ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አባቶቹን ጠልፎ ፤
በጣላቸው ድንጋይ ፤
ልጅየው ሳይማር ዳግም ተደናቅፎ ወድቆ ከተደፋ፤
ድንጋዩ ልጁ እንጅ ድንጋይ ምን አጠፋ???

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እየሄዱ ~መግደል

መንገድ የጀመረ
የሸፈተ ልብን
በተማፅኖ ምልጃ ላያስቀሩት ነገር
ህመሙ ቢከብድም
ምን አማራጭ አለ ከመሸኘት በቀር፡፡

ያ'ንቺም ልብ እንዲያ ነው
የሸፈተ ተጓዥ
መንገድ የጀመረ ብኩን ስደተኛ
እኔም እንደዛ ነኝ
ህመሙ ያቃተኝ
አማራጭ አጥቼ
ልብሽን የሸኘው ቀሪ በሽተኛ፡፡

መንገድሽ ህመሜ
መሸፈትሽ ፀፀት የህሊና ቁስል
ህመሜ ድህነትሽ
ስብራቴ ተስፋ ላንቺ መልካም እድል፡፡

በበዛው ፍቅሬ ላይ
በአንድ የታጠረው የምርጫዬ ግድብ
ለነጠፈው ፍቅርሽ
እልፍ አማራጭ ሆኖ የፍላጎትሽ ግብ
ይኸው ባንቺ ቀዬ
የገባዎት ሰማይ
የማጠልቅ ጀንበር ፀሀይን አትሞ
በኔ ቀዬ ላይ ግን
እንደመሸ ቀረ ላይነጋ ጨልሞ፡፡


((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
Forwarded from WORDS
“Lie
is a thin line between Love and Hate!”


@words19 ✔️
*የኔ ትውልድ*

አገር ምድሩ ተራኮተ
አፍ ተወልዶ ጆሮ ሞተ
አዋቂነት ተሟሸሸ
አለማወቅ በረከተ
አፈር ለዘር ተሟገተ
አፈር ለአፈር ጉድጓድ ማሰ
አፈር ለአፈር ተካሰሰ
መበላላት መቀማማት
መጠላለፍ መተማማት
መተራመስ መንጠራወዝ
በነገር ላይ ነገር መምዘዝ
አንገት ለአንገት መገዛገዝ
እዚም እዚያም መወዛወዝ
ሚዛን ማጣት ማቀላቀል
ይሄን ከዚያ ያንን ከዚህ
ማደባለቅ ማመሳቀል
የህይወት ጭንቅ የዕለት ምስ
ደስታን ጥሎ ደስታን ማሰስ
ሰላም ጥሎ ሰላም ማሰስ
ፍቅርን ጥሎ ፍቅርን ማሰስ
እውነት ጥሎ እውነት ማሰስ
ይሄ ሆኗል የዛሬው ቅርስ
ህ¡ የኔ ትውልድ¡

[አቶ እገሌ]

@getem
@getem
@gebriel_19
አሲማሙየ(አሴሞየ)
(የጳጉሜ የልጅነት ዝማሬያችን..በስነ ቃል አገጣጠም ስልት የተዘየነ)


የዘመን ጉንጉን ሹርቤ ገላዉ፤
የበጋዉ ካሳ የደም አባላዉ፤
የጸደይ ኩርፊያ የመጸዉ ምርጊት፤
የገሳዉ ድፎ ያገር መግላሊት፤
የከሰለ ገል ጠል የናፈቀዉ፤
የሰማይ ምጣድ እሳት የሞቀዉ፤
የሰማይ ግለት የወንዙ እሪታ፤
የጅረት ሀሩር የጥም ስቅታ፤
ሲንጠዉ ከርሞ እንደተኮሰ፤
የበጋዉ ሙሽር ቀልቡ ታመሰ።


በል ርገጥ ርገጥ እንዳሽከር በቅሎ፤
በል ሰበር ሰካ እንደ ሀይ ጃሎ፤
የቆላዉ እፊያ የደጋዉ ገንፎ፤
ሀምሌን ይጦማል በጋዉን ሰንፎ፤
በበጋዉ ሲዞር እግሩን ሲያማታ፤
አታዉቅም ሚስቱ እራቷን በልታ፤
የእጁን ስንፍና እንዳናይበት፤
ፍስለታ ግቢ ይላል በግንቦት፤
ገና በግንቦት ሰኔ ሳይገባ፤
ላርስ ነዉ ብሎ ሆዱ እየባባ፤
አመመኝ ብሎ ጋቲራ ገባ።


ጋቲራ ገብቶ የጠመቁት እለት፤
አርባ መጋኛ በእጁ ወጣለት፤
የመጋኛዉ ስም ቁጥሩ ሲፈታ፤
አባ ስንፍና አባ ቸልታ፤
ከቸልታዉ ላይ ሆዱ መብዛቱ፤
ቤተስኪያን ስማ አታዉቅም ሚስቱ፤
የአባ ሰነፍ ሚስት ተኝቶ አዳሪ፤
ያልበላችዉን ቂጣ ቆጣሪ፤
አፈረች አሉ ባደባባይ፤
መሬት ለመሬት እንደ እንጉዳይ፤
በቁና ጥርብብ ብድር ለመደች፤
ደሞ ለከርሞ እየተሳለች፤
ሀገሩ ሁላ ብድሯን ፈርቶ፤
ወይ አይላትም ጥሪዋን ሰምቶ፤
አዳ ዘንድሮ ቀየዉ ቢምራት፤
በሸንጎ ጠርቶ ምክር መከራት።


የሰነፉ ሚስት የአባ ሸንበቆ፤
በሽታ አይገለዉ ወይ አይሞት ታንቆ፤
ክረምቱ ሳያልፍ እሸት ሳይመጣ፤
ጋቲራ ሂዶ ጠበል ይጠጣ፤
መስከረም ሳይብት በጳጉሜይቱ፤
ባሴሞየ ወግ በእናት ባባቱ፤
የጁ ካሰኘዉ ጋራ ጊወርጊስ፤
መቻሬ ይዉረድ ማልዶ ይገስግስ፤
መስከረም ሳይብት ጣዩ ሳይመጣ፤
እጠቡኝ ብሎ አባ ጋር ይምጣ፤
በግንቦት ሀሩር በሰኔ ላይ፤
ቤትሽ ያልሞቀዉ ባደባባይ፤
የሰነፉ ሚስት ስንቅ የለሽቱ።


በእንተ ለማርያም በይ ባዛኝቱ፤
በእንቁጣጣሽ ቀን በመስከረሙ፤
መች ይጠቅምና ማንጎራጎሩ፤
በጳጉሜ ሰማይ በዉሃዉ ላይ፤
ባልሽን ይዘሽ ከጠበል ዋይ፤
የታጠበለ እለት የአሲማሙየ፤
ያኔ ነዉ አጀብ ባልሽን ላየ፤
ያቄመ ገላ ዝንጉ ሰዉነት፤
ጳጉሜ ያበራል የታጠበ እለት፤
በአሲማሙየ ዉሃ የነካ፤
በጳጉሜ ጠበል ህልሙን የለካ፤
የርዚቁ ድንበር የለዉም ድካ።


አሴማሙየ የልጅነቴ፤
የዉሀሽ ገላ ዉብ ምልክቴ፤
ይዞኛልና የበጋዉ ግርሻ፤
ጠልፎኛልና የዘመን ጥሻ፤
አረም ዉጦታል የፍቅሬን እርሻ፤
ባምስቱ ቀንሽ ልጠበልበት፤
ንጹህ ገላየን ላስመልስበት፤
አሴሞየ ..ሴሞ
አሲማሙየ..ሴሞ..
"እ..ንትን" ያለዉ…ከእንትናየ
ማን በነገረልኝ…
እረ እናንተ ሆየ…
አ..ሲ..ማ..ሙ..የ…አሴሞየ


((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!💚

@getem
@getem
@balmbaras
ልብ አልባው ገጣሚ
#አልደክምም~ስላንቺ

የፊደላት ጥምረት
ቃላት እያነፀ ሀረግ አሰባጥሮ
ከልቤ ድርሳን ላይ
በምናብ ቀለማት ስንኞችን ፈጥሮ
ከነጩ ብራና
በሾተላይ ብዕር እንድፅፍሽ ሲያዘኝ
ለምን እንደው እንጃ
አንዳች ነገር አለ እጄን የሚይዘኝ፡፡

ግን እታገላለሁ
ከሰማይ ማማ ስር ሰንደቅሽን አይቼ
ከፍታሽን ሳስብ
ብርታት እያገኘሁ ለዛሉ ክንዶቼ፡፡

ያኔ ለመሻቴ
ሀሳብ እያማጥኩኝ ነፍሴ ብትገረጣም
እጄ ቢታሰርም
አንቺን ምፅፍበት ብልሀት አላጣም፡፡

ስለዚህ ልፃፍሽ
እያነሱ መብለጥ ባንቺ ቢገለጥም
የካዱሽ ይካዱ
የ'ጆቼ መታሰር ከክብርሽ አይበልጥም፡፡

እመኚኝ እምዬ
ከፍታሽ ክብሬ ነው አልቀርም ወድቄ
ሰላምሽ ይመለስ
ሁሌም በሰማይ ላይ ከፍ ይበል ሰንደቄ
እኔም እፅፋለሁ
መቼም ሳይታክተኝ ስንኞች አርቅቄ፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
1👍1
///ቅኔ///
በ'ውቀት ደረጃችን ስንመድብ በቀላል
ቅኔ ሁለት ነው የኔና ያንተ ይባላል
ለኔ ወርቅ የሆነው ላንተ ሰም ይሆናል


(ማፊ)
@getem
@getem
@getem
በረከት በላይነህ©

"ተያይዞ ቢቆም ፥ ሁሉም ለአመሉ
አጥር አይምሰልሽ ፥ የከበበሽ ሁሉ!"
。。。


@getem
@getem
ፅና!!!!!!

ሃገሩ በሞላ፤
ድምፅህን ባይሰማው፤ ለጀማው ባትደምቅም፤
ሰው የለኝም ብለህ፤ ከጀመርከው መንገድ መሄድ እንዳትደክም፤
እስከዛሬ ድረስ፤
ከጩኸት በስተቀር፤
እውነት በሰው ብዛት፤
ፍትህ በሰው ብዛት፤ተበይኖ
አያውቅም!!!!"

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️



@getem
@getem
@balmbaras
ህይወት እና ቅኔ
------------// ©ሲራክ //---------------

ዝምታ ቅኔ ነው
ትዝታ ህይወት ነው
ህይወት ፣ አለት ፣ ዜማ ፣ ምስል እና ቅራኔ
ጥልቅ ፣ ረቂቅ ፣ መንገድ ፣ የሀሳብ ምናኔ
ህይወት አለት ሆና ዜማ ስትቀኝ
ምስሏም ይገለፃል ቅራኔዋም በቀኝ
እንዲህ ነው ትዝታ
የህይወት ትውስታ
ቅኔ ረቂቅ ነው ጥልቅ ነው መንገዱ
ምናኔ ሀሳብ ነው ቅራኔው ጥማዱ
ስለዚህ
ትዝታም ቅኔ ነው ምስጢር የታወረ
ዝምታም ህይወት ነው ዜማው የሰመረ
.............ትዝታ
..............ህይወት
................ቅኔ
............ዜማ
የምናኔ መንገድ ሲቃረን ሲስማማ
ይህ ነው ሌላ የለም የኑረት አላማ
///////////////- #ሲራክ ////////////////
ሲራክ ነኝ
ከሚዛን ተፈሪ
ኢትዮጵያ
@siraaq

@getem
@getem
@getem
- ዋሻ

ድሮ የሰው ፍጡር እዋሻ ነበረ
ተራራ አለቱን እየቦረቦረ
አፈሩን ድንጋዩን እየሰረሰረ
ተራራን እንደጨርቅ እየተረተረ።
ዝናብ እንዳይመታው ፀሀይ እንዳይመታው
ይሰራ ነበረ ዋሻ በየቦታው።
ብርዱ እንዳይገለው ሙቀትንም ሽቶ
እሳትን ፈጠረ ድንጋይን አጋጭቶ
ነበልባል ፈጠረ አለትን አፋጭቶ።

አሁን በዚ ዘመን ዋሻ ኑሮ ቀርቶ
ሁሉም ከትንታጉ ከዋሻው ተፋቶ
ያን የትንፋግ ህይወት
የላቦቱን ሙቀት ሁሉንም ረስቶ
ያ መጠጋጋቱን
ያ መጨራመቱን
ያ መተፋፈኑን
ያ መገፋፋቱን ያንን ሁሉ ትቶ
ባለበት ሰዓት ላይ
ብዙ ዘመን አልፏል
ብዙ ህፃን ተወልዶ ብዙ አዛውንት አርፏል
ወንበር ተቀያይሯል ዙፋን ተለዋውጧል
መንበር ተዟዙሯል ስርዓት ተገላብጧል።
ከቀለበት ቅምያ ግብግቡ መሃል
ቀምቶ የተቀማው በእጅጉ ያዝናል
መቀማቱን እንጂ
እሱም መቀማቱን ፈፅሞ ይረሳል።

ከቀለበት ቅምያ ግብግቡ መሃል
ቀምቶ የተቀማው በእጅጉ ያዝናል
ሰዉ ሁሉ ሞቆት እሱን ይበርደዋል
በጠራራ ፀሃይ ብርድ ብርድ ይለዋል
ተራራ ፈልጎ ጥልቅ ዋሻ ይሰራል
አለቱን በብልሃት ይቦረቡረዋል።
ከዘመናት በፊት ሰዎች ሚያረጉትን
ድንጋይ እያጋጩ እሳት ሚፈጥሩትን
ሙቀትን ፍለጋ ድንጋዮች ያጋጫል
ያረጁ አለቶችን እርስ በርስ ያፋጫል
ያፋጫል ያጋጫል ያጋጫል ያፋጫል
ሙቀትን ፍለጋ ድንጋዮች ያጋጫል።
የዋሻው አለቶች እንዳይፈራርሱ
ወጣ ወጣ ሚሉት እንዲለሰልሱ
ቅቤ ይቀባቸዋል በእጁ በምላሱ።

ቀምቶ የተቀማው ያ ቀለበት ፀር
ድንጋይ እያጋጨ
ዘመናት ያለፈ አለት እያፋጨ
ለራሱ ሙቀት ሲል እሳትን ሲፈጥር
ምናልባት አንድ ቀን
በግዚያት መካከል በቀናቶች ክምር
ያገኘው ይሆናል እራሱን ካለት ስር
ዋሻው ተደርምሶ
አለቱ ፈራርሶ
ድንጋዩም በስብሶ
ያገኘው ይሆናል
እራሱ ተጥሎ ከፍርስራሹ ስር
ከክምሩ መሃል ከአለቱ ንብርብር።

[አቶ እገሌ]


@getem
@getem
@getem
"ህይወትም ህልም ናት
የአልጋ ላይ መኝታ
ሰው ከእንቅልፉ ይነቃል
የሞተ ለታ"
ከበደ ሚካኤል
መንቃት እንጂ ዛሬ
ሳልሞት ተቀብሬ
ለምን ልውረድ ካፈር
አስቤ ሳልሰራ
ሰርቼ ሳልከብር
ክብር ልበል እንጂ
እድሜ እንደሆን አጭር
ትላንት የነበረው
ዛሬ ሲቀነጭር
አይቻለሁ ባይኔ
__...ወይኔ

Join me
@hanahailu

@getem
@getem
"የአንድ አይነት አይነቶች"
( መልአኩ ስብሐት ባይህ)
መጋቢት 18-2011ዓ.ም
:
:
ፍቅሬ ባንቺ በኩል የኔ መልክ ይታያል
በአበባየሁሽ ቅኝት ሆያ ሆዬ ደምቋል።
በአታሞሽ ድላቄ በትረ ምቴ ልቋል
ሞቋል በቃ ትንፋሻችን ሞቋል።
የእኔነቴ አንድምታ ካንቺነትሽ ዘልቆ
በከንፈርሽ ካፊያ ውርጭ ንጥለት ደርቆ
አረም ኩርፈታችን በእቅፈታችን ደቅቆ
የዛች እመ-ምኔት ምርቃቷ ጠድቆ
የአንቺነትሽ ድርሳን እኔነቴን ሰብቆ
ሞቋል በቃ ትንፋሻችን ሞቋል
የእኔነት ሕላዌ እኛነትን ጠልቋል።

@poem_with_mela

@getem
@getem
"እነሆ ለፈጠረኝ"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*************
የልቤ ናርዶስ ጸዳል
ፍቅርህ ከፅናት ሲበቅል።
ከደጅህ ምዕራፍ ብጠጋ
ብለብስ ግርማ ወፀጋ።
በመቅደስህ ማዕጠንት ቡራኬ
ብሩህ ሲሆን ጭጋግ መልኬ።
በምጥቁ መአዛህ መረዋ
የውስጤ እርኩሰት ሲሰዋ።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
ከፍትህ ሚዛን ወለል ላይ
ክህደተ ጴጥሮስ ሲሰማኝ።
ፍርሀት ልቤን አናውጦ
ስማፀን ቀኔን ቀን ውጦ።
ዘልቀህ ድንገት ከህዋሴ
ስትለግስ ምህረት ለነፍሴ።
ይቅር ባይነትህ ሲበዛ
ምናቤ ላንተ ሲገዛ።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
በድኩም አካል በእንጭጬ
ገድለ ጠበልክን ሲረጬ።
ሳምራዊ ትምከት ሲሰማ
ቀና ሲል ዝንብል ጨለማ።
ኩሉህ ብርሃን አርፎብኝ
ጥኡም ምግባርህ ሰፍሮብኝ።
ከጀንበሯ ጥልቅ ስፍራ
የሲቃዬ እቶን ሲገራ።
ለሚያልፍ ዕለት
የማያልፍ እውነት ስታበራ።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
ከቤትህ ስር ከታቦቱ
ከውዳሴህ በረከቱ።
በእልፍ ኣላፍ የተመን ጫፍ
አጥልተኸብኝ እፁብ አክናፍ።
ስሸጋገር ከጣረ-ሞት
ወደ ጸዳል ምሉዕ ሕይወት።
በእናትህም በእናቴ
ለምድር "ማር" ለሰማይ "ያም" በእመቤቴ።
ከስሞ ሳየው የምጤን ማት
እርሷን ባንተ ስሳለማት።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
.
.
.
ተጻፈ:- ፳፻፰ ዓ.ም
@poem_with_mela


@getem
@getem
🌻 የጳጉሜ እንባ 🌻
•°•°•°•°•°•°•°•°••°•°•

ዓመት ዞሮ ሲሄድ
መስከረም ሊጠባ፤
ጳጉሜን ሆድ ሲብሳት
ሰማዩ ሲያነባ፤
ከዓመቱ ጉድፍ
ነፍሴ እንድትፀዳ፤
ዛሬ ላይ ልከፍል
የከረመ ዕዳ፤
በጳጉሜ እንባ
የ'ኔን እንባ ላብስ፤
በሰማዩ ለቅሶ
የ'ኔን ገላ ላድስ፤
በጳጉሜ እንባ እኔ እጠመቃለው፤
በሰማዩ ለቅሶ አካላቴ ሲርስ ነፍስን እዘራለው።

. . . . . . .

#ኤልቆሻዊው
{የጳጉሜ}

@getem
@getem
@gebriel_19
*ሀገር ቤት ሲታሰብ*
(ምግባር ሲራጅ)



ያነፈሰን ነፋስ
ያቃጠለን ፀሐይ
የመሸብን ፅልመት
የጋረደን ሰማይ፡፡
በኑሯችን መሃል
የሰማነው አዛን
አሜን ያልነው ኪዳን
ተጋግዘን ያዘንነው
የባልንጀራ ሃዘን፡፡

ከረመዳን ጧሚ
የቀመስነው አፍጥር
አንጀት ያስጠፈረን
የማርያም ለት ዝክር፡፡

ሰላም ለመሳጣት
ካስቀዳሽ ትከሻ
ስመን ያነሳነው
የከርቤ እንክብል
ከሩቅ የሰማነው፤ ያድባር ሽማግሌ
የሚከረክር ሳል፡፡

ጣራችን ያረፈ
የደመራ ቁራጭ
ጥቋቁር ጥላሸት
በድግግም ብዛት
ተቀብለን ያልነው
መንዙማ ማህሌት፡፡
አንድነት፤
ባንድነት፡፡
በስውር መዳፉ፤ እያጨባበጠ
ሀገር ከመናፈቅ፤ የለም ያመለጠ፡፡

#ዘንባባ ከተሰኘችው መፅሀፍ የተወሰደ

@getem
@getem
@getem
👍2
አጥቢ ሀገር
(በላይ በቀለ ወያ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
.
.
ሰማይ እርቃን ሲሆን...
የደመናን ካባ ፣ ከላዩ አውልቆ
ፀሐይ ጭኗን ስትከፍት...
ምድር በሷ ሙቀት ፣ ቆፈኑን አላቆ
አዲስ አመት ገባ !
"ኢዮሐ አበባዬ ፣ ኢዮሐ አበባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ልጇ ጡት እንዲጥል...
ሀገር የጡቷን ጫፍ ፣ ሬት ሳትቀባ
ለዘመናት ሳያድግ...
አሁንም ይኖራል ፣ መሥከረም ሲጠባ፡፡
ኢዮሐ አበባዬ ፣ ኢዮሐ አበባ
አዲስ አመት ገባ ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ኢዮሐ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መሥከረም ሲጠባ...
ያ'ደይ አበባና ፣ የመሥቀል ወፍ ሶሪት
ታይቶ በመጥፋት ውል ፣ በመርገፍ አዙሪት
ባ'መት አንድ ጊዜ ፣ ዞረው ሲገናኙ
ነፋስ ሲያሳልፉ ፣ ሳሮች እየተኙ
በነፋስ ተገፍተው...
ሚረግፉ ቅጠሎች ፣ ይህንን ተቀኙ፡፡
"ዛፍ " የሚሏት ሀገር...
ፀሐይ ንጉስ ሾማ ፣ ከላይ ስትቃጠል
ነፋስ የገፋው ቀን...
መርገፍ ነው እድሉ ፣ "ህዝብ" የሚሉት ቅጠል፡፡
ምን ቅጠል ቢረግፍ...
ወድቆ ቢሰበሰብ ፣ ቢጣባ ካፈሩ
አበቦች ሚያፈካ ፣ ፍግ ነው መቃብሩ፡፡
።።።።፣፣።።።፣፣።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።፣፣፣፣፣፣
ኢዮሃ አበባዬ ፣ ኢዮሃ አበባ
ሀገር የጡቷን ጫፍ ፣ ግራዋ ሳትቀባ
ዘመን ሲቀያየር...
የማያድግ ልጇ ፣ መስከረም ሲጠባ...
ከቢራቢሮ ጋር ...
ልጆች ሲጫወቱ ፣ ለመያዝ ሲለፉ
አበባ ለመሳም ፣ ንቦች ሲጣደፉ
በአሞሮች ልፊያ...
ጭራሮ አካሎች ፣ ተሰብረው ሲረግፉ
ይህንን ተቀኙ ፣ ይህንን ለፈፉ...
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
"ዛፍ በሚሏት ሀገር ፣
በቅጠሎች መርገፍ ፣
በሐዘን ተጎድቶ ፣ የሚኖር ጭራሮ
እጣው ችቦነት ነው ፣ ይማገዳል ታስሮ፡፡
በቅጠሎች መርገፍ ፣
ቁጭት አቅም ነስቶት ፣ የሚኖር ጭራሮ
እንኳንስ አሞራን...
መሸከም አይችልም ፣ አንዲት ቢራቢሮ ።
ካለበት ተለቅሞ...
"ችቦ ነህ" ተብሎ ፣ ምን ታስሮ ቢማገድ
ሀቅን ይጠቁማል ፣ ጭስ ሆኖ በመሥገድ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምን አቅሙን ቢያጣ...
አስረው ሲማግዱት ፣ ቢያከስመው መንደዱ
ባ'ማኞች ግንባር ላይ...
የመሥቀል ቅርፅ ይዞ ፣ ይታያል አመዱ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ዛፍ የሚሏት ሀገር...
ፀሐይ ንጉስ ሾማ ፣ ከላይ ስትቃጠል
በነፋስ ሲገፋ...
መርገፍ ነው እድሉ ፣ ህዝብ የሚሉት ቅጠል
የቅጠሎች መርገፍ...
ያገባኛል ብሎ ፣ ሚወግን ጭራሮ
ካለበት ተለቅሞ...
ችቦ ነህ ተብሎ ፣ ይማገዳል ታስሮ፡፡
።።።።።።።።።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።።፣
እያጠባች ምትኖር...
ሀገር የጡቷን ጫፍ ፣ ጡት አስጥል ሳትቀባ
ዘመን ሲቀያየር ፣
የማያድገው ልጇ
ጡት ያልጣለ ልጇ ፣ ያው መሥከረም ጠባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ኢዮሃ አበባያ ፣ ኢዮሃ መስከረም
የቅጠሎች መርገፍ...
ትንሳኤ ይሆናል ፣ ላበቦች መለምለም፡፡
ኢዮሃ አበባዬ ፣ መስከረም ጠባዬ
ለረገፈ ሳዝን...
አስረው ያነዱኛል ፣ ችቦ ነው ተብዬ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምን ጭራሮ ቢነድ...
ከህይወት ቢቀነስ ፣ ሲደመር ደመራ
ከስሞ አመድ ሲሆን...
ባማኞች ግንባር ላይ ፣
የመስቀል ቅርፅ ይዞ ፣ ይታያል ሲያበራ፡፡

( በላይ በቀለ ወያ )

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
@getem
👍1
*መለየት
(በእውቀቱ ስዩም)

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡

@getem
@getem
@getem
... ላንቺ 2...
የነፋስን በሬ ወጀቦ እያረሰው
የተፈጥሮን አጥር አርቴ እያፈረሰው
ቅንድብ ተቀንድቦ ኩልም እያነሰው
ወዝ በጠረረበት በዚህ የምጥ ጊዜ
ሴቶች መስታዊት ፊት ሲያበዙ ትካዜ
መታደል ነው እንጅ መባረክ አብዝቶ
እንዲህ ያል ቁመና
እንዲህ ያል ወዘና
እንዲህ ያል ደምግባት ከወዴት ተገኝቶ
የክንፍሽን ብርታት እያወቀው ሆዴ
የማትበላ ወፍ በከንቱ ማጥመዴ
ቃላት ማሰማመር ስንኝ መደርደሬ
አላስችል ቢለኝ ነው ይቅር በይኝ ፍቅሬ
ዘመን ሲለዋወጥ መስከረም ሲጠባ
ወይንም ባልጋብዝሽ ባልሰጥሽ አበባ
እንደ መስቀል ወፌ ስትመጭ ለዓመቱ
ከንፈርሽ ባይስመኝ ባይንሽ ዳብሽኝ እቱ
አውደ ዓመት ሲበሰር በወፎቹ ዜማ
እንኳን አደረሰሽ ውቢት የኔ ዓይናማ

ዶ/ር ጌታነህ ካሴ ለMeti
@getanehkassie

@getem
@getem
@getem
👍1