ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
——————
መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ!
አምባ ወጥቼ እኩለ-ሌት ፤ ስለት ገብቼ በስሟ
ከርሞ ሰይጣን በሷ አስቶኝ፤ ልገላገል ከህመሟ
ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ፤ ደጋግሜ፤ ማህሌት ቆሜ
ሆዴ ቃትቶ ባር ባር ብሎ፤እርቃኔን ከሷ ታድሜ
ደጀ ሰላሟን በአራት እግር፤ ተንበርክኬ ተሳልሜ
በስጋዬ እሚነደውን፤ በጸሎት ላቤ አጣጥሜ
እፎይ ብዬ አመስግኜ፤ ውዳሴዋን ደጋግሜ…
ገና ከደጅዋ እልፍ ሳልል፤ ደሞ ይምጣ የቁም ህልሜ?
ሌት በጥምቀቷ የነጣው፤ ነጋ፤ ደፈረሰ ደሜ።
ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘልኝ፤ አዬ የስለት አታምጣ!
በውጣ ውረድ በጠበል፤ ባሣር ወዜ ቢገረጣ
ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ፤ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ!

@getem
@getem
@lula_al_greeko
#እኔና_ቤቴ
.
በእንባ ለማራጨት ፥ ቀልድ መቼ ጠፋ?
ከእሬት የመረረ ፥ ከእናት ሞት የከፋ።
.
እንቀልድ ካልንማ ፥ ብዙ አለ ቁምነገር
በሳቅ አንከትክቶ ፥ ጥሎ 'ሚያንፈራፍር።
.
ጠላው በጋን ሞልቷል፥ ምንጭ ውሃም አላጣን
ይሁን ብለን አለን ፥፥ ቅ..ራ..ሪ እየጠጣን ።፡
--------------------------//--------------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@lula_al_greeko
#ሊያባብ_ነው_መሰለኝ
:
ሳይሰምርልኝ ቀርቶ ሳያፈራም ቢቀር
ከዐመታት በፊት ዘር ዘርቼ ነበር።
:
ለዚያውም ምርጥ ዘር ....
...ከእውነት ፍሬ ማህፀን በእውነት ተረግዞ
...ደርሶ የተወለደ ብዙ ተወዝውዞ።
:
ምንም እንኳ ያኔ እውነት ቢያጅበውም
ከዘራሁት ዘር ግን ፍሬ አላገኘውም።
:
በዚም የተነሳ ስላጣሁት ፍሬ
ውስጤ ደምቶ ነበር እየው እስከዛሬ።
:
ዛሬ ግን ቀን ቆጥሮ ለድካሜ ዋጋ
እውነት ጀንበሪቷን ወደኔ ሊያነጋ
ተስፋ አትቁረጥ ብሎ ቡቃያን አሳየኝ
ያኔ የዘራውት ዘር ሊያብብ ነው መሰለኝ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
አስተያየቶን @Henokbirhanu
@getem
@getem
//ባክህ ቶሎ ይምጣ// (፪)
(ስምረት አበበ)

ልጅ የአባቱን መምጣት ስለምን ይጠላል
ደም ያስተሳሰረው ገመድ መች ይላላል
ከነሀጢያቴ ወዶ ልጁ ካደረገኝ
ምንም ሳልሰራለት ጽድቁን ከሸለመኝ
ሸክላ ሰሪው እርሱ እኔን ሸክላ ወዶ
ሀጢያቴን ካነፃ በመስቀል ጠርቆ
እኔ ማን ሆንኩና እርሱን የማርመው
ሲሳሳት አላውቅም ሁሌም ትክክል ነው
በሱ ጽድቅ ሙሉነት አልጠራጠርም
የኔን ጨምር ብዬ የሱን አላጎድፍም
ጊዜው ቢረዝም ቢያጥር መምጫው የወዳጄ
ሁሌም ናፍቃለው እስካየው በደጄ!
[ማራናታ]
(ለእዮብ እና ማርያማዊት ግጥም የተሰጠ ምላሽ 😍😍)

@getem
@getem
@poemmedia
''አንቺነትሽ''

ያማረ ገላሽ ውብ ፊትሽ
አይደለም ያሸነፈኝ
ያንበረከከኝ ።

ይልቁንም እቴ
በምርጫ የሰራሺው ስብዕናሽ
አመለካከከትሽ እና ምግባርሽ
ትህትናሽ: ቀናነትሽ እና ቁም ነገርሽ

በምከንያት በጥበብ; በጥልቅ መረዳት
የገነባሺው ማንነት ።
ሺ እጥፍ በልጦ ከደማቁ ውበት
ስንቱን ድንቅ ካሰኘ ደም ግባት
አንቺነትሽ ረታኝ
አሸነፈኝ ።

እቴ
የሴትነት ትርጉሙ አንቺ ነሽ
ከዳሌ እና ጡትሽ
ከከንፈር እና ጥርስሸ
ከአይንሽ እና ቅንድቦችሽ
ካማረው ገላሽ
ከውቡ ፊትሽ
.
.
.
.

በልጠሽ የተገኘሸ
ተፃፈ በቴድሮስ ገ.አብዝጊ በላይ

@getem
@getem
የተዘበራረቀን ማዘባረቅ(ልዑል ሀይሌ)
.
(እንዴት ነህ ካልሺኝ
ይመስገነው እንዲህ ነኝ)
.
ሳልምሽ ሌቱ መሸ
ሳስብሽ ቀኑ ነጋ
ስራብሽ ውሃ አጥቼ
ስጠማሽ ጉርሻ ጠፋ
.
ጆሮዬ ተለጉሞ
ቃል ማውጣት እያቃተው
አፌ መስማቱን ረሳ
ፍቅርሽ አቅሌን እያሳተው
.
(እንዴት ነህ ካልሺኝ
ይመስገነው እንዲህ ነኝ)
.
ጫማ ቁጥርሽን ከኮቴሽ
ለማንበብ እየተጣጣርኩ
ከርቀት በምታልፊበት
ሀሳብ ህልምሽን እየሳልኩ
የምራብሽ ጥጋበኛ
የምፆምሽ ፆም ገዳፊ
ምናል ደህንነቴን ባትጠይቂኝ
ምናል ብኖርበት ብታርፊ
.
(እንዴት ነህ ካልሺኝ ግን
ይመስገነው እንዲህ ነኝ)
.
እራቴን በጠራራ ፀሐይ በልቼ
ቀን ላልምሽ ማንቀላፋ
በድቅድቅ ጨለማ ምሳ በልቼ
አንቺን ላገኝ
ከጨረቃ ከዋክብቱ የምጋፋ
.
እኔ እንዲህ ነኝ
.
ነይ
አዘባርቂው ንግግሬን
ነይ
ውሎዬን አበላሺው
.
የተዘባረቀን ማዘባረቅ
ማስተካከል እንደሆነ እንዳትረሺው
.
ነይ!
(እንዴት ነህ ካልሺኝ ግን
ይመስገነው እንዲህ ነኝ)
17-09-10

@getem
@getem
@lula_al_greeko
🔥1
//ምስኪኗ//


ማሬ ነሽ እያለ
ልብ እያማለለ
ማሬ ነሽ ሲያበዛ
በፍቅሩ ደንዝዛ
በምላሱ ፈዝዛ

በሰው አገር ሆና
በሃሳብ መንምና

አገሩ ቁጭ ብሎ
ለሷ ያዘነ መስሎ
መቼ! ትመጫለሽ?
ምን! ትፈልጊያለሽ?
ብሩን ልያዝልሽ
መሬትም ልግዛልሽ
እያለ ሲሞላት
ሃቅ እየመሰላት
ስትልክ ስትሰጠው

እሷ በሰው አገር
በጣም ስትቸገር
ያልፍልኛል ብላ
ሃሳብ በሱ ጥላ

ያላትን ሳትሳሳ
ልካለት ጨርሳ
ጨራርሳ ስትወጣ
ወደአገር ስትመጣ

ያመነችው ወጣት
እሷን የጠበቃት
ለለፋችው ልፋት
ምንም ሳይገዛላት

እቃም ባይገዛላት
ገንዘቧን ባይሰጣት
ታማኝ በሆነላት!

እሱ ሌላ ይዞ
በሱሱ ደንዝዞ
ማሬ መሬት ቀርቶ
እሱ የልቡን ሰርቶ
አሷን አንከራቶ
ባዶ አስቅርቶ።

ምስኪኗ እህታችን!
ይህን ሁሉ ለፍታ
ወደ አገሯ ገብታ

ድካሟን ሳትረሳ
ያለውን አበሳ
ወጣች ተመልሳ

@getem
@getem
@fuadmeansheart
👍1
ምን አይነት ቄስ ናቸው ፣ ምፀት የለመዱ
"አባት ይፍቱኝ" ስል
"አብይ ይፍታህ "ብለው ፣ አሳልመውኝ ሔዱ
።።።።።
ዳሩ እውነት አላቸው ፣ ቀልዳቸው ቢመርም
ምህረት ያውቃልና
እኛ ብናጠፋም ፣ አምላክ ሰው አያስርም።

(( በላይ በቀለ ወያ ))

@getem
@getem
@lula_al_greeko
🔥1
Birhanu Henok:
#ይታየኛል
:
:
ሴት ከሆን ማናግር ስልክ ተደውሎ
አናትሽ ላይ ወቶ የሆነ ዛር ዘሎ
ምትደውለው ማናት?
የት ነውስ ምታውቃት?
ደርሶ ቁጥርክን ለምንስ ሰጠሀት?
አምጣው ስልኩን በቃ!! እንደውም ላዋራት!!
ሁሌ ባልሺኝ ቁጥር አላማርርሽም
አሁንስ ሰለቸሺኝ መቼም አልልሽም።
:
:
ሁለታችን ሆነን ስናቀና መንገድ
በፊት ከማታውቂያት ወይ ወዳጅ ወይ ዘመድ
ድንገት ስንገናኝ ከሁሉ አስቀድመሽ
እኔ ባለቤቱ አንቺ ግን ምኑ ነሽ?
ባልሺም ጊዜ ከቶ አልነደድኩብሽም
ለሰው ይምሰል እንጂ ለኔ ግን በፍፁም ጨቅጫቃ አይደለሽም።
:
:
ስልኬን ስትነካኪ ካየሽ የሴት ፎቶ
ቁጣሽ ግሎ ንሮ ወዲያው ደምሽ ፈልቶ
ባይንሽ ቂጥ እያየሽ የጥያቄ ውርጅብኝ
ገና አንዱን ሳልመልስ ስላዘነብሺብኝ
ጭራሽ አይከፋኝም
አዎንታዊነቱ እኔን አይጠፋኝም።
:
:
እቤታችን ሆነን ተቃቅፈን በደስታ
እየተሳሳቅን ፊልም ያየንም ለታ
አንዲቷን ተዋናይት እንደው ሳላስበው
ያልኩሽ እንደሆነ በጣም ነው ምታምረው
ከባጡም ከቆጡም ሰበቦች ደርድረሽ
እየገላመጥሺኝ ቻናሉን ቀይረሽ
ሌላ ሌላ ነገር ስትከፍቺብኝም
ጨቅጫቃነት መስሎ እኔን አይሰማኝም።
:
:
አንዳች ጉዳይ ገጥሞኝ
ከደጅ ውዬ ማታ እቤቴ ስመጣ
እየቀየጥሺብኝ ሰላምታና ቁጣ
ከማን ጋር የት ገብተክ ከማን ጋር የት ወጣ
ከማን ጋራ ምን በልተ ምንስ ደግሞ ጠጣ
ብለሺኛል ብዬ አልበሳጭ እኔ
የልብሽ ነው እንጂ የአፍሽ ለምኔ።
:
:
የሚገርመው ነገር ...
ዘንድሮ ሰው ሁሉ የት ገባ የት ወጣ ጭቅጭቅ መስሎታል
"ቅናት" ካሉት ቅኔ ሰሙን ብቻ አንግቦ ወርቁን ዘንግቶታል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ ...
ገብቶኛል ድብቁ
ጌጥ ሆኖኛል ወርቁ።
:
:
እንዲ አረግሺኝ ብዬ እንዲያም አልሺኝ ብዬ
አላፈገፍግም ፍቅራችንን ጥዬ።
:
:
እንደውም የኔ ውድ
በየቀኑ ቅኚ በየቀኑ በዪኝ እጅግ ደስ ይለኛል
ከቅናትሽ ጀርባ ፍቅርሽ ይታየኛል
"ቅናት" ሚሉት ቅኔ ወርቁ በርቶልኛል።

#ሄኖክ_ብርሃኑ

ለአስተያየቶ
@henokbirhanu

@getem
@getem
@getem
👍1
ከጥንት ጀምሮ ~ስናየው የኖርነው
ሲቃጠል የሚስቅ ~ዘወትር እሳት ነው ።
_____(ገሞራው )__________
"እንደ ማሽላ እየሳቅን ያለበት ሁኔታ ነው እያየን ያለነው "
/እሱባለው /


@getem
@getem
😂😜😜
የግንቦት ሀያ በአል አቀባበር እንዴት ነው?

በሬው
@wegoch
@wegoch
@getem
ለእዮብ ዘማርያም
እና
ስምረት


ብዙ ከዘገየህ ቀርተሀል
ብየ አለምን እንዳላይ፣
ቶሎም መጠህብኝ ፍኖስ ሳላበራ
በጨለመ ሰማይ፣

ከምታስጨንቀኝ ከምታሸብረኝ
ፋኖስን ፍለጋ ከምታራሩጠኝ

እባክህን አምላክ ከዚህ ሁላ ጣጣ
በንስሀ ፀሎት እራሴን ሳልቀጣ
ብዙም እንዳዘገይ ቶሎም እንዳትመጣ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
..

ከፍቶህ ተጎሳቁለህ
እያዩ እንዳላዩህ
ባላየ ዝም እሚሉህ

አልበቃ ሲላቸው.....

እንዲህ ነው እንዲህ ናት
እያሉ በኩራት
በራሳቸው ችሎት
ተከሳሽ በሌለበት
ፍርድ ከመስጠት

ምነው?.....

ያንተን ኑሮ ኖረው
በተጓዙሉህ ጉዞህ
እያንዷንዷ እርምጃህ
የዘወትር ስሜትህ
አድምጠው ተረድተው
አንተን መስለው
አንተን ሆነው
በፈረድብህ ።
...



Tedros g. Belay

@getem
@getem
...እኔ...

ላንች ያለኝ ፍቅር
እንደ ስጋ ምኞት
እንደጌታ ታምር
ሺመሽም ሲነጋም
አድሮ የሚጨምር።

(ግጥም እዎዳለው)

@getem
@getem
#በዕውቀቱ_ሥዩም

ወደ ምንም የሚያደርስው መንገድ

ቸኳይ የሚመስለው
ፈጣን የሚመስለው
በውልውል መኪና
በፋሺን መጫምያ
ወይም በባዶ እግሩ
ሸው እልም የሚለው
ይሄ ሁሉ ምሁር ይሄ ሁሉ ማይም
መንገዱን የሞላው ከታችም ከላይም
ሲመላለስ እንጂ ሲደርስ አይታይም፡፡

@getem
@getem
@lula_al_greeko
               "ውበት እና አፍንጫ"

   የሾለ አፍንጫሽ ውብ ነው የተባለው
   የውበት መለኪያ የአፍንጫ መሰልከክ
   ሆኖ እንዳይመስልሽ
   ይልቅስ ደፍጣጣው ሰልካካ እንድትባይ
      እድል ፈጠረልሽ
 
      ሰልካካ አፍንጫ
    ከደፍጣጣው አንፃር ተመዝኖ የመጣ
    የውበት መግለጫ
    መሆኑን ዘንግተሽ
    ውበት መሰልከክ ነው እያልሽ ባገሩ ትመፃደቂያለሽ

     ረስተሽው አንጂ
     ሰልካካ አፍንጫ
     ደፍጣጣ አፍንጫ
      ምንም ተነፃፅረው (አንዱ ከአንዱ በልጦ)
      ውበትን መለኪያ ማሳያ ቢሆኑ
      ሁለቱም ሲነኩ የሚወጣው ነገር አንድ አይነት መሆኑ
      
        ከ ዮሴፍ ግርማ ወርቅነህ
          @getem
          @Wegoch


  
  
አንችን የሳምኩለት
( © #እሱባለው_ኢትዮጵያዊ )

ገነት እንደገባሁ ~ ልቤ ተደስቶ
ሀጥያተኛ ሲማር ~ ሲኦልም ተከፍቶ
ክዋክብት በሀሴት~ ከሰማይ ሲረግፉ
ተራሮች ተንደው ~ ምድር ሲነጠፉ
ደራሲያን ሁሉ ~ ስላንቺ ሲፅፉ


ስደተኛ ሁሉ ~ እቤት ተመልሶ
ጤና የነሳቸው ~ ሁሉም ተፈውሶ
ስራ ፈላጊዎች ~ አግኝተው እንጀራ
እናት በልጆቿ ~ በልቧ ስትኮራ
በሰልፍ የሰለቹት
ታክሲ ጠባቂዎች ~ መኪና ሲገዙ
አበዳሪ ሀገራት~ እዳ ሲሰርዙ
መንግሥት ያሰረውን ~ በምህረት ሲፈታ
ሀሳብ አሸንፎ ~ ጥይትን ሲረታ
ጎዳና እሚተኛው~ ቪላ ተሸልሞ
ብሄርተኛው ሁሉ~ ባንድነቱ ቆሞ


ፍጡራን በሙሉ
በደስታ ሲሞሉ

በረሃዉ ለምልሞ~ በአበቦች ይደምቃል
አራዊት በፊናው~ በፍቅር ይስቃል
የምመኘው ሁሉ ~ ሆኖ ይታየኛል
አንቺን የሳምኩለት ~ እንዲህ ያደርገኛል ።
______ ዛሬ |2010_______

@getem
@getem
@lula_al_greeko
🤩1
ስዕል ሙዚቃ ነው


በእርሳስ ተጭሮ ቀለም የተቀባ
ለነፍስ የቀረበ
ከሩቅ የሚያደምጡት ልብን የሚያባባ
ስዕል ሙዚቃ ነው

በነጠብጣብ ልቀት፡ስንኝ ተደርድሮ
በቡሩሽ የሚዜም፡በሀሳብ ገመድ ታስሮ
ስዕል ሙዚቃ ነው

በቀለማት ቅኝት በአርምሞ ሚደመጥ
ሲያሻው
የሚያስጨፍር ጮቤ የሚያስረግጥ

……ሰለሞን ጠቢቡ

@getem
@getem
@AmharicTreka
በትግል የተገኘ ውበት
(በላይ በቀለ ወያኔ)
.
.
ባሩድ ባሩድ የሚል ፣ የገላሽ መአዛ
ዜና ዜና ሚሸት ፣ ያንደበትሽ ለዛ
እንደ እግረኛ ጦር...
የተደረደረው ፣ የሚማርክ ጥርስሽ
እንደ ሻብያ ጦር...
የሚንቀጠቀጠው ፣ ዳሌሽ እና ጡትሽ
ስልጣን ስልጣን የሚል ...
ቢስሙት ማይሰለች ፣ የስስ ከንፈርሽ ጣ'ም
ይህ ሁሉ ውበትሽ ፣ ሚናፍቀው በጣም
በፅኑ ትግል እንጂ ፣ በተፈጥሮ አልመጣም

@getem
@getem
@lula_al_greeko
😁1
 በ አገኘሁ አሰግድ

“ ያስለቅሳል እንጂ ይህስ አያሳቅም
ግንድ ተደግፎ ዝንጀሮ ጫት ሲቅም”
(አማርኛ እንዳበጁሽ አትበጂም)

@getem
@getem
#አለማማር_ማማር
:
:
ገጣሚው በግጥሙ ገና ከምርጊቱ
ውበትን ያደንቃል
ወረቀት ብዕሩም የቆንጆን ሴት ፀዳል
እልፍ ያንፀባርቃል።
:
:
አንደኛው ገጣሚ:
:
:
ዐይኖችሽን አይተው ኮከቦች አፈሩ
ድንቄም ብርሃን ሆንን ብለው ተናገሩ።
ፀሀይዋም ጠለቀች ባለችበት ቦታ
አንቺን ብታይ ጊዜ ተደናግራ ፈርታ።
እውነት እልሻለው ምዬ በዚ ሰማይ
ጨረቃም ሻማ ናት ካንቺ አንፃር ስትታይ።
እያለ ይገጥማል እያለ ይፅፋል
ቃላትን መልምሎ ውበትን ያጎርፋል
ሰማይ ጠቀስ ግጥሙን በቀለም ይነድፋል።
:
:
ሌላኛው ገጣሚም:
:
:
ገና ከሩቅ ሳይሽ ይድናል ህመሜ
ብሞትም አይቆጨኝ ከንፈርሽን ስሜ።
ባለንጋ ጣቶችሽ የዳበስሺኝ እንደው
እንደ ቶን እሳት ነው ውስጠቴ ሚነደው።
ዳሌሽ እየኮራ ባትሽ ላይ ሲሳለቅ
እኮሰምናለው እንደመታው መብረቅ።
ወገብሽ ሲል ዘመም ጥርስሽ ሲገለጥ
ነግቶ ይመሽብኛል ምራቄን ስውጥ።
እያለ ይገጥማል እያለ ይፅፋል
መልዕቁን ዘርግቶ ቁንጅናን ይቀዝፋል
ዘንድሮስ ገጣሚው በውበት ተለክፏል።
:
:
አቤት ጊዜው ከፋ አቤት ጥበብ ከፋ
ለመልከ ጥፉ ሴት የሚገጥም ጠፋ።
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ባንድ አሳብ ታጠረ
መልከ ጥፉነትም ግጥም ሳይሆን ቀረ።
:
:
ይህን ተመልክቶ ይህን ዐይቶ ኖሮ
ሌላም ሰው እንዲለምድ
ለመልከ ጥፉ ሴት ግጥምን በመፃፍ
እስኪ እኔው ፈር ልቅደድ።
:
:
ያ ገጣጣው ጥርስሽ የኔ ጥርስ ቢሆን
ምነኛ ታደልኩኝ
ያለምንም ችግር አጥንት እንደ ስጋ ስለሚቆርጥልኝ።
ብይ ሚያክሉትን እነዚያን ዐይኖችሽ ያየዋቸው እንደው
ምን እንዶን ባላውቅም አንድ ስሜት አለ ልቤን የሚርደው።
ከእጥረቱ የተነሳ አልያዝም ብሎሽ
ፀጉርሽ ሲፈታ
ያንን ያየው ጊዜ ከቃላት በላይ ነው የሚሰማኝ ደስታ።
የከናፍሮችሽ ትልቅ ዳቦ ማከል
በውነት ይገርመኛል
የራበኝ እንደሆን ሄደ ግመጣቸው
ብሎም ያሰኘኛል።
እያልለኩኝ ገጥማለው እያልኩኝ ፅፋለው
የመልከ ጥፉን ሴት ውበት አገዝፋለው
አለማማር ማማር እንደሆነም ነድፋለው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
ለአስተያየቶ @Henokbirhanu

@getem
@getem