ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
####ይሰቀል!###
(ቁ.1)

ያ ከርታታ ምስኪን
ይለብሰው ይጎርሰው
የሚቀምሰው ያጣ
በስርቆት ተይዞ
በአደባባይ ቆሞ
በሞት እንዲቀጣ።
ጀማው በጠቅላላ
ህዝበ-አዳም ሁሉ
"ይሰቀል! ይሰቀል! "
እያሉ ይጮሀሉ።
አንቺንም አየሁሽ
ከተሰበሰበው ከሰፊው ህዝብ
መሀል ከ'ምብርቱ ላይ ቆመሽ
ሳንቃ ደረትሽን
ለፀሀይ አጋልጣሽ
መቃው አንገትሽን በረጅሙ
አስገሽ
በኮራው ውብ ዳሌሽ
ግራ ቀኝ ተጋፍተሽ
በሙዚቃው ድምፅሽ
አብረሽ ከነ'ሱ ጋር
"ይሰቀል! ይሰቀል!"
እያልሽ ትጮኺያለሽ።
መስረቅ ካስኮነነ
እሱን "ይሰቀል!" ካልሽ
የ'ኔን ነብሴን ልቤን ቀልቤን
ሁሉ ሰርቀሽ
እስኪ መልሺልኝ
አንቺን ማን ሰቀለሽ!?


(መንግስቱ መ.)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ዝሰንውብነት(ልዑል ሀይሌ)
.
ዝንብ!
አበባው በሞላው በውብ ፅዱ ቦታ
መች የልቡ ይደርሳል
የቆሻሻ ክምር ሆኖበት ትዝታ
.
በቆሻሻ ናፍቆት ዝንቡ ያንጎራጉራል
ከአደይ መሀል ቆሞ ገንዳውን ይጣራል
.
"ቆሻሻ ናፈቅሺኝ ቆሻሻ ናፈቅሺኝ
ለምን ነው ከአበባው የሄድሽው ጥለሺኝ?
.
ነይ ከቆሻሻው ላይ አንሺኝ ከአበባው
ትዝታሽ ገደለኝ ጠፋኝ ዙሪያ ገባው"
.
እያለ ሲተዝት ሲያንጎራጉርላት
የዝንቡ ትዝታ ንቧን ሳቅ ቢገላት
.
በንብነት መኖር
መች ዝንብን ያስመኛል?
ከአበባው ይልቅ
ከቆሻሻው ክምር ትልቅ ጣዕም ይገኛል
.
ከውብ ፅጌረዳ ጉርሻ እየቀሰሙ
ውብ ነገር እያዩ ውብ ድምፅ እየሰሙ
እንደ ንቧ መኖር ምኑ ያስደንቃል?
ማንም ሰነፍ ፍጥረት
በተመቸ መንገድ መራመዱን ያውቃል
.
ይልቅ እንደ ዝንቡ!
.
ከቆሻሻው ክምር ከተናቀው መንደር
የራስን ፈልጎ ራስ እንደማሳደር
.
ወደር የለሽ ደስታ ዝንብን እንደማከል
ሁሉም ከሸሸው ላይ የራስ ጎጆ መትከል
.
የታል የሚያስደስት?
.
ዝንብ ሆኖ እንደመብረር
ዝንብ ሆኖ እንደማረፍ
በሁሉም ተጠልተው
ሆድ እያጠገቡ የገዛ ነፍስ ማትረፍ
.
ምናል የሚያስደስት?
.
ጥላቻን ማግለልን ከልብ ሳያዘልቁ
ከፍጥረት ግርፋት
በቆሻሻ ክምር ራስ እየደበቁ
.
ዝንብ ሆኖ እንደመኖር
ዝንብ ሆኖ እንደማየት
ምን ጥንካሬ አለ?
በሁሉ ተገፍተው ዕድሜ እንደማቆየት

@getem_sourcebot

@Getem
@getem
@getem
👍1
አርብና አረብ ገንዳ!!!!!!!!!!!!!!


መገን አረብ ገንዳ፤
አርብ ረፋዱ ላይ፤
የቢላል ምልክት፤
አዛኑ ሲሰማ፤ ቁኽጥባው ሲዘረዘር፤
ጦሳም አሚን ይላል፤ እንኳንስ የአደም ዘር።


((( ጃ ኖ ))(

መልካም ጁምኣ!!!!!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
አዋጅ አዋጅ አዋጅ!!


በነገው እለት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የድጋፍ
ሰልፍ ለማድረግ ወደ መስቀል አደባባይ ለምትወጡ
የአዲስ አበባ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ ባዶ
እጃችሁን እንዳትወጡ ተብላችኋል።
በክረምት ወር በብርድና በቁር እየተመቱ የጎዳናን ህይወት
ለሚጋፈጡ ዜጎቻችን፤ የማትለብሷቸውን፤ ቁም
ሳጥኖቻችሁ ውስጥ ያለ አገልግሎት የተቀመጡ ልብሶችን
በአንድ እጃችሁ ይዛችሁ መውጣት እንዳትረሱ።
ድንገት በእለቱ ቲሸርት ከገዛችሁ ቅያሪውንም መለገስ በጎ
ተግባር ነው። የእለቱን መልዕክት የያዘ ቲሸርት መለገስ
ከፈለጋችሁም እሰየው። ብቻ ለወገኖቻችን መስቀል
አደባባይ ባዶ እጃችሁን እንዳትመጡ።
አስተባባሪዎቹን በእለቱ ለማገዝ በጎ ፍቃደኛ የሆናችሁ
በሚከተሉት ስልኮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን
እንገልጻለን።

@Balmbaras
@Lula_al_greeko
🇪🇹ዘር ሳይኖር ሀገር ነበር 🇪🇹

ይህ የኢትዮጲያ ቻናሎች ድምጽ ነው

🇪🇹ስለሰላም እና አንድነት ፤ ስለ ፍቅር እና መከባበር ፤ስለ መዋደድ እና መተባበር ባጠቃላይ ስለ ኢትዮጲያዊነት እሴት እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹የብሄር ልዩነት ዉበት እንጂ ለመከፋፋል ምክንያት እንዳልሆነ እንመሰክራለን፡፡

🇪🇹የሀይማኖት ልዩነት ለመተሳሰር እና ለመተሳሰብ ምክንያት እንጂ ለጠላት በር መክፈቻ አለመሆኑ እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹የአምላክ ቃል ኪዳን ያለበን ፤ ከ3000 ዓመት በላይ የራሳችን ታሪክ ያለን ፤ የአብሮ መኖር ተምሳሌት የሆነች ሀገር እንዳለን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹በአባቶቻችን ደም ተቀልሞ የተጻፈ ታሪክ ባለቤት ፤የመሰዋት ሀገር ባለቤት እንደሆንን እንመሰክራለን፡፡

🇪🇹የራሳችን ባህል ወግ እና ስረአት ባለቤት ፤የአክሱም ላሊበላ ፤የሶፍ ኡመር ፤የፋሲል የቴድሮስ ሀገር ፤አባጂፋር እና ከማንም በፊት የነበረው ታላቁ የገዳ ስረአታችን የኛ መገለጫ መሆኑን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹በሀገራችን የሰላም ጥሪ ፤ፍቅርና መተሳሰብ እያመጣ ላለው ታላቁ መሪያችን ክቡር ዶክተር ጠ/ሚንስተር አብይ አህመድ ጎን መቆማችንን እና በነገው እለት ባለው ሰልፍ ላይ አብሮነታችንን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹ይቺን የመሰዋእት ሀገር የመረከብ ሀላፊነት የኛ ነው፡፡ የአንድነት መሰረታችን መደመር ነው፡፡

🇪🇹ከምንም በፊት ኢትዮጲያ ፡፡ የኛ አንድነት ለጠላት የማይናድ ተራራ ነው፡፡

🇪🇹እነሆ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ ፤ኢትዮጲያዊ ነኝ የምትል ከሆነ የሀገርክን ድምጽ አድምጥ ፤ ስለ ሰላም ዘምር ፤የአምላክህን ጥሪ ስማ ፡፡

🇪🇹አብራችሁን በመቆም ኢትዮጲያ ሀገራችንን ለለዉጥ ጎዳና እንውሰዳት ፡፡ ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታዉን ይወጡ፡፡

🇪🇹አምላክ ኢትዮጲያን ይባርክ ፡፡🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
መልአክ!!!!!


ከተገኘ ባገር፤
የወንድሙን መንገድ፤
እየደለደለ ቀድሞ የሚያበጅ፤
እሱማ መልአክ ነው፤ ክንፍ የለውም እንጅ!!!!!!

(( ጃ ኖ ))

@Balmbaras
@getem
@getem
👍1
# ሠላሜ_ሠላሜ

ልዩ አመል ያመጣን
ከመስመር የወጣን
መሪ አንገት አዙሮ ፥ በዱላው ሚመታው
ሰለሜ ~ ሰለሜው ፥ አብቅቷል ጨዋታው።
:
ያውና ... ያውልሽ ...
እዪ ወዲያ ማዶ
ተመልከች አሻግረሽ፣
:
እንደ ጥማድ በሬ ፥ ሸክም ወስደው ድርሻ
ህዝብ እና ሹመኛው ፥ ገጥመዋል ትከሻ።
-------------------------//------------------------
( በርናባስ ከበደ )

[ # የጠቅላይ_ሚኒስትር_ዶክተር_አብይ_አህመድን_ማስተ
ዋል_የተሞላበት_አላማና_መንገድ_እደግፋለሁ ።]

@Getem_sourcebot
@getem
@getem
በእድገት ማማ ላይ ፍቅር ስትንተራስ
ቅንነት የረሳ አይጠፋም ቦንብ እራስ

ሮዚ የያቡ
@getem
@getem
የከፍታ ቅኔ!!!!!!!


እንደዋልያ እግሮች፤ ፀንቶልኝ ጉልበቴ፤
ይኸው ደግሞ ዛሬ፤
ቆንጥሩን ጉድባውን ዳገቱን ወጥቼ፤
በተራራው ጫፍ ላይ፤
ከፍ ብዬ ስሄድ፤
ቁልቁል ተሸቀንጥሮ፤ወደቀ ጠላቴ!!!"""
Ameeeeeennnn

((ጃኖ ))

@balmbaras
@getem
@getem
"ለፍቅር ብተኛት ለጠብ አረገዘች"
ሆነና ነገሩ
በነጭ እርግብ ፋንታ ቦምቡን ወረወሩ
የእፉኝት ልጅ ሁሉ ተስፋ ቢስ ደረመን
ገደልናቸዉ ቢልም አንጠፋም ደህና ነን
ከመኖርም በላይ ነገን የሚያሳየን
ባንድ የተገመደ ትልቅ ፍቅር አለን።

(ሰለሞን ሰሃለ)

@getem
@getem
‘’ ኢትዩጵያዬ ‘’
እንኳን ሰው ፣ ተደስቶ ተሽሞንሙኖ ሳር ቅጠሉ
ተከትቦ ተጠርዞ ፣ መሪ ቃሉ
ከመደመር መብዛት ፣ ከመብዛት አንድነት
ካንድነት መዋደድ ፣ ከመዋደድ እድገት
ያለን ህዝብ ለመግታት
ምን ሚሉት ቂልነት ፣ ወገን ላይ ማፈንዳት?
እናት እህት መጉዳት?

ይህን የሚደግፍ ፣ ካለ በየቤቱ
ህሊና የሌለው ፣ የሆነ ነው ከንቱ
ይልቅ ሳይረፍድበት ፣ ይደመር ከጀማው
የፍቅር ስንኝ ነው ከኛ የሚሰማው
የማያልቅ ይቅርታ ከ አብይ ሚፈልቀው
መደመር ብቻ ነው
ኢትዩጵያዊነት ብቻ
ስሜት የሚሰጠው
ፍቅርን የሚያበዛው።

#አሸናፊ ገብሬ ከጅማ ዩኒቨርስቲ

@getem
@getem
#መደመር_ቅኔ_ነዉ !! ((1)) "
-
( ምንተስኖት ዋቆ)
-
ይነጋል ታያለሽ ፣
ብዬ የገጠምኩልሽ ፣
የሶስት ሺ አመት : ታላቋ ወይዘሮ ፣
ብርሀን ወጣልሽ : ፅልመት ተዘርሮ ።
ዛሬ ላይ ቢነጋም : ከመቼዉም ማልዶ ፣
# ለማ አንድነትሽ : # አብይሽን ወልዶ ።
-
-
( # 2010_ዴቻ )

ETHIOPIAN

@getem
@getem
፧፧፧ እስቲ በመሰንቆ ቅኔ እንዝረፍ፦
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፦ ያዝ እንግዲህ ፦፦፦፦
የቅጠሉ ሽታ ፥ እጅግ አፍኖኛል
ይሄንን ሺፈራው ፥ ብነቅል ይሻለኛል
ተወዲህ ሲዳማ ፥ ተወዲያ ጋምጎፋ
በሞሪንጋ ሽታ ፥ ቤታችን ከረፋ ።



አይ አባ ሀይለ ማርያም ፥ ጭቁኑ የግዜር ሰው
መንበሩ ለብልቦት ፥ ሆዴን አላወሰው
ይሻል ነበር ወንጌል ፥ እንደልማዳችን
ውርስ አስቀጥል ብለው ፥ወጡ ተልባችን ።



ለቆረሱት ስጋ ፥ ላፈሰሱት ጠጅ
ከፋዩ አንተ ነህ ፥ በርትተህ ስራ'ጅ
ትነዳለህ አሉ ፥ ተቀምጠህ ጋቢና
ስንቱ ወጣት ቆሞ ፥ ቀርቶ በጎዳና ።



ለማ ለማ ሲሉኝ ፥ አረሙ መስሎኛል
ለካስ ጤናዳም ነው ፥ተሩቁ ታይቶኛል
ስንቱን ጂኒ ሁላ ፥ ያስላቅቃል አሉ
አባይ እረገፈ ፥ እንደሳር ቅጠሉ ።



ታደሰልኝ ሀይሌ ፥ ካሱም እንደ ካሳ
መርገም ቤቴ ቀርቶ ፥ በረከት ተረሳ
ጳጳስ ቄስ አልጠፋ ፥በሀገር በቤቱ
ስብሃት እያሉ ፥ምነው የማይፈቱ ።



አቢይ አቢይ ቢሉ ፥ ያው ጦሙን ነው ብዬ
ሰውም አቢይ አለው ፥ኸረ እናንተ ሆዬ
በመንበር ቢሆኑ ፥ በመድረክ ቢቆሙ
ቁርጥ የመሰለኝ ፥ ድስትና ግጣሙ
ሲናዳነ ኖሮ ፥ ስንቱ እንከፍ ጋሬጣ
ይገዛኛል ያልኩት ፥ አባት ሆኖኝ መጣ
ልክ እንደብሉያት ፥ እንደመፃህፍት
ክፋ መጣ ብዬ ፥ ስጀምር ትንቢት
ጣድቅ ንጉስ ታየኝ ተወደ ናዝሬት ።



እኔ እጣን አለበኝ ፥ ለፂዮን ታቦት
ልቦና ይስጥህ ብዬ ፥ የተሳልኩበት
ወይ እንደ ገሞራ ፥ ያሙቅህ በሳት ።



እንዴት አድሯል አባይ ፥ያፈለገ ጣና
ገዴን ያመጣልኝ ፥ አርጎ ባለዝና
በኣባይ አናት ላይ ፥ ባህር ዳር ደመቀ
ዛሬ ያኮራኝ ገባ ፥ እንዳልተሳቀቀ ።



ወየሁ መጣ ፍቅሬ ፥ የብዕሩ ጌታ
ፍቅር የድሬ ሰው ፥ የቶሎሳ ሽታ
ቲያስተሳስር ያድራል ፥ ሀበሻን ባንዳፍታ
ፍቅር ጠፋ ብዬ ፥ ባገር በመንደሩ
ቀለም ይዞ መጣ ፥ ፍቅሬ ተነክብሩ
ይቀባኝ ጀመረ ፥ ያረሰርሰኝ
ሀገሬን ሀገሬን ፥ ሀገር አሰኘኝ
በመስተፋቅሩ ፥ አስለፈለፈኝ ።



በሉ ፍቷትማ ፦
እነባለ እውቀት ፥ እነ በሳሰሉ
እንዳሻው ይሆናል ፥ ብላችሗል አሉ
ሰው ታልዘለለበት ፥ እንዳሻው ባገሩ
ሀገሬ ማለቱ ፥ ምንድነው ሚስጥሩ ።


አልያም ተርጉሟት ፦
እነ ወሬ አደር ፥ እነ ነውር ጌጡ
እንዳሻው ይጥፉል ፥ ብላቹ አቃልጡ
እኔ እንደው ብያለሁ ፥ ዐለሙ ይፍረደኝ
እንኳን በናት ምድሬ ፥ የትም እንዳሻው ነኝ ።





14-10-10
( እንዳሻው አለማየሁ ፦ ፦ ።)

@getem
@getem
#ወረት_ብቻ_እንዳይሆን

ወደ ገነት ስትሮጥ ፥ ቅን ነብሴን ለማፅደቅ
ቀኜን ቀን ቢጥላት ፥ ተቆርጣ ብትወድቅ፣
ወረት ብቻ እንዳይሆን ፥ ነገረ ሥራዬ
እግሬን ተሸከምኳት ፥ እኔም በተራዬ።
-----------><----------
( በርናባስ ከበደ )

@getem_sourcebot
@getem
@getem
ቢኒ የቅዱስ ሚካኤል ልጅ

ዶ= ዶግ አመድ አድርጎት የጅቦቹን ሴራ
ክ= ክብር አጎናፅፎ የእማማን አደራ
ተ= ተገኘቷል ሙሴያችን ፍቅር ለሀገራችን
ር= ርስት ሆኖ ሊቆየን ውሎ ከልባችን
አ= አብሮነት አዋቂ በፍቅር ማራኪ
ብ= ብርሃን ፈንጣቂ አንድነት ሰባኪ
ይ= ይሁን ብሎ አማኝ
አ= አይሰስት ቸር አዳኝ
ህ= ህያው አስተሳሰብ ብሄራዊ አርማ
መ= መድሃኒቷ የሆነ ከልብ የሀገር ካስማ
ድ= ድንቅ ሰው ተገኝቷል ዛሬ ደስ ይበልሽ ኩሪልን እማማ


እናመሰግናለን ታላቁ መሪያችን
ታሪካዊ ቀን 16/10/2009
ለዚች ታሪካዊ ቀን በመብቃታችን እድለኞች ነን ለሞቱት ወገኖቻችን ነፍስ ይማርልን🙏🙏🙏
ለተጎዱትም ምህረቱን ስጥልን 🙏🙏🙏

@getem
@getem
@getem
👍3
ነቢል መሐመድ (ዘ፡ፓሳህ ፡!፡)

ከምድረ ሐበሻ ሀገር ፍቅርን ሊሰብኩ
ቢሹ ፣
በቦምብ አድርገው ፈጇቸው አገርን ከህብረት ሊያሸሹ ፣
ቢሸሽ ወዴት ሰው ከራሱ ፣
ኀላም ፊቱም ያለው ከ'ርሱ ፣
የማንነት ጥንቱም ፊቱ ፣
እኔነት ነው እርሱነቱ ፡፡

መታሰቢያነቱ ፦ ክቡር ጠ/ሚኒስቴር
ዶ/ር አብይ አህመድን ለምንደግፍ ሁሉ እርሱ ውስጥ እኛነታችን አለ ላልን ሁላ ፡፡

@getem
@getem
ምስክሬ ናቸው

በንፋስ ሽውታ የመጣው ናፍቆትሽ፣
በልቤ ከትቤ ያነገስኩት ፍቅርሽ፣
በመልህቅ ሸብቦ ኣስሮ የያዘኝ ልብሽ፣
በፍላፃ የወጉኝ ክዋክብት አይኖችሽ፣
ምስክር ተደርገው ከሸንጎ ይቅረቡ፣
ሀቄን ያስረዱልኝ ሳይንተባተቡ፣
በውስጤ ያለውን እውነት ስለሚያውቁ፣
አልሻም ሌላ ኣካል እነርሱ ይጠየቁ።

29–09–2010 አብርሽ(ሀዩ)

@getem
@getem