ግጥም ብቻ 📘
64.2K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
(በላይ በቀለ ወያ)


ሎተሪ ሻጭ እኔ...
እድል እድል እያልሁ ፣ እድሌ ቢያመልጥም
በጄ ያለን እድል
በማግኘት ምኞት ውስጥ ፣ ላለ ሰው ብሸጥም
እንደ ቆራጭ ልቦች
ተስፋ እየገመድኩኝ ፣ እድሌን አልቆርጥም፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሎተሪ ነሽ አንቺ...
ከልብ ለቆረጠሽ ፣ ተስፋ ለሰነቀ
አገኛለሁ ብሎ
እድል ለሚሞክር ፣ እድል እየፋቀ፡፡
።።።
@getem_sourcebot


@getem
@getem
@lula_al_greeko
🌈🌈ውድ ሀበሾች🌈🌈

ሰላም ናት ሀገሬ፡
ፍቅር ናት ሀገሬ፡
ልማት ናት ሀገሬ፡
ጥጋብ ናት ሀነሬ፡
በኢቢሲ ወሬ፡፡

❤️❤️አሌክስ አብርሃም❤️❤️

@getem
@beckyalexander
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
'ከሽፍታ' የተሰረቀች ግጥም
(በረከት በላይነህ)

-----------
ገና!
ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤
ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ።

በዳዴ ዘመኔም፣
በ'ወፌ ቆመችም!'፤
አውዴ ክፉ ነበር ለወሬ አይመችም።

እንደ ሚዳቋ ነፍስ እንደ ነብር ጥፍር፤
ስጋትም- ጭካኔም-ነበር የዕውቀቴ ስር፣
"ተጨቆንኩ!"
"ተበደልኩ!"
"ተረገጥኩ!"
"ተገፋሁ!"
"ተቀማሁ!"።
መሬቱ ጠላቴ፤
ሰማዩ ብሶቴ።

ተስፋ ትዝታዬን ሊያጠፋ ለቃቅሞ፤
ባፈሙዝ ያየኛል ገዳይ ደጅ ቆሞ።

ወዘተ...
በእነዚህ 'ምግቦች' አድጎ ሰውነቴ፤
እኮ እንደምን አይሆን 'ጥርጣሬ' ሀብቴ?
መገርሰስ፣ መደምሰስ፣ ማሳደድ-ውበቴ?
ስለዚህ አይድነቅህ!
ቀርበህ ወደድከኝም፣ ርቀህ ጠላኸኝም፤
ገድዬህ ካላለፍኩ የኖርኩ አይመስለኝም።

____
ገጣሚ በረከት በላይነህ (የመንፈስ ከፍታ)

@getemsource


@getem
@getem
ደህና ነኝ!
በገጣሚ # ሰለሞን ሳህሌ

"ደህና ነህ?" እያሉ
ለጠየቁኝ ሁሉ
"ደህና ነኝ" ልበል ወይ?
ደህና ነዉ እንዲሉ
ብየ ብጠይቀዉ
"ደህና መሆንህን
ከልባቸዉ ሽተዉ ለጠየቁህ ቀርቶ
ደህና መሆንህም ለሚያሳምማቸዉ
ይበልጥ እንዲያማቸዉ።

@getem_sourcebot
@getem
@getem
።።።። የምላሼ ምክንያት ።።።።።።።
.
.
እያየሽ አይን አይኔን
እያየሁ አይንሽን
በአፈቀርኩህ መርዶሽ
ሰትንጭው አለሜን
'ወድሀለው ስትይ
ሴትነትሽን ስተሽ
ክብርሽን አዋርደሽ
አንቺነትሽን ትተሽ
ስሜትሽን ሰትነግሪኝ
የተርበተበትኩት
የተንተባተኩት
የምለው የጠፋኝ
ባልወድሽ አይደለም....

ስብዕናሽ አንሶ
ውበትሽ ጎሎብኝ
እምልልሻለሁ!!!
በፍቅር በርሃ
በቀለጠው ልቤ
በማለዳ ጀምበር
በጨለመ ቤቴ
እምልልሻለሁ!!!

ከፍቅር በመነነ
በነተበ ሀሳቤ
ብቸኝነት ይሙላ
ይቆፈር እት'ብቴ
....
ፍቅርሽን ይያሳጣ
ሀሳብሽን ይንሳኝ
አልወድሽም ያልኩሽ
ብወድሽ ነው እቴ!
.........
ውዴ ሙች እያሉኩሽ
የቆሰለ ሩብ ልብ
የመከነ ፍቅሬ
ኦናነት የሞላው
ሲታወሰኝ በ'ሬ
ፍቅርን የገደፈ
ሳይፅፈ የነጠፈ
ቢታየኝ ብዕሬ
..........
አንገቴን ሰብሬ
ፍቅርሽን ቀብሬ
ታምኝኛለሽ ፍቅሬ
እንዲያ እየወደድኩሽ
እየራብሽኝ አንቺ
እየጠማኝ ፍቅርሽ
.
.
.
ግን ሰለምወድሽ
አልወድሽም አልኩሽ
.
.
.
ታዲያ በወደድኩሽ
ከምናምንቴ ልብ
ከተራቆተ ቤት
ልጠብቅሽ ባልኩሽ
"እንደዛ ስወደው
አይወደኝም" እያልሽ
ታወሪያለሽ አሉ
ላገር ለከተማው
ለጠየቀሽ ሁሉ
. . . . . .
እኔ ግን ልንገርሽ ......
ብወድሽ እንጂማ
ፍቅርሽ ቢያሸንፈኝ
ጠላሁሽ ያልኩተኝ
ባልወድሽ ኖሮማ
እያሳ'ሳቅኩ ስቄ
በጥርሴ ለብልቤ
እዶልሽ ነበረ
አዋክቤ ክቤ
ፍቅር ካመከነው
ከበረዶው ልቤ ።


ከ ሚራዥ
ለ "አንቺ"

@getem
@getem
@lula_al_greeko
"ለምን ሞትህ" ቢሉት ...
አልሞትኩም እያለ ፣ ትውልድ ይሟገታል
ድሮስ
ኖሮ የማያውቅ ህዝብ ፣ ምን ሆኖ ይሞታል?!!!
።።።።።
(በላይ በቀለ ወያ )

@getem_source
@getem
@getem
"ዘቅዝቀው ሰቅለውት ፣ የዓለሙን ካርታ
እግር ነው ሚታየው ፣ በጭንቅላት ቦታ።
(በረከት በላይነህ)

።።።።።።
አለሙ በሙሉ
የአለምን ካርታ ፣ ዘቅዝቆ ቢያዋቅር
እግር አይታየኝም
ጭንቅላት ለማየት ፣ ስለማቀረቅር ።
(በላይ በቀለ ወያ)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
##እኔና እሷ
(ጌትነት እንየው)

በልብ ስር ምሽግ
በጦርነት ሜዳ ፤
አመሏን ሳልመዝን
ኃይሏን ሳልረዳ፣
ፍቆሯን ተፋልሜ
ልጥላት ገጥሜ፣
አለምሁ ተንበርክኬ
ተኮሰች ተኝታ፣
ምኗን እደሆነ ሳትሁት
ምኔ እንደሁ ተመታ፣
ማረከችኝ ስቃ
እጄን ሰጠሁ በቃ
ግን ድሏም አልቆየ
ሽንፈቴም አልጠና፣
ሴትነቷ ለዬ
ወንድነቴ ቀና፣
ተጣጣን በጠባይ
ተቷቷውን በድህና፣
እኔም እኔ ሆኜ
እሷም እሷ ሆና!!


ለመላክ @getem_sourcebot

@getem
@getem
@getemsource
1
#እንጂ_ምን_ኣጠፋሁ

ሚስቴ ነሽ ስልሽ
"እናትህ ነኝ" እያልሽ
ሰርክ እየተከፋሁ
እናቴ ነሽ ብዬ
ሚስቴን ላስስ ወጣሁ
Ezana Mesfin

@getem
@getem
@getem_sourcebot
ገጠር ለምትኖረው ወንድሜ

እንደምን ነህ ክንዴ
እኔ አለሁ በደህና
ልጆች ደህና ናቸው
ጫቅሎቹ በሙላ?
~~~~~~~~~
ከብቶችሳ ክንዴ ደህና ተዋልደዋል?
ጎረቤቱ ሁላስ በደህና ከርመዋል
~~~~~~~~~
ሰብሉስ ያፈራል ማሳውስ እንዴት ነው
ዩርያውና ዳፑን በደምብ ለመደው
~~~~~~~~~
ሽምብራና ጤፉስ ጎተራ ይሞላል
ቅቤና ወተቱስ ለወዳጅ ይተርፋል
~~~~~~~~~
ድሮ እንደነበረው
አልፎ ሃጅ እንግዳስ ተቤትህ ይገባል
እግሩን ይታጠባል ቡን ይፈላለታል
ተሸቱ ተማሩ እስቲጠግብ ይበላል
~~~~~~~~~
ብቻ ኸመስገን ነው እንደሱ ተሆነ
ባሕልና ወጉ ታልተበታተነ
~~~~~~~~~
የኔን ነገር ተወው
የከተሜ ነገር ምንም ጥሩ የለው
ክፉም እንዳልለው
ቡላሌ አጥልቄአለው
ለውርጩ የሚሆን ጨርቅ ቀይሬአለው
ታዲያ ምን ያደርጋል
የሰው የመኪናው ጫጫታው ከብዶኛል
ታምቡሬ ተዛብቶ በሽታ ሁኖኛል
አካሌም ደንዝዟል
ጉልበቴ ሟሙቷል
~~~~~~~~~
ተይችና ተይች የግር ጉዞ የለም
እድሜ ለመኪና ስንዝር ይዞህ እልም
~~~~~~~~~
ነዳጅ ታገር ጠፍቶ ሰው በግሩ የሄደ ለት
በጨርቅ ታጅሎ ይቀራል ለሳምንት
አይመጣም መስሪያ ቤት
~~~~~~~~~
አይ ከተሜ ጀግናው ምኑን እንደበላው
ጣይ ነካ ታረገው ወዲያው ሽብልል ነው
~~~~~~~~~
የምግቡን ነገር ተወኝ ወንድማለም
ለመኖር ነው እንጂ ጠግቦ መብላት የለም
~~~~~~~~~
እንጀራውም ተፌስታሉ ሳስቷል
ለያውም ጀሶ የንጨት ብናኝ ይጨምሩበታል
~~~~~~~~~
አብሮ መብላት የለም ጎረቤት ተጣርቶ
ለራስ መጎድጎድ ነው ደጁነን ዘጋግቶ
~~~~~~~~~
ስማ ወንድማለም ሰው በጣም ረክሷል
እምነት የለለውን ሐይማኖት አብዝቷል
~~~~~~~~~
ኑሮው ውድ ሆነና ቲበዛ ችግሩ
ሰው መስራት አቆመ ላገሩ ለክብሩ
~~~~~~~~~
ይልቅ ለነጮቹ ተወዲያ ላሉቱ
ሰው ያከማቻሉ በብር ሚሸጡቱ
~~~~~~~~~
አሁን አሁንማ ብቻውን ሚያወራው
የቀወሰው በዝቷል
አዛኝ የለም እንጂ ሰው በቁሙ ሞቷል
~~~~~~~~~
ይገርምሃል ክንዴ
የከብት ማዋያው ሜዳው ሁሉ ጠፍቷል
ሰማይ የሚነካ ቤት ሰርተውበታል
~~~~~~~~~
ታዲያ እንዲህ ያለውን ቤት የሰሩት ሰዎች
እግዜር ቅርባቸው ነው
ሆዳቸው ት..........ል.........ቅ ነው
~~~~~~~~~
ሌላ ቤት ጭማሪ የፈለጉ እንደሁማ
ለቸሩ ፈጣሪ ወተው ይነግሩታል ተቤታቸው ማማ
እርሱም ቸር ነውና ለቅርብ የሚሰማ
~~~~~~~~~
ያሉትን በሙሉ ውሰዱ ይላቸዋል
የምድር ድካማቸውን ያከማችላቸዋል
በሕንጻ ስራቸው ያፈሰሱትን ደም ይቆጥርላቸዋል
~~~~~~~~~
እናልህ ወንድሜ
አገር አምሮበታል!
ሰው ግን ደክሞታል!
~~~~~~~~~
እናም ሁሉን ትቼ ወደ ገጠር
ልመጣ ነው እልኃለሁ
እኔ ባልከብር እንኳ አገር አከብራለሁ!!!።
~~~~~~~~~//~~~~~~~~~~
## ኤፍሬም አለም ##
@ ጎንደር አዘዞ

@getem_sourcebot
@getem
@getem
ግብር ከፋይ ግጥም
(ልዑል ሀይሌ)

ጥያቄ አለኝ ላንቺ!
70 ዓመት ለመኖር 50 ዓመት መበደር
50 ለመበደር 20 ዓመት መታሰር
የተፈረደ ሰው
ባልኖረው ኑረት ውስጥ
የቱ ጥያቄ ነው
ግብር ተከፍሎበት ቶሎ ሚመለሰው?
.
ከእናት ሆድ ሲወጣ ለማይኖረው ዕድሜ
ቶሎ ለሚቀጠፍ ቶሎ ለሚሰበር
ለምን ነው ንገሪኝ ከገላው ተቆርጦ ዕትብቱ ሚቀበር?
.
ሌላም ጥያቄ አለኝ!
በፍቅር ንግድ ዓለም
ዕልፍ ትዝታዎች ገዝቶ ላተረፈ
በዋጋ ግሽበት ውስጥ
የዕምነቱን ሱቆች ከስሮ ለቆለፈ
በግብር ትመና ከሽያጩ በላይ
ግብር እንዲከፍል የተፈረደ ሰው
የቱ ጥያቄ ነው ቶሎ ሚመለሰው?
.
ሌላም ጥያቄ አለኝ!
ላንቺ ሳቅ ፈገግታ ጥርስን ሸጦ ማደር
ላንቺ ቁመት መርዘም መሰላል መበደር
አፈር እንዳይነካሽ 'ኮብልስቶን ማንጠፍ'
ስጦታ እንዳያምርሽ ፅጌረዳ መቅጠፍ
ላንቺ ሕይወት ሲባል
ሕይወቱን በመክፈል ለተፈረደ ሰው
ባልኖረው ኑረት ውስጥ
የቱ ጥያቄ ነው ቶሎ ሚመለሰው?
የቱ ጥያቄ ነው?
መወለድ ምንድነው?
መልስሽን አውቃለሁ ቋንቋ ነው ትያለሽ
ዘር መቁጠሩን ተዪ ከቋንቋ ምን አለሽ?
ይልቅ መልሺልኝ
መወለድ ምንድነው?
ማንነት ምንድነው?
መሞትስ ምንድነው?
ከነዚህ መካከል ቅድሚያ የሚመለስ
ግብር ምከፍልበት ጥያቄ የቱ ነው?
ሌላም ጥያቄ አለኝ?
እስካሁን ለፃፍኩት ለገለጥኩት ሃሳብ
በጥያቄ አንድምታ
ግብሩን ገምቺልኝ ስንት ስንኝ ልክፈል
የስንቱን ቤት ልምታ?

@getem_sourcebot


@getem
@getem
👍2
ናፍቆትሽ ቀለም ነው

ዛሬ ባትኖሪ - ካካሌ ብትርቂ - አለሽ ከመንፈሴ
ኑሮን ምኖርብሽ - ተስፋን ማልምብሽ - የለት ተቀን ሱሴ
ቀለሜ ነሽ ለኔ - ያውም የተዋበ - ህብር ቀለም ያለው
ለአይን ማራኪ - አግራሞት ፈጣሪ - ብዙ ፍቅር ያለው
ብዙ መውደድ ያለው
ናፍቆትሽ ቀለም ነው!
#አሹ2010


@getem_sourcebot
@getem
@getem
የፍቅር ከፍታ

አፍቅራኝ ስታምነኝ
የዋህነቴ ላይ ፥ ነፍስሽ ተንጠልጥላ
ስጦታ እንዲሆነኝ
ከህልሞችሽ ቆርሰሽ ፥ ሰጠሺኝ ጃንጥላ !

ወዲያው ዝናብ ጣለ
ይረሰርስ ጀመር ፥ የሰፈሬው ግዛት
ሰፈርተኛው ሮጠ
ከዝናብ ሊጠለል ፥ ጃንጥላ ለመግዛት

አየሽው አይደለ?
ከጅል ሲያስቆጥረኝ ፥ የፍቅርሽ ከፍታው
በልብሴ አስጠለልኩት
ውድ ጃንጥላሽን ፥ ዝናብ እንዳይመታው !!

( ናትናኤል ጌቱ )

@getem_sourcebot

@getem
@getem
625 ቁጥር 1(ልዑል ሀይሌ)
.
የእባቡን ጉድ-ጓድ
እንድትለኪበት ክንዴን ስዘረጋ
የእሳቱን ምድጃ
እንድታነሺበት እጆቼን ሳስጠጋ
.
ፀሐይ ጋርጄልሽ ራሴን ባጠቆርሁኝ
ዝናብ አስጠልዬሽ ውሃውን ባቆርሁኝ
.
ሰውነቴን ሁሉ ስላንቺ እያሳደርሁ
ጥለሺኝ ስትሄጂ
ከራሴ ገላ ላይ ያንቺን ገላ ቆጠርሁ
ያንቺን ሀሳብ ቆጠርሁ
.
እንዴት ነው? ሸሽተሽኝ የሄድሽበት ሃገር
ያስተዳድራል ወይ እምነት ሸጦ ማደር
.
እንዲያው ልጠይቅሽ
እምነትን መነገድ ያከስራል ያተርፋል?
ክንድን ቆርጦ መውሰድ ያከስራል ያተርፋል?
ልብ አድምቶ መሄድ ያከስራል ያተርፋል?
የኔማ ህመም ነው
ከጊዜ ጋር መጥቶ ከጊዜ ጋር ያልፋል
.
ያንቺ ግን ጨነቀኝ
ህልሞቼን ነጥቀሺኝ እንደምን ልተኛ
ቅዠቴን ነጥቀሺኝ እንደምን ልተኛ
ሸክሜ ቀለለ ምን ሰርቼ ልብላ
ሃሳቤን ወስደሽው የማስበው ጠፋ
ጭንቀቴን ሰርቀሽኝ
አለመጨነቄ እያስጨነቀኝ ነው በነጋ በጠባ
.
በነጋ በጠባ..
እጆቼን ዘርግቼ ፊትሽን አጥባለሁ
እንጀራ ዳቦውን እየጠቀለልኩኝ
አፌን እያጎረስኩ ቁርስ አበላሻለሁ
ጠግቤ እየዋልኩኝ
ያጠገብኩሽ መስሎኝ
ተመስገን እስክትዪ እጠብቅሻለሁ
.
እንዴት ነው ክደሽኝ የሄድሽበት ሃገር
ያስተዳድራል ወይ ወዳጅ ሸጦ ማደር?
.
ያስተዳድራል ወይ
(ይቀጥላል...)
07-10-10
@getem_source


@getem
@getem
1
ጥበቃ

የሰጎን እንቁላል መሳይ ማንነቴ
በስብሶ እንዳይፈርስ በአይን እይታሽ ጠብቂኝ እናቴ

Fun-Dan=Mental


@getem_sourcebot
@getem
@getem
*አንቺን ላለማሰብ*
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)

አንቺን ላለማሰብ እኔማ በኔ ቤት፣
ከውስጤ አውጥቼ አብዝቼ ለመርሳት፣

ሲጋራውን ለኮስኩ ጢሱ እንዲጋርደኝ፣
ምስልሽን ከዓይኔ ወዲያ እንዲወስድልኝ፣

ደግሜ ደግሜ ልረሳሽ ባጤሰው፣
ከንፈርሽ ናፈቀኝ ከንፈሬን ሲነካው፣

እሱን ወዲያ ትቼ መጠጡንም ብጋት፣
አንቺን ላለማሰብ አንቺኑ ለመርሳት፣

እያንገዳገደ ደጅሽ ይወስደኛል፣
ልረሳሽ ስደክም ትዝታሽ በልጦኛል፣

ፀሀይንም ሳያት አስታውስሻለሁ፣
ትዝ ይልሽ እንደሆን ውበቷን ካንቺ ጋር አመሳስያለሁ፣

ጨረቃንም ሳያት እነኚያ ምሽቶች ይከሰቱብኛል፣
ከባዶነት ነጥቀው ካለፈው ምናኔ ወስደው ይከቱኛል፣
አንቺን ላለማሰብ ለኔ አንቺኑ ማሰብ እጅግ ይቀለኛል፣

ያላረኩት የለም ከውስጤ ላወጣሽ፣
ግና፣
ልረሳሽ ያልኩለት የባሰ ወደድኩሽ፣

አንቺን ለመርሳት ስል አንቺን እያለምኩኝ፣
ትዝታን ለመቅበር ብዙ ብዙ ጣርኩኝ፣

የሄድንበት መንድ እኔና አንቺ አብረን፣
ያወራኛል ደርሶ ይጠይቃል አንቺን፣

ከፀሀዯ ንዳድ የተከለልንበት፣
ያ የሾላ ዛፍም አነሳሽ በድንገት፣

አንቺን ላለማሰብ ማሰብ ባላቆምም፣
ትዝታሽ አስሮኛል የትም አላመልጥም፣

ብራመድ ጎዳናው፣
ብቀመጥም ጥላው፣

ማለዳ ንጋቱ፣
ድጋሜም ምሽቱ፣
ያንቺ ወዳጅ ናቸው አንቺን ሚተርቱ፣

ይገርምሻል ውዴ እኔኮ እንዲ ነኝ፣
አንቺን ላለማሰብ አንቺን እያሰብኩኝ፣
ለመርሳት ፈልጌ ሁሌ እያስታወስኩኝ፣
ትዝታን አግብቼ የተሰቃየሁኝ፣

እኔኮ እንዲ ነኝ፣
አንቺን ካለማሰብ መሞት የሚቀለኝ፣
ምንድነው ግን ቅኔው ፍቺና ንገሪኝ፣
አንቺን ለመርሳት ስል አንቺን ሚያሳስበኝ፣

ለሄድሽው መውደዴ

ናፍቀሽኛል

ሚያዚያ 24/08/10 ረቡዕ ማለዳ 12:40...



@getem
@getem
@yeneta
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (☺️ልዑል☺️)
🙏እንኳን ለ1439ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ።

ኢድ ሙባረክ ለ ሙስሊም ኢትዮጵያኖች ።
💚💛❤️
💚ግጥም ብቻ💚
💛 ስዕል ብቻ 💛
❤️ ወግ ብቻ ❤️
💚💛❤️
@getem @seiloch @wegoch

@Lula_al_greeko
👏የካፊያ ምች👏
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተፈሪ ዓለሙ(1974)

ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ
ካላጣችው ሰዓት ከቤት አስወጣችኝ
ጥርቅም እቅፍ አድርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የእድሜ ልክ ልክፍቱን ያኔ አስለከፈችኝ

መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የእኔ ልብ በሷ የሷ በእኔ ጠፋ
የሰማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን
ውሃ ጠማኝ ውሃ እዘነበብን

ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ
በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ
እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ
የዘመን ህመሜን ያን እለት ታመምኩኝ
አሁን አሁን ታዲያ!

ደመናው ሲጠቁር ነጎድጓድ ሲያጓራ
ነፋስ ሲያጉረመርም ክረምቱን ሲጠራ
ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ
ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ

..........................ምች ተሳልሜ



@getem
@getem
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM