ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንዱ ባንዱ ሲስቅ
በሃሳብ መጫወቱ
ትንቅንቅ ሙግቱ
ባልከፋ በበጀ
ስዉን ባደረጀ …
በየራሱ ጎራ
በሠራው ተራራ
በአተያዩ ዳራ
ሁሉ ከተኩራራ
ልቡ ከተዘጋ
አንጎሉ ከረጋ
ራሱን ካልበለጠ
ለዕውቀት ካላማጠ …
የራስን ማዳነቅ
በሌላው መሳለቅ
ምንድነው ልቀቱ?
የት ጋ ነው ጥልቀቱ?
እንዴት ያሳድጋል?
ማንን ይለውጣል?
አፍ ከጆሮ ሲልቅ
ስሜት ካሳብ ሲጠልቅ
አመክንዮ ይሞታል
ጆሮ ይገነዛል
ሙግት ክርክሩ
ድንቅ አዲስ ነገሩ
ይሆናል መጣያ
ጭቃ መቀባቢያ…
ሀሳብና አሳቢን
ነጥለን ካላየን
እንዱ ባንዱ ሲስቅ
ሲያላግጥ ሲሳለቅ
ጀምበሯ አዘቅዝቃ
እሷም በኛ ስቃ
በማይገባን ቋንቋ
አይቀርም መጥለቋ።
©ምህረት ደበበ

@getem
@getem
@beppa_19
°°°ግዜማ°°°
ግዜማ ጥበብ ነው
ቅኔን ያረገዘ ፤
ሌትና ቀናትን
በሰም የጠረዘ፤
በወርቅ ዝፋኑ
መለኮት የያዘ፤
እሞድሽ

@getem
@getem
@getem
'ከሽፍታ' የተሰረቀች ግጥም
(በረከት በላይነህ)

-----------
ገና!
ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤
ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ።

በዳዴ ዘመኔም፣
በ'ወፌ ቆመችም!'፤
አውዴ ክፉ ነበር ለወሬ አይመችም።

እንደ ሚዳቋ ነፍስ እንደ ነብር ጥፍር፤
ስጋትም- ጭካኔም-ነበር የዕውቀቴ ስር፣
"ተጨቆንኩ!"
"ተበደልኩ!"
"ተረገጥኩ!"
"ተገፋሁ!"
"ተቀማሁ!"።
መሬቱ ጠላቴ፤
ሰማዩ ብሶቴ።

ተስፋ ትዝታዬን ሊያጠፋ ለቃቅሞ፤
ባፈሙዝ ያየኛል ገዳይ ደጅ ቆሞ።

ወዘተ...
በእነዚህ 'ምግቦች' አድጎ ሰውነቴ፤
እኮ እንደምን አይሆን 'ጥርጣሬ' ሀብቴ?
መገርሰስ፣ መደምሰስ፣ ማሳደድ-ውበቴ?
ስለዚህ አይድነቅህ!
ቀርበህ ወደድከኝም፣ ርቀህ ጠላኸኝም፤
ገድዬህ ካላለፍኩ የኖርኩ አይመስለኝም።
@getem
@getem
#jeko
ቅዳሜ እና ናፍቆት !!!!!!


ከቅዳሜ መሃል፣ አንዳንዱ ቅዳሜ፣
አልጠገብኩም ይላል፣
እንደ ሙና ከንፈር፣ ተስሜ ተስሜ።
ይኸውልሽ ውዴ፣
ብዙ ቀን አለፈኝ፣
የሚሳም ቅዳሜ፣
ፍልቅልቅ ቅዳሜ፣ ከኔ ማጀት ወጥቶ፣
ፈልገኝ ይለኛል፣
ከነምናምኑ ካንች ጉያ ገብቶ።
እንደ በትረ ሎሚ፣ ተንቦክቦክ እያለ፣
ሉባንጃ ያወደው፣ ብርጉድ የታጠነ፣
ለጀማ እሚበቃ፣
ሙት የሚቀሰቅስ፣
ዘበናይ ቅዳሜ ካንች ከንፈር አለ???
ግን ውዴ፣
አንዳንዱ ቅዳሜ፣
ቀን አይወጣለትም፣
አያገማሸርም አያሞቅም ማጀት፣
ልክ እንደ አቦል ቡና፣
ውል ባለ ጊዜ ፣
ይዘውራል ራስ፣ ይፈትናል አንጀት።
እናም ሸጋዬዋ፣
ደማቁ ቅዳሜ፣
ሁሌ እንደለመድኩት ፣
ፍልቅልቅ፣
ፍንድቅድቅ፣
ሽሙንሙን እያለ፣ ቀኔ እንዲደምቅልኝ፣
የምወድሽዋ፣
ፍ .ል.ቅ.ል.ቅ.ል.ቅ ብለሽ፣ እባክሽ ሳቂልኝ።
ሳቂልኝ!!!!

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

ሸጋ ሸግዬ ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!!

@Nagayta
@getem
@getem
ለቅዳሚታችን ጭማሪ ጀባታ!




የላይኛው!!!!!!


ከነ መምሬ አሊ፤
ከሸህ በላይ ሃገር ፤ ተሰርቶ እትብታችን፤
በሰውነት ልኬት፤
ሰው በመሆን ሚዛን ፤ ተሰፍሮ ልባችን፤
ከሰውነት መንበር፤
እንግፋችሁ ሲሉን፤
እንለያችሁ ሲሉን ፤
ያንቀጠቅጠናል ያንገሸግሸናል አይወድም ቀልባችን።
እነ ቦተሊካ፤
ላይሳካላቸው፤
የእምነት ለምድ ለብሰው፥ የተንኮልን ኩታ፤
በታችኛው መንደር ፤
ታቹን እያሰቡ ፤
መስጂዲና ደብሩን ፤ ተለያይ እያሉት ቢገፉት ጧት ማታ፤
ህልማቸው ከንቱ ነው፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
ታቹን ንቀን ትተን፤
ከላይ ተቃቅፈናል ተቃቀፉ ብሎን የላይኛው ጌታ።

((( ጃ ኖ ))💚💛

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!

@getem
@getem
@Nagayta
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!
በተጨማሪም ገፄን በመቀላቀል ያትርፉ!!

@yeMERI_terekoch
የጊዜሽ እውነታ! !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
የፎቶ ዓለም ነው!
የብልጭታ ዘመን...
ታይታ የሞላው ፥ መታበይ የሰራው
አዋቂው ብዙ ነው !
በራሱ ዛቢያ ላይ ፥ መንገድ 'ሚያቀናው።
ጎዳናው አንድ ነው!
የለም የተለየ...
ጠርጣሪው እልፍ ነው!
ገለባ ሸንትሮ ፥ ሽንብራ ያለየ።
መቅረዝ ተሸካሚው.. .
አትሮኖሱን ዘርጊው...
ባለ ጧፉ ብዙ
ባለ መጣፍ ብዙ
መድረኩ ላይ ቆሞ ፥ እኔን ስሙ 'ሚለው
እሪያው አሸን ነው!
ያሉትን አድምጦ ፥ በመንጋ 'ሚጎርፈው
#ይኸው ተመልከቺ!
ስንደዶው መች ጠፋ?
አክርማው መች ጠፋ?
ባለሙያው ብዙ
ባለ ወስፌው ብዙ
እንዴት ቢሰፋ ነው?
መሶቡ ሳያምር ፥ የሚታይ ሰበዙ?
#አየሽ!
በዚህች በጉድ ሀገር...
ቱባውን አፍታቶ ፥ ክሮቹን ወድሮ
ጋቢ ልስፋ 'ሚለው ፥ ሸማኔው ቢበዛም
ሁሉም እርቃኑን ነው!
የሞቀው ሰው የለም ፥ ውርጩም አልተረታም።

@getem
@getem
@paappii
ከእናቴ ያስተረፍኩትን
ደብቄዉ የምኖር
ስስታም ነበርኩኝ
ለእዉነተኛ ፍቅር

መጣሽ
አገኘሁሽ
ከሰሰትኩት ጋራ
የደበኩትንም የናቴን ሰጠሁሽ

ይሄዉ አደራየ
ማተብ ነዉ አጥልቂዉ
የራሱ መልስ አለዉ
ፍቅርን ጠይቂዉ
የኔን ባትችይ እንኳ
የእናቴን ጠብቂዉ

ሶሎሞን ሳህለ
@getem
@getem
#jeko
Miki ebalalew ye gonder university ye 3gna amet temari negn kelay yelakulachu ehitachin tsigereda tibalalech egna betechalen akim lemasebaseb mokirenal enantem yetechalachun adirgulat.
1 be silk. ye enatua silk new( +251 96 143 1288) weyim beakal bemeteyek tikur anbesa hospital bemehed
2 be accountbkutrua bemasgebat be ajal weyim *886# be mobile banking ke 5 birr eske chalachut
3 keguadegnochachu ga bemehon bemasebaseb
4 be telegram be facebook endihum beteleyayu social midiawoch share bemadreg
Endihum andand gudayochin keslbetesebochua ga bemehon mascheres yechalachutin bemadreg alenilish beluat.

Melkamin bemadreg yetebarekewun ye edme zemenachinin melsen enbarkew.
Lerechemari mereja @mikihaile bemegbat mawarat tichilalachu.
Egziabher ethiopian ena hizbochuan yibark amen amen amen 🙏🙏🙏
🔥1
እቴ
(በውቀቱ ስዩም)

ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤

... እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።

እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን

@getem
@getem
👍32
እግዚዎ አዳማ
በጨለማ
አቦ ናዝሬት በኩለሊት

(ነብይ መኮንን )
```````````````

ሺ ኮከብ ካናትሽ ፈጦ
ስንት አምፖል አይኑን አጉርጦ
አስፋልትሽ በብርሀን አጊጦ
ጉድሽ በጭለማ ፈርጦ
ቡና ቤቱ ደጃፍ በሩ....
ባንኮኒው ከሰው ተፋጦ
ሙቀት ትነት
ዳንስ ጩኸት
ሴት ወንዱን ሳይወድ አስምጦ
ያራውጠዋል አዳሜን
ሞራ እድሉን ለሊት ገልጦ፡፡
እግዚዎ አዳማ
በጨለማ
አቦ ናዝሬት
በኩለሊት
አልጋ ፍለጋ የሚሮጠው
ሴት አዳር የሚያካልለው
ሰክሮ በድጋፍ የሚቆመው
ግብግብ ገጥሞ የሚጮኸው
ይራወጣል ዳር እስከዳር
ይራወጣል ሰፈር መንደር
ሽቅብ ቀጨማ ድንበር
እስከ አሮጌ አዳማ ዳር ዳር
ቁልቁል እስከ እሩቅ ጮሬ በር
ጎኑን እስከ ቦይ ማዶ አጥር
ላዩን ሀዲዱን ታኮ
ታቹን አቡስቶ ቡሉኮ
መሀል ከእርግብግቢትሽ ላይ
የማርያም ሰፈር አዋይ
የገዳም ሰፈር አዋዋይ
የቁርቁራ አድባር ሲሳይ
ሳር ሰፈር ነፃነት ሜዳ.....
መስጊድ አራዳ ፍሙ ላይ
ምንጃር ጎዳናን አካሎ.....
በየ ቀዬው የማታ አዋይ
ስንቱ ሲነድ ስንቱ ሲጋይ
አይኑ ከመብራት ሲተያይ
አምፖሉም ቀይ
ብሌኑም ቀይ
ቤት ምድሩም ቀይ
የአዳም ዘር ቀይ
አንዱ ሀይ ሀይ
አንዷ ውይ ውይ
ሌላው ዳይ ዳይ
እግዚዎ አዳማ
በጭለማ
አቦ ናዝሬት
በኩለሊት፡፡
ዙርያሽ በተራራ ክበብ
ጥግሽ በጋራ አለት ድባብ
የልምለየሜሽን ንባብ
ቁልቁል ለረባዳሽ ሲያነብ
ኮርኒስሽ የሰማይ ኮከብ
ምድርሽ የአዋራ ቅቤ ቅብ
ፍሬሽ የዋንዛ እንኮይ ጥጋብ
ገፅሽ የባህር ዛፍ ክብካብ
ዋርካሽ የቁርቁራ መሶብ
በጨለማሽ ሁሉ ጥቁር
በኮከብሽ ሁሉ ፍቅር
.
እያለ ይቀጥላል...


ሸጋ ሰንበት!💚💛
@getem
@getem
@Nagayta
ቀረሽ እንደዋዛ፣
እንደ ድመቶቹ፤
የትም እንደሚያድሩት፣
እንደ ስልክ እንጨቶች፤
እንደ ዛፍ ሀረጎች፣
እንደ ቤት ክዳኖች፤
ብርድ አቆራመደኝ?
ስጠብቅ ስጠብቅ
˝ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ፤
የልጅነት አይኔ ሟሟ እንደ በረዶ፤
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር፤
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር፤
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር፤
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር፤
ብርድ አቆራመደኝ፤
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ፤
ውርጩ ቀለደብኝ፤
ጨለማው ሳቀብኝ፤
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ?
መስኮቶች ጨልመው፤
ቤቶች ተቆልፈው፤
ከተማው ሲተኛ፣
አይተዋል ያያሉ፤
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ፤

ገብረ ክርስቶስ ደስታ

@getem
@getem
@beppa_19
👍1