ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ዜብራን ረገጥነው!!!!!


ዜብራ ቡራቡሬ፣ መልኩን አሳምሮ፣
በሽንቅጥ ወገቡ፣ አምሮ ተገሽሮ፣
ቁልቁል እያባጨን፣
በሞንዳላ ጭኑ፣ ከላይ ተከምሮ፣
ሁሌም ይለን ነበር፣
"መረጋገጥ ነበር፣ ይህን ሁሉ ዶሮ።"
ግና፣
መንገድ አያመጣው፣ አይስበው አያጣ፣
እኛ ያገር ዶሮች፣
ዛሬ ተሳክቶልን፣ ሽርሽር ስንወጣ፣
ዜብራ አባ ፎካሪው፣
ድንገት መንገድ ገብቶ፣
ያን ሁሉ ሽለላ፣ ቀረርቶ ዘንግቶ፣
ዶሮ ረጋገጠው፣ መንገድ ላይ ተኝቶ።
ጉድ እኮ ነው!!!!!
በቀረርቶ ጩኸት፣
በረጋጭ ፉከራ፣ እረግጣለሁ ያለ፣
አይ ቅሌት!!!!!!
ርጋጩ ረግጦት ፣ ሲረጋገጥ ዋለ!!!!!!!!!!

((( ጃ ኖ )))

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
👱እኔ ሳነብልሽ👱‍♀

👦👧👨👱‍♀👱👩👴👵

ፀሐይ ማቃጠልዎን ትታ፡
ታዳምጠኛለች ሁሉንም እረስታ፡
እኔ ሳነብልሽ እሚሄዱት ይቆማሉ፡
የጠወለጉ አበባዎች መልሰው ይፈካሉ፡
ያጐነበሱ ዘፎች ቀና ቀና ይላሉ፡
ወፎች ሊሰሙኝ ተሰብስበው ይመጣሉ።

እኔ ሳነብልሽ

በልጅነት አፌ በሚንኮላተፈው፡
ሁሉም ነው የሚሰማኝ ማንም ሳይሰለቸው፡
ውዴ እኔ ለ አንቺ ሳነብ፡
ሊያዳምጡኝ ዝሆኖች ቁጭ ይላሉ፡
ኤሊዎች ሊሰሙኝ ፈጥነው ይመጣሉ፡
ወንዝ፣ፋፎቴዎች ቃላያት በሙሉ፡
እኔ ሳነብልሽ ለአፍታ ፀጥ ይላሉ።

📝📝📝📝📝📝📝📝
ፊሊሞን የማርያም ልጅ
22/10/2010

@getem
@getem
@itsmefilimon
👍1
...እመኚኝ !!
:
ነይ ግቢ በሞቴ
እቤት ማንም የለም የለችም እናቴ
እመኚኝ ግዴለም ምንም አናደርግም
ወደ ውስጥ ገብተሽ በሩን ብዘጋውም
አንድ ላይ ተቀምጠን አብረን ብናወጋም
ከንፈርሽን ልስም ወዳንቺ ብጠጋም
ብስምሽም እንኳን ስጋት እንዳገባሽ
ምንም አናደርግም
.
..
በፀጉሮችሽ መሃል ጣቴን ባንሸራሽር
ጠረንሽን ቢሸተኝ ገብቼ አንገትሽ ስር
እጄ ይይዘው አጥቶ ጡትሽን ቢነካካ
እየጨባበጠ መጠኑን ቢለካ
እንዳትጠረጥሪኝ
ለሌላ እንዳይመስልሽ ውዴ ሙች እመኚኝ
.
..
በዚህ ሁሉ መሃል በስሜት ገንፍዬ
ልብስሽን ባወልቅም ልብሴን ወዲያ ጥዬ
እርቃንሽን ሆነሽ እርቃኔንም ሆኜ
አልጋው ላይ ብጥልሽ በክንዴ ዘግኜ
በሚገርም ሁኔታ ፍቅር ብንሰራም
እመኚኝ አለሜ እኔ ልሙትልሽ ምንም
አናደርግም
------------//-----------
(ምንጭ
ግጥምና ገጣሚያን ማህደር)
.
:
@getem
@getem
@getem
1
////-----//////


ፈጣሪ ነው እንጂ ፣ ሰው አይፈርድም በሰው
ብሎ ሲያንጎራጉር...
ሰዎች ፈርደውበት የተበደለ ሰው
እኔ ግን እላለሁ!
የሰው ልጅ ነው እንጂ ፣ አምላክ ፍርድ አያውቅም
በበደሎች ሁሉ...
የማይሸነፍ ነው ፣ የቸርነቱ አቅም፡፡
፡፡፡፡
ከሐጢያቶች ሁሉ ፣ ምህረቱ ያይላል
እኛ "ፍረድ" ስንል ፣ እርሱ "ይቅር" ይላል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አናም እኔ ለኔ...
የማንጎራጉረው ፣ አንድ ዘፈን አለኝ
ፍርዱ ቢለያይም...
ይቅር ብሎ ማለፍ ፣ ፍርድ ነው መሠለኝ!"

ምንጭ፦የቴሌግራም ግጥም ምሽት
አቤ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
ሰው መስለሺኝ ነበር
...............
እስኪ ስሚኝ ውዴ
ልጠይቅሽ አንዴ
ላንቺ የሰው ልጅ ማለት ትርጉሙ ምንድነው?
ፍቅርና ክብር ተስፋስ ምን ማለት ነው?
ስላንቺ ሳወራ ስላንቺ ስናገር
ለካስ አላውቅሽም ሰው መስለሺኝ ነበር
ለኔ እንኳን ግድ የለም ኃላ እንዳትጎጂ
መናቁን ተይና ሰው ማክበር ልመጂ
ለኔ ሲሆን ጊዜ ስጠራሽ ብውልም
እየቻልሽ አትችዪም እያለሽ የለሽም
ከቻልሽ አገናዝቢ ካልገባሽ ጠይቂ
ትንሽ የሚባል ሰው እንደሌለ እወቂ
ህሊና ላለው ሰው ትርግሙ ለገባው
እሺ ብሎ መቅረት እምቢ እንደማለት ነው
እኔ እኮ የሚገርመኝ ታሪክ እንደሰራ
አላፊ በሆነው በመልኳ ስትኮራ
ትመጪያለሽ እያልኩ በተስፋ ብኖርም
ባትመጪም ቅጠሪኝ ማለት ግን አልችልም
እናም አንዴ ስሚኝ ይጠቅምሻልና
ማስመሰሉን ትተሽ ሰው ሁኚ እንደገና

(ጉልላት አበበ)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍2
💗ታ ስ ፈ ል ጊ ኛ ለ ሽ

በተለይ በክረምት ሙቀት ሲያስፈልገኝ

በተለይ በምሽት ለብቻየ ስገኝ

ብርድና ባዶነት ተባብረው ሲመጡ

ባንች ተገፍትረው ፈጥነው እንዲወጡ

ከላዬ ቁጭ በይ ግርማዬ ሞገሴ

እቅፍፍፍ ስታደርጊኝ ትረካለች ነፍሴ

ጌጤ ነሽ ለአካሌ ክብርና ውበቴ

በይ ነይ ልደርብሽ ከታናሿ ቤቴ
.
.

.
.
.
.
.
.
.
.
.
ታስፈልጊኛለሽ ወፍራሟ ጃኬቴ፡፡


ዘላለም
❤️😂
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ምታተኛነትህን
@getem
@getem
መፍትሄ
(በረከት በላይነህ)

በር መስኮት ዘግተህ ፣
ቀዳዳውን ደፍነህ
የለኮስከው ሻማ "በራ"! ፣"ጠፋ"! ካለ፤

ጠርጥር!
ቤት ያፈራወ ንፋስ ከጎጆው እነዳለ።

@getem
@getem
@getemsource
እረፍት_የለሽ_ስሜት

የንጉርጉሮ ~ ንዝረት፣
እምቅ የሃሳብ ንፍዘት፣

ህይወት በቅሬታ ምጥ ሲሞላ፣
ነገር ውስጥ ውስጡን ሲብላላ፣
አንጎል ተወጥሮ በጭንቅ ሲጉላላ፣

በመፍትሄ አልባ አልቦነት፣
አዕምሮ ተጠቦ በጭንቀት፣
የተስፋ ሻማ እልም ያለ 'ለት፣

ሆኖ ይቀራል ያልለየለት፣
የተዳፈነ እሳት
ወኔ የለሽ ~ ዕብደት!!!

እረፍት



ስሜት!!!

# ሀብታሙ_ወዳጅ


#ETHIOPIAN
@getem
@getem
@getem
ከሳቁ አይቀር፣ እንደ ጃገማ!!!!
ልብ እስኪሰማ!!!!!!
ካዮ አይቀር፣ እንደጃኖ!!!
በጥልቅ ሆኖ!!!

@balmbaras
@getem
@getem
(ዘ፡ፓሳህ ፡!፡ )
<~~~~~~~~~~~>
ረስቼሻለሁ ፡፡፡
*
ድንገት ሳስታውስሽ ብትናፍቂኝም ፣
ፍቅሬ አለሜ ስልሽ ፍቅርን ባትሰጭኝም ፣
አንቺነትሽ ናፍቆኝ
ፍቅሬ ፍቅሬ ብልም ፣
ማፍቀር ከመለየት ባይስተካከልም ፣
እውነት እውነት ፍቅሬ ረስቼሻለሁ
ብትታወሽኝም ።
#::::::::::::::::::::::::::::::::::::#

ግን አፈቅርሻለሁ !!!

መርሳት ማለት ዳሩ ምን ይሆን ግን
ፍቅሬ ¿?
በልብ ውስጥ ያደገች ያበበችን ፍሬ ;
ከፍቅር ብራና ፣
ከላባ ጫፍና ፣
ከቀይ ቀለምና ፣
የደመቀን ፊደል የሚሰርዝ አርማ ፣
ማፍቀር የሚልን ቃል የሚሰርዝ ቃል ነው መርሳት ማለትማ !፤!

ብትናፍቂኝም
ረስቼሻለሁ ፥
ግን አፈቅርሻለሁ ፡፡...

#getamiwochu
@getem
@getem
@getem
👍1
#የኔ_ሌላ_ምስል
:
እንቅፋት አግኝቶኝ ፥ ስጓዝ በዱር በመንገድ
ከወገቤ ቢያጥፈኝ ፥ ሰላምታ እንደ መስገድ፣
ዘመዴ እጄን ሲይዝ ፥ 'እኔን!' ሲለኝ ፈጥኖ
'ይድፋህ!' ሲል ጠላቴ ፥ ሲረግመኝ ጨክኖ፣
ጓዴ ግን ሳቀብኝ ፥ አንጀቱ እስኪቆስል
እርሱ ነው ወዳጄ ፥ የኔው ሌላ ምስል።
--------------------//--------------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@getem
📗📒📕 ኢ - ስብራት

-- ልዑል ሀይሌ

ለተሰበረ እግር ድጋፍ ቢፈጠርም
ምርኩዝን ተማምኖ እግር አይሰበርም

@getem
@getem
ታገል ሰይፉ ለ ዶክተር አብይ 16k
ግጥም ብቻ
ታገል ሰይፍ

፨ ፍቅር ያሸንፋል 😊

ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getemsource
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem
የጁምኣው አርበኛ! !!!


እንዴት ነህ አህመዲን፤
ገሞራው ከታቢ ። የጁምኣው አርበኛ ፤
አውቀዋለሁ እኔ ፤
አልሃምዱ ሚለውን ፤ ያንተን አማርኛ ፤
ዱኣማ ይዘናል፤ አላረፍንም እኛ ።
እንዴት ነህ ፊርአውን፤ የአህመዲን አሳሪ ፤
እንጃልህ ዘንድሮ ፤
እንደቆላ ሽፍታ ፤ አጥተሃል መካሪ ።


ተራራው ቢከመር ፤
ገደሉ ቢከመር ፤ ያው ላንድ ሰሞን ነው ፤
አትጠራጠሩኝ ፤
ባህሩን ሰንጥቆ ፤
በመሃል የሚያልፈው ፤
የጀሊሉ ባሪያ ፤ አህመዲናችን ነው! !!!!
ይኸው ነው!!!!!
ወላሂ ይኸው ነው! !!!!!

((( ጃ ኖ )))

@balmbaras
@getem
@getem
አሰታራቂ የለም
(በእውቀቱ ስዩም)

ጠብ ምድርን ባይሞላት
አቤል ባይፈጠር
አቤል ያቤል ጠላት
አቤል የራሱ ጠር
አንድ ሰው ለሁለት ተከፍሎ ሲፋለም
ሸምጋይ ወይ ገላጋይ
አስታራቂ የለም

@getem
@getem
@lula_al_greeko
---------------------------------------------------
በፀጉሩ ጫፍ ስቦ ፥ አለት ሲያንቀሳቅስ
አይተን ተደምመን ፥ ተገርመን ሳንጨርስ፣
አጃኢብ! ... አጃኢብ! ...
ማን እንደሱ ታላቅ?
ማን እንደሱ ጠቢብ?
እግሩን ሽቅብ ልኮ ፥ የዝቅዝቅ ወረደ
በጭንቅላት መጥቶ ፥ በምላሱ ሄደ።
---------------------------------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@getem