የጁምኣው አርበኛ! !!!
እንዴት ነህ አህመዲን፤
ገሞራው ከታቢ ። የጁምኣው አርበኛ ፤
አውቀዋለሁ እኔ ፤
አልሃምዱ ሚለውን ፤ ያንተን አማርኛ ፤
ዱኣማ ይዘናል፤ አላረፍንም እኛ ።
እንዴት ነህ ፊርአውን፤ የአህመዲን አሳሪ ፤
እንጃልህ ዘንድሮ ፤
እንደቆላ ሽፍታ ፤ አጥተሃል መካሪ ።
ተራራው ቢከመር ፤
ገደሉ ቢከመር ፤ ያው ላንድ ሰሞን ነው ፤
አትጠራጠሩኝ ፤
ባህሩን ሰንጥቆ ፤
በመሃል የሚያልፈው ፤
የጀሊሉ ባሪያ ፤ አህመዲናችን ነው! !!!!
ይኸው ነው!!!!!
ወላሂ ይኸው ነው! !!!!!
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
@getem
እንዴት ነህ አህመዲን፤
ገሞራው ከታቢ ። የጁምኣው አርበኛ ፤
አውቀዋለሁ እኔ ፤
አልሃምዱ ሚለውን ፤ ያንተን አማርኛ ፤
ዱኣማ ይዘናል፤ አላረፍንም እኛ ።
እንዴት ነህ ፊርአውን፤ የአህመዲን አሳሪ ፤
እንጃልህ ዘንድሮ ፤
እንደቆላ ሽፍታ ፤ አጥተሃል መካሪ ።
ተራራው ቢከመር ፤
ገደሉ ቢከመር ፤ ያው ላንድ ሰሞን ነው ፤
አትጠራጠሩኝ ፤
ባህሩን ሰንጥቆ ፤
በመሃል የሚያልፈው ፤
የጀሊሉ ባሪያ ፤ አህመዲናችን ነው! !!!!
ይኸው ነው!!!!!
ወላሂ ይኸው ነው! !!!!!
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
@getem
...ጆርጅቡሽ . አናውጤው...
>[ ትዳር በጠመንጃ ]<
///////////////////////
አንጀት ልቧን ከፍታ
ውስጧ ሳታኖረው
ባህሪውን ሳታውቅ ምላሱን ሳትስለው
ፍቅሬ ሆዴ ብላ ሳታቆላምጠው
ይቺ የባላገሩዋን ልጂ
ትዳር ጠመንጃ አዝሎት
እጁዋ ተጠርፎ ከኋላ እያጀባት
ዋይ ዋይ ብላ ብትጮህ
ምንም ሰሚ የላት
ግፋ ቢል የሰማት አንድ ሂዎት ነበራት
ያ ሂዎት ሂዎቷ ትንሽ ቢያዳምጣት
ዝም ነው ዝምታ
ማንም መልስ አይሰጣት
በዝምታው መሃል ተከቦ ሹክሹክታ
በሃሳብ ማእበል እራሱን ሲማታ
እጣው ለሷ እንዳይደርስ ዝም ስትል ፈርታ
የሷ እውነት ነው የማታ የማታ
ይቀጥላል
@getem
@getem
@getem
>[ ትዳር በጠመንጃ ]<
///////////////////////
አንጀት ልቧን ከፍታ
ውስጧ ሳታኖረው
ባህሪውን ሳታውቅ ምላሱን ሳትስለው
ፍቅሬ ሆዴ ብላ ሳታቆላምጠው
ይቺ የባላገሩዋን ልጂ
ትዳር ጠመንጃ አዝሎት
እጁዋ ተጠርፎ ከኋላ እያጀባት
ዋይ ዋይ ብላ ብትጮህ
ምንም ሰሚ የላት
ግፋ ቢል የሰማት አንድ ሂዎት ነበራት
ያ ሂዎት ሂዎቷ ትንሽ ቢያዳምጣት
ዝም ነው ዝምታ
ማንም መልስ አይሰጣት
በዝምታው መሃል ተከቦ ሹክሹክታ
በሃሳብ ማእበል እራሱን ሲማታ
እጣው ለሷ እንዳይደርስ ዝም ስትል ፈርታ
የሷ እውነት ነው የማታ የማታ
ይቀጥላል
@getem
@getem
@getem
ሪጎሬ!!!!!!
እሱም ቀኑ ደርሶት፤
በሙዚቃው ሜዳ፤
ከባድ ሪጎሬ፤ ጠርዞ ሲያስገባ፤
ሎጬ የገባበት፤
ጎሉን እንዳነቀ፤ ምነው ሆዱ ባባ።
ከጦቢያ ቅጠል ላይ፤
በጦቢያ ተሳልቀው፤
ባንዲራዋን ንቀው፤
አፋቸውን ለቀው፤
ምች የመታቸውን፤
የሚፈውስበት፤
ደማ ከሴ ዜማ፤
ከበገናው ጋራ፤ ሆ ብሎ ሲያነሳ፤
ምች የመታው ሁሉ፤
እንደ እንቆቆ ጠጪ፤ ተንዘፈዘፈሳ።
በአንዲት ሪጎሬ እየተበሳጩ፤
በደርቅ እግራቸው እየተወራጩ ፤
ኳሱም እየካደ፤ ሲያመልጥ ከእግራቸው፤
ይኸ ብላቴና፤
ዛሬም በሪጎሬ በሎጬ ሸኛቸው።
((( ጃ ኖ )))
((( መልካም ልደት ጀግናዬ )))🎂🎂🎂🎂
@balmbaras
@getem
@getem
እሱም ቀኑ ደርሶት፤
በሙዚቃው ሜዳ፤
ከባድ ሪጎሬ፤ ጠርዞ ሲያስገባ፤
ሎጬ የገባበት፤
ጎሉን እንዳነቀ፤ ምነው ሆዱ ባባ።
ከጦቢያ ቅጠል ላይ፤
በጦቢያ ተሳልቀው፤
ባንዲራዋን ንቀው፤
አፋቸውን ለቀው፤
ምች የመታቸውን፤
የሚፈውስበት፤
ደማ ከሴ ዜማ፤
ከበገናው ጋራ፤ ሆ ብሎ ሲያነሳ፤
ምች የመታው ሁሉ፤
እንደ እንቆቆ ጠጪ፤ ተንዘፈዘፈሳ።
በአንዲት ሪጎሬ እየተበሳጩ፤
በደርቅ እግራቸው እየተወራጩ ፤
ኳሱም እየካደ፤ ሲያመልጥ ከእግራቸው፤
ይኸ ብላቴና፤
ዛሬም በሪጎሬ በሎጬ ሸኛቸው።
((( ጃ ኖ )))
((( መልካም ልደት ጀግናዬ )))🎂🎂🎂🎂
@balmbaras
@getem
@getem
👍2
ሁለት የካሳ ልጅ!!!!!!
መቼስ ዘመን አይደል፣
ዶሴ እየገለጠ፣
ነቃሽ እየጠራ፣ ፍርድ የሚያስተነትን፣
መቼስ ትውልድ አይደል፣
በእናት ሃገር ምሎ፣
ትንሳኤ እየራበው፣
ባንዲራውን አምኖ፣ በሞት የሚኳትን።
ከዶሴው ፅህፈት ላይ፣
ደመቅመቅ ብሎ፣
በደም የተፃፈ የብራና ገላ፣
ባይኑ ሲዞርበት፣
የጥቁር ሰው ማተብ፣ የፍኖው ጀበርና፣
በጆሮው ሲያሽቃርር፣
የበልጅጉ ጬኸት፣ የፈረሱ ዳና፤
እያንገበገበው፣
የጫካው ጦም ማደር፣ የአንበሳው እርጅና፣
ለካስ ከሞት መሃል፣
ቴዲም ይወለዳል፣ ዳግም እንደገና።
አንዱ መዩ ካሳ ፣ የቋራው ሞስለኔ፣
ህልመ ምትሃተኛ፣
እንደ ቆላ መደድ፣ እንደ ዲማ ቅኔ፣
አገር ሰርቶ ሲሰጥ ፣
ጋፋት ጉብታው ላይ፣ አይቻለሁ ባይኔ።
ይህኛው ትንሹ፣ የኔ ዘመን ፋኖ፣
ጃ!!!!! ተነስ ይለኛል፣
ካባቶቹ ድካ፣ ጉብታው ላይ ሆኖ።
በላይ በመቅደላ፣ከመይሳው ጋራ፣
ጎፈር አጋሚዶ፣
አፍሮ የማበጥር፣ሹርቤ ' ምሰራ፣
የምመነሽረው፣
አንዱን በቀረርቶ፣ አንዱን በውጅግራ፣
የምወዘውዘው፣
አንዱን በጎራዴ፣ አንዱን በዳንኪራ፣
እኔም የካሳ ነኝ፣
በባንዲራው ቀለም፣
ድካየን የማበጅ፣ ህልሜን የምሰራ።
በጨለማ መሃል፣
ላይን በጋረደው፣ ድንግዝግዝ ጎዳና፣
አላይም እያለ፣
ውሃ ውሃ ሲሸት፣
የእናቴን ባዶ አንጀት፣ የእንቅቧን ገመና፣
በጨለማው መሃል፣ጨለማ እያሰሰ፣
ወጋገን ፍለጋ፣
ሰርጣ ሰርጡን በእጁ፣ በእግሩ እየዳበሰ፣
በጨለማው መሃል፣
ድብታን ተጋብቶ፣
ሃገር እያዛጋ፣ በሞት አዚም ታንቆ፣
የብርሃን ሽንቁር፣
አይቻለሁ ያለ፣
በንስር አይኖቹ፣ አደባባይ ዘልቆ፣
እነ ጆፌ አሞራ፣
ና እንምከር እያሉ፣
ና ውረድ እያሉ፣ መቼ ያቆዩታል፣
ሰማይ የዋለውን፣
በዱልዱም ክንፋቸው፣ መሬት ያወርዱታል፣
ከሄደበት ሳይደርስ፣
ወራጅ ነው እያሉ፣ ስም ያወጡለታል።
ጆፌ አሞራ ነክሶት፣
ቁራ ቁሬ ለክፎት፣
የብርሃን ክንፎቹን፣
የጠሊቅ አይኖቹን፣
በጆፌዎች ምንቃር ፣
እየተጎተተ ፣
ምናብና ህልሙን፣ ንስር ከተቀማ፣
ከተፈረደበት፣
በነፈዞች ጉባይ፣ በጅሎች ከተማ፣
አይኖርም ባለራይ፣ አይቆይም አይናማ።
ግና መዩ ካሳ፣
እኒያ ጥላቶችህ፤
ካልተረዱት ራእይ፣
ካልጀመሩት መንገድ፣
ሌላ ወሽመጥ ከፍተው፣ መስቀልያ አበጁ፣
ሂደው ሳይጨርሱ፣
በጎዳና ቆመው፣ በጎዳና አረጁ።
ይኸው ደግሞ መጣ፣
የማለዳው ኮከብ፣
የመድረኩ ልኡል፣ ሸገናው ሸገኑ፣
ጃ !!!! ብሎ ሲፎክር፣
ይኸ ያገሬ ሰው፣
ይሽራል በሽታው፣ ይከፈታል አይኑ።
እኔም በመይሳው፣
በገብርዬ ጓንዴ፣ በአካልዬ ጥላ፣
ያስተሰርእይ የምል፣
በጥቁር ሰው ቅኔ፣ በቴዲ ሽለላ፣
እኔም መይሳው ነኝ፣
የሚጋረፍ ቃንቄ፣ የጠላት አሽከላ፣
በጀግና ስም ምየ፣
ህልሜን የምቀጥል፣ ህልሜን የማሰላ።
((( ጃ ኖ )))
መልካም ልደት ጀግናዬ!!!🎂🎂🎂🎂🎂
@balmbaras
@Getem
@getem
መቼስ ዘመን አይደል፣
ዶሴ እየገለጠ፣
ነቃሽ እየጠራ፣ ፍርድ የሚያስተነትን፣
መቼስ ትውልድ አይደል፣
በእናት ሃገር ምሎ፣
ትንሳኤ እየራበው፣
ባንዲራውን አምኖ፣ በሞት የሚኳትን።
ከዶሴው ፅህፈት ላይ፣
ደመቅመቅ ብሎ፣
በደም የተፃፈ የብራና ገላ፣
ባይኑ ሲዞርበት፣
የጥቁር ሰው ማተብ፣ የፍኖው ጀበርና፣
በጆሮው ሲያሽቃርር፣
የበልጅጉ ጬኸት፣ የፈረሱ ዳና፤
እያንገበገበው፣
የጫካው ጦም ማደር፣ የአንበሳው እርጅና፣
ለካስ ከሞት መሃል፣
ቴዲም ይወለዳል፣ ዳግም እንደገና።
አንዱ መዩ ካሳ ፣ የቋራው ሞስለኔ፣
ህልመ ምትሃተኛ፣
እንደ ቆላ መደድ፣ እንደ ዲማ ቅኔ፣
አገር ሰርቶ ሲሰጥ ፣
ጋፋት ጉብታው ላይ፣ አይቻለሁ ባይኔ።
ይህኛው ትንሹ፣ የኔ ዘመን ፋኖ፣
ጃ!!!!! ተነስ ይለኛል፣
ካባቶቹ ድካ፣ ጉብታው ላይ ሆኖ።
በላይ በመቅደላ፣ከመይሳው ጋራ፣
ጎፈር አጋሚዶ፣
አፍሮ የማበጥር፣ሹርቤ ' ምሰራ፣
የምመነሽረው፣
አንዱን በቀረርቶ፣ አንዱን በውጅግራ፣
የምወዘውዘው፣
አንዱን በጎራዴ፣ አንዱን በዳንኪራ፣
እኔም የካሳ ነኝ፣
በባንዲራው ቀለም፣
ድካየን የማበጅ፣ ህልሜን የምሰራ።
በጨለማ መሃል፣
ላይን በጋረደው፣ ድንግዝግዝ ጎዳና፣
አላይም እያለ፣
ውሃ ውሃ ሲሸት፣
የእናቴን ባዶ አንጀት፣ የእንቅቧን ገመና፣
በጨለማው መሃል፣ጨለማ እያሰሰ፣
ወጋገን ፍለጋ፣
ሰርጣ ሰርጡን በእጁ፣ በእግሩ እየዳበሰ፣
በጨለማው መሃል፣
ድብታን ተጋብቶ፣
ሃገር እያዛጋ፣ በሞት አዚም ታንቆ፣
የብርሃን ሽንቁር፣
አይቻለሁ ያለ፣
በንስር አይኖቹ፣ አደባባይ ዘልቆ፣
እነ ጆፌ አሞራ፣
ና እንምከር እያሉ፣
ና ውረድ እያሉ፣ መቼ ያቆዩታል፣
ሰማይ የዋለውን፣
በዱልዱም ክንፋቸው፣ መሬት ያወርዱታል፣
ከሄደበት ሳይደርስ፣
ወራጅ ነው እያሉ፣ ስም ያወጡለታል።
ጆፌ አሞራ ነክሶት፣
ቁራ ቁሬ ለክፎት፣
የብርሃን ክንፎቹን፣
የጠሊቅ አይኖቹን፣
በጆፌዎች ምንቃር ፣
እየተጎተተ ፣
ምናብና ህልሙን፣ ንስር ከተቀማ፣
ከተፈረደበት፣
በነፈዞች ጉባይ፣ በጅሎች ከተማ፣
አይኖርም ባለራይ፣ አይቆይም አይናማ።
ግና መዩ ካሳ፣
እኒያ ጥላቶችህ፤
ካልተረዱት ራእይ፣
ካልጀመሩት መንገድ፣
ሌላ ወሽመጥ ከፍተው፣ መስቀልያ አበጁ፣
ሂደው ሳይጨርሱ፣
በጎዳና ቆመው፣ በጎዳና አረጁ።
ይኸው ደግሞ መጣ፣
የማለዳው ኮከብ፣
የመድረኩ ልኡል፣ ሸገናው ሸገኑ፣
ጃ !!!! ብሎ ሲፎክር፣
ይኸ ያገሬ ሰው፣
ይሽራል በሽታው፣ ይከፈታል አይኑ።
እኔም በመይሳው፣
በገብርዬ ጓንዴ፣ በአካልዬ ጥላ፣
ያስተሰርእይ የምል፣
በጥቁር ሰው ቅኔ፣ በቴዲ ሽለላ፣
እኔም መይሳው ነኝ፣
የሚጋረፍ ቃንቄ፣ የጠላት አሽከላ፣
በጀግና ስም ምየ፣
ህልሜን የምቀጥል፣ ህልሜን የማሰላ።
((( ጃ ኖ )))
መልካም ልደት ጀግናዬ!!!🎂🎂🎂🎂🎂
@balmbaras
@Getem
@getem
🎉1
«አለቅሽም»
እድሜ ቢገረጅጅ
ኑሮዬ ቢል እጅጅ
ብወረር በሽበት
አካሌ ቢሻግት
መንገዱ ቢያደክመኝ
አድራሻሽ ቢርቀኝ
ሌላ ስጠብቂ
ሌላ ስትናፍቂ
ስቃየን ባታውቂ
ስከተልሽ እኔ
በህይወት ዘመኔ
ሌላ አይታይ ለኔ
እኔ አልታይ ላንቺ
ባትረጅም አንቺ
ባይገባሽ ማፍቀሬ
አይሻለሁ ማሬ
አይኖችን ወርውሬ
፡
አሰናብቶኝ ብሄድ
ጊዜም በኔ ቢፈርድ
አንቺም ብለሽ እምቢ
ሌላ ~ስታልሚ ስታስቢ
አይንሽ እኔን ጠልቶ
ልብሽ እኔን ከድቶ
ሆኘብሽ ቡትቶ
ተሽቀንጥሬ ብወድቅ
ልቤ አንቺን ሲናፍቅ
ለምን ሆንኩኝ ብርቱ
ማፍቀር ማለት እቱ
ይህ ነውና እውነቱ
ተጠልቶ መውደድን
ተሸሽቶ መቅረብን
ተረስቶ ማሰብን
እንዳንቺ እና እንደኔ
እንድህ ነው ሔዋኔ
፡
አሰናብታይ ምድር
ብገባም መቃብር
ይመጣል እምባዬ
ይፈልቃል እምባዬ
ልክ በምንጭ መልክ
ከደጅሽ ጉብን ስር
ይመጣል አጥንቴ
ባይችልም ጉልበቴ
ይመጣል ብሶቴ
ይመጣል ናፍቆቴ
፡
በህይወት እንዳለሁ ወደኔ ባትመጭም
እመጣለሁ እኔ መጓዝ አልሰለችም
አፈር ቢጫነኝም መቸም አለቅሽም!
.....................
ተፃፈ፡ በአወቀ ካሳው
ሰኔ 29/2010 ዓ.ም
@getem @getem
@getem @getem
እድሜ ቢገረጅጅ
ኑሮዬ ቢል እጅጅ
ብወረር በሽበት
አካሌ ቢሻግት
መንገዱ ቢያደክመኝ
አድራሻሽ ቢርቀኝ
ሌላ ስጠብቂ
ሌላ ስትናፍቂ
ስቃየን ባታውቂ
ስከተልሽ እኔ
በህይወት ዘመኔ
ሌላ አይታይ ለኔ
እኔ አልታይ ላንቺ
ባትረጅም አንቺ
ባይገባሽ ማፍቀሬ
አይሻለሁ ማሬ
አይኖችን ወርውሬ
፡
አሰናብቶኝ ብሄድ
ጊዜም በኔ ቢፈርድ
አንቺም ብለሽ እምቢ
ሌላ ~ስታልሚ ስታስቢ
አይንሽ እኔን ጠልቶ
ልብሽ እኔን ከድቶ
ሆኘብሽ ቡትቶ
ተሽቀንጥሬ ብወድቅ
ልቤ አንቺን ሲናፍቅ
ለምን ሆንኩኝ ብርቱ
ማፍቀር ማለት እቱ
ይህ ነውና እውነቱ
ተጠልቶ መውደድን
ተሸሽቶ መቅረብን
ተረስቶ ማሰብን
እንዳንቺ እና እንደኔ
እንድህ ነው ሔዋኔ
፡
አሰናብታይ ምድር
ብገባም መቃብር
ይመጣል እምባዬ
ይፈልቃል እምባዬ
ልክ በምንጭ መልክ
ከደጅሽ ጉብን ስር
ይመጣል አጥንቴ
ባይችልም ጉልበቴ
ይመጣል ብሶቴ
ይመጣል ናፍቆቴ
፡
በህይወት እንዳለሁ ወደኔ ባትመጭም
እመጣለሁ እኔ መጓዝ አልሰለችም
አፈር ቢጫነኝም መቸም አለቅሽም!
.....................
ተፃፈ፡ በአወቀ ካሳው
ሰኔ 29/2010 ዓ.ም
@getem @getem
@getem @getem
በርዬ እሽሩሩ!!!!
ሰውን ያህል ንጉስ፣
ሰውን ያህል ቅዱስ፤
አምኜው የነበር፤
እስከልቤ ድረስ፤ እስከ አለም ፍፃሜ፤
እምነት እየበላ፤
ቃል እያፈረሰ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤ አልሻረም ህመሜ።
አዎ አልተሻለኝም፤
ማመን ያነቆረው፤ አልጠገገም ቁስሉ፤
ይሻለኝ እንደሆን፤
ደበስበስ አድርገኝ፤ በርዬ እሽሩሩ፤
አንተ ስትዳብሰኝ፤
የጭካኔ ሰንኮፍ፤ ይነቀላል ስሩ፤
የተዘጋው ተስፋ፤
ባንተ ፍቅር ትንፋሽ፤ ይከፈታል በሩ።
(( ጃ ኖ ))
ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ!!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
ሰውን ያህል ንጉስ፣
ሰውን ያህል ቅዱስ፤
አምኜው የነበር፤
እስከልቤ ድረስ፤ እስከ አለም ፍፃሜ፤
እምነት እየበላ፤
ቃል እያፈረሰ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤ አልሻረም ህመሜ።
አዎ አልተሻለኝም፤
ማመን ያነቆረው፤ አልጠገገም ቁስሉ፤
ይሻለኝ እንደሆን፤
ደበስበስ አድርገኝ፤ በርዬ እሽሩሩ፤
አንተ ስትዳብሰኝ፤
የጭካኔ ሰንኮፍ፤ ይነቀላል ስሩ፤
የተዘጋው ተስፋ፤
ባንተ ፍቅር ትንፋሽ፤ ይከፈታል በሩ።
(( ጃ ኖ ))
ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ!!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
✦✦ እጣ ፈንታ ✦✦
ከመንገድ ተመርጠህ
በሞቴ ተብለህ
ዳቦ የምትጎርሰው።
ገና ስትዘራ
በዚያች ስዴ ግንባር
ስምህ ተፅፎ ነው።
✍ አንዷለም አባተ ✍
ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
@getem
@getem
ከመንገድ ተመርጠህ
በሞቴ ተብለህ
ዳቦ የምትጎርሰው።
ገና ስትዘራ
በዚያች ስዴ ግንባር
ስምህ ተፅፎ ነው።
✍ አንዷለም አባተ ✍
ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
@getem
@getem
✦✦ ጎልማሳው ✦✦
እድሜው ተቆጠረ
ልደቱም ደረሰ
አርባ ዓመቱ ሞልቶ
ድግስ አስደገሠ
የሻማ ዋጋ ግን
ስላልተቀመሠ
ሁለት °ፓኮ° ክብሪት
ለክብሩ ለኮሠ።
✍ አንድነት ሰርፀ
ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
@getem
@getem
እድሜው ተቆጠረ
ልደቱም ደረሰ
አርባ ዓመቱ ሞልቶ
ድግስ አስደገሠ
የሻማ ዋጋ ግን
ስላልተቀመሠ
ሁለት °ፓኮ° ክብሪት
ለክብሩ ለኮሠ።
✍ አንድነት ሰርፀ
ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
@getem
@getem
‹‹ምንድነው ትዝታ?››
ብሎ ለዘፈነ ፤ ወይ ላንጎራጎረ
መልሱን እያወቀው፤
በትዝታ ቅኝት፤ ሲጠይቅ ለኖረ
ትዝታ መልስ አለው……..
‹‹ምንድን ነው?›› ማለት ግን፣ ምን ማለት ነበረ?
፣፣፣፣፣፣፣፣።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ትዝታማ ማለት …
እኛ ሁላችንም
የሆነ ዘመን ላይ ፤የነበረን ነገር፤
አሁን ላይ የሌለን፤ ትዝታ ነው ፍቅር ::
አሁን ፍቅር የታል?
ማን ለማን ሲል ኖረ? ማን ለማን ይሞታል?
ስለ ሰው ልጅ ፍቅር….
ተሰቅሎ የሞተም፤ ዛሬ ላይ ተነስቷል፤
ገድሎ መኖር እንጂ፤ ሞቶ ማኖር ቀርቷል፡፡
ኖረን ያለፍንበት፤ ፍቅር በፊት ቀረ፤
ትዝታ መልስ አለው…..
‹‹ምንድን ነው ?››ማለት ግን፤ ምን ማለት ነበረ ?
።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ትዝታማ ማለት…
እኛ ሁላችንም
የሆነ ዘመን ላይ፤ የነበረን ነገር፤
አሁን ላይ የሌለን ፤ትዝታ ነው ትዳር፡፡
አሁን ትዳር የታል? ትዳር ድሮ ቀረ፤
በቃል ነው ሚፈታው፤ በቃል የታሰረ፤
ቃል በጣም ረክሷል::
ሰማይና ምድር…
በቃል ካለመኖር ፣ እንዳልተፈተረ፤
ፈጣሪው እራሱ ፤ ቃል እንዳልነበረ፤
ቃል በጣም ረክሷል.....
ምንድን ነው ለሚሉ፤
እንዲህ ነው ተብሎ፤ በምን ይመለሳል?
*
‹‹ምንድነው ትዝታ?››፤
ብሎ ለዘፈነ፤ ወይ ላንጎራጎረ፤
መልሱን እያወቀው፤
በትዝታ ቅኝት፤ ሲጠይቅ ለኖረ
ትዝታ መልስ አለው……..
‹‹ምንድን ነው?›› ማለት ግን ምን ማለት ነበረ?
።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ትዝታማ ማለት …
እኛ ሁላችንም፤ የሆነ ዘመን ላይ፤ የፈጠርነው ነገር፤
አሁን ላይ የሌለን ፤ትዝታ ነው ሀገር::
ሀገር አሁን የታል ?
ሀገሬን የሚል ሰው ፣ በሀገሩ ይሞታል ::
ኖረን ያለፍንበት….
ፍቅር በፊት ቀረ፤
ትዳር በፊት ቀረ ፤
ሀገር በፊት ቀረ፤
ትዝታ መልስ አለው …
‹‹ምንድን ነው?›› ማለት ግን ፣ምን ማለት ነበረ ?
.
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ብሎ ለዘፈነ ፤ ወይ ላንጎራጎረ
መልሱን እያወቀው፤
በትዝታ ቅኝት፤ ሲጠይቅ ለኖረ
ትዝታ መልስ አለው……..
‹‹ምንድን ነው?›› ማለት ግን፣ ምን ማለት ነበረ?
፣፣፣፣፣፣፣፣።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ትዝታማ ማለት …
እኛ ሁላችንም
የሆነ ዘመን ላይ ፤የነበረን ነገር፤
አሁን ላይ የሌለን፤ ትዝታ ነው ፍቅር ::
አሁን ፍቅር የታል?
ማን ለማን ሲል ኖረ? ማን ለማን ይሞታል?
ስለ ሰው ልጅ ፍቅር….
ተሰቅሎ የሞተም፤ ዛሬ ላይ ተነስቷል፤
ገድሎ መኖር እንጂ፤ ሞቶ ማኖር ቀርቷል፡፡
ኖረን ያለፍንበት፤ ፍቅር በፊት ቀረ፤
ትዝታ መልስ አለው…..
‹‹ምንድን ነው ?››ማለት ግን፤ ምን ማለት ነበረ ?
።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ትዝታማ ማለት…
እኛ ሁላችንም
የሆነ ዘመን ላይ፤ የነበረን ነገር፤
አሁን ላይ የሌለን ፤ትዝታ ነው ትዳር፡፡
አሁን ትዳር የታል? ትዳር ድሮ ቀረ፤
በቃል ነው ሚፈታው፤ በቃል የታሰረ፤
ቃል በጣም ረክሷል::
ሰማይና ምድር…
በቃል ካለመኖር ፣ እንዳልተፈተረ፤
ፈጣሪው እራሱ ፤ ቃል እንዳልነበረ፤
ቃል በጣም ረክሷል.....
ምንድን ነው ለሚሉ፤
እንዲህ ነው ተብሎ፤ በምን ይመለሳል?
*
‹‹ምንድነው ትዝታ?››፤
ብሎ ለዘፈነ፤ ወይ ላንጎራጎረ፤
መልሱን እያወቀው፤
በትዝታ ቅኝት፤ ሲጠይቅ ለኖረ
ትዝታ መልስ አለው……..
‹‹ምንድን ነው?›› ማለት ግን ምን ማለት ነበረ?
።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ትዝታማ ማለት …
እኛ ሁላችንም፤ የሆነ ዘመን ላይ፤ የፈጠርነው ነገር፤
አሁን ላይ የሌለን ፤ትዝታ ነው ሀገር::
ሀገር አሁን የታል ?
ሀገሬን የሚል ሰው ፣ በሀገሩ ይሞታል ::
ኖረን ያለፍንበት….
ፍቅር በፊት ቀረ፤
ትዳር በፊት ቀረ ፤
ሀገር በፊት ቀረ፤
ትዝታ መልስ አለው …
‹‹ምንድን ነው?›› ማለት ግን ፣ምን ማለት ነበረ ?
.
@getem
@getem
@lula_al_greeko
<<ፌሽታ ላይ ነኝ>> (ለተመራቂዎች)
በምስለ ማሽመሟጠጥ " ኡኡቴ ምን ተገኘ ደ'ሞ ምን ሆነክ ነው?" ለመሚል
ሁናቴዉ ከንክኖ ደስታዬ ላስከፋው
መል'ክት እንዲሆነዉ
አብዝቶ 'ንዲያጦው
ቃላቴን ሰድሬ እነዲህ አስፍርያለዉ
(ትናንት)
በሀዘኔ ሀሩር የተነነው እምባ ተዳብሎ ተቋጥሯል
ባ'ናቴ ትይዩ እነደ ጥጠ ተባዝቶ ለምልሞ ለንቁጧል
ያለፍኩበት ሀሩር የንዳዱ ጡነቻ ነፍሴን
አኮስምኖ
ጉልበት ቅስሜን ሰብሮ
ተስፋ ከዘረፈኝ ከረምረም ብሏል
(ዛሬ)
ተዳምር ቁጭ ያለው የ'ምባዬ ጥርቅም
በለቅሶዬ ብዛት ከመብረቅ ጎልብቶ አንዲህ ሲያጉረመርም
ባ'ምሳለ ኮፍያ መነሳንስ ሆኖ ዛሬ የምታዩት
የልፋት ድካሜ የ'ምባዬ ሽልማት
የላቤን በረከት
አሁን ልወስደው ነው ፌሽታ ላይ ነኝ ያልኩት
ናትናአል ሰለሞን (Nat Son)
@getem
@getem
@getem
በምስለ ማሽመሟጠጥ " ኡኡቴ ምን ተገኘ ደ'ሞ ምን ሆነክ ነው?" ለመሚል
ሁናቴዉ ከንክኖ ደስታዬ ላስከፋው
መል'ክት እንዲሆነዉ
አብዝቶ 'ንዲያጦው
ቃላቴን ሰድሬ እነዲህ አስፍርያለዉ
(ትናንት)
በሀዘኔ ሀሩር የተነነው እምባ ተዳብሎ ተቋጥሯል
ባ'ናቴ ትይዩ እነደ ጥጠ ተባዝቶ ለምልሞ ለንቁጧል
ያለፍኩበት ሀሩር የንዳዱ ጡነቻ ነፍሴን
አኮስምኖ
ጉልበት ቅስሜን ሰብሮ
ተስፋ ከዘረፈኝ ከረምረም ብሏል
(ዛሬ)
ተዳምር ቁጭ ያለው የ'ምባዬ ጥርቅም
በለቅሶዬ ብዛት ከመብረቅ ጎልብቶ አንዲህ ሲያጉረመርም
ባ'ምሳለ ኮፍያ መነሳንስ ሆኖ ዛሬ የምታዩት
የልፋት ድካሜ የ'ምባዬ ሽልማት
የላቤን በረከት
አሁን ልወስደው ነው ፌሽታ ላይ ነኝ ያልኩት
ናትናአል ሰለሞን (Nat Son)
@getem
@getem
@getem
አሚን አሚን እንጅ!!!!!!!
ግማሹን በቱፍታ፤ ግማሹን በጉፍታ፤
መገን ኩሌ ሸጋ፤
በቅዳሜ ሰማይ፤
ከጀማው መሃከል፤
ቀልቧንም እጇንም፤ ለዱኣ ዘርግታ፤
ሃጃው ይውጣ ብላ ፤
ከእነነዬ መሃል፤
ዱኣ አስደርጋለኝ፤ ይህን ስሜን ጠርታ፤
ከላዬ በነነ፤
ከጎኔ ሟሸሸ፤
የተጫነኝ አዚም፤ የያዘኝ በሽታ።
ሃጃህ ይሙላ ብላ፤
እሷ ስትመርቀኝ፤
ልበል እንጅ ጓዴ፤ ልበል አሚን አሜን፤
አሜን እያልኩ ነው፤
ጉልበቴ የፀናው፤ ያዳንኩት ህመሜን።
ኧረ አሜን!!!!!!!!!!!
((( ጃ ኖ )))
ሸጋ ቅዳሜ!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
ግማሹን በቱፍታ፤ ግማሹን በጉፍታ፤
መገን ኩሌ ሸጋ፤
በቅዳሜ ሰማይ፤
ከጀማው መሃከል፤
ቀልቧንም እጇንም፤ ለዱኣ ዘርግታ፤
ሃጃው ይውጣ ብላ ፤
ከእነነዬ መሃል፤
ዱኣ አስደርጋለኝ፤ ይህን ስሜን ጠርታ፤
ከላዬ በነነ፤
ከጎኔ ሟሸሸ፤
የተጫነኝ አዚም፤ የያዘኝ በሽታ።
ሃጃህ ይሙላ ብላ፤
እሷ ስትመርቀኝ፤
ልበል እንጅ ጓዴ፤ ልበል አሚን አሜን፤
አሜን እያልኩ ነው፤
ጉልበቴ የፀናው፤ ያዳንኩት ህመሜን።
ኧረ አሜን!!!!!!!!!!!
((( ጃ ኖ )))
ሸጋ ቅዳሜ!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
~~~ የበሬ Aማርኛ ~~~
እወጋሃለሁኝ ! እወጋሃለሁኝ!
የሚል ድምጽ ብሰማ
በጣም ተገርሜ በሬም በስው ቓነቓ
መናገር ጀመረ በልንደን ከተማ?
የውም ከገበታው ባበሻ ቱምታ
በሙዚቃ ድምቀት በብዙ ጨዋታ
ወገን ከወገኑ በተገናኘበት
እስክሰታ ዳንኪራ በሚረገጥበት
በለንደን ከተማ ባበሻ ሬሰቶራንት
አረ ሆቼ ! በሉ በሬ ድምፅ አወጣ
አይደለም ከበረት ወይንም ከጋጣ
ክትፎ ነህ ተብሎ ከተከተፈበት
በቆጮ ተጊጦ ከተሰየመበት
ቀይ ወጥ ነህ አበቃ በሰታቴ ላንቃ
በሽንኩርት በቅመም ተሰርቶ ሲያበቃ
እወጋሃለሁኝ !! በሰው Aማረኛ
መናገር ጀመረ በሬም ልክ እንደኛ
በኛው አማረኛ በሰዋሰውኛ
ዞር ብዬ ጉዳዩን ከምንጩ ሳጣራ
አየሁ የጨበጠ ጠርሙስና ካራ
በሬ የመሰለ ጠብደል የሰው ፍጡር
በያዙኝ ገላግሉኝ አገሩን ሲያሸብር
ልክ ቁርጥ በቃ ቡሬ መጋላዬን
የምትለዩበት ከቡሬ ይንን
መጋላ ቡሬዬ አይገላገልም
አያስጠነቅቅም አያግደረድርም
ጉንጮቹ ያበጡ አይኖቹ በውፍረት
ተስበው ወደውስጥ ገብተው የጠፉበት
ጭንቅላቱ ትንሽ ማስተዋል ማሰቢያው
ካካለቱ ግዝፈት ሰናነፃፅረ
ልክ የበሬ ነበር የሰውነት ትክሉ
ሲለፋ ሲደክም የዋለ አካሉ
አእምሮውንና እውቀትን ጨቁኖ
በውስኪ፡ በቮድካ፡ በቢራዎች ደብኖ
ከዚያ በፊት ደግሞ ጫት የጫተበቱ
አረንጛዴ ቅጠል አለ ባንደበቱ
ቢላ አልያዘም እንጂ ጠርሙስ አልጨበጠ
በቡሬም አፍ አለ ጨሌ የተጋጠ
የትኛውን ይሆን ከብት የምንል እኛ?
ስራውን ለመግለጽ መሆኑን መናኛ::
ደረጀ 2006 ሎንደን
@getem_sourcebot
@getem
@getem
እወጋሃለሁኝ ! እወጋሃለሁኝ!
የሚል ድምጽ ብሰማ
በጣም ተገርሜ በሬም በስው ቓነቓ
መናገር ጀመረ በልንደን ከተማ?
የውም ከገበታው ባበሻ ቱምታ
በሙዚቃ ድምቀት በብዙ ጨዋታ
ወገን ከወገኑ በተገናኘበት
እስክሰታ ዳንኪራ በሚረገጥበት
በለንደን ከተማ ባበሻ ሬሰቶራንት
አረ ሆቼ ! በሉ በሬ ድምፅ አወጣ
አይደለም ከበረት ወይንም ከጋጣ
ክትፎ ነህ ተብሎ ከተከተፈበት
በቆጮ ተጊጦ ከተሰየመበት
ቀይ ወጥ ነህ አበቃ በሰታቴ ላንቃ
በሽንኩርት በቅመም ተሰርቶ ሲያበቃ
እወጋሃለሁኝ !! በሰው Aማረኛ
መናገር ጀመረ በሬም ልክ እንደኛ
በኛው አማረኛ በሰዋሰውኛ
ዞር ብዬ ጉዳዩን ከምንጩ ሳጣራ
አየሁ የጨበጠ ጠርሙስና ካራ
በሬ የመሰለ ጠብደል የሰው ፍጡር
በያዙኝ ገላግሉኝ አገሩን ሲያሸብር
ልክ ቁርጥ በቃ ቡሬ መጋላዬን
የምትለዩበት ከቡሬ ይንን
መጋላ ቡሬዬ አይገላገልም
አያስጠነቅቅም አያግደረድርም
ጉንጮቹ ያበጡ አይኖቹ በውፍረት
ተስበው ወደውስጥ ገብተው የጠፉበት
ጭንቅላቱ ትንሽ ማስተዋል ማሰቢያው
ካካለቱ ግዝፈት ሰናነፃፅረ
ልክ የበሬ ነበር የሰውነት ትክሉ
ሲለፋ ሲደክም የዋለ አካሉ
አእምሮውንና እውቀትን ጨቁኖ
በውስኪ፡ በቮድካ፡ በቢራዎች ደብኖ
ከዚያ በፊት ደግሞ ጫት የጫተበቱ
አረንጛዴ ቅጠል አለ ባንደበቱ
ቢላ አልያዘም እንጂ ጠርሙስ አልጨበጠ
በቡሬም አፍ አለ ጨሌ የተጋጠ
የትኛውን ይሆን ከብት የምንል እኛ?
ስራውን ለመግለጽ መሆኑን መናኛ::
ደረጀ 2006 ሎንደን
@getem_sourcebot
@getem
@getem
የሃውጃኖ ልጆች! !!!
መገን እነ እንትና ፤
ሰብስበው ሲወስዱት፤
የዳርጌን ምንሽር፤
የአርቢሴን ጠመንጃ፤
አምጡ እንመዝግበው እንጣፈው እያሉ፤
የሃውጃኖ ልጆች ፤
ዋጃ ከወንዙ ዳር ፤ ምነው ተታለሉ???
የነጃኖ ወንድም ፤
ዋጃ ከወንዙ ዳር ፣
የዘራው በርበሬ ፤ በእጁ እየበተነ ፤
ያስላቸው ይዟል ፤
በነጋ በጠባ እያስተነተነ! !!!
አንዴየ በዳዩ ፤
አንደዜ በዋጃ ፤
በመሆኒ በኩል ፤
በጨርጨር በባላ ፤
ጅኒ እንደመታው ሰው አመላለሰሽ ፤
ወትሮም መች ሊቀናሽ ፤
አላዮኝም ብለሽ ፤ የሰው ድብ ሰርቀሽ ።
አለማፈርሽ! !!!
መገናይ ሃውጃኖ ፤
ያፈላው ጀበና ፤
ውሃው አልቆ ነበር ፤
አቦልና ቶናው ፤ ቅጅው ተጀምሮ ፤
አሜን አትይም ወይ ፤
ሊቀዳ ነው አሉ በረካው ዘንድሮ ፤
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
@getem
መገን እነ እንትና ፤
ሰብስበው ሲወስዱት፤
የዳርጌን ምንሽር፤
የአርቢሴን ጠመንጃ፤
አምጡ እንመዝግበው እንጣፈው እያሉ፤
የሃውጃኖ ልጆች ፤
ዋጃ ከወንዙ ዳር ፤ ምነው ተታለሉ???
የነጃኖ ወንድም ፤
ዋጃ ከወንዙ ዳር ፣
የዘራው በርበሬ ፤ በእጁ እየበተነ ፤
ያስላቸው ይዟል ፤
በነጋ በጠባ እያስተነተነ! !!!
አንዴየ በዳዩ ፤
አንደዜ በዋጃ ፤
በመሆኒ በኩል ፤
በጨርጨር በባላ ፤
ጅኒ እንደመታው ሰው አመላለሰሽ ፤
ወትሮም መች ሊቀናሽ ፤
አላዮኝም ብለሽ ፤ የሰው ድብ ሰርቀሽ ።
አለማፈርሽ! !!!
መገናይ ሃውጃኖ ፤
ያፈላው ጀበና ፤
ውሃው አልቆ ነበር ፤
አቦልና ቶናው ፤ ቅጅው ተጀምሮ ፤
አሜን አትይም ወይ ፤
ሊቀዳ ነው አሉ በረካው ዘንድሮ ፤
((( ጃ ኖ )))
@balmbaras
@getem
@getem