ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አ-ብ-ይ


አ= አንድ ላይ
ብ= ብንደመር
ይ = ይበጀናል! !!!

((( ጃ ኖ ))

@Balmbaras
@getem
@getem
🤩1
«ታውቂያለሽ አለሜ!»

(ይበልጣል ስዩም)
:
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ህይወት ፋርስ ቲያትር…
ሰው ይሉት ተዋናይ አለም ይሏት መድረክ፣
በእኔ ምስኪን መኖር
ተውኔቱ ሲሰራ ታሪኩ ሲተረክ!
የድማሜ አድማስ…
ከማሰብ ጉልላት አጀብ የተከለ፣
እኔ ይሉት ሰውነት…
ከመሆን እንዳይደርስ በሰው ተከለለ!
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ምልሽን ሳልጨርስ…
ቅንጣት ጅማሮዬን…
የአካሌን ሀቂቃ ላንቺ ሳልተነፍስ
ኢመንት እምነት የለሽ…
ጥራዝ ነጠቁ ሰው ተወዶ ከየሱስ
ተቀበል ይለኛል!
ጌታን ያህል ንጉስ!
መጠን የሌለውን ችሎ ላያሲዘኝ
እነደ ተራ ፍራንክ…
ተቀበል እያለ ለምነው የሚያዘኝ?
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ጆሮዬ እሰኪበጠስ
ሊሰጥ የወደደ ሊሰብክ የወደደ
ፍቅረኛው ብትደውል…
የቃል ኢየሱሱን…
እኔ ጋር ወርውሮ ሊቀበላት ሄደ!
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?

ድማሜን ይዤ …. ምልሽን ሳልጨርስ…
ድንፋታም ሰካራም…
ስሙ እሰኪጠፋበት አረቄ የጠጣ፣
መጠጣት እርኩሰት…
ከሰው አፍ ያውላል ሊል ከመንገድ ወጣ!
የቃላትን ድንበር….
በአፉ እየሻረ…
ጉልድፍ አንደበቱ እንዳንገረገረው
"መጠጥ ጣረ ሞት!
ነው ለሞት ሩብ ጉዳይ " ብሎ የተናገረው!
አፍንጫ ይሉት አካል አይቀበል የለ ማሽተት እያዛለኝ፣
በግትልትል ትንፋሽ …
ስካሩን አውሶኝ አጠጣ አትስከር ለምነው የሚለኝ?
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?

በግረም በሰው ልክ…
የኪሶቹን ደጃፍ በአየው አዝቅዝቄ
ከምክር በኋላ…
ጉሮሮው ሲደርቅ…
ይጎነጨው ዘንዳ ያኖረው አረቄ
ኮዳ ሙሉ አረቄ!
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?

ከኪሶቼ አድባር …
አውጥቼ ያልጣልኩት ህጌ ያደረኩት፣
ሺህ ጊዜ አንብቤ…
በእንባ ተጥለቀልቄ ከልቤ ያተምኩት…
ያ ያንቺ ደብዳቤ….
ሰው ሁን ከሚል መግቢያ…
ሀተታ እና መዝጋያው ሌላ ያልተፃፈበት፣
ሰው መሆን በቃላት…
ከዙፋኑ ወድቆ ትቢያ ያረፈበት!
እ…. አስታወስሽው…
የምኞቴ እግር…
ተለወጥ ባልሽው ልክ ዘውትር እየሮጠ፣
ላንቺ ሰው ለመሆን…
ራሱን ለመውለድ ዘመን ነው ያማጣ!
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ያ ያንቺ ደብዳቤ…
ሰው መሆኔን ንቆ ሰው እንድሆነ ያረዳ፣
የእኔን ምስኪንነት…
ሀቂቃ ያልሽውን ሀሰት ያልተረዳ!
መጣሁ ብሎ ልብሽ…
ሰርክ የሽሽት ዘፈን እያብሰለሰለ፣
የዜማሽ ተቃርኖ…
ያለመመጣት ግጥምሽ ደብዳቤው ላይ አለ!
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ምልሽን ሳልጨርስ…
ሰው ሁን ሚለው!
ሀረግ ሰው ሁን ሚለው ትዛዝ ልቤን እየናጠው፣
በአምላክ ከመፈጠር…
ድንበር ላይ አሽሽቶ ማነው የለወጠው!
ሰው ላንቺ ምንድነው?
·
ምልሽን ሳልጨርስ…
ትሆኚው አይደለም…
ታዪው እንኳን ባይንሽ ላፍታ ያልተመኘሽው፣
እርባን ሳትጥዪ…
ከክርፋታም ትቦ ከቆሻሻ ጋራ ለምን ያለሽው?
ሰው ነው ያልሽው ጎዳሽ….
ወይስ ጊዜ ሲሄድ ሰው መሆኑ ገባሽ?
አይገባንም እንጂ አንረዳም እንጂ ….
አማኝ ነው ያልሽው ሰው አለማመን ይዞ!
አትጠጡ የሚል በሱስ ተወዝውዞ!
በግዜር መሰራትን…
ተራ እምነት አድረጎ…
በሰውኛ ልኬት ሰውን እየሳለ፣
ከናዱት በኋላ…
ዘመን ማያንፀው ስንት መጉደል አለ!

@getem_sourcebot

@getem
@getem
@getem
likeን አየነው ከእግር እስከራሱ ፤
shareንም አየነው ከእግር እስከራሱ ፤
በጣም የሚመቸው ፥
ወደራስ ህሊና ሰክነው ሲመለሱ ።

((( ጃ ኖ ))

@Balambaras
@getem
@getem
የቱ ነኝ?(ልዑል ሀይሌ)

እኔ ያንቺ አፍቃሪ!..
ከፊደል ቂመኛ
የቀለም ተማሪ
ሰላሜን ያጣሁ ሰው
ሰላም አስከባሪ
.
ያንቺ በሽተኛ
የሃገር ሁሉ ዶክተር
ላንቺ እጄን የሰጠሁ
ለሃገር ዘብ የምቆም
ጀብደኛ ወታደር
.
ሁለት ጭምብል ያለኝ
ሲያሻኝ የምለብሰው
ሲያሻኝ የማወልቀው
ሲያሻኝ የማላላው
ሲያሻኝ የማጠብቀው
ሲገባም ሲወጣም
ለይቼ ማላውቀው
.
አንዳች እውነት አለ
አንዳች ሀሰት አለ
ባንቺና በሕይወት
አንቀልባ ላይ ያለ
ባንዳችሁ ጀርባ ላይ
ወጥቶ የታዘለ
.
የቱ ጀርባ እንደሆን
ለይቼ ማላውቀው
በአንዳች እውነት ነው
አንደኛውን ይዤ ሌላውን ምለቀው
.
የቱ ነው ትክክል?
የትኛው ነኝ እኔ?
የቱ ነው ጤናዬ
ወዴት ነው ህመሜ?
.
አላውቅም!
.
ግና አሁንም አለሁ!
አንቺን ተደግፌ ኑሮንም ሳልለቀው
'የቱ ነው ትክክል?'
'የትኛው ነኝ እኔ?'
ለሚለው ጥያቄ መልሱን እስከማውቀው?
.
የቱ ነኝ?!
13-10-10

@getem_sourcebot
@getem
@getem
2
“እንጠብቅሻለን” - የሳምንቱ ምርጥ ግጥም፤ በኤፍሬም ስዩም፤ Best Poem by Ephrem
ኤፍሬም ስዩም

፨ እንጠብቅሻለን 😢

ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem
.........ዘንግተኸው እንጂ.......

ከዚችጋ ስትከንፍ ከዚያች ጋር ስትበር፤
እንደምጠብቅህ - ተናግሬ ነበር።
እየጠበኩህ ነው - በቃሌ ጸንቼ ፤
ስትመጣ ማፈርሰው - ትዳር አበጅቼ፡፡

ገጣሚውን አላወቅነውም❤️
@getem_sourcebot
@getem
@getem
የቀኑ ምርጥ ፎቶ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏


@Wegoch
@Getem
####ይሰቀል!###
(ቁ.1)

ያ ከርታታ ምስኪን
ይለብሰው ይጎርሰው
የሚቀምሰው ያጣ
በስርቆት ተይዞ
በአደባባይ ቆሞ
በሞት እንዲቀጣ።
ጀማው በጠቅላላ
ህዝበ-አዳም ሁሉ
"ይሰቀል! ይሰቀል! "
እያሉ ይጮሀሉ።
አንቺንም አየሁሽ
ከተሰበሰበው ከሰፊው ህዝብ
መሀል ከ'ምብርቱ ላይ ቆመሽ
ሳንቃ ደረትሽን
ለፀሀይ አጋልጣሽ
መቃው አንገትሽን በረጅሙ
አስገሽ
በኮራው ውብ ዳሌሽ
ግራ ቀኝ ተጋፍተሽ
በሙዚቃው ድምፅሽ
አብረሽ ከነ'ሱ ጋር
"ይሰቀል! ይሰቀል!"
እያልሽ ትጮኺያለሽ።
መስረቅ ካስኮነነ
እሱን "ይሰቀል!" ካልሽ
የ'ኔን ነብሴን ልቤን ቀልቤን
ሁሉ ሰርቀሽ
እስኪ መልሺልኝ
አንቺን ማን ሰቀለሽ!?


(መንግስቱ መ.)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ዝሰንውብነት(ልዑል ሀይሌ)
.
ዝንብ!
አበባው በሞላው በውብ ፅዱ ቦታ
መች የልቡ ይደርሳል
የቆሻሻ ክምር ሆኖበት ትዝታ
.
በቆሻሻ ናፍቆት ዝንቡ ያንጎራጉራል
ከአደይ መሀል ቆሞ ገንዳውን ይጣራል
.
"ቆሻሻ ናፈቅሺኝ ቆሻሻ ናፈቅሺኝ
ለምን ነው ከአበባው የሄድሽው ጥለሺኝ?
.
ነይ ከቆሻሻው ላይ አንሺኝ ከአበባው
ትዝታሽ ገደለኝ ጠፋኝ ዙሪያ ገባው"
.
እያለ ሲተዝት ሲያንጎራጉርላት
የዝንቡ ትዝታ ንቧን ሳቅ ቢገላት
.
በንብነት መኖር
መች ዝንብን ያስመኛል?
ከአበባው ይልቅ
ከቆሻሻው ክምር ትልቅ ጣዕም ይገኛል
.
ከውብ ፅጌረዳ ጉርሻ እየቀሰሙ
ውብ ነገር እያዩ ውብ ድምፅ እየሰሙ
እንደ ንቧ መኖር ምኑ ያስደንቃል?
ማንም ሰነፍ ፍጥረት
በተመቸ መንገድ መራመዱን ያውቃል
.
ይልቅ እንደ ዝንቡ!
.
ከቆሻሻው ክምር ከተናቀው መንደር
የራስን ፈልጎ ራስ እንደማሳደር
.
ወደር የለሽ ደስታ ዝንብን እንደማከል
ሁሉም ከሸሸው ላይ የራስ ጎጆ መትከል
.
የታል የሚያስደስት?
.
ዝንብ ሆኖ እንደመብረር
ዝንብ ሆኖ እንደማረፍ
በሁሉም ተጠልተው
ሆድ እያጠገቡ የገዛ ነፍስ ማትረፍ
.
ምናል የሚያስደስት?
.
ጥላቻን ማግለልን ከልብ ሳያዘልቁ
ከፍጥረት ግርፋት
በቆሻሻ ክምር ራስ እየደበቁ
.
ዝንብ ሆኖ እንደመኖር
ዝንብ ሆኖ እንደማየት
ምን ጥንካሬ አለ?
በሁሉ ተገፍተው ዕድሜ እንደማቆየት

@getem_sourcebot

@Getem
@getem
@getem
👍1
አርብና አረብ ገንዳ!!!!!!!!!!!!!!


መገን አረብ ገንዳ፤
አርብ ረፋዱ ላይ፤
የቢላል ምልክት፤
አዛኑ ሲሰማ፤ ቁኽጥባው ሲዘረዘር፤
ጦሳም አሚን ይላል፤ እንኳንስ የአደም ዘር።


((( ጃ ኖ ))(

መልካም ጁምኣ!!!!!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
አዋጅ አዋጅ አዋጅ!!


በነገው እለት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የድጋፍ
ሰልፍ ለማድረግ ወደ መስቀል አደባባይ ለምትወጡ
የአዲስ አበባ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ ባዶ
እጃችሁን እንዳትወጡ ተብላችኋል።
በክረምት ወር በብርድና በቁር እየተመቱ የጎዳናን ህይወት
ለሚጋፈጡ ዜጎቻችን፤ የማትለብሷቸውን፤ ቁም
ሳጥኖቻችሁ ውስጥ ያለ አገልግሎት የተቀመጡ ልብሶችን
በአንድ እጃችሁ ይዛችሁ መውጣት እንዳትረሱ።
ድንገት በእለቱ ቲሸርት ከገዛችሁ ቅያሪውንም መለገስ በጎ
ተግባር ነው። የእለቱን መልዕክት የያዘ ቲሸርት መለገስ
ከፈለጋችሁም እሰየው። ብቻ ለወገኖቻችን መስቀል
አደባባይ ባዶ እጃችሁን እንዳትመጡ።
አስተባባሪዎቹን በእለቱ ለማገዝ በጎ ፍቃደኛ የሆናችሁ
በሚከተሉት ስልኮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን
እንገልጻለን።

@Balmbaras
@Lula_al_greeko
🇪🇹ዘር ሳይኖር ሀገር ነበር 🇪🇹

ይህ የኢትዮጲያ ቻናሎች ድምጽ ነው

🇪🇹ስለሰላም እና አንድነት ፤ ስለ ፍቅር እና መከባበር ፤ስለ መዋደድ እና መተባበር ባጠቃላይ ስለ ኢትዮጲያዊነት እሴት እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹የብሄር ልዩነት ዉበት እንጂ ለመከፋፋል ምክንያት እንዳልሆነ እንመሰክራለን፡፡

🇪🇹የሀይማኖት ልዩነት ለመተሳሰር እና ለመተሳሰብ ምክንያት እንጂ ለጠላት በር መክፈቻ አለመሆኑ እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹የአምላክ ቃል ኪዳን ያለበን ፤ ከ3000 ዓመት በላይ የራሳችን ታሪክ ያለን ፤ የአብሮ መኖር ተምሳሌት የሆነች ሀገር እንዳለን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹በአባቶቻችን ደም ተቀልሞ የተጻፈ ታሪክ ባለቤት ፤የመሰዋት ሀገር ባለቤት እንደሆንን እንመሰክራለን፡፡

🇪🇹የራሳችን ባህል ወግ እና ስረአት ባለቤት ፤የአክሱም ላሊበላ ፤የሶፍ ኡመር ፤የፋሲል የቴድሮስ ሀገር ፤አባጂፋር እና ከማንም በፊት የነበረው ታላቁ የገዳ ስረአታችን የኛ መገለጫ መሆኑን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹በሀገራችን የሰላም ጥሪ ፤ፍቅርና መተሳሰብ እያመጣ ላለው ታላቁ መሪያችን ክቡር ዶክተር ጠ/ሚንስተር አብይ አህመድ ጎን መቆማችንን እና በነገው እለት ባለው ሰልፍ ላይ አብሮነታችንን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹ይቺን የመሰዋእት ሀገር የመረከብ ሀላፊነት የኛ ነው፡፡ የአንድነት መሰረታችን መደመር ነው፡፡

🇪🇹ከምንም በፊት ኢትዮጲያ ፡፡ የኛ አንድነት ለጠላት የማይናድ ተራራ ነው፡፡

🇪🇹እነሆ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ ፤ኢትዮጲያዊ ነኝ የምትል ከሆነ የሀገርክን ድምጽ አድምጥ ፤ ስለ ሰላም ዘምር ፤የአምላክህን ጥሪ ስማ ፡፡

🇪🇹አብራችሁን በመቆም ኢትዮጲያ ሀገራችንን ለለዉጥ ጎዳና እንውሰዳት ፡፡ ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታዉን ይወጡ፡፡

🇪🇹አምላክ ኢትዮጲያን ይባርክ ፡፡🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
መልአክ!!!!!


ከተገኘ ባገር፤
የወንድሙን መንገድ፤
እየደለደለ ቀድሞ የሚያበጅ፤
እሱማ መልአክ ነው፤ ክንፍ የለውም እንጅ!!!!!!

(( ጃ ኖ ))

@Balmbaras
@getem
@getem
👍1
# ሠላሜ_ሠላሜ

ልዩ አመል ያመጣን
ከመስመር የወጣን
መሪ አንገት አዙሮ ፥ በዱላው ሚመታው
ሰለሜ ~ ሰለሜው ፥ አብቅቷል ጨዋታው።
:
ያውና ... ያውልሽ ...
እዪ ወዲያ ማዶ
ተመልከች አሻግረሽ፣
:
እንደ ጥማድ በሬ ፥ ሸክም ወስደው ድርሻ
ህዝብ እና ሹመኛው ፥ ገጥመዋል ትከሻ።
-------------------------//------------------------
( በርናባስ ከበደ )

[ # የጠቅላይ_ሚኒስትር_ዶክተር_አብይ_አህመድን_ማስተ
ዋል_የተሞላበት_አላማና_መንገድ_እደግፋለሁ ።]

@Getem_sourcebot
@getem
@getem
በእድገት ማማ ላይ ፍቅር ስትንተራስ
ቅንነት የረሳ አይጠፋም ቦንብ እራስ

ሮዚ የያቡ
@getem
@getem
የከፍታ ቅኔ!!!!!!!


እንደዋልያ እግሮች፤ ፀንቶልኝ ጉልበቴ፤
ይኸው ደግሞ ዛሬ፤
ቆንጥሩን ጉድባውን ዳገቱን ወጥቼ፤
በተራራው ጫፍ ላይ፤
ከፍ ብዬ ስሄድ፤
ቁልቁል ተሸቀንጥሮ፤ወደቀ ጠላቴ!!!"""
Ameeeeeennnn

((ጃኖ ))

@balmbaras
@getem
@getem
"ለፍቅር ብተኛት ለጠብ አረገዘች"
ሆነና ነገሩ
በነጭ እርግብ ፋንታ ቦምቡን ወረወሩ
የእፉኝት ልጅ ሁሉ ተስፋ ቢስ ደረመን
ገደልናቸዉ ቢልም አንጠፋም ደህና ነን
ከመኖርም በላይ ነገን የሚያሳየን
ባንድ የተገመደ ትልቅ ፍቅር አለን።

(ሰለሞን ሰሃለ)

@getem
@getem