ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
"ወድያና ወዲህ"

እርስ በእርስ እጆቼ
ተጣልተው፣
ተጋጭተው በፈጠሩት ጩኸት፣
ብርታት ፣ ሞራል ብሎ
ሌላው ሲፈነጥዝ ሲደሰት ዋለበት፡፡


ቢኒያም ዋስይሁን

@getem_source


@getem
@getem
#እጎዳብሻለው
:
:
የሱነገርበቃኝባፍንጫዬ ይውጣ
ፍቅሩን በማለቴ ለምንስ ልቀጣ
ብለሽ የላክሺብኝ ወቀሳሽ ደርሶኛል
ካጠፋሁት አንፃር እንደውም ያንሰኛል።
ባፍንጫሽም ልውጣ ይበለኝ አምናለው
ግን ፍቅሬ ...
ከልብሽከወጣውእጎዳብሻለው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@Henokbirhanu


@getem
@getem
@getem
ጥላ ቢሶች
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ረቂቅ መስታወት ነው ፣ የሰው ልጆች ገላ
ብርሀን ሲያርፍበት ፣ ሚያንፀባርቅ ጥላ።
።።።።።።።።
ሚያንፀባርቅ ጥላ ፣ ብርሀን ሲንቆረቆር
በፀሐይ መገለጥ ፣ የማይሸነቆር
ጥላውን ይመስላል ፣ ሰው የውስጡ መጥቆር።
።።።።።።
በፀሐይ መገለጥ ፣ ጨለማን አይገርዝም
ክፋቱን ያህላል ፣ ሰው ጥላው ሲረዝም።
።።።።።።።።
ሰው ጥላው ሲረዝም ፣ ፀሐይን ይቀብራል
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ ውጪ ጥላው ያጥራል
ውጭ ጥላው ሚያጥር ፣ የውስጡን ያበራል።
።።።።።
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ የተዘጉ ጋኖች
ጥላ ቢሶች ናቸው ፣ ሙሉ ብርሀኖች።

@getem_sourcebot


@getem
@getem
@getem
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (☺️ልዑል☺️)
የመፅሀፍ ምርቃት

376 የተሰኘው የግጥም መፅሐፍ
ታላላቅ ገጣሚያን እና የጥበብ ሰዎች በተገኙበት

ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ.ም . ከቀኑ 11:00 ላይ በብሄራዊ ትያትር አዳራሽ ይመረቃል።

እርሶም በዕለቱ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

@getem
@getem
፨፨ ፆም ፨፨

ሀበሻ በሙሉ ስራ ስለፈታ
ፍራንካውም ሳስቶ
ወና ቀርቶ ጎታ
እንዴት ጠግቦ በልቶ!
በምን ፆሙን ይፍታ?
እንጃ....
ወትሮ ካወደቀው ከጣለው ፍሪዳ
ሰርክ ከሚጋተው ከበረቱ ገንዳ
ስለ ነብሴ ብሎ ስጋውን የጎዳ
ዛሬ ተገላብጦ
የሆድ ተስፋው ሟጦ
ሙዝ እየተገፋ አናቱ ላይ ወጥቶ
ላሚቶቹ ነጥፈው አኩሪ አተር ጠጥቶ
እንጀራው በኖራ....በጀሶ ተቦክቶ
ልኳንዳ ሲኒማ ሜንጦ አይኑን ሰክቶ
መብል በሌለበት እንዴት ሰው ይፆማል?
አሽከር በሌለበት ገዢ ኬት ይመጣል?
ባልተሰጠ ምርጫ
ምን ተገኝቶ ብልጫ
የሚሆን ማምለጫ
የሚሆን መቀጫ
እንጃ......
የታሰረ አንጀቱን
ጎስቋላ ማጀቱን
ገና ፆም ....ፍልሠታ
ነነዌ ...ረመዳን
እያለ ማጣቱን ራቡን ከሚቆጥር
ባይፆም ለማይበላ
ጠኔያም የሆድ ...ቁ ጥር
መፆም እስኪያድለው በሞላ ገበታ
በፆሙ እየፆመ አብይ ፆሙን ይፍታ።

"በአብርሀም ተክሉ"

@getem
@getem
ሀገረ የሠፋበት
ቀን የረዘመበት
እንደ ቀትር ቡና አለያ እንደ ጫት
መኖር ሱስ ሁኖበት
ዝም ብሎ የሚኖር
በቀን መሀል ሚዞር
ከርታታ ሰው አለ
ብየሽ አልነበረ

ያ' ሰው እኔ ነኝ (mintesnot)

@getem_sourcebot


@getem
@getem
ሺ ሰማንያ


መቼም ላንለያይ ገፃችን አንድ ሆኖ
ከአንድ እናት ተወልደን ደማችን ተቀድቶ
በግራና በቀኝ ጡቷን ምገን አድገን
ጭቃ አቡክተን ግድብ ሰርተን
ተደባድበን በአንድ በልተን
ፍቅራችን አይሎ ላንጣላ ምለን
እየኖርን ነበር ፍቅርን አስቀድመን
የቀን "ጎዶሎ" ነው እኛን የለያየን.......
:
:
:
:

እንጂ መች ተጣላን
አሁንም አንድ ነን....!!

ዳግማዊ በየትም (ዳግሮ)
@DagRo

@getem
@getem
ወዴት ልሂድ ?
( ናትናኤል ጌቱ)


አፍቅረው ሲገፉ
ባንኮኒ ፊት ቀርበው ፥ ድራፍት እየላፉ
በተጎዱት መጠን ፥ ካሳ እንዲሆናቸው
ካሳ ቢራ መሀል ፥ ሲደበቅ ፊታቸው
እኔ ያንቺ ምስኪን ፥ አያጣኝ ሰቀቀን
ወዴት ሂጄ ልርሳሽ?
ገና ከጅምሩ ፥ መጠጥ ቤት ተዋውቀን


@getem_sourcebot

@getem
@getem
ወፍ አዳኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
" የሰማይ ወፎችን ፣ ተመልከቱ
አይዘሩ አያከማቹ ፣ አያጭዱ ጎተራ አይከቱ
ለመኖር ባይጨነቁም ፣አምላክ ግን በቸርነቱ
ሳይመግባቸው አያድርም ፣
እኔ ግን ወፍ አይደለሁም ፣ ከወፎች ኑሮ አልማርም
ካልዘራሁና ካላጨድኩ ፣ ካላከማቸው አልኖርም
በላቤ ጎጆ ካላቆምኩ ፣ በወፎች ጎጆ አላድርም
ቸርነቱን ተማምኜ ፣ እጅ እግሬን አላጣጥፍም
ከሰማይ መና ስጠብቅ ፣ ከምድር እርግማን አላልፍም።
በላቤ እንዳድር አዞኛል ፣
ካልሰራሁ መኖር የማልችል ፣ ከመኖር ጭንቀት የማልድን
ከሰማይ ወፎች እያየሁ
የቸርነቱን ስጠብቅ ፣ በርሀብ አይኔን ሳይከድን
ከምድር ቀስት ሰርቼ ፣ የሰማይ ወፎችን ላድን።
@getem_sourcebot


@getem
@getem
🌈🌈ውድ ሀበሾች🌈🌈

የማታ ጀምበር

ካንዱ ቤት ወደአንዱ በጣራው ተራምዳ፡
የጋራውን አናት እየነካች ሄዳ፡
እዩት ከስር ጥላው፡
የማይደርስበትን፡
እዩት ሰውን ጥላው፡
ሲለፋ ሲባክን፡፡

❤️❤️ገብረ ክርስቶስ ደስታ❤️❤️

@getem
@beckyalexander
# ዘመዴን ስስመው
🖍 ገጣሚ - ደበበ ሰይፉ

ዘመዴን ስስመው
ጉንጬ ቢሻክረው
እኔንም ሻከረኝ፤
እድሜ መለስለሱ ማብቃቱ ታወቀኝ።

@getem_sourcebot
@getem
@getem
SOLYANA
ኤፍሬም ስዩም
ፍቅሬ በሶልያና😭 ምርጥ ግጥም


ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot

@getem
@getem
376
ስም ያለው ሞኝ ነው?

ስም ያለው በሙሉ ሞኝ ከተባለ
ሁሉም ባለ ስም ነው ሞኙ ወዴት አለ?
ስም ያለው ሞኝ ነው ?
ሀገሬ ስም አላት ህዝቡዋ ስም አላቸው
ባለስም ሞኝ ነው ሁሉም ሞኞች ናቸው
ስለዚህም አኔ ሽሽት ጀምሪያለሁ
በሞኞች ሀገር ዉስጥ
ብልጥ እንድሆን ብዬ ስሜን ትቼዋለው ።
@getem
📙376 ልዑል ሀይሌ
ሊመረቅ አንድ ቀን ብቻ ቀረው! !!

376 የተሰኘው የግጥም መፅሐፍ
ታላላቅ ገጣሚያን እና የጥበብ ሰዎች በተገኙበት

ነገ ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ.ም . ከቀኑ 11:00 ላይ በብሄራዊ ትያትር አዳራሽ ይመረቃል።

እርሶም በዕለቱ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

@getem
@getem
376


በኔ ቤት…(ልዑል ሀይሌ)
በኔ ቤት……
ፍየል ቅጠል አይታ
ሳትበላ ታድራለች
ዶሮ ጥሬ ረግጣ
ልፆም ነው ትላለች
ውሻ ስጋ እያየ
በረሀብ ይሞታል
ሰው እህል ቀርቦለት
ባዶ ድስት ይከፍታል

በኔ ቤት……
አንበሣ ሚዳቋን
አቅፎ ይስማታል
ጅብ ስጋ ላይበላ
ምሎ ይገዘታል
ዕባብ ሰውን አይቶ
አይተናኮልም
ነብር ጎሽ አይጥልም

በኔ ቤት……
አንድ ብር ላይ ያለው
ትንሹ እረኛ መሳቁን ያቆማል
የሰፌዱም ስፌት
ሳንቲም ላይ ይሆናል
ወተት የጠጣ ህፃን
ሰክሮ ተንገዳግዶ
የአስር ዓመት ልጅ
አስር ልጆች ወልዶ
የሰፈር አዛውንት
ሰፈር ይቦርቃል
ሩቅ ያለው ቀርቦ
ቅርብ ያለው ይርቃል


አሁንም…
ከጣልሺኝ ቦታ ላይ
ብቻዬን ቁጭ ብዬ
ታምራዊ ስዕል
በአይምሮዬ ስዬ
ሀሳቤን ጥጃለሁ
ማይበስል ማይመስል
ዳግም በህይወቴ
አገኝሽ ይመስል

@getem_sourcebot

@getem
@getem
@lula_al_greeko
--------------------
(በዕውቀቱ ስዩም)

ክልክል ነው!!!
--------------------

ማጨስ ክልክል ነው
ማፏጨት ክልክል ነው
መሽናት ክልክል ነው
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል?
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ
"መከልከል ክልክል ነው"፤
የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡
@getem_sourcebot

@getem
@getem
ተጠራጣሪ ነኝ !!

ብፁዕ ፃድቅ ሁሉ…
ከአላህ ጋራ ሁኖ ፥ ኮኮቦች ቢያዘንብም
ማርያም ስትፈትል ፥ አብሯት ቢሸምንም
ተጠራጣሪ ነኝ!
ሰው ሁሉ ሌባ ነው ፥ ማንንም አላምንም!

የሻማችን እሳት ፥ ብርሀን ሲቀማ
ለዘመናት ያህል ፥ ስላየን ጨለማ
ፃድቅ በግራ እጁ
ጨረቃን ቢሰጠን ፥ እንባችን ይደርቃል
እኔ ግን አላምንም !
ምናልባት ቀኝ እጁ ፥ ፀሀይን ይሰርቃል! !

በጨለማ ዘመን
ጥቂት መራራቱ
ጥቂት ደግነቱ
ብርሀን ሰርታ እንጂ ፥ መልአክ የሚመስለው
የትኛው ፍጡር ነው
ከአውራ ጣቱ ጣገብ ፥ ሌባ ጣት የሌለው ??

(ናትናኤል ጌቱ)

@getem_sourcebot
@getem
@getem
👍1
#ምን_ይውጠኝ_ነበር?
*
*
ዕድል የቀናኝ ለት ዐይኖችሽን ካየው
ድንገት እንኳ ላፍታ፣
የጆሮዬን ታምቡር ሊቀደው ይደርሳል
የልቤ ትርታ።
:
:
ከጨበጥሺኝ ደሞ ለስላሳው መዳፍሽ
አርፎ መዳፌ ላይ
አንቺን በነካ እጄ ሌላ ሰው መጨበጥ ያስጠላኛል ብታይ።
:
:
የገጠሙ እንደሆን ሰላምታን አስታከው ጉንጭሽና ጉንጬ፣
ከርማ እንደተፈታች እንደንቦሳይቱ አልጠግብም እሮጬ።
:
:
እንደው የገረመኝ
በድንገት ተያይተን
ሰላም ተባብለን
ጉንጭ ተገጣጥመን
እኔ ላይ ካሳደርሽ ያንን ሁሉ ስሜት
ያንን ሁሉ ነገር፣
ማርን በሚያፈልቁት በከናፍሮችሽ
ከንፈሬን ብትስሚኝ ምን ይውጠኝ ነበር?

#ሄኖክ_ብርሃኑ
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu

@getem_soursebot
@getem
@getem
አይኔ

አይኔ አፈጠጠ ረጅም አብርቶ
በክህደትሽ ቁና ስትሰፍሪኝ አይቶ
ልብሽ ከባእድ እጅ ሰተት ብሎ ገብቶ
በብረቱ ብረት አይኔ ተመልክቶ
ዉዴ ይሄንንማ አታደርግም ከቶ
ብሎ የሚመሰክር
አይቶ በብረቱ ክዶ 'ሚከራከር
ያየውን የሚክድ ያልፈራ ኩነኔ
ይሄ ከንቱ አይኔ ያንቺ ወይስ የኔ?


በ ያሬድ መላኩ

@getem_sourcebot


@getem
@getem
👏👏👏ደስስ ሲል👏👏👏

ዛሬ ዕለተ ሰኞ ሰኔ 4 ቀን የልዑል ሃይሌን አዲስ የግጥም መድብል ለመመረቅ በሁላችንም ቤት (በብሄራዊ ቲያትር) ተሰይመን ነበር።
ያለማጋነን ልብን በሚገዙ አ ስ ደ ሳ ች ስንኞች ታጅበን ደስ የሚል , ነገን ጨምሮ ደስ አስደርጎ የሚያስውል ማራኪ ምሽት አሳልፈን መጣን
ልዕል ሃይሌ ስላወኩህ ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር ያክብርልኝ።
መፅሃፍህን እንድንመርቅ ስለጋበዝከን
መልካሙን ሁሉ እመኝልሃለሁ። 🙏


ሚኪያስ ልየው (@Mykey21)

@Getem
በታገል ሰይፉ
ታገኝ አንደው ፈልግ


ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@getem
@getem