ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እግሮቼን ያፀናል!!!!!!


ከዘመናት በፊት አለም ሳትፈጠር፤
ከናንተ ወገብ ላይ፤
እትብቴ እንዲሰራ፤
በሰማዩ ጌታ፤ ተፅፎልኝ ነበር።


እሰየው ተመስገን፤
ይኸው ደግሞ ዛሬ፤
አደራ ልጆቼን ፤
የሚለው ምህላችሁ፤
ያ ምርቃታችሁ፤መች ተለይኝና፤
በህይወት ባህር ፊት፤
የእናቴ ምርቃት፤
የአባቴ ቡራኬ፤ ሆኖኝ ለእግሬ ዳና፤
ተሻገር እያለኝ፤
እለፈው እያለ፤
እግሮቼን ያፀናል፤ ዛሬም እንደገና።

(( ጃ ኖ ))

የናንተ ቀን አንድ ቀን ብቻ አይደለም ዘላለም ነው!!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
# ግራ_የገባው_ቀኝ

ንጋት እስከሚሆን ከንጋት ጀምሮ
ዘራሰብ ሲፋጠን ሲጓዝ ወደ ድሮ፣
ባለው ነፃ ፈቃድ በተሰጠው ስልጣን
ለመልኣክ ተስሎ ገብሮ ለሰይጣን፣
ትላንት ያጣሁትን ነገ አገኘው ብሎ
ቀናትን ሲሻገር በድር ተንጠልጥሎ፤

ያረዘመው ተስፋው በመታገስ ቅባት
ከሆዱ አላልፍ ሲል እንዳንገት ክራባት፣
ለማቆየት ብቻ፣
ለማሠንበት ብቻ፣
ላም ያለች በሰማይ
ወተቷን ላታሳይ፣
አልፎ ሃጅ ዳመና ሰማዩን ሲዞረው
አካፍቶ ዞር ሊል ዘንቦ ላያሽረው፣

እረፍት የነፈጉት
ባይተዋር ያረጉት ምስጢራት ሲፈቱ
ደሞ ሌላ ትንግርት ሲደቀን እፊቱ፣
ግራ ዘፈን አዝማች
መርዶ እና ምስራች
በሁለት በኩል ጠምዶት
መሳቅ ማልቀስ ከብዶት፣

ህልሙ በቀን ሦስቴ ሲኮስስ ሲጎላ
ቅርፁን ሲለዋውጥ እንደ ጀምበር ጥላ፣
ከውሃ እና ከእሳት ጎዳናው ሲዋቀር
መኖርም መሞትም ሳይቻለው ሲቀር፣
ምስጋና እና ምሬት ከከንፈር ላይ ሸሹ
'ምንም አይልም' ሆነ ሰው ሁሉ ምላሹ።
----------------------//-----------------------
(ከ በርናባስ ከበደ )

@getem_sourcebot
@getem
@getem
📙ውድ የዚህ ቻነል ተከታዮች እንዴት ናችሁ? እንደሚታወቀው ቻነሎቻችን እስከዛሬ ድረስ በተቻላቸው መጠን የተመረጡ:
ግጥሞችን (@getem)እና
ወጎችን (@wegoch) ፣ሲያቀርቡላችሁ ቆይተዋል የህ እንዳለ ሆኖ በቀርብ ቀን ደሞ አድማሳቸውን ሰፋ አድርገው የተወደዱና የተመረጡ ግጥሞችን እና ወጎችን ከ ሚኪ pictures (@mykeypictures) ጋር በመተባበር በከፍተኛ ጥራት በፎቶ ይዘዉላችሁ ሊቀርቡ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

ከግጥም ብቻ እና ወግ ብቻ
(@lula_al_greeko)

Mykey ምስሎች
(@mykey21)
1
የወፍ ፆም(ልዑል ሀይሌ)
መሬት ጦም አደረ
ጦሜን እንዳላድር
ከሰማይ ልፈልግ
ጥሬ-ያለው ምድር
.
ሁዳዴም አላውቅም
የሰኔም አላውቅም
እናንተ ባትበሉ
ደጅ በትኑልኝ ጥሬ እንድለቅም
.
እኔ አልፆምም እንጂ...
ብበርም በሰማይ
ልነካ ብደርስም የፈጣሪን መንበር
እንደ ቅርበቴማ
ፆም ፀሎቴ ሁሉ በተሰማ ነበር
.
ዳሩ ምን ያደርጋል?
የጨበጡት ጋሻ ማፈሻ እየሆነ
ጦር እንደሚመክት
ለራቀ ይታያል ቅርብ ቆሞ እያለ

@getem_sourcebot
@getem
@getem
1
ወዳጄ ዛሬም እደግምልሃለሁ!!!!!!!
ይኸንን ሰውየ ካለማድነቅ ይልቅ አድንቆ መሣሣት
ሳይሻል አይቀርም!!!!

@Balmbaras
@getem
@getem
የኮልታፋ ግጥም(ልዑል ሀይሌ)
ፆም ስለሆነ እንጂ
የምላስ ወለምታ በቅቤ ይታሻል
አጥንት ስለሌለው
ቅቤውን ሲጠጣ እንዳዲስ ይሟሻል
.
እኔም አሸባሊ
ምሽቴም ሽብልተኛ ተካስሰን ተካስሰን
በሽብል ትዳል ውስጥ
የወለድነው ዓብይ ፍቅል ሰጥቶ ካሰን
11-10-10


@getem_sourcebot

@getem
@getem
1
በአንቻሮ ቅዳሜ!!!!!!


ምን ሊፈይድ ሰኞ፣
ምን ለያደርግ ማክሰኞ፣
እረ የምን እሮብ፣
የምንትስ ሀሙስ፣
ቀና ቀኑ ሁሉ፣ገለል በል ከፊቴ፣
ይገማሸርበት፣
የቀኑ ባለሟል፣የቀኑ ከበርቴ፣
ቅዳሜ ሸግየው፣ ቅዳሜ ፍትፍቴ።
የምትል ውብ ቅኔ፣
ትላንትና ወዲያ፣ ደግሞ ወዲያ ማታ፣
ድንገት ከሃድራው ላይ፣ሰተት ብላ ገብታ፣
ማክሰኞን ሞሸርናት፣በቅዳሜ ፋንታ።
ማክሰኞ ማለዳ፣
የተሸላለመው፣የቅኔ ማሰሮ፣
ይኸው ተከፈተ፣
በላይ ገንዳው ዘማች፣ ባንቻሮ ባንቻሮ።
ሃጃ ነበረብኝ፣
መውደድ ነበረብኝ፣የወንድም ሀቂቃ፣
እንኳን ለኔ ናፍቆት፣ላንቻሮ እሚበቃ።
ድረስልኝ ብሎኝ፣
ዝለቅልኝ ብሎኝ፣ሽሙንሙን ባልንጀር፣
ትላንት መልእክተኛ፣
ካንቻሮ ቀበሌ፣ ተልኮብኝ ነበር።
ወዳጅ በጠፋበት፣
ጓዱ በሸሸበት፣ በዚህ ድፍድፍ ዘመን፣
ጀነት መግባት አይደል፣
ና ድረስ ተብሎ፣በወንድም መለመን።
ናፍቄያለሁ ብሎ፣
ድረስልኝ ጓዴ፣ ድረስ ቶሎ ካለ፣
ከዚህ በላይ ህይወት፣መታመን የት አለ።
በጓደኛ ናፍቆት፣
በወንድም ወዳጃ፣
እሽ ማለት መስሎኝ፣የሚያወጣው ሃጃ።
ምን ገጠመው ጓዴን፣
ከቶ ምን አገኘው፣
ቶሎ ድረስ ያለኝ፣ ባንቻሮ በገዳም፣
ምን መንገድ ቢመቱ፣የወዳጅ አይጎዳም።
ብየ ሳላበቃ፣ብየ ሳልጨርሰው፣
ፋጦ አቀበቲቱ፣ በሃድራ እምትጨሰው፣
የባልንጀርና የወዳጅ ሃቂቃ፣
ፋጦ አቀበቲቱን፣ሲወጧት ነው በቃ።
እያለች ሸኘችኝ፣ አብሽር ገራሙ ሰው፣
ባልንጀር ነው ቀድሞ፣
የወዳጁን ፅዋ፣ቀድሞ የሚቀምሰው።
በሚል ዝይን ቅኔ፣ እየወረበችኝ፣
መገን ፋጦ ሙሄ፣ አንቻሮ ዶለችኝ።
ይኸው ከፍትፍቱ፣
ያው እረከቦቱ፣
እንደ ንጉስ ጉባይ፣
በባልንጀር ይሁን፣ መገን በወጭቱ፣
ባንተው ይሁን ብላ፣ዘለቀች ልጅቱ።
ከልጅቷ በቀኝ፣ የቆመው ባልንጀር፣
በኔ አሮ በእሷ አሮ፣ ተጀንኖ ነበር።
ሃድራው ተጋግሞ፣ ሲገለጥ ሀቂቃ፣
በዚያች በሸጋ ልጅ ፣ተፈረደ በቃ።
የታመመው ጓዴ ፣እንዲህ ተቸግሮ፣
ቀልቡ የወየበው፣ ልቡናው ተሳክሮ፣
በሌላም አይደለ፣ ባንች አሮ ባንች አሮ።
የተባለች ጊዜ፣ ልጅቱ ደንግጣ፣
እረ በሸሆቼ፣ በገታ በገታ፣
ይህን መሳይ ጎበዝ፣
እንደምን ይወዝወዝ፣እንደምን ይረታ፣
አሻ፣
ወዶ መናወዝን፣አላህም አይሻ፣
አንቻሮ ላይ ሞልቶ የፍቅር ወጌሻ።
እያለች ልጅቱ፣ ጀማው መሃል ገብታ፣
እያሰማመረች፣
ነፍሷን በምርቃን፣ ገላዋን በጉፍታ፣
ነይ ሳሚው ተብላ፣ ከንፈር ስትመታ፣
ባልንጀሬ ሻረ፣
ይሁን አሁን ብሎ፣ ጀምኣው ተፈታ።
እቴ መድሃኒቴ፣
የኔ ሸሙናይ፣
በቅዳሜ ሃድራ፣ባንቻሮ ሰማይ፣
ከንፈር እየበላሽ፣ብቅ አትይም ወይ።

((( ጃ ኖ ))(

@balmbaras
@getem
@getem
ምጽ!!!!!!


ከራሳችሁ ጓሮ ፤
አንድ እግር በርበሬ ፤ ሳታውቁት ዘርታችሁ ፤
እንግርግብ አድርጎ ፤ለብልቦ ፈጃችሁ ።

(( ጃ ኖ ))


ወዳጄ ዛሬም እደግምልሃለሁ!!!!!!!
ይኸንን ሰውየ ካለማድነቅ ይልቅ አድንቆ መሣሣት
ሳይሻል አይቀርም!!!!

@Balmbaras
@getem
@getem
★የሀሜተኞች የእምነት ቃል★

ድብቅ መልክ ስለን
ማንነትን ጥለን
ከራሳችን ሸሽተን
ከልባችን ጠፍተን
ንዋይ እና ደስታን እያፈላለግን
ለስንቱ እየቀረብን ከስንቱ እየራቅን
ታች ሸለቆ ወርደን ወሬ እያዋዛን
ጫፍ ተራራ ወጥተን ሀሜት እያባዛን
ምላስ የተባለ
በሁለት የተሳለ
ሰው ጨራሽ መሳሪያ
በሞላባት አለም
ያየን የለም እንጂ
ያላየነው የለም

ምንያህል ጥላሁን
ሰኔ 4/2010

@getem
@getem
@getem_sourcebot
ስነ-ልቡና

ከጎሽ አናት ቀንድ ነቅለን ወስደን ለበግ ብንገጥምላት
ታጌጥበት እንደሁ እንጂ ከተኩላ ጥርስ አያስጥላት
ባሩድ ቢምግ እንደ ሱረት ጥይት ቢዘግን እንደ ቆሎ
ፈሪም በትጥቅ አይጀግንም ክንብንቡን ወድያ ጥሎ
ነፍጥ አንግቦም ይማረካል ጠላት በእጁ ሲሞግተው
ሰው ልቡ ነው የሚያሸንፍ ሰው ልቡ ነው የሚሞተው።
***
በርናባስ ከበደ

@geteM
@getem
@lula_al_greeko
የከፍታ ቅኔ!!!!!!


ነገረኛው ሁሉ፤
ክንፉን ሰብሮ ሊያወርድ፤
የድንጋይ ውርጅብኝ፤ እየወረወረ፤
እሱም አልተመታ፤ ጠላት ጓጉቶ ቀረ፤
ሰውየው እንደሆን፤
እየዋለ እያደር፤
እንደ ንስር ሽቅብ፤ ከፍ ብሎ በረረ።

((( ጃ ኖ ))

@balmbaras
@getem
@getem
አንዳንድ ሰው

አንዳንድ ሰው አለ በጣም አስገራሚ
ላዩ ጤነኛ ነው ውስጡ ግን ታማሚ

አንዳንድ ሰው አለ ከልቡ አማራሪ
ግን ተመልሶ ከጥፍቱ ተማሪ

አንዳንድ ሰው አለ ከልቡ ወዳጅ
የራሱን ትቶ የሰው አሳዳጅ (ሃሃሃሃሃ)
:
አንዳንድ ሰው አለ ርቆ አሳቢ
ዛሬ ላይ ቆሞ ነገውን አንባቢ

አረ ብዙ አለ ይወራቢባል
አንዱን እየጣልን አንዱ ላይ ብንውል

ደሞ እረስቼ ፍቅር ነኝ ባዩን
እቴም ፍቅር እረ እኛን እዩን
ተፍቀርን ባዬች ለስሜት ኗሪዎች
ከዛ በዘለለ ድራማ ሰሪዎች

DaDa Coffee

@getem_sourcebot

@getem
@getem
@getem
ሰውዬው!!!!!!!!

በእንቶ ፈንቶ ወሬ፣
በአርቲ ቡርቲ፣ ጩኸት፣
በድሪቶ ድልቂያ፣
ይወድቃል መስሏቸው፣ሲገፉ ሲገፉ፣
ጭራሽ!!!!
ጎራውን የሚንድ፣
ገፍትሮ የሚጥል፣
ጥሶ የሚገባ፣ የቆላ ጅግሳ፣
ሰባብሮ የሚጥል፣ አርማጃው ጃውሳ።
ልቡ ሙልት ያለ፣
ውስጡ የታተመ፣
በድልና ስኬት፣ ካፍ እስከ ገደፉ፣
ይህንን ጃውሳ፣
የብረት ግድግዳ፣
የብረት ምሰሶ፣አርገውት አረፉ!!!!!!!

((( ጃ ኖ ))

@balmbaras
@getem
@getem

ወዳጄ ዛሬም እደግምልሃለሁ!!!!!!!
ይኸንን ሰውየ ካለማድነቅ ይልቅ አድንቆ መሣሣት
ሳይሻል አይቀርም!!!!
ዶ/ር ዐቢይ ለኢትዮጵያ የጻፈው ደብዳቤ

-/- ‹‹እኔ አንችን
ስወድሽ››
(©መላኩ አላምረው)

---›
ልክ እንደ ምኒልክ - እንደነ ጣይቱ፤
ለአንች ነፃነት - እንደሚቆጡቱ…
እንደ አፄ ካሌብ - ባሕር ተሻግሬ፤
እንደ አባባ ጃንሆይ - ክፉን ተናግሬ፤
እንደ አፄ ዮሐንስ - አንገቴን ሰጥቼ፤
ልክ እንደ መይሳው - ራሴን አጥፍቼ፤
እንደነ ገብርዬ - እንደ ጀግናው በላይ፤
ከአንች ክብር በቀር - የራሴን ቤት ላላይ፤
በፍጹም መታመን፤
በጽናት በመቆም - ከሕዝቦችሽ ጋራ፤
ወይ በአንድነት ልንኖር…
ወይም ላ‘ንች ክብር - ሞትን ልንጋራ፤
---›
እኔ አንችን ስወድሽ…
ቃሌን ያደመጠ - ተስፋየንም ያዬ፤
ሼሁ እየሰገደ - ቄሱ እየጸለዬ፤
በሕዝብ እንባና - በሕፃን ለቅሶ፤
የእናቶች ጸሎት - ወደ ጌታ ደርሶ፤
ጥበብ እንዲቸረኝ - የሰማዩ መሪ፤
እየተንበረከክሁ - ለአንችው ፈጣሪ፡፡
---›
እኔ አንችን ስወድሽ...
በሰላም አይደለም - ጸጥታ ባለበት፤
በተንኮል መሐል ነው - ሴራ በበዛበት፡፡
-›
በጥንቃቄ ነው - ያለመዘናጋት፤
በብዙ ሩጫ ነው - ሌት ተቀን በመትጋት፡፡
ክፉ ሚያሴሩብሽ - እንዳሉ ሰምቼ፤
እንቅልፍ እየነሳኝ - ረፍቴን አጥቼ፡፡
-›
ይኸው ጊዜው ከፍቶ - በእጅሽ የበላ፤
ከመሶብሽ ሰርቆ - ጓዳውን የሞላ፤
ማመስገኑ ቢቀር - በቃኝ ማለት ትቶ፤
ጅብ ሆኖ መጣብሽ…
መብላቱ ሲገርመን - ሊያስበላሽ አጫርቶ፡፡
---›
እኔ አንችን ስወድሽ…
የመበቃቀልን - የአጋንንት ሴራ፤
የጎጠኝነትን - የስንፍና ሥራ፤
የምቀኝነት - የተንኮልን ገመድ፤
የመጠፋፋትን - የዝቃጮች ወጥመድ፤
በፍቅር ረትቼ፤
ምህረትን ሰጥቼ፤
ሌባን አስመልሼ፤
ለተበዳይ ክሼ፤
ለተጣሉ እርቅን - ለሌቦች ይቅርታን፤
ለወጣቶች ተስፋን - ለአባቶች ጡረታን፤
ለእናቶች ሳቅን - ለሕፃናት ደስታን…
ለመስጠት ሌት ተቀን - እየለፋሁልሽ፤
በማይሻር ኪዳን - ሰርክ እየማልሁልሽ!!!
---›
እኔ አንችን ስወድሽ…
በበፍጹም እምነት ነው - ፍርሃት አስወግጄ፤
የተንኮል ተራራን - ከሕዝብሽ ጋር ንጄ፤
በአምላክሽ አምኜ - ተስፋሽን አጽንቼ፤
ከቻልሁ ልሞትልሽ - ልክ እንደ አባቶቼ!!!
---›
እንጅ እናታለም…
እንደ የቀን-ጅቦች - ፈጽሞ አልወድሽም፤
ከሕዝበብሽ ነጥዬ…
ከአካልሽ ከፍዬ - ጠላት አልሰጥሽም፡፡
-›
አካልሽን ነክሶ…
መንፈስሽን ረብሾ - ልብሽን ‘ሚያደማ፤

፦ETHIOPIAN
@getem_sourcebot

@getem
@getem
@lula_al_greeko
አ-ብ-ይ


አ= አንድ ላይ
ብ= ብንደመር
ይ = ይበጀናል! !!!

((( ጃ ኖ ))

@Balmbaras
@getem
@getem
🤩1
«ታውቂያለሽ አለሜ!»

(ይበልጣል ስዩም)
:
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ህይወት ፋርስ ቲያትር…
ሰው ይሉት ተዋናይ አለም ይሏት መድረክ፣
በእኔ ምስኪን መኖር
ተውኔቱ ሲሰራ ታሪኩ ሲተረክ!
የድማሜ አድማስ…
ከማሰብ ጉልላት አጀብ የተከለ፣
እኔ ይሉት ሰውነት…
ከመሆን እንዳይደርስ በሰው ተከለለ!
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ምልሽን ሳልጨርስ…
ቅንጣት ጅማሮዬን…
የአካሌን ሀቂቃ ላንቺ ሳልተነፍስ
ኢመንት እምነት የለሽ…
ጥራዝ ነጠቁ ሰው ተወዶ ከየሱስ
ተቀበል ይለኛል!
ጌታን ያህል ንጉስ!
መጠን የሌለውን ችሎ ላያሲዘኝ
እነደ ተራ ፍራንክ…
ተቀበል እያለ ለምነው የሚያዘኝ?
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ጆሮዬ እሰኪበጠስ
ሊሰጥ የወደደ ሊሰብክ የወደደ
ፍቅረኛው ብትደውል…
የቃል ኢየሱሱን…
እኔ ጋር ወርውሮ ሊቀበላት ሄደ!
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?

ድማሜን ይዤ …. ምልሽን ሳልጨርስ…
ድንፋታም ሰካራም…
ስሙ እሰኪጠፋበት አረቄ የጠጣ፣
መጠጣት እርኩሰት…
ከሰው አፍ ያውላል ሊል ከመንገድ ወጣ!
የቃላትን ድንበር….
በአፉ እየሻረ…
ጉልድፍ አንደበቱ እንዳንገረገረው
"መጠጥ ጣረ ሞት!
ነው ለሞት ሩብ ጉዳይ " ብሎ የተናገረው!
አፍንጫ ይሉት አካል አይቀበል የለ ማሽተት እያዛለኝ፣
በግትልትል ትንፋሽ …
ስካሩን አውሶኝ አጠጣ አትስከር ለምነው የሚለኝ?
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?

በግረም በሰው ልክ…
የኪሶቹን ደጃፍ በአየው አዝቅዝቄ
ከምክር በኋላ…
ጉሮሮው ሲደርቅ…
ይጎነጨው ዘንዳ ያኖረው አረቄ
ኮዳ ሙሉ አረቄ!
·
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?

ከኪሶቼ አድባር …
አውጥቼ ያልጣልኩት ህጌ ያደረኩት፣
ሺህ ጊዜ አንብቤ…
በእንባ ተጥለቀልቄ ከልቤ ያተምኩት…
ያ ያንቺ ደብዳቤ….
ሰው ሁን ከሚል መግቢያ…
ሀተታ እና መዝጋያው ሌላ ያልተፃፈበት፣
ሰው መሆን በቃላት…
ከዙፋኑ ወድቆ ትቢያ ያረፈበት!
እ…. አስታወስሽው…
የምኞቴ እግር…
ተለወጥ ባልሽው ልክ ዘውትር እየሮጠ፣
ላንቺ ሰው ለመሆን…
ራሱን ለመውለድ ዘመን ነው ያማጣ!
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ያ ያንቺ ደብዳቤ…
ሰው መሆኔን ንቆ ሰው እንድሆነ ያረዳ፣
የእኔን ምስኪንነት…
ሀቂቃ ያልሽውን ሀሰት ያልተረዳ!
መጣሁ ብሎ ልብሽ…
ሰርክ የሽሽት ዘፈን እያብሰለሰለ፣
የዜማሽ ተቃርኖ…
ያለመመጣት ግጥምሽ ደብዳቤው ላይ አለ!
ታውቂያለሽ አለሜ ምን እንደሚገርመኝ?
ምልሽን ሳልጨርስ…
ሰው ሁን ሚለው!
ሀረግ ሰው ሁን ሚለው ትዛዝ ልቤን እየናጠው፣
በአምላክ ከመፈጠር…
ድንበር ላይ አሽሽቶ ማነው የለወጠው!
ሰው ላንቺ ምንድነው?
·
ምልሽን ሳልጨርስ…
ትሆኚው አይደለም…
ታዪው እንኳን ባይንሽ ላፍታ ያልተመኘሽው፣
እርባን ሳትጥዪ…
ከክርፋታም ትቦ ከቆሻሻ ጋራ ለምን ያለሽው?
ሰው ነው ያልሽው ጎዳሽ….
ወይስ ጊዜ ሲሄድ ሰው መሆኑ ገባሽ?
አይገባንም እንጂ አንረዳም እንጂ ….
አማኝ ነው ያልሽው ሰው አለማመን ይዞ!
አትጠጡ የሚል በሱስ ተወዝውዞ!
በግዜር መሰራትን…
ተራ እምነት አድረጎ…
በሰውኛ ልኬት ሰውን እየሳለ፣
ከናዱት በኋላ…
ዘመን ማያንፀው ስንት መጉደል አለ!

@getem_sourcebot

@getem
@getem
@getem
likeን አየነው ከእግር እስከራሱ ፤
shareንም አየነው ከእግር እስከራሱ ፤
በጣም የሚመቸው ፥
ወደራስ ህሊና ሰክነው ሲመለሱ ።

((( ጃ ኖ ))

@Balambaras
@getem
@getem
የቱ ነኝ?(ልዑል ሀይሌ)

እኔ ያንቺ አፍቃሪ!..
ከፊደል ቂመኛ
የቀለም ተማሪ
ሰላሜን ያጣሁ ሰው
ሰላም አስከባሪ
.
ያንቺ በሽተኛ
የሃገር ሁሉ ዶክተር
ላንቺ እጄን የሰጠሁ
ለሃገር ዘብ የምቆም
ጀብደኛ ወታደር
.
ሁለት ጭምብል ያለኝ
ሲያሻኝ የምለብሰው
ሲያሻኝ የማወልቀው
ሲያሻኝ የማላላው
ሲያሻኝ የማጠብቀው
ሲገባም ሲወጣም
ለይቼ ማላውቀው
.
አንዳች እውነት አለ
አንዳች ሀሰት አለ
ባንቺና በሕይወት
አንቀልባ ላይ ያለ
ባንዳችሁ ጀርባ ላይ
ወጥቶ የታዘለ
.
የቱ ጀርባ እንደሆን
ለይቼ ማላውቀው
በአንዳች እውነት ነው
አንደኛውን ይዤ ሌላውን ምለቀው
.
የቱ ነው ትክክል?
የትኛው ነኝ እኔ?
የቱ ነው ጤናዬ
ወዴት ነው ህመሜ?
.
አላውቅም!
.
ግና አሁንም አለሁ!
አንቺን ተደግፌ ኑሮንም ሳልለቀው
'የቱ ነው ትክክል?'
'የትኛው ነኝ እኔ?'
ለሚለው ጥያቄ መልሱን እስከማውቀው?
.
የቱ ነኝ?!
13-10-10

@getem_sourcebot
@getem
@getem
2