ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የተከበራችሁ የ ግጥም ብቻ ቤተሰቦች

ሥዕል ብቻ ሚለው ቻናላችን ላይ የ ሥዕል ውድድር እየተካሄደ ይገኛል ገብታችሁ ይመጥናል ለምትሉት ሥዕል ድምዕ እንድትሰጡልን በ አክብሮት እንጠይቃለን 🙏

@seiloch
@seiloch
@seiloch



ግጥም ብቻ
ሥዕል ብቻ
@gebriel_19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
///// "አልሰጥም!" ትያለሽ?/////

ይህን ሁሉ ግዜ
ይህን ሁሉ ወራት
መልሶ መላልሶ
ዘውትር ቢለምንሽ
"አልሰጥም!" ትያለሽ?
እንዲህ ተመችቶሽ
እንዲህ ተወልውለሽ
ሊፈርጥ የደረሰ
ዳሌ ተሸክመሽ
ትርንጎ ጉንጭሽን
በዲምፕል አስጊጠሽ
ውብ ከናፍርሽን
እንዲህ አሞጥሙጠሽ
በአሎሎ አይኖችሽ
ተድላን እያስነበብሽ
ይህ ምስኪን "እባክሽ?"
ብሎ ሲማፀንሽ
ድምፅሽን ከፍ አርገሽ
"አልሰጥም!" ትያለሽ?
በችግርሽ ዘመን
ነበረ ከጎንሽ
ሰው በሚያሻሽ ግዜም
ከቶም አልተለየሽ
የስኬትን እርካብ-
"ሀ" ብለሽ ስትርግጪ
ነበር ድጋፍሽ
የዝና ፈረስሽን ስትፈናጠጪ።
እኮ አሁን ያ አልፎ
ታሪክ ተቀይሮ
ሃሴት አስፈንድቆሽ
እሮሮሽ ተቀብሮ
ካንቺ ተመኝቶ
ካንቺ እግር ተደፍቶ
በ'ንባ ሲማፀንሽ
"አልሰጥም!" ትያለሽ?
ዛሬ ቀን ሞልቶልሽ
ተመልካች አግኝተሽ
በአንድናቂ ተከበሽ
በዝና ተውጠሽ
ረጅም ሽንጥሽን
ያለልክ መዘሽ
በወርቅ አልማዝ ዕንቁ
እንዲህ ተንቆጥቁጥሽ
በሃብት በልፅገሽ
ሁሉ ተርፎ ሞልቶሽ
ቁንጅና አረስርሶሽ
ውበት ተደፍቶብሽ
አንዳችም ሳታጪ
አንዳች ሳይጎልሽ
በረከት የሚያፈስ
ያን ገነት አንደበት
ያን ውብ አፍሽን
በ እምቢታ ሞልተሽ
"እባክሽን እቱ አንድ ሺህ ብር
ብድር"
ስጪኝ ብሎ ቢልሽ
እንዲህ ሲማፀንሽ
"አልሰጥም!" ትያለሽ???
እቱ ሙች! ክፉ ነሽ!!!

Hahahaha....
I Gotch you guys!
(መንግስቱ መ)

@getem
@getem
@getem
የቁንጅና ወራት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
የወጣትነትሽን
የውብ ቁንጅናሽን
የሴት ተፈጥሮሽ..
ከሴትነትሽ ላይ - አውልቆ ለመጣል
‹‹ወጣት እድሜሽ ያልፋል
ውበትሽ ይረግፋል››
ቢሉሽ
የከጀሉሽ
ሊበሉሽ።
………….
እናም..
በሴት ተፈጥሮሽ ላይ፣
ወጣት እድሜሽ ቢያልፍም፣
ውበትሽ አይረግፍም፡፡
።።።።።።።።
ምክንያቱም…….
ከሴት ተፈጥሮ ላይ፣
ወጣት እድሜ ሲሸሽ - እርጅና አስከትሎ
ውበት ግን አይረግፍም!
እናት ከመሆን ጋር - ይመጣል ተኩሎ !!!

( በላይ በቀለ ወያ )

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
#ልቀቀን!
-
አንት ራስ-አምላኪ ፥ ለራስ ምስል ሰጋጅ
ያዙኝ ልቀቁኝ ባይ -
ቃልህ እንደ ንጉሥ ፥ ንግግርህ አዋጅ፣
ጉልበትህ የድመት ፥ ግሳትህ ያንበሳ
ዕንባህ ቅርር የሚል -
መሽቶ ማይነጋልህ ፥ ሥምህ ካልተነሳ፣...
ዋ! ብቻ ሙዚቃህ ፥ ሰርክ ማስፈራራት
ትን ይለን ይመስል -
አንተ ሳትባርከው ፥ የበላነው እራት፣...
.
ባክህ ተለመነን
ዛሬን እሺ በለን፣ ...
በፈጠረህ አምላክ ፥ ባበጀህ ከጭቃ
ባልቀጠርንህ ችሎት ፥ አትቁም ጠበቃ!!
.
ጣቶችህን ሰብስብ ፥ ደጃችን አትድረስ፣
እርግፍ አርገህ ተወን ፥ እንሙት ... እንጨረስ!
ግዴለም እንፈንዳ ፥ እንፍረጥ እንደ እንቧይ
ብቻ አንተ ልቀቀን ፥ ከቅዠትህ ሰማይ ፨፨
------------------------//------------------------
(በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@getem
ይህን ያህል ዘመን ፤
በኦና ጎጆው ውስጥ ፤
ምነው በባዶ ቤት ፤
ቆልፎ መቀመጥ ዘግቶ ብቻ ማውራት ፤
አይጨንቀውም ዛሬም በሩን ገርበብ አርጎ አይወጣም አንዳንዴ ፤
ትይኛለሽ አሉ የማለዳዋ ልጅ የከንፈር ወዳጄ፤
የልቤን አዳራሽ፤
በላምባዲና ቁልፍ፤
ቆልፈሽ የሄድሽው አንችው መሆንሽን ዘነጋሽው እንዴ???

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
የ 2011 # የአመቱ_የመጨረሻው_ዝክረ_ኸሚስ
☞ ዝክረ ኸሚስ ( 43 )
..
ሰው በመሆን መንገድ
።።።።።።።።።።።።።።።።
ሸጋ ነፍስ ገልጦ ፣
ሰው በማለት ዜማ ፣
ከዱንያ እራስጌ ላይ የሀቁን ውብ ሀድራ እያንጎራጎረው ፣
" ስማኝማ " እያለ እርቀት ላይገረግር መድረስ ላያክረው።
የነፍሴን ባልጃ ፣
የጂስሜን ቢሊኮ ፣
ያፈር ገላ ልብሴን ቁረንጮየን ገፎ ድቤነት አውጥቶኝ ፣
ሲደባኝ ሰማሁት በውደታው መዳፍ እንደ ሀድራው ሽቶኝ ።
.
<< ብቻነት ጥፍጥናው ፣
ከነፍስህ አንጀት ላይ ደስ የሚል ህመሙ ፣
ሰው የሆንክ ለት ነው ጣሙ የሚገባህ የመሄጃ መሙ ።
ሰው ለመሆን ደግሞ ...
መነጠል አለብህ ከሚሸነግልህ ቁስልህን አግሞ ።
ለመነጠል ደግሞ ...
ካብሮነት ሊያጋልል በዳይ ያስፈልጋል ገፍታሪ ደጋግሞ ! >>
.
ይለኛል !
በገምሻራው ሌሊት ፣
ሀድራው ገደምዳሜ ፣
ጋሜው ክምብል ደፋ በኸሚሱ ሞገድ ፣
ዋናው ከኒያው ነው ቼቼ ለመኮልኮል ዝምቻው ላይታገድ ፣
በነፍስያ እንቅፋትገርፍጦ በሚያደርስ ሰው በማለት መንገድ ።
..
እውነቱን ነው !
ሰው የመሆን ጣሙ ...
የነፍስያን ቡጡ የእኔነትን ትግል ፣
ተጋጥመው ረተው እንደመገላገል ፣
የኔነትን አመል ከራስ እንደማግለል ፣
የሚጣፍጥ የለም መቻያ ላደለው ሀቁን ለጠቆመ ፣
ከመገፋት መንገድ በብቻነት ምርኩዝ ሰው ሆኖ ለቆመ ።
..
ሰው ነው የሰው ወንፊት ...
ግርዱ ተለይቶ ሰው የመሆን ፍሬ ለዘር እንዲታደም ፣
አዙሮ ‘ ሚመታ ካለም ግፋት በፊት ሰው ነው የሚቀደም ።
ያኔ ነው ከፍታ ፣
የከጀሉት መኖር ፣
ወና ሌሊት ገፍተው ፣
ብቻ ሲማልዱ ከቀን ወፍ ተቀድቶ ፈጅሩ ሲዘምር ፣
ያኔ ነው ሰው መሆን የወጋገኑ ቀን ንጋቱ ‘ ሚጀምር ።
.
ሰው መሆን አፍታ ነው ...
ማርፈጃ አያስደካም አይገፋም እስኪጠር እስኪመሽ ይርቃል
ደግሞ አፍታ ለመሆን በአቅል ለማስተንተን ብቻነት ይበቃል ።
ያኔ ...
ሰው በመሆን ንጋት ፣
ሰው በመሆምን ቀትር ፣
ሰው በመሆን ጀንበር ፣
በህብሩ ሰንጠረዥ በቀን ስሌት ግብር ፣
ሸጋ ህልም ፈትሎ ሌሊቱን ሲያደግስ ምሽቱ ሲነጠፍ ፣
በሰውነት ንጋት ሸጋ አድማስ ለመኳል ማምሻው ሲዘነጠፍ ፣
( ያኔ ነው ሰው መሆን )
በሚያቆስል ቀን ውስጥ በሚያገረሽ ሌሊት ፣
ባለፈው ሲያክሙት የህመሙን መግል የፊቱን በኋሊት ።
..
ሀየይይይ ... !
..
..
ሸጋ ነፍስ ገልጦ ፣
ሰው በማለት ዜማ ፣
ከዱንያ እራስጌ ላይ የሀቁን ውብ ሀድራ እያንጎራጎረው ፣
ስማኝማ እያለ እርቀት ላይገረግር መድረስ ላያክረው።
የነፍሴን ባልጃ ፣
የጂስሜን ቢሊኮ ፣
ያፈር ገላ ልብሴን ቁረንጮየን ገፎ ድቤነት አውጥቶኝ ፣
ሲደባኝ ሰማሁት በመወዳድ መዳፍ እንደ ሀድራው ሽቶኝ ።
..
እንግዲህ ምን እችል ፣
በምን አቅሜ ልዘልቅ የወዳጄን መዝሙር ፣
በገዛ እኔው ድቤ ሰው በመሆን አግቦ የናልኝን አሽሙር ።
አልጅልም ባልንጀር ፣
አልሶብርም ለይሉን ፣
በኸሚሱ ግላጭ የጠናውን ሃጃ ዘንበን ለማረስረስ ፣
የሙሃባን ፈረስ በሀድራ ለጉሜ በነፍሴ ለመድረስ ።
..
( ወዲህም እዝነት ነው .. )
ቢንድው ተማያልቅ ፣
ከፍቅሩ ቁልል ነገን መሻገሪያ ሊያድል ሲገመድል ፣
የሻለት ብቻ ነው ሰው እንሁን የሚል ወዳጅ የሚታደል ።
..
በልማ ባልንጀር ፣
መጣሁኝ እንግዲህ ፣
ካለመድረስ ወዲህ
ኸሚስ ሽቅርቅሩ ቀሃ ጀባው ደርሷል አወሉን ገምጨ ፣
የመሻገሪያውን የቀለሙን ቀንድል ቀንበጤን ሸምጥጨ ፣
አፍታም አላረፍድ ፣
ሰው በመሆን መንገድ ፣
በተገማሸረው በወዳጃው ጥርጊያ ደግ ልንገናኝ ፣
በኮከብ ምልክት በጠፍ ጨረቃ ሌት እደወጣ መናኝ ፣
በወለላው ሀድራ እንደ ከፋው ሽፍታ እያንጎራጎርኩኝ ።
እዘልቅልሃለሁ ... !!
___
ሙሀመድ ሙፍቲ ( ጀዋድ ) 💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
ሀገር ማለትማ...

(ሚካኤል አስጨናቂ )

.

ሀገር ማለት ሰው ነው ብለሽ ያልሽኝ ዕለት

ሀገር ሰው አይደለም እያልኩሽ ስሟገት

ምክንያት ነበረኝ!

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ትዝ ይልሽ እንደሆን እንዲህ እልሽ ነበር ከመስኩ ዳር ሆነን

ተራራውን ወንዙን ሜዳውን እያየን..

.

ዓለሜ!

ሀገር ማለት እኮ ተራራ ማለት ነው

ከምድር ከፍ አርጎ ፈጣሪ ያነፀው

.

ከተራራው አናት ከላይ ተቀምጠሽ

ቁልቁል እንደምታይ መስኩን ዝቅ ብለሽ

ሀገርም ያለሽ ቀን ከፍታው ያንቺ ነው

ከማማው አናት ላይ በኩራት እንደቆምሽ

ዝቅ ብለሽ ማየት ነው!

"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ሀገር ማለትማ!

ሀገር ማለትማ....

አዎን ተራራ ነው

ማንም እየካበ ማንም የሚያፈርሰው።

.

በቆመ ተራራ አናት የወጡ ለት

ከበላይ እንዳሉ የበታችን ማየት

አውቃለሁ ያኮራል..

እመኚኝ የኔ ውድ!

ሀገርም ያለሽ ቀን እንደዚህ ያደርጋል።

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

የተናደስ ዕለት?...

የተናደስ ዕለት ተራራው ሲፈርስ?!

ከፍታሽ ያልፍና ይጀመራል ማነስ

ወርዶ መገኘት ነው ቁመት መለካካት

ትከሻን አስታኮ አቀብ መንጠራራት

.

አየሽው ዓለሜ?

አየሽው ዓለሜ? .... ሀገር ተራራ ነው

ማንም እየካበ ማንም የሚያፈርሰው

.

ሀገር ማለትማ ሲክቡት የሚካብ በኩራት የሚያደምቅ

ሲንዱት የሚናድ ተስፋሽን የሚያደቅ

ተራራ ማለት ነው!

እና ታዲያ ፍቅሬ...

ዕውን አንቺ እንዳልሽው ሀገር ማለት ሰው ነው?

.

አይደለም የኔ ውድ!

ሀገር ሰው አይደለም!

ሀገር ማለትማ ሜዳና መስኩ ነው

ፈጣሪ አንጣሎ ዘርግቶ የጣለው።

አዎን!

.

አዎን!

.

አዎን ሀገር ማለት ሳር ያቆጠቆጠ ለጥ ያለ ሜዳ ነው

የቤት ብቻ ሳይሆን የጫካም እንስሳ መቶ የሚግጠው።.

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ሀገር ማለትማ

ሀገር ማለትማ ሜዳና መስክ ነው

ከጫካ ውስጥ ወቶ በቤት እንስሳ ላይ አለቃ መሆን ነው።

.

እና ታዲያ ዓለሜ

ሀገር ማለት ሰው ነው?

እኔ ብቻ ልጋጥ የሚሉት አባባል

የሰው ባህሪይ ነው?

.

አይደለም የኔ ውድ

አይደለም ዓለሜ

እንደውም ልንገርሽ.. .

ሀገር ማለትማ

ሀገር ማለትማ ፏፏቴው ወንዙ ነው

አፈር ተሸክሞ የመጓዝን ዕጣ ፈጣሪ የቸረው

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ሀገር ማለትማ!

ሀገር ማለትማ..ጉቶ እየነደሉ ግንድ ይዞ መዞር ነው

ማደሪያ ዳስ አጥቶ ህልምን መናፈቅ ነው

.

ሀገር መቆለል ነው

ሀገር መደርመስ ነው

ሀገር በመስክ ላይ 

ቦርቆ መዝለል ነው

ግንድና አፈር ይዞ

ሲጓዙ እየዋሉ ሲጓዙ ማደር ነው።

እና አንቺ እንዳልሽ ሀገር ሰው አይደለም

ቀን እየተጓዙ ማታ በማሸለብ ሀገርነት የለም

.

እልሽ ነበር ያኔ ከመስኩ ዳር ሆነን

ተራራውን ወንዙን ሜዳውን እያየን። 

@getem
@getem
@getem
/// ሰዶ_ማሳደድ///
.
‹‹ጊዜው የሩጫ ነው!››፣ ‹‹ተነስ ሩጥ!›› ብለውኝ
‹ወዴት?› ‹ለምን?› ሳልል፣ ደርሰው ቢያጣድፉኝ!
ማቄን ጨርቄን ጥዬ፣ ተንደርድሬ ወጣሁ
ከራቅኩኝ በኋላ፣ ከቅዠቴ ነቃሁ!!
እናም…
እናማ….
የነጋው እስኪመሽ፣ መሽቶም እስኪነጋ
ይኸው ‘ባዝናለሁ...
የወጣሁበትን፤ ጎጆዬን ፍለጋ!!
--//--
( በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@getem
1👍1
/////------/////


እንደ አባቴ ገዳይ ልክ እንደ ሉሲፈር ሁሌ እጠላሻለው፤

ድንገት ስቅ ሲለኝ እያነሳሺኝ መስሎኝ ፎቶሽን አያለው።
ይህው እስከዛሬ..........
ካንቺ ወይም ከኔ አለኝ ልቤ አልፀና፤
መጥላት እና መውደድ ሆነብኝ ፈተና።

[ በለጠ ተክሉ ]


@getem
@getem
@gebriel_19
አርቲስት ተዘራ ለማ
ነብስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን!! 🙏🙏
ማንንም ቢሆን ድንገት ማጣት ከባድ ነዉ። በተለይ ደግሞ የምትወደዉ ሰዉ ሲሆን ይከብዳል። ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለሙያ አጋሮቹ መፅናናትን እንመኛለን!!
#RIP😭
👍1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
((እጣ ፈንታ))
.......
ታቦት ይሰራ ዘንድ ፤ እንጨት ይመረጣል
ወንበር ይሰራ ዘንድ ፤ እንጨት ይፈለጋል
ታቦት ይከብር ዘንድ ፤ ሰው ይሸከመዋል
ወንበር ይዋረድ ዘንድ ፤ ሰው ይሰፍርበታል
ሸክላ ሰሪው ካለ አንድም ለዋንጫ ነው አንድ ለማሰሮ
ሸክላ ሰሪው ካለ አንድም ትከብራለህ አንድም ትወድቃለህ
ጴጥሮስ የወይን ዋንጫ የከበረ ታቦት
ይሁዳ እንስራ የወደቀ እንጨት
ጎን ለጎን ሆነው አብረው የበቀሉ
ተቆርጠው ሲወድቁ ፤ የህይታቸው ዳራ ፤የነፍሳቸው ትርጉም ሁሉም ለየቅሉ
ከአንድ ሸክላ አፈር የተድበለበሉ
አንዳቸው በወይን ሌሎቹ በጠላ እስከ አፍ ይሞላሉ

ታድያ እኔስ
ምን ይሆን እጣዬ
ምን አድርጎኝ ይሆን ያ ሸክላ ሰሪዬ
አድርጎኝ እንደሆን የዛ ጴጥሮስ ዘመድ
ወይስ ታንቄ እሞት በይሁዳ ገመድ
ሸክላነት እጣዬን ለይቼ ባላውቅም
በወይን መደሰቴ በጠላ መስከሬን ፈፅሜ አልተውም።

(((ሞሲሳ ደምሴ)))

@getem
@getem
@getem
👍2
ደጋሽ ነጋሽ

በምድር እንፋሎት ዶሮ ወጥ አበሰልኩ
በጨረቃዋ ፍም ድፎ ዳቦ ጋገርኩ
መአልቱ ሲነጋ የህልሜን ቀን ደገስኩ
✧✧✧✧✧✧✧✧
ሲራክ


@getem
@getem
@siraaq
አባቶቹን ጠልፎ ፤
በጣላቸው ድንጋይ ፤
ልጅየው ሳይማር ዳግም ተደናቅፎ ወድቆ ከተደፋ፤
ድንጋዩ ልጁ እንጅ ድንጋይ ምን አጠፋ???

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM