ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
*አንቺን ላለማሰብ*
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)

አንቺን ላለማሰብ እኔማ በኔ ቤት፣
ከውስጤ አውጥቼ አብዝቼ ለመርሳት፣

ሲጋራውን ለኮስኩ ጢሱ እንዲጋርደኝ፣
ምስልሽን ከዓይኔ ወዲያ እንዲወስድልኝ፣

ደግሜ ደግሜ ልረሳሽ ባጤሰው፣
ከንፈርሽ ናፈቀኝ ከንፈሬን ሲነካው፣

እሱን ወዲያ ትቼ መጠጡንም ብጋት፣
አንቺን ላለማሰብ አንቺኑ ለመርሳት፣

እያንገዳገደ ደጅሽ ይወስደኛል፣
ልረሳሽ ስደክም ትዝታሽ በልጦኛል፣

ፀሀይንም ሳያት አስታውስሻለሁ፣
ትዝ ይልሽ እንደሆን ውበቷን ካንቺ ጋር አመሳስያለሁ፣

ጨረቃንም ሳያት እነኚያ ምሽቶች ይከሰቱብኛል፣
ከባዶነት ነጥቀው ካለፈው ምናኔ ወስደው ይከቱኛል፣
አንቺን ላለማሰብ ለኔ አንቺኑ ማሰብ እጅግ ይቀለኛል፣

ያላረኩት የለም ከውስጤ ላወጣሽ፣
ግና፣
ልረሳሽ ያልኩለት የባሰ ወደድኩሽ፣

አንቺን ለመርሳት ስል አንቺን እያለምኩኝ፣
ትዝታን ለመቅበር ብዙ ብዙ ጣርኩኝ፣

የሄድንበት መንድ እኔና አንቺ አብረን፣
ያወራኛል ደርሶ ይጠይቃል አንቺን፣

ከፀሀዯ ንዳድ የተከለልንበት፣
ያ የሾላ ዛፍም አነሳሽ በድንገት፣

አንቺን ላለማሰብ ማሰብ ባላቆምም፣
ትዝታሽ አስሮኛል የትም አላመልጥም፣

ብራመድ ጎዳናው፣
ብቀመጥም ጥላው፣

ማለዳ ንጋቱ፣
ድጋሜም ምሽቱ፣
ያንቺ ወዳጅ ናቸው አንቺን ሚተርቱ፣

ይገርምሻል ውዴ እኔኮ እንዲ ነኝ፣
አንቺን ላለማሰብ አንቺን እያሰብኩኝ፣
ለመርሳት ፈልጌ ሁሌ እያስታወስኩኝ፣
ትዝታን አግብቼ የተሰቃየሁኝ፣

እኔኮ እንዲ ነኝ፣
አንቺን ካለማሰብ መሞት የሚቀለኝ፣
ምንድነው ግን ቅኔው ፍቺና ንገሪኝ፣
አንቺን ለመርሳት ስል አንቺን ሚያሳስበኝ፣

ለሄድሽው መውደዴ

ናፍቀሽኛል

ሚያዚያ 24/08/10 ረቡዕ ማለዳ 12:40...



@getem
@getem
@yeneta
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (☺️ልዑል☺️)
🙏እንኳን ለ1439ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ።

ኢድ ሙባረክ ለ ሙስሊም ኢትዮጵያኖች ።
💚💛❤️
💚ግጥም ብቻ💚
💛 ስዕል ብቻ 💛
❤️ ወግ ብቻ ❤️
💚💛❤️
@getem @seiloch @wegoch

@Lula_al_greeko
👏የካፊያ ምች👏
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተፈሪ ዓለሙ(1974)

ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ
ካላጣችው ሰዓት ከቤት አስወጣችኝ
ጥርቅም እቅፍ አድርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የእድሜ ልክ ልክፍቱን ያኔ አስለከፈችኝ

መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የእኔ ልብ በሷ የሷ በእኔ ጠፋ
የሰማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን
ውሃ ጠማኝ ውሃ እዘነበብን

ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ
በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ
እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ
የዘመን ህመሜን ያን እለት ታመምኩኝ
አሁን አሁን ታዲያ!

ደመናው ሲጠቁር ነጎድጓድ ሲያጓራ
ነፋስ ሲያጉረመርም ክረምቱን ሲጠራ
ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ
ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ

..........................ምች ተሳልሜ



@getem
@getem
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ካልፈለግሽ_ክብርሽን
:
:
ሰማዩ ዳምኖ ብርድ ብርድ ሲለኝ
መተሽ አሟሙቂኝ ያላንቺስ ማን አለኝ።
:
:
ፀሀይ ከሆነ ግን ካጠገቤ አትምጪ
ግዬ ገማግልሽ እዚያው ተቀመጪ።
:
:
ለምን ብለሽ ካልሺኝ ትንሽ ከጋልኩኝ
እራሴን ማሸነፍ ስለሚያቅተኝ
እኔን ብለሽ መተሽ አጉል ከምቶኚ
ያልጠበቅሺው ገጥሞሽ በኔ ከምታዝኚ
ፀሀይ የሆነ ቀን ቅሪብኝ ባክሽን
እምቢ ካልሽ ደሞ
ነይ ምነ ችግር አለው ካልፈለግሽ ክብርሽን።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu


@getem
@getem
🌿🌾🌙💫🌟💫💐
አዬ ከራማው ሠፊ ነው
ሀድራው የበዛ ነው
ምን ይነገር ለሱ
ራህመቱ ብዙ
የፍቅርን ስብሐት
ካአንድነት ጋር አብሮ ክልኤቱ ብሎ
በፈሪሀ ሰበዝ ልዩ ወ ውበቱ
ያኖረን ባንድላይ ሠናይ ሠብ ብሎ ።

......ጎፍታኮ ዋቀዮ....
....አጃይብ ያረቢ.....
ማድመቅህን አብዛው:ውበት ጨምርልን
በፈሪሀ ብዛት ብርሃን አብዛልን
ሐድራችን ይሙላልን
ሐሴት እንድናረግ: ጨለማ እንዲጠፋ
ፍቅርን አሰልሰው አስርግ እንዳይወጣ
በረካህ ይበርክት በምድራችን ይሙላ
አሜን ይሁንልን ከራማችን ይሙላ።️

@ቤሊና (07/10/2018 ዓ.ም)

🌟💫ኢድ ሙባረክ🌟


@getem_sourcebot
@getem
@getem
#የፍቅር ጥግ#

ሳቅሽ ፅጌረዳ፥ያልተቀነጠበ
አይንሽ ላይ ያሸተ፥ጥርስሽ ላይ ያበበ
አፍሽ የወይን ዛፍ
ከማር የማይነጥፍ
ሽንጥሽ የወርቅ አልጋ፥አመለ ወላንሳ
ጎዝጉዘዉ ቢተኙ፥አጋም የሚያስረሳ።

ቀረሮ ደረቴ፥ አልታደለምና ከቶ ላንቺ ገላ
ዘብ አደርሽ ሆንኩኝ፥እንዳይገባ ሌላ።



ማፍቀር ማለት መቅናት ማለት ነዉ።የፍቅር ጥጉም ቅናት ነዉ። ፍቅር በቅናት ይገለፃል:ነገር ግን ቅናት ሁሉ ፍቅር አይደለም።


(የዋርካ ስር ነፍሶች)

@getem_sourcebot
@getem
@getem
1
ውሻ ነኝ
=== ==
የጉዞየ ምዕራፍ የህይወቴ ቃና
በፍቅርሽ ማዕበል መንፈሤ የፀና፣
..
ካወኩሽ ጀምሮ ከጥንት እሥከ ዛሬ
ላንች የሠሠትኩት የለም ነበር ፍቅሬ።
..
ያኔ ሙሉ ነበርኩ እጄ ያለጠረ
ልቤም ደሥተኛ ነው በፍቅር የከበረ።
..
የምትፈልጊውን ሁሉን የማሣካ
ባንች ደሥታ ብቻ ውሥጤ የሚረካ።
..
እሡ ነበር ለኔ የደሥታየ ጣራ
የኔን ሥም ረሥተውት ባንች ሥም ሥጠራ።
..
እንዲህ ትይኝ ነበር...
" ከሠማይ የራቀ ከውቅያኖሥ የሠፋ
ላንተ ፍቅር አለኝ ፍፁም የማይጠፋ።
አጣህ ነጣህ ብየ አልወጣም ካንተ እቅፍ ቃሌን ባላከብር
ምላሤ ይታጠፍ። "
በሚጥም ልሣንሽ ብለሽኝ ነበረ
ይሄው ጊዜ ሺሮት ቃልሽ ተሠበረ።
..
የኔ ንብረት አልቆ ፍቅሬ ግን በርትቶ
ያንች ፍቅር ሢያረጅ ገንዘብሽ በርክቶ፣
..
ያጣ መናጢ ነው ብለሽ ተጠየፍሽኝ
ወዳላቸው ሥትሄጅ እኔን ግን ሸሸሺኝ።
..
አንች ብትሸሺኝም አልቀነሠም ፍቅሬ
እንደ ሎሌሺ ሁኝ ሥከትል አብሬ፣
..
አንችን ተከትየ በሆንኩሽ ጠበቃ
" ውሻ ነህ እንዴ አንተ ? አትከተል በቃ! "
ብለሽ አኮራሽኝ ቆረጥሽልኝ ጥሜን
ዳግም እንዳያመኝ ፈወሥሽው ህመሜን።
..
ውለታየን ክደሽ ፍቅሬን ብትንቂ
ሠድበሽ አሥደሠትሽኝ ሚሥጥሩን ሣታውቂ።
..
ለሁሉም ንገሪ ሣትደብቂያቸው
አንችን የምከተል ውሻ ነው በያቸው።
..
አንዴ ከወደደ መልሶ እማይከዳ
ጥላቱን ነው እንጅ ወዳጅ እማይጎዳ፣
..
ቃሌን የምጠብቅ ለጌታየ ታማኝ
አንችኮ "ተኩላ" ነሽ እኔ ግን " ውሻ " ነኝ። ...............
.........አወ እኔ ውሻ ነኝ
በይ የኔን ውሻነት ላገር አሣውቂ
ያንችን ተኩላነት ግን እንዳትደብቂ።
....
ማንም በሌለበት በባህር ዳርቻ
ሥንዝናና ነበር እኔና አንች ብቻ፣
..
ጨለማው ተተካ ቀኑ ተቀየረ
ተኩላው አብሮ ሢሄድ ውሻው ብቻ ቀረ።
....................አወ እኔ ውሻ ነኝ።።።

ከገጣሚ ናትናኤል የተወሰደ ፡፡ ለቃሌ ታማኝ ነኝ
~~~~~~~~~

ምንም ብንለያይ አደራ አትርሳኝ
ብለሽ መዳፍሽን በጄ ያስመታሽኝ
በስምሽ ያስማልሽኝ
የገባሁልሽ ቃል እንዳልፈረሰ ነው
ቃል አባይ አይድለሁ እስካሁን ህያው ነው

በትዝታ ቅኝት በሰመመን ዜማ
ክረምት'ና በጋ ቀን ወይም ጨለማ
ሳንካ ሳይሆንብኝ መፈራረቃቸው
ወቅት…
ቦታ…
ጊዜ…
አንዳች ሳያግደኝ …
በክፉም በደጉ አስታውስሻለው

ጨረቃ ስትወጣ ጨረቃን እያየሁ
በሰማይ ሰሌዳ በክዋክብት ብዛት አንቺኑ ስላለሁ
አስታውስሻለሁ

ሆዴም ሆዱን ብሶት የተከፋሁ ግዜ
ብቸኝነት ወርሶኝ ሰፍሮብኝ ትካዜ
በሬን ዘጋግቼ ብቻዬን ቤቴ ውስጥ
በሀሳብ ድር ትብታብ ቆዝሜ ስቀመጥ
ደግሞ ውል ብሎኝ በሬ እንዲቆረቆር
ጉዳዬ ነው የሚል ስለኔ መቸገር
ሰው ያስፈለገኝ 'ለት . . .


ሌላከየትመቶ
BYNati

@getem
@getem
አንቺ ካለሽልኝ
( እሱባለው ኢትዮጵያዊ)
አንቺ ካለሽልኝ
*
*
*
ሁሉም ይኖረኛል።
የጠየኩት ሁሉ፤ ይመለስልኛል
አለቆቹ ሁሉ፤ ይታዘዙልኛል።
*
*
አንቺ ካለሽልኝ
ሁሉም ይኖረኛል
*
*
ቤታችን በደስታ ፤በሃሴት ይሞላል
ሁሉ ያሸበርቃል
ግቢያችን በፍቅር ፤ ሳይበላ ይጥግባል
አንቺ ካለሽልኝ
ሁሉም ይኖረኛል።
********
ሁሌም ኑሪልኝ
ሰኔ ፰ ፪ሺህ፲
( እሱባለው ኢትዮጵያዊ)
@getemsource


@getem
@getem
እንዴት ያለው ንጉስ ነው!!
ጊዜን የቀደመ ጊዜን የበለጠ
ክብሩን አሳንሶ መሪ የጨበጠ፡፡

Eዙ
እድለኞች ነን!!!

@getem
@getem
#ናፍቆት

//ኑረዲን ዒሣ//


ስጋዬን ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት
ቆዳዬን ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት
እፎይ አስታገስኩት
ፀጥ ረጭ አረኩት።

የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ
ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ
ምንም አላረኩት
ምንም አላከኩት
ላልችል ችየ ቻልኩት።

አልፎክተው ነገር፣ ቆዳዬን መንቅሬ
አላኝከው ነገር፣ ስጋዬን ሰርስሬ
ይኸው እስከዛሬ፣
አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ(ህ) ፍቅሬ።

ያበደች የተረጋጋች ቅዳሜ
@lula_al_greeko

@getem ..
@getem
@getemsource
Forwarded from SPACE COMPUTER
" አለንጋ" የግጥም መድብል
ነገ ሰኔ 10/2010 ይመረቃል።

በገጣሚና ደራሲ ትዘዘው ክንዴ
"አለንጋ" የግጥም ስብስቦች

በዕለቱ ገጣሚያን ስራቸውንና የተመረጡ ከመፅሀፉ የተወሰዱ ግጥሞችን ያቀርባሉ።


ነገ እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሄራዊ ቤተመፅሀፍት እና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ የጥበብ ሰዎች በተገኙበት ይመረቃል።

እናንተም ተጋብዛችዋል
መግብያ በነፃ

@lula_al_greeko

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
አንተ የሌለህ እለት

ሰማይ ይታረሳል
ምድር ይታመሳል
መልካም እውነት ወርዶ
ሀሠት ይፀነሳል።

አንተ የሌለህ እለት
ጨረቃ አዘቅዝቃ
ወይ ምድር ትላለች
ፀሀይ ሰማይ ጠፍታ
ምድር ትቆማለች።

አንተ የሌለህ እለት
ውቅያኖሶች ሸሽተው
ምድርን ይከድናሉ
ነፍሳቱ ነጉደው
ምድርን ይመታሉ።

አንተ እዚህ ከሌለህ
ጉልበት ይለምሻል
ፍቅር ይቆሽሻል
ልቦች ይደማሉ
ሰዎች ይከዳሉ
መሞት ይመኛሉ።

ስለዚ አንተ ሰላም
አንተ የመኖር ተስፍ
ከኛ እርቀህ አትሂድ
ከኛ ዘንድ አትጥፍ።🙏🙏

........ ((ሊዱ))

@getem_sourcebot
@getem
@getem
ጨ ረ ቃ ....(ከ ጌታየ )

ጨረቃ...
አንዛብ በፈተለ
ቁር ባዘለ ንጋት፣

ባዲስ ሂወት ተስፋ
በፈገግታ ውህደት፣

ወይንም!
በነፍስ እልፊያ
በእስትንፋስ ጥምርት፡፡

ጎህ ሳይቀድ ፈንጥቆ
በተራራ ቁንጮ እንደሚወጣ አደይ፣

በውድቅቱ ሌሊት
በሰማይ አድማስ ላይ፣
.........ፈንድቀሽ ስትታይ፣

በክዋከብት ዓለም
በንግሰት ዘመንሽ፣

ቀና ብሎ ለሚያይ
አይቶ ለሚያደንቅሽ፣

በግዛትሽ ዙፋን
በደስታ ሰክረሻል፣

ላስተዋለሽ ደግሞ
በውብ ሳቅሽ መሀል
ሀዘን ሰንቀሻል፣

አንቺ ውብ ጨረቃ...
"
"
ስለ አንዳች ኩርፊያሽ
እንደ ማለዳ ጉም
ፍካትሽ ተነነ፣

የተከዘው ልብሽ
ሳቅሽን ተወነ፣

ይህ...ስለምን ሆነ?

ከዋከብት አዘኑ....!
"
"
ከዋከብት አዘኑ፣
ከ'ግርሽ ስር ተደፍተው
ማቅ ለብሰው ለመኑ፣

ቁጥር ፈታ በሚል
በጎለሰው ፊትሽ
ደመናው ተጨንቋል፣

ባይኖቹ ኮረጆ
እንባውን ሰንቋል፣

ነፋስ ተቆጥቶ
እሳትን አስንቋል፡፡

እናም...
በዚች የምጥ ሌሊት
ከሰማይ ሰማይ ላታርጊ፣

በአርያምሽ ፀንተሽ
ለዘላለም ላትመስጊ፣

የፍንደቃ እንቁ ሳቅሽን
በዕንባሽ ግምጃ ስትሸሽጊ፣

አንቺ ውብ ጨረቃ፣

ላላወቁሽ የፍንደቃ፣
.......የቡረቃ፣

ልብ ላሉሽ ደግሞ.....
የዕንባ ዶፍ የሳግ ሲቃ፣

እናም..........በቃ!
በዚች ከንቱ አለም፣

ሞትሽን የሚሞት
ቤዛ ሚሆን የለም፣

የዙፋንሽ አቻ
ባልንጀራሽ ፀሃይ፣

የዕንባሽን ትንፋገን
የውስጥሽን ስቃይ፣
...እንፋሎትሽን ሳታይ፣

ከተራሮች ጀርባ
እግሯን ዘርግታለች፣
ከሞቀው ዕልፍኟ
ሰላም ትሰብካለች፣



__////____________
february 13/2010
.....☞[Getaye.T]


@getem_sourcebot

@getem
@getem
ያልወደደ አበደ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
በሰው የደረሰ...
በኔ ላይ እንዳይደርስ ፣ ስፈራና ስቸር
ወድጄሽ እንዳላብድ ፣ ስጠነቀቅ ነበር፡፡
ታድያ ምን ያደርጋል
በከንቱ ፍርሃት ፣ ባክኖ መጠንቀቄ
ዋናው እብደት ነበር ፣ ከመውደድ መራቄ፡፡

@getem_sourcebot

@getem
@getem
አለቀ! !!!!


በሮቹ ልግመኛ፤ ገበሬው ደንቆሮ ፤
አይናገርም ወይ፤ ዘር አለቀ ብሎ! !!!!!!!!
በየበራበሩ ፤
ዘር እየበተነ ፤
ና ግባ ና ውጣ ሲል እየሰማሁት ፤
ሸረኛው ገበሬ ፤
የጠመደበትን ስፍራውን አጣሁት ።
ይህን ቆፍጣና ልጅ ፤
ደንዳናውን መሬት ፤
እያለሰለሰ በመላ በዘዴ ፤
አዲሱን ገበሬ ፤
ዘር ዘር አርገህ ዝራ ፤
ብሎ ማደናገር ሼም አይደለም እንዴ? ??

(( ጃ ኖ )))

@balmbaras
@getem
@getem
"ሞሪንጋ! !!!!


የፈረንጅ ሞሪንጋ ፤
ስንት አይነት በሽታ ሰርክ እየፈወሰ ፤
የኛ ሃገር ሺፈራው ፤
በየበራበሩ ብዙ ሰው ጨረሰ ።

(( ጃ ኖ ))

@balmbaras
@getem
@getem
የቀበሮ ፀሎት
(ታገል ሰይፉ)
------
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡

@getem_sourcebot

@getem
@getem
👍1
አዝራር እና ንጋት
(ተገጠመ በዳንኤል ስዩም)


ሸሚዝ እወዳለሁ
በተለይ በተለይ አንቺ ከለበሽው
በተለይ በተለይ
እኔም እንዳይጨንቀኝ
አንቺም እንዳይጨንቅሽ
አንድ ሁለቱን አዝራር ፣ ፈተሽ ከለቀቅሽው
ጠይም እወዳለሁ
በተለይ በተለይ ፣ አንቺ እንደጠየምሸው
............
ይህ በእንዲህ እነዳለ...
እነሆ በቀደም ፣ ሸሚዝ ለብሰሽልኝ
ሁለት አዝራር ከፍተሽ ፣ ስሬ ወድቀሽልኝ
በፍቅራችን መሐል
እኔም እንደዘበት
ሁለት አዝራር ብከፍት ፣ ውበትን ፍለጋ
ብርሐን ሞላው ፊቴን...
ጠይም ደረትሽ ላይ ፣ ሁለት ፀሐይ ነጋ ።

@getemsource

@getem
@getem