ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
‹‹ጠ›› እና ‹‹ፀ››
Demeke Kebede

ታገሬ ወጥቼ - ከተማ ገብቼ
ገድ ቀናኝና - ካንቺ ተዋድጄ
አልችል ብል ልለምደው - የከተማን ኑሮ
በአነጋገሬ ላይ - አሰማሽ እሮሮ፤
‹‹ፀሐይ›› አልኩ ብዬ - ‹‹ጠሀይ›› በማለቴ
‹‹ፀጉር›› ልል ፈልጌ - ‹‹ጠጉር›› የሚልን ቃል - ከአፌ በማውጣቴ
ተበሳጨሽና - ቁጣ አዘነብሽብኝ
በ‹‹አድርግ››ና ‹‹አታድርግ›› - ግማሽ ቀን ዋልሽብኝ፤
‹‹ ‹ፀ› ማለት ሲገባህ - ‹ጠ›ን አትጥራ ሁሌ - ዳግም እንዳልሰማ
እንዳታዋርደኝ - እንዳታስፎግረኝ - በነቃ ከተማ
በቃህ አቁም በቃ - ዘወትር ‹ጠ› አትበል
‹ጠሎት›ንም ‹ፀሎት› - ‹ጠሀይ›ን ‹ፀሐይ› በል!››

ትዕዛዝሽን ላከብር - ምን ብጠነቀቅም
‹‹ጠ››ን በ‹‹ፀ›› ተክቼ - ተናግሬ አላውቅም፤
ይህን አየሽና…
‹‹ይቅር እንለያይ - በአንተ አልፈር እኔ
ከብጤህ ተዛመድ - አቻ ሽቷል ጎኔ!››
ብለሽ ተለየሽኝ - ያላንዳች ይሉኝታ
ባላወቅሁት ‹‹ቅጥበት›› - ባልገመትኩት አፍታ፤
ሳስበው አመመኝ…
ሰበብሽ ያበግናል - ያጨሳል፣ ያደብናል
ሰው እንዴት በቋንቋ - ፍቅርን ይመዝናል?

ታዲያ ምኔ ዋዛ - ምኔ ሞኝ ነውና
እኔም በተራዬ - እንተከተክ ጀመር - ‹‹ፀ››ን ተካሁኝና
ይኸው ይኸውና …
‹ፅፍራም› ነሽ፣ ‹ገፃፃ› - ፍቅር የማይገባሽ
‹ፀብ› እንጅ መዋደድ - ‹ፄና› የሚነሳሽ
እስኪ አሁን በሞቴ
ምኑ ነው ‹ፅፋቴ›?
በ‹ፀራራ› ፀሐይ - ‹ወክ› እናድርግ ማለቴ?
‹ፀርሙስ› ሙሉ ቢራ - በቀን ‹መፀፃቴ›?
በ‹ፀፀር› ጎዳና - ‹ፀጅ› ይዤ ‹መውፃቴ›?
ነው ወይስ ኮብልዬ - ከ‹ገፀር› ‹መምፃቴ›?
በያ ንገሪኛ
ምኑ ነው እሚያሳፍር - ይህ የኔ አማርኛ?
እኔ ግን ልንገርሽ?
በ‹ፀበልም› ባልድን - ባይለቀኝም ፍቅርሽ
አብሮ መውፃት መግባት - ሰርክ ካሳፈረሽ
ወይ ካሸማቀቀሽ
ከእኔ ጋር መታየት - ከሰው ካሳነሰሽ
ያውልሸ ጎዳናው - ሂጅ ወደፈለገሽ
‹ቢፄ›የን አላፃም
‹ፀብራራ›ው ‹ገፀሬ› - ‹ፃፃ› አለኝ መሰለሽ!!
@getem
@getem
#jeko
#አይደለሽም
:
:
:
እኔ ነኝ ሔዋኑ እኔ ነኝ የሱ ሴት
ካ’ጥንቱ የተበጀው የጎኑ ባለቤት
ረዳቱ እንድሆን የተፈጠርኩለት
ማለትሽን ሰማው
ከመቼውም ይልቅ በዚ ቃልሽ ደማው።
:
:
ይባስ ብለሽ ደግሞ ...
ግራጎን አጥንቴ ሔዋኔ ነሽ እንድል ከጅለሻል አሉ
እውነትም አንቺ ሴት የዛች ሔዋን ሚስጥር አልገባሽም ቅሉ።
:
:
በዚህ አያያዝሽ አንቺ ነሽ ሔዋኔ ...
...ፈፅሞ አልልሽም
ምክንያቱም ደግሞ ተግባርሽን ሳየው...
...ሔዋኔ አይደለሽም።
:
:
አንቺና ያቺ ሴት
ሔዋን ተብዬዋ የሕያዋን እናት
ስትነፃፀሩ ስትመሳከሩ
ሰማይና ምድር ለየቅል ነው ዳሩ።
:
:
አንቺ በጣም ጨዋ መሽኮርመም መግደርደር
በጨዋታ መሀል ፈገግ ብሎ ማፈር
የተጠናወተሽ
የተቸረሽ ሴት ነሽ።
:
:
ሔዋን ግን ዓይናውጣ
እራቁቷን ሆና አዳም ፊት ምትመጣ
ማንንም ሳታፍር በቀን በጨለማ
ብትለብስ እንኳ እንትኗ ላይ ብቻ ቅጠል አገልድማ።
:
:
አንቺ እኮ ብሩክ ነሽ ፈጣሪን ምትፈሪ
አስርቱን ትዕዛዛት ሰርክ ምታከብሪ።
:
:
ሔዋን ተብዬ ግን ...
እንኳን አስር ትዕዛዝ ልትጠብቅ ይቅርና
አንድ ትዕዛዝ ከብዷት የሰጠች እኮ ነች ለሰይጣን ፅሞና።
:
:
በዚህ አያያዝሽ አንቺ ነሽ ሔዋኔ ፈፅሞ አልልሽም
ምክንያቱ ደግሞ ተግባርሽን ሳየው ሔዋኔ አይደለሽም።
:
:
ግራጎን አጥንቴ ሔዋኔ ለመሆን
ከልብሽ እርግጡን ፈልገሽም ከሆን
ምንም ሳታቅማሚ ጭራሽ ሳትሰጊ
ቀጥሎ ምልሽን እንደ ሔዋን አርጊ።
:
:
ትዕዛዛቱን ትተሽ
ከቅዱሱ ይልቅ እርኩሱን ቃል ሰምተሽ
ካለሁበት ቦታም እርቃንሽን መተሽ
የጎመጀውትን እፀበለስ ስጪኝ
ካምላክሽ ተጋጭተሽ እኔንም አጋጪኝ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu

@getem
@getem
@getem
"ድክመትሽን ደከምኩት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
**************
እርፍታን የሻተች ነፍሴ
ፈቅዳሽ አንቺን ለህዋሴ ።
ኑረትሽን ስኖር
መምጣትሽን ስቀር ።
ዛሬም ጎህ ቀደደ
መስከረም ያለ እድሜው በአደይ ተገመደ
ዘንድሮም እንዳምናው
ጅራፋት ሲያዜሙ
በትራን ሲጋሙ
ስዕላት ሲቀልሙ ።

ሙልሙላት ሲደፉ
ኮረዶች ሲጋፉ
ጎረምሶች ሲላፉ።
ይሄ ሁሉ ሲሆን
አንቺ ግን የለሽም
ድክመትሽን ስደክም ።
@getem
@getem
@poem_with_mela
ለሽፍደት! ለፍቅር! ለምሽታችን!


የ“ደፋሩ” ገብሬ - “ደፋር ግጥም”
-------------------------------------------
“የመጀመሪያ ቀን” የተሰኘውና በገብረ ክርስቶስ ደስታ የተጻፈው ግጥም ከተጻፈበት ዘመን
አንፃር እጅግ "ደፋር" የሚሰኝ ግጥም ነው - “ኤሮቲካዊ” ይዘት ያለው። የተፃፈበት ጊዜ
ባይገለጥም በ1950ዎቹ መጨረሻ ወይም በ1960ዎቹ መጀመሪያ የከተበው ለመሆኑ
መገመት አይከብድም። እንዴት ቢባል አብዛኛዎቹ የገብሬ ግጥሞች በነዚህ ዓመታት
መካከል ነውና የተፃፉት። በዚያን ጊዜ አይደለም በአሁኑ ዘመን (በዚህ በ"ዘመነ- ላቦሮ")
እንኳን "ዓይንህን ላፈር ፣ ውጉዝ ከመ አርዮስ” ሊያስብል የሚችለው ይህ "ደፋር ግጥም"
በደፋሩ ገብሬ በዚያን ጥብቅ ጊዜ መፃፉ የሚደንቅ ነው። እስኪ አንብቡትና ፍረዱ።
በአርጀንቲናዊቷ ሠዓሊ ሄሌና ዊርዝቢኪ በተሣለው “Erotic Night” ሥዕል አጅቤ እነሆ
ብያችሁ አለሁ። መልካም ንባብና መልካም መደመም። አስተያየታችሁ ይጠበቃል -
ከተቻላችሁ !
* * *
ለመጀመሪያ ጊዜ
----------------------
(ገብረክርስቶስ ደስታ)
አየችው
ተያዩ፣
አየና ወደዳት፤
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ
ሁለት ራት መጣ፣
ብርጭቆ ተጋጨ፤
አየችው
ተያዩ፣
አያት
ተሳሳቁ፤
በጠረዼዛው ሥር
ጭኗ ጭኑን ነካው፤
ሲያያት
ፈገግ አለች፣
አየችው
ፈገገ፤
እጇን በጁ ያዘው
ጠበቅ አደረጋት፣
ጠበቅ አረገችው፤
ከፈሉና ወጡ፤
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ነደዱ፤
ትንፋሻቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ፤
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ !!!


"ናካይታ"💚

@getem
@getem
@Nagayta
# ጦቢያ ግጥም በጃዝ 102ኛ ምሽት ጥር 6 ዕሮብ

ቦታ:- ራስ ሆቴል
መግቢያ :-100 ብር
ሰዓት: 11:00

@getem
@balmbaras
ቀናሁ

=== ===
ለመንኩት አምላክን
አበባ እንዲያደርግሽ
ንብ ሆኜ መጥቼ
እየዞርኩ ልቀስምሽ
ማለዳ ማለዳ
በበራፋችሁ ሳልፍ
ብመለከት ጊዜ
ፀሀይ ስትሞቂ
ፈጣሪን ለመንኩት
"ፀሀይ አርገኝ "ብዬ
ውብ #ሠውነትሽ ላይ
እንዳርፍ ዘና ብዬ፡፡
ያንገትሽ #ማተብ
ያለ ማንም ከልካይ
ገብቶ ሲንከላወስ
በጡቶችሽ ክፋይ
ብመለከት ጊዜ...
ቀናሁ በማተብሽ
ቀናው በመስቀሉ
ጡትሽን ተንተርሶ
በመዋል በማደሩ፡፡
#ቅዳሜ እረፋድ ላይ
ስትመጭ ከገበያ....
ትኩስ ለጋ ጎመን
በክንድሽ ታቅፈሽ
በሌላኛው እጅሽ
ዘንቢል አንጠልጥለሽ..
ብመለከት ጊዜ...
እንደ ጎመን መሆን
ተመኘው ለቅፅበት
በአካሌ እንዲሠራጭ
የአክናድሽ ሙቀት
ተመኘው ለቅፅበት
መሆን እንደ ዘንቢል
ውብ ለሥላሳ ጣትሽ
በገላዬ እንዲውል፡፡
ትናንትና ደግሞ..
ከኛ ቤት ፊት ለፊት
ውሐ ስትቀጂ
ከየት እንደ መጣ
ያልታወቀ ንፋስ
ቀሚስሽን ገልቦ
ጀምበር የመሠለ
ያ ውቡ ጭንሽን
ቢያሳየኝ በስሱ
እምልልሻለው
ቀናሁ በንፋሱ፡፡

doju.

@getem
@getem
@getem
😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄንን አዲስ እና ምንም ያልተሰራበት ብራንድ የ tattoo ማሽን መግዛት የሚፈልግ
+251934039346
@Cher46 ያናግረን

@seiloch
#ዝም_ያለ_መሸታ

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

የተጋባ ዋንጫ
ተደቅኖ ፊትሽ ፥ ጠላሽን ስጠማ
ቦለቲካው ይዞሽ
በሆዴ አመሀኝተሽ ፥ ጆሮዬ ሲደማ
በሰዎች ቋምጬ ፥ በዋጥኩት አረፋ
ከሳባ ጀምሮ
የነገርሽኝ ታሪክ ፥ በኔ ዘመን ጠፋ ።
ኧ........ረ #ቅጅልኝ !!
#ሆ !!......
እገሌ....... እንዲህ አደረገ
እገሌ........ ይህን አመጣ
በዚያን ዘመን ........የተገፋ
በዚህ ግዜ........ ቀኑ ወጣ
ይሄኛው ለሾርኒ ፥ ለቧልት ተቆጣ
ይህኛው ደንገጡር ፥ ጭን-ገረድ አወጣ
#የኔ_ዘር ....
#ያንተ_ዘር...
ይህን አወደመ
ይህን አመረተ
አትበይኝ ................ #ወ_ዘ_ተ
በሄድኩበት ሁሉ
ዘር ሽሉ እያደገ ፥ ወላድ እየሞተ
ቅርናት ቅርናት ቃና ፥ ሀገር እሳት ገብታ ፥ ስለተሻተተ
ልጠጣነው የመጣሁ...
እራሴን ልረሳ
የጆሮዬን ቅርሚያ ፥ ሳይወድል ላከሳ
ዝ.........ም ብለሽ ቅጅልኝ
ዝ..........ም ብዬ ልጠጣ
ለመሳም ካልሆነ በቀር
ከንፈርሽ አይንቀላወስ ፥ ምላስሽ ጉልበት አያውጣ።

@Abr_sh

@getem
@getem
@GETEM
#ምን_ይውጠኝ_ነበር?
:
:
:
ዕድል የቀናኝ ለት ዐይኖችሽን ካየው
ድንገት እንኳ ላፍታ፣
የጆሮዬን ታምቡር ሊቀደው ይደርሳል
የልቤ ትርታ።
:
:
ከጨበጥሺኝ ደሞ ለስላሳው መዳፍሽ
አርፎ መዳፌ ላይ
አንቺን በነካ እጄ ሌላ ሰው መጨበጥ ያስጠላኛል ብታይ።
:
:
የገጠሙ እንደሆን ሰላምታን አስታከው ጉንጭሽና ጉንጬ፣
ከርማ እንደተፈታች እንደንቦሳይቱ አልጠግብም እሮጬ።
:
:
እንደው የገረመኝ
በድንገት ተያይተን
ሰላም ተባብለን
ጉንጭ ተገጣጥመን
እኔ ላይ ካሳደርሽ ያንን ሁሉ ስሜት
ያንን ሁሉ ነገር፣
ማርን በሚያፈልቁት በከናፍሮችሽ
ከንፈሬን ብትስሚኝ ምን ይውጠኝ ነበር?

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu

@GETEM
@GETEM
የጥር 7ቱን ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር የግጥም አብዮት ልጆች የተካተቱበት እና ለዚሁም መድረክ ብለው ብዙዎቹ ከክፍለ ሀገር ድረስ መምጣታቸው ነው ።
እዚሁ መንደራችን ላይ አብረውን ሲውሉ ብዙ ቁብ የማንሰጣቸው ባዘሉት ሀሳብ እና ፍልስፍና እንዲሁም የግጥም ጥበብ ደግሞ ወደፊት ሀገራችን አንቱ ብላ የምትጠራቸው ልጆችን ያካተተ ነው ።
እኛ ማለትም (እኔና አብሪሽ) ይሄን መድረክ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና የምንለው ኪሳራውን ተቋቁመን ቅድሚያ ለስሜታችን በመስጠት ሲሆን ከምንም በላይ መድረክ ያላገኙ ልጆች መድረክ እንዲያገኙ በማሰብ ነው ።
ጥር 7 ሁላችንም በፓናሮማ ሆቴል እንገናኝ !!
👍1
ድርሳነ ፍቅር!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።
#አንቺ የእኔ ጣዖት!
እኔ ያንቺ አማኝ
የምዕመኑ ጠሎት ቅዳሴና አዛኑ
በየት በኩል ይሰማኝ?
።።።
እሳት ያንቺ ገላ ~ መብረቅ ያንቺ መውደድ
በየት መንገድ ልጓዝ ~ እምን ላይ ልራመድ?
ዓይኖችሽ ጉልላት
ጥርሶችሽ በረዶ
ጣቶችሽ አለንጋ....
ሠንበር የወረሰው ~ ቁስል ልቤን ይዤ
እንደምን አልሰጋ?
።።።።
#እኔ
መድሀኒቴ አንቺ
በሽታዬም አንቺ
አንቺን እየዋጥሁኝ ~ አንቺን የምታመም
ባንቺ እየታመምሁኝ ~ ባንቺ የምታከም
.
ባለ አንድ ድዌያም ~ ባለ አንድ ክኒና
ወይ አልሞት ፥ ወይ አልድን
ወይ አልኖር በደህና!

@getem
@getem
@getem
#ዛሬ ራስ ሆቴል እንገናኝ!

# ጦቢያ ግጥም በጃዝ 102ኛው ምሽት በራስ ሆቴል ይቀርባል


እንደምነው ሮብ፤ የሃሙስ ጓደኛ ፤
እንገጥማለን ብለን፤ ሸዋ ገባን እኛ! !!!!
ነገር የመጣኝ ቀን ፤ ነገር እገጥማለሁ ፤
ግጥም የመጣኝ ቀን፤ ግጥም እገጥማለሁ ፤
ያገጣጠመኝ ቀን ግጣም እገጥማለሁ ፤
መግጠም ነው እንግዲህ ፤
ከዚህ ወዲያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ ፤
አለም አይደለም ወይ ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ ።

ይኸው ነው!💚
@getem
@balmbaras
ለንጉሱ ልደት
❤️👑❤️

ይኸው ነው! !!!!!

እየውልህ ተሜ ፤
ከግድግዳው አናት ፤
ከሹርቤው ጋራ ፤ የሚገማሸረው ፤
የኔና ያንተ አባት ፤
መይሳው የሚሉት ፤ የባንዳ ጠላት ነው ።
እናም እኔና አንተ ፤
ዘወትር ጠዋት ማታ ፤
እንደ ቀማኛ ሰው ፤ የምንሳደደው ፤
ይኸንን ሹርቤ ፤
ይህንም ጉንጉን ሰው ፤
እንዳላማ ሰንደቅ ፤
ከፍ አርገን ከፍ አርገን ፤ ስለሰቀልነው ነው! !!
ይኸው ነው! !!!
ማርያምን !!!!! ይኸው ነው! !!!

(((( ጃ ኖ ()💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
#ይታየኛል
:
:
ሴት ከሆን ማናግር ስልክ ተደውሎ
አናትሽ ላይ ወቶ የሆነ ዛር ዘሎ
ምትደውለው ማናት?
የት ነውስ ምታውቃት?
ደርሶ ቁጥርክን ለምንስ ሰጠሀት?
አምጣው ስልኩን በቃ!! እንደውም ላዋራት!!
ሁሌ ባልሺኝ ቁጥር አላማርርሽም
አሁንስ ሰለቸሺኝ መቼም አልልሽም።
:
:
ሁለታችን ሆነን ስናቀና መንገድ
በፊት ከማታውቂያት ወይ ወዳጅ ወይ ዘመድ
ድንገት ስንገናኝ ከሁሉ አስቀድመሽ
እኔ ባለቤቱ አንቺ ግን ምኑ ነሽ?
ባልሺም ጊዜ ከቶ አልነደድኩብሽም
ለሰው ይምሰል እንጂ ለኔ ግን በፍፁም ጨቅጫቃ አይደለሽም።
:
:
ስልኬን ስትነካኪ ካየሽ የሴት ፎቶ
ቁጣሽ ግሎ ንሮ ወዲያው ደምሽ ፈልቶ
ባይንሽ ቂጥ እያየሽ የጥያቄ ውርጅብኝ
ገና አንዱን ሳልመልስ ስላዘነብሺብኝ
ጭራሽ አይከፋኝም
አዎንታዊነቱ እኔን አይጠፋኝም።
:
:
እቤታችን ሆነን ተቃቅፈን በደስታ
እየተሳሳቅን ፊልም ያየንም ለታ
አንዲቷን ተዋናይት እንደው ሳላስበው
ያልኩሽ እንደሆነ በጣም ነው ምታምረው
ከባጡም ከቆጡም ሰበቦች ደርድረሽ
እየገላመጥሺኝ ቻናሉን ቀይረሽ
ሌላ ሌላ ነገር ስትከፍቺብኝም
ጨቅጫቃነት መስሎ እኔን አይሰማኝም።
:
:
አንዳች ጉዳይ ገጥሞኝ
ከደጅ ውዬ ማታ እቤቴ ስመጣ
እየቀየጥሺብኝ ሰላምታና ቁጣ
ከማን ጋር የት ገብተክ ከማን ጋር የት ወጣ
ከማን ጋራ ምን በልተ ምንስ ደግሞ ጠጣ
ብለሺኛል ብዬ አልበሳጭ እኔ
የልብሽ ነው እንጂ የአፍሽ ለምኔ።
:
:
የሚገርመው ነገር ...
ዘንድሮ ሰው ሁሉ የት ገባ የት ወጣ ጭቅጭቅ መስሎታል
"ቅናት" ካሉት ቅኔ ሰሙን ብቻ አንግቦ ወርቁን ዘንግቶታል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ ...
ገብቶኛል ድብቁ
ጌጥ ሆኖኛል ወርቁ።
:
:
እንዲ አረግሺኝ ብዬ እንዲያም አልሺኝ ብዬ
አላፈገፍግም ፍቅራችንን ጥዬ።
:
:
እንደውም የኔ ውድ
በየቀኑ ቅኚ በየቀኑ በዪኝ እጅግ ደስ ይለኛል
ከቅናትሽ ጀርባ ፍቅርሽ ይታየኛል
"ቅናት" ሚሉት ቅኔ ወርቁ በርቶልኛል።


#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu

@getem
@getem
@getem
ዛሬ ታላቁ ልብ የተወለደበት ቀን ነዉ
ጥር 6 1811
እኔ አባትህ...
ከዘፍጥረቴ ስጀምር
ከጦቢያዬ አብራክ ስወጣ
ከአፈሯ እሸት ቀምሼ
ከምንጯ ውሃ ስጠጣ
ብትኑን ሰብስቤ ይዤ
የሩቁን ባንድ ጠቅልዬ
"ይማሯል እንደ አካልዬ
ይዋጓል እንደ ገብርዬ"
ብዬ
ዝመናን ጋፋት ላይ ጥጀው
ልብ ላይ እድገትን ስዬ
እኔ አባትህ...
የታጠቅ የጦሩ ጌታ
ላገሩ ተጓዥ አውታታ
እውቀትን አጭቶ ያገባ
በጃኖ በነጩ ኩታ
ለእድገት እሰየሁ እንጂ
ለውድቀት ጦር የማልፈታ
እኔ አባትህ...
ዝንት ዓለም የማስበውን
ከዘመን በፊት ጀምሬው
የእውቀት ብልጭታ ገመዱን
ከዙፊል ውሃ ነክሬው
እውቀት ይበጃል ብየ
ላገር ለወገን ነግሬው
አንድነትን ከፍ ለማድረግ
ትንፋሼን ላገር ገብሬዉ
እኔ አባትህ...
ያባት ያያቴ ታሪክ
መክሰሙ ያንገበገበኝ
የድንቁርና ጋሬጣ
ከእርምጃየ ያልበገረኝ
መድፉን ሰርቼ ያልጠገብኩ
መርከቡም ያላስቸገረኝ
አድምጠኝ ልጄ ልንገርህ
አጤ ቴዎድሮስ እኔ ነኝ
በል ተነስ ቁጭ ካልክበት
መቅረዙን ያዘው በእጆችህ
መማር ነው ትልቅ ብርሓን
ጨለማ ይራቅ ከደጅህ
ካባትህ የወረስከውን
አቀብል ለልጅ ልጆችህ
ውል ሳትይዝ ሙግት ላትገጥም
'ሀ' ሳትል ፊደል ላትጠራ
እውቀትን ታጥቀህ ተነሳ
እሱ ነው ደምቆ የሚያበራ
በታሪክ ትልቁ ዶሴ
ሀገር የሚጠራበት
ካለፉት እየቀሰመ
እውነቱን የሚረዳበት
ዛሬውን አፅንቶ አቁሞ
ነገውን የሚቀርፅበት
ቴዎድሮስ ከሚሉት መቅረዝ
ሶሎሞን ሳህለ
@getem
@getem
#jeko
"ማወቄን ጠላሁት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*************
ያኔ ያኔ
በኋሊት ምናኔ።
ከየኔታ እግር ሥር
በጨቅላነት እድሜ ፊደል ስንቆጥር።
ያን የንጽኸት ልኸቀት
ያን የልግሰት ሹመት
አስተውለው በነበር በልሙጩ ሹረት
ዛሬን ባውቀው ድንገት
ድንገት ድንገት ድንገት
በአስኳላዊ ትዕንቢት
በመሀይም ትዕቢት።
ሆነብኝ መጨረት
ሳይፈሱ መረጨት
ሳይርሱ መጎንጨት።
እናም
"ሀ" በል ሲሉኝ "ሀ"ን ስላት
"ለ" በል ሲሉኝ "ለ"ን ስላት
"ሀ"ም ግዕዝ ናት
"ለ"ም ግዕዝ ናት
እያሉ
የዛገ ብስ ጣርያ ያለቀ እድፍ ድንጋይ
የሳሳ ሰሌዳ ያልፈገገ ሰማይ።
ባልታደሰ ሙዳይ ጠመኔው ተቀምጦ
ጨዋነቴ ረቅቆ ብጥባጦቴ በልጦ።
ግርፋቴ ሲነግስ
ከዕውቀት ማማ ላይ ውድቀቴ ሲጠነስ።
ደብተሬ ትዝ አለኝ
ደብተሬ ትዝ አለኝ
ባለ አስራ ስድስቱ
ስምሽን እንደ ድር የደረድኩበቱ
ትዝ አኝ ትዝታሽ
ቤተ - መጻፍት በሚል ስውል ቤተ - ልብሽ።
ማወቅ ይሉት ክፉ
ለሌላ ሳይሆኑ ለራስ የመትረፉ።
አንቺን አስረስቶ
ፍቅርሽን አስቶ
ሊቅነት ሲቸረኝ ልቅነቴን ሽቶ።
ሀገሬን ሚያሰኘኝ ከሀገሬ ነጥሎ
ማወቄን ጠላሁት መማር አንቺ ጥሎ።
አውቀሽኝ ሀገሬን
ሳላውቅሽ መኖሬን።
.
.
.
@getem
@getem
@poem_with_mela
ላልቅስበት
[ ቴዎድሮስ ካሳሁን_ቴዲ አፍሮ]

በነገር ፍም እሳት እያቃጠላቹ
ለማዘኔ ምክንያት እናንተው ሆናቹ
አታልቅስ አትበሉኝ ከፍቶኝ እያያቹ

ሁሉም እየጫረ እሳት ሲለኩሰው
ሻማ እንኳን ያነባል እንባ አውጥቶ እንደሰው!!
@getem
@getem
#jeko