልኮ
#መልስ #ሲጠባበቅ
በዚህ ወገን ሆኜ እኔም ጠይቄያለሁ
ማይደርስብኝ መስሎኝ ምን አለው ብያለሁ
በሴት ወገን ስንሆን የወንዱን ባናውቅም
ምን አለው ተብሎ ሰው አይጠየቅም
ሀቅ ተዟዙሮ
ቦታ ተቀያይሮ
የትናንት ተቀባይ ከነገ ወዲያ ይልካል
በሴቷ ጠይቆ በወንድ ይጠየቃል
ሸፋፍነነው እንጂ
ደፍረን ከጠራነው ነገሩ ያሳስባል
በንግድ አጠያየቅ
ምን አለው አይደለም ስንት አለው ነው ሚባል
ባንክ ቤት ስንት አለው በጥሬው ያኖረው
ስንት መኪና አለው የሚያሽከረክረው
ስንት ካሬ መሬት ካርታ የወጣለት
ስንት ክፍል ቪላ የተንጣለለለት
በልጅ የደም ቀለም የሌለንን ስንስል
ልጅ የምንድር ሳይሆን ገዢ ነው ምንመስል
የመመኘት ቀመር
የማዟዟር ብዜት በዘመን ሲጣፋ
ምን አለው ነው እንጂ
ከዬት አመጣው የሚል ሽማግሌ ጠፋ
#እኔ #ምለው ?
የማካፈል ስሌት ዞሮ የመጣ ‘ለት
ምን ያህል ይዘናል ምን አለው ለማለት
#ይልቅ
እግዚአብሔር አድሎት
በጥላቻ ዘመን የሰው ልጅ ሲፋቀር
አፍቃሪ ልብና
ሁሉም ነገር አለው ከሀብት በስተቀር
ሀቁን እያወቅነው ውጠን ከማባበል
ምን አለውን ትተን ምን የለውም እንበል
=====||=====
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@beppa_19
1
#የሐገር #ፍቅር #ስሜት
አረንጓዴ ቢጫ
ቀይ ቀለም ካየ ብእሩን ያነሳል
ገጣሚ አይናፋር ነው
አንገት ይደፋና ስንኝ ይቀልሳል
* * *
ካድሬ ግን ደፋር ነው
ካድሬ ፈጣጣ ነው መች አይቶ ይለቃል
በሰው ሀገር ገብቶ ኮኮብ ይጠይቃል
ከሙሉቀን ሰ•

\💚መልካም💛 ቀን❤️\

@getem
@getem
@beppa_19
( ነቃበል)
ጀምበሯ ሳትጠልቅ ፣ የወደቀን አንሳ፤
ህልምህ እንዲሰምር ፣ መስጠትን አትርሳ፤
አላካፍል ብለህ ፣ ብቻህን አትብላ፤
ገሀነምንሽተህ ፣ ፅድቅህን አትጥላ፤
ቤዚቾ

@getem
@getem
🙏 50 % @ ( ) 🙏


ነገር ለማመስጠር ፤ ማንም ቢጣጣርም
በተቀደደው ልክ ፤ መበርገዱ አይቀርም

@getem
@getem
@getem

አምደማሪያም ጠይብ (ፊዳው)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
(በjo)

በፀጥታ ላይ ትዝታ
በትዝታ ላይ መኝታ...
በነበር ላይ እንሆናለን
በባዶ ሜዳ እንከብራለን።

አይ እኛ........

ፀጥ ብሎ መኝታ
ከዛም ተስፋ ማድረግ፤
እረብሻን ቀስቅሶ
በአንዱ እንባ ላይ ማደግ፤
ነበር እንጂ ያለን
መች ደረሰ ላሁን፤
ቀደምት ታሪካችን
መች ጠቀመን አሁን፤

አዎን መች ጠፍቶናል.........

ደግሞም ተስፋ ማድረግ
አልጋ ላይ ተኝቶ፤
የህልም እንጀራን ማኘክ።

ግና ከዚህ ሁሉ......

ነበር ሳይሆን ለሁን፣
ግዜው ክፉ ሳይሆን፣
ፀሀይቱም ሳትጠልቅ፣
ጨረቃም ሳትለቅ........
በድቅድቅ ጨለማ
እንደሚበራ ኮከብ
አሁን ነው መፈንጠቅ.......




ተፃፈ በ @Mak_bale
29.5.2012

@getem
@getem
@getem
👍1
ደጋሽ ነጋሽ
በምድር እንፋሎት ዶሮ ወጥ አበሰልኩ
በጨረቃዋ ፍም ድፎ ዳቦ ጋገርኩ
መአልቱ ሲነጋ የህልሜን ቀን ደገስኩ
✧✧✧✧✧✧✧✧
ሲራክ @siraaq

@getem
@getem
@getem
@getem
ፈላጊው ሲፈለግ
©ሲራክ
እንባዬን አድርቆ ውስጤን ያቆሰለ
እልፍ አመት ያኖረኝ ያ ፍቅርሽ የታለ?

ሲራክ @siraaq
#
@getem
@getem
@getem
@getem
#ሹ ክ ሹ ክ ታ
እንቺ
የኔ ኮልታፋ
በለሌሊቱ ሰማይ
ከፀጥታው በላይ
በመሸው አለም ላይ
የኛ ሹክሹክታ ነው ሚሰማው ባለም ላይ
በጣፋጭ አንደበት
በኮልታፋው አፍሽ ስትንሾካሾኪ
#አፈቅልሀለሁ ብለሽ ፍቅርሽን ስትሰብኪ
ሌሊቴን በኮልታፋው አፍሽ ከቶ ስታፈኪ
      ሰይጣን ተላካፊው ከቶ ግርም ሲለው
      ደግሞ በዚ ምሽት ደሞ የምን ፍቅር ነው
      ጥያቄ ሲያበዛ መግቢያ መውጫው
        ሰይጣንስ ቢጠፋው
      ሚለክፈውን ጉብል አንቺ ስታስቆሚው
      #አፈቅልሀለሁ ስትይኝ
      ከቶ ሚቃጠለው
ከፀበል ቀጥሎ የኔ ኮልተረፋ ናት ለሰይጣን መፍትሄው
    አቦ ተኮላተፊልኝ
አፍሽ ሲኮላተፍ
የኔ ልብ ይመታል
ቃል ስታጣምሚ
ሀሴቴ ይመጣል
ወልከፍ ስትይልኝ
ጥርሴ ይፈለቀለቃል
የማላቀው ስሜት እንዲህ ሹክ በላት ይለኛል
ፍቅሌ
አቅልሻለሁ ሁሌ
ተኮላተፍኩ እንዴ
አወየው እድሌ
አንደበትሽ
ከኔ ስለሆነ ነው
አሁንማ
ትናጋሽ የኔም ነው

                             ተፃፈ በብላቴናው ብዕር

@getem
@getem
@getem
@getem
አንፃር
ፍቅር የዘላለም ደቂቃ
መሰልቸት የደቂቃ ዘላለም
አኗኗሩ እንጂ
ጊዜ ሩቅ አይደለም
ህይወት አላጠረም።
####////////////####
#የምድር ዘላለም
ዲበኩሉ ጌታ
@getem
@getem
@getem
@siraaq
ላንቺ ስል...
(በላይ በቀለ ወያ)


<<እንጀራ እወዳለሁ >> ፥ ስትዪኝ ሰምቼ
አንቺን ደስ እንዲልሽ ፥ አብሲቱን ጠጥቼ
ሞቼልሽ ነበረ ፥ ኩፍታ አብዝቼ😂
ደግሞ እንደገና…
<<ማፍቀር መታደል ነው>> ፥ ስትይ ሰማሁና
አንቺን እረስቼ ፤ ሌላ አፈቀርኩልሽ
ምን ማልሆነው አለ ፥ አንቺን ደስ እንዲልሽ?!😂
።።።
@getem
@getem
#jeko
1
ኤዶማዊ ውበት
©ሲራክ
ኤዶማዊት ውበት ፍኖተ ገሞራ
እንዲህም አላየው ውበት ከዚያ ጎራ
ከእሱዋ ኒቄጥራ .....
በአውደ ሲመቱ መርቆ ቢፈጥራት
ከስምም ስም መርጦ ኢትዮጵያዊት አላት
______°°°________°°°________
ስጦታነቷ ለኔዋ ለኤዶሜ ትሁንልኝ
ሲራክ @siraaq
----
@getem
@getem
@getem
👍1
አጥብቆ ተመልካች
/በዕውቀቱ ስዩም/
*--------------*
አይሽ አይሽና
አበባ ከንፈሯ
አበባ ከንፈሯ
ከንፈሯ እንዴት ያምራል!
እንኳን የኔን ገላ ንቦችን ይጠራል
እያልኩ አስባልሁ
ከንፈርሽን አያለሁ።
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አበባ ከንፈሯ
አበባ ከንፈሯ
ትንሽ አብጧል መሰል
ማነው የቀጠፋት?
ተስማ ነውንጂ መቼም ንብ አይነድፋት
እያልኩ አስባለሁ
ከንፈርሽን አያለሁ።
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይደለም ከንፈሯ
አይኔ ነው ያበጠው
አይቶ ያታለለ
ከንፈሯን ያሳየኝ ቅል እያሳከለ
እያልኩ አስባለሁ
ከንፈርሽን አያለሁ።
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይሽ አይሽና
አይኔን እንቃለሁ
ከፊቴ የማየው
ከንፈር ይሁን ግንባር
እንዴት ብዬ አውቃለሁ?
እያልኩ አስባለሁ።
~~~~~~~~~~~

@getem
@getem
@beppa_19
1