ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ምን_ይውጠኝ_ነበር?
*
*
ዕድል የቀናኝ ለት ዐይኖችሽን ካየው
ድንገት እንኳ ላፍታ፣
የጆሮዬን ታምቡር ሊቀደው ይደርሳል
የልቤ ትርታ።
:
:
ከጨበጥሺኝ ደሞ ለስላሳው መዳፍሽ
አርፎ መዳፌ ላይ
አንቺን በነካ እጄ ሌላ ሰው መጨበጥ ያስጠላኛል ብታይ።
:
:
የገጠሙ እንደሆን ሰላምታን አስታከው ጉንጭሽና ጉንጬ፣
ከርማ እንደተፈታች እንደንቦሳይቱ አልጠግብም እሮጬ።
:
:
እንደው የገረመኝ
በድንገት ተያይተን
ሰላም ተባብለን
ጉንጭ ተገጣጥመን
እኔ ላይ ካሳደርሽ ያንን ሁሉ ስሜት
ያንን ሁሉ ነገር፣
ማርን በሚያፈልቁት በከናፍሮችሽ
ከንፈሬን ብትስሚኝ ምን ይውጠኝ ነበር?

#ሄኖክ_ብርሃኑ
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu

@getem_soursebot
@getem
@getem
አይኔ

አይኔ አፈጠጠ ረጅም አብርቶ
በክህደትሽ ቁና ስትሰፍሪኝ አይቶ
ልብሽ ከባእድ እጅ ሰተት ብሎ ገብቶ
በብረቱ ብረት አይኔ ተመልክቶ
ዉዴ ይሄንንማ አታደርግም ከቶ
ብሎ የሚመሰክር
አይቶ በብረቱ ክዶ 'ሚከራከር
ያየውን የሚክድ ያልፈራ ኩነኔ
ይሄ ከንቱ አይኔ ያንቺ ወይስ የኔ?


በ ያሬድ መላኩ

@getem_sourcebot


@getem
@getem
👏👏👏ደስስ ሲል👏👏👏

ዛሬ ዕለተ ሰኞ ሰኔ 4 ቀን የልዑል ሃይሌን አዲስ የግጥም መድብል ለመመረቅ በሁላችንም ቤት (በብሄራዊ ቲያትር) ተሰይመን ነበር።
ያለማጋነን ልብን በሚገዙ አ ስ ደ ሳ ች ስንኞች ታጅበን ደስ የሚል , ነገን ጨምሮ ደስ አስደርጎ የሚያስውል ማራኪ ምሽት አሳልፈን መጣን
ልዕል ሃይሌ ስላወኩህ ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር ያክብርልኝ።
መፅሃፍህን እንድንመርቅ ስለጋበዝከን
መልካሙን ሁሉ እመኝልሃለሁ። 🙏


ሚኪያስ ልየው (@Mykey21)

@Getem
በታገል ሰይፉ
ታገኝ አንደው ፈልግ


ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem
#ሃገር_ማለት_ዳቦ...

ሃገር ማለት ዳቦ
ዳቦ ማለት ሃገር
አይኖች ተጨናብሰው በጭስ ምትጋገር

ሃገር ማለት ዳቦ
ሃገር ማለት እናት
አናስቆርስ ብለው ልጆች የሞቱላት

ሃገር ማለት ዳቦ
ሃገር ማለት እናት
እየትቆረሰች ጎረቤት ሚወስዳት

ብርሃን ታዬ(Bra Han)

@getem_sourcebot

@getem
@getem
ወገኔ

ወገን ወቶ ሜዳ ቀረ
ሩቅ አስቦ ቅርብ አደረ
እንቀየር ብሎ ያለውን ሰቶ
በረሃን አቋርጦ ጫካውን ትቶ
ህይወቱን ሰውቶ ነገውን አስቦ
እንዳልሆነ ሆነ በሞት ተገድቦ

DaDa Coffee
@getem_sourcebot

@getem
@getem
Forwarded from SPACE COMPUTER
😍ባርኒ ተመልሷል😍


# የታለፈ_እና_ያለፈበት




የነብሳችን ጥማት
የስጋችን ሐሴት፣
ፍላጎት ስሜቱ
ሙቀቱ -- ግለቱ፣
ቸብቸቦ ሙዚቃው፣ የደነስንበቱ
ቀልድና ጨዋታው፣ የፈገግንበቱ፣
ዥንጉርጉር ልብሳችን
ጥምልምል ፀጉራችን
ጥድፍድፍ ኮቴያችን
ዜማ ፉጨታችን፣
የረገጥነው መሬት፣ የእግራችን ዳና
ሲቀር ከኀላችን፣ ሰው ተጓዥ ነውና፣

ከአንጀት ያሳቀን
አድሮ ቢያሳቅቀን፣
የኮረኮረን ጣት፣ ቢያስነባን መልሶ
ያበድንለት ነገር፣ ቢያሳብደን ደርሶ፣
ሁሉ አልዋጥ ቢለን
ቢያን..ገሸ..ግሸን
ዛሬ ላይ ቢያስጠላን ፣ የትላንቱ ቀለም
አልፈነው ነው እንጂ፥ አልፎበት አይደለም።
-----------------------//---------------------
( በርናባስ ከበደ )

:
በነገራችን ታች ... ይህ ግጥም እርጅናና ሃሳብ ተጫጭኖኝ በ26ተኛ
አመት የልደቴ በአሌ ዋዜማ የከተብኩት መሆኑ ታሳቢ ይሁንልኝ። የዛሬ
26 አመት (ሰኔ 5፣ 1984 )ስወለድ ቀኑ ደመናማ ነበር። እናም...
ከማህፀን ስወጣ እንደ ቻይና ሞባይል ድንገት "እሪሪሪ!!" አልኩኝ።
እማዬም በእሪታዬ ውስጥ አንዳች ጥበባዊ መጠራት ተመለከተች።
''ይሄ ልጅ ልቅሶው ቤት ይመታል፣ ገጣሚ ነው ሚሆነው'' አለች።
የጠ.ሚ/ሩ እናት በሰባት አመቱ ትንቢት ተናገሩ። የኔዋ ግን በሰባት ቀኔ
ከልቅሶዬ ዜማ ሰምና ወርቅ አገኘችበት።
እናላችሁ .... ብዙም ወራት ሳልቆይ ... አፌን የፈታሁበትን ሃሌታ ቃል
ተናገርኩ። በዚህም ገጣሚነቴ እስከወድያኛው ተረጋገጠ። ቃሉም
የሚከተለው ነበረ። .....
.
.
.
☞☞☞"ውዴ!"☜☜☜
:
:
እና .... መልካም ልደት ለኔ!!
:
እንደ ህፃናቱ እንደነ ሚጣ ልደት እናዝግ እንዴ???....
:
" አምሳ አመትህ ነው?"
:
'አ..ይ..ደ..ለ..ም!!!!'
:
"አርባ ዘጠኝ አመትህ ነው?"
:
'አ..ይ..ደ..ለ..ም!!!!''
:
'አርባ ስምንት አመትህ ነው?"
:
'አ..ይ..ደ..ለ..ም!!!!'

"አርባ ሰባት አመትህ ነው?"

'አ..ይ..ደ..ለ..ም!!!!'

"አርባ ስድስት ኣመትህ...... ??"

"ኧረ ኡ!ኡ!ኡ!! አይደለም አልኳቹ እኮ!! ልታሳብዱኝ ነው እንዴ??"







እንኳን ተወለድክልን ባርኒ
ግጥም ብቻ

@getem_sourcebot
@getem
@getem
1👍1👎1
ቀድሞ የደረሰ ፀሎት
#በፀጋዬ ወንድወሰን

በሮች ሁሉ ሞቱ በጎችም ታረዱ
ያነሱት ፍጥረቶች ዶሮዎች ተጎዱ
ነፍስን ያጠፋ ሰዉ እርሱ ቀጠፋቸዉ
አባሮ ካሉበት ቀርጥፎ በላቸዉ ፡፡
( . . . )

#ዶሮዎች ፀለዩ

#በጎች ተማጸኑ

#በሮችም መከሩ

አያዉቁትን አምላክ አንጋጠዉ ለመኑ
የሩሀቸዉ ችግር የነፍሳቸዉ መላ
ሰዉ ነዉ ጭራቃቸዉ እነርሱን የበላ ፡፡

ስለዚህ
( . . . )

ሰዉን ጭራቅ ብለዉ በጭራቅ መስለዉ
ላ’ጥፊ ሰዎቻቸዉ
ብለዉ ተማፀኑ ሰዉን ላክባቸዉ !!!

@getem_sourcebot
@getem
@getem
ሰላም የግጥም ብቻ ወዳጆች (@getem)

መሶብ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ በብሔራዊ ቲያትር ጋር በመተባበር ፣ ፯ ኛውን ዙር "አንዲር የሙዚቃ ትርኢት " ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር እንደሚቀርብ የባንዱ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም በባንዱ ውስጥ የዋሽንት ችሎታ ባለቤት የሆነው አርቲስት ጣሰው ወንድሙ ሹክ ብሎናል።
በዕለቱ በባንዱ የተቀነባበሩ አዳዲስ ሙዚቀዎች፣ በ ፰ ሴት ድምፃውያን የሚቀርቡ ዜማዎች እንዲሁም ልዩ የዳንስ ትርኢት እንደሚቀርብ ሰምተናል።

በነገራችን ላይ የሙዚቀ ትርኢቱን ለመታደም መግቢያው በነፃ መሆንንም ለማወቅ ችለናል።



@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
@Getem
Forwarded from MarkdownBot
ሳያነብት እንዳያልፉ

// የስስታሙ ነጋዴ ታሪክ //

በአንድ ወቅት አንድ ፈጣሪ በሰጠው ጸጋ አመስግኖ የማያውቅ
ስስታም ነጋዴ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን
..........ሙሉ መረጃ ለማግኘት እናለመማር ብቻ ይህንን ሠማያዊ ፅሁፍ ይንኩት👈
#ወንድ ልጅ ሲጣላ#
ሰኞ

እርም የና'ቴን ስጋ፥ካ'ንቺ ገላ ብገኝ
ስምሽን ብጠራ፥ምርቅ ሆኖ ይነቀኝ፤

ማክሰኞ

ፍቅርሽ እንደ ቅጠል ፥ከላዬ ረገፈ
አይኔ ወፍራም ዳሌ፥ክንዴ ሽንጥ አቀፈ
ጣቴ እንደ ብርቱካን፥ቆንጆ ልጦ በላ
አዱኛዬ አበበ፥ ማር ከደጀ ፈላ፤

ዕረቡ

አይጭኑት ባ'ህያ፥አያስሩት በገመድ
እንዴት ያደርጉታል፥የዚያችን ልጅ መዉደድ፤

ሃሙስ


አመፀኛዉ ልቤ፥ዛሬ አንቺን ተመኘ
እግሬ በማለዳ ፥እደጅሽ ተገኘ፤

ዓርብ

ሆድሽ ከቶ አይጨክን፥ልብሽ በኔ ዓይፅና
ካ'ንቺ ተነጥዬ፥ሰዉ አልሆንምና፤

ቅዳሜ

እንደ ቀትር ፍትፍት፥አብዝቼ ልጉረስሽ
አልጠገብኩምና፥ደግሜ ብስምሽ
ስጭኝ ከንፈርሽን፥የሰዉ ስጋ ልብላ
አጥንቴ ይለምልም፥ሰይፌ ዝሆን ይቅላ፤

እሁድ

አንገትሽን ስዳብስ፥አፌ ከከንፈርሽ ሲገጥም
ያይንሽን ጮራ ተከትዬ፥አየሁ ስትስሚኝ አዲስ አለም።


(መሪጌታ)


@getem_sourcebot


@getem
@getem
👍1
ምተራ
///////////////

አጭር ነህ ይለኛል
አጎንብሶ እያየ
መሬት ማይነካ እግር
እግዜር መች ፈጠረ?

(መለስ አመሃ)

@getem
@getem
#ዓይናማው_ቢመራት

ወልዳ እንዳልበተነች አገሬ ታውራ
መሰብሰብ ይዛለች በሰው ስትመራ

Ezana Mesfin

@getem_sourcebot
@getem
@getem
👆👆
በቅርብ ከወጣው የልዑል ሃይሌ አዲስ የግጥም መድብል ላይ ድምፅ ፩ እንሆ

ርዕስ _ *805*ፍቅር#
ገጣሚ _ ልዑል ሃይሌ
አቅራቢ _ሚኪያስ ልየው @Mykey21
"እኛ ስንዋደድ"
አናት ስላት እናት
ሁሌ እምናፍቃት
ደስታ ስላት ደስታ
ማትጠፋ ላንዳፍታ
እሳት ስላት እሳት
ደፍረዉ የማይነኳት
ፍቅር ስላት ፍቅር
ስለሷስ ብዘምር
ስለ ክብሯ ለመናገር
ላልጨርስ አልጀምር......
.
.
.
.
.
......ብቻ አለች አንድ ሀገር
ከህዝቦቿ ጀርባ ካድማሷ ባሻገር

(የ ሙሉ ልጅ እንድሪስ)
@getem_sourcebot
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)


ሎተሪ ሻጭ እኔ...
እድል እድል እያልሁ ፣ እድሌ ቢያመልጥም
በጄ ያለን እድል
በማግኘት ምኞት ውስጥ ፣ ላለ ሰው ብሸጥም
እንደ ቆራጭ ልቦች
ተስፋ እየገመድኩኝ ፣ እድሌን አልቆርጥም፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሎተሪ ነሽ አንቺ...
ከልብ ለቆረጠሽ ፣ ተስፋ ለሰነቀ
አገኛለሁ ብሎ
እድል ለሚሞክር ፣ እድል እየፋቀ፡፡
።።።
@getem_sourcebot


@getem
@getem
@lula_al_greeko
🌈🌈ውድ ሀበሾች🌈🌈

ሰላም ናት ሀገሬ፡
ፍቅር ናት ሀገሬ፡
ልማት ናት ሀገሬ፡
ጥጋብ ናት ሀነሬ፡
በኢቢሲ ወሬ፡፡

❤️❤️አሌክስ አብርሃም❤️❤️

@getem
@beckyalexander
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
'ከሽፍታ' የተሰረቀች ግጥም
(በረከት በላይነህ)

-----------
ገና!
ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤
ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ።

በዳዴ ዘመኔም፣
በ'ወፌ ቆመችም!'፤
አውዴ ክፉ ነበር ለወሬ አይመችም።

እንደ ሚዳቋ ነፍስ እንደ ነብር ጥፍር፤
ስጋትም- ጭካኔም-ነበር የዕውቀቴ ስር፣
"ተጨቆንኩ!"
"ተበደልኩ!"
"ተረገጥኩ!"
"ተገፋሁ!"
"ተቀማሁ!"።
መሬቱ ጠላቴ፤
ሰማዩ ብሶቴ።

ተስፋ ትዝታዬን ሊያጠፋ ለቃቅሞ፤
ባፈሙዝ ያየኛል ገዳይ ደጅ ቆሞ።

ወዘተ...
በእነዚህ 'ምግቦች' አድጎ ሰውነቴ፤
እኮ እንደምን አይሆን 'ጥርጣሬ' ሀብቴ?
መገርሰስ፣ መደምሰስ፣ ማሳደድ-ውበቴ?
ስለዚህ አይድነቅህ!
ቀርበህ ወደድከኝም፣ ርቀህ ጠላኸኝም፤
ገድዬህ ካላለፍኩ የኖርኩ አይመስለኝም።

____
ገጣሚ በረከት በላይነህ (የመንፈስ ከፍታ)

@getemsource


@getem
@getem
ደህና ነኝ!
በገጣሚ # ሰለሞን ሳህሌ

"ደህና ነህ?" እያሉ
ለጠየቁኝ ሁሉ
"ደህና ነኝ" ልበል ወይ?
ደህና ነዉ እንዲሉ
ብየ ብጠይቀዉ
"ደህና መሆንህን
ከልባቸዉ ሽተዉ ለጠየቁህ ቀርቶ
ደህና መሆንህም ለሚያሳምማቸዉ
ይበልጥ እንዲያማቸዉ።

@getem_sourcebot
@getem
@getem