ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የጊዜሽ እውነታ! !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
የፎቶ ዓለም ነው!
የብልጭታ ዘመን...
ታይታ የሞላው ፥ መታበይ የሰራው
አዋቂው ብዙ ነው !
በራሱ ዛቢያ ላይ ፥ መንገድ 'ሚያቀናው።
ጎዳናው አንድ ነው!
የለም የተለየ...
ጠርጣሪው እልፍ ነው!
ገለባ ሸንትሮ ፥ ሽንብራ ያለየ።
መቅረዝ ተሸካሚው.. .
አትሮኖሱን ዘርጊው...
ባለ ጧፉ ብዙ
ባለ መጣፍ ብዙ
መድረኩ ላይ ቆሞ ፥ እኔን ስሙ 'ሚለው
እሪያው አሸን ነው!
ያሉትን አድምጦ ፥ በመንጋ 'ሚጎርፈው
#ይኸው ተመልከቺ!
ስንደዶው መች ጠፋ?
አክርማው መች ጠፋ?
ባለሙያው ብዙ
ባለ ወስፌው ብዙ
እንዴት ቢሰፋ ነው?
መሶቡ ሳያምር ፥ የሚታይ ሰበዙ?
#አየሽ!
በዚህች በጉድ ሀገር...
ቱባውን አፍታቶ ፥ ክሮቹን ወድሮ
ጋቢ ልስፋ 'ሚለው ፥ ሸማኔው ቢበዛም
ሁሉም እርቃኑን ነው!
የሞቀው ሰው የለም ፥ ውርጩም አልተረታም።

@getem
@getem
@paappii
ከእናቴ ያስተረፍኩትን
ደብቄዉ የምኖር
ስስታም ነበርኩኝ
ለእዉነተኛ ፍቅር

መጣሽ
አገኘሁሽ
ከሰሰትኩት ጋራ
የደበኩትንም የናቴን ሰጠሁሽ

ይሄዉ አደራየ
ማተብ ነዉ አጥልቂዉ
የራሱ መልስ አለዉ
ፍቅርን ጠይቂዉ
የኔን ባትችይ እንኳ
የእናቴን ጠብቂዉ

ሶሎሞን ሳህለ
@getem
@getem
#jeko
Miki ebalalew ye gonder university ye 3gna amet temari negn kelay yelakulachu ehitachin tsigereda tibalalech egna betechalen akim lemasebaseb mokirenal enantem yetechalachun adirgulat.
1 be silk. ye enatua silk new( +251 96 143 1288) weyim beakal bemeteyek tikur anbesa hospital bemehed
2 be accountbkutrua bemasgebat be ajal weyim *886# be mobile banking ke 5 birr eske chalachut
3 keguadegnochachu ga bemehon bemasebaseb
4 be telegram be facebook endihum beteleyayu social midiawoch share bemadreg
Endihum andand gudayochin keslbetesebochua ga bemehon mascheres yechalachutin bemadreg alenilish beluat.

Melkamin bemadreg yetebarekewun ye edme zemenachinin melsen enbarkew.
Lerechemari mereja @mikihaile bemegbat mawarat tichilalachu.
Egziabher ethiopian ena hizbochuan yibark amen amen amen 🙏🙏🙏
🔥1
እቴ
(በውቀቱ ስዩም)

ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤

... እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።

እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን

@getem
@getem
👍32
እግዚዎ አዳማ
በጨለማ
አቦ ናዝሬት በኩለሊት

(ነብይ መኮንን )
```````````````

ሺ ኮከብ ካናትሽ ፈጦ
ስንት አምፖል አይኑን አጉርጦ
አስፋልትሽ በብርሀን አጊጦ
ጉድሽ በጭለማ ፈርጦ
ቡና ቤቱ ደጃፍ በሩ....
ባንኮኒው ከሰው ተፋጦ
ሙቀት ትነት
ዳንስ ጩኸት
ሴት ወንዱን ሳይወድ አስምጦ
ያራውጠዋል አዳሜን
ሞራ እድሉን ለሊት ገልጦ፡፡
እግዚዎ አዳማ
በጨለማ
አቦ ናዝሬት
በኩለሊት
አልጋ ፍለጋ የሚሮጠው
ሴት አዳር የሚያካልለው
ሰክሮ በድጋፍ የሚቆመው
ግብግብ ገጥሞ የሚጮኸው
ይራወጣል ዳር እስከዳር
ይራወጣል ሰፈር መንደር
ሽቅብ ቀጨማ ድንበር
እስከ አሮጌ አዳማ ዳር ዳር
ቁልቁል እስከ እሩቅ ጮሬ በር
ጎኑን እስከ ቦይ ማዶ አጥር
ላዩን ሀዲዱን ታኮ
ታቹን አቡስቶ ቡሉኮ
መሀል ከእርግብግቢትሽ ላይ
የማርያም ሰፈር አዋይ
የገዳም ሰፈር አዋዋይ
የቁርቁራ አድባር ሲሳይ
ሳር ሰፈር ነፃነት ሜዳ.....
መስጊድ አራዳ ፍሙ ላይ
ምንጃር ጎዳናን አካሎ.....
በየ ቀዬው የማታ አዋይ
ስንቱ ሲነድ ስንቱ ሲጋይ
አይኑ ከመብራት ሲተያይ
አምፖሉም ቀይ
ብሌኑም ቀይ
ቤት ምድሩም ቀይ
የአዳም ዘር ቀይ
አንዱ ሀይ ሀይ
አንዷ ውይ ውይ
ሌላው ዳይ ዳይ
እግዚዎ አዳማ
በጭለማ
አቦ ናዝሬት
በኩለሊት፡፡
ዙርያሽ በተራራ ክበብ
ጥግሽ በጋራ አለት ድባብ
የልምለየሜሽን ንባብ
ቁልቁል ለረባዳሽ ሲያነብ
ኮርኒስሽ የሰማይ ኮከብ
ምድርሽ የአዋራ ቅቤ ቅብ
ፍሬሽ የዋንዛ እንኮይ ጥጋብ
ገፅሽ የባህር ዛፍ ክብካብ
ዋርካሽ የቁርቁራ መሶብ
በጨለማሽ ሁሉ ጥቁር
በኮከብሽ ሁሉ ፍቅር
.
እያለ ይቀጥላል...


ሸጋ ሰንበት!💚💛
@getem
@getem
@Nagayta
ቀረሽ እንደዋዛ፣
እንደ ድመቶቹ፤
የትም እንደሚያድሩት፣
እንደ ስልክ እንጨቶች፤
እንደ ዛፍ ሀረጎች፣
እንደ ቤት ክዳኖች፤
ብርድ አቆራመደኝ?
ስጠብቅ ስጠብቅ
˝ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ፤
የልጅነት አይኔ ሟሟ እንደ በረዶ፤
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር፤
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር፤
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር፤
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር፤
ብርድ አቆራመደኝ፤
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ፤
ውርጩ ቀለደብኝ፤
ጨለማው ሳቀብኝ፤
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ?
መስኮቶች ጨልመው፤
ቤቶች ተቆልፈው፤
ከተማው ሲተኛ፣
አይተዋል ያያሉ፤
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ፤

ገብረ ክርስቶስ ደስታ

@getem
@getem
@beppa_19
👍1
➬ ያልተፈታ ቅኔ ➪
©ሲራክ
ዳዊቴን ደግሜ ከማክዳሽ ምድር
ቅኔን ተግቻለሁ
በታሰረ አካሌ ያሰርሽው ልብሽን
ሳስፈታ ኑሬያለሁ
ቅኔሽን ተግቼ አጥቼሽ እያለሁ ....
ካሰረኝ ልብሽ ዳር በማይፈታኝ ወኔ
ምን ልሆን መጣለሁ?
አየሽ አንቺ አካሌ
እኔ ማለት በቃ የመሄድ ፅዋ ነኝ
የተገፊ ማሪ
እኔ ማለት በቃ ጎደሎ አክርማ
በሞላ ሀገር ኗሪ
ዳዊቴ ተደግሞ ከማክዳሽ ምድር ቅኔሽ ተጠጥቶ
በታሰረ አካሌ በጠፈርሽው ልብሽ
ሲከፋ ይኖራል እምባ ባይኑ አግቶ
➪➪➪➪ሲራክ ➮➮➮➮
ጥር 2 ሺህ ፲፪
@siraaq
#
@getem
@getem
@getem
@getem
✤✣ይታይሽ የኔ አለም✣✤

ይታይሽ የኔ አለም
አዎን ተመልከቺ
አስተውይ እናቴ....
የእህቶቼን ሳቅ
የልጆችሽን ድምፅ
ሳጣው ከሰፈሬ።
፨፨፨፨፨፨
አዎን ኢትዮጵያዬ
በወንዞች በሳርሽ
በእርሻ ባፈርሽ
ቦርቀው ያደጉት
እነዛ ልጆችሽ......
ዛሬ ምነው ጠፉ
ደብዛ ተሠወረ
ማን ቀማሽ ከእጆችሽ።
፨፨፨፨፨፨፨
አዎን የኔ ልእልት
የሉም ከቤታቸው
ቀዬ መንደራቸው
ብቻውን ይጮሃል..
እናትም ተጨንቃ
አይኗ አንባን ያነባል።
ህፃናት አጥተዋል
ጡትን ከአፋቸው....
የእናታቸው መጥፋት
እንባ እያስነባቸው።
ያልተዘጋው ማጀት
ዛሬም አፉን ከፍቷል ....
እምዬ ከሌለች
እታአለም ካልመጣች
አሻፈረኝ ብሏል።
፨፨፨፨
እናም እታለሜ
አዎን አስተውዪ
የህዝቦችሽን ግፍ
የአጥፊዎችሽን ደባ ...
የእህቴን በደል
የቀሚሷን እንባ።
አዎን ተመልከቺ
መፍትሔ የሌለው
ጩኸቴን አድምጪ
✣✣✣✣✣
እናም ኢትዮጵያዬ
እስኪ ጠይቂያቸው
ወንዘና ተራራ
አእዋፍ ዛፎቹን ..
ጋራ ሸንተረሩን
መስካመስክ ዋሻውን ..
አይቻለሁ ያለ
ካለ..
የሲቃን ድምፅ
ያደመጠ ...
የሀዘንን እንባ
የጠረገ...
የእምዬን ፍርሀት ተመልክቶ
ለእህቶቹ ተቆርቁሮ
አንደራሱ የታገለ
እስኪ ጠይቂ ካለ !!!!!!


ተፃፈ @Mak_bale
23.5.2012
@getem
@getem
@getem
=================

ቆሜ ብታዘበው፤
ከፀሃይ መጥለቂያ እስከ ፀሃይ መውጫ፣
ድምሩ ዜሮ ነው፤
የኀሊዮሽ ሙሾ የክብ አለም ሩጫ፡፡


@abiye12

👇👇👇👇
@getem
@getem
@getem
~~የመሔዷ መምጣት~~
"""""""""""""""""""""""""""
👉መኮንን አልማው ተፃፈ👈
''""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ቅርብ ሳለ ፍቅሯ
ሩቅ ሆኖ አዳሯ
የአይኗን ብርሃን በአይኔ ለማየት ጓጉቼ
ገላዋን በጣቴ መዳበስ ሰስቼ
ናፍቆቷን አውርቼ
ነይ ስላት... ነይ ስላት
የመፈለግ ኩራት
ልቧን ስለሞቀው ዝና እየመሠላት
ቆማ ስትወላውል
ጊዜዋን ስትገድል
እንደ ኤሳው በኩር ዕድሏን ለውጣው
መምጣቷን ገድሎ ነው መሔዷ የመጣው!
""""""""""""""""""""/""""'/""""""""'/""""""""""""""""""
..............23/05/2012/ዓ.ም~ሀዋሣ

@getem
@getem
@getem
የውጊያ ስልት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሙሴ በበትሩ
ፈርኦን በጦሩ
ኤርትራ ባሕር ላይ ፣ ጦርነት ጀመሩ፡፡
።።።።
ሙሴ በበትሩ…
ግዙፍ ባህር ከፍሎ ፣ ህዝቡን አሻገረ
ፈርኦን በጦሩ
ከነ ወታደሩ
ባሕር ሰጥሞ ቀረ፡፡
።።፣፣
ውጊያ የማይችል ሕዝብ
ግዙፍ ባሕር ከፍሎ ፣ በተዓምር ሲሻገር
ሌላ የውጊያ ስልት
ቀይሮ ይመጣል ፣ ቢሰምጥም ወታደር፡፡






የተሻገረ ህዝብ
ለቀሪ መንገዱ
አሳ እያጠመደ ፣ ከባህር ሲያወጣ
የፈርኦን ወታደር
ሞቶ ለመዋጋት
በአሳ ገላ ላይ ፣ እሾህ ሆኖ መጣ!!!
።።።።
።።።፣
"አሳን መብላት
እንዳይወጋህ ፣ በብልሃት!"
@getem
@getem
#jeko
2
IMG_3490.jpg
172 KB
"የወንድ ምጥ ያማል!"
"የወንድ ምጥ ያማል" ብሎ ሲፅፍ አንዱ
"የሴት ልጅ ይብሳል" ብለው ሌሎች ካዱ!
ፃፊውም 'ካጅውም ያው አዳም ነው ወንዱ
በበለስ ፍሬና በሷ የወረዱ, ከዛ የተዋረዱ::

እርሱስ ቀጥ ያለ ነው የርሷ ግን ጠማበት
ግራ ጎን አጥንቷ ቆልመም ያለችበት
ሊያቀናት ቢሞክር 'ምትሰበርበት!

ግን እንዴት ሆኖ ነው የወንድ ምጥ 'ሚብስ?
በየወሩ አበባው ከማጀቱ 'ሚፈስ?
ነፍስ ጡሮ አንጀቱ እስኪወልድ 'ሚያለቅስ?!
.........እናስ? ደሞ ከዚያስ?!

ግን እንዴት ሆኖ ነው የወንድ ልጅ ጫንቃው
በዘመኑ ላንዴ ዝንተዓለም አፍቅሮ ሁሉን 'ሚንቀው
ይከዳው የሷ ልብ ወንድነቱን ነጥቆት የሚሆን አለቃው
የሚጫወትበት ሲያነሳ ሲጥለው ልቡን ሲነርተው

እንግዲያስ.....
በልቧ ጭካኔ በወሳኝነቷ እሷን የሚያስመልጥ
አንተን የሚያስላዝን ካንተ ዘንድ የማይቆርጥ
ከእግዜር የተቸራት ደሞዟ ነው የርሷ ምጥ!
ስለዚህ አዳም ሆይ.....
የልቧን ቅመም ቋት ላትስተካከለው ላትሰፍረው አትሩጥ
ማጀቷን ላትኖር የሷን ልብ አትመኝ አርግዘህ ላታምጥ
ለአፍቃሪ ልብህ ምጥህ ጭንቀትህ ነው በል አርፈህ ተቀመጥ!!!

©️አቤንኤዘር ጥላሁን/papi
Feb. 1, 2020

@getem
@getem
አንቺ👧

አንቺ ጥቁሯ ሴት ጠይም ነዉ ቀለምሽ
አንቺ ሳቂታ ሴት ነጭ' ናቸው ጥርሶችሽ
አንቺ ተላላ ሴት ደማቅ ነው እምነትሽ
አንቺ ገራገር ሴት አረንጓዴ ቤትሽ
አንቺ ስታለቅሺ የማይታይ እንባሽ
አንቺ ስትጮሂ የማይረብሽ ድምፅሽ
አንቺ ጠንካራ ሴት ከነ ትልቅ ህልምሽ
አንቺ ኢትዮዽያዊት በቀለም ታጅበሽ
በስሜት ተከበሽ
ለ22 አመትሽ እንኳን አደረሰሽ ::

መልካም ልደት ቃልኪዳን ካሳ::
👨‍👩‍👧‍👦Makrinam
10/05/2012

@getem
@getem
👍31
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እንዲህ እንደዛሬ...
በመሀከላችን
ንፋስ ሳይግባብን ፣ ፍጥረት ሳይፈጠር
በኔና አንቺ መሀል...
የነበረው ክፍተት ፣ አንድ ስንዝር ነበር።
አንቺ ሰማይ ሆነሽ እኔ ደግሞ ምድር!!!
............................................
በዚህ ስንዝር መሀል....
እስትንፋስ ያላቸው ሰዎች ተፈጠሩ
እነዚህ ሰዎችም....
ቅርብ ላለች ሰማይ
የምድርን ሀጥያት ይነግሯት ጀመሩ።
"ምድር ዘማዊ ነው
ምድር ሀጣዊ ነው
ብትሸሺው ይሻላል ይህ ዓለም ጠፊ ነው"
እያሉ ሲነግሯት የሰው ወሬ ሰምታ
ሰማይ ፊኛ ሆና...
ትለጠጥ ጀመረ ከኔ ተለይታ
በሰዎች እስትንፋስ...
ወደ ላይ ተነፍታ
ወደጎንም ሰፍታ።
.......................................
እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ
የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ
እንዲህ እንደዛሬ
ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ።
................................................
እንደውም እንደውም...
በዛ ስንዝር መሀል ያኔ የተፈጠሩ
እዛሬ ላይ ሆነው..
"ሰማይ ቅርብ ነበር" እያሉ ሚያወሩ
እድሜ የሰጣቸው
ጥቂት ሰዎች አሉ
የኔና ያንቺ ፍቅር የሚመሰክሩ።
.............................................
እንደውም እንደውም....
ሌላ አይነት ማስረጃ ሌላ አይነት ምስክር
ሰማይ ቅርብ ሳለሽ ምጣድ ሆኜ ምድር
እንዲህ እንደዛሬው...
ነፋስ አቀጣጥሎት
ነፋስ የሚያጠፋው እሳት ሳይፈጠር
የሰው ልጆች ሁሉ
በፀሐይ በርሀን ምግብ ያበስሉ ነበር።
.............................................
ፀሐይ ውበትሽ ነው ጠዋት የምሞቀው
ቀን ተቃጥዬበት ሌት የምናፍቀው።
ለሊት ላይ ያመኛል ህመሜም አንቺው ነሽ
ቀኑ ጨለማ ነው...
ነግቶ እስካይሽ ድረስ ትናፍቂኛለሽ።
...........................................
መቼ ነው ሚነጋው?
ፀሐዩ ውበትሽ ምድርን የሚከድነው
መርዙ መድሀኒትሽ...
በሽታዬን ገድሎ ህመሜን ሚያድነው
ካፈቀሩት ጋራ....
እንኳን ላንድ ለሊት
ላፍታ ያህል እንኳን መለያየት ሞት ነው።
.............................................
መቼ ነው ሚነጋው ልቤን ይበርደኛል
ንጋት ላይ የሚሸሽ..
ወረተኛ ፍቅር ጤዛው በዝቶብኛል
አንቺ የሌለሽበት...
ራሴን ሳስበው ራሴን ያዞረኛል።
ለራስ ምታት ህመም..
መድሀኒት እንዲሆን
በሽታን የሚገድል መርዝ ነው ሚቀመም።
...................................
እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ
የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ
እንዲህ እንደዛሬ.
ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ።
#belay bekele weya

@getem
@getem
@beppa_19
እየሔዱ መጠበቅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
‹‹እየሄድክ ጠብቀኝ›› - ስትይኝ ሄጃለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ….
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ…
አክሱምን እንዳየሽ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ጠራቢው እኔ ነኝ!
ያለፍኩት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ሰማይ ጠቀስ ሐውልት - የተፈለፈለ፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
አክሱም ሐውልት ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ጥበብ አለ!!
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ላሊበላን አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ፈልፋዩ እኔ ነኝ፤…
ያለፍሁት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ህንፃ ቤተ-መቅደስ ፤ የተፈለፈለ፡፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
በላሊበላ ውስጥ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ፅናት አለ፡፡
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ትክል ድንጋይ አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
የኔው መቃብር ነው!
ውድቀቴም እዛው ነው! ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ባባራ ዘመኑ፤
የራሱን መቃብር - ለመትከል የቻለ፤
መኖር የሚመስል - መሞትም ያይደለ፤
በጢያ ድንጋይ ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ውድቀት አለ፡፡
ከውድቀቴ ኃላ - ባይንሽ የምታዪው፤
ታምር የሚመስል - ታሪክ የምትይው፤
ምልክት የሚሆን - መንገድ ስላልተውኩኝ፤
ከመሞቴ በፊት..
ውድቀቴን፤
ሽንፈቴን፤
ከመቃብሬ ላይ - እንዲህ ብዬ ፃፍሁኝ፡፡
ሩጫዬን ጨረስኩ፤
ሰው ነኝ - ተሸነፍኩ!!!
እናምልሽ ውዴ….
‹‹እየሔድህ ጠብቀኝ›› - ያልሽው ቃል ስህተት
ነው፤
ቃሉም ገብቶሽ እንደው…
መራመድ መሄድ ነው፤
መሮጥም መሄድ ነው፤
መብረርም መሄድ ነው፤
አንቺ እንድትደርሺብኝ …
እኔ እየሞትሁ - እጠብቅሻለው!!!
****************
@getem
@getem
#jeko
1
ኑ ደም በመለገስ በክቡሩ ስጦታ ክቡሩን የሰው ልጅ ሕይወት ከሞት እንታደግ...!

የካቲት 1፣2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በመገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማው አጠገብ!
ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድዎን ይዘው ይመጡ!

ጉራማይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅት!!!

@Guramayelie

+251955431015

@GURAMAYLIE