ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የቀበሮ ፀሎት
(ታገል ሰይፉ)
------
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡

@getem_sourcebot

@getem
@getem
👍1
አዝራር እና ንጋት
(ተገጠመ በዳንኤል ስዩም)


ሸሚዝ እወዳለሁ
በተለይ በተለይ አንቺ ከለበሽው
በተለይ በተለይ
እኔም እንዳይጨንቀኝ
አንቺም እንዳይጨንቅሽ
አንድ ሁለቱን አዝራር ፣ ፈተሽ ከለቀቅሽው
ጠይም እወዳለሁ
በተለይ በተለይ ፣ አንቺ እንደጠየምሸው
............
ይህ በእንዲህ እነዳለ...
እነሆ በቀደም ፣ ሸሚዝ ለብሰሽልኝ
ሁለት አዝራር ከፍተሽ ፣ ስሬ ወድቀሽልኝ
በፍቅራችን መሐል
እኔም እንደዘበት
ሁለት አዝራር ብከፍት ፣ ውበትን ፍለጋ
ብርሐን ሞላው ፊቴን...
ጠይም ደረትሽ ላይ ፣ ሁለት ፀሐይ ነጋ ።

@getemsource

@getem
@getem
ምስክር ነበረኝ(ፈራጅ ዳኛ ባገኝ)

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ለጉዳቴ መጠን ፍትህ የሚከፍለኝ
ስለውነት የሚፈርድ ፈራጅ ዳኛ ባገኝ
ክሴንማ አስረጂ ምስክር ነበረኝ

አንደኛ ምስክር ትሁነኝ ጨረቃ
ደምቃ ምትታየው እኛ ስንስቅ ስቃ
ስንት ያወራንባት ስንት የመከርንባት
ላትከጂኝ ላልከዳሽ የተማማልንባት
.
አሁንማ ባየሽ ስትሄጂ ከፍቷታል
መሳቅ አቁማለች እንደኔው አርጓታል
በመቅረትሽ ዜና እንደኔው አዝናለች
ዳኛ ይገኝ እንጂ...ዳኛ ይገኝ እንጂ ትመሰክራለች

ሁለተኛ ደሞ ያቺን ካፌ አድርጊያት
በልጅነት ጊዜ ስንቱን ያየንባት
ገብትን ለመዝናናት ሳንቲም ስለሚያጥረን
ለሁለት የምንጠጣው አንድ ምሪንዳ አዘን
አነዛም ጊዜያት በፍቅር ተባርከው
ብንደፋው አያልቅም እንኳን ጠጥተነው
.
እናም ያቺም ካፌ ፍቅራችን አይታለች
እንደ ስኳር ጣፍጧት ቃላችን ሰምታለች
ዳኛ ይገኝ እንጂ...ዳኛ ይገኝ እንጂ ትመሰክራለች

ያቺን የውሃ ምንጭ የተራጨንባት
የፍቅራችን ጠበል የተጠመቅንባት
ይህንን አይታለች ሶስተኛ ትሁነን
ቀለበት ሰርተናል ዘንባባውን ቀጥፈን
ቃል ኪዳን ገብተናል ወፎቹን አድመን
.
እናማልሽ ውዴ ይህን ታስታውሳለች
ዳኛ ይገኝ እንጂ...ዳኛ ይገኝ እንጂ ትመሰክራለች

ዘርዝር ካልሽኝ ደሞ እንኪ በየተራ
ለሁለት ያጠገበን ያ ኩርማን አንጀራ
ጉንፋን ስለያዘኝ የተሳልሺው ሻማ
እንቅልፍ እንቢ ሲልሽ የማዜመው ዜማ
ያ ጥርጊያ ያ መንገድ ያ የዋርካ ዛፉ
አቦ አታስለፍልፊኝ ዳኛ በለለበት ትዝብት ነው ትርፉ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፡፡፡፡፡፡፡መኖር ደጉ(ዳዊት)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
“ሲጋራ አጨሳለሁ ላንች ስል ላንች ስል
ከጭሱ መካከል አገኝሽ ይመስል”
ብሎ ቢል አጫሹ…
እኔ ጠጬ ደግሞ…
“መጠጥ እጠጣለሁ ላንች ስል ላንች ስል
አልኮል እጋታለሁ ላንች ስል ላንች ስል
ሌሊት ሲያስመልሰኝ
ካንጀቴ አስወጥቼ እጥልሽ ይመስል”

geTami ........

@getem
@getem
@lula_al_greeko
እግሮቼን ያፀናል!!!!!!


ከዘመናት በፊት አለም ሳትፈጠር፤
ከናንተ ወገብ ላይ፤
እትብቴ እንዲሰራ፤
በሰማዩ ጌታ፤ ተፅፎልኝ ነበር።


እሰየው ተመስገን፤
ይኸው ደግሞ ዛሬ፤
አደራ ልጆቼን ፤
የሚለው ምህላችሁ፤
ያ ምርቃታችሁ፤መች ተለይኝና፤
በህይወት ባህር ፊት፤
የእናቴ ምርቃት፤
የአባቴ ቡራኬ፤ ሆኖኝ ለእግሬ ዳና፤
ተሻገር እያለኝ፤
እለፈው እያለ፤
እግሮቼን ያፀናል፤ ዛሬም እንደገና።

(( ጃ ኖ ))

የናንተ ቀን አንድ ቀን ብቻ አይደለም ዘላለም ነው!!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
# ግራ_የገባው_ቀኝ

ንጋት እስከሚሆን ከንጋት ጀምሮ
ዘራሰብ ሲፋጠን ሲጓዝ ወደ ድሮ፣
ባለው ነፃ ፈቃድ በተሰጠው ስልጣን
ለመልኣክ ተስሎ ገብሮ ለሰይጣን፣
ትላንት ያጣሁትን ነገ አገኘው ብሎ
ቀናትን ሲሻገር በድር ተንጠልጥሎ፤

ያረዘመው ተስፋው በመታገስ ቅባት
ከሆዱ አላልፍ ሲል እንዳንገት ክራባት፣
ለማቆየት ብቻ፣
ለማሠንበት ብቻ፣
ላም ያለች በሰማይ
ወተቷን ላታሳይ፣
አልፎ ሃጅ ዳመና ሰማዩን ሲዞረው
አካፍቶ ዞር ሊል ዘንቦ ላያሽረው፣

እረፍት የነፈጉት
ባይተዋር ያረጉት ምስጢራት ሲፈቱ
ደሞ ሌላ ትንግርት ሲደቀን እፊቱ፣
ግራ ዘፈን አዝማች
መርዶ እና ምስራች
በሁለት በኩል ጠምዶት
መሳቅ ማልቀስ ከብዶት፣

ህልሙ በቀን ሦስቴ ሲኮስስ ሲጎላ
ቅርፁን ሲለዋውጥ እንደ ጀምበር ጥላ፣
ከውሃ እና ከእሳት ጎዳናው ሲዋቀር
መኖርም መሞትም ሳይቻለው ሲቀር፣
ምስጋና እና ምሬት ከከንፈር ላይ ሸሹ
'ምንም አይልም' ሆነ ሰው ሁሉ ምላሹ።
----------------------//-----------------------
(ከ በርናባስ ከበደ )

@getem_sourcebot
@getem
@getem
📙ውድ የዚህ ቻነል ተከታዮች እንዴት ናችሁ? እንደሚታወቀው ቻነሎቻችን እስከዛሬ ድረስ በተቻላቸው መጠን የተመረጡ:
ግጥሞችን (@getem)እና
ወጎችን (@wegoch) ፣ሲያቀርቡላችሁ ቆይተዋል የህ እንዳለ ሆኖ በቀርብ ቀን ደሞ አድማሳቸውን ሰፋ አድርገው የተወደዱና የተመረጡ ግጥሞችን እና ወጎችን ከ ሚኪ pictures (@mykeypictures) ጋር በመተባበር በከፍተኛ ጥራት በፎቶ ይዘዉላችሁ ሊቀርቡ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

ከግጥም ብቻ እና ወግ ብቻ
(@lula_al_greeko)

Mykey ምስሎች
(@mykey21)
1
የወፍ ፆም(ልዑል ሀይሌ)
መሬት ጦም አደረ
ጦሜን እንዳላድር
ከሰማይ ልፈልግ
ጥሬ-ያለው ምድር
.
ሁዳዴም አላውቅም
የሰኔም አላውቅም
እናንተ ባትበሉ
ደጅ በትኑልኝ ጥሬ እንድለቅም
.
እኔ አልፆምም እንጂ...
ብበርም በሰማይ
ልነካ ብደርስም የፈጣሪን መንበር
እንደ ቅርበቴማ
ፆም ፀሎቴ ሁሉ በተሰማ ነበር
.
ዳሩ ምን ያደርጋል?
የጨበጡት ጋሻ ማፈሻ እየሆነ
ጦር እንደሚመክት
ለራቀ ይታያል ቅርብ ቆሞ እያለ

@getem_sourcebot
@getem
@getem
1
ወዳጄ ዛሬም እደግምልሃለሁ!!!!!!!
ይኸንን ሰውየ ካለማድነቅ ይልቅ አድንቆ መሣሣት
ሳይሻል አይቀርም!!!!

@Balmbaras
@getem
@getem
የኮልታፋ ግጥም(ልዑል ሀይሌ)
ፆም ስለሆነ እንጂ
የምላስ ወለምታ በቅቤ ይታሻል
አጥንት ስለሌለው
ቅቤውን ሲጠጣ እንዳዲስ ይሟሻል
.
እኔም አሸባሊ
ምሽቴም ሽብልተኛ ተካስሰን ተካስሰን
በሽብል ትዳል ውስጥ
የወለድነው ዓብይ ፍቅል ሰጥቶ ካሰን
11-10-10


@getem_sourcebot

@getem
@getem
1
በአንቻሮ ቅዳሜ!!!!!!


ምን ሊፈይድ ሰኞ፣
ምን ለያደርግ ማክሰኞ፣
እረ የምን እሮብ፣
የምንትስ ሀሙስ፣
ቀና ቀኑ ሁሉ፣ገለል በል ከፊቴ፣
ይገማሸርበት፣
የቀኑ ባለሟል፣የቀኑ ከበርቴ፣
ቅዳሜ ሸግየው፣ ቅዳሜ ፍትፍቴ።
የምትል ውብ ቅኔ፣
ትላንትና ወዲያ፣ ደግሞ ወዲያ ማታ፣
ድንገት ከሃድራው ላይ፣ሰተት ብላ ገብታ፣
ማክሰኞን ሞሸርናት፣በቅዳሜ ፋንታ።
ማክሰኞ ማለዳ፣
የተሸላለመው፣የቅኔ ማሰሮ፣
ይኸው ተከፈተ፣
በላይ ገንዳው ዘማች፣ ባንቻሮ ባንቻሮ።
ሃጃ ነበረብኝ፣
መውደድ ነበረብኝ፣የወንድም ሀቂቃ፣
እንኳን ለኔ ናፍቆት፣ላንቻሮ እሚበቃ።
ድረስልኝ ብሎኝ፣
ዝለቅልኝ ብሎኝ፣ሽሙንሙን ባልንጀር፣
ትላንት መልእክተኛ፣
ካንቻሮ ቀበሌ፣ ተልኮብኝ ነበር።
ወዳጅ በጠፋበት፣
ጓዱ በሸሸበት፣ በዚህ ድፍድፍ ዘመን፣
ጀነት መግባት አይደል፣
ና ድረስ ተብሎ፣በወንድም መለመን።
ናፍቄያለሁ ብሎ፣
ድረስልኝ ጓዴ፣ ድረስ ቶሎ ካለ፣
ከዚህ በላይ ህይወት፣መታመን የት አለ።
በጓደኛ ናፍቆት፣
በወንድም ወዳጃ፣
እሽ ማለት መስሎኝ፣የሚያወጣው ሃጃ።
ምን ገጠመው ጓዴን፣
ከቶ ምን አገኘው፣
ቶሎ ድረስ ያለኝ፣ ባንቻሮ በገዳም፣
ምን መንገድ ቢመቱ፣የወዳጅ አይጎዳም።
ብየ ሳላበቃ፣ብየ ሳልጨርሰው፣
ፋጦ አቀበቲቱ፣ በሃድራ እምትጨሰው፣
የባልንጀርና የወዳጅ ሃቂቃ፣
ፋጦ አቀበቲቱን፣ሲወጧት ነው በቃ።
እያለች ሸኘችኝ፣ አብሽር ገራሙ ሰው፣
ባልንጀር ነው ቀድሞ፣
የወዳጁን ፅዋ፣ቀድሞ የሚቀምሰው።
በሚል ዝይን ቅኔ፣ እየወረበችኝ፣
መገን ፋጦ ሙሄ፣ አንቻሮ ዶለችኝ።
ይኸው ከፍትፍቱ፣
ያው እረከቦቱ፣
እንደ ንጉስ ጉባይ፣
በባልንጀር ይሁን፣ መገን በወጭቱ፣
ባንተው ይሁን ብላ፣ዘለቀች ልጅቱ።
ከልጅቷ በቀኝ፣ የቆመው ባልንጀር፣
በኔ አሮ በእሷ አሮ፣ ተጀንኖ ነበር።
ሃድራው ተጋግሞ፣ ሲገለጥ ሀቂቃ፣
በዚያች በሸጋ ልጅ ፣ተፈረደ በቃ።
የታመመው ጓዴ ፣እንዲህ ተቸግሮ፣
ቀልቡ የወየበው፣ ልቡናው ተሳክሮ፣
በሌላም አይደለ፣ ባንች አሮ ባንች አሮ።
የተባለች ጊዜ፣ ልጅቱ ደንግጣ፣
እረ በሸሆቼ፣ በገታ በገታ፣
ይህን መሳይ ጎበዝ፣
እንደምን ይወዝወዝ፣እንደምን ይረታ፣
አሻ፣
ወዶ መናወዝን፣አላህም አይሻ፣
አንቻሮ ላይ ሞልቶ የፍቅር ወጌሻ።
እያለች ልጅቱ፣ ጀማው መሃል ገብታ፣
እያሰማመረች፣
ነፍሷን በምርቃን፣ ገላዋን በጉፍታ፣
ነይ ሳሚው ተብላ፣ ከንፈር ስትመታ፣
ባልንጀሬ ሻረ፣
ይሁን አሁን ብሎ፣ ጀምኣው ተፈታ።
እቴ መድሃኒቴ፣
የኔ ሸሙናይ፣
በቅዳሜ ሃድራ፣ባንቻሮ ሰማይ፣
ከንፈር እየበላሽ፣ብቅ አትይም ወይ።

((( ጃ ኖ ))(

@balmbaras
@getem
@getem
ምጽ!!!!!!


ከራሳችሁ ጓሮ ፤
አንድ እግር በርበሬ ፤ ሳታውቁት ዘርታችሁ ፤
እንግርግብ አድርጎ ፤ለብልቦ ፈጃችሁ ።

(( ጃ ኖ ))


ወዳጄ ዛሬም እደግምልሃለሁ!!!!!!!
ይኸንን ሰውየ ካለማድነቅ ይልቅ አድንቆ መሣሣት
ሳይሻል አይቀርም!!!!

@Balmbaras
@getem
@getem
★የሀሜተኞች የእምነት ቃል★

ድብቅ መልክ ስለን
ማንነትን ጥለን
ከራሳችን ሸሽተን
ከልባችን ጠፍተን
ንዋይ እና ደስታን እያፈላለግን
ለስንቱ እየቀረብን ከስንቱ እየራቅን
ታች ሸለቆ ወርደን ወሬ እያዋዛን
ጫፍ ተራራ ወጥተን ሀሜት እያባዛን
ምላስ የተባለ
በሁለት የተሳለ
ሰው ጨራሽ መሳሪያ
በሞላባት አለም
ያየን የለም እንጂ
ያላየነው የለም

ምንያህል ጥላሁን
ሰኔ 4/2010

@getem
@getem
@getem_sourcebot
ስነ-ልቡና

ከጎሽ አናት ቀንድ ነቅለን ወስደን ለበግ ብንገጥምላት
ታጌጥበት እንደሁ እንጂ ከተኩላ ጥርስ አያስጥላት
ባሩድ ቢምግ እንደ ሱረት ጥይት ቢዘግን እንደ ቆሎ
ፈሪም በትጥቅ አይጀግንም ክንብንቡን ወድያ ጥሎ
ነፍጥ አንግቦም ይማረካል ጠላት በእጁ ሲሞግተው
ሰው ልቡ ነው የሚያሸንፍ ሰው ልቡ ነው የሚሞተው።
***
በርናባስ ከበደ

@geteM
@getem
@lula_al_greeko
የከፍታ ቅኔ!!!!!!


ነገረኛው ሁሉ፤
ክንፉን ሰብሮ ሊያወርድ፤
የድንጋይ ውርጅብኝ፤ እየወረወረ፤
እሱም አልተመታ፤ ጠላት ጓጉቶ ቀረ፤
ሰውየው እንደሆን፤
እየዋለ እያደር፤
እንደ ንስር ሽቅብ፤ ከፍ ብሎ በረረ።

((( ጃ ኖ ))

@balmbaras
@getem
@getem
አንዳንድ ሰው

አንዳንድ ሰው አለ በጣም አስገራሚ
ላዩ ጤነኛ ነው ውስጡ ግን ታማሚ

አንዳንድ ሰው አለ ከልቡ አማራሪ
ግን ተመልሶ ከጥፍቱ ተማሪ

አንዳንድ ሰው አለ ከልቡ ወዳጅ
የራሱን ትቶ የሰው አሳዳጅ (ሃሃሃሃሃ)
:
አንዳንድ ሰው አለ ርቆ አሳቢ
ዛሬ ላይ ቆሞ ነገውን አንባቢ

አረ ብዙ አለ ይወራቢባል
አንዱን እየጣልን አንዱ ላይ ብንውል

ደሞ እረስቼ ፍቅር ነኝ ባዩን
እቴም ፍቅር እረ እኛን እዩን
ተፍቀርን ባዬች ለስሜት ኗሪዎች
ከዛ በዘለለ ድራማ ሰሪዎች

DaDa Coffee

@getem_sourcebot

@getem
@getem
@getem
ሰውዬው!!!!!!!!

በእንቶ ፈንቶ ወሬ፣
በአርቲ ቡርቲ፣ ጩኸት፣
በድሪቶ ድልቂያ፣
ይወድቃል መስሏቸው፣ሲገፉ ሲገፉ፣
ጭራሽ!!!!
ጎራውን የሚንድ፣
ገፍትሮ የሚጥል፣
ጥሶ የሚገባ፣ የቆላ ጅግሳ፣
ሰባብሮ የሚጥል፣ አርማጃው ጃውሳ።
ልቡ ሙልት ያለ፣
ውስጡ የታተመ፣
በድልና ስኬት፣ ካፍ እስከ ገደፉ፣
ይህንን ጃውሳ፣
የብረት ግድግዳ፣
የብረት ምሰሶ፣አርገውት አረፉ!!!!!!!

((( ጃ ኖ ))

@balmbaras
@getem
@getem

ወዳጄ ዛሬም እደግምልሃለሁ!!!!!!!
ይኸንን ሰውየ ካለማድነቅ ይልቅ አድንቆ መሣሣት
ሳይሻል አይቀርም!!!!