፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠
ተበላችሁ
~~~~~
"የበላና የተማረ ወድቆ አይወድቅም
በርታ ተማር" ብላችሁ
ያሳደጋችሁት ልጃችሁ
የብሂሉን ልክነት አረጋግጦ
ተምሮ ተምሮ ስልጣኑን ጨብጦ
'ውለታ ይመልሳል፣ ህዝብ ያገለግላል'
ብላችሁ እናንተ ምላሽ ስትጠብቁ
እውቀቱን መች አጣት አጅሬ ጥንቁቁ
ዞሮ የናንተኑ ሀብታችሁን ግጦ
የቀረውን ሸጦ
ቅርጥፍ አርጎ በላ የሀገር አደራ
ብላችሁት የለም አይወድቅም የበላ።
~~~~~~~~~~~~~~~
ከሜሮን ጌትነት
፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠
@getem_sourcebot
@getem
@getem
ተበላችሁ
~~~~~
"የበላና የተማረ ወድቆ አይወድቅም
በርታ ተማር" ብላችሁ
ያሳደጋችሁት ልጃችሁ
የብሂሉን ልክነት አረጋግጦ
ተምሮ ተምሮ ስልጣኑን ጨብጦ
'ውለታ ይመልሳል፣ ህዝብ ያገለግላል'
ብላችሁ እናንተ ምላሽ ስትጠብቁ
እውቀቱን መች አጣት አጅሬ ጥንቁቁ
ዞሮ የናንተኑ ሀብታችሁን ግጦ
የቀረውን ሸጦ
ቅርጥፍ አርጎ በላ የሀገር አደራ
ብላችሁት የለም አይወድቅም የበላ።
~~~~~~~~~~~~~~~
ከሜሮን ጌትነት
፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠
@getem_sourcebot
@getem
@getem
👍1
አብረን ስለታየን
ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አባትሽ አወጁ
ህጉን ለማስፈፀም
ታላቅ ወንድምሽም ጩቤ አይጠፋም ከጁ
እህትሽ ባንድ ጎን
አሳልፋ ሰጠች ነብሷን ለስለላ
ፍቅር አመፅ ሆነበት ቤተሰብሽ ሁላ።
ይህንን ባይ ሸሸሁ አንግሼሽ በልቤ
የሙት ፍቅረኛና የወንጀለኛ እህት እንዳትሆኚ አስቤ።
ወደ እስር ቤቱ ስንቅ
መቃብርጋ አበባ ስታመላልሺ
ከእንቡጥነት ነጥፈሽ ፍካት እንዳትረሺ
ስላንቺ ሸሸሁኝ በይ ስለኔ ሽሺ።
<<የገደለው ባልሽ
የሞተው ወንድምሽ
ሐዘንሽ ቅጥ አጣ።>>
የሚል አይነት ተረት ከደጅሽ ሳይመጣ
ፍቅራችን እንዲተርፍ ከጀግንነት ልውጣ።
(ፍቃዱ ጌታቸው)
@getem_sourcebot
@getem
@getem
ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አባትሽ አወጁ
ህጉን ለማስፈፀም
ታላቅ ወንድምሽም ጩቤ አይጠፋም ከጁ
እህትሽ ባንድ ጎን
አሳልፋ ሰጠች ነብሷን ለስለላ
ፍቅር አመፅ ሆነበት ቤተሰብሽ ሁላ።
ይህንን ባይ ሸሸሁ አንግሼሽ በልቤ
የሙት ፍቅረኛና የወንጀለኛ እህት እንዳትሆኚ አስቤ።
ወደ እስር ቤቱ ስንቅ
መቃብርጋ አበባ ስታመላልሺ
ከእንቡጥነት ነጥፈሽ ፍካት እንዳትረሺ
ስላንቺ ሸሸሁኝ በይ ስለኔ ሽሺ።
<<የገደለው ባልሽ
የሞተው ወንድምሽ
ሐዘንሽ ቅጥ አጣ።>>
የሚል አይነት ተረት ከደጅሽ ሳይመጣ
ፍቅራችን እንዲተርፍ ከጀግንነት ልውጣ።
(ፍቃዱ ጌታቸው)
@getem_sourcebot
@getem
@getem
ጥላ ቢሶች
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ረቂቅ መስታወት ነው ፣ የሰው ልጆች ገላ
ብርሀን ሲያርፍበት ፣ ሚያንፀባርቅ ጥላ።
።።።።።።።።
ሚያንፀባርቅ ጥላ ፣ ብርሀን ሲንቆረቆር
በፀሐይ መገለጥ ፣ የማይሸነቆር
ጥላውን ይመስላል ፣ ሰው የውስጡ መጥቆር።
።።።።።።
በፀሐይ መገለጥ ፣ ጨለማን አይገርዝም
ክፋቱን ያህላል ፣ ሰው ጥላው ሲረዝም።
።።።።።።።።
ሰው ጥላው ሲረዝም ፣ ፀሐይን ይቀብራል
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ ውጪ ጥላው ያጥራል
ውጭ ጥላው ሚያጥር ፣ የውስጡን ያበራል።
።።።።።
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ የተዘጉ ጋኖች
ጥላ ቢሶች ናቸው ፣ ሙሉ ብርሀኖች።
@getem_sourcebot
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ረቂቅ መስታወት ነው ፣ የሰው ልጆች ገላ
ብርሀን ሲያርፍበት ፣ ሚያንፀባርቅ ጥላ።
።።።።።።።።
ሚያንፀባርቅ ጥላ ፣ ብርሀን ሲንቆረቆር
በፀሐይ መገለጥ ፣ የማይሸነቆር
ጥላውን ይመስላል ፣ ሰው የውስጡ መጥቆር።
።።።።።።
በፀሐይ መገለጥ ፣ ጨለማን አይገርዝም
ክፋቱን ያህላል ፣ ሰው ጥላው ሲረዝም።
።።።።።።።።
ሰው ጥላው ሲረዝም ፣ ፀሐይን ይቀብራል
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ ውጪ ጥላው ያጥራል
ውጭ ጥላው ሚያጥር ፣ የውስጡን ያበራል።
።።።።።
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ የተዘጉ ጋኖች
ጥላ ቢሶች ናቸው ፣ ሙሉ ብርሀኖች።
@getem_sourcebot
@getem
@getem
@getem
፨፨ ፆም ፨፨
ሀበሻ በሙሉ ስራ ስለፈታ
ፍራንካውም ሳስቶ
ወና ቀርቶ ጎታ
እንዴት ጠግቦ በልቶ!
በምን ፆሙን ይፍታ?
እንጃ....
ወትሮ ካወደቀው ከጣለው ፍሪዳ
ሰርክ ከሚጋተው ከበረቱ ገንዳ
ስለ ነብሴ ብሎ ስጋውን የጎዳ
ዛሬ ተገላብጦ
የሆድ ተስፋው ሟጦ
ሙዝ እየተገፋ አናቱ ላይ ወጥቶ
ላሚቶቹ ነጥፈው አኩሪ አተር ጠጥቶ
እንጀራው በኖራ....በጀሶ ተቦክቶ
ልኳንዳ ሲኒማ ሜንጦ አይኑን ሰክቶ
መብል በሌለበት እንዴት ሰው ይፆማል?
አሽከር በሌለበት ገዢ ኬት ይመጣል?
ባልተሰጠ ምርጫ
ምን ተገኝቶ ብልጫ
የሚሆን ማምለጫ
የሚሆን መቀጫ
እንጃ......
የታሰረ አንጀቱን
ጎስቋላ ማጀቱን
ገና ፆም ....ፍልሠታ
ነነዌ ...ረመዳን
እያለ ማጣቱን ራቡን ከሚቆጥር
ባይፆም ለማይበላ
ጠኔያም የሆድ ...ቁ ጥር
መፆም እስኪያድለው በሞላ ገበታ
በፆሙ እየፆመ አብይ ፆሙን ይፍታ።
"በአብርሀም ተክሉ"
@getem
@getem
ሀበሻ በሙሉ ስራ ስለፈታ
ፍራንካውም ሳስቶ
ወና ቀርቶ ጎታ
እንዴት ጠግቦ በልቶ!
በምን ፆሙን ይፍታ?
እንጃ....
ወትሮ ካወደቀው ከጣለው ፍሪዳ
ሰርክ ከሚጋተው ከበረቱ ገንዳ
ስለ ነብሴ ብሎ ስጋውን የጎዳ
ዛሬ ተገላብጦ
የሆድ ተስፋው ሟጦ
ሙዝ እየተገፋ አናቱ ላይ ወጥቶ
ላሚቶቹ ነጥፈው አኩሪ አተር ጠጥቶ
እንጀራው በኖራ....በጀሶ ተቦክቶ
ልኳንዳ ሲኒማ ሜንጦ አይኑን ሰክቶ
መብል በሌለበት እንዴት ሰው ይፆማል?
አሽከር በሌለበት ገዢ ኬት ይመጣል?
ባልተሰጠ ምርጫ
ምን ተገኝቶ ብልጫ
የሚሆን ማምለጫ
የሚሆን መቀጫ
እንጃ......
የታሰረ አንጀቱን
ጎስቋላ ማጀቱን
ገና ፆም ....ፍልሠታ
ነነዌ ...ረመዳን
እያለ ማጣቱን ራቡን ከሚቆጥር
ባይፆም ለማይበላ
ጠኔያም የሆድ ...ቁ ጥር
መፆም እስኪያድለው በሞላ ገበታ
በፆሙ እየፆመ አብይ ፆሙን ይፍታ።
"በአብርሀም ተክሉ"
@getem
@getem
ወፍ አዳኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
" የሰማይ ወፎችን ፣ ተመልከቱ
አይዘሩ አያከማቹ ፣ አያጭዱ ጎተራ አይከቱ
ለመኖር ባይጨነቁም ፣አምላክ ግን በቸርነቱ
ሳይመግባቸው አያድርም ፣
እኔ ግን ወፍ አይደለሁም ፣ ከወፎች ኑሮ አልማርም
ካልዘራሁና ካላጨድኩ ፣ ካላከማቸው አልኖርም
በላቤ ጎጆ ካላቆምኩ ፣ በወፎች ጎጆ አላድርም
ቸርነቱን ተማምኜ ፣ እጅ እግሬን አላጣጥፍም
ከሰማይ መና ስጠብቅ ፣ ከምድር እርግማን አላልፍም።
በላቤ እንዳድር አዞኛል ፣
ካልሰራሁ መኖር የማልችል ፣ ከመኖር ጭንቀት የማልድን
ከሰማይ ወፎች እያየሁ
የቸርነቱን ስጠብቅ ፣ በርሀብ አይኔን ሳይከድን
ከምድር ቀስት ሰርቼ ፣ የሰማይ ወፎችን ላድን።
@getem_sourcebot
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
" የሰማይ ወፎችን ፣ ተመልከቱ
አይዘሩ አያከማቹ ፣ አያጭዱ ጎተራ አይከቱ
ለመኖር ባይጨነቁም ፣አምላክ ግን በቸርነቱ
ሳይመግባቸው አያድርም ፣
እኔ ግን ወፍ አይደለሁም ፣ ከወፎች ኑሮ አልማርም
ካልዘራሁና ካላጨድኩ ፣ ካላከማቸው አልኖርም
በላቤ ጎጆ ካላቆምኩ ፣ በወፎች ጎጆ አላድርም
ቸርነቱን ተማምኜ ፣ እጅ እግሬን አላጣጥፍም
ከሰማይ መና ስጠብቅ ፣ ከምድር እርግማን አላልፍም።
በላቤ እንዳድር አዞኛል ፣
ካልሰራሁ መኖር የማልችል ፣ ከመኖር ጭንቀት የማልድን
ከሰማይ ወፎች እያየሁ
የቸርነቱን ስጠብቅ ፣ በርሀብ አይኔን ሳይከድን
ከምድር ቀስት ሰርቼ ፣ የሰማይ ወፎችን ላድን።
@getem_sourcebot
@getem
@getem