ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ፍጭው!!!!

እቴ ቸግሮኛል፤
የኔ ሃገር ዋዘኞች ወዲህና ወዲያ እየተዛመዱ፤
እንዳይሆን እንዳይሆን፤
እብቅና አዝመራው እየተላመዱ፤
ቁርጥ ነው ዘንድሮ፤
መጅሺን ያዥና፤
ፍጭውና ይለይ አሰርና ግርዱ።

((( ጃ ኖ ))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
"…ግን ግን… ብላቴናዎቹ ምን በደሉ?
የማንን አደራ በልተው… የማንን አማና አጎደሉ?
እምብርታቸው ያላረረ… አጥንተቸው ያልከረረ
ሰማይ በቀል እንቋጠረ… እጣቸውን እየመነጠረ
መንገዳቸው እያጠረ
እንደ ደራሽ ውሃ አግተልትሎ
በራብ አኮርማጅ ተልትሎ
ከእናት እቅፍ በግፍ ነጥቆ
ምላሱ ሊቃመስ ተባጥቆ
ሲሰለፍብን በአጭር ታጥቆ
እያየህ ዝም ካልክማ…?
እውነት…እውነት ከመንበርህ የለህማ!…"


((( ሙሉጌታ ተስፋዬ ))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
ለጤዛ ተዋድቀን

(በ.ስ)

"እድሚያችን ሰባ ነው ቢበዛም ሰማንያ"
ይህም ኑሮ ሆኖ ጠዋት ማታ ፍልሚያ
አንዱ ካንዱ ጥዋ: ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደ ቄጤማ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ ባጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የትገብተን እንረፍ?
በዶፍ ዝናብ አገር ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን ያከትማል አንድቀን።

@getem
@getem
ሲፈቀር የሚባል...
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
"ፈገግ ስትዪ...
ጥርስሽ ምስራቅ ሆነኝ ፣ የፀሐይ መውጫ በር
ከሳቅሽ ሰማይ ላይ ...
ንጋቴን አያለሁ ፣ ተሰቅላ እንደጀንበር።
አንቺ ስትስቂ...
የጨረቃ ገላ ፣ እስኪያልቅ ይሸረፋል
"ሙሉ"
"ግማሽ"
"ሩብ"
እያለ ይጠፋል
ኮከብ እንደ ቅጠል ፣ እግሬ ስር ይረግፋል።"
ብዬሽም አልነበር?
..................................
"ስታኮርፊ ደሞ
ነፍስሽ ምእራብ ነች ፣ መውጫ ለጨለማ
ከኩርፊያሽ ሰማይ ላይ...
ምሽቴን አያለሁ ፣ ንጋቴን ስቀማ።
አንቺ ስታኮርፊ...
ሳቅሽ ሚያደርቃቸው ፣
"ኮከብ ነን" ባይ ሁላ ፣ ይድናል ከመርገፍ
ጨረቃም ሙሉ ነች...
ዳግም ስትስቂ አይታ ፣ ገላዋ እስኪሸረፍ
እስከዚያው ድረስ ግን....
ምን ጨለማ ቢገዝፍ፣
ትንሽ ብርሀንን ፣ አይችልም ማሸነፍ!!"
ብዬሽም አልነበር?
...................................
"ስትስሚኝ ደግሞ...
መለኮት ከንፈርሽ ፣ ከንፈሬን ሲያጠምቀው
ምኔ እንደተነካ ፣ሳይገባኝ ሳላውቀው
ከገነት ደጃፍ ነው ፣ ደርሼ ምወድቀው።
ሲኦል ከቆመ ነፍስ ፣ ገነት የወደቀ አይደል የሚፀድቀው!!?"
ብዬሽም አልነበር?
ግን በቃ አትመኚኝ!!
ይሄን ሁሉ ያልሁሽ...
ስለጠፋብኝ ነው ፣ ልልሽ ያልሁት ነገር!!!
.....................................
አሁን ግን የምልሽ...
"ልቤና አንደበቴ ፣ አይተዋወቅም
አፍቃሪና እውነት....
ሩቅ ለ ሩቅ ናቸው!
ሰማይ ከምድር ላይ ፣ ያን ያህል አይርቅም
ሳፈቅርሽ እንዲህ ነኝ...
የምልሽ ሲጠፋኝ ፣ ያልሁትን አላውቅም!!!
ግን አፈቅርሻለሁ።"
እያልሁሽ አልነበር?
የማይባል የለም! ፣ ይባላል ሲፈቀር!!!!

@getem
@getem
@getem
👍1
((በርናባስ ከበደ))

"ዘመዴ ነህ አሉ ...
በአያት በምንጅላት ፡ ሥሩ እጅግ ቢርቅም
ማን ብዬ ላንባልህ?...
ዝንጀሮዎች እንደሁ ፡ ዘር መቁጠር አናውቅም!!"

@getem
@getem
@getem
#እስኪ.....
(ቤዛዊት ከበደ)

ይስቃሉ በሀሣቤ
ይስቃሉ በጉልበቴ
ይስቃሉ በጥረቴ
.
.
ይበላሉ ከማጀቴ
ይጠጣሉ ከማጀቴ
ከእጄ ፍሬ ከደም ላቤ
ይቆርሣሉ ከስኬቴ
.
.
ያደንቃሉ ያን ሀሣቤን
ያደንቃሉ ያን ጉልበቴን
ያደንቃሉ ሙሉ ቤቴን
.
.
እንዲህ እንደዚ እያሉ
ይኖራሉ ከቤቴ ጎን አጥር ጋርደው
ወይ ለወሬ
ወይ ለስርቆት
ወይ ለፅድቅ እንዲመቻቸው::
.
.
እኔም አለሁ
እስኪፀዳ ማድጋዬ
እስኪከዳኝ ቀኝ ጉልበቴ
እስኪጎድል ሙሉ ቀኔ
.
.
ይሀው አለሁ
..
እኔም አለሁ
.
.
ምርቃቴን ይዤ
እርግማኔን ትቼ!!

@getem
@getem
@getem
ለኢትዮጵያ!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
,
,
ይብላኝለት እንጂ...
በዘር ተከፋፍሎ ፣ ለሚታመስ ቤቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ተሸርፎ ተሸርፎ ፣ ላለቀ መሬቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ደረቷን ስትደቃ ፣ ለወረደው ጡቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ባዘን ፀጉሯን ስትነጭ ፣ ለገጠበ አናቷ
ይብላኝለት እንጂ..
ቁንጅናውን ላጣ ፣ ማድያታም ፊቷ...
፡፡፡፡፡፡፡
ከዚ ሁሉ ኋላም
የዘመን ጥላሸት ፣ መልኳን ተለቅልቃ
ቁንጅናዋ ርቋት ፣ ፉንጋነትን ታጥቃ
ልንጠላት አንችልም ፣ ውብ ሀገር ነች በቃ!!!

@getem
@getem
@getem
ዝክረ _ኸሚስ
ልጅት ሳይሞቅ ፈላ
************
ባለ ሁለት ጆሮ ……ገንቦየን አንግቼ
በዋርማ በፎሌ…… ከሚንጩ ቀድቼ
ዳለች እና ቦራን ……ከወንዙ አጠጥቼ
ከጅረቱ አጠገብ… ካለችው አከያ እንጠላጠላለሁ
ከለምለሙ ዛፍ ላይ …… እመለምላለሁ
ለቤታችን ጉዝጓዝ ……ቅጠል እቆርጣለሁ።
ከዛፉ ላይ ሁኘ ዝቅዝቅ ስመለከት የበለጠ አያለሁ
በእየ ቀንዘሉ ላይ ጢብ ጢብ ብየ እታች እዳፋለሁ
ከጅረቱ በታች ወዳለችው ገደል እጄን እሰዳለሁ
ቄጠማ ጠጄ ሳር …… አደሱን አጭዳለሁ።

ለማለሙን ሁሉ ……ባንድነት ሸክፌ
ገንቦየን አዝየ ……ጉዝጓዜን ታቅፌ
ዳለች እና ቦራን…… ከፊት እየነዳሁ
ለአንድየ ምነግረው …… ዱአ እያሰናዳሁ
ስሄድ ስገሰግስ
ከቀየየ ስደርስ
አባባ እና አየዋ …… ጃኖ ተሸፋፍነው
ማዶ ማዶ እያዩ ……ከቀልባቸው ሁነው
አውዱማው አጠገብ …… ወግ እያወጉ ነው
እንዴት ነሁ አይወይ…… አማን ነው መንደሩ?
ሸጋ ነወይ አጥቢያው ……እንዴት ውሏል ዱሩ?
ብየ እጅ ነሳሁኝ………እንዳባት አደሩ
አየዋም ጭራዎን ……ከግራ ወደቀኝ እየነሰነሱ
«አማን ሁኚ!» ብለው ……ነገያ መለሱ።

እኔም እየጠደፍኩ…… ወደ ቤቴ አቅንቼ
ገንቦና ዋርማየን …… ኸማጄት ከትቼ
እቅፍ ሙሉ ለምለም…… ለእማማ ሰጥቼ፤
እናት አለም ሆዴ …
ያወዱድ ያወዱድ …… ያወዱድ እያለች
የቀልብ የሙራዷን …… እያንጎራጎረች
ከመደብ እስከ ዘብጥ…… ትጎዘጉዛለች
እታለም ከምድጃው…… ወይራ ታጬሳለች።

ሰማይ ሲጨላልም…… አዱኒያን በበረት
ፍየሎቹን በጋጥ …… ደጃፉን በብረት
ሸክፎ ቢገባ …… አባታለም ክንዴ
የቤታችን ድባብ ……መለወጡ ባንዴ፤
ግር አለው ሁናቴው ……ገረመው በጠና
ቀኑ ሀሙስ መሆኑን …… ዘንግቶታልና፤

ከቀጠላው አናት…… እየተሰየመ
በወይራ በአድሩሱ ……እየተደመመ
ከጭሱ ጋር ስበን ……ቃል ሳይናገረኝ
ቀልብ የሚገዛውን……ፈገግታዉን ቸረኝ ።
ፈዋሽ ልዝብ እጆቹን……ሰዶ ወደ አናቴ
«ጎሽሽ!» ሲል አባባ …… «አበጀሽ እናቴ!»
ከነበረው በእጥፍእመረቅናለሁ …ይብሳል ፍጥነቴ
አይ ነብስ አለማወቅ…… አወይ ልጅነቴ!

በፋኖስ ታጅቦ … እንጀራው በሞሰብ ወጡ በሰታቴ
ከቀረበ ወድያ…… ብሉ እየተባለ ጠጡልኝ በሞቴ
በሳቅ በፍስሀ …… እንደተጎራረስን ይነሳል ገበታ
እምድጃውን ከበን…ቡና እየተቆላ ይደራል ጫወታ
እኔ ሀድራ ወዳጅ…
ልጅት ሳይሞቅ ፈላ…
ማጨዱ ሳይበቃኝ ……ቀጤማ እና አሪቲ
አደስና ከሴ ……ጠጀሳር አሽኩቲ
መጎዝጎዝ ሳያንሰኝ…… ጓሳ እና ሉባንጃ
ኸሚስ አመሻሹን ያቅበጠብጠኛል የነካኝን እንጃ

ጥፍጥሬ ማህል ልጅ ……ምርቃት ለምጄ
«አወል ጀባ!» እላለሁ …… ጀበና ጨምድጄ
የቤታችን አውራ የምኞትሽ ይሁን ብሎ ቢመርቀኝ
«በአሚን»ተቀብየው…… ቀይ ባህር ዘፈቀኝ
ይሄው በዛን ዘመን ……ምኞት አጣምሜ
በስደት አለቀ …… ተጋመሰ አለሜ !
ምፅ!ምፅፅ!


ውዶቼ
የምኞታችሁ አይሁን ይልቅስ የሚበጃችሁ ይሁን!
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይድና ወሀቢበና ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወአስሀቢሂ አጅመኢን!!

ሸጋ ኸሚስ ሸጎቼ!


@getem
@getem
@balmbaras
👍2
ከላይ!!!!!


የታች ሰፈር ልጆች ፤
የታች ቤት ግርደኞች፤
ደግሞ ይኸን ሰሞን፤
በጭራቅ ፉከራ፤
እየወዘወዙን ፤

\

\

\

እየሳቡን ፤ ይዘዋል ጉተታ፤
አላወቁም መሰል፤
ከ"ላይኛው" ሆነው፤ አገር እንዳፀኑ ሃጅና መርጌታ።
መገን የላይኛው!!"

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ!💚

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
( አቢ ጌቱ )
.
ከነመፈጠሬ
እርሳኝ ብለሽኝ
ለትውስታ እሚሆን ፥ ትዝታ ነፍገሽኝ
ደግሜ አፈቀርኩሽ ፥ ሌላ ሴት መስለሽኝ።

@getem
@getem
@getem
ብትቀሪ ጊዜ
(ቡሩክ ኮርሳዊ ዘ ቀለሟ)


የቆሙቱ ነቁ
ጅምሮች አለቁ
ብርድ ሆነ ወበቁ
:
መጉደልሽን አይቶ መሙላቴ ኮሰሰ
ንቃቴ ቦዝዞ ድባቴን ለበሰ
:
ብትመጪስ ጊዜ?
በነገ መያዜ
በማጣት መፍዘዜ
በናፍቆት መንፈዜ
:
አ ል ጥ ም አለሽና
ነጎድሽ እንዳገና
ወደ ሩብ ዘላለም
ያኔ ዛሬ አይደለም::


@getem
@getem
@getem
👍1
አደይ ሚክስድ አርት !

ዩቶጵያ ቪዥዋል አርትስ ክለብ ከ አዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በወጣት የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተከሸነ የድብልቅ ጥበባት (Mixed art) ኤግዝቢሽን ከመስከረም 14-20 ደረስ በአዲስ አበባ ሙዚየም ለእይታ ይበቃል ፡፡ የጥበብ ድግሳችን ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል !

መክፈቻ ሰዓት ፡- 11:30

ለበለጠ መረጃ

0984871096
0942600644
0973950532

@Utopiavisualarts
@utopiavisualarts
( አለሙ አዳፋ)
አክባሪ ተንቆ - ተከባሪ ልቆ
አዳማጭ ተረስቶ - ተናጋሪ ደምቆ
ከማወቅ - መታወቅ
ከማየት - መታየት...
ከመውደድ - መወደድ
ከመስማት - መሰማት...
ከሚመኝ ኗሪ ጋር
በምጓዘው መንገድ - በማልፋቸው ቀናት
ካንቺ ውጭ ለሌላ
ልቤ ቀጣፊ ነች - ነፍሴም ዱርየ ናት፡፡
.
አድባሬ ...
ሀገሬ❤️
@getem
@getem
@kaleab_1888
የሀበሻ ቅጥፈት
በሚካኤል አስጨናቂ


@getem
@getem
@getem
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

መውደድ በዝምታ
_____________

የኔ ልብ እንዲሁ ነው...

ዝምታ ያነቀው
ተጓዥ መስሎ ፈሪ፣
ለፍቅር ሸፍቶ፣
ተመልሶ ደግሞ፣
ፍቅርን አባራሪ።

ያንቺን ብርቅዬ ልብ፣
አጠምዳለሁ ብሎ፣
አሰሳ ፍለጋ
ሲንከራተት ውሎ፣
ኢምንት ስትቀረው፣
ፍርሀት የሚያጠምደው
ቆርጦ ይነሳና፣
አለሁኝ ይልና፣
የዝምታ ነፋስ፣
መልሶ የሚሰደው።

አይኖቼም ያው ናቸው....

አንቺ የሌለሽ ጊዜ፣
አንቺን ያልማሉ፣
ፀጥ ባለው ሌሊት
ከዕንቅልፍ ይሸሻሉ።
ካይኖችሽ ተዋደው፣
በፍቅር እሳት ነደው፣
ልተኛ ስላቸው፣
እምቢ ነው መልሳቸው።

ወዲያ ወዲህ እያሉ፣
በድቅድቅ ጨለማ፣
ያንከራትቱኛል፣
ጥርት አርገው ስለው፣
ከነ መላው አካልሽ፣
አንቺን ያሳዩኛል።

ድንገት ስትመጪ ግን...
ውልብልብ አይኖቼ፣
እንዳልተርክልሽ፣
የልቤን አውጥቼ፣
አይንሽን እንዳላይ፣
ፍርሀቴን እንዳልተው፣
ይከለክሉኛል፣
አትያት ይሉኛል፣
ገላጣው መሬት ላይ፣
ቁልቁል ተሰክተው።

አንደበቴም ያው ነው....

ሲያገኝሽ ይዘጋል፣
ሲያጣሽ ይከፈታል፣
ቀን ቀን ዝም ይልና፣
ሌሊት ይበረታል።

ማንም በሌለበት
ያለ አንዳች ፍራቻ፣
እልፍ አእላፍ ቃላት፣
እየደረደርኩኝ፣
አንቺን ማሰብ ብቻ።

ድንገት ሳገኝሽግን...
ከንፈሬ ታትሞ፣
ምላሴ ይታሰራል፣
ድንጉጥ አንደበቴ፣
"ምን ልበል" እያለ፣
በቃላቶች መሐል፣
ተለጉሞ ይቀራል።

እጆቼም ያው ናቸው....

አንቺን ያዩ ጊዜ፣
ከሁዋላዬ ዞረው፣
ይቆላለፋሉ፣
ቀጭኑ ወገቤን፣
ምሽግ ያደርጋሉ፣
ለስላሳ ጉንጭሽን፣
ሊዳብሱ ብለው፣
ፈርተው ይመለሳሉ።

ደግሞ አንቺ ሳትኖሪ...

ድንግርግር እጆቼ፣
"ብዕር አምጣ" ይሉኛል
ስንኝ አሰባስበው፣
ለሚያሰቃይ ፍቅርሽ፣
ግጥም ያፅፉኛል።

የኔ ፍቅር እንዲህ ነው...
ብቻዬን በመሆን፣
ያለአንዳች ፍራቻ፣
እልፍ አእላፍ ቃላት፣
እየደረደርኩኝ፣
አንቺን ማሰብ ብቻ።

በቃ እንዲህ ልውደድሽ....

ከጥርሶችሽ ጋራ፣
የሚስቅ ፊትሽን፣
በማያዩ አይኖቼ፣
አካልሽን መንካት፣
በሚፈሩ እጆቼ፣
በህልፍ አክናፍ ብቻ፣
በሩቁ እያሰብኩሽ፣
ሳልቀርብሽ ሸሽቼ።

ግን አንድ ተስፋ አለኝ....

በጨለማው አለም፣
አጥርተው የሚያዩሽን፣
አይኖቼን ከፍቼ ፣
ታትመው የቆዩትን፣
ፈሪ ከንፈሮቼን፣
ለቃላት ፈትቼ፣
ልብሽን መማረክ፣
የተሳነው ልቤን፣
በግድ አበርትቼ፣
እንቀፋት ብለው፣
ይንደረደሩና፣
ደረስን ይሉና፣
ፈርተው የሚደበቁ፣
ተሸናፊ እጆቼን፣
እንደ አሞራ ክንፍ፣
በሰፊው ዘርግቼ፣
በህይወት እስካለሽ ፣
በህይወት እስካለሁ፣
ግድ የለም ጠብቂኝ ፣
የሚርቅ ቢመስልም፣
አንድ ቀን መጣለሁ።

( ጠብቂኝ)

ዮሐንስ ገርማሜ

@getem
@getem
@getem
👍2
እረክተን ሳንጠጣ ፥ አለቀ ተደፍቶ
በቅጡ ሳይፈላ ፥ ሚገነፍል በዝቶ
.
« ሚኪ እንዳለ»

@getem
@getem
@getem
ቅድሚያ ለሀገሬ
_____

ጥሩ ሰራህ ብለው.... ወርቅን
ቢሸልሙኝ፣
የስኬት ዘውድ ብለው...አክሊል
ቢደፉልኝ፣
ምኑ ሊያስደስተኝ...
........ ..........
እናት ኢትዮጵያዬን
መሰረት ዋልታዬን...
ከወዟ ሊቀማት፣
ከርስቷ ሊሻማት፣
በስውር የመጣ፣
ካየሁኝ ምቀኛ፣
እንኳን አንድ ሌሊት
ደቂቃም አልተኛ!!!
…………… …………………

ዮሐንስ ገርማሜ

@getem
@getem
@getem