ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሞሪንጋ!!!!


የፈረንጅ ሞሪንጋ ፤
ስንት አይነት በሽታ ፤ ሰርክ እየፈወሰ ፤
የኛ አገር ሽፈራው ፤
በጠራራ ጸሃይ እልፍ ሰው ጨረሰ ።
ብለን ተቀኝተን ፤
ነግረን ሳናበቃ ፤ በጉባኤ ፊት ፤
ያገሬ ገበሮች ፤
ይህንን ሺፈራው ፤
በዶማ ቆፍረው፤ መንግለው ጣሉት ።

(( ጃ ኖ ))

@Balmbaras
@getem
@getem
አቤቱ . . .
(አሌክስ አብርሃም)

ካገር ማድጋችን ውስጥ
የጥላቻ እርሾ …የቂም ቡኮ ይፍሰስ
ኑሮ የደቆሰው ደሳሳ ጎጇችን በባርኮት ይታደስ
እንደ አደይ ድምቀት ፈገግታችን ይፍካ
የተራቆተ ኪስ ይሙላ በፍራንካ
የታመሙ ነፍሳት … በገፍ ይፈወሱ
የጤና አንፋሳት በምድራችን ፊት ላይ ዘላለም ይንፈሱ
የኑሮ እርካታ ይወረድ እንደመና
የተጨቆነ ነብስ ይፈታ ይዝናና
ከኑሮ ማሳችን የፍራት አዝመራ
በነፃነት ማጭድ ከስሩ የጋጠጥ ፍራት እኛን ይፍራ !
የህፃናቶች ሳቅ በደጃችን ይድመቅ
ያዋቂወች እረፍት በሰላም ይመረቅ
ከእስረኞች አንጓ ካቴናቸው ይውለቅ
የመለያየት ግንብ በፍቅር መብረቅህ ተንኮታኩቶ ይውደቅ !!
ጎዳናዎቻችን ሞት ሞት አይሽተቱ
ወጣቶች አሻግረው ነገን ይመልከቱ
ቤታችን ይጎዝጎዝ ተስፋ እንደቄጤማ
ለተራብን እህል ውሃ ለተጠማ
በሰ. . .ፊው ይከፈት የመሪዎች ጆሮ
ህዝብ ድምፁ ይሰማ ያመፃን መቃብር
የአፈናን ትቢያ በፅናት ቆፍሮ !
ብሶት ሰለቸና
ምሬቱ መረረና
በማያልቅ ውቂያኖስ የማያልቅ ዋና
መዳከር ይብቃና
የፈጣሪ እጆች በባርኮት ይዘርጉ
እንደኖህ መርከብ ደጅ...
የክፋት ቀዳዶች በጣቱ ይዘጉ!!
ጥግንግን እድገቶች ውሽልሽል ፍስሃ
ተጠራርጎ ይሂድ እንደክረምት ውሃ
እንዳዲስ ውለደን አዲስ ጀምበር ይውጣ
ጥላቻ ያልፀነሰ አዲስ ትውልድ ይምጣ
ለሁሉም የሚታይ ብልፅግና ይዝነብ
አንዱ ሃሴት ሲያደርግ በተከፉ ዓይኖቹ ሌላው አይታዘብ
እንደጥጋብ ማእድ ምድራችን አትግፋን
ስደት ያቀጨጨን ዘፀአት ያፋፋን
ከፋን
ከምር ከፋን !!
እስከመቸ ድረስ
በልተን …ራብተኞች
ከፍለን ባለ እዳ
በራሳችን ምድር
መኖር እንደባዳ
ተዋልደን መካኖች
ተባዝተን ብቸኞች
ተከናንበን …..እርቃን ?
በቃን
ከምር በቃን !!\

@getem
@getem
@getem
#የጥምቀት_ጨዋታ_በሰኔ_16

ቦንብ ብወረውር ደረቱን ልመታው
በፍቅር ሸፍኖት አጣሁት ከቦታው
እንኪያስ...
የመሪው ልብ እና የተመሪ ቀንዶች
በአንድ ተደምሮ
የወረወርኩት ቦንብ እራሴን ከተፈኝ
አቅጣጫ ቀይሮ ፡፡

Anteneh_Tesfaye


@getem
@getem
@getem
የሁለት ዓለም ሰዎቹ 16k
ግጥም ብቻ
ክፍት ግጥም

፨ የሁለት ዓለም ሰዎች

▼▼▼▼▼
@Getemsource
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem
ወዮ ተዋህዶ!

አበው ከበቁበት እግዚኦታ እንደ ጥንቱ
ማህረነ ክርስቶስ ኪራላይሶ ማለቱ
ከነዛ ገዳማት አለ ወይ ጠሎቱ
የካህናቱ ወረብ ሽብሻቦ ውበቱ
ምነው ቅጡን ጎላብኝ ቅለቱ?
ገድል ድርሳናቱ ተዓምር ድህነታቸው፤
ማመስገኛው ወረብ ማህሌት
ዜማቸው
ከወዴት ዘመመ ከወዴት ጠፋቸው?
እስኪ ተጠየቁኝ ፈላጊስ አላቸው?
በፀሎት በምልጃ ደጁን ሚጠብቁ፤
ቀን ከሌት በመቅረዝ ባሉበት ሚደምቁ፤
መቃዳቸው የታል የትስ ተደበቁ?

÷÷÷÷÷

ታቦት ለንግስ ወቶ ገበያ ሚያደራ
ካህንሽ ምን ሆናል ለይቶ ሚጠራ?
ምዕመንሽ በረከት ለዛ ቅጡን ያጣ
ለምን ይሆን እንደው እማይፈራ ቁጣ
የተክልዬ አቋቋም ሰዓታት ማህሎቱን
አስተምረሽ መክረሽ ሆነሽ ፀሐይቱ
ልጅሽ ጥርስ አወጣ ሊነክስሽ በብርቱ
ቅዳሴሽ በዛ አለ ይቀነስ ሰዓቱ
የሰማዕታት ዝክር ሁሉ ታምራቱ
ሲል ሰማው ያ ልጅሽ ደርሶ ወረቱ፡፡
ወዮ ተዋህዶ ....
ዋኔ ለሄደ ክዶ

ናርዶስ ካሳሁን ና ውድነህ ተሾመ

@getem
@getem
@getem
👍1
~~~ግልባጭ~~~~
@ አቤል ምህረት
......
ላለማልቀስ መሳቅ ~ ላለመሞት መኖር
ላለመራብ መብላት ~ ላለማረፍ መብረር
ላለመውደቅ መቆም ~ ላለመሮጥ መዞር
ላለማማጥ መትፋት ~ በቃል ዋሽቶ ማደር
........
ቢመስልም ዕጣዬ፤
ግልባጩ እውነት ...
ቁምነገሩ ሀሴት ሆኗል ፈገግታዬ።

@getem
@getem
@getem
እኔን ምን አገባኝ

ቢሻክርም ፀጉርሽ ባያውቅም ለስልሶ
ገፅታሽ ባይታይ ውበትን ተላብሶ
አፍንቻ ባይኖርሽ ብትሆኚ ጎራዳ
አቋምሽ ባይማርክ ቢሆንም እንግዳ

እኔን ምን አገባኝ

አይንሽ ነጥብ ቢያክል ባይሆንም የጎላ
ከንፈርሽ ባያምር ባይመስል የሚበላ
ምን ጥርስሽ ስድሩ ውሉ 'ንኳ ቢጠፍ
ለሰው የዘነበው ላንቺ ባያካፋ

እኔን መን አገባኝ

እግርሽ ባይመጠን ቢመስል ከአዳም
ወዘናሽ ባይመጣ ብትሆኚ አመዳም
የዘንባባ ማር ነሽ ባይባልልሽም
የማድነቂያ ቅኔአት ላንቺ ባይደርሱሽም

እኔን ምን አገባኝ

በመንገድ ባይለክፉሽ ባይስብም ቁንጅናሽ
እንደነ እገሌ ሙገሣ ባይደርስሽ

እኔን ምን አገባኝ

ልቤ ከወደደሽ ካረገሸ የግሉ
እነዚህ ልኬቶች ከአፈር ይገባሉ
አልገጥምም አልፅፍም እንደዚህ እያልኩኝ
እ ኔ ም ን አ ገ ባ ኝ!
የኔ አለም አንቺ'ኮ የውበት ሁሉ ውብ
ውበት ካ'ንቺ ሚዘንብ ደርሶ ሚንጠባጠብ
አይንሽም ይልቃል ከሰማይ ጨረቃ
አየኸኃት በማታ ካ'ንቺ ተደብቃ
ፀሀይም ከፊትሽ በሚወጣው ፀዳል
አየሑ ስትጋጋል እራሱአን ስትከልል

እኔን ምን አገባኝ

ፀጉርሽም ዞማ ነው ማረፊያው ከዳሌሽ
በጥበብ ተሰርቱአል ባት ወተረከዝሽ
ስልክክ እንዳለ ነው ቀጭኑ አፍንጫሽ
ከገመድ ይቀጥናል ሸንቃጣው ወገብሽ
ስንቱን ይማርካል ይህ አረማመድሽ
የኔታን ያስታል ያ ሞንዳላ ዳሌሸ

እኔን ምን አገባኝ

ጥርስሽም ነጭ ነው እንደ ሀጫ በረዶ
እንደተከመረው ከሰማይ ላይ ወርዶ
ጣቶችሽ አለንጋ ጥፍሮችሽም ሰለት
የማይገለፁ ባልተማረ አንደበት

ቢሆን ምን አገባኝ

አልገጥምም አልፅፍም እንደዚህ እያልኩኝ
የኔ 'ምላት ሔዋን እ ስ ክ ት መ ጣ ል ኝ

ኧረ መን አግብቶኝ
ሆሆሆሆሆሆ ምን አገባኝ::
ስሙ አልተገለፀም

@getem
@getem
1👍1
እናት እሙ ገላ !


ደግሞ አንድ ቀን ላንቺ ከቶ ምን ሊረባ?
ዓመት ሙሉ ማሰብ
ዓመት ሙሉ ማክበር
ዓመት ሙሉ መውደድ
ዓመት ሙሉ ማፍቀር
በዘመን ቢመተር ከአንጀት ላይገባ !


ሰማሽ እሙ ገላ …


ተወርቶ ተነግሮ
በጽሁፍ ተሞንጭሮ
በፎቶ ተሰቅሎ
በቃል ተሸልሎ
ብዙ ተፎክሮ ያልቅ እንደሆን እንጃ
የተራመድኩበት የፍቅር ስጋጃ..


እማምዬ ውዴ …


አንቺ የኔ ምንጣፍ መረማመጃዬ
የኑሮ ግብግብ መለማመጃዬ
መውጣቴ መውረዴ
መውደቅ መነሳቴ
ደስታዬ ኩራቴ
ሃዘኔ ክሳቴ
ጉስቁልና ጥጌ
ጌጤና ማረጌ…


ደግሞ አንድ ቀን ላንቺ ከቶ ምን ሊረባ?
ዓመት ሙሉ ማሰብ
ዓመት ሙሉ ማክበር
ዓመት ሙሉ መውደድ
ዓመት ሙሉ ማፍቀር
በዘመን ቢመተር ከአንጀት ላይገባ!


_ // አብዲ ሰዒድ // _


@balmbaras
@getem
@getem
. . . የኔታና ሚስ . . .


ሀ – ሁ . . . አ – ቡ – ጊ – ዳ
ሀ – ሁ . . . አ – ቡ – ጊ – ዳ
ገና ከማለዳ ልጅነቴን ለምዳ
ከስትንፋስ ከደሜ ከነፍሴ ተዋህዳ . . .
ሀ – ግእዝ . . . ሁ – ካእብ
ሂ – ሳልስ . . . ሃ – ራብእ
ሄ – ኻምስ . . . ህ – ሳድስ
ሆ – ሳብእ . . . ስክልስ . . .
በዜማ ስለቅም፣ በህብር ሳወድስ
መልእክተ ዮሐንስ፣ መልክተ ዮሐንስ
ስከልስ ስከልስ፣ ለነፍሴ ሳሰልስ . . .
በአገራዊ ቃና
ሕይወቴ እንዲቃና
የኔነት፣ እኔነት፣ በደሜ እንዲዘራ
የኔታ በኩርኩም፣ አባም በከዘራ
የለፉልኝ እኔ፣ ያደድኩት ልጃቸው
ዛሬ ወጉ ደርሶኝ አባት ሆኜላቸው . . .
ልጄን ከቀለም ቤት በኩራት ሰድጄ
አቡጊዳም እዳ፣
እኔነትም ባዳ፥
ሆኖበት ሲቸገር አይቼ ነድጄ! . . .
እ – ን – ደ – ተ – ብ – ከ – ነ – ከ – ን – ኩ
እ – ን – ደ – ተ – ብ – ሰ – ለ – ሰ – ል – ኩ
“ኤ ፎር አፕል” ብሎ ልጄ አፉን ፈታ
“ኤን ብቻ!” የምትሰብክ ከፊደል ገበታ
ግእዝ የማታዜም፣ ቅኔ የማትፈታ
ማንነት ‘ማይገዳት፣ ለ’ሱ የሌላት ቦታ
ሚስ ናት የሱ የኔታ
ሚስ ናት የሱ ጌታ::
_ // _
_ // © አብዲ ሰዒድ // _

@Balmbaras
@Getem
@getem
1
# ሞት_ቀደመኝ

ሳታንኳኳ፣ ባጥር ዘላ
ከግቢዬ ዘው ብላ
ስለት ብጤ አንጠልጥላ፣
ግራ ቀኟን ስታማትር ...
ስትንሿከክ ብደርስባት
እላዯ ላይ ሰፈርኩባት።

ገዳዬ ጋር ተቆላልፈን
ገጥመን ሳለ ፍልሚያ ትግል፣
(አፍታም ሳትቆይ ...)
ድፍት አለች -- መሬት ክንብል።

(ወድቃ ሳያት ....)
መስሎኝ ነበር ለአንድ አፍታ
ትንፋሽ አጥሯት ራሷን ስታ።
(ፈራች መሰል ...)
ሳትመለስ በዛው ቀረች
ባልገድላትም በጄ ሞተች።

ወየው! ወየው!
ወየው! ወየው!
ጉድ አረገኝ መልኣከ ሞት
(አዘናግቶ... አደናግሮ )
በማር ማንኪያ ጋተኝ ሃሞት።

ራሱን ሳይገልጥ
ፍንጭ ሳይሰጥ፣
መጣሁ ሳይል ሰዓት ጠቅሶ
አጉል ሰራኝ ድንገት ደርሶ።

ድንገት ውርድ
ነብሷን ውስድ።
ቋጠሮዬን መሬት ብትን
ሳልጠይቃት የላካትን።
-----------//------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@getem
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇷🇪🇷🇪🇷

ቴዲ አፍሮ (ዳህላክ)

በይ እንዲህ ነው ህልሜ ሲፈታ
ለህፃን ነፍስ ይራራል ጌታ
አትሙት ብሎት ያለ ሀጢያቱ
መዳን ሆነ ለመርከቢቱ
ቂም ማወቁ ልቡን አይረዳም
እስከሚደርስ ፍሬያችን ለአዳም
ካስተማርሺው ፍቅርን በጊዜ
አይሻለሁ ወይ በሱ ጊዜ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ እንዳልከዳሽ

ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getemsource
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem
📖 በ — ቃ— ኝ (ብዬ ነበር)

እኔማ,

ሀዘንን ጉዳትን ህመም ስብራትን
ፍቅር ምናምንቴ ጂኒ ጃንካ ወሬ የላዉኩት እኔ
ባለመኖሬ ዉስጥ ደስታን ያተረፍኩኝ
ሀሴትን ያቀፍኩኝ
ሰላም ዉስጥ ነበርኩኝ

ግና,
አንድ ዘላለም ላይ
እድል ጀርባ ሰጥታኝ ለመኖር ብታጨኝ
ሳልፈልግ ፈልገህ 'ረፍቴን ሰረ'ከኝ
መኖርህን በግድ ኑረህ እየዉ አልከኝ

ዛሬ ግን ተለመን ይብቃህ በለኝ በቃኝ
እስትንፋስህ ስራ ኑሮህ ደግሞ ቀንበር
ሆኖብኛል እና
መኖርህን ወሰድ ኑሮዬን ግን ስጠኝ

ካለመኖሬ ዉስጥ ጎትተህ አዉጥተህ
ከፈቃዴ ዉጭ ኑር ብለህ እንዳልከኝ
አሁን አልኑርና ኑሮህን አንሳልኝ
መኖርህን እንካ መኖሬን ግን ስጠኝ::


©ናትናኤል ሰለሞን (ናት ሰን) (24/05/2010

@getem
@getem
@getem
ተራማጅ ህልም
(ናትናኤል ጌቱ)

በለምለም መስክ ላይ
አበባ 'ሚበትን ፥ ክንፋም ሰረገላ
እንደ ጠዋት ጸሀይ
ፈገግታ እያደለ ፥ ነፍስን የሚሞላ
አትመስይም?..ትመስያለሽ?...አላውቅም ...እኔንጃ!

ብቻ ገበያው ላይ
በሸማቾች መንገድ ፥ በሻጭ መነገጃ
ብርቱካን አነሳሽ...
ትርንጎም አነሳሽ
ብዙ ቀሚስ ለካሽ
ብዙ እቃዎች ነካሽ !
ይህን ሁሉ እያረግሽ

የሻጭ አይኖች በርተው ፥ አፍጠው ሲያዩሽም
ይደነቃሉ እንጂ ፥ አያስከፍሉሽም
.
ለምን ያስከፍሉሽ?
የጀነትን ታምር ማየት ፥ ምድርም ሁኖ ሰው ይጠማል
እውን መሀል የሚራመድ ፥ ህልም ማየት ያስገርማል

@getem
@getem
@lula_al_greeko
#ወድሽ_ነበር_አለሁ !

አሁን ደረስኩ ሲል ፥ ጓዙን አንጠልጥሎ
ቅድም ተብሎ ሊሸኝ ፥ ሊሄድ ተገንጥሎ፣
አሁን ከአሁን በፊት ፥ ከአፌ ላይ ቢበርም
በሚመጣው አሁን ፥ ሳልወድሽ አልቀርም።
------------------------//------------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@Getem
@getem
አቤቱታ ለፈጣሪ
(ልዑል ሀይሌ)
.
ምን አቅም አለኝና
ከማሳህ ዘር ልምረጥ
ምን ጉልበትስ ኖሮኝ
ከተከልከው ችግኝ
ለኔ ሚሆን ልቁረጥ?
.
ይሄ ዘርህ ያምራል
ያንን ዘር ልንቀለው
እያልኩ ብፎክርም
እኔም ቅንጣት ዘር ነኝ
አንተ የተከልከውን ልቀጥፍም አልችልም
.
እስቲ ልጠይቅህ
ያ'ለሙ ገበሬ
የምድሩ ዘር ሁሉ ባንተ እጅ ነውና
የዘር አረም በቅሏል
ጎተራህ ሳይወድም ጣለው ንቀልና
.
አንተን ላዝህ ቀርቶ
ቀና ብዬ ላይህ ድፍረትም ባይኖረኝ
የዘራኸን ሁሉ እየተቋጠርን
የምናልቅ መስሎኝ
ያንተ ልፋት መና ከንቱ ሆኖ ታየኝ
.
እባክህ ፈጣሪ!
እባክህ ኤልሻዳይ
ዘር ሚባለውን
ከዓይምሯችን ጣለው
እኛ ፍጥረቶችህ ተዋደን እንድታይ!
.
እባክህ!
እባክህ!
.
እባክህ ፈጣሪ
በፈጠርካት ምድር ድንበር አበጅተን
የኔ ነው የኔ ነው ተባብለን አድረናል
ሁሉ ያንተ መሆኑን
ዘንግተን ከኖርን ብዙ ዓመት ሆኖናል
.
ትዕዛዝ አይሁንና
ከበረት ወጥተናል
ምናለ ብትመጣ ላፍታ ብትመልሰን
በምድርህ አይደል ወይ
ዘር እያማረጥን ምንጋጨው አርሰን
በተጋጨን ቁጥር
ምናመሸው ቀኑን
ምናነጋው ሌቱን አልቅሰን አልቅሰን
.
እባክህ!
እባክህ!
.
.
እባክህ አምላኬ
.
በባቢሎን ምክንያት
ሐጢያታችን በዝቶ
ቋንቋ ልሳናችን ለይተህ ቃኝተሃል
ግድ የለም አሁን ግን
ቋንቋችንን ቀማን
እንዳንደርስብህ ግንቡ ይሻልሃል
.
እባክህ!
እባክህ!
.
.
.
እባክህ ጌታ ሆይ
.
መጮሁ ደክሞናል
መጮህ አቅቶናል
መጣራት አቃተን
ተዋደዱ እንዳልከን
ተፋቀሩ እንዳልከን
መስማማቱን አጥተን
በአምሳልህ ተፈጥረን
አምሳልህን ሸጠን
ለዘር ቀለም ሰጥተን
.
እባክህ!
እባክህ!
.
.
.
እባክህ ፈጣሪ!
አንተን ልናከብር
የፈጠርክልን አንደበት ተዘጋ
አንተን ዘንግተናል
ውዳሴያችን ሁሉ
ዘሬ ዘሬ ሆኗል በነጋ በጠባ!
.
እባክህ!
እባክህ!
.
እባክህ ፈጣሪ
በፈጠርካት ምድር ድንበር አበጅተን
የኔ ነው የኔ ነው ተባብለን አድረናል
ሁሉ ያንተ መሆኑን
ዘንግተን ከኖርን ብዙ ዓመት ሆኖናል
.
እባክህ!
እባክህ!
.
አንተን ላዝህ ቀርቶ
ቀና ብዬ ላይህ ድፍረትም ባይኖረኝ
የዘራኸን ሁሉ እየተቋጠርን
የምናልቅ መስሎኝ
ያንተ ልፋት መና ከንቱ ሆኖ ታየኝ
.
እባክህ ፈጣሪ!
እባክህ ኤልሻዳይ
ዘር ሚባለውን
ከዓይምሯችን ጣለው
እኛ ፍጥረቶችህ ተዋደን እንድታይ!

20-10-10
(ልዑል ሀይሌ)

@getem_sourcebot
@getem
@getem
#አብይ_ጉዳይ

ከዘመናት በፊት
በጦቢያ ምድር ላይ አንድ ዘር ወደቀ
ከዘመን በኋላ
ጊዜያትን ቆጥሮ ስር ይዞ ፀደቀ
የፀደቀው ፍሬ
አሽቶ አበበ ለማ ተጎንጉኖ
ይህን ጊዜ ታድያ
ሀገራት ዘገቡት አብይ ጉዳይ ሆኖ ፡፡

Anteneh_Tesfaye

@getem
@getem
@getem
ጥ – ሬ. . . !


“ዶሮ ብታልም ያው ጥሬዋን”
_ ብለህ ያልከኝ ጓዴ


በል እንካ ጥሬ ቃል
_ ከጥሬ ልቦና፣ ለጥሬው ዘመዴ . . .
*
ዶሮስ ጥሬ አለመች፣ ጥሬ ነው አለሟ ፣
ጥሬ ነው ህይወቷ፣ ጥሬ ነው ሰላሟ . . .
‘ምትከርመው በጥሬ
‘ምትኖረው ለጥሬ
አኗኗሯ ጥሬ
አሟሟቷም ጥሬ
ጥሬ… ጥሬ… ጥሬ…
እሷን መች ጠርጥሬ?! …
*
ይብላኝ እንጂ ለኔ፣ ይብላኝ እንጂ ላንተ !
በጥሬ ህልም ዓለም፣ ቀንህና ቀኔ ለተንከራተተ . . .


ተቃውሟችን ጥሬ
ድጋፋችን ጥሬ
ሽብራችን ጥሬ
ህዳሴያችን ጥሬ
ሃዘናችን ጥሬ
ደስታችንም ጥሬ
ጥሬ… ጥሬ… ጥሬ…
ብዙ ቀባጥሬ
“ልማት አሸብሬ” . . .
ሐይሌን አስደንብሬ . . .


እኔና አገሬን አጉል ከማጠፋ
ጥሬ እየጠረጠርኩ እስቲ ላንቀላፋ
አንተም ከጥሬህ ጋር ጥሬ ቀንህን ግፋ . . .

(© አብዲ ሰዒድ፣ ነሐሴ 2004)

@Balmbaras
@getem
@getem
#ሳትመጪ_ነይ !

የጀመርሽው መንገድ ፥ ጉዞሽ እንዲቃና
በስሌት ተራመጅ ፥ ስሜቱን ተይና፣
ከልካይ የለም ብለሽ ፥ አቲጅ በመደዳው
ፈንጂ ወረዳ ነው ፥ የጨዋታ ሜዳው፣
ይልቅ ኳሷን ላኪያት ፥ ትሂድ ቃልሽን ሰምታ
ከነ ሙሉ አካልሽ ፥ ህልምሽ ግቡን ይምታ።
-----------------------//------------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
"""የጦቢያ ባለሃብት"" !!!!!!


እርሻዬን ቀምቶ፣
ማጀቴን ደፋፍቶ ፣
ከቤቴ አስወጥቶ፣
ማረሻየን ሰብሮ፣ ሞፈሬን ቆስቁሶ፣
ጎተራዬን ንዶ፣ ጎጆዬን አፍርሶ፣
ቂጣዬን አንኩሮ፣ ኑሮዬን ከርችሞ፣
እንቁጭልህ ይላል፣
የማየውን እንጅ፣
የማያጎርሰኝን፣ ዳቦ ተሸክሞ።

((( ጃ ኖ )))


((( ሸጋ ጁምኣ ))


@balmbaras
@getem
@getem