ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ዛሬ ታላቁ ልብ የተወለደበት ቀን ነዉ
ጥር 6 1811
እኔ አባትህ...
ከዘፍጥረቴ ስጀምር
ከጦቢያዬ አብራክ ስወጣ
ከአፈሯ እሸት ቀምሼ
ከምንጯ ውሃ ስጠጣ
ብትኑን ሰብስቤ ይዤ
የሩቁን ባንድ ጠቅልዬ
"ይማሯል እንደ አካልዬ
ይዋጓል እንደ ገብርዬ"
ብዬ
ዝመናን ጋፋት ላይ ጥጀው
ልብ ላይ እድገትን ስዬ
እኔ አባትህ...
የታጠቅ የጦሩ ጌታ
ላገሩ ተጓዥ አውታታ
እውቀትን አጭቶ ያገባ
በጃኖ በነጩ ኩታ
ለእድገት እሰየሁ እንጂ
ለውድቀት ጦር የማልፈታ
እኔ አባትህ...
ዝንት ዓለም የማስበውን
ከዘመን በፊት ጀምሬው
የእውቀት ብልጭታ ገመዱን
ከዙፊል ውሃ ነክሬው
እውቀት ይበጃል ብየ
ላገር ለወገን ነግሬው
አንድነትን ከፍ ለማድረግ
ትንፋሼን ላገር ገብሬዉ
እኔ አባትህ...
ያባት ያያቴ ታሪክ
መክሰሙ ያንገበገበኝ
የድንቁርና ጋሬጣ
ከእርምጃየ ያልበገረኝ
መድፉን ሰርቼ ያልጠገብኩ
መርከቡም ያላስቸገረኝ
አድምጠኝ ልጄ ልንገርህ
አጤ ቴዎድሮስ እኔ ነኝ
በል ተነስ ቁጭ ካልክበት
መቅረዙን ያዘው በእጆችህ
መማር ነው ትልቅ ብርሓን
ጨለማ ይራቅ ከደጅህ
ካባትህ የወረስከውን
አቀብል ለልጅ ልጆችህ
ውል ሳትይዝ ሙግት ላትገጥም
'ሀ' ሳትል ፊደል ላትጠራ
እውቀትን ታጥቀህ ተነሳ
እሱ ነው ደምቆ የሚያበራ
በታሪክ ትልቁ ዶሴ
ሀገር የሚጠራበት
ካለፉት እየቀሰመ
እውነቱን የሚረዳበት
ዛሬውን አፅንቶ አቁሞ
ነገውን የሚቀርፅበት
ቴዎድሮስ ከሚሉት መቅረዝ
ሶሎሞን ሳህለ
@getem
@getem
#jeko
"ማወቄን ጠላሁት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*************
ያኔ ያኔ
በኋሊት ምናኔ።
ከየኔታ እግር ሥር
በጨቅላነት እድሜ ፊደል ስንቆጥር።
ያን የንጽኸት ልኸቀት
ያን የልግሰት ሹመት
አስተውለው በነበር በልሙጩ ሹረት
ዛሬን ባውቀው ድንገት
ድንገት ድንገት ድንገት
በአስኳላዊ ትዕንቢት
በመሀይም ትዕቢት።
ሆነብኝ መጨረት
ሳይፈሱ መረጨት
ሳይርሱ መጎንጨት።
እናም
"ሀ" በል ሲሉኝ "ሀ"ን ስላት
"ለ" በል ሲሉኝ "ለ"ን ስላት
"ሀ"ም ግዕዝ ናት
"ለ"ም ግዕዝ ናት
እያሉ
የዛገ ብስ ጣርያ ያለቀ እድፍ ድንጋይ
የሳሳ ሰሌዳ ያልፈገገ ሰማይ።
ባልታደሰ ሙዳይ ጠመኔው ተቀምጦ
ጨዋነቴ ረቅቆ ብጥባጦቴ በልጦ።
ግርፋቴ ሲነግስ
ከዕውቀት ማማ ላይ ውድቀቴ ሲጠነስ።
ደብተሬ ትዝ አለኝ
ደብተሬ ትዝ አለኝ
ባለ አስራ ስድስቱ
ስምሽን እንደ ድር የደረድኩበቱ
ትዝ አኝ ትዝታሽ
ቤተ - መጻፍት በሚል ስውል ቤተ - ልብሽ።
ማወቅ ይሉት ክፉ
ለሌላ ሳይሆኑ ለራስ የመትረፉ።
አንቺን አስረስቶ
ፍቅርሽን አስቶ
ሊቅነት ሲቸረኝ ልቅነቴን ሽቶ።
ሀገሬን ሚያሰኘኝ ከሀገሬ ነጥሎ
ማወቄን ጠላሁት መማር አንቺ ጥሎ።
አውቀሽኝ ሀገሬን
ሳላውቅሽ መኖሬን።
.
.
.
@getem
@getem
@poem_with_mela
ላልቅስበት
[ ቴዎድሮስ ካሳሁን_ቴዲ አፍሮ]

በነገር ፍም እሳት እያቃጠላቹ
ለማዘኔ ምክንያት እናንተው ሆናቹ
አታልቅስ አትበሉኝ ከፍቶኝ እያያቹ

ሁሉም እየጫረ እሳት ሲለኩሰው
ሻማ እንኳን ያነባል እንባ አውጥቶ እንደሰው!!
@getem
@getem
#jeko
ሁለት ገፅ
"''""""""""""

መራራና ጣፋጭ በአንድ ፅዋ መቅመስ
በግማሽ ፊት ስቀው በግማሽ ፊት ማልቀስ
በአንድ ጎን በርትተው በአንድ ጎን መቅለስለስ
በአንድ ልብ ኩሩ ሆነው በአንድ ልብ መልከስከስ
እልልታና ሙሾ በአንድ ላይ መዋረስ።

@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
ዛሬ ከ ቀኑ 11.00 ሰዓት ላይ በፓናሮማ ሆቴል #ቀንዲል የጥበብ ምሽት ይጠብቃችኋል። አድራሻ...ከመገናኛ 22 መንገድ በስተግራ በኩል ከቫምዳስ ሲኒማ አጠገብ ነው።
።።።።።።።።።።
የአርነት ጥያቄ?!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
እኔም አንድ ሰሞን !
እንደ ክፉው ሳዖል
እልፍ አንገት ለመቁረጥ
ሰይፍ ይዤ ስሮጥ
በቃላትህ በትር ፥ በድምፅህ ድንፋታ
መሬት ላይ ወድቄ ...
ልቤን አስማረክሁኝ ፥ መንፈሴ ተረታ ።
ከዛ ካህን ፈለግሁ ...
በደሌን ተናዘዝሁ ...
ደግሞም ያንተ ካህን ፥ መጥሀፍ አዋቂ
የስምህ ቀዳሽ ሰው ፥ ቃላትን አርቃቂ
ሰይፍ እንዳነሳ ፥ ሰይጣን በኔ አድሮ
እልፍ አንገት ለመቁረጥ ፥ እንደቆየ አሲሮ
ስህተቱን ጠቅሰው
እንደነበር አርገው
ከቃልህ ቀንጭበው
መክረው አስተማሩኝ!
ይሄን ባሉኝ ማግስት ...
እኔም ያንተ ፍጥረት....
ጲላጦስን ሆኜ እጄን እያነፃሁ
ንሰሐዬን ሻርኩኝ ።
አንተም ይሄን ስታይ!
በአርያም ደንፍተህ ...
አይደረግም ብለህ.. .
ለምን ? እንዳትለኝ!
.
ሰይጣን በኔ አድሮ ፥ ለሚቀላው አንገት
ለሚያቆየው በደል ...
በኔ ነፍስ ፈንታ ፥ ራሱ ይወንጀል ።
እኔ ምን ተዳዬ ???

@getem
@getem
@getem
#ምርጥ ( #ምርትነሽ_የማነ)

እቴትዬና..... እሜ
አደዬና ......ሀርሜ
በየ ፈርጀ ........ፈርጁ
በእያንዳንዱ ቋንቋ ፥ ቃላት ቢወዳጁ
አንቺን .....እኮ እናቴ
የጠዋት አስኳላ ፥ የልጅነት ሀብቴ
ኑር አንተ ለኔ .......ባይ
ቅንጣት ሳይታወስ ፥ ላንቺ ያንቺው ጉዳይ
በጉያሽ አቅፈሺኝ ፥ በጪንጫ ተኝተሽ
ውሀ ባፍሽ ርቆ ፥ ወተቱን ያጠጣሽ
ማጀት ያጠቆረሽ
ረሀብ ያከሳሽ
ጎኔን ....... ጨርቄን...... ማቄን
የሚሉት ጥበቃ ፥ ከራስ በላይ ንፋስ ፥ ሰይሞ መዳከር
ላንዲት ነብስ ስስት
ላንድ አካል መንቧቸር
ከራስ በላይ ልጄ'ን
በሚል ልግስና ፥ እድሜን በመቸርቸር
ብ 'ርክ በማለት ፥ ብርክሽን የረሳሽ
በመከነ ቀለም ፥ ብዕርሽ የጠፋች።
ያ..............#ፀሀይ ውበትሽ
ኩሽና ተሳስሮ ፥ ከምጅጃ ግርጌ፥ ዕድያው የቀረ
ወዘናሽ ተሟጦ ፥ ገፅሽ የጠቆረ
በመጨናበስ #ነው
አካልሽ ለጋሱ ፥ አይነ ግቡ መልኬን ፥ ዛሬ የወቀረ ።

የአፍላነት ግዜሽ
ጥንቡሳሱን ጥሎ ፥ ያለ እድሜሽ ያረጀሽ
ደ 'ስታን ልክ እንደ መርዝ
ለልጅ በመኖር ውስጥ ፥ ዘመንሽ የቀማሽ
በአለሙ መሀል ፥ ለአለም እንግዳ
ትክሻሽ የሳሳ ፥ ቅስምሽ የተጎዳ
የህይወት ቀንበር ተጫኝ
ለፍሠሀ ባዳ !!
ሀኪም እናታለም
#ኮስማናዋ #እናቴ!!!
የህይወት መቅድሜ
የጉም ቀን መብራቴ
ተስፋ አለምሽ ይጥና
#በርቺልኝ በሞቴ
እናትነትሽ ነው ፥ በዚህ ልፋጭ አለም ፥ የቀን ክራሞቴ።

የሰማዩ ንጉስ የምድሩም ጌታ
ከምንም አብልጦ ፥ እናቱን ይወዳል
ትንሽም ሲራሩ
እናቴ ያሉ እንደው ፥ ምዕንተ ማርያም ፀሎት ይማለዳል
ውህብቶ ብዙ ነው ፥ ዳና በመከተል ፥ በገፍ ይሰደዳል
እናቴ ለሚሉት እናት መሆን ያውቃል
ስለዚህ ....
ልጄን ብለሽ አንቺ ፥ ፊቱን እንደ ሰማሽ
ያብቃኝ ....
አንቺም ያብቃሽ....
ለልጅ የተሰዋ
አድሮ የበረታ ፥ የህላዌ ጥዋ
ብሩህ ጀምበር ገጥሞ
በልጅ የፈዘዘ ፥ ዳግም በልጅ ቀልሞ
እንጥፍጥፍ አለም ....በእድሜ ስልቻ ፥ ጠብቆ ተቀምቅሞ
እያጠነጠነ...... የግዜ ሰሌዳ ፥ በመቁጠሪያ ሲታሽ
አድማስ ተሻጋሪ ... #ቦግ!!! ብሎ ማታሽ

ውድ ሸማሽ ሆኜ ፥ መቀነት ያውለኝ
ለውበት ...ለድጋፍ ፥ መጠቅለል የቀናኝ
ገንዘብ ....መቋጠሪያ
ውጋት ......ማባረሪያ
ላዱኛ ቀን ብርታት
ለጭንቅ ቀን ፅናት
አድርጎ .....እኔን ላንቺ ፥ ፈቅዶልኝ ፈጥሪ
የእናቱን ቀን አውጪ ፥ በወዘናው ጣሪ
ግብ ቀንቶት ፅናቴ
ሹልክ ብለሽ ወጥተሽ ፥ ከኑሮ ግርግር
ከእንጉርጉሮ አለም ፥ ጠማማ ውንግርግር
ምርቃትሽ ደርሶኝ ....መነን ሁኚ እናቴ
ባንቺ ውስጥ እንደኖርኩ ፥ በኔ ትኖሪ ዘንድ ፥ ይባረክ ጉልበቴ።

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
ለቅዳሚት መዳረሻ!
❤️

እኔ ለወዳጄ
አንዲት ናት ግዳጄ
ሲመጡ መቀበል
ሲሄድ መሸኘት
እንደልቡ ሲሆን
የልቡን ለማግኘት።


(ሙሉጌታ ተስፋዬ)አያ መሌ! የልቤ!
ይኸው ነው!
❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@getem
@getem
@balmbaras
ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ! አለሜዋ!


በአንቻሮ ቅዳሜ!!!!!!

ምን ሊፈይድ ሰኞ፣
ምን ለያደርግ ማክሰኞ፣
እረ የምን እሮብ፣
የምንትስ ሀሙስ፣
ቀና ቀኑ ሁሉ፣ገለል በል ከፊቴ፣
ይገማሸርበት፣
የቀኑ ባለሟል፣የቀኑ ከበርቴ፣
ቅዳሜ ሸግየው፣ ቅዳሜ ፍትፍቴ።
የምትል ውብ ቅኔ፣
ትላንትና ወዲያ፣ ደግሞ ወዲያ ማታ፣
ድንገት ከሃድራው ላይ፣ሰተት ብላ ገብታ፣
ማክሰኞን ሞሸርናት፣በቅዳሜ ፋንታ።
ማክሰኞ ማለዳ፣
የተሸላለመው፣የቅኔ ማሰሮ፣
ይኸው ተከፈተ፣
በላይ ገንዳው ዘማች፣ ባንቻሮ ባንቻሮ።
ሃጃ ነበረብኝ፣
መውደድ ነበረብኝ፣የወንድም ሀቂቃ፣
እንኳን ለኔ ናፍቆት፣ላንቻሮ እሚበቃ።
ድረስልኝ ብሎኝ፣
ዝለቅልኝ ብሎኝ፣ሽሙንሙን ባልንጀር፣
ትላንት መልእክተኛ፣
ካንቻሮ ቀበሌ፣ ተልኮብኝ ነበር።
ወዳጅ በጠፋበት፣
ጓዱ በሸሸበት፣ በዚህ ድፍድፍ ዘመን፣
ጀነት መግባት አይደል፣
ና ድረስ ተብሎ፣በወንድም መለመን።
ናፍቄያለሁ ብሎ፣
ድረስልኝ ጓዴ፣ ድረስ ቶሎ ካለ፣
ከዚህ በላይ ህይወት፣መታመን የት አለ።
በጓደኛ ናፍቆት፣
በወንድም ወዳጃ፣
እሽ ማለት መስሎኝ፣የሚያወጣው ሃጃ።
ምን ገጠመው ጓዴን፣
ከቶ ምን አገኘው፣
ቶሎ ድረስ ያለኝ፣ ባንቻሮ በገዳም፣
ምን መንገድ ቢመቱ፣የወዳጅ አይጎዳም።
ብየ ሳላበቃ፣ብየ ሳልጨርሰው፣
ፋጦ አቀበቲቱ፣ በሃድራ እምትጨሰው፣
የባልንጀርና የወዳጅ ሃቂቃ፣
ፋጦ አቀበቲቱን፣ሲወጧት ነው በቃ።
እያለች ሸኘችኝ፣ አብሽር ገራሙ ሰው፣
ባልንጀር ነው ቀድሞ፣
የወዳጁን ፅዋ፣ቀድሞ የሚቀምሰው።
በሚል ዝይን ቅኔ፣ እየወረበችኝ፣
መገን ፋጦ ሙሄ፣ አንቻሮ ዶለችኝ።
ይኸው ከፍትፍቱ፣
ያው እረከቦቱ፣
እንደ ንጉስ ጉባይ፣
በባልንጀር ይሁን፣ መገን በወጭቱ፣
ባንተው ይሁን ብላ፣ዘለቀች ልጅቱ።
ከልጅቷ በቀኝ፣ የቆመው ባልንጀር፣
በኔ አሮ በእሷ አሮ፣ ተጀንኖ ነበር።
ሃድራው ተጋግሞ፣ ሲገለጥ ሀቂቃ፣
በዚያች በሸጋ ልጅ ፣ተፈረደ በቃ።
የታመመው ጓዴ ፣እንዲህ ተቸግሮ፣
ቀልቡ የወየበው፣ ልቡናው ተሳክሮ፣
በሌላም አይደለ፣ ባንች አሮ ባንች አሮ።
የተባለች ጊዜ፣ ልጅቱ ደንግጣ፣
እረ በሸሆቼ፣ በገታ በገታ፣
ይህን መሳይ ጎበዝ፣
እንደምን ይወዝወዝ፣እንደምን ይረታ፣
አሻ፣
ወዶ መናወዝን፣አላህም አይሻ፣
አንቻሮ ላይ ሞልቶ የፍቅር ወጌሻ።
እያለች ልጅቱ፣ ጀማው መሃል ገብታ፣
እያሰማመረች፣
ነፍሷን በምርቃን፣ ገላዋን በጉፍታ፣
ነይ ሳሚው ተብላ፣ ከንፈር ስትመታ፣
ባልንጀሬ ሻረ፣
ይሁን አሁን ብሎ፣ ጀምኣው ተፈታ።
እቴ መድሃኒቴ፣
የኔ ሸሙናይ፣
በቅዳሜ ሃድራ፣ባንቻሮ ሰማይ፣
ከንፈር እየበላሽ፣ብቅ አትይም ወይ።

((( ጃ ኖ ))💚💛

"ናካይታ"💚

@getem
@getem
@balmbaras
አቦ ቅዳሜም አይደል የዳዊት ሙዚቃ እየሰማን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው ...ምን ይላል ይሄ የኔ የሙዚቃ ንጉስ የመጀመሪያው የሙዚቃው የመጨረሻው የግጥሙ ስንኞች ላይ በዛ በሚገርም ድምፁ እንዲህ ይላል......


ባይወጉን አይደለም በነጭ ያልተገዛን
ተቸግረው እንጂ ስንሞት እየበዛን
ስንት ሺህ ጀግኖችሽ ከእነፈረሳቸው
ለፍቅር ሞተዋል ላንቺ ለእናታቸው

ምን ልሁን ባላገሩ❤️
ምን ልሁን ባለ-ሀገሩ❤️


#ይሄን እየሰሙ አለመገማሸር እንዴት ይቻላል ያውም በቅዳሜ ያውም በሸጋዋ ! ባለገር ሁኑ ሸጋ ቅዳሜ ጀባ!

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
የአስተርዮ ማርያም!!!!!


የማሽላው ሃገር፤
የጁ ዶሮ ግብር፤ ኣላ ገዶ ነው፤
ጥንቅሹን ወልዲያ፤ ምን አበቀለው???


ጥንቅሹ ወልዲያ የበቀለውማ፤
ሸጋ ልጅ ዘርታው ነው፤
መቻሬ ሜዳ ላይ፤
በእነነየ ቱፍታ፤ በየጁ ከራማ።


በወይብላ ማርያም፤
በጉባርጃ ማርያም፤ በወለላይቱ፤
መቻሬ ውድመን፤
ዋልካውን ቢጭሩት፤
አፈሩን ቢያዋዩት፤ ጥንቅሽ ነው መሬቱ።


ላዩን በውድመን፤
ታቹን በሸህ ዳና፤
በአውጋሩ በአድባሩ እኔው ተመርቄ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
እርሻየ ጥንቅሽ ነው ከጉራ እስከ ወርቄ።


የጁን ያህል ሃገር፤
መርጦን ያህል ደብር፤
ያበቀለው ጥንቅሽ፤
በልቼ ነው እንጅ፤
ማር ከንፈር አድርጎ፤ አጣፍጦ ሚያኖረኝ፤
የማር ዘነብ ሚዜ፤
የነ ጥንቅሽ ወንድም፤
ለወዳጅ ነው እንጅ፤
ለሷሂብ ነው እንጅ፤ እኔን የሚገደኝ፤
ላሽከር ለሹምባሹ፤ አይሞቀኝ አይበርደኝ፤
ዘበናይ ወሎየ፤
ሰው ለክቶ ሚያድር፤ሰው ነው ያሳደገኝ።


መልኬ ጥቁር ውሃን፤
አላውሃን ጅረቱን፤ እየቆነጠረ ፤
ቱባው ማንነቴ፤
በሰውኛ ጠረን፤
በሰው መሆን ሚዛን እየተሰፈረ፤
በአዳምነት ወረት ፤
ጓዳና ማጀቴ እየተሞሸረ፤
መገን የኔ ነገር፤
ከድፍረስ ባህር ላይ፤
ጅረት እለያለሁ፤
ያውም እኔን እኔን፤ እኔን የመሰለ፤
በፍቅር ረመጥ፤
በሙሃባው እሳት የተንቀለቀለ፤
በሰውነት ቀለም፤
በሰው መሆን አጀብ፤
ነፍሱ የሸገነ፤ አይኑ የተኳለ፤
አላውሃ መሌው ዳር፤
ይጠብቃል ጓዴ፤
ርጥብ ማሽላውን ውልቢኝ እንዳዘለ፤
በናፍቆት አይኖቹ ፤
በራ በሩን ያያል፤
ደግሞ ለጥምቀቱ፤ ለአስተርዮ ማርያም ይመጣል እያለ።


እንዲህ ያለም የለ!!!!!!

((( ጃ ኖ))💚💛❤️

@getem
@getem
@Nagayta
ጥምቀትና ውበት
"""""""""""""""""""""

አንድ ሎሚ ይዤ
ከውቢት ደረት ላይ ወርውሬ ላስቀምጥ
በታቦት ማረፊያ
ከእላይ እታች ስል ቆንጆዎች ሳማርጥ

ዓይኔ ዛብሮ ቀረ
እግሬም ተንከራውቶ
ሀሞቴ ፈሰሰ ልቤም ዋትቶ ዋትቶ
ማንን ከማን ይምረጥ
ቆንጆ ባገር ሞልቶ።

መገን አዲስ አበባ
ስንቱ ጉብል ታየ ከታች እስከላይ
የሴት ልጅ ውበቷ
ያገር ባህል ልብሷ ሽንሽኗ ነው ወይ?


ያገር ልብሷን ለብሳ
ታቦት ስታወጣ ታቦቱን ስትሸኝ
ሁሏ ሴት ማማሯ
ምድር አረገደች ለወዳጇ ይብላኝ።

(የኔማ😔)

ሎሚውም ደረቀ
አይናዋጅ ሆነበት ልቤም ተንሰላውጆ
ሸገር አሸብርቃ
ነክሽ ነካ ስትል በከተሜ ጉብል በአዲስ አበባ ቆንጆ።

ብላም አስመኘችኝ
የውበቷ ንግስት መለሎ ወጣት
ምን አለ በሆነ
ሁል ጊዜ ከተራ ሁል ግዜ ጥምቀት።

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@getem
@getem
@getem
ሎሚ ወሳጅ ጠፋ?????!!!!!!!!!

በሃምሌ ተለክፎ ፤
በነሃሴ አፍቅሮ፤ ህዳር የጠናበት ፤
በጥምቀት ይድናል ፤
የመምሬ ጠበል ፤ ውሃ ሲፈስበት ።


ይብላኝ እንጅ ላንች ፤ እኔስ ግዴለኝም ፥
ጥምቀት ከደረሰ ፤
እታጠበዋለሁ ፍቅርሽ አይገለኝም ።


አምና ጉባላፍቶ ፤ ሎሚ እንኪ ብልሽ ፤
ግንባርሽ ተቆጣኝ ፤ አባጨኝ ፊትሽ፤
ዘንድሮ ሸጎቹ ፤ መጡ ሊነጥቁሽ ።
ሎሚ አልከጅል ብለሽ፤ ስትይ ገባ ወጣ ፤
ከእጅ የሚመነጥቅ፤ ሎሚ መጣጭ መጣ ።


እንካ ሲሉት ሎሚ፤ የተግደረደረ ፤
ዘንድሮም እንዳምናው፤ሎሚ ናፍቆ ቀረ ።
ይብላኝልሽ ላንች ፤ ሎሚየን ለናቅሽው ፤
ወዶ መለመንን ፤ ከእንግዲህ ቅመሽው ።
ተሽሎኛል ዛሬ፤ ከአምናው በጥቂቱ ፤
በጠበል ለቆኛል ፤ የመውደድ ግዝቱ ።


ሎሚ ስጠኝ ያልሽው፤ አለቀብኝ እኔ ፤
የስንት ሰው ሎሚ ፤
መጥምጠሽ አኝከሽ ፤
መሮሽ ስትጥይው ፤ እያየሁሽ ባይኔ ።


እቴ በታቦቱ ፤
እቴ በጥምቀቱ ፤ በአድባሩ በአውጋሩ፤
ያንች ሰፈር ልጆች ፤
ሎሚ አንወስድም ብለው ፤ ሎሚ ናፍቀው ቀሩ ።
አንች ባለ ዱኣ ፤
ቀየው የመረቀሽ ፤ በተራ በተራ ፤
እየው በዚያ ሰፈር ፤
ተከምሮልሻል ፤
ሊወረወርብሽ ፤ የሎሚ ተራራ ።
እመጣለሁ ቆንጂት ማለዳ ቀድሜ ፤
ጠበሉን ሲረጩኝ ፤
ከተፋዘዝኩበት፤ ይገለጣል አይኔ ።


አምና በትፍትፍሽ ዛሬ በአንባርሽ ፤
ሎሚ ስወረውር የገረገረሽ ፤
የወደደ ገላ በቀልብ ያሰረሽ፤
ማለዳ ነይና ፤
ሎሚው እንዲቀናሽ ፤ ጠበሉ ይፍታሽ! !!!

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ የጥምቀት በዓል!!💚💛❤️

@getem
@getem
@Nagayta
እንደው ስጠረጥር....በሲራክ
<unknown>
ገጣሚ አሌክስ አብርሃም
አንባቢ ሲራክ
@getem
@getem
@getem
#
@siraaq
የዋርካ ስር ጤዛ
ሲራክ
ገጣሚ እና አንባቢ ሲራክ
@siraaq
#
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)


በተራበው ጎኔ፣ በተጎዳው ኪሴ
እኔም ሰው ነኝና፣
የከንፈር ወዳጄን ተጠምታብኝ ነበሴ
የጥምቀት ለት ሎሚ፣
ኪሴን በሚጎዳ በሚነርት ዋጋ
ይሁን ብየ ገዛሁ፣
ደረቷን ልመታ የዛችን ውብ ሸጋ።

ሎሚውን በእጄ ያዝኩ
ኮረዳዋን ፈለግኩ
ባ'ይኖቼ አማተርኩ

ከኋላዋ አየኋት...
ፀጉሯ ሹሩባ ነው፣ ፊቷ አይታይም
ኋላዋ ካማረ...
ፊቷ ምንም ይሁን እኔን አይጨንቀኝም

ዳሌዋ... ቢዮንሴን ያስንቃል
በንቅልፍ የቧዘዘን አጣድፎ ያነቃል
ስንት የወጣባትን፣
የኛን ሳተላይት ከቻይና ያመጥቃል (አንጥሮ😂)

ወገቧ... አካበድክ ባትሉኝ
ከቀጭኗ እግሬ ሚወፍር አይመስለኝ

ወይኔ ሹሩባዋ
ለመግለፅም እንኳን አንደበትን ያስራል
በቆሙበት መሬት አፍዞ ያስቀራል።

ወደራሴ መጣሁ...
ልወርውር አልወርውር?
ልወርውር አልወርውር?

ወረወርኩ...
ድምም... እዛው ዳሌዋ ላይ
አሟት ዩን ደስ ብሏት ዞር ብላ ብታይ
የኔ ልብ ደንግጣ ልትበር ወደ ሰማይ

እየሮጠች መጣች፣
እያነፈነፈች ትንፋሿ እስከሚያጥራት
ክፉ አስባ ይሆን ልሩጥ ልጠብቃት?

ደረሰች...
ፊቴ ከመድረሷ፣
አንድ ጊዜ በጥፊ አወላመመችኝ
ወደላይ ወደታች፣
መላ ሰውነቴን በደምብ ቃኘችኝ
ወደግራ ጆሮየ በጣም ተጠጋችኝ

ጊዜው የድንጋይ ነው ሎሚ አታባክን
ኪስህን አሟጠህ፣
በገዛኸው ሎሚ ፈፅሞ አትጨክን
አሁን ሳናቅማማ ቶሎ እንሽጠው
ይሄ ውድ ሎሚ፣
ላ'ዲሱ ጎጇችን ትልቅ መሰረት ነው
ብላ አቀፈችኝ
እሰየው ዘንድሮ ለኔም ተሳካልኝ።

@getem
@getem
#jeko
" #ባውቶማቲክ_ግዜ#መሸከሙ_ጓንዴ ...
#አይከብድም_ወይ_ጓዴ"

ይብላኙን ለነሱ…
በጠዋት ገስግሰው ፥ አንድ ኪሎ ሎሚ ፥ ገዝተው ለደረሱ
ያውም በዚ ግዜ
ሎሚ ጥሪው ከብሮ ፥ ከጅ ላይ በጠፋ ፥.... በተወደደበት
ሜክ አፕ የለቀመው ፥ ሴቱም እንከን የለሽ ፥ ውበት በደፋበት
ወንዱም አቅሉን ስቶ
ሎሚ በተረሳው ፥ የመኪና ቁልፉን ፥ እያነጣጠረ
አይፎኑን ደረት ላይ ፥ ሰዶ እያነጠረ

"አይፎን ብወረውር .....እስፖንጇን መታሁት
አወይ ተሳክቶልኝ......ጡቷን ባገኘሁት"

በሚል ሀርሞኒካ .....ትዳር የሚናፍቅ
አልሞ ተኳሿ .....ከሷ ብዙም ሳይርቅ

እያረጋገፈች ከመሬት አንስታ
የላክልኝ አይፎን .....የሰደድከው ቁልፉ
ከደረቴ ነጥሮ....መሬት መዘርገፉ
አንተም ጎበዝ አጥቂ.....
ጎበዝ ተከላካይ ፥ መርጦ ገራም ልብህ የመሸናነፉ
ማመላከቻ ነው ፥ ቅኔው ሲተረተር ፥ እንዲያው በግርድፉ
ለዚህ ....ለዚህ እንጂ ፥ ዱላ ለመመከት
ውበት ጎሎት አይደል
በል ነዳጁን ስጠው ፥ ቦታ እንያዝ እና ፥ ማማሩን ተመልከት
ብለው ተያይዘው ፥ ከስርፋው ታበሱ
ያንን ሁሉ ሎሚ ፥ የሸመተው ጉብል ፥ ለማን ይስጠው እርሱ
በዚህ የሀሳብ ዚቅ....... እንደተዘፈቀ
ታቦቱን ያጀበ ፥ የሞንሟኖች መንጋ ፥ ሳይገላመጠው ከተራው አለቀ
ይህን እያየሁኝ....
ከሎሚም ፣ ከቁልፉ ፥ የቀረሁኝ እኔ
ጉብታው ላይ ቆሜ ፥ ሲወጣና ሲወርድ ፥ አየዋለው ባይኔ
ድንገት ፥ ተስፋ ራሱ ፥ ተስፋ ቆርጦ ሳለ
ለመሄድ ሲነሳ ፥ የኪሎ ዘንቢሉን ፥ እንደጠቀለለ
አምሮት የምታጭር...ጥበቃ እምትገታ
ካለችነት ቦታ ፥ በፍጥነት ተነስታ
ወደርሱ ቸኮለች ፥ ተሳልሞ ለመሄድ ፥መነሳቱን አይታ
ለጥቂት ሰአታት ፥ አንድ ላይ አወሩ
ፈገግ አለች እሷ......ተፈታ ግንባሩ
ነጠላ ሸፍና ፥ እጁን ጨበጠችው
ያንን ሁሉ ሎሚ ፥ አንድ ራሷ መጥታ ፥ እሷው ወሰደችው።

ይህኔ...
የማላውቀው ጓዴ
በለስ ቀንቶት ባየው ፥ በባከነው አይኔ
እሰይ..........አልኩኝ እኔ....
እንደአቅሙ ጣጥሯል ...
አልተሰበሰበም ...በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ፥ አዝኖ ልክ እንደኔ
ከቆመ የዳኸ ፥ አስር እጅ እንዲሻል ፥ መክሮኛል ዘመኔ ።

#ኋላ_ግን_ስሰማ .... #ልጅቷ_ጭማቂ_ቤት_አላት...(😁😁😁)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
እኔማ እጠርጋለሁ!!!!


ቀይ ባህርን ከፍሎ፤
ባሳለፈን ጊዜ፤
በሰይፉ እየመራ፤
ባህሩን አቁሞ፤ ፀጥ አርጎ ወጀቡን
በክንፉ ለመራኝ፤
እንኳንስ በቁሜ፤
ከዊልቼሬም ሆኜ፤
እጠርግለታለሁ፤
ለታቦቱ ክብር፤ ጎዳና መንገዱን፤
እጠርግለታለሁ፤
ሚካኤል ሲመጣ፤
በሁለት እግሮቼ፤ እንድቆም አውቃለሁ።


((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@Nagayta