ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ምስክሬ ናቸው

በንፋስ ሽውታ የመጣው ናፍቆትሽ፣
በልቤ ከትቤ ያነገስኩት ፍቅርሽ፣
በመልህቅ ሸብቦ ኣስሮ የያዘኝ ልብሽ፣
በፍላፃ የወጉኝ ክዋክብት አይኖችሽ፣
ምስክር ተደርገው ከሸንጎ ይቅረቡ፣
ሀቄን ያስረዱልኝ ሳይንተባተቡ፣
በውስጤ ያለውን እውነት ስለሚያውቁ፣
አልሻም ሌላ ኣካል እነርሱ ይጠየቁ።

29–09–2010 አብርሽ(ሀዩ)

@getem
@getem
የኔ መንገድ!!!!!


ከባርነት ጫጉላ፤
ከግርድና ማጀት፤
ና ውጣ ተብየ፤
የተጠራሁበት፤
የተቀባሁበት፤
የተመረጥኩበት፤
የልቤን ከነአን፤
በነፍሴ ሰሌዳ፤ በደም ቀለም ፅፌ፤
እንደ ኢያሱ ካሌብ፤
ከነአንን ወረስኳት፤
የሞት ውሽንፍሩን፤ ባህሩን አልፌ።


ፈርኦን ሞኝ ነው፤
ተከትሎኝ ነበር፤
በግዞት ማድጋ ፤
መልሶ ሊግተኝ፤ የምሬት ሰፍነጉን፤
ተመለስ እያለ፤
እያግተለተለ፤
የፉከራ ሰልፉን፤ የትእቢት ፈረሱን።


እናም እንደዚህ ነው፤
በሰው መንገድ ቀንተው፤
በሄድኩበት ዱካ፤
እንሂድ እናስቀረው፤ ብለው የፎከሩ፤
ባህሩ ተከፍሎ፤
መልካውን ስሻገር፤
መንገዱ በላቸው፤ ውሃ ሆነው ቀሩ።


ይኸው በኔ ቀዬ፤
የሰው መንገድ ጥጉ፤
ለነሱም የሚሆን እየመሰላቸው፤
በሰው መንገድ ቀንተው፤
ከመንገድ ሊያስቀሩኝ፤
መንገድ የጀመሩ፤
እንደ ፈርኦን ጦር፤ ቀይ ባህር ዋጣቸው።

((( ጃ ኖ )))

@Balmbaras
@getem
@getem
#ከመለስ የተላከ ደብዳቤ


እንደው ዶክተር አብይ
ህዝቡን ምን አረከው ~ ምንድን አስነካኸው

ራዕዬን ትቶ
ከኔ በላይ ላንተ ~ እንዲህ የሰገደው??

ከሁሉ ከሁሉ
እኔን የገረመኝ
የሲኦሉ ጌታ ~ ሰይጣን እንኳ ባቅሙ

በመደመር ወንጌል
የፍቅር ደብዳቤ
ማመልከቻ ፅፎ
ለእግዜር በመላኩ
መልአክታት ሁሉ ~ ባንተ ተገረሙ፡፡

ምን ሰይጣኑ ብቻ
ሲኦልም ቃጠሎው ~ በፍቅር ቀዝቅዞ

ሰላም የበዛበት
መዝናኛ ይመስላል ~ ባንተ ድርጊት ፈዞ፡፡

እንደው ግን በሞቴ
ሀምሳ ሎሚ ላንዱ ~ መጫኛ ሸክም ነው

የሚለውን ተረት
የሀገሬን እውነት ~ እንዴት እረሳኸው??

የሚል ፅሁፍ ፅፌ
በመንፈሴ ብልክ ~ እንድተነትነው

አንተ ግን ብልጥ ነህ
ክፍልፍሉን ሁላ
ደምረህ ደምረህ ~ ወደ አንድ አመጣኸው፡

እና ይገርምሀል
እኔ በሰራሁት ግፍና መከራ ~ ይደሰታል ያልኩት

ሰይጣንም እንደ ሰው
ሙድ እዬያዘብኝ
አያጅቦ እንዴት ነህ ~ ይለኛል ቀን ከሌት፡፡
፡<
እናም እባክህን
እዚህ እንኳ ልረፍ ~ ፍቅርህን ላክልኝ

እዚያም ላሉ ጅቦች
መደመር ይበጃል ~ ብለህ ንገርልኝ፡፡

# መለስ ነኝ ከሲኦል
ሚኪያስ

@getem
@getem
ትንሽ ቁረጭና!!!!!!!


አንች እናት!!!!!
ውብ እናት!!!!!!
ልስጥህ አትበይኝ፣
ውሰድ አትበይኝ፣ ርስትሽ ይቅርብኝ፣
ሰርክ ከሚያበራው፣
ከብርሃን ፈገግታሽ፣
ከሩህሩህ አንጀትሽ፣ መቼም አይበልጥብኝ።
ከብቱን ላሙን ተይው፣
አልፈልግም እኔ፣
ያንችን ጠገራ ብር፣ ወርቅ ማርትሬዛ፣
እምዬ ልንገርሽ፣
ክስካሽ ፈረንካ፣
እንጀራ ነው እንጅ፣ደግነት አይገዛ።


እናም አንች ሸጋ፣
እናም አንች እናቴ፣
የሆዴን ልንገርሽ፣
ቤትሽን የሞላው፣ ጠገራው ርስቱ፣
ጋሻ የገመሰው፣ ከብትና መሬቱ፣
ውሰድ አትበይኝ
ከቶ ምን ሊሆነኝ፣ ኮተታ ኮተቱ፣
እረ ምን ሊረባኝ፣ ምን ሊሆነኝና፣
ብሩንም እርስቱን፣
እኔ አልፈልገውም፣ ይቅርብኝ ተይና፣
ካንጀትሽ አካፍሊኝ፣ትንሽ ቁረጭና።

((( ጃ ኖ )))

ሸጋ ቀን !!!


@balmbaras
@getem
@getem
👍1
:
"ተያይዞ ቢቆም ፥ ሁሉም ለአመሉ
አጥር አይምሰልሽ ፥ የከበበሽ ሁሉ!"
。。。
በረከት በላይነህ©

@getem
@getem
@getem
ሞሪንጋ!!!!


የፈረንጅ ሞሪንጋ ፤
ስንት አይነት በሽታ ፤ ሰርክ እየፈወሰ ፤
የኛ አገር ሽፈራው ፤
በጠራራ ጸሃይ እልፍ ሰው ጨረሰ ።
ብለን ተቀኝተን ፤
ነግረን ሳናበቃ ፤ በጉባኤ ፊት ፤
ያገሬ ገበሮች ፤
ይህንን ሺፈራው ፤
በዶማ ቆፍረው፤ መንግለው ጣሉት ።

(( ጃ ኖ ))

@Balmbaras
@getem
@getem
አቤቱ . . .
(አሌክስ አብርሃም)

ካገር ማድጋችን ውስጥ
የጥላቻ እርሾ …የቂም ቡኮ ይፍሰስ
ኑሮ የደቆሰው ደሳሳ ጎጇችን በባርኮት ይታደስ
እንደ አደይ ድምቀት ፈገግታችን ይፍካ
የተራቆተ ኪስ ይሙላ በፍራንካ
የታመሙ ነፍሳት … በገፍ ይፈወሱ
የጤና አንፋሳት በምድራችን ፊት ላይ ዘላለም ይንፈሱ
የኑሮ እርካታ ይወረድ እንደመና
የተጨቆነ ነብስ ይፈታ ይዝናና
ከኑሮ ማሳችን የፍራት አዝመራ
በነፃነት ማጭድ ከስሩ የጋጠጥ ፍራት እኛን ይፍራ !
የህፃናቶች ሳቅ በደጃችን ይድመቅ
ያዋቂወች እረፍት በሰላም ይመረቅ
ከእስረኞች አንጓ ካቴናቸው ይውለቅ
የመለያየት ግንብ በፍቅር መብረቅህ ተንኮታኩቶ ይውደቅ !!
ጎዳናዎቻችን ሞት ሞት አይሽተቱ
ወጣቶች አሻግረው ነገን ይመልከቱ
ቤታችን ይጎዝጎዝ ተስፋ እንደቄጤማ
ለተራብን እህል ውሃ ለተጠማ
በሰ. . .ፊው ይከፈት የመሪዎች ጆሮ
ህዝብ ድምፁ ይሰማ ያመፃን መቃብር
የአፈናን ትቢያ በፅናት ቆፍሮ !
ብሶት ሰለቸና
ምሬቱ መረረና
በማያልቅ ውቂያኖስ የማያልቅ ዋና
መዳከር ይብቃና
የፈጣሪ እጆች በባርኮት ይዘርጉ
እንደኖህ መርከብ ደጅ...
የክፋት ቀዳዶች በጣቱ ይዘጉ!!
ጥግንግን እድገቶች ውሽልሽል ፍስሃ
ተጠራርጎ ይሂድ እንደክረምት ውሃ
እንዳዲስ ውለደን አዲስ ጀምበር ይውጣ
ጥላቻ ያልፀነሰ አዲስ ትውልድ ይምጣ
ለሁሉም የሚታይ ብልፅግና ይዝነብ
አንዱ ሃሴት ሲያደርግ በተከፉ ዓይኖቹ ሌላው አይታዘብ
እንደጥጋብ ማእድ ምድራችን አትግፋን
ስደት ያቀጨጨን ዘፀአት ያፋፋን
ከፋን
ከምር ከፋን !!
እስከመቸ ድረስ
በልተን …ራብተኞች
ከፍለን ባለ እዳ
በራሳችን ምድር
መኖር እንደባዳ
ተዋልደን መካኖች
ተባዝተን ብቸኞች
ተከናንበን …..እርቃን ?
በቃን
ከምር በቃን !!\

@getem
@getem
@getem
#የጥምቀት_ጨዋታ_በሰኔ_16

ቦንብ ብወረውር ደረቱን ልመታው
በፍቅር ሸፍኖት አጣሁት ከቦታው
እንኪያስ...
የመሪው ልብ እና የተመሪ ቀንዶች
በአንድ ተደምሮ
የወረወርኩት ቦንብ እራሴን ከተፈኝ
አቅጣጫ ቀይሮ ፡፡

Anteneh_Tesfaye


@getem
@getem
@getem
የሁለት ዓለም ሰዎቹ 16k
ግጥም ብቻ
ክፍት ግጥም

፨ የሁለት ዓለም ሰዎች

▼▼▼▼▼
@Getemsource
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem
ወዮ ተዋህዶ!

አበው ከበቁበት እግዚኦታ እንደ ጥንቱ
ማህረነ ክርስቶስ ኪራላይሶ ማለቱ
ከነዛ ገዳማት አለ ወይ ጠሎቱ
የካህናቱ ወረብ ሽብሻቦ ውበቱ
ምነው ቅጡን ጎላብኝ ቅለቱ?
ገድል ድርሳናቱ ተዓምር ድህነታቸው፤
ማመስገኛው ወረብ ማህሌት
ዜማቸው
ከወዴት ዘመመ ከወዴት ጠፋቸው?
እስኪ ተጠየቁኝ ፈላጊስ አላቸው?
በፀሎት በምልጃ ደጁን ሚጠብቁ፤
ቀን ከሌት በመቅረዝ ባሉበት ሚደምቁ፤
መቃዳቸው የታል የትስ ተደበቁ?

÷÷÷÷÷

ታቦት ለንግስ ወቶ ገበያ ሚያደራ
ካህንሽ ምን ሆናል ለይቶ ሚጠራ?
ምዕመንሽ በረከት ለዛ ቅጡን ያጣ
ለምን ይሆን እንደው እማይፈራ ቁጣ
የተክልዬ አቋቋም ሰዓታት ማህሎቱን
አስተምረሽ መክረሽ ሆነሽ ፀሐይቱ
ልጅሽ ጥርስ አወጣ ሊነክስሽ በብርቱ
ቅዳሴሽ በዛ አለ ይቀነስ ሰዓቱ
የሰማዕታት ዝክር ሁሉ ታምራቱ
ሲል ሰማው ያ ልጅሽ ደርሶ ወረቱ፡፡
ወዮ ተዋህዶ ....
ዋኔ ለሄደ ክዶ

ናርዶስ ካሳሁን ና ውድነህ ተሾመ

@getem
@getem
@getem
👍1
~~~ግልባጭ~~~~
@ አቤል ምህረት
......
ላለማልቀስ መሳቅ ~ ላለመሞት መኖር
ላለመራብ መብላት ~ ላለማረፍ መብረር
ላለመውደቅ መቆም ~ ላለመሮጥ መዞር
ላለማማጥ መትፋት ~ በቃል ዋሽቶ ማደር
........
ቢመስልም ዕጣዬ፤
ግልባጩ እውነት ...
ቁምነገሩ ሀሴት ሆኗል ፈገግታዬ።

@getem
@getem
@getem
እኔን ምን አገባኝ

ቢሻክርም ፀጉርሽ ባያውቅም ለስልሶ
ገፅታሽ ባይታይ ውበትን ተላብሶ
አፍንቻ ባይኖርሽ ብትሆኚ ጎራዳ
አቋምሽ ባይማርክ ቢሆንም እንግዳ

እኔን ምን አገባኝ

አይንሽ ነጥብ ቢያክል ባይሆንም የጎላ
ከንፈርሽ ባያምር ባይመስል የሚበላ
ምን ጥርስሽ ስድሩ ውሉ 'ንኳ ቢጠፍ
ለሰው የዘነበው ላንቺ ባያካፋ

እኔን መን አገባኝ

እግርሽ ባይመጠን ቢመስል ከአዳም
ወዘናሽ ባይመጣ ብትሆኚ አመዳም
የዘንባባ ማር ነሽ ባይባልልሽም
የማድነቂያ ቅኔአት ላንቺ ባይደርሱሽም

እኔን ምን አገባኝ

በመንገድ ባይለክፉሽ ባይስብም ቁንጅናሽ
እንደነ እገሌ ሙገሣ ባይደርስሽ

እኔን ምን አገባኝ

ልቤ ከወደደሽ ካረገሸ የግሉ
እነዚህ ልኬቶች ከአፈር ይገባሉ
አልገጥምም አልፅፍም እንደዚህ እያልኩኝ
እ ኔ ም ን አ ገ ባ ኝ!
የኔ አለም አንቺ'ኮ የውበት ሁሉ ውብ
ውበት ካ'ንቺ ሚዘንብ ደርሶ ሚንጠባጠብ
አይንሽም ይልቃል ከሰማይ ጨረቃ
አየኸኃት በማታ ካ'ንቺ ተደብቃ
ፀሀይም ከፊትሽ በሚወጣው ፀዳል
አየሑ ስትጋጋል እራሱአን ስትከልል

እኔን ምን አገባኝ

ፀጉርሽም ዞማ ነው ማረፊያው ከዳሌሽ
በጥበብ ተሰርቱአል ባት ወተረከዝሽ
ስልክክ እንዳለ ነው ቀጭኑ አፍንጫሽ
ከገመድ ይቀጥናል ሸንቃጣው ወገብሽ
ስንቱን ይማርካል ይህ አረማመድሽ
የኔታን ያስታል ያ ሞንዳላ ዳሌሸ

እኔን ምን አገባኝ

ጥርስሽም ነጭ ነው እንደ ሀጫ በረዶ
እንደተከመረው ከሰማይ ላይ ወርዶ
ጣቶችሽ አለንጋ ጥፍሮችሽም ሰለት
የማይገለፁ ባልተማረ አንደበት

ቢሆን ምን አገባኝ

አልገጥምም አልፅፍም እንደዚህ እያልኩኝ
የኔ 'ምላት ሔዋን እ ስ ክ ት መ ጣ ል ኝ

ኧረ መን አግብቶኝ
ሆሆሆሆሆሆ ምን አገባኝ::
ስሙ አልተገለፀም

@getem
@getem
1👍1
እናት እሙ ገላ !


ደግሞ አንድ ቀን ላንቺ ከቶ ምን ሊረባ?
ዓመት ሙሉ ማሰብ
ዓመት ሙሉ ማክበር
ዓመት ሙሉ መውደድ
ዓመት ሙሉ ማፍቀር
በዘመን ቢመተር ከአንጀት ላይገባ !


ሰማሽ እሙ ገላ …


ተወርቶ ተነግሮ
በጽሁፍ ተሞንጭሮ
በፎቶ ተሰቅሎ
በቃል ተሸልሎ
ብዙ ተፎክሮ ያልቅ እንደሆን እንጃ
የተራመድኩበት የፍቅር ስጋጃ..


እማምዬ ውዴ …


አንቺ የኔ ምንጣፍ መረማመጃዬ
የኑሮ ግብግብ መለማመጃዬ
መውጣቴ መውረዴ
መውደቅ መነሳቴ
ደስታዬ ኩራቴ
ሃዘኔ ክሳቴ
ጉስቁልና ጥጌ
ጌጤና ማረጌ…


ደግሞ አንድ ቀን ላንቺ ከቶ ምን ሊረባ?
ዓመት ሙሉ ማሰብ
ዓመት ሙሉ ማክበር
ዓመት ሙሉ መውደድ
ዓመት ሙሉ ማፍቀር
በዘመን ቢመተር ከአንጀት ላይገባ!


_ // አብዲ ሰዒድ // _


@balmbaras
@getem
@getem
. . . የኔታና ሚስ . . .


ሀ – ሁ . . . አ – ቡ – ጊ – ዳ
ሀ – ሁ . . . አ – ቡ – ጊ – ዳ
ገና ከማለዳ ልጅነቴን ለምዳ
ከስትንፋስ ከደሜ ከነፍሴ ተዋህዳ . . .
ሀ – ግእዝ . . . ሁ – ካእብ
ሂ – ሳልስ . . . ሃ – ራብእ
ሄ – ኻምስ . . . ህ – ሳድስ
ሆ – ሳብእ . . . ስክልስ . . .
በዜማ ስለቅም፣ በህብር ሳወድስ
መልእክተ ዮሐንስ፣ መልክተ ዮሐንስ
ስከልስ ስከልስ፣ ለነፍሴ ሳሰልስ . . .
በአገራዊ ቃና
ሕይወቴ እንዲቃና
የኔነት፣ እኔነት፣ በደሜ እንዲዘራ
የኔታ በኩርኩም፣ አባም በከዘራ
የለፉልኝ እኔ፣ ያደድኩት ልጃቸው
ዛሬ ወጉ ደርሶኝ አባት ሆኜላቸው . . .
ልጄን ከቀለም ቤት በኩራት ሰድጄ
አቡጊዳም እዳ፣
እኔነትም ባዳ፥
ሆኖበት ሲቸገር አይቼ ነድጄ! . . .
እ – ን – ደ – ተ – ብ – ከ – ነ – ከ – ን – ኩ
እ – ን – ደ – ተ – ብ – ሰ – ለ – ሰ – ል – ኩ
“ኤ ፎር አፕል” ብሎ ልጄ አፉን ፈታ
“ኤን ብቻ!” የምትሰብክ ከፊደል ገበታ
ግእዝ የማታዜም፣ ቅኔ የማትፈታ
ማንነት ‘ማይገዳት፣ ለ’ሱ የሌላት ቦታ
ሚስ ናት የሱ የኔታ
ሚስ ናት የሱ ጌታ::
_ // _
_ // © አብዲ ሰዒድ // _

@Balmbaras
@Getem
@getem
1
# ሞት_ቀደመኝ

ሳታንኳኳ፣ ባጥር ዘላ
ከግቢዬ ዘው ብላ
ስለት ብጤ አንጠልጥላ፣
ግራ ቀኟን ስታማትር ...
ስትንሿከክ ብደርስባት
እላዯ ላይ ሰፈርኩባት።

ገዳዬ ጋር ተቆላልፈን
ገጥመን ሳለ ፍልሚያ ትግል፣
(አፍታም ሳትቆይ ...)
ድፍት አለች -- መሬት ክንብል።

(ወድቃ ሳያት ....)
መስሎኝ ነበር ለአንድ አፍታ
ትንፋሽ አጥሯት ራሷን ስታ።
(ፈራች መሰል ...)
ሳትመለስ በዛው ቀረች
ባልገድላትም በጄ ሞተች።

ወየው! ወየው!
ወየው! ወየው!
ጉድ አረገኝ መልኣከ ሞት
(አዘናግቶ... አደናግሮ )
በማር ማንኪያ ጋተኝ ሃሞት።

ራሱን ሳይገልጥ
ፍንጭ ሳይሰጥ፣
መጣሁ ሳይል ሰዓት ጠቅሶ
አጉል ሰራኝ ድንገት ደርሶ።

ድንገት ውርድ
ነብሷን ውስድ።
ቋጠሮዬን መሬት ብትን
ሳልጠይቃት የላካትን።
-----------//------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@getem
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇷🇪🇷🇪🇷

ቴዲ አፍሮ (ዳህላክ)

በይ እንዲህ ነው ህልሜ ሲፈታ
ለህፃን ነፍስ ይራራል ጌታ
አትሙት ብሎት ያለ ሀጢያቱ
መዳን ሆነ ለመርከቢቱ
ቂም ማወቁ ልቡን አይረዳም
እስከሚደርስ ፍሬያችን ለአዳም
ካስተማርሺው ፍቅርን በጊዜ
አይሻለሁ ወይ በሱ ጊዜ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ እንዳልከዳሽ

ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getemsource
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem
📖 በ — ቃ— ኝ (ብዬ ነበር)

እኔማ,

ሀዘንን ጉዳትን ህመም ስብራትን
ፍቅር ምናምንቴ ጂኒ ጃንካ ወሬ የላዉኩት እኔ
ባለመኖሬ ዉስጥ ደስታን ያተረፍኩኝ
ሀሴትን ያቀፍኩኝ
ሰላም ዉስጥ ነበርኩኝ

ግና,
አንድ ዘላለም ላይ
እድል ጀርባ ሰጥታኝ ለመኖር ብታጨኝ
ሳልፈልግ ፈልገህ 'ረፍቴን ሰረ'ከኝ
መኖርህን በግድ ኑረህ እየዉ አልከኝ

ዛሬ ግን ተለመን ይብቃህ በለኝ በቃኝ
እስትንፋስህ ስራ ኑሮህ ደግሞ ቀንበር
ሆኖብኛል እና
መኖርህን ወሰድ ኑሮዬን ግን ስጠኝ

ካለመኖሬ ዉስጥ ጎትተህ አዉጥተህ
ከፈቃዴ ዉጭ ኑር ብለህ እንዳልከኝ
አሁን አልኑርና ኑሮህን አንሳልኝ
መኖርህን እንካ መኖሬን ግን ስጠኝ::


©ናትናኤል ሰለሞን (ናት ሰን) (24/05/2010

@getem
@getem
@getem
ተራማጅ ህልም
(ናትናኤል ጌቱ)

በለምለም መስክ ላይ
አበባ 'ሚበትን ፥ ክንፋም ሰረገላ
እንደ ጠዋት ጸሀይ
ፈገግታ እያደለ ፥ ነፍስን የሚሞላ
አትመስይም?..ትመስያለሽ?...አላውቅም ...እኔንጃ!

ብቻ ገበያው ላይ
በሸማቾች መንገድ ፥ በሻጭ መነገጃ
ብርቱካን አነሳሽ...
ትርንጎም አነሳሽ
ብዙ ቀሚስ ለካሽ
ብዙ እቃዎች ነካሽ !
ይህን ሁሉ እያረግሽ

የሻጭ አይኖች በርተው ፥ አፍጠው ሲያዩሽም
ይደነቃሉ እንጂ ፥ አያስከፍሉሽም
.
ለምን ያስከፍሉሽ?
የጀነትን ታምር ማየት ፥ ምድርም ሁኖ ሰው ይጠማል
እውን መሀል የሚራመድ ፥ ህልም ማየት ያስገርማል

@getem
@getem
@lula_al_greeko