ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
((ፍትህ ሞተች አሉ))

መቸም አዛኝ የላት
መቸም ወዳጅ የላት
ደረት እየደቃ
ዋይ ዋይ ብሎ ሚያለቅስ፤ እንባ ሚያፈስላት።

ወዳጅ ዘመድ ሲሞት፤ ካንጀት ያለቀሰው
ፍትህ ሞተች ሲባል፤እንባ እንዴት ቸገረው።

ደስየ ደምሌ
@getem
@getem
#jeko
መገን
እጆች እጨብጭበው በነየ ወዳጃ
በንፍሮ መረባ በዱበርቲው ሀጃ
አሊም ባልዳበሰው ከንቱ መጋረጃ
አጀብ እያስባሉ ሀዲራቸዉ ሳይገባ
መወዳጅት ጠፍቶ ሆዳችን ሲባባ
አይብጅም ተብሎ ተደፍቶ አየሁት ንፍሮውም ሳይረባ !!!!!
ፈርሀን ይመር
መስከረም 01/2008

@getem
@getem
@getem
።።።።።።የምርቃና ግፉ።።።።።።
በረከት በላይነህ

የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ " ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ጻፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ።


@getem
@getem
@getem
ተሻገር ስትባል
:
ፍቃዱ ጌታቸው

<<ነገን አታያትም!>>
ብሎ ያለኝ ዶክተር
በቅጡ ቻው ሳይለኝ ፣ አጠገቤ ሞተ
ሳይንሳዊ እውቀቱ
የለገሰው ትንቢት ፣ ዓይኔ ስር ሻገተ
መቆም ለመሻገር ፣ ዋስ ላይሆን ታወቀኝ
ልቤም በቅፅበቷ
በሞት ላይ ተበተ!
:
ዶክተሩን ያመኑት
ለፍትሐቴ ቄስ ለእርቃኔ ከፈን ፣ ተግተው ሲያሰናዱ
የፀኑት ሊያተርፉኝ
ተዓምር እንዲሆን ፣ ደጀ ሰላም ሔዱ።

ተዓምር ገዘፈ
ነገ ዛሬ ሆነች ፣ ተገኘሁ በእቅፏ
ተነጥቄ ወጣሁ ፣ ከሟቾች ወረፋ!
:
የእድሩን ጥሩንባ ፣ የፀሐይ ሳቅ ውጦት
የወዳጅን እንባ ፣ መፍነክነክ ተክቶት
የሐሴት ፅንሰቱ ፣ ካልጋዬ ሲወለድ
አየኋት ረፍቴን
ካረዳኝ ተናንቃ ፣ አስከትላው ስትሔድ።

ሌላ ቀን
ሌላ እድል
ሌላ መኖር አቅፎኝ ፣ አዲስ ፀሐይ ፈካ
ከትንቢት ይልቃል
ከእውቀት ይመጥቃል
በሕይወት ሲፈልግህ ፣ የእጣህ በረካ።

@getem
@getem
@getem
ነግሬሽ ነበረ !
(በላይ በቀለ ወያ)

ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን ያስደምማል
ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል
ነግሬሽ ነበረ፡፡
ሰማይ ሚያህል ጭንሽ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል
ምን ተራራ ቢያህል...
ጡትሽ አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም፡፡
ነግሬሽ ነበረ
የናትነት ስሟ ፣
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ፡፡
ነግሬሽ ነበረ
አትስደበኝ እያልሽ ፣ የነገርኩሽ ሁሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመስላሉ፡፡
@getem
@getem
#jeko
1
====================

ለፍቶ የሚያበላው፤
ምስኪኑ ባሪያ እንደወጣ ቀረ፣
ያ'ባወራው ጎጆ፤
ማሟሻ የራቀው
የልጁ ላንቃ ደጅ ተከፍቶ አደረ፡፡

@abiye12

@getem
@getem
@getem
Forwarded from Sunset Hiking
Event - Goshu Meda Camping Trip ⛺️

Date :- February 1 - 2, 2020 🎈

Departure Spot - Piassa Tayitu Hotel 🎪

Departure Time - 2:00Am Local time 🚩

Price - 1199.99 🙈💰

🎉🎊Package 🎋🎊

🔵🚍 - Tourist level Bus
🔴⛺️- Tent, campfire &tea
⚫️🍝 - Traditional Roasted meat ( 🐏), Lunch and snaks🍟🍤
⚪️ 2 liter Bottled water
🔵 Park entrance with Guide
🔴photograph 📷

Brought to you by Sunset Hiking Group
for more join the
🔸channel @sunsethiking
🔹the group @sunsethike
🔻📷 @sunsetphotography

🎫 tickets available at
@Paappii
@thomaskagnew
@useryise
@Chere_daregot
ለጁምኣችን!
💚

የሰከነች ሰፊና...
°°°°°°°°°°°°°°°°
ከባለቅኔው ሙሉ ጌታ ተስፋዬ ((አያ ሙሌ))የልቤ❤️❤️
ከሰከነች ሰፊና ግጥም የተጨለፈች ቡራኬ!!
•••••••••••••••••••
.....
....... ........
.......
...... ..........
ምን አለ የተሰወረ?
እህ... ብሎ ሰምቶ፣
አይቶ ገምቶ ተስማምቶ፣
እንደ ጎኑ ካደረ፣
እንዳቅሙ ከሰደረ፣
ምን አለ የተሰወረ??
ምን አለ??
እራሱን ካልበከለ፣
ምን አለ የታቀበ? ምን አለ የተከለከለ??
ለኩርማን ሲል፡ በርግማን ካልተቀጨ፣
...........................ባለፈው ከተቆጨ፣
ደጀ ሰላም ከልተዳፈረ፡ አረጋዊ ካላንጓጠጠ፣
.....................ሰው ላይ ካላፈጠጠ፣
እኩያን* አክብሮ፡ በክፋት ካላፈጠጠ፣
ባለቤቱ ካላጋደለ!
ምን አለ የተሰወረ? ምን አለ የጎደለ??
ምን አለ የማያምር??
ከሳሽ መንፈስ ተጣብቶት፣
የሚይዘውን የሚጨብጠውን አሳጥቶት፣
እሱ ሽቶት፡ ሞት ሸቶት፣
በቁሙ ካልበከተ፡ ይቅር ሲሉት የማይምር፣
ምን አለ የማያምር??
ምን አለ??
በእብለት፡ የሰይፍ ስለት ካልነከሰ፣
ውድ ሊሆን ሲማፀደቅ፡
የማነህ የሚለው አጥቶ፡ ጥምቡን እስኪጥል ካረከሰ፣
ቀጥ... ብሎ ያልጠና፡ ምን አለ ያነከሰ??
ምን አለ የሚያስፈራ??
ውል ጥሶ፣
ምራን በጥሶ፣
የትም ባክኖ ካልመከነ፣
በራሱ ካልጨከነ፣
°°°°°°°
እንደ መልካም የስንዴ ዘር፡
ጎልቶ አብቦ በጊዜ በስሎ ካፈራ፡
እንኳን ፍራት ሀፍረት የለም!!
°°°°°°°
በሰው ዳስ ድግስ፡
ልጁን ሊሞሽር፡ ጎምበስ ቀና ካላለ፣
የሚያሳፍር ምን አለ??
ባይን አዋጅ ሚዛን እየመተረ፡
በሰፋው ቁና እየሰፈረ፡ ዋጋ ሊተምን ካልቃጣው
እንኳን ካገር ገበያ፡
ማነው? ከእድር ከመንደር የሚያወጣው??
ምን አለ የተሰወረ??
ምን አለ የሚያስጨንቅ? ሌት እንቅልፍ የሚነሳ??
አንደበቱ ካልወሰለተ፡ እጁ የሰው ካላነሳ!!
ስጋትም ውጋትም፡ ምን አመጣው??
ሆዱን በእህል፡ ልቡን በልህ ከቀጣው
ነውሩን ሸንጎ ካላወጣው፣
ጭንቀትማ አይታሰብም!!
ሰው!... እንኳን ሰው ፡ ወፍ ያልዘራውን አይሰበስብም!!
ምን አለ ያልተፈቀደ??
ዓይን ያለመውን፡ ልብ ካቀደ!!
...
.....

ሸጋ ጁምኣ!💚

#4ቀን🎂🎂

@getem
@getem
@balmbaras
#ለቅዳሚታችን መዳረሻ!


አሁን በዚች ቅፅበት ከሚወዷት ጋራ!!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
(1)
{{ .................ርበሽኝ ነበር፣
..................ተጠምቸሽ ነበር፣
አቀፍኩሽ ታቀፍሽኝ፡ በእቅፍሽ ሞትኩኝ፣
ሳምሽኝ ተሳምኩልሽ፡ ባሳሳምሽ ዳንኩኝ፣
በልብሽ ላይ ነገስኩ፡ ከሰማይ ገዘፍኩኝ፣
..................ረክሸ ነበር፣
ባረክሽኝ ተቀደስኩ!!
በሙቅ እቅፍሽ ውስጥ፡ ዘላለሜን አበብኩ፣ }}
...............!!
( 2)
{{ .........
በፍቅር አምልኮ፡ በውበት ውዳሴ፡ ልቡ ለሚሰየፍ፣
ከገነት ይሞቃል፡ ከኤዶም ይልቃል፡ የሸጋ ሴት እቅፍ፣
...............ከጊዜ የላቀ፣
...............ከቦታ የራቀ፣
...............ከሐቅ የረቀቀ፣
በሚያፈቅሩት እቅፍ፡ በሚወዱት ጉያ፡ ውበት ለመመስጠር፣
ምጥጥ ነው እንጂ፡ ጉርስ ነው እንጂ፡ የሸጋን ሴት ከንፈር፣
.................ግሩም እንኮይ ገላ፣
.................ጥዑም የሸት ዛላ
..................የወይን ዘለላ፣
እንጆሪ የሚያስንቅ፡ የሸጋ ሴት ከንፈር፣
ሳም ጉርስ አርጎ፡ ህያው ሁኖ መኖር፣
..........እቅፍ ነው እንጂ፣
..........ጉርስ ነው እንጂ፣
..........ምጥጥ ነው እንጂ፣
ለዘላለም ህይወት፡ ለዘላለም ደስታ፣
ከነፍስያ ዘልቆ፡ እስኪያብብ እፎይታ፣
በሸጋ ሴት እቅፍ!!
የኤሊያስን ትንቢት፡ የያሱን ተአምር፣
የዮብን ትእግስት፡ የዳዊትን መዝሙር፣
የሙሴን ትእዛዝ፡ የአሮንን በትር፣
ይን ሁሉ የሚያስንቅ!!
ጊዜ የማይሽረው፡ ዘመን የማይረታው፡ ውበት ለመሸመን፣
በመውደድ ሉባንጃ፡ በፍቅር እጣን ጭስ፡ ዘላለም መታጠን፣
እዚጋ ሞት የለም!!
.....በጥዑም መዓዛ፡
.....በፍቅር እጣን ጭስ ፡ ውብ ህይወት አብቧል፣
እዚህ ህመም የለም፡
.....በጡት ተሞሽረው፡
.....ከንፈር እየሳሙ፡ ጤንነት መንጭቷል፣
እዚህ መድሎ የለም፡ ባፈቀሩት ገላ፡ ፍትሕ ፀድቆ አሽቷል።
እዚህ ሀዘን የለም፡ በታቀፉት እቅፍ፡ ሀሴት ተደግሷል፣
ካፈቀሩት ገላ፡ እጣን አለ ከርቤ፡ ፅድቅ የከተበ፣
ከሚወዱት ገላ፡ እውነት አለ ሠላም፡ አፍርቶ ያበበ፣
........አሁን በዚች ቅፅበት!!
........ከሚወዱት ጋራ፡ መዋሀድ መጣመር፣
........ሠርክ መቀደስ ነው፡ ህያው ሁኖ መኖር፣


#እብዱ
ሸጋ ምሽት!💚

"ናካይታ"💚

@getem
@getem
@balmbaras
ወገግታ የስነ ጽሑፍ ወ ሥዕል ምሽት
ሰኞ ጥር 18 በ ሃገር ፍቅር ትያትር ቤት ከ 11:00 ጀምሮ

@getem
@getem
#እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


ሰውነት!!!!!


የመቅደሱ ማእጠንት፤
የዛውያው ሃጃ፤
በጨለማው ዘመን ፤
በሰው በላው ወራት፣
ጸዳል እየረጨ፤
በእዝነት ወጋገን ላይ፤ ካልሰራ ብርሃን ፤
ምን ሊረባኝ ከቶ ፤
ሰው አልባ መሻኢክ፤ አልቦ ፍቅር ካሃን።።


ጽና ሰውነቴ፤
በርታ አዳምነቴ፤
ቱባ ወረትህን፤
ውብ ሰውነትህን፤
በሰውአዊ ልክህ ፤ መልክህን አስከብር፤
ከሰው ልኬት ወርዷል ፤
በእኔ ብቻ ዜማ፤
በእኔ ብቻ ስሙኝ፤ ሰው እያዳፈነ ፣ ዛውያና ደብር።
አለም አስጠልቶን፤
ዱኒያ እየነጀሰን፤
ልንጣዳ ብለን፤
ብንገባ ከለዋ ፤ ብንሸሽ ወደ ገዳም ፤
ኑ ያለን ከዳሚ፤
ኑ ያለን ዘካሪ፣
በዚያም ገፍቶ ጣለን፤ በዚያም ገፍቶ አስወጣን።


የቤተስኪያኑ ራስ፤
የመስጂዱ ሚናር ፤
ከሰው ስፍር በታች፤
ከሰው ድካ በታች ፤ ከሆነ ሚዛኑ፤
እነ አባ ግርታ፤
ቅዳሴውን ተውት፤
ሶላቱንም ተውት፤
በጉድል ስፍራችሁ፤
በዘንባላው ቁና፤ ተበላሽቷል ቀኑ ፤
ለሰማይ ያሰበው፤
ሸቃጭ ሆኖ ቀርቷል፤
ሃቅን እየሸጠ ፤ ሃቅን እየገፋ ሁሉም ለወገኑ ፤
የአምልኮ ጸበኞች፤
ትሰሙኝ እንደሆን፤
ዛውያውን ተውት ፤
ደብሩን ልቀቁና ፤
ሰው በጎደለበት ሰው የሚል ሰው ሁኑ፤
አለበለዚያማ፤
ሰውን ለማፋረስ፤
ሃገር ለመነጀስ ፤ ጠማማና ክፉ መች አነሰው ቀኑ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
"ናካይታ"💚
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!
#3ቀን🎂🎂
@getem
@getem
@Nagayta
1
እስቲ ልጠይቅህ?
(ሚካኤል አስጨናቂ)
#ጉልበት በአዕምሮ ላይ ክንዱን ሲያበረታ
የሴትነት ክብር
እንደዋዛ ታይቶ ፣ በነውር ሲረታ
ፅልመት ገሀድ ወጥቶ ብርሀን ሲገታ
ይሄን ሁሉ አይተን
ከዳስ ተቀምጠን
አልሰማንም እያልን በዝምታ እንዳናልፍ
እንባ ባህር ሆኖ ተንጣሏል ከበራፍ ።
አዎን በዚህ ወራት!
የአያት የአባቶቼ ተረት እውን ሆኖ
በዝንጀሮ ዳኛ በገደል ፍትህ ቤት እውነቷ ተዳፍኖ
ከዳር ተቀምጣ ለቅሶ በምትዘራ
በአንዲት ምስኪን ሴት ብዙ እውነታዎች ሀገር ተወጥራ
እንዲሁ እንደዋዛ ፣ እንዲሁ እንደዘበት
ውለታዋን ሽሮ ፣ ክዶ ለመገኘት
እናት እያነባች ...
አልሰማሁም ብሎ ፣ ዋሽቶ ለመቧለት
ይቻላል ወይ እውነት ??

#ፍትህ ለታገቱ ሴት እህቶቻችን

@getem
@getem
@getem
ሰይጣን ቅጣትህ ነው



"ሀጥያቴ" ነው አትበል
ኮሽ ባለ ቁጥር
" በደሌ" ነው አትበይ
ኮሽ ባለ ቁጥር


ሀጥያቴ በደሌ
'ምትሉት ሽንገላ
ከጀርባው ያዘለው

ሰይጣን አሳሳተን
የሚል አንድምታ አለው

እንዲህ ነው እንግዲህ
ሰው ድንቁርናውን
ማመን ሲቸግረው
ጥፋቱን በሙሉ
በድንቁርና ልጅ
ማሳበብ ነው ሚያምረው


እንዳውም እንዳውም
ማንም ተነሳስቶ
ስሙን እንዳያጎድፈው
የሰይጣንን ትርጉም
እዚ ታች ልፃፈው


በድንቁርናህ ልክ
የ -ተ-ፈ-ለ-ፈ-ለ-ው
አሳሳችህ ሳይሆን
ሰይጣን ቅጣትህ ነው
በካሽ የምትከፍለው


አምደማሪያም ጠይብ(ፊዳው)

@getem
@getem
@saveme24
👍1
ሰይጣን ቅጣትህ ነው



"ሀጥያቴ" ነው አትበል
ኮሽ ባለ ቁጥር
" በደሌ" ነው አትበይ
ኮሽ ባለ ቁጥር


ሀጥያቴ በደሌ
'ምትሉት ሽንገላ
ከጀርባው ያዘለው

ሰይጣን አሳሳተን
የሚል አንድምታ አለው

እንዲህ ነው እንግዲህ
ሰው ድንቁርናውን
ማመን ሲቸግረው
ጥፋቱን በሙሉ
በድንቁርና ልጅ
ማሳበብ ነው ሚያምረው


እንዳውም እንዳውም
ማንም ተነሳስቶ
ስሙን እንዳያጎድፈው
የሰይጣንን ትርጉም
እዚ ታች ልፃፈው


በድንቁርናህ ልክ
የ -ተ-ፈ-ለ-ፈ-ለ-ው
አሳሳችህ ሳይሆን
ሰይጣን ቅጣትህ ነው
በካሽ የምትከፍለው

@getem
@getem
@getem
#አምደማሪያም ጠይብ(ፊዳው)
1
የታወሩ ነፍሶች
©ሲራክ
አንባቢው ጀግና ሰውዬ
ባለ ስል አእምሮ ያለው
ከቅኔ አሸት መፅሀፎች
ያሻውን ቀጥፎ የበላው
አውሮፓን በቀኙ ረግጦ
ሀገሩን በግራ አሳልጦ
እራሱን ማንበብ ያልቻለው
ምን ልቦናን ቢያጣ ነው????
======//=======
@siraaq
#
@getem
@getem
@getem
     #ቀናሽ አሉ
በቆምሽበት ሌላ ሳቆም
ማዶ ሆነሽ አየሽ አሉ
ስሜን ጠራሽ ጮሽም አሉ
አውለበለበሽ በጅሽ ሁሉ
በእንባ ጠፋ የአይንሽ ኩሉ

ግን ስህተቱ አንቺ ጋ ነው
አጉል ቅናት መለየት ነው
ሺ ቢመጣ ሚወደድ ሰው
ንግስቴ አንቺ
 ፍቅሬ እኮ ላንቺ ነው

                 ተፃፈ በብላቴናው ብዕር
--------------//----------
@getem
@getem
@getem
:::::::::::ሐሌታ ስርዞች:::::::::::

በኖርክበት ምድር ባለህበት መሬት
ለማኖርህ እንጂ ለመሮር አትሙት
ስለየቱ ገላህ ካፈር ለተሰራው
ሰገነትም ሆነክ ራስህን አድነው
ከወረተኛ ሰው የታነፅኩኝ ልባም
ህመሜን ለመፃፍ ወረቀት ምቃርም
ካሌታዎች ተርታ ከልለችው አለም
ወይ ኖሬ አላለኩኝ ወይ ሞቼ አላወኩም

@getem
@getem
@getem
#ሳምሶን_ጌቱ
Event - Goshu Meda Camping Trip ⛺️

Date :- February 1 - 2, 2020 🎈

Departure Spot - Piassa Tayitu Hotel 🎪

Departure Time - 2:00Am Local time 🚩

Price - 1199.99 🙈💰

🎉🎊Package 🎋🎊

🔵🚍 - Tourist level Bus
🔴⛺️- Tent, campfire &tea
⚫️🍝 - Traditional Roasted meat ( 🐏), Lunch and snaks🍟🍤
⚪️ 2 liter Bottled water
🔵 Park entrance with Guide
🔴photograph 📷

Brought to you by Sunset Hiking Group
for more join the
🔸channel @sunsethiking
🔹the group @sunsethike
🔻📷 @sunsetphotography

🎫 tickets available at
@Paappii
@thomaskagnew
@useryise
@Chere_daregot