ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የዋርካ ስር ጤዛ
ሲራክ
ገጣሚ እና አንባቢ ሲራክ
@siraaq
#
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)


በተራበው ጎኔ፣ በተጎዳው ኪሴ
እኔም ሰው ነኝና፣
የከንፈር ወዳጄን ተጠምታብኝ ነበሴ
የጥምቀት ለት ሎሚ፣
ኪሴን በሚጎዳ በሚነርት ዋጋ
ይሁን ብየ ገዛሁ፣
ደረቷን ልመታ የዛችን ውብ ሸጋ።

ሎሚውን በእጄ ያዝኩ
ኮረዳዋን ፈለግኩ
ባ'ይኖቼ አማተርኩ

ከኋላዋ አየኋት...
ፀጉሯ ሹሩባ ነው፣ ፊቷ አይታይም
ኋላዋ ካማረ...
ፊቷ ምንም ይሁን እኔን አይጨንቀኝም

ዳሌዋ... ቢዮንሴን ያስንቃል
በንቅልፍ የቧዘዘን አጣድፎ ያነቃል
ስንት የወጣባትን፣
የኛን ሳተላይት ከቻይና ያመጥቃል (አንጥሮ😂)

ወገቧ... አካበድክ ባትሉኝ
ከቀጭኗ እግሬ ሚወፍር አይመስለኝ

ወይኔ ሹሩባዋ
ለመግለፅም እንኳን አንደበትን ያስራል
በቆሙበት መሬት አፍዞ ያስቀራል።

ወደራሴ መጣሁ...
ልወርውር አልወርውር?
ልወርውር አልወርውር?

ወረወርኩ...
ድምም... እዛው ዳሌዋ ላይ
አሟት ዩን ደስ ብሏት ዞር ብላ ብታይ
የኔ ልብ ደንግጣ ልትበር ወደ ሰማይ

እየሮጠች መጣች፣
እያነፈነፈች ትንፋሿ እስከሚያጥራት
ክፉ አስባ ይሆን ልሩጥ ልጠብቃት?

ደረሰች...
ፊቴ ከመድረሷ፣
አንድ ጊዜ በጥፊ አወላመመችኝ
ወደላይ ወደታች፣
መላ ሰውነቴን በደምብ ቃኘችኝ
ወደግራ ጆሮየ በጣም ተጠጋችኝ

ጊዜው የድንጋይ ነው ሎሚ አታባክን
ኪስህን አሟጠህ፣
በገዛኸው ሎሚ ፈፅሞ አትጨክን
አሁን ሳናቅማማ ቶሎ እንሽጠው
ይሄ ውድ ሎሚ፣
ላ'ዲሱ ጎጇችን ትልቅ መሰረት ነው
ብላ አቀፈችኝ
እሰየው ዘንድሮ ለኔም ተሳካልኝ።

@getem
@getem
#jeko
" #ባውቶማቲክ_ግዜ#መሸከሙ_ጓንዴ ...
#አይከብድም_ወይ_ጓዴ"

ይብላኙን ለነሱ…
በጠዋት ገስግሰው ፥ አንድ ኪሎ ሎሚ ፥ ገዝተው ለደረሱ
ያውም በዚ ግዜ
ሎሚ ጥሪው ከብሮ ፥ ከጅ ላይ በጠፋ ፥.... በተወደደበት
ሜክ አፕ የለቀመው ፥ ሴቱም እንከን የለሽ ፥ ውበት በደፋበት
ወንዱም አቅሉን ስቶ
ሎሚ በተረሳው ፥ የመኪና ቁልፉን ፥ እያነጣጠረ
አይፎኑን ደረት ላይ ፥ ሰዶ እያነጠረ

"አይፎን ብወረውር .....እስፖንጇን መታሁት
አወይ ተሳክቶልኝ......ጡቷን ባገኘሁት"

በሚል ሀርሞኒካ .....ትዳር የሚናፍቅ
አልሞ ተኳሿ .....ከሷ ብዙም ሳይርቅ

እያረጋገፈች ከመሬት አንስታ
የላክልኝ አይፎን .....የሰደድከው ቁልፉ
ከደረቴ ነጥሮ....መሬት መዘርገፉ
አንተም ጎበዝ አጥቂ.....
ጎበዝ ተከላካይ ፥ መርጦ ገራም ልብህ የመሸናነፉ
ማመላከቻ ነው ፥ ቅኔው ሲተረተር ፥ እንዲያው በግርድፉ
ለዚህ ....ለዚህ እንጂ ፥ ዱላ ለመመከት
ውበት ጎሎት አይደል
በል ነዳጁን ስጠው ፥ ቦታ እንያዝ እና ፥ ማማሩን ተመልከት
ብለው ተያይዘው ፥ ከስርፋው ታበሱ
ያንን ሁሉ ሎሚ ፥ የሸመተው ጉብል ፥ ለማን ይስጠው እርሱ
በዚህ የሀሳብ ዚቅ....... እንደተዘፈቀ
ታቦቱን ያጀበ ፥ የሞንሟኖች መንጋ ፥ ሳይገላመጠው ከተራው አለቀ
ይህን እያየሁኝ....
ከሎሚም ፣ ከቁልፉ ፥ የቀረሁኝ እኔ
ጉብታው ላይ ቆሜ ፥ ሲወጣና ሲወርድ ፥ አየዋለው ባይኔ
ድንገት ፥ ተስፋ ራሱ ፥ ተስፋ ቆርጦ ሳለ
ለመሄድ ሲነሳ ፥ የኪሎ ዘንቢሉን ፥ እንደጠቀለለ
አምሮት የምታጭር...ጥበቃ እምትገታ
ካለችነት ቦታ ፥ በፍጥነት ተነስታ
ወደርሱ ቸኮለች ፥ ተሳልሞ ለመሄድ ፥መነሳቱን አይታ
ለጥቂት ሰአታት ፥ አንድ ላይ አወሩ
ፈገግ አለች እሷ......ተፈታ ግንባሩ
ነጠላ ሸፍና ፥ እጁን ጨበጠችው
ያንን ሁሉ ሎሚ ፥ አንድ ራሷ መጥታ ፥ እሷው ወሰደችው።

ይህኔ...
የማላውቀው ጓዴ
በለስ ቀንቶት ባየው ፥ በባከነው አይኔ
እሰይ..........አልኩኝ እኔ....
እንደአቅሙ ጣጥሯል ...
አልተሰበሰበም ...በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ፥ አዝኖ ልክ እንደኔ
ከቆመ የዳኸ ፥ አስር እጅ እንዲሻል ፥ መክሮኛል ዘመኔ ።

#ኋላ_ግን_ስሰማ .... #ልጅቷ_ጭማቂ_ቤት_አላት...(😁😁😁)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
እኔማ እጠርጋለሁ!!!!


ቀይ ባህርን ከፍሎ፤
ባሳለፈን ጊዜ፤
በሰይፉ እየመራ፤
ባህሩን አቁሞ፤ ፀጥ አርጎ ወጀቡን
በክንፉ ለመራኝ፤
እንኳንስ በቁሜ፤
ከዊልቼሬም ሆኜ፤
እጠርግለታለሁ፤
ለታቦቱ ክብር፤ ጎዳና መንገዱን፤
እጠርግለታለሁ፤
ሚካኤል ሲመጣ፤
በሁለት እግሮቼ፤ እንድቆም አውቃለሁ።


((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@Nagayta
"ይድረስ ለኔይቱ እንስት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
************
እቴዋ መቀነቴ
ድምቅ ዓለሜ
በግብርሽ ክሳሜ
እምዘልቅ ቆሜ
ወና ነው ሌማቴ ከንቱነው ባዶነት
እኔ እምትወክል ሰርጻ እማትገባበት

በአፍላ ጅማሮ የአፍታ እድሜዬን
ፈትለሽ ላትቋጪው አልቦ ክዳን ሕልሜን

እቴዋ መቀነቴ
አንቺ የሕዋሴ ባህር ኃዳፍ
የሥጋ ነፍሴ መዳፍ
በሸክላ ሰሪው የአፈር ክምር
ባንቺነትሽ ግብዓት እኔነቴ ሲጣመር

ምነው ግና?
ምነው ግና? ስንፍ ሆነብኝ
ሳልጀምረው ያ ውዳዴሽ አበቃብኝ።

ምነው ግና?
ምነው ግና?
በፍቅራችን ቀነ ውልደት ሕልፈታቱ የታወጀ
በቅምጥናው አሉታነት ለዘመናት የደረጀ
ምነው? ምነው? ቅ.....ር.....ባ.....ታ.....ች.....ን ባጀ ።
@getem
@getem
@poem_with_mela
#ተነድፈሽ_ክበሪ
:
:
እኔ አልነደፍም የሚለው ፉከራ
በገዛ አንደበትሽ በኩራት ሲወራ
ካንዴም አስር ጊዜ ደርሶ ሰምቻለው
ትክክል ነው ብሎም የሚያጎበጉብ ሰው በቅርብ አይቻለው።
:
:
እውነት ነው ወይ ብዬም በዙሪያሽ ያሉትን ዞሬ ሳጤናቸው
መላከፍ ነው እንጂ መንደፍ የማይችሉ ተራ ዝንቦች ናቸው።
:
:
አፍኜው ነው እንጂ ድሮም ያንቺ ነገር ያንገበግበኛል
ከንቱ ፉጨት ከቦሽ መኩራትሽ ገርሞኛል።
:
:
ከ ዐጀቦችሽ አንፃር መደምደምሽን ሳይ አናገረኝ እንጂ የሆዴ መከፋት
ባንቺ አልተጀመረም አደባባይ ቆሞ በጀሌ ተከቦ አጉል ጉራ መንፋት።
:
:
እውነት እውነት ስልሽ ያለመነደፍሽን ሚስጥሩን ላወቀው
ልክ እንደኔ ሁሉ ሆድ ቢብሰው እንጂ ቅንጣትም አይደንቀው።
:
:
ይልቁን አንቺ ሴት አንዣባቢሽ በዝቶ እንዳትዘናጊ
የማሩን እንጀራም ያንቺ እንድታደርጊ
ተነድፎ ለመክበር በይ ከንብ ተጠጊ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu

@getem
@getem
@getem
#ጌታ የተጠመቀብሽ

በጥምቀት በዓለት ቀሚስ ይበጣጠስ
ለኔ ጥምቀት ጊዜ ፍቅርን መበጣጠስ
  ለጌታ ጥምቀት ለት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሴጣን ይባረራል
 ለኔና አንቺ ፍቅር ግን ለጥምቀት በዓል ለት
  መለያየት የሚል ክፉ መንፈስ ወርዷል
ባብሮነት ጎዳና ካንቺ ልሆን ብዬ
በስምሽ በጥምቀቱ አንቺዬ
ምን ጉድ አሰማሽው ለዚ ለጆሮዬ
   ጌታ የተጠመቀብሽ ወቧ የኔ ባህር
     አልኩልሽ ስብርብር
    ጭንቀት አደረገኝ ውርር
ሚያለያየን ነገር ሚያራርቀን ነገር በዛ ብለሺኛል
መሆንን ከፈራሽ እኔ ብላቴናው ምንስ ይሻለኛል
  ጌታ የተጠመቀብሽ
ከልብሽ ከሆነ በቀኑ ሚካኤል እስቲ አንዴ ማዩልኝ
       ምለሽ ከተገዘትሽ እቺን ቅኔ ፍቺ እንደው በማልሺልኝ
ፍቅርን ማግኘት ስሻ
መፅሀፍ ቅዱስ ብሻ
ከቅዱስ መፅሀፍ ገፅ ያዝኩኝ ፍተሻ
      ጌታ የተጠመቀባት ይለኛል አንዱ ገፅ
       ተነስቷል ያለችው ትንሳኤን አብሳሪ ይለኛል ሌላው ገፅ
የእዳ ደብዳቤ ባንቺ በባህሯ ዛሬ እኮ ተፋቀ
መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሴጣንም በሸቀ
       በትንሳኤው ጊዜ
      መንፈስ ቅዱስ አረገ
    ዲያቢሎስ ታሰረ ክርስቶስ በደሙ ሰውን ከሲኦል ታደገ
             
ተፃፈ በብላቴናው ብዕር

@getem
@getem
👍1
"የመረጨት ስምረት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
************
በባሕረ ቡራኬው
በጥባሌ ጥማቄው
ሕዝበ አዳም ፍጥረቱ
በንጋት ጉዞ ፍሰቱ
ምራቄውን ሰንቆ
እርኩስናውን አርቆ
በእግዚኦታው ተማጽኖ
ዕምንተ ክሩን ጎንጉኖ

ሲተም በትማሜ ዥረት
ለይቅርታ ለበረከት
ለጉዳሌው ጉድል ሙሌት
ውዳሴውን ሊደርስበት
በዓለ ክብሩን ሊነግስብት

የእመቤቴን ቸርነቷን
የምልጃዋን ተአምራቷን
ሊነፍስበት ደግነቷን
ሊጸናበት መሠረቷን

አደግድጎ በነጠላ
በጧፍ ከርቤ በዣንጥላ
ስዕለቱን ለምህላ
መባ ሲሰጥ ፍጡር ሁላ ።
ሻማ ዘቢብ ውብ ካባውን
የምስጋና በረካውን
ዕጹብ ሊያደርግ መከራውን።
በቀኑ ስምር ቀኑን ሰርቶ
ከእጦት ይልቅ አግኚ ሞልቶ
በአንድነት ግምድ ግፍፊ ዓለም
አንዱ ባንዱ ሲተራረም
ሕብር ሸማ ፍቅርን ሲቀልም
ድምጻችን ላይነጥፍ ተሰማ
ከሰማየ ሰማያት ከዘለዓለሙ ከራማ
አዬ ጥምቀት የነፍስ አርማ ።

ተጻፈ:-11/05/2012 ዓ.ም
@getem
@getem
@poem_with_mela
((ፍትህ ሞተች አሉ))

መቸም አዛኝ የላት
መቸም ወዳጅ የላት
ደረት እየደቃ
ዋይ ዋይ ብሎ ሚያለቅስ፤ እንባ ሚያፈስላት።

ወዳጅ ዘመድ ሲሞት፤ ካንጀት ያለቀሰው
ፍትህ ሞተች ሲባል፤እንባ እንዴት ቸገረው።

ደስየ ደምሌ
@getem
@getem
#jeko
መገን
እጆች እጨብጭበው በነየ ወዳጃ
በንፍሮ መረባ በዱበርቲው ሀጃ
አሊም ባልዳበሰው ከንቱ መጋረጃ
አጀብ እያስባሉ ሀዲራቸዉ ሳይገባ
መወዳጅት ጠፍቶ ሆዳችን ሲባባ
አይብጅም ተብሎ ተደፍቶ አየሁት ንፍሮውም ሳይረባ !!!!!
ፈርሀን ይመር
መስከረም 01/2008

@getem
@getem
@getem
።።።።።።የምርቃና ግፉ።።።።።።
በረከት በላይነህ

የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ " ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ጻፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ።


@getem
@getem
@getem
ተሻገር ስትባል
:
ፍቃዱ ጌታቸው

<<ነገን አታያትም!>>
ብሎ ያለኝ ዶክተር
በቅጡ ቻው ሳይለኝ ፣ አጠገቤ ሞተ
ሳይንሳዊ እውቀቱ
የለገሰው ትንቢት ፣ ዓይኔ ስር ሻገተ
መቆም ለመሻገር ፣ ዋስ ላይሆን ታወቀኝ
ልቤም በቅፅበቷ
በሞት ላይ ተበተ!
:
ዶክተሩን ያመኑት
ለፍትሐቴ ቄስ ለእርቃኔ ከፈን ፣ ተግተው ሲያሰናዱ
የፀኑት ሊያተርፉኝ
ተዓምር እንዲሆን ፣ ደጀ ሰላም ሔዱ።

ተዓምር ገዘፈ
ነገ ዛሬ ሆነች ፣ ተገኘሁ በእቅፏ
ተነጥቄ ወጣሁ ፣ ከሟቾች ወረፋ!
:
የእድሩን ጥሩንባ ፣ የፀሐይ ሳቅ ውጦት
የወዳጅን እንባ ፣ መፍነክነክ ተክቶት
የሐሴት ፅንሰቱ ፣ ካልጋዬ ሲወለድ
አየኋት ረፍቴን
ካረዳኝ ተናንቃ ፣ አስከትላው ስትሔድ።

ሌላ ቀን
ሌላ እድል
ሌላ መኖር አቅፎኝ ፣ አዲስ ፀሐይ ፈካ
ከትንቢት ይልቃል
ከእውቀት ይመጥቃል
በሕይወት ሲፈልግህ ፣ የእጣህ በረካ።

@getem
@getem
@getem
ነግሬሽ ነበረ !
(በላይ በቀለ ወያ)

ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን ያስደምማል
ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል
ነግሬሽ ነበረ፡፡
ሰማይ ሚያህል ጭንሽ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል
ምን ተራራ ቢያህል...
ጡትሽ አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም፡፡
ነግሬሽ ነበረ
የናትነት ስሟ ፣
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ፡፡
ነግሬሽ ነበረ
አትስደበኝ እያልሽ ፣ የነገርኩሽ ሁሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመስላሉ፡፡
@getem
@getem
#jeko
1
====================

ለፍቶ የሚያበላው፤
ምስኪኑ ባሪያ እንደወጣ ቀረ፣
ያ'ባወራው ጎጆ፤
ማሟሻ የራቀው
የልጁ ላንቃ ደጅ ተከፍቶ አደረ፡፡

@abiye12

@getem
@getem
@getem
Forwarded from Sunset Hiking
Event - Goshu Meda Camping Trip ⛺️

Date :- February 1 - 2, 2020 🎈

Departure Spot - Piassa Tayitu Hotel 🎪

Departure Time - 2:00Am Local time 🚩

Price - 1199.99 🙈💰

🎉🎊Package 🎋🎊

🔵🚍 - Tourist level Bus
🔴⛺️- Tent, campfire &tea
⚫️🍝 - Traditional Roasted meat ( 🐏), Lunch and snaks🍟🍤
⚪️ 2 liter Bottled water
🔵 Park entrance with Guide
🔴photograph 📷

Brought to you by Sunset Hiking Group
for more join the
🔸channel @sunsethiking
🔹the group @sunsethike
🔻📷 @sunsetphotography

🎫 tickets available at
@Paappii
@thomaskagnew
@useryise
@Chere_daregot
ለጁምኣችን!
💚

የሰከነች ሰፊና...
°°°°°°°°°°°°°°°°
ከባለቅኔው ሙሉ ጌታ ተስፋዬ ((አያ ሙሌ))የልቤ❤️❤️
ከሰከነች ሰፊና ግጥም የተጨለፈች ቡራኬ!!
•••••••••••••••••••
.....
....... ........
.......
...... ..........
ምን አለ የተሰወረ?
እህ... ብሎ ሰምቶ፣
አይቶ ገምቶ ተስማምቶ፣
እንደ ጎኑ ካደረ፣
እንዳቅሙ ከሰደረ፣
ምን አለ የተሰወረ??
ምን አለ??
እራሱን ካልበከለ፣
ምን አለ የታቀበ? ምን አለ የተከለከለ??
ለኩርማን ሲል፡ በርግማን ካልተቀጨ፣
...........................ባለፈው ከተቆጨ፣
ደጀ ሰላም ከልተዳፈረ፡ አረጋዊ ካላንጓጠጠ፣
.....................ሰው ላይ ካላፈጠጠ፣
እኩያን* አክብሮ፡ በክፋት ካላፈጠጠ፣
ባለቤቱ ካላጋደለ!
ምን አለ የተሰወረ? ምን አለ የጎደለ??
ምን አለ የማያምር??
ከሳሽ መንፈስ ተጣብቶት፣
የሚይዘውን የሚጨብጠውን አሳጥቶት፣
እሱ ሽቶት፡ ሞት ሸቶት፣
በቁሙ ካልበከተ፡ ይቅር ሲሉት የማይምር፣
ምን አለ የማያምር??
ምን አለ??
በእብለት፡ የሰይፍ ስለት ካልነከሰ፣
ውድ ሊሆን ሲማፀደቅ፡
የማነህ የሚለው አጥቶ፡ ጥምቡን እስኪጥል ካረከሰ፣
ቀጥ... ብሎ ያልጠና፡ ምን አለ ያነከሰ??
ምን አለ የሚያስፈራ??
ውል ጥሶ፣
ምራን በጥሶ፣
የትም ባክኖ ካልመከነ፣
በራሱ ካልጨከነ፣
°°°°°°°
እንደ መልካም የስንዴ ዘር፡
ጎልቶ አብቦ በጊዜ በስሎ ካፈራ፡
እንኳን ፍራት ሀፍረት የለም!!
°°°°°°°
በሰው ዳስ ድግስ፡
ልጁን ሊሞሽር፡ ጎምበስ ቀና ካላለ፣
የሚያሳፍር ምን አለ??
ባይን አዋጅ ሚዛን እየመተረ፡
በሰፋው ቁና እየሰፈረ፡ ዋጋ ሊተምን ካልቃጣው
እንኳን ካገር ገበያ፡
ማነው? ከእድር ከመንደር የሚያወጣው??
ምን አለ የተሰወረ??
ምን አለ የሚያስጨንቅ? ሌት እንቅልፍ የሚነሳ??
አንደበቱ ካልወሰለተ፡ እጁ የሰው ካላነሳ!!
ስጋትም ውጋትም፡ ምን አመጣው??
ሆዱን በእህል፡ ልቡን በልህ ከቀጣው
ነውሩን ሸንጎ ካላወጣው፣
ጭንቀትማ አይታሰብም!!
ሰው!... እንኳን ሰው ፡ ወፍ ያልዘራውን አይሰበስብም!!
ምን አለ ያልተፈቀደ??
ዓይን ያለመውን፡ ልብ ካቀደ!!
...
.....

ሸጋ ጁምኣ!💚

#4ቀን🎂🎂

@getem
@getem
@balmbaras
#ለቅዳሚታችን መዳረሻ!


አሁን በዚች ቅፅበት ከሚወዷት ጋራ!!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
(1)
{{ .................ርበሽኝ ነበር፣
..................ተጠምቸሽ ነበር፣
አቀፍኩሽ ታቀፍሽኝ፡ በእቅፍሽ ሞትኩኝ፣
ሳምሽኝ ተሳምኩልሽ፡ ባሳሳምሽ ዳንኩኝ፣
በልብሽ ላይ ነገስኩ፡ ከሰማይ ገዘፍኩኝ፣
..................ረክሸ ነበር፣
ባረክሽኝ ተቀደስኩ!!
በሙቅ እቅፍሽ ውስጥ፡ ዘላለሜን አበብኩ፣ }}
...............!!
( 2)
{{ .........
በፍቅር አምልኮ፡ በውበት ውዳሴ፡ ልቡ ለሚሰየፍ፣
ከገነት ይሞቃል፡ ከኤዶም ይልቃል፡ የሸጋ ሴት እቅፍ፣
...............ከጊዜ የላቀ፣
...............ከቦታ የራቀ፣
...............ከሐቅ የረቀቀ፣
በሚያፈቅሩት እቅፍ፡ በሚወዱት ጉያ፡ ውበት ለመመስጠር፣
ምጥጥ ነው እንጂ፡ ጉርስ ነው እንጂ፡ የሸጋን ሴት ከንፈር፣
.................ግሩም እንኮይ ገላ፣
.................ጥዑም የሸት ዛላ
..................የወይን ዘለላ፣
እንጆሪ የሚያስንቅ፡ የሸጋ ሴት ከንፈር፣
ሳም ጉርስ አርጎ፡ ህያው ሁኖ መኖር፣
..........እቅፍ ነው እንጂ፣
..........ጉርስ ነው እንጂ፣
..........ምጥጥ ነው እንጂ፣
ለዘላለም ህይወት፡ ለዘላለም ደስታ፣
ከነፍስያ ዘልቆ፡ እስኪያብብ እፎይታ፣
በሸጋ ሴት እቅፍ!!
የኤሊያስን ትንቢት፡ የያሱን ተአምር፣
የዮብን ትእግስት፡ የዳዊትን መዝሙር፣
የሙሴን ትእዛዝ፡ የአሮንን በትር፣
ይን ሁሉ የሚያስንቅ!!
ጊዜ የማይሽረው፡ ዘመን የማይረታው፡ ውበት ለመሸመን፣
በመውደድ ሉባንጃ፡ በፍቅር እጣን ጭስ፡ ዘላለም መታጠን፣
እዚጋ ሞት የለም!!
.....በጥዑም መዓዛ፡
.....በፍቅር እጣን ጭስ ፡ ውብ ህይወት አብቧል፣
እዚህ ህመም የለም፡
.....በጡት ተሞሽረው፡
.....ከንፈር እየሳሙ፡ ጤንነት መንጭቷል፣
እዚህ መድሎ የለም፡ ባፈቀሩት ገላ፡ ፍትሕ ፀድቆ አሽቷል።
እዚህ ሀዘን የለም፡ በታቀፉት እቅፍ፡ ሀሴት ተደግሷል፣
ካፈቀሩት ገላ፡ እጣን አለ ከርቤ፡ ፅድቅ የከተበ፣
ከሚወዱት ገላ፡ እውነት አለ ሠላም፡ አፍርቶ ያበበ፣
........አሁን በዚች ቅፅበት!!
........ከሚወዱት ጋራ፡ መዋሀድ መጣመር፣
........ሠርክ መቀደስ ነው፡ ህያው ሁኖ መኖር፣


#እብዱ
ሸጋ ምሽት!💚

"ናካይታ"💚

@getem
@getem
@balmbaras
ወገግታ የስነ ጽሑፍ ወ ሥዕል ምሽት
ሰኞ ጥር 18 በ ሃገር ፍቅር ትያትር ቤት ከ 11:00 ጀምሮ

@getem
@getem