ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
"ሚስቴ እና ሰበቧ!"
.
ለስጋዋ ስትኖር
-- ነፍሷን አሞኝታ
አገኘዃትና
-- ስትሳም ተኝታ
ምነው ምን በደልኩሽ?
-- ብዬ ስጠይቃት
እግሯ ስር ወድቄ
-- በእንባ ስማጸናት
እንደለመደችው
-- ሰበብ አዘጋጅታ
አንተ መስለኸኝ ነው
-- አለችኝ ተነስታ!

አቤኑ

@getem_sourcebot

@getem
@getem
እኔን


አፈሯ....
የሰጡትን ሁሉ ባግባቡ ሚያፈራ
አየሯ....
ከሁሉም ተስማምቶ ለኑሮ ሚደራ
ምድሯ....
አረንጓዴ መስህብ ጋራ ሸንተረሯ
ነበር የሚያውድ ከርቀት ጠረኗ
ምን ቢያውድ ጠረኗ ቢስማማ አየሯ
ያለ አብራኮቿ አያምር አይደላ



ልጆቿ ለበአድ ለነጭ አጎብድደው
ለተሻለ ህይወት መረገጥን ወደው
ሁሉን ነገር ገፈው እርቃኗን ቢያስቀሯት
ሀደኪ በንብርክክ ጀመረች መጣራት
ኑልኝ ቡቃዬቼ ብላ ስትጣራ
እመት ባይ ብታጣ ነጎየች ከምድሯ



ልጆቿን ፍለጋ ወገቧን ሸብ አርጋ
ምትሸምትበትን ዘንቢል አርጋ ጠጋ
ጎጆዋን ቆለፈች አብራካን ፍለጋ
ፍቅራቸው አናውዟት መስሏት አልጋ ባልጋ
እማ ጥላ ነጉዳ ቀዬውም ተከፋ
መኖሯ ነበረ የሚያደርገው ፈካ
የሚያደርገው ፋፋ



ግና ምን ያደርጋል
እንኳንስ ጠረኗ....
እንኳንስ አካሏ.....
ተናፍቆዋል ድምፃ
ሌላው ሁሉም ቀርቶ ሄሎ የምትለው
በመደበኛ ስልክ ጢሊው በምትለው


ምነው ሀደኪዬ? ድምፅሽ እንዲ ጠፋ
ንዳዱ አቃተሽ? ይህም ባንቺ ከፋ
አዪ ሀርሜ ኪያ...
በምድርሽማ ነበረችሽ ጎጆ ከንዳድ ማምለጫ
ገያም ስትወጪ ዘርጋ ምታደርጊያት ነበረችሽ ጥላ
ዛሬ ግን ፀሀዩ ጎመራ ሆኖብሽ
በብርሀኑ ፈንታ እሳት ሲተፋብሽ
ምነው ያቺ ጥላ ብታንዣብብሽ



ሀርሜ ኪያ ምነው ድምፅሽ ጥፍት አለ?
የውሀ ጥማቱ ባንቺ ላይ ሀየለ?
በምድርሽማ ነበረችሽ ኩሬ
ከቤትሽ ዝቅ ብሎ ከኮረብታው ግርጌ
ከርሱ ጨለፍ አርገሽ እግሮችሽን ታጥበሽ
እንዳልተሸከምሽው በእንስራሽ ሞልተሽ
ዛሬ ቀን ቢጨልም እርሱም ጨከነብሽ?



ንዳዱን ጥማቱን ርሀቡን ተቋቁመሽ
ፍሬን ስለማግኘት በጣም ተስፋ አድርገሽ
ፍቅር ባጀገነው ልባም ልብ ታግዘሽ
ጥቂት ማይል ሲቀርሽ ምነዋ ተሸነፍሽ?
ከሀሩር በረሀ ስለምን ተጋደምሽ?
ቀና በይ ሀደኪ ንቂ ሀርሜ ኪያ
ባብራክ አትጨክኝም እናውቃለን እኛ
እኔን ሀደኪዬ እኔን ሀርሜ ኪያ
ተሸንፈሽ ወደቅሽ ከዚህ ከበረሀ?
አዶተና ምነው ጊንጡም ጨከነብሽ
የንዳድ ላይ እባብ አስችሎት ነደፈሽ?


እኔን ሀደኪዬ....
እኔን ሀርሜኪያ....
ገላሽ አፈር ናፍቆት ቀረ በአዉላላ?
ሰው ዝር ከማይልበት ከሀሩሩ ስፍራ
ጅስምሽ ተንጋለለ ከዚያ ከበረሀ
እኔን ሀደኪዬ...
እኔን ሀርሜ ኪያ....




By @Nutabintislam

@getem_sourcebot

@getem
@getem
👍2
የሳቅሽብኝ ጊዜ የሳቅሽልኝ መስሎኝ
ልቤ ተንሸራቶ ከደጃፍሽ ቢገኝ
ሳትግደረደሪ ና ግባ በይልኝ፡፡

ከንቱ ብኩን ልቤ ከደጃፍሽ በር ስር
ቆሞ የሚያንኳኳው
ከራሴ ከሸሸ ከኔነት ከራቀ ስንት ዘመን አለው፡፡

ሰው አልባ እኔነቴ
ሠው መሆንን ንቆ ሠው መሆንን ጥሎ
ሰውነትን ገሎ
የሳቅሽበት ጊዜ የሳቅሽለት መስሎት
ዳግም እንደገና
ሠው መሆንን ቢሽት
እረፍት ላጣች ነፍሴ
በልብሽ ከተማ ጎጆአችን ቀልሰሽ
አዳኝ መልኣክ ሆነሽ
ሠው አርጊው መልሰሽ ፡፡

     Esuba ( koblayu)

@getem_sourcebot

@getem
@getem
ይኸ ይሻለኛል

------------------

መጣች
ቀረች
ሄደች
አረፈደች ብየ
ሁሌ ከምሳቀቅ
ይኸ ይሻለኛል

መጣች የለ
ሄደች
አረፈደች የለ
ቀረች
ብቻ
ይኸ ይሻለኛል

ከማደር ቆዝሞ
ከመዋል ተዳክሞ
ባፈቀረ መንፈስ
ከሆነው ተስፋ ቢስ

ይኸ ይሻለኛል
እራሴን ቀጥሬ
እራሴን ብጠብቅ
እራሴን ሰድጄ
እራሴን ብመልስ

ይኸ ይሻለኛል
እራሴ አረፋጅ ብሆን

እናም ተይው ቅሪ
ከተመቸሽ ኑሪ
ሂጅ አትመለሽ
አታረፍጂ ደግመሽ

ለኔ ይኸ ይሻለኛል።

@Soll B..AvA

@getem
@getem
👍1
የመፅሀፍ ምርቃት

376 የተሰኘው የግጥም መፅሐፍ
ታላላቅ ገጣሚያን እና የጥበብ ሰዎች በተገኙበት

ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ.ም . ከቀኑ 11:00 ላይ በብሄራዊ ትያትር አዳራሽ ይመረቃል።

እርሶም በዕለቱ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

@getem
@getem
፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠
ተበላችሁ
~~~~~
"የበላና የተማረ ወድቆ አይወድቅም
በርታ ተማር" ብላችሁ
ያሳደጋችሁት ልጃችሁ
የብሂሉን ልክነት አረጋግጦ
ተምሮ ተምሮ ስልጣኑን ጨብጦ
'ውለታ ይመልሳል፣ ህዝብ ያገለግላል'
ብላችሁ እናንተ ምላሽ ስትጠብቁ
እውቀቱን መች አጣት አጅሬ ጥንቁቁ
ዞሮ የናንተኑ ሀብታችሁን ግጦ
የቀረውን ሸጦ
ቅርጥፍ አርጎ በላ የሀገር አደራ
ብላችሁት የለም አይወድቅም የበላ።
~~~~~~~~~~~~~~~
ከሜሮን ጌትነት
፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠

@getem_sourcebot

@getem
@getem
👍1
#ሯ

ቢሸኝም ጭልፊቱ
ቢሄድም ሳሞራ
እርግብ መች ይመጣል
ተተኪው ኣሞራ


Ezana Mesfin

@getem_sourcebot

@getem
@getem
አብረን ስለታየን

ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አባትሽ አወጁ
ህጉን ለማስፈፀም
ታላቅ ወንድምሽም ጩቤ አይጠፋም ከጁ
እህትሽ ባንድ ጎን
አሳልፋ ሰጠች ነብሷን ለስለላ
ፍቅር አመፅ ሆነበት ቤተሰብሽ ሁላ።

ይህንን ባይ ሸሸሁ አንግሼሽ በልቤ
የሙት ፍቅረኛና የወንጀለኛ እህት እንዳትሆኚ አስቤ።

ወደ እስር ቤቱ ስንቅ
መቃብርጋ አበባ ስታመላልሺ
ከእንቡጥነት ነጥፈሽ ፍካት እንዳትረሺ
ስላንቺ ሸሸሁኝ በይ ስለኔ ሽሺ።

<<የገደለው ባልሽ
የሞተው ወንድምሽ
ሐዘንሽ ቅጥ አጣ።>>
የሚል አይነት ተረት ከደጅሽ ሳይመጣ
ፍቅራችን እንዲተርፍ ከጀግንነት ልውጣ።

(ፍቃዱ ጌታቸው)

@getem_sourcebot


@getem
@getem
ነቢል መሐሙድ ፡፡

ከነገሩ ሁሉ ሁሉም ነገር አልቆ ፣
መራራቅ ሲያይል ከመፋቀር ልቆ ፣
በስተመጨረሻም ካበቃም በኋላ እኔ እንዳለሁ አለሁ ፣
ከመኖር ምኞቴ ሁሉም ነገር አልቆ መኖር ጀምሬያለሁ ፣
አንቺን አገኛለሁ ሚል ተስፋ የለኝም ውዴ ሆይ ልናገር ፣
ህልሜ ሁሉ አልቋል ተስፋዬም እንደዛው ፍቅሬ ብቻ ሲቀር !!!

@getem_sourcebot

@getem
@getem
ሜሮን ጌትነት፣(ዙረት)


ቅጣት በበረከት
፠፠
"ለኃጥአን የመጣ . . . "
ነውና ተረቱ
ለኔ ከታዘዘው
ደርሶሃል ጥቂቱ
በል አንተም አትርሳኝ
ብድርህን መልስ
በረከት ሲያድሉህ
የድርሻዬን ቀንስ።
፠፠


@getem
@getem
@getem
"ወድያና ወዲህ"

እርስ በእርስ እጆቼ
ተጣልተው፣
ተጋጭተው በፈጠሩት ጩኸት፣
ብርታት ፣ ሞራል ብሎ
ሌላው ሲፈነጥዝ ሲደሰት ዋለበት፡፡


ቢኒያም ዋስይሁን

@getem_source


@getem
@getem
#እጎዳብሻለው
:
:
የሱነገርበቃኝባፍንጫዬ ይውጣ
ፍቅሩን በማለቴ ለምንስ ልቀጣ
ብለሽ የላክሺብኝ ወቀሳሽ ደርሶኛል
ካጠፋሁት አንፃር እንደውም ያንሰኛል።
ባፍንጫሽም ልውጣ ይበለኝ አምናለው
ግን ፍቅሬ ...
ከልብሽከወጣውእጎዳብሻለው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@Henokbirhanu


@getem
@getem
@getem
ጥላ ቢሶች
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ረቂቅ መስታወት ነው ፣ የሰው ልጆች ገላ
ብርሀን ሲያርፍበት ፣ ሚያንፀባርቅ ጥላ።
።።።።።።።።
ሚያንፀባርቅ ጥላ ፣ ብርሀን ሲንቆረቆር
በፀሐይ መገለጥ ፣ የማይሸነቆር
ጥላውን ይመስላል ፣ ሰው የውስጡ መጥቆር።
።።።።።።
በፀሐይ መገለጥ ፣ ጨለማን አይገርዝም
ክፋቱን ያህላል ፣ ሰው ጥላው ሲረዝም።
።።።።።።።።
ሰው ጥላው ሲረዝም ፣ ፀሐይን ይቀብራል
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ ውጪ ጥላው ያጥራል
ውጭ ጥላው ሚያጥር ፣ የውስጡን ያበራል።
።።።።።
ውስጡ ብርሀን ያለው ፣ የተዘጉ ጋኖች
ጥላ ቢሶች ናቸው ፣ ሙሉ ብርሀኖች።

@getem_sourcebot


@getem
@getem
@getem
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (☺️ልዑል☺️)
የመፅሀፍ ምርቃት

376 የተሰኘው የግጥም መፅሐፍ
ታላላቅ ገጣሚያን እና የጥበብ ሰዎች በተገኙበት

ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ.ም . ከቀኑ 11:00 ላይ በብሄራዊ ትያትር አዳራሽ ይመረቃል።

እርሶም በዕለቱ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

@getem
@getem
፨፨ ፆም ፨፨

ሀበሻ በሙሉ ስራ ስለፈታ
ፍራንካውም ሳስቶ
ወና ቀርቶ ጎታ
እንዴት ጠግቦ በልቶ!
በምን ፆሙን ይፍታ?
እንጃ....
ወትሮ ካወደቀው ከጣለው ፍሪዳ
ሰርክ ከሚጋተው ከበረቱ ገንዳ
ስለ ነብሴ ብሎ ስጋውን የጎዳ
ዛሬ ተገላብጦ
የሆድ ተስፋው ሟጦ
ሙዝ እየተገፋ አናቱ ላይ ወጥቶ
ላሚቶቹ ነጥፈው አኩሪ አተር ጠጥቶ
እንጀራው በኖራ....በጀሶ ተቦክቶ
ልኳንዳ ሲኒማ ሜንጦ አይኑን ሰክቶ
መብል በሌለበት እንዴት ሰው ይፆማል?
አሽከር በሌለበት ገዢ ኬት ይመጣል?
ባልተሰጠ ምርጫ
ምን ተገኝቶ ብልጫ
የሚሆን ማምለጫ
የሚሆን መቀጫ
እንጃ......
የታሰረ አንጀቱን
ጎስቋላ ማጀቱን
ገና ፆም ....ፍልሠታ
ነነዌ ...ረመዳን
እያለ ማጣቱን ራቡን ከሚቆጥር
ባይፆም ለማይበላ
ጠኔያም የሆድ ...ቁ ጥር
መፆም እስኪያድለው በሞላ ገበታ
በፆሙ እየፆመ አብይ ፆሙን ይፍታ።

"በአብርሀም ተክሉ"

@getem
@getem
ሀገረ የሠፋበት
ቀን የረዘመበት
እንደ ቀትር ቡና አለያ እንደ ጫት
መኖር ሱስ ሁኖበት
ዝም ብሎ የሚኖር
በቀን መሀል ሚዞር
ከርታታ ሰው አለ
ብየሽ አልነበረ

ያ' ሰው እኔ ነኝ (mintesnot)

@getem_sourcebot


@getem
@getem
ሺ ሰማንያ


መቼም ላንለያይ ገፃችን አንድ ሆኖ
ከአንድ እናት ተወልደን ደማችን ተቀድቶ
በግራና በቀኝ ጡቷን ምገን አድገን
ጭቃ አቡክተን ግድብ ሰርተን
ተደባድበን በአንድ በልተን
ፍቅራችን አይሎ ላንጣላ ምለን
እየኖርን ነበር ፍቅርን አስቀድመን
የቀን "ጎዶሎ" ነው እኛን የለያየን.......
:
:
:
:

እንጂ መች ተጣላን
አሁንም አንድ ነን....!!

ዳግማዊ በየትም (ዳግሮ)
@DagRo

@getem
@getem
ወዴት ልሂድ ?
( ናትናኤል ጌቱ)


አፍቅረው ሲገፉ
ባንኮኒ ፊት ቀርበው ፥ ድራፍት እየላፉ
በተጎዱት መጠን ፥ ካሳ እንዲሆናቸው
ካሳ ቢራ መሀል ፥ ሲደበቅ ፊታቸው
እኔ ያንቺ ምስኪን ፥ አያጣኝ ሰቀቀን
ወዴት ሂጄ ልርሳሽ?
ገና ከጅምሩ ፥ መጠጥ ቤት ተዋውቀን


@getem_sourcebot

@getem
@getem
ወፍ አዳኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
" የሰማይ ወፎችን ፣ ተመልከቱ
አይዘሩ አያከማቹ ፣ አያጭዱ ጎተራ አይከቱ
ለመኖር ባይጨነቁም ፣አምላክ ግን በቸርነቱ
ሳይመግባቸው አያድርም ፣
እኔ ግን ወፍ አይደለሁም ፣ ከወፎች ኑሮ አልማርም
ካልዘራሁና ካላጨድኩ ፣ ካላከማቸው አልኖርም
በላቤ ጎጆ ካላቆምኩ ፣ በወፎች ጎጆ አላድርም
ቸርነቱን ተማምኜ ፣ እጅ እግሬን አላጣጥፍም
ከሰማይ መና ስጠብቅ ፣ ከምድር እርግማን አላልፍም።
በላቤ እንዳድር አዞኛል ፣
ካልሰራሁ መኖር የማልችል ፣ ከመኖር ጭንቀት የማልድን
ከሰማይ ወፎች እያየሁ
የቸርነቱን ስጠብቅ ፣ በርሀብ አይኔን ሳይከድን
ከምድር ቀስት ሰርቼ ፣ የሰማይ ወፎችን ላድን።
@getem_sourcebot


@getem
@getem
🌈🌈ውድ ሀበሾች🌈🌈

የማታ ጀምበር

ካንዱ ቤት ወደአንዱ በጣራው ተራምዳ፡
የጋራውን አናት እየነካች ሄዳ፡
እዩት ከስር ጥላው፡
የማይደርስበትን፡
እዩት ሰውን ጥላው፡
ሲለፋ ሲባክን፡፡

❤️❤️ገብረ ክርስቶስ ደስታ❤️❤️

@getem
@beckyalexander