ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ደህና ነኝ!
[ሰለሞን ሣህለ]

"ደህና ነህ?" እያሉ
ለጠየቁኝ ሁሉ
"ደህና ነኝ" ልበል ወይ?
ደህና ነዉ እንዲሉ
ብየ ብጠይቀዉ
"ደህና መሆንህን
ከልባቸዉ ሽተዉ ለጠየቁህ ቀርቶ
ደህና መሆንህም ለሚያሳምማቸዉ
ይበልጥ እንዲያማቸዉ ደህና ነኝ በላቸው።

@getem
@getem
@getem
👍1
አዎ እኔ ደህና ነኝ
============
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ብቻ ዝም ብሎ እራሴን ያመኛል
የወገኔ ስቃይ፣
አንቅልፍ እየነሳ ይቀሰቅሰኛል!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ሽብር አናውዞታል የልቤን ከተማ
ሰው በሞተ ቁጠር፣
ደረት እየደቃሁ አበራለሁ ሻማ!
አዎ እኔ ደህናነኝ፣
እብደት ተጠግቶኝ ዝም ብዬ ስቃለሁ
ሀገሬ ቁጭ ብዬ፣
ልክ እንደ ባይተዋር ሀገር ናፍቃለሁ!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ወገኔ ባልኩት ሰው ዘመኔን ምጉላላ
ሆዴን እየራበው፣
በቀን ሀያ ግዜ መከራ ምበላ!
እናም፣
ሀዘን አሰቃይቶኝ ልቤ እየበገነ
አሁን ያልኩት ነገር ደህንነት ከሆነ
አዎ እኔ ደህና ነኝ!

©እዮብ ዘ ማርያም
@getem
@getem
#jeko
#አልገጥምም


ጦረኛ ተዋጊ
የጎሳ ነፃ አውጪ ፥ #በቀፈቀፈ አገር
ከብዕር በዘለል
ባፈሙዝ ቃታ ነው ፥ ብዙ የሚነገር
በኔ.....አገር
ሲወድ ፣ ሲጠላ
ለሀዘን ለደስታው ፥ ባሩድ እየማገ
ሲፎክር ፣ ሲሸልል ፥ በጥይት ላደገ
ካደባየው በላይ
ከመግደሉ በላይ ፥ አፈር ከከተተው
የጣለው ሲነሳ
ተኩሶ ሲስት ነው ፥ ፀፀት የሚያኝከው ።
ይህንን ስታውቂ...
አጠገቤ ቆሞ ፥ የቀኑ ጃዊሳ
አረ ጎራው ሲለኝ ......ሊሸልል ሲነሳ
ስለ #ሀገር ግጠም
ለምን ትይኛለሽ ? ሸጉበሽ ከክንዴ
ቃልሽን የሰማ...
እንጋጠም ቢለኝ
ማስታወሻ ደብተር ፥ ጋሻ ይሆናል እንዴ?

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh


@getem
@getem
@getem
አራራይ
°°°°°°°
የኔ እዉነት መሸነፌ
የኔ ጠላት መሸነፌ
የኔ አቅም መሸነፌ
አትናፍቀኝ ትለኛለች -
በሷ መኖር ተለክፌ፣

ያ'ለም ነገር አያጓጓኝ
ያለኝ አድጎም አያስመካኝ።
ይሰለቻል ሁሉ ኑሮ…
ድግግሞሽ ቀጣይ -ድሮ፣
ይታክታል አፈር ላ'ፈርሥ
ሆኖ ላያልፍ መንፈራፈር…
ናፍቃኝ እንጂ ምስራቅ ያየሁ፣
በፍቅሯ እንጂ ቀን የለየሁ፣
ምን ያጓጓል ሰባት ዓለም
መኖሯ እንጂ ኸይር ለምለም…
እሷ ለኔ መዳን መምጫ
እሷ ለኔ ፀሐይ መዉጫ
ከታካች ቀን ከጨለማዉ፣
ማርያም መንገድ የማምለጫ…

እኔ ለሷ ጎርፍ ደራሽ
እኔ ለሷ ግንቧን አፍራሽ፣
ወገብ አስራ ከካበችዉ
ጥርሷን ነክሳ ካፀናችዉ፣
ዓለም መሳይ አላቃቂ
በግራ መንገድ < ቀኝ አጥማቂ፣

የኔ እዉነት መሸነፌ
የኔ ጠላት መሸነፌ
የኔ አቅም መሸነፌ
አትናፍቀኝ ትለኛለች -
በሷ መኖር ተለክፌ፣

እንዴት ልቻል እሷን መተዉ
እንዴት ቻለች እኔን መተዉ፣
ምን ብከፍ በመዉደዴ
ምን ብፀና በንዳዴ፣
ችዬ ነበር እንደ ቃሏ
ናፍቆት እንጂ የማይከላ…

አዉ አቃለሁ እንዳቅሜ
እንደ መቻል እንደ ቆሜ፣
ያኖረኝም የኖረኝም
ይሁን ብዬ በኔ ስፈርድ፣
ችዬበት ነዉ ናፍቆ መንደድ…

እና ለምን ይከፋታል…?
እና ለምን ይነዳታል…?
ያዉ ንገሯት ቁርጧን ትወቅ…
መናፈቄ ዓለሜ ነዉ
መተከሌ- መቆም መፅደቅ…!
ቢቻ ትዉሰድ ይቅርታዬን…
የሞኝ ፍቅር ዉትወታዬን…



"ናካይታ"

አ ፈ ቅ ር ሻ ለ ሁ ኝ❤️


@getem
@getem
@Nagayta
👍2
እናፍቅሻለሁ ! !
(በ ሰለሞን ሳህለ)
.
ልንገርሽ አይደለ
ከፍ ካለው ቦታ ከፍ ብዬ ቁሜያለሁ
ሰው ያለ አይመሥለኝም ባንቺ ቆርቤያለሁ
አሁንም አሁንም እናፍቅሻለሁ...
ሥላንቺ ከሆነ፣ ብርቱ ነኝ ኃያል ነኝ!
የሸረኞች ደባ፣ የተፈጥሮ እንቅፋት ችሎ እማያቆመኝ
ሐብሌ አይደለሽም አንገቴ ላይ የዋልሽ
ቀለበቴም ሳትሆኝ ጣቴ ላይ ያኖርኩሽ
ዕድሜ የማይፍቀው ንቅሳቴ አንቺ ነሽ!...
ያንተው ነኝ ብለሽኝ
የራስሽ ነኝ ብዬ...
እንዴት አልናፍቅሽ ናፍቆት አበባዬ?
መናፈቅስ በእርሱ - በእርሱ ያምርበታል፣
ተብሎ እሥከሚወራ
ተብሎ እሥከሚነገር
እናፍቅሻለሁ አንቺ የኔ ፍቅር!...
...
እንኳን ከኔ ጠፍተሽ...እንኳን ከኔ እርቀሽ
አጠገቤም ሆነሽ ትናፍቂኛለሽ...
የመዋደድ ኬላ መድረሻ ደንበሩ
መናፈቅ እኮ ነው የፍቅር ደም ሥሩ
አለሽ ጨረቃ ላይ
አለሽ ፀሐይዋ ላይ
አለሽ ሰማዩ ላይ
የትም አይሻለሁ የኔ ሙሉ ክፋይ
ተራራው አንቺ ነሽ
ባሕር ወንዙ አንቺ ነሽ
አገር ምድሩ አንቺ ነሽ
የትም ቦታ ሆኜ የትም ቦታ ሆነሽ
እናፍቅሻለሁ ትናፍቂኛለሽ...
...
ርዕሰ አንቀጽ ሠበር ዜና አንቺ ነሽ
ትረካዬ አንቺ ነሽ
ገሃድ ሕልሜ አንቺ ነሽ
ልብ ወለዴ አንቺ ነሽ
ቲያትሬ አንቺ ነሽ
ሰኞና ማክሰኞ ሮብ ሐሙሴ ነሽ
ዓርብ ቅዳሜ ነሽ
እለተ ሰንበቴ ሁሌ ምሳለምሽ
ማረፍያዬ እሁድ ነሽ
የትም ቦታ ሆኜ የትም ቦታ ሆነሽ
እናፍቅሻለሁ ትናፍቂኛለሽ ! ! !
@getem
@getem
#jeko
❗️Only 2 more days left!(ሁለት ቀናት ብቻ ይቀራሉ!)
⛺️ ⛺️ ⛺️ የካንፒንግ ጉዞ ወደ ጎሹ ሜዳ ⛺️ ⛺️ ⛺️

የመነሻ ቀን: - ጥር 26/2012🎈
የመመለሻ ቀን: - ጥር 27/2012🎈
የመነሻ ቦታ - ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል 🎪
የመነሻ ሰዓት - 2: 00 🚩

ዋጋ - 1199.99 🙈💰🙈💰

🎉🎊 “ጥቅል” 🎋🎊
🔵🚍 -የትራንስፖርት አገልግሎት(በቱሪስት ደረጃ አውቶቡስ)
🔴⛺️-ቴንት(ድንኳን)፣ ሻይ ቡና፣ ካንፕፋየር
⚫️🍝 - የተጠበሰ የበግ ሥጋ (🐏)፣ ምሳ እና እስናክ(ሃይል ሰጪ ምግቦች)🍟🍤
⚪️ 2 ሊትር የታሸገ ውሃ
🔵 የጋይዳንስ ክፍያ ከፓርክ መግቢያ ጋር
🔴ፎቶግራፍ ፎቶግራፍ 📷

በሰንሴት ሃይኪንግ የተዘጋጀ
የበለጠ መረጃ ፓናሎቻችንን ይቀላቀሉ
🔸channel @sunsethiking
🔹the group @sunsethike
🔻📷 @sunsetphotographyy

🎫ቲኬቶች
@Paappii
@thomaskagnew
@useryise
@Chere_daregot
ጋር ይገኛሉ
እኔ ተውኩሽ እንጂ፣ ማን አባቱ ቀማኝ
ከኔ ለባሰበት፣ ሰጠውሽ ለለማኝ።

(ገጣሚ:--ልዑል ሀይሌ)


@getem
@getem
የጃገማ ፀሃይ!!!!!!!


ጠየቀችው ልጅት፣
ይህንን ሳተና፣ይህንን ጅግሳ፣
ሲራመድ የኖረ፣
ሲጨፍር የኖረ፣
በባንዳ መቃብር፣በሰላቶ ሬሳ።


ደግማ ጠየቀችው፣
ጃገማ ግን ማነው????
የኬሎ ልጅ ማነው????
እንደ አደይ አበባ፣
እንደ መስቀሏ ወፍ፣ የተሽሞነሞነው፣
በአበሻ ጦር ሜዳ፣
በዲሞፍተር ቃንቄ፤ ሜዳይ ያሸገነው?


ኧረ ይህ ሰው ማነው?????
እየገራረማት፣
እየደናነቃት፣
ዘመን በማይሽረው፣
በአባቷ ወላፈን፣ በቃንቄው ተገርማ፣
ጠየቀች አባቷን፣
በጨዋ ልጅ ወገብ፣ ጎንበስ ቀለስ ብላ፣
ጃገማ አባ ዳማ፣
የበረሃው ግለት፣ የናዳው ስባሪ፣
የጠላትን ምሽግ፣
የሰላቶን ክምር ደርምሶ ፎካሪ።


ጀግና ልብ እንጅ የለውም ምላስ፤
እንኳንስ ስሙ ጥላው የሚዋስ።
ብሎ ጃገማ፤
አልጋውን ንቆ ድንገት ቀጥ አለ፤
በሃሳብ ጥሻ፤
በትዝታ ጦር እየሸለለ።


""" ዘራፍ!!!!!!!
ዘራፍ!!!!!!
ዘራፍ ፣አካኪ ዘራፍ!!!!!!!!
ጃገማ ኬሎ፣
የጦቢያ ዶቃ፣ የዳማ ፈረስ፣
ጎራው ላይ ሲዘልቅ፣ ምሽግ እሚያፈርስ።
ሃይ ዘራፍ ብሎ፣ ዘሎ ሲገባ፣
ይዝረጠረጣል ባንዳና ሌባ።
ዘራፍ ጃገማ ባለውጅግራ፣
ጎጆ መስርቷል፣
ቃል ኪዳን አስሯል፣ ከጦቢያ ጋራ።
ስማ ንገረው፣ ያን የባንዳ ዘር፣
እንጫጫዋለሁ፣ እንደ ጎመንዘር!!!!
የበጋው መብረቅ፣ የእሳቱ ጉማጅ፣
እንደ እርጥብ ቃሪያ፣
የሚለበልብ፣ ስሙ የሚፋጅ፣
የአባ ዳማ ልጅ፣
ከዘር ማንዘሩ፣ ጠላት አዋራጅ።""

"""
ብሎ ሲፎክር
እንደ ፈላ መጅ፣ እንደጀበና፣
ፊቱ ለበሰ ፣
ኢትዮጲያ የሚል፤ ቀስተ ደመና።


ይች ልጅ ጠየቀች፣
አባቷን ደጋግማ፣ ደጋግማ ጠየቀች፣
በአበሻ ልጅ ማእረግ፣
የዚህን ጃውሳ፣ አይን አይኑን እያዬች።
ጅግሳው ጃገማ፣
በሸገነው ቃሉ፣ ባጭሩ ነገራት፣
መቼስ የጀግና ልጅ፣የአባት ወግ አይጠፋት።
ትክዝክዝ እንዳለ፣
እንባ እንዳቀረረ፣
ይኸው ይኸ ጀግና፣ እንዲህ ተናገረ፣


አየሽ የትምወርቄ፤
አርበኛ በደሙ፤
ጀግና በድምድሙ፤
በአጥንቱ መግሮ ፤በተሰራች ሃገር፤
ከሞት ይቆጠራል፤
ለሠላቶ ውላጅ፤
የሚቆራርሱት ጣቢታ መጋገር።


ባንዳ ቀኑ ገጥሞት፤
ወንበር የሰጡት ቀን፤ ሃገር ይወገሻል፤
አርበኛም ዱር ወዶ፤
ካገር ሞት የኔ ሞት፤
ይቅደምና ልሙት፤
እያለ ከቤቱ ከደጁ ይሸሻል።


ግን እንዲህም ሆኖ፤
በአርበኞቹ ጥላ፤
በደም የተዋጀ፤
በአጥንት የታጠረ፤
የነፃነት ቅኔ፤
በትውልዱ ቀለም፤
እየተማገረ ቅኔው እስኪፈታ፤
አይፈርስም ሰንደቁ፤
በአልብላቢት ከንፈር፤ በምላስ ሩምታ፤
ያኔ ይፈወሳል፤
ምን አገባኝ ይሉት፤ የዘመን በሽታ።


እየውልሽ ልጄ፤
የጃገማን ድንበር፤
የጃገማን ሰንደቅ፤
ቀስተ ደመናውን፤
ብጣሽ ጨርቅ እያሉ፤
በርኩሰት አፋቸው፤ ንቀው ያዋረዱ፤
በየመሸታው ቤት፤
ቂጡን ገልቦ ሚሄድ፤
ችው ችው የሚባል፤ ቡችላ ወለዱ።


እናምልሽ ልጄ፤
ሞተን የሰራናት፤
ወድቀን ያነሳናት፤
ኢትዮጲያ እምትባል፣
ገራሚ አገር አለች፣
እድሜዋን ፈጀችው፣
አርበኛን አዋርዳ፣ ባንዳ እየሰቀለች።
ዘመን ቡቱቶዋን፤
እከክዋን አራግፋ፤
ባንዳ ቤቱ ሲፈርስ፣
ሰላቶ ሲረክስ፣ ፊቱ ሲገረጣ፣
ያኔ ነው የኔ ልጅ፣
የጃገማ ፀሃይ፣
በአበሾቹ ሰማይ፣ ቀድማ የምትወጣ።
ኧረ ትውጣ!!!!!!!!!"
"""

( ብወደው፣ብወደው ለማልጠግበው፣ ለጄኔራል ጃገማ
ኬሎና ለልጁ የትም ወርቅ ጃገማ)

መልካም ልደት!!!💚💛❤️

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@Nagayta
@getem
@getem
#እ-ህ-ቴ
አዎን ይሰማኛል
እረቀሽ ብጠፊ
መልክሽ ይታየኛል
የሰው ያለህ የሚል የሲቃማው ድምፅሽ አዎን ይሰማኛል
ተማፅኖ ልመናሽ ከሩቅ ይጠራኛል
ከመአድ ስቀርብ ተርቦ የሚጮኸው ሆድሽ እኔን ያስርበኛል
ትኩስ የአይን እንባሽ አይኔን እያቃጠለ
የደም እንባ እኔን ያስነባኛል
እህቴ
አረ ወዴት አለሽ
ውቧ እህት አለሜቱ
እርዛቱ እንዴት ያዘሽ እቴዋይቱ
ጀግናዋ ተማሪ ቁሩስ እንዴት ያዘሽ ብላቴናይቱ
የአፋኝሽ ዛቻ አረ እንዴት አረገሽ እህቴ ባለተስፋይቱ
ቱ ቱ ቱ ቱ ቱ ቱ
አረ ለኔ ያርገው
ወዴት ከተተብኝ
ምን ጅብስ በላብኝ
ምኑ የሰው ጅብ ነው አንቺን የበላብኝ
አልጮህ ያለ አፋኝ  -እህቴን- ከየት ከተተብኝ
ከየትኛው ዋሻ አንቺን ደበቀብኝ
የቱ መግነዣ ነው አንቺን የሳበብኝ
አልጮህ ያለ አፋኝ
የሰው በላ አፋኝ
እህቴን ከየት አረገብኝ
ወዴት ከተተብኝ
ከየት ደበቀብኝ
እምዬ ኢትዮጵያ
ዋሻሽ ሚስጥር እኮ ያዘብኝ
ሸለቆሽ የእህቴን መገኛ አልነግርህም አለኝ
ደንሽ አረንጓዴው እንዳልሰማ ሆኖ ዝምታ አበዛብኝ
እምዬ ልጅሽ ጠፍታ እርቃ እንዴት ይዝለቅልኝ
መላ በዪኝና ጫካሽን ጠይቀሽ
ዋሻ ሸለቆውን ሚስጥር አስፈትተሽ
እህቴን ከቤት መልሺልኝ



                         ተፃፈ በብላቴናው ብዕር
@getem
@getem
@getem
👍3
====================

"አጣ መነመነ"
"የለውም" ተብሎ ሰው እንዴት ይናቃል፣
ሰው ሆነው ለማለፍ ሰው መሆን ይበቃል፡፡

@abiye12

@getem
@getem
@getem
1
ቅ.. ጣት በሲራክ
c-ራክ
ገጣሚ እና አንባቢ ሲራክ
@siraaq
#
@getem
@getem
@getem
@getem
#ሰማይ_እና_ውዴ

ይሄውልሽ ውዴ
ባይኖቼ አማትሬ ፥ ሰማዩን እያየሁ
ውሎና አዳርሽን
ባፍቃሪ ልቦና ፥ መገመት ችያለሁ።
ሰማይ ፍንትው ሲል
ሰማያዊ መልኩን ፥ በገላው ሲደፋ
ከአድማስ መነሻ
እስከ አድማስ መቋጫ ፥ ሲያውለበልብ ተስፋ
አዋፋት ሳይሰጉ
ሲበሩ ሲቀዝፉት ፥ በላዩ ሲዋኙ
ንስንስ ነጫጭ ጌጦች
የዳመና ገጾች ፥ ገላው ላይ ሲገኙ
አንቺ ተደስተሽ
በፍፁም መፍለቅለቅ ፥ የዋልሽ ይመስለኛል
የሰማዩ ቀለም
ሰማያዊው መልኩም ፥ ምስክሬ ሆኗል።
ደግሞ ሌላ ጊዜ
ሰማይ መልኩን ቋጥሮ ፥ ደርሶ ሲያስገመግም
በመብረቅ ትርኢት
ብልጭ ድርግም ሲል ፥ ጩኸት ሲደጋግም
እዬመላለሰ
አሁንም አሁንም ፥ ሲያምቧርቅ ሲያጓራ
አዋፋት ሸሽተውት
እንሸሸግ ሲሉ ፥ በጎጆቸው ጣራ
ዛሬ ተናደሻል
ግልፍተኛ ቁጣ ፥ ወርሶሻል እላለሁ
የቋጠረ መልኩን
ከጩኸቱ ጋራ ፥ ሰማዩን እያዬሁ።
ደግሞ አንዳንድ ጊዜ
ዳመናን ሰብስቦ ፥ ሰማይ ሲዝረበረብ
ዶፍ ጥሎ በፍርጃ
ምድርን ሲያጨቀያት ፥ ገላዋ ላይ ሲሰንብ
የሀዘንሽ ምክንያት
ምሬትሽ ሳይገባኝ ፥ አለቀሽ እላለሁ
የእንባሽን ክብደት
በዝናቡ መጠን ፥ በዶፉ እለካለሁ።
ይሄውና እንግዲህ
ባፍቃሪ ልቦና
ውሎና አዳርሽን ፥ አይቼ ስመዝን
የውስጥሽን ስሜት
ደስታና ሀዘንሽን ፥ ቁጣሽን ስተምን
ሰማይ ነው ምስክር
በማይነጥፍ መልኩ ፥ የሚያሳዬኝ አንቺን፡፡

@getem
@getem
Mikiyas
1
በ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው
"የይሁዳ ገመድ" ግጥምን በኮንቴምፖራሪ ዳንስ ቪዲዮ በቅርብ ቀን ይለቀቃል።

@getem
@getem
@getem
እናቴ ኑሪልኝ
በንቆቅልሽ አፅናፍ በዘመን ቋጠሮ
በነፍስ ህቡዕ ስንኝ ምስጥረ ተፈጥሮ
በፍቅር ዓለም ቅኝት የቋንቋ ስድራት
ሊገልጣት አቅም ያለው ፍች የለም ለእናት።
ምንጭ ፦ #FB

@getem
@getem
@getem
በጁማኣ በረካ፤

በዛውያው ቂርኣት፤
በሶላቱ ነት ላይ፤
ርዚቅ ተሸክሞ፤ መለይካ ይወርዳል፤
አዛኑ ሲሰማ፤
እንኳን ከታች መንደር፤ ከላይ ይሰገዳል።

((( ጃ ኖ )))(

ሸጋ ጁምኣ!!!💚

@getem
@getem
@Nagayta
እውነት ሄድሽ በቃ?
(እዮብ ዘ ማርያም)
-
ምትወጃት ጨረቃ
ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ
ነብሴም እንቺን ለምዳ፣
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ
እውነት ሄድሽ በቃ?
ለቅሶ ይሰማኛል፣
የሚያነቡ ሰዎች ከፊቴ አያለሁ
አፈር ቡንን ይላል፣
መቃብር ሲቆፈር እመለከታለሁ
ምን እያረጉ ነው?
ምን እንደሚያደርጉ እኔ ምን አውቃለሁ
ድንዝዝ ብያለሁ!
መደንዝዝ ታውቂያለሽ፣
ሳይነቃነቁ ዝም ብሎ መገተር
ምንም ስሜት አልባ፣
በጥፊ ቢመታ ወይም ቢገፈተር
ደንዝዝ ብያለሁ አዎ ልክ እንደዛ
እንዲሁ እንደ ወዛ!
ፎቶሽን የያዙ፣
አሮጊት ሴትዮ ደረት ይመታሉ
እንዳንዶች በዕንባ፣
እህህ እያሉ ይንከራተታሉ
የማልቀስ
የማንባት
እነዚህ ስሜቶች እኔ ጋ የታሉ?
ፍርጃ
ፍዝዝ ብያለሁ ያላንዳች እርምጃ
ድንዝዝ ብያለሁ የነካኝን እንጃ!
በቆምኩበት ቦታ፣
እንደተገተርኩኝ ዕንባ ሳላወጣ
የለቅሶ የዋይታ፣
አሰቃቂ ድምፀት እየተጠጋኝ መጣ!
ድንገት ብንን አልኩኝ፣
ይደልቅ ጀመረ ልቤ በሀይል መምታት
ለሁለት ተከፈልኩኝ አነቃኝ ማመንታት!
በዚህ...፣
ዘላለማዊ ናት አትሞትም እሷ
በዚያ...፣
እመን
እመን
እመን
ከንግዲህ አትመጣም አፈር ሆኗል ልብሷ!
በጥርጥር መሀል
በማመንም መሀል ልቤ እየዋለለ
ዕንባዬ ጠብ አለ!
ጉም ዙሪያዬን ሞላው ጨለማ ከለለኝ
መሄድ መሞትሽን አመንኩኝ መሰለኝ!
ለራሴ አዘንኩኝ ባዘን ሆዴ ባባ
አምርሬ አለቀስሁ ታጠብኩኝ በዕንባ!
አይመስለኝም ነበር
በግዜ ምትከፍቺው የማቃብርን በር!
መውደድ ሳይዳብሰኝ ፍቅር ሳይነካካኝ
አልቀርብሽም ነበር፣
መሆንሽን ባውቀው እዚህ ድረስ ጨካኝ::
ላትመጪ ነገር
ላትመለሽ ነገር
ወዴት ሄጄ ልበድ፣
የልቤን ትኩሳት ምን ብዬ ልናገር?
ምትወጃት ጨረቃ
ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ
ነብሴም እንቺን ለምዳ፣
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ
እውነት ሄድሽ በቃ?


@getem
@getem
@beppa_19
👍1
አንዱ ባንዱ ሲስቅ
በሃሳብ መጫወቱ
ትንቅንቅ ሙግቱ
ባልከፋ በበጀ
ስዉን ባደረጀ …
በየራሱ ጎራ
በሠራው ተራራ
በአተያዩ ዳራ
ሁሉ ከተኩራራ
ልቡ ከተዘጋ
አንጎሉ ከረጋ
ራሱን ካልበለጠ
ለዕውቀት ካላማጠ …
የራስን ማዳነቅ
በሌላው መሳለቅ
ምንድነው ልቀቱ?
የት ጋ ነው ጥልቀቱ?
እንዴት ያሳድጋል?
ማንን ይለውጣል?
አፍ ከጆሮ ሲልቅ
ስሜት ካሳብ ሲጠልቅ
አመክንዮ ይሞታል
ጆሮ ይገነዛል
ሙግት ክርክሩ
ድንቅ አዲስ ነገሩ
ይሆናል መጣያ
ጭቃ መቀባቢያ…
ሀሳብና አሳቢን
ነጥለን ካላየን
እንዱ ባንዱ ሲስቅ
ሲያላግጥ ሲሳለቅ
ጀምበሯ አዘቅዝቃ
እሷም በኛ ስቃ
በማይገባን ቋንቋ
አይቀርም መጥለቋ።
©ምህረት ደበበ

@getem
@getem
@beppa_19
°°°ግዜማ°°°
ግዜማ ጥበብ ነው
ቅኔን ያረገዘ ፤
ሌትና ቀናትን
በሰም የጠረዘ፤
በወርቅ ዝፋኑ
መለኮት የያዘ፤
እሞድሽ

@getem
@getem
@getem
'ከሽፍታ' የተሰረቀች ግጥም
(በረከት በላይነህ)

-----------
ገና!
ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤
ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ።

በዳዴ ዘመኔም፣
በ'ወፌ ቆመችም!'፤
አውዴ ክፉ ነበር ለወሬ አይመችም።

እንደ ሚዳቋ ነፍስ እንደ ነብር ጥፍር፤
ስጋትም- ጭካኔም-ነበር የዕውቀቴ ስር፣
"ተጨቆንኩ!"
"ተበደልኩ!"
"ተረገጥኩ!"
"ተገፋሁ!"
"ተቀማሁ!"።
መሬቱ ጠላቴ፤
ሰማዩ ብሶቴ።

ተስፋ ትዝታዬን ሊያጠፋ ለቃቅሞ፤
ባፈሙዝ ያየኛል ገዳይ ደጅ ቆሞ።

ወዘተ...
በእነዚህ 'ምግቦች' አድጎ ሰውነቴ፤
እኮ እንደምን አይሆን 'ጥርጣሬ' ሀብቴ?
መገርሰስ፣ መደምሰስ፣ ማሳደድ-ውበቴ?
ስለዚህ አይድነቅህ!
ቀርበህ ወደድከኝም፣ ርቀህ ጠላኸኝም፤
ገድዬህ ካላለፍኩ የኖርኩ አይመስለኝም።
@getem
@getem
#jeko