ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
( አለሙ አዳፋ)
አክባሪ ተንቆ - ተከባሪ ልቆ
አዳማጭ ተረስቶ - ተናጋሪ ደምቆ
ከማወቅ - መታወቅ
ከማየት - መታየት...
ከመውደድ - መወደድ
ከመስማት - መሰማት...
ከሚመኝ ኗሪ ጋር
በምጓዘው መንገድ - በማልፋቸው ቀናት
ካንቺ ውጭ ለሌላ
ልቤ ቀጣፊ ነች - ነፍሴም ዱርየ ናት፡፡
.
አድባሬ ...
ሀገሬ❤️
@getem
@getem
@kaleab_1888
የሀበሻ ቅጥፈት
በሚካኤል አስጨናቂ


@getem
@getem
@getem
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

መውደድ በዝምታ
_____________

የኔ ልብ እንዲሁ ነው...

ዝምታ ያነቀው
ተጓዥ መስሎ ፈሪ፣
ለፍቅር ሸፍቶ፣
ተመልሶ ደግሞ፣
ፍቅርን አባራሪ።

ያንቺን ብርቅዬ ልብ፣
አጠምዳለሁ ብሎ፣
አሰሳ ፍለጋ
ሲንከራተት ውሎ፣
ኢምንት ስትቀረው፣
ፍርሀት የሚያጠምደው
ቆርጦ ይነሳና፣
አለሁኝ ይልና፣
የዝምታ ነፋስ፣
መልሶ የሚሰደው።

አይኖቼም ያው ናቸው....

አንቺ የሌለሽ ጊዜ፣
አንቺን ያልማሉ፣
ፀጥ ባለው ሌሊት
ከዕንቅልፍ ይሸሻሉ።
ካይኖችሽ ተዋደው፣
በፍቅር እሳት ነደው፣
ልተኛ ስላቸው፣
እምቢ ነው መልሳቸው።

ወዲያ ወዲህ እያሉ፣
በድቅድቅ ጨለማ፣
ያንከራትቱኛል፣
ጥርት አርገው ስለው፣
ከነ መላው አካልሽ፣
አንቺን ያሳዩኛል።

ድንገት ስትመጪ ግን...
ውልብልብ አይኖቼ፣
እንዳልተርክልሽ፣
የልቤን አውጥቼ፣
አይንሽን እንዳላይ፣
ፍርሀቴን እንዳልተው፣
ይከለክሉኛል፣
አትያት ይሉኛል፣
ገላጣው መሬት ላይ፣
ቁልቁል ተሰክተው።

አንደበቴም ያው ነው....

ሲያገኝሽ ይዘጋል፣
ሲያጣሽ ይከፈታል፣
ቀን ቀን ዝም ይልና፣
ሌሊት ይበረታል።

ማንም በሌለበት
ያለ አንዳች ፍራቻ፣
እልፍ አእላፍ ቃላት፣
እየደረደርኩኝ፣
አንቺን ማሰብ ብቻ።

ድንገት ሳገኝሽግን...
ከንፈሬ ታትሞ፣
ምላሴ ይታሰራል፣
ድንጉጥ አንደበቴ፣
"ምን ልበል" እያለ፣
በቃላቶች መሐል፣
ተለጉሞ ይቀራል።

እጆቼም ያው ናቸው....

አንቺን ያዩ ጊዜ፣
ከሁዋላዬ ዞረው፣
ይቆላለፋሉ፣
ቀጭኑ ወገቤን፣
ምሽግ ያደርጋሉ፣
ለስላሳ ጉንጭሽን፣
ሊዳብሱ ብለው፣
ፈርተው ይመለሳሉ።

ደግሞ አንቺ ሳትኖሪ...

ድንግርግር እጆቼ፣
"ብዕር አምጣ" ይሉኛል
ስንኝ አሰባስበው፣
ለሚያሰቃይ ፍቅርሽ፣
ግጥም ያፅፉኛል።

የኔ ፍቅር እንዲህ ነው...
ብቻዬን በመሆን፣
ያለአንዳች ፍራቻ፣
እልፍ አእላፍ ቃላት፣
እየደረደርኩኝ፣
አንቺን ማሰብ ብቻ።

በቃ እንዲህ ልውደድሽ....

ከጥርሶችሽ ጋራ፣
የሚስቅ ፊትሽን፣
በማያዩ አይኖቼ፣
አካልሽን መንካት፣
በሚፈሩ እጆቼ፣
በህልፍ አክናፍ ብቻ፣
በሩቁ እያሰብኩሽ፣
ሳልቀርብሽ ሸሽቼ።

ግን አንድ ተስፋ አለኝ....

በጨለማው አለም፣
አጥርተው የሚያዩሽን፣
አይኖቼን ከፍቼ ፣
ታትመው የቆዩትን፣
ፈሪ ከንፈሮቼን፣
ለቃላት ፈትቼ፣
ልብሽን መማረክ፣
የተሳነው ልቤን፣
በግድ አበርትቼ፣
እንቀፋት ብለው፣
ይንደረደሩና፣
ደረስን ይሉና፣
ፈርተው የሚደበቁ፣
ተሸናፊ እጆቼን፣
እንደ አሞራ ክንፍ፣
በሰፊው ዘርግቼ፣
በህይወት እስካለሽ ፣
በህይወት እስካለሁ፣
ግድ የለም ጠብቂኝ ፣
የሚርቅ ቢመስልም፣
አንድ ቀን መጣለሁ።

( ጠብቂኝ)

ዮሐንስ ገርማሜ

@getem
@getem
@getem
👍2
እረክተን ሳንጠጣ ፥ አለቀ ተደፍቶ
በቅጡ ሳይፈላ ፥ ሚገነፍል በዝቶ
.
« ሚኪ እንዳለ»

@getem
@getem
@getem
ቅድሚያ ለሀገሬ
_____

ጥሩ ሰራህ ብለው.... ወርቅን
ቢሸልሙኝ፣
የስኬት ዘውድ ብለው...አክሊል
ቢደፉልኝ፣
ምኑ ሊያስደስተኝ...
........ ..........
እናት ኢትዮጵያዬን
መሰረት ዋልታዬን...
ከወዟ ሊቀማት፣
ከርስቷ ሊሻማት፣
በስውር የመጣ፣
ካየሁኝ ምቀኛ፣
እንኳን አንድ ሌሊት
ደቂቃም አልተኛ!!!
…………… …………………

ዮሐንስ ገርማሜ

@getem
@getem
@getem
ወንዘኛ!!!!!!!


በቆሙበት መሬት ፤
የተደበቀውን፤
ያንን የውሃ ጋን፤
ቆፈር ቆፈር አርገው ፤
የእርሻውን ማጠጫ በውሃ እንዳይሞሉ፤
የኛ አገር ጥመኞች፤
ወደ ገዛ እርሻቸው፤
ውሃ እንፈልግ ብለው ፤ ጠልቀው ሳይቆፍሩ፤
በአጀብ በሆሆታ፤
ወንዝ እናምጣ ብለው ፤
የገዛ እርሻቸውን፤ ጥለው ኮበለሉ፤
ውሃ ባልጠፋበት፤
ወንዝ እንፈልግ ብለው፤ ወንዝ ገብተው ቀሩ።


ባለሁበት ቀየ ፤
የመሬት ስር ውሃ፤
ቆፍሩኝ እያለ ቁሞ በተጠንቀቅ፤ ልክ እንደበረኛ፤
ወንዝ አምጡልኝ ብሎ ይኸው ይናውዛል ስስታም ወንዘኛ።
በቆምኩበት ምድር ፤
የቆመ ውሃ አለኝ፤
ዶማየን አምጡልኝ ፤
ወንዝ እፈልግ ብየ፤ውሃየን አልሰጥም፤
ግን እስከዚያ ድረስ፤
ውሃ ጠማኝ ብየ ወንዝና ወንዘኛን አልለማመጥም።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋዋ እምወድሽዋ ቅዳሜ! ለናተም ያማረ ቅዳሜ ይሁንላቹ!

@getem
@getem
@balmbaras
We do have a Turkey scholarship opportunities in advance for each department. Hopefully students who take their Entrance exam in 2011 can benefit alot from this chance. Wait us for the detail of scholarship.
@foreignwork
@Coolrepublic
Any one who is university or college graduate who wants to work in Poland can contact us now. For this round we need individual who do have a renewed Ethiopian passport and willing to work in a factory with a granted safety and reasonable payment. This will enables you to get two years work permit and Schengen VISA.
@foreignwork
@Coolrepublic
ግራ ነው መንገዴ
°°°
፰\፩\፪፳፲፪ ©ዘርዓሰብ
°°°

ሰዎች ይመክራሉ በለመዱት መንገድ በዚህ ሂድ እያሉ
የቀደመውን ሰው ያልተመረመረ ህይወት ሳያሰሉ፤

እኔ ግራ ተጓዥ፣ ብቻ ጉዞ መራጭ፣
ሰው የማይደርስብኝ፣ ከሰው የማልጋጭ፤

የግራውን መንገድ ማንም አልሄደበት፤
ከሊቅ እስከ ደቂቅ በቀኙ ብቻ ነው ሁሌ የሚጋፉበት።

አምላክን በጸሎት ግራ አውለኝ አልኩት፣ አዋለኝ በግራ
ቃሌ አከበረችኝ የጸሎቴን ምላሽ ቃልህን አክብራ።

አይዝልም ጉልበቴ ምን ቢርቅ መንገዱ
አጀብ ይቅርብኝ ቀኝ በሚል ሰበብ በጅምላ መሄዱ

ሁሉ በቀኝ ብሎ ግራውን ቢተወው
ፍኖቱ ባይሰምር ባይሄዱበት ቀድመው
ጠልፎ ጣይ የለውም መንገዱ ቀና ነው።

ጻድቁም እርኩሱም፣ ደግም ይሁን ክፉ
ሁሉም በቀኝ ነው ታትረው የሚጋፉ።
ከሰይጣን ሰይጥነው የሚጠላለፉ።
ከመተራመስ ውጭ አልታየኝም ትርፉ።

በኑሮ ትጋት ውስጥ፣ ግራው ቀንቶልኛል፣ ይመስክር ጅማቴ
በርምጃ ነው እንጂ፣ በጠልፎ ጣይ ሰዎች፣ አልዛለም ጉልበቴ።

ከሚተመው ጋራ በቀኝ ለመብረር ከማብቀል ይልቅ ክንፍ
ለብቻ ባርምሞ ባልተሄደበት ላይ ያደርሳል እግር ጽንፍ።

\ዘርዓሰብ\

@getem
@getem
@getem
#ጥላዬ

ፊን-ፊን ስትይ ፥ በሰማዩ ጋሪ
ሽቦ የታደለ ፥ ዣንጥላ ወጣሪ
ጥበብ ከነ መርፌ ፥ መጨበጡን ረሳሽ
ያገው ጥላ መሰል
ከፍ ያልሽበት ሰማይ ፥ ለዝንት የዘረጋሽ።
ይልቅ ተመከሪ ፥ ገርነት አይግፋሽ
አውታርሽ መብዛቱ
ገትሮ የሚውል ፥ የሚጥል ቃሬዛ
አይምሰልሽ ዋዛ !!!
ዝናብ ካላስጣለ ፥ ሽንቁሩ እየበዛ
ፀሀይ ካልከለለ ፥ ማድያት ከነዛ
ማን ወዶ ሊጠለል ...ማን ስርሽ ሊገዛ
የከበበ ሳይሆን
ያስተዳደረ ነው ፥ እድሜ የሚገዛ።

ነሀሴ 2011
#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem
#ቸል እያሉ መጉደል! 

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።
ለቅፅበት ህላዌ ፥ ተግተው 'ሚባትሉ

በህብር ታጅበው ፥ ጭረው የሚውሉ

ዶሮዎች!

ለቅመው አዳሪዎች...

ከእጀባው ወጥታ.. .. ከመንጋው ተጠቅታ

በታደነች ጫጩት.. .

ሀዘን ተሸብረው ፥ ለስጋት ተድረው ፥ ጮኸው ይንጫጫሉ

ከአፍታ በኋላ.. .

ዳግም ፍርሀት ሽረው ፥ በኗሪነት ተስፋ ፥ ጥሬ ይለቅማሉ ።

#እነዛ ዶሮዎች.. .

አንድም በፍርሀት 

አንድም በቸልታ

አንድ ጊዜ በጩኸት

አንዴ በፀጥታ...

ጥሬ ሲናጠቁ ፥ መሬት እየጫሩ

ከቁጥር ተናንሰው ...

ከመንጋነት ጎድለው ፥ ምንም ሆነው ቀሩ።

#አሁን በዛ መሬት!

ለቅፅበት ህላዌ ፥ ተግተው 'ሚባትሉ 

በህብር ታጅበው ፥ ጭረው የሚውሉ

አዳዲስ ዶሮዎች.. .

ጭሮ አዳሪዎች.. .

አንድም በፍርሀት 

አንድም በቸልታ 

አንድ ጊዜ በጩኸት

አንዴ በፀጥታ...

ኗሪ ነን እያሉ ... ጥሬ ይለቅማሉ ።

#እኔ

#ድመት ይታየኛል!

እንደ ሙት መልዓክ ፥ ጥፍሮቹን ያሾለ

ነፍስን ጌጥ አድርጎ ፥ አይኖቹን የኳለ

ጨለማውን ህልፈት ፥ ጀርባው ላይ ያዘለ

ቀስ እያለ ይቀርባል.. .

...........................፥ ቸልታቸው አለ ።


@getem
@getem
@getem
ጊዜ ልጠይቅህ
°°°
ጉልበት ክንፍህ አይዝል የማትደክም በራር
ቅንጣት ድጭ አይልብህ ህይወት ስትሸበር።

በዘይቤ ፈሊጥ ሰው ሁን ልጠይቅህ
ሳታስጠብቅ መልስ በየትም ስላለህ

ለሰቆቃ ረዝመህ፣ ለሀሴት ማጠርህ
ለኛ የማይገባን ምንድነው ምሥጥርህ?

ጭንቀት ለጠናበት፣ ሀዘን ላናወዘው
ለምን ይሆን ቀኑ ካመት የሚረዝመው?
በመፈንጠዝ ሰዓት፣ በሀሴት በፍቅር
ለምን ይሆን ቀኑ ከደቂቃ የሚያጥር?

ራስገዝ ነህና አስኳለ ኅላዌ ማዕከለ ሁሉ
የግዑዝ የህይወት የዳር የማህሉ
ንገረን ምሥጢሩን፣ የሁለንታ ጥጉን
የማይሆን በማሰስ በከንቱ እንዳንባክን
ጊዜ ሆይ እባክህ ወዲ በል መልስህን።
°°°
ከዘርዓሰብ ሣጌጥ
፲፩-፩-፪፳፲፪ ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👍1
ኢትዮጵያ
(ደሱ ፍቅርኤል)
ያገራችን ስሪት
ሁለት መልክ አለው ወተትና ቡና
ግማሽ ክርስትና ፥ ግማሽ እስልምና
ኢትዮጵያዊነት - ማንኪያ የምንለው
የሚጣፍጥ ፍቅር - ስኳር የምንለው
ሁሉን አቀፍ ሀገር - ስኒ የምንለው
ቡናውን ከወተት
አማስለው ቀየጡት
እናም
ቡና መሆን ቀርቶ ጥቁርነት ጠፍቶ
ወተት መሆን ቀርቶ ነጭነት ተረስቶ
ባለ ቡላ ቀለም ሆነዋል ማኪያቶ
ታድያ.............
ማንም እጁን ሰዶ ውህዱን ሊደፋ ስኒ ሲያዘነብል
ያየኸው እንደሆን - ይህን ቃል ልብ በል
የሆነውን ሁሉ ለልጅህ ስትነግር
ማኪያቶውን እንጅ ቡናውን ደፋ አትበል
ወተቱን ደፋ አትበል
@getem
@getem
@getem
👍2
ዳሪክ የጥበብ ምሽት

በምሽቱ ግጥም
ወግ
ዲስኩር
የስዕል ሥራውች ይቀርባሉ
ሐሙስ መስከረም 15 /2012 ዓ/ም
በዳሪክ ቡና
ኮሌጅ(አዳማ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት)

@getem
@GETEM
@GETEM
ራያ ነኝ ወራባየ፤
የአናዎቹ ልጅ የነ ሸህየ፤
አይነግረኝም ወይ፤
በዋጃ ግድም ያነን ልጅ ያየ።
እርጎየ ሙሄ፤ የራያይቱ፤
ቆቦ አላማጣ፤
መውደድ ገደለኝ እኔ ልጅቱ።


ቀልቤ ሲሳከር ግራ ገብቷቸው፤
አረዳው ሁሉ ዱኣ ገብተዋል አላህ ይርዳቸው፤
ላዩን መሆኒ ታቹን በዋጃ፤
ይኸው እግር በእግር፤
ያመላልሰኛል የነካኝን እንጃ።
ትፍትፌ ማይ ማይ ጉፍታየ ሸጋ፤
ይኸው ይዣለሁ ፤
በየመንገዱ ያንን ገምሻራ እሱን ፍለጋ።
መገን መውደድ!!""

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ለውብ ቀን!
💚

የሚያተኩሱ ግጥሞች!
Written by ደረጀ በላይነህ


ግጥም በስሜት እየናጠ፣ ሀሳብ ሰብስቦ፣ በዜማ ጥፍጥና ወደ ጆሮና ነፍስ
የሚደርስ ጥበብ ነው:: ይሁን እንጂ ስሜት ብቻውን ግጥም አይሆንም፡፡ ኢ.
ኤ. ግሪኒንግ ላምቦርን የሚሉትም እንደዚያ ነው፡፡ እኔም በዚያ እስማማለሁ፡፡
ማዕበል ያናወጠው ባህር ሁሉ አሳ ይዞ ብቅ አይልምና።
ሀሳብ በስሜት ውስጥ ሊሳሳና ሊደድር እንደሚችል ግን መናገር ይቻላል።
አንዳንዴ በሰከነ ስሜት ከፍ ያለ አተያይ፣ የረቀቀ ስልት፣ የሚኮረኩር ቋንቋ፣
የጠነነ ምናብ ሊነጠብ ይችላል፤ አንዳንዴ ደግሞ ተቃራኒው፡፡
የዘላለም ገበየሁ ‹‹በገሃነም ሥር መፅደቅ›› የሚለውን የግጥም መጽሐፍ
ሳነበው፤ የስሜት ሃያልነት የከባቢ ጠረን፣ የዘመን ሀሳቦች ጠረን
አይቼበታለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም ‹‹ዳሞትራ›› የሚል የግጥም መጽሐፍ
ያሳተመው ይህ ወጣት ገጣሚ፤ ጥሩ ጥሩ ሀሳቦች መንቀስ፣ ዜማው ባልተናጋ
ስልትና በልከኛ/አጫጭር አርኬዎች ማስቀመጥ እንደሚችል ታዝቤአለሁ፡፡
በሚያዝናና ስሜት፣ የቆረፈዱ ሀሳቦችንና ምሬቶችን ለአንባቢ በማድረሱ
ተደስቼ ነበር፡፡ ብዙ የግጥም ሊቃውንት እንደሚስማሙበት፤ የግጥም ግቡ
መፈላሰፍ ወይም መስበክ ሳይሆን ነፍስን ወደ ፈንጠዝያ ማሳፈር ነውና
‹‹ዳሞትራ›› እንዲያ ነበር፡፡


አዲሱ መጽሐፉ ግን እንደ ‹‹ዳሞትራ›› አይደለም፤ አንዳንዴ በቁጣና ምሬት
ትካዜው አፍጥጦ ይታያል:: አጥንቱ ላይ ያለበሰው ሥጋ የአደይ አበባ ያህል
ቀለሙ አልደመቀም፣ የህጻን ልብ ያህል ጣፋጭ ሳቅ አልሳቀም፡፡ ግን ደግሞ
ለዛ ቢስና አስቀያሚ አይደለም፤ ኮርካሪ ስሜቶች ያንጠለጠሉት ወዛም ጥበብ
አለው፡፡ እስቲ የተወሰኑትን እንይ፡-


‹‹አማራነት ዛሬ››
የሚዘርፉት አልማዝ የሚያፈርሱት አድባር
የሚሸጡት ርስት የሚያደርቁት ባህር፡፡
*
ጠባቂ ያጣ ዛፍ የሚቆርጡት ዋርካ
የሚያረግፉት ቅጠል የሚያሄዱት ጫካ፡፡
*

በገነባት አገር ጧት ማታ ’ሚገደል
የተረሳ ታሪክ የተናቀ ገድል፡፡
(አማራነት ዛሬ)
ገጣሚው ሀዘን ውስጥ ነው፡፡ ‹‹አማራ››ን በለዋጭ ዘይቤ ውስጥ እየሳለ፣
ብሶቱን ቁጭቱንና ክሱን በስንኝ ዜማ ይዘምራል፡፡ ወይም ግራና ቀኙን
ይወቅሳል፡፡ ይህ የገጣሚው የራሱ ሀቅ፣ የግሉ ሚዛን ነው። ምናልባትም
ገጠመኞች ሊጠቅስ፣ ታሪክ ከወደ ኋላ ሊተነትን ይችላል፡፡ ብቻ ሀሳቡን
እየተነፈሰ ነው:: የጋለ ልቡን ወላፈን በስንኝ ቋጥሮ ለአንባቢው በዜማና
በውበት ማዕድ እየፈተፈተ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከቅርብ ጊዜው የፖለቲካ አየር፣
የአገሪቱ የለውጥ ማዕበልና የብሔር ግጭቶች ቀለም የሰጠው ሀሳብ ነው፡፡
ግጥም እንዲህ ነው፤ ከስሜት ይነሳና በስሜት ንፋስ ውስጥ የጊዜውን
ቀለም ያሳያል፤ የትርታውን ከበሮ ይደልቃል፡፡ የዘላለም ግጥሞች ባብዛኛው
የፖለቲካ ደጅ የሚያንኳኩ፣ ብሶት የሞላባቸው ናቸው፡፡ ቢሆንም ማስጠሎና
ምንቅርቅር አይደሉም:: አስተዋይ ሀሳቦችም አሉት፡፡

‹‹ሀገሬ መልሽ?!››
ጥቁር አፈር ይዘሽ ሳይቸግር ማዕድኑ
ልጅሽ ለምን ከሳ? ለምንስ ሳሳ ጎኑ?
ድህነት ’ሚባል ትልቅ ባላጋራ
ምነው አብሮ ኖረ ከልጆችሽ ጋራ
በአጉል ወሬ ናዳ በጭምብል ተጋርደን
በጥላቻ ናውዘን ፍቅር ገድለን ሄደን
ምንድነው ትርፋችን
በባዶ ቤታችን??
በማለት… ለምን ባዶ ሆንን እያለ ነው፡፡ የዳዊት ልጅ አምኖንን አፍቅሮ
በየዕለቱ ሲከሳ ‹‹የንጉሥ ልጅ ሆይ ለምን ከሳህ?›› እንዳለው የመጽሐፍ
ቅዱስ ታሪክ፤ ምንም ሳናጣ ለምን ከሳን? ለምን ሳሳን? ድህነት ለምን
በቆርፋዳ እጆቹ አቅፎ ያንገላታናል?... ለምን በገጠጠ ጥርሱ ይነጨናል?...
እያለ አገሩን ይጠይቃታል። በወሬ ናዳ እየፈረሰች፣ በፍቅር ረሀብ የምንሳቀቀው
ልጆችዋ፤ የጥፋቱ ሁሉ መነሾ ራሳችን ነን፤ የምናገኘው ትርፍ ግን ምንድነው?
የሚል አንደምታ አለው፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ቤታችን ባዶ ነው፤ በባዶ ቤት ምን
ያናጨናል? በሚል ቁጭት ከንፈሩን የሚነክስ ይመስላል፡፡ ግጥሙ ሊሪክ
ስለሆነ ስሜቱ ላቅ ያለ፣ ቁጭቱ የመረረ ነው፡።

‹‹ሞት ወይም ሕይወት››
ህዝቤ ሲያሳድዱት ለምን ይሰደዳል
ንብረትና አድባሩን ለምን ጥሎ ይሄዳል?
ንገሩት ወገኔን
እንደያዙት አሳ ባህር እንደከበደው
በሞቱ ብቻ ነው የሚድን ከፍዳው፡፡
ይህም ግጥም ባሳለፍነው አንድ አመት ውስጥ ያለውን አታካች ስደትና
መፈናቀል የሚያሳይ ነው፡፡ ‹‹ከዚህ ኑሮ ሞት ይሻላል!›› የሚል ይመስላል፡፡
ሰው የኖረባትን ቀዬ፣ ንብረቱንና ደብሩን ለቅቆ ከሚሄድ፤ ከዚህ ፍዳ ይልቅ
ሞት መቅመስ ከሰቀቀን መዳን ነው አይነት ነው፡፡ ግጥሙ አሁንም በሬት
የተነከረ፣ እንባ ያነቀው ነው፡፡ ግን ደግሞ የምንኖርበት በአይናችን ያየነው፣
በጆሯችን የሰማነው ሀቅ ነው። አንድ የስነ ግጥም ፕሮፌሰር፤ ‹‹ምሬትን
ሀዘንንና ልቅሶን ወደ ዘና አርጌ ለውጦ ሞቱን በተስፋ ቀለም ለብጦ ማቅረብ
የጥሩ ገጣሚ ሚና ነው›› ይላሉ፡፡ ቀጥታ እየጎፈነነ እየቧጠጠ ባይሆን
ይመረጣል፡። ዘላለም፤ እንደ ‹‹ዳሞትራው›› ዘመን ሁን ባይባልም፣ የተስፋ
ጥርሶቻችንን፣ የፈገግታችንንና የነገአችንን ቀለም፣ ፅልመት ጥርስ ላይ
አትሰካቸው መባል አለበት፡፡

የደረቁ የሀሳብ ገፆችን በሌላ የሕይወት መልክ የገለጠበት በቀጣዩ ግጥም
አይነት ለዛ ጠምቋቸዋል:: (ግን ጥቂት ሆኑ)
ከከንፈሮችሽ ዳር እድሜ ይወለዳል
ከእቅፍሽ ሲያነጉ መሞት ይሰደዳል
በጭኖችሽ መሀል ገነት ተገንብቷል
የፀደቀው ብቻ የኔ ገላ ላልቷል
ሀጣን ተዳፍረውሽ ሰብረው እንዳይገቡ የገነትሽን በር
የኔ ውድ ቅጠሪኝ ስጠብቅሸ ውዬ ስጠብቅሽ ልደር፡፡
ይህ የፍቅር ፍካሬ፣ የፍቅር አለም ውበት ነው:: የአለምን ኮተት አስጥሎ
በገነት ወንዞች ዋና የሚያስተምር ሊቅ! ሞትን እየገረፈ የሚያባርር የሕይወት
ንጉስ! ሀጢአን የማይደፍሩት፣ በቅድስና የተጠበቀ የድድቅ ቅጥር!
ከከንፈሮችዋ ማህጸን ውስጥ እድሜ የሚያረዝም መድሃኒት የሀሴት ነበልባል
ብቅ ይላል፡፡ አለም መአዛዋን ትቀይራለች፡፡ ታዲያ ይህቺ የሕይወት ቅመም
እድል ትስጠኝና ቀጠሮ ብታረፍድ እንኳ ሳልመረር ልጠብቃት፤ አንድ ቀን
አይደለም፤ ደግሜ ደጋግሜ ሌትና ቀን ልጠብቃት ይላል፡፡ ይህ የሕይወት
ሌላኛው የውበትና የተስፋ ክንፍ ነው፡፡ በዚህ መብረር እድሜ ያረዝማል!...


‹‹ሀገሬ አርጅታለች››
ሀገሬ አርጅታለች ጃርቶች በቀሉባት
እሾህ እያፀደቁ ወይን ነቀሉባት
ሀገሬ አርጅታለች
ከመታመን ክፍሏ
ከፍቅር ወለሏ
ጥላቻ ከተተ
እምነትና አንድነት በምድሯ ከሰሙ
ሰው መሆን ሻገተ፡፡
ወይን ተነቅሎ እሾህ ሲተከል መኖሩ ሀቅ ነው። ጃርቶች በቅለው ቀስት
ማስወንጨፋችንን ባለፉት አመታት አይተናል፡፡ ዛሬም እሳቱ እየላሰን፣ ክፋቱ
እያፈረሰን ነው፡፡ መታመን ጠፍቶ የጎሪጥ መተያየት ውስጥ ነን፡፡ አይናችንን
ጨፍነን ካልካድን በቀር ጥላቻ አንቆ ይዞናል፡። ታንኳችን በማዕበል
እየተናጠች ነው፡፡ እምነትና አንድነት ከስሞ፣ መለያየትና መናቆር ሰማይ ጥግ
ደርሷል፡፡ ይሁንና ሌላም ተስፋ አለ - እሸት ያንጠለጠሉ፣ ብሩህ ቀን ያረገዙ
ዜጎችም አሉን፡፡ ነፍሳቸውን ስለ ጎዶላችን ቤዛ ለማድረግ የተዘጋጁ ሕሩያን
አልታጡም፡፡ በረሀብ እያዛጋን በጥላቻ እየነፈርን እንዳንኖር፣ የታሪካችን
ምዕራፍ በሀዘን እንዳይዘጋ፤ አደባባያችን ላይ አበባ የሚነሰንሱ ከታሪክ ገጽ
አልተፋቁም፡፡


‹‹ንጉሳችንና ያንቺ መዘናጋት›› የሚለው ግጥሙም ይህንኑ የሀገር ነገር
ያዜማል፡፡
እንኳንስ አንድ ሰው
እንባሽን ሊያብሰው
መቶ ሚሊየን ሕዝብ ሊያድንሽ ቢተጋ
ሕመሙ ጽኑ ነው የቆሰለ ጉበት በጦር የተወጋ
እናልሽ እናቴ…
ጋብቻ ማፍረስ ነው የመዳንሽ ውሉ
አንቺን በልቶ መግደል
አንቺን መጥባት ብቻ
ችጋራም ማድረግ ነው የባልሽ
አመሉ፡፡
***
እንዲያው ቢሆን እንኳ…
ንጉሱን ብናምነው
የበዙ እባቦችን እንደምን አድርጎ አንድ ርግብ ይመራል
አንድ ሻማ ብቻ የጨለመ ሀገርን እንደምን ያበራል
ቤተ እምነቶች ዱዳ ሽማግሌው ዱጋ ጋዜጠኛው ዱዳ
እንዳልተወለደ እንዳልኖረ ሁሉ ሕዝብሽም እንግዳ፡፡
…ግጥሙ ይቀጥላል፡፡ የዚህ ግጥም ወቀሳ ብዙ እውነት አለው። ፍርሃትና
ጥርጣሬው፣ ነባራዊው እውነትም አሳማኝ ነው፡፡ በተለይ ሁለተኛው አንጓ ላይ
ያለው ሀሳብ በእምነት ተቋማቶቻችን፣ በጋዜጠኞቻችን… በአጠቃላይ
በሽንቁሮቻችን ላይ አተኩሯል፡፡
መጽሐፉ አሁን ባለንበት አገራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ መረር ያለና
የሚያሳዝንም ነው፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ሚዛን የሳተ ይመስላል፡፡ ወደ አንድ ጥግ
የሄዱ ግጥሞች አሉ፡፡ ገጣሚ የአገር ወገን፣ የሕዝቦች ተገን መሆኑን ግን
መርሳት የለበትም፡፡ እንደ መጽሐፍ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን ጭብጦቹ ከአንድ
ድንኳን የተመዘዙ፣ ባለ ተመሳሳይ ጭብጥና ድምጽ መሆን የለባቸውም፡፡
ስሜት የጥበቡን ዋልታዎች እንዳይበትን መጠንቀቅና ምሰሶውን ሁለንታዊ
ማድረግ ያስፈልገዋል፡፡ በተረፈ ገጣሚው ክፍተቶቹን ሞልቶ፣ በግሩም
ሥራዎች እንደሚመለስ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡


#ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ


ውብ ቀን!💚

@getem
@getem
@balmbaras
1
እንደ... እያልኩኝ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንደ በርሃ ሰው ውሃ እንድተጠማ፤
እንደተራበ ጅብ ጩኸቱ ሚሰማ፤
ስራ እንደሚወደው ታታሪ ገበሬ፤
እኔ ያንች ወዳጅ ምወድሽ አምርሬ፤
እንኳን አሁንቀርቶ በይወት እያለው፤
ድምፅሽን ሰሰማ አይንሽን እያየው፤
ህይወቴን በሙሉ ዘመኔን ይቅርና፤
እኔ ያንች ወዳጅ ሙቼም ያውነኝና፤
እሁን እንዳለሁኝ ያሁኑን ልንገርሽ፤
ምላሴ እስኪዝል ፍቅሬን ላዚምልሽ፤
ምክንያቱም ከሞትኩኝ ምንም ባፈቅርሽም፤
እንችን መውደድ እንጂ መናገር እልችልም።
እናም ውዴ እኔ እንዳልኩሽ፤
ከዚ ቀደም እንዳወራሁልሽ፤
ወተት እንዳየ ህጻን እየሰሰትኩልሽ፤
አበባ እንዳየ ንብ ሁሌ እየጓጓሁሽ፤
ምድር አፏን ከፍታ እስክትውጠኝ ድርስ፤
ሰማይ አለት ሆኖ እላዬላይ ቢፈስ፤
እኔ ያንችወዳጅ ምንም የማይመስለኝ፤
የወዳጆችሽ ዋና አናቱ እኔነኝ።
የኔ ቆንጆ እውነት እልሻለው፤
እንደበቴ ደክሞ መግልጽ እስኪያቅተው፤
እስኪፈጠር ድረስ አዲስቃል ስላንቺ ቃላት ሁሉ አልቀው፤
ከምነግርሽ በላይ ከልብ ወድሻለው።

ናት ዘኢትዮጽያ

@getem
@getem
@getem
3
Forwarded from Abel Almaz ቲዩብ
አቤል አልማዝ ትዝታ'ና ሙዚቃ:
ግጥምን በጃዝ ታዋቂ አርቲስቶች ይታደማሉ ትኬት ከvip ጀምሮ እኛ ዘንድ ይገኛለ @dipeluwa1122 ከ ሙሌ ጎን እንሁን ገቢው ለ ሙላለም ታከለ