ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አገር ዕንቁጣጣሽ!
(በዕውቀቱ ሥዩም)
..
የ’ዳ ክንድሽ አቅፎኝ
ያሳር ክንፍሽ አቅፎኝ
እንቁሽን ስመኘው
ጣጣሽ ብቻ ተርፎኝ
መኖርን ስፈራ - መሞትም ስፈራ
ካየር ንብረት በቀር - ንብረት ሳላፈራ
ወሩ ተጠራቅሞ - አንድ ደርዘን ሞልቶ
እንደባለጌ ልጅ - በሩን በግሩ ከፍቶ
አዲስ ዘመን ገባ
አዲስ አመት ገባ
ያለ መስቀል ወፎች... ያለ አደይ አበባ።

በግዜር ሰራሽ ማማ፣
ቁራ ብቻ ሰፍሯል
የመስቀል ወፍማ፣
ወይ አገር ለውጧል
ወይ ልብሱን ቀይሯል።
.
አዲስ አመት ገባ...
በቄጤማ ምትክ - ቡልኬት ጎዝጉዞ
በቅፍ አደይ ምትክ -ጉንጉን ሽቦ ይዞ
በሉባንጃ ምትክ- አቡዋራ እያጤሰ
በፈንድሻ ምትክ - ጠጠር እያፈሰ።
.
አዲስ አመት ገባ...
አዲስ እንዲህ ዋዛ
ተፈጥሮ በውበት - መንፈሴን ሳይገዛ
በመአዛው ሳይዋጅ፣
መስከረም መግባቱን - በሬድዮ ልስማው?
እንደ መንግስት አዋጅ።


@getem
@getem
@getem
ለእዮብ ዘ ማርያም
መልስ በፀጋየ

ጥሩ ይሰሩ ይመሰል
ቶሎ አትምጣ ይላሉ
ጥሩ የሠሩ ይመስል
ቶሎ ና ይላሉ


:
:
ለኔ ግን አምላኬ
ከዚህ ሁሉ ጣጣ
ብዙም እንዳዘገይ
ቶሎም አንዳትመጣ።

@getem
@getem
@getem
ዘመን እንደ ታንኳ

መውደድሽ ሳይቃኘው
ለሚመለስ ወዳጅ
ህመምሽን ጨምሮ
ለቆመብሽ ከደጅ
ልሂድ ልሂድ ቢልም
ባይያዝሽ እንኳ
ይመጣል ጠብቂው
ዘመን እንደ ታንኳ

(አማኑኤል ደርበው)

@getem
@getem
👍1
አበባና ዘመን!!!!! ዘመንና አበባ! !!!!


አበባ ለዘመን፣ ቀለም እያዋሰ፣
ዘመን ለመስኩ ዳር፣የእንቁጣጣሽ ጥሎሽ ፣ ጃኖ እያለበሰ፣
የመስከረም አደይ፤ በመልካው ከንፈር ላይ ሳቅ እየደገሰ፤
ታዲያ በዚህ መሃል ፥
እቴ ለምን ይሆን??
"ጠብቅ እመጣለሁ!!!!"
የሚለው ያ ቃልሽ፣
መልሶ መላልሶ መልሶ ፈረሰ???


ደማቃው መስከረም፣
ሸብራቃው መስከረም፤
ይዘልቀው ይሆን ወይ????
ይቻለው ይሆን ወይ????
የከረመን ፍቅር ፣
የሻገተን መውደድ፣
አዚሙን ገላልጦ፣በብርሃን ፀዳል ማንቃት እንደገና፣
ይሆንለት ይሆን፣
ገጥሞ መቀጣጥል፣የፈረሰውን ቃል፣ የእምነቱን ቁመና????


ይህ አበባ ማለት፣
የመስክ ላይ ቆሎ፣
ፍክትክት ፣ፍንድቅድቅ ፣ ፍልቅልቅ አለሳ???
አዝመራና እሸቱ፤
ሜዳው ላይ ሲያሽቃርር ፣
እንደ እምቦሳ ጥጃ፣ እንደ ደንገላሳ፣
ደግሞ በእርሻየ ላይ፤
የከረመ መውደድ፣
የከሰረ ናፍቆት፣
እንደ እንግጫ በዝቶ አለሁኝ እያለ፣ ሆ ብሎ ይነሳ???


በከረመው ሰማይ፣ በሃምሌ ደመና፣
አደይ አበባየ ልምጣ አልምጣ እያለች በጉም ተሸፍና ፤
ነይልኝ እያልኳት፣
ጳጉሜ ዝናብ ጥሏል ፤ጎርፍ ነው አለችኝ መንገዷም አልቀና፤
ብየ አልቅሼ ነበር፤
ምነው በኔ መንደር፤
ዝናብ አልሆን አለ ፤ አይኔ ላይ ያበጠው የናፍቆት ደመና??


በናፍቆት ሲጠሩት፤
ወይ!!!!! ያላለ መውደድ፣
እሽ እማይል መንገድ፣ያላከመው ናፍቆት፣ ያላደለው ገላ፣
ቢስሙት አይድንም፣
ቢጠሩት አይሰማም፣ ጳጉሜ ከበረረ ከተሸኘ ዃላ።


ሃኒ የኔ ቆንጆ !!!!
የሚለውን ተረት፣ ተይው ገደል ይግባ፣
ምን በወጣኝ ዛሬ፣
በእንቁጣጣሽ ማጀት፣በሃኒ ቁልምጫ፣ ሆዴ የሚባባ??
ይልቅ፣
ያ ደማሙ ፍቅርሽ፣
ያ ጌጠኛው ሳቅሽ፣አይኔን የሚያሽረው፣ ካንጀቴ እሚገባ፣
ይህ ከርታታው ልቤ፣አልመጣችም ብሎ፣ ቂም የማይጋባ፣
ስትልኪልኝ ነው፣
የመስኩን ላይ እሸት፣
አደይ እንጉዳዩን፣ የአድባሩን ቀዘባ፣
ውብ አንች ሳቅሽን ፣ ውብ አደይ አበባ።


አበባና ዘመን፣ዘመንና ተስፋ፣ ከተሸባረቁ፣
በመስኩ ገላ ላይ፤ እቅፍቅፍ ብለው ፍቅር ከወደቁ፣
ናፍቆት ላሰከረው፣
መውደድ ላተኮሰው፣ በእንቁጣጣሽ ሰሞን፣
ለካስ መድሃኒት ነው፣እንቁጣጣሽ ብሎ፣ በአበባ ማሽሞንሞን።


ይኸውልሽ ማሬ፣
ጳጉሜ ተፋሰሰ፣ እንቁጣጣሽ ገባ፣
ቀንሽና ቀኔ፣
አለ እንደተራበ፣ አለ እንደተዛባ፣
ወይ መውደዴ አልሻረ፣ ወይ እግርሽ አልገባ፣
አይዞህ ይለኛል፣
የማዶ አገር ፍቅርሽ፣
በጄ እያስታቀፈኝ፣በስእል ያማረ ፤ ናፍቆትና አበባ።


እናም፣
ከምናምን ከንፈር፣ ከተደሟሞሰ፣
ከሽፍንፍን ገላ፣ ቂም ከተለወሰ፣
ከእመጣለሁ ተስፋ፣ ከተልፈሰፈሰ፣
ከጠብቀኝ ምኞት፣ ከተልከሰከሰ፣
ይቅርብሽ እቴ ሆይ፣
ምኞት ምን ሊፈይድ፣ ቅዠት ምን ሊረባ፣
ያን የለመድኩትን፣
ችፍርግ አበባሽን፣
እንቁጣጣሽ ብለሽ ላኪው ቤቴ ይግባ።
አየሽ፣
አገኝሽ ይሆናል፣
ትመጭ ይሆናል፣
በመስከረም ሰማይ፣
ምድር እንዳማረች፣ቄጤማ ነስንሳ፣ እንግጫ ደርባ፣
ግን እስከዚያው ድረስ፣
መጣሁኝ እያለ፣ጳጉሜ ሲያረገርግ፣ መስከረም ሲገባ፣
ትልኪው አታጭም፣ሳቅና ሆይ ላሌ፣ ሆየና ወሸባ፣
መላክ አይሰለችሽ፣
ያንኑ ፖስት ካርድ ፤
ከላዮ ያለበት ፤እንግጫና ናፍቆት፣ አደይና አበባ።

((( ጃ ኖ ))💚🌼💛🌼❤️🌼

@getem
@getem
@balmbaras
ግጥም ብቻ 📘
Photo
እሰይ የምስራች ዘመን ተሻገርን
አምናን አሳልፎ ለዘንድሮ አበቃን
ይመስገን ፈጣሪ ለንስሀ ህይወት እድሜ ጨመረልን
አሁን ካካፈለን ከዚህ አዲስ አመት
ሳይሆን መዋተቱ ለስጋ ፍላጎት
ልክ እንደ አበቦቹ አፍርተን አሽተን
ደግሞ እንደ አዕዋፉቱ ለእርሱ ዘምረን
ዘመን ለንስሀ ዕድሜ ለፍስሀ አምላክ ካቀናጀን
ተመስገን እንበለው ምን አለ የሌለን

Nani girma

@getem
@getem
በአንድነት እንዘምን
______
🌼🌼🌼🌼🌼
አሮጌዋን አመት
ቆፈኑን ተሻግረን
ክረምቷን አጀብናት፣
በውርጩ ዘለቅናት
የሰማይ ዶፍ አልፈን፣
ውሃው ላይ ተንሳፈን፣
የሀምሌን ነጎድጓድ
ምጡን ተቋቁመን፣
ይኸው ተገናኘን፣
ዳግም በአዲስ ዘመን።🌼
አደይ ሽሙንሙኗ፣
ሲነጉድ ዘመኗ፣
በመስከረም ነፍሷ፣
ከተፍ ትላለች
ከተራሮች አናት፣
በቢጫ ቀሚሷ።

ጀምበር ሳቅ ስትል፣🌼
በአዲሷ መስከረም፣
ተነቅሎ ይወገድ፣
የጥላቻው አረም።

መስከረም ስታጌጥ፣
የዘር ፍቅር እሳት፣
ውሃ ይደፋበት፣
አስክሮ የሚጥል፣🌼
የብሔር አረቄ፣
ሀይሉ ይድከምበት።
በአንድነት ሰማይ ላይ፣
ከ ሰላም ደመና ፣
ጠማማ የነበረው፣
ዳግም እንዲቃና፣
የጥላቻው በርኖስ፣
ይውደቅ ከገሀነብ፣
ለስኬቱ ጣሪያ፣
የሰላም ዶፍ ይዝነብ።

አሮጌው አመት አልፎ፣🌼
አዲሱ ሲገባ፣
ለምልማ ያጌጠች፣
አዲሲቷ ኢትዮጵያ፣
እንድትገነባ፣
የደረቀው ሰላም፣🌼
በፍቅር እንዲርስ፣
አንቆ የሚያስቀረውን ፣
የጥሉን ግድግዳ፣
በአንድነት እናፍርስ።🌼
በአደይ አበቦች፣
መሐል ላይ ተከበን፣
ያቺ የመስቀል ወፍ፣
እንዳትታዘበን፣🌼
ለእድገት ከፍታ፣
ተስፋን እያለምን፣
ከአዲሱ ዘመን ጋር፣
በአንድነት እንዘምን።

መልካም አዲስ አመት!!!

ዮሐንስ ገርማሜ

@getem
@getem
@getem
👍2
ደስ ይላል መስከረም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በግርሻ'ጣይ ሰርዶ ነቅሎ በሚያዚያንሽ ተርበጥብጦ ...
በግንቦት ሐሩር ተቀቅሎ ... በፀሐይ አብስሎ በዝናብ አብቅሎ
ከወዳጅ ከዘመድ ተቀላቅሎ ...
ባዝራን ከአህያ አዳቅሎ ...
በባለበርሸት ሽልም በቅሎ ...
ተፈናጦ አብሮ ገስግሶ ...
ጅራፍ ግርፊያ ሆያ ሆዬ ...ቡሄ በሉ ተጫውቶ ...
ኪዳነ ምሕረትን አንግሶ ... ደግሞ በወሩ ለአስተሮዬው..
ግሼን ማሪያም እማአርያም ... ደጀሰላም ደርሶ ለመሳለም..
" እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ ..
ዐደይ ለምለም ለኔ እንዳንቺ የለም..."
እያሉ ንጥቂያ ...
ከጀንበር መፍለቂያ እሥከ ጀንበር መጥለቂያ
አለላ ነቅሎ ባሕር እንጉዳይ ...
ጀግና ሰውገዳይ...
አካል እንጉዳይ...
እያሉ ሲያንጎራጉሩ
ደስ ይላል መስከረም !
.
ቡቃያው ጣል ከንበል ሲስ ...
ሽሩባዋ ወርዶ እንዲያ ሲዘናፈል ...
ልቤ እንደበቆሎ ያድራል ሲፈለፈል...
በቀጭን ተሰርታ ሥትል ዘንከት ዘንከት ...
ጃሎ ሲል ሊያነጋ አገር በመለከት ...
ለመስቀል ጠንስሶ ... በማድጋ ገንቦ ለእንግዳ ቀንሶ ...
በሞቴ አፈር ስሆን እያለ ሲያጋፍር ...
ጥርስ እንጎቻ አስፍቶ አሞጭ በመሰለው እርጎ ፍርፍር ...
እንኳን ሳቅ ጨዋታው ድብድቡ ልፊያው ...
ድገሙኝ ያሰኛል ሰፈፍ የለሽ ሞገድ መደዶ ዘር ዜማ ሲቆረቆር ክትፊያው..
ደስ ይላል መስከረም !
.
የሽንብራ ሸት እየጠረጠሩ ...
የልጅነት ሚዜ 'ኧረ አይዋ ክንዴ' እያሉ እየጠሩ ..
አብሮ ወፍ ጥበቃ ማማ ላይ ተሰቅሎ ...
ካፊያውን በገሳ በአንድ ተጠልሎ...
እሳት አቀጣጥሎ በቆሎ ጠባብሶ ...
አየሁ አላየሁም...ሰማሁ አልሰማሁም ...
በላልቶ አፍ አብሶ ...
ለስለሶ አስፈትሎ የ'ናት ኩታ ለብሶ ...
ላዋቂ ተልኮ ለልጅ ተጎናብሶ ...
ደስ ይላል መስከረም !
.
እንደቢራ ቢሮ አበባ ለአበባ ዐደይ እንቡር እንቡር ...
በፍቅር ለመክረም ... !
ደስ ይላል መስከረም !
ወፉ ከነ ጎጆው እሥከ መናጆው ...
ንቡ ከነ ቀፎው መረባ ከነ እርፎው ...
በዐደይ ለምለም ክብር ለመስከረም ክብር ...
ቅዱስ ! ቅዱስ ! ቅዱስ !
የዓመት አሥራት ሊያፈስ ...
ሊያስገባለት ግብር ...
በዝማሬ ሲያብር ...
አንጄት ሲበረብር ... !
ደስ ይላል መስከረም !
ተዋዶ ወዶ ተወሕዶ ... ያንጀት ተፈቃቅዶ ...
ባንድ አብሮ ለመክረም ...
ደስ ይላል መስከረም !
ለቅኔ ዘረፋው ጠፈፍ ሲል ፈፋው ...
የቆሎ ተማሪ ያ ተመራማሪ ...
የወላዲት አምላክ የድንግል አዝማሪ ...
ያ ደበሎ ለባሽ .... !
በእግዚትነ ማሪያም ...እባካቹህ እባሽ እባካቹህ ቁራሽ..
እያለ ሲለምን ...
ከጥንቅሹ ቅንጥሽ ማሩቴ ባይሰጠው ...
አይቀር መደንገጡ አራሽ አባ ወራሽ ማብላት ያሰለጠው..!
የማይለወጠው..!
በዐይኑ እየመዘነ በልቡ እማይመርጠው ...
ገሩ ባላገሩ...!
ያ ባለሞፈሩ ያ ባለዘገሩ ...,!
በሞቴ ነው ቋንቋው ስሞት ነው ነገሩ...!
ደስ ይላል መስከረም !
.
ወዶ ተወሕዶ ያንጀት ተፈቃቅዶ ...!
አንድ ልብ አቅዶ...!
አንድ ላይ ለመክረም...!
ደስ ይላል መስከረም !
...
ጥቅምትና ኅዳር ቢያዋውል ምንጭ ዳር ...
ታኅሳስና ጥር ዐውድማ አስለቅልቆ ጥሪት እሚያስቋጥር..
የካቲት መጋቢት መኸር አስከትቶ ቢያበስል እንደ ዐቃቢት..
ሚያዚያና ግንቦቱ ተርቲበኛው ቀርቦ ወርዶ ራከቦቱ...
የላም ልጅ በዋንጫ ቢቀርብ ሥልባቦቱ...
ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ እንደ ቄስ ምናሴ...
እያረበረበ ደግሞ እየወረበ...
ሰማይ በበረቀ ታርሶርሶ ሲስረቀረቅ...
ከራሱ እስኪታረቅ...!
ሁሉም እንደ ግብሩ..
ሁሉም እንደ ሙያው...!
አሥራ ሁለቱም ወር ...
እዮሃ አበባዬ መስከረም ሲጠባ..
ያኔ ነው ገቢያ..
ያኔ ነው መታያው ...
ያኔ ነው ማባያው ...
ደስ ይላል መስከረም ! ! !
.
( ሙሉ ጌታ ተስፋዬ )💚🌼💛🌼❤️🌼

… እንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡
ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡
ሌላም ብዙ ነበር
ሌላም… ደግሞ ሌላ
አለብኝ ትዝታ!
ዘመዶቼ ሳሙኝ
ጓደኞቼም ጋብዙኝ
ሊስትሮ ጨብጠኝ
ባለጋሪ ንዳ መንገዴን አሳየኝ
ያገሬ ልጅ ቆንጆ ‹‹ቤት ለእንግዳ›› በይኝ
አለብኝ ትዝታ…
ገ/ክርስቶስ ደስታ
(እንደገና)🌼🌼🌼

…በይ ብር በይ ቢራ ቢሮ፣ ክረምት ላንቺ
ብቻ አለፈ
ሌላው በጎርፍ ጎረፈ
ሞተ፣ በተኛበት ረጋ…
ፀደይ ላንቺ ብቻ ነጋ
ሽር ብለሽ መንቆጥቆጥ ነው፤ ከዚያም፤
ከዚያም፤ ከዚያም ሰምሮ
አወቅሁብሽ፤ ነቃሁብሽ፤ አንቺ ሕይወት
ቢራ ቢሮ…
ቀናሁ መሰል አንች ወላዋይ?
ነይ ብር በይ እንወያይ
አንቺ የዕፅዋት አዋዋይ
ከፀደይ ጋር ፀደይ መሳይ
ከአበባም አበባ መሳይ…
ምን አለበት ላንዲት ሰሞን
ቢራ ቢሮ እኔ አንቺን ብሆን?
ፀጋዬ ገ/መድህን
(ሕይወት ቢራቢሮ)🌼🌼🌼

… ወፎች ሲዘምሩ ሰማይ ደማስ መስሎ፣
ሐሴት ገባ ልቤ በውበት ተኩሎ፡፡
ዮሐንስ አድማሱ
(ወፎች በተጥለግለግ - 1955 ዓ.ም)
* * *
…ነበረች አበባ፣
በሾህ ተቀንብባ፣
መዓዛዋ ዘምቶ፣
ተወርዋሪን ኮከብ አቀረበው ጠርቶ፡፡
በውበት ብትልቅ ይህች የዋህ አበባ፣
ረብ የሰው ዘየ በሾህ ተቀንብባ፣
እሾህ አያስደርስ፣ ቆንጥሩ አያስጠጋ፣ የዘመን
ጋሬጣ አድርጓት ሰለባ፣
በእጦት መቃጠል ነው መዓዛዋ ሲያውድ
ከልብ እየገባ፡፡
ዮሐንስ አድማሱ
(ተወርዋሪ ኮከብ)🌼🌼🌼

የተስፋዬ ዛፉ
ሊከረከም ቅርንጫፉ፣
ሥሩ ሲነቃቀል
ሲበጠስ ሲፈነገል፤
ጭላንጭል ስትዳፈን
ብርሀን ዐይኑ ሲከደን፣
አንጥፌ ደርቤ ማቄን
ዘንግቻት እንቁጣጣሽን
ፀደይ አበባ ዐደዬን፣
በድቅድቅ ተቀመጥሁኝ
ላለማሰብ እያሰብሁኝ፣
የልቤን ልበ ባሻነት ገሰጽኩኝ
ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አረኩኝ፡፡
ደበበ ሰይፉ
(የተስፋዬ ዛፉ)🌼🌼🌼


@getem
@getem
@balmbaras
1👍1
🌻🌻🌻🌻
ተስፋ እንደሚያበስር አደይ አበባ
እንደሚታይ ብሩህ እድል
የለበሰ የ ወርቅ ካባ
ሸክሙ ቀላል የሚጣፍጥ
ቢጎረብጥ የማያሰምጥ
ፍክት ያለ አዲስ ዘመን
ፍክት ያለ አዲስ አመት
ጣጣ የለሽ እንቁ ብቻ
የደስታ አመት ይሁንል
ወደር ይጣ አምሳያ አቻ ፡፡

Happy New Year
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
UFO

@getem
@getem
@getem
ወቅታዊ አበባየሁሽ
(በላይ በቀለ ወያ)ፈገግ ብላችሁ ዋሉ

.
.
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
እስከመቼ "እህ " ሆ እንላን
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
አበባየሁሽ
/ለምለም/
ገንቡ በተራ
/ለምለም/
እንጨት ሰባብረን
/ለምለም/
ቤት እስክንሰራ
/ለምለም/
እንኳን ቤትና
/ለምለም/
የለንም አጥር
/ለምለም/
ደጅ እናድራለን
/ለምለም/
ዘር ስንቆጥር
/ለምለም/
ዘርማንዘር ቆጥረን
/ለምለም/
ሥንሰራ ቤት
/ለምለም/
ለውጡን ሚመራው
/ለምለም/
ደጉ መንግስት
/ለምለም/
ያፈርስብናል
/ለምለም/
መዝናኛ ቦታ ለመገንባት ፡፡
........................... ......
አደይ
ያገር ጉዳይ
ውይ ስቃይ፡፡
አደይ
የጋራ ታሪክ ፣ የለንም ባይ
የጋራ ድንጋይ አይደለም ወይ
።።።
እቴ አበሳ አቴ አበሳዬ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
አቴ አበሳ ስትለኝ ከርማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ባንክ ዘርፋ ነፃ አውጪዬማ
ጥላኝ ጠፋሽ ፣ ድምጿን ሳልሰማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መብራት ሀይል ሁሌ ጨለማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ውሃ ልማት ውሃ ሚያስጠማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መንገድ ሞልቶ መጎዝ ነው አድማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
ይሁን ኑሮ ከተባለማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"
...................
እዬዬ
እህ ሁሌ እዬዬ
ገዦች አሉ ብዬ
በገዛ ሀገሬ ላይ በዛብኝ ስቃዬ፡፡
........... ......................
ይሸታል ሽንኩርት ሽንኩርት
የአባብዬ ምኩት
አይሸትም ዶሮ ዶሮ
የእማምዬ ጓሮ
ዶሮ አልሰሩም መሠል ፣ ሽንኩርት ዋጋው ንሮ
።።
ከብረው ይቆዩን ከብረው
ተረኝነትን ጥለው ፣ዘረኝነትን ቀብረው
ሺህ አክቲቪስቶች አስረው
ቅድሚያ ለሰው ልጅ ሰጥተው
ህዝቦችን አቀራርበው
ሜንጫና ዱላ ጥለው
አንዲት ኢትዮጵያን ይዘው
ከብረው ይቆዩን ከብረው።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለመላው የአንዲት ኢትዮጵያ እምነት ተከታዮች መልካም አዲስ አመት

@getem
@getem
@GEBRIEL_19
👍1
እነሆ መስከረም መጣ
ኑ!
አዲስ እቅድ እናውጣ።
ቃል-ኪዳናችንን..
ራስ-ለራስ የገባነውን...
ከኻቻምና ያሳደርነውን...
አምናም አስበን ያልፈፀምነውን ...
ኑ!
አሮጌው ውጥናችንን እንኳል
ዘንድሮስ አይቀርም ይሳካል...!!!

(በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@gebriel_19
እይታ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እዮሀ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መስከረም ሲጠባ
ወደ ሀገሬ ልግባ

ሐሜት ባይሆንብኝ ስር የሌለው ወሬ
መኖርን እሻለው እኔስ በሀገሬ

እኔን የገረመኝ
በዚህች ሀገር ውስጥ ሰርክ የሚለፈለፍ
መስከረም በጠባ በወራቱ ግዜ ሁሌ የሚለፈፍ
ይህ መዝሙር መልክቱ በሌላ ስናየው
ብዙ ያልተመለሰ ግዙፍ ጥያቄ አለው

ለምሳሌ
አንድ ሀገር ላይ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልግባ ምን አይነት ፈሊጥ ነው
አንድ ሀገር ውስጥ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልሂድ ማለትስ ምንድነው
አንዳች ነገር ባይኖር ድብቅ ሴራ ነገር
ባለ ሀገሩ ህዝቤ እንዲህ አይልም ነበር

በዛኛው ጫፍ ሆነን ነገሩን ስናየው
ግጥሙ ሲገጠም
ስንኝ ሲደረደር ክልል እና ብሄር አለ እንደማለት ነው
አለበለዚያ ግን
ገጣሚው ሰውዬ
ወይ ይጠነቁላል ወይ ነብይ ነበር ብሎ መመስከር ነው

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም አዲስ ዓመት
ናብሊስ
@nablis12
@getem
@getem
@getem
እንዲህ ነኝ!(ልዑል ሀይሌ)
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
የቁስሌን መጠን ቁሰሉና ለኩ ፤
የሚያሳክከኝን ውሰዱና እከኩ፤
የሚያመኝን ሕመም ታመሙና ኑሩት፤
የልቤን ፍላሎት
አይገልፀውምና እንዲሁ ሲናገሩት።
.
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
’ሚነፍሰውን ንፋስ
በጎኔ ሚዘልቀው በጎናችሁ አዝልቁት፤
’ሚዘንበውን ዝናብ
’ሚያበሰብሰኝን በጉንጫችሁ አውርዱት፤
..
የሚያንገበግበኝ
የወዳጄን ክህደት በወዳጅ ተካዱ፤
እሾህ ላይ ስራመድ በእሾህ ላይ ሂዱ።
..
ያኔ ነው ምታውቁት
የኔን የሕይወት ፈር፤
“ደህና ነው” በሚል ቃል ይህ ሁሉ ሲሰፈር።
፲፪.፩.፲፩ ዓ.ም.

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ተራማጅ
(በተስፋ ብዙወርቅ)

የዘገየ ህይወት
ከግቡ እንዲደርስ መፍጠን ይሻልና
መሮጡን መረጠ ሁሉም ቸኮለና
ተራማጁ ሁሉ ሄደ በመኪና፡፡



መስከረም 2

@getem
@getem
@getem
ለ 10ኛ ክፍል የማትሪክ ተፈታኞች በሙሉ ውጤት ዛሬ 10:00
ስላሚወጣ በቀላሉ ውጤቶን ለማየት @neaea_neaea_bot ተጠቀሙ ፣ ቀላል ፣ ቀልጣፋ እና ታአማኒ ያለምንም የሰው ጣልቃ ገበነት 24/7 የሚሰራ ።
@neaea_neaea_bot
የእርሶን እና የጓደኞዎቾ ለማየት ይህን bot ይጠቀሙ


12 ኛ ምድብ ምት ጠብ ቁም እዚሁ bot ላይ ታገኙታላችሁ

@getem
@getem
*ሀቅ*

አንቺ የሌለሽ ሰሞን
ሄዋን ሳትፈጠር
አዳም እንደሆነው
ባዶ ነው 'ማልመው
ባዶ ነው 'ምሆነው፡፡

(ምግባር ሲራጅ) ዘንባባ

@getem
@getem
@getem
#እንቁ_ለጌጥሽ
🌼🌼🌼🌼🌼

እንዴት ያለ እድል ፥ አወይ ጥቁር ምላስ
ባከላትሽ ታዞ
በትንታግ ዘመንሽ አዲስ እጣሽ ሲላስ
ምርቃት ይሁን እርግማን
ዋርሳ ይሁን ስጦታ .....ሳይገባሽ
እንቁ-ለጣጣሽ ብትባይ
ስለምን ለቤ'ክ አልሽ?
እልፍ አዲስ አመት ፥ አያሌ መባቻ
ጌጡ የት ሄዶብሽ ?
ችጋር የተረፈሽ ፥ ባያትሽ ስልቻ
አንድ ቀን እልልታ ፥ ሶስት መቶ ቀን ለቅሶ
ዘረኛ ቋቁቻ
እንደ ሸማ ጥለት ፥ ሰውነትሽን ወርሶ
አንጀቱ የቀናው ፥ መብሉን አስመልሶ
የሚበላው ያጣም
ጥሬውን ቆርጥሞ ፥ በምራቅ ለውሶ
እኩል ...እየ-ዬ ነው !!!
ባሳለፍነው ዘመን ፥ ከእልልታው ለጥቆ
ለነብስ እየሰጉ ፥ ለስጋ ተሳቆ
አይሻገር የለ ፥ ሶስት መቶ ቀን አልቆ
አዲስ ዘመን መጣ
ካለንበት ቡኮ ፥:ከማጡ ሳንወጣ።
አዲስ አመት በሚል ፥ ደስታ ልትቃርሚ
ጭቃ መደላድል ፥ ምን አምነሽ ትቆሚ?
ጣትሽ ሳይጠነከር እድፍሽ ሳይጠራ
ሽንሽን ብትለብሺ ከሀር የተሰራ
ያዳለጠሽ ግዜ
መሬት ባለጌ ነው ስጋሽን አይፈራ
ለቀን አያውልሽ የጥበብሽ ጮራ።

እና ከተረዳሽ ከገባሽ መልእክቴ
እርግማንሽን አንሺ !!!
ላይተር ሳያጠፉ ፥ መመፃደቅ ይቅር ፥ መዘወሩ ቦቴ
የተመረቀ ቀን
እንኳንስ በእንቁ ፥ ይከብራል በአርቴ
እንቁ ለጣጣሽ ይታጠፍ
እንቁ ለጌጥሽ #እናቴ !! ።

#አብርሀም_ተክሉ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#መልካም_አዲስ_አመት_ጣጣችን_ይፈንገል_በሰላም_በፍቅር_በደስታ_በብልፅግና_ማጌጫ_2012_ይሁንልን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


@getem
@getem
@getem
"ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን"
(ይኸው ነው!)

"የዘመን ዕውነት ነን በደግነት ሰማይ በጥበብ የኖርን
ትግስትም ልክ አለው ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን
ማተብ አስሮን እንጂ ተጣልተን እንዳንቀር በክፍፍል ገደል
ካገር ፍቅር በልጦ ሞት ብርቃችን አይደል
ንገሩት_ለዛ_ሰው
ከአለም ጫፍ እስከ ጫፍ
ሀይል እንደተራራ ገዝፎ ቢከመርም
ክንዱን አፈርጥሞ
እልፍ የሰገደለት ጀግና ቢሰደርም
ዓለም የሞተበት
የጠላት ማርከሻ ጦር ቢደረድርም
በአንድ አይናችን ሰላም
በኢትዮጵያችን ክብር አንደራደርም "


ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ
@getem
@getem
@getem
ግጥም ሲፃፍበት!!!


ሲሄድ እያየነው ፤
እንደ ደራሽ ውሃ በስሜት ገንፍሎ፤
ጉልፍልፍ እያለ፤
ትልቁን ትንሹን በጉያው አጅሎ፤
ሃገሬው እያየው፤
ይሉኝታ ጠፍቶበት በአጀብ በሆሆታ ሲሄዴ ተግተልትሎ፤
ወንድሙን እንደ በግ፤
ሆ ብሎ በደቦ ዛፍ ላይ አንጠልጥሎ፤
በመንጋ ጉባኤ፤ ንፁሃንን ሰቅሎ፤
የገዛ ወገኑን በድንጋይ ውርጅብኝ በአደባባይ ወግሮ፤
በሜንጫ በዱላ ምስኪኖቹን ቀብሮ፤
መኪና እያስቆመ ፤
የገዛ ወገኑን ንብረት እየቀማ በሽፍትነት አድሮ፤
ዘሎ እየዘረፈ የሰው ድንኳን ሰብሮ፤
ወንድሙን ሲያደማ ሙቅ ውሃ እየደፋ ጀበና ወርውሮ፤
እንዴት መንጋ ይክፋው ፤
ግጥም ሲፃፍበት መንጋ ነህ ተብሎ???

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras