ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ቀጥረሽኝ....
ፈላስፋ አደረግሽኝ(ርእሱ ነው)
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፣።።፣።፣
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!

@getem
@getem
@lula_al_greeko
ስወድሽ ውደጂኝ
(Dakstar)


ውዴ.....
እኔ አንቺን መውደዴ
መጥፎ እድል አይደለም ችግር የሚያመጣ
ወንጀልም አይደለም በህግ የሚያስቀጣ
ሀጢያትም አይደለም አንገት የሚያስደፋ
ሰማይ ቤት አትቆምም ነብሴ ተጠይቃ-ትዕዛዝ ተላልፋ
ታድያ አንቺን መውደዴ ምን ላይ ነው ጥፋቱ?

ወደድኩሽ ማለቴስ ምንድነዉ ክፋቱ?
ጠልተሺኝ እንዳይሆን ቁርጡን እንዳላውቀው
እንደምትወጂኝ ነው ውስጥሽ 'ሚያሳብቀው።
ታድያ እየተዋደድን አንድ ሆኖ ውስጣችን
ለምን እንራራቅ እንሁን ለብቻችን

ስለዚህ ውድዬ.......
ባንቺ ጨርቅ ሳልጥል ወይ ሳታሳብጂኝ
በፍፁም ተማምነን ሳልከዳሽ ሳትከጂኝ
-- ሳልጎዳሽ ሳትጎጂኝ
መራራቁን ትተሽ ስወድሽ ውደጂኝ

@Dakstar5🎭
@getem
@getem
ሀገሬ ነው

ሀገሬ ነው ይላል ሀገሩን ድሮ
አባቱ የሰጠውን ጥሎታል ዘንድሮ
ታድያ ለምንድነው ሀገሬ ነው የሚለው
ሀገር ሳይኖረው ሀገሬ ነው ያለው
እቴም ስልጣኔ ወጉ ያላማረ
የራሱን ሳያቅ የሰው እየተማረ
እቴም እድገት አምጪ
ለራሷ ሳትሆን ለሰው ተንጫጪ
ሀገሬ ነው ይላል የሰው አድማቂ
የራሱን ክዶ የሰው ናፋቂ


DaDa Coffee


@getem
@getem
//ቶሎ አትምጣ//
በማሪያማዊት

የትኛው ፅድቄ ነው የቱ መልካም ስራ
እባክ ቶሎ ና ብሎ የሚያስጠራ
ግብሬ ካላማረ ስራዬ ከከፋ
የስም አመኔታ በውስጤ ቢሰፋ
ትዛስህን ከጣስኩ በአደባባይ ቆሜ
ውስጥህን ከሰበርኩ ክፋትን ሰንቄ
ልቦና እንድትሰጠኝ ጥፋቴን አውቄ
ልፀልይ ወዳንተ ተፀጽቼ በእንባ
እባክህ አትምጣ ንሰሀ እስክገባ

ማርያማዊት
(እዬብ ዘ ማርያምን ደግፌ ነው)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
---እንቆቅልሽ ---


አንድ ሰው ተራበ
እጆቹን ታጠበ
መዓድ አቀረበ
የገበታው ዓይነት መዓዛው ቢያውድም
ለተራበ ስጋው ያቀረበው ሁሉ ምን በቂ ቢሆንም
ዕትኡ በሰላም እስኪባል አልበላም

እንቆቅልሽ
ሌላውም ተርቦ
እጆቹን ተጣጥቦ
ማዕዱን አቅርቦ
ካማረ ገበታው ካረደው ፍሪዳ ከጠላ ከጠጁ
ሊጠጣ ሊበላ ቢዘረጋም እጁ
ፍላጎት ግን ከዳው
በድኑን አስቀምጦ መንፈሱ ግዜ አጣ ሐሳብ
አነጎድው

እንቆቅልሽ
አንድም ከዚ አለ
ተርቦ የዋለ
ምን ርሃብ ቢሰማው ቢጨማደድ ፊቱ
ምን  ቢጮህም ወስፋቱ
እጁን አይታጠብ
ማዕዱን አያቀርብ
ጥግ ይዞ ተቀምጧል
በደከሙ  ዓይኖቹ ህዝቡን ያማትራል

እንቆቅልሽ
አማኝ ነብሱን ብሎ
ሐብታሙ ሲጨነቅ
ድሃው ግን በማጣት
ሶስት ሰወች ተራቡ  ዓለም እንደዚ ናት
እንቆቅልሽ ህይወት እንቆቅልሽ ዓለም
ከጥያቄ በቀር ምን ጊዜም መልስ የለም!!!!!!!

(((ሳሚ ዘ-ሖኅተ)))

@getem
@getem
(((በላይ በቀለ ወያ )))
በአዲስ የ ግጥም መድብል


"እልፍ " ላሉት እልፍ
እልል ላሉት ክንፍ
በምታድል ሀገር
ከባሻገር ወዲያ ፣ አለና ባሻገር
ድልድይ ሆኖ ያልፋል
ሌሎችን አሻግሮ ፣ ራሱ 'ማይሻገር ።

እነሆ በቅርቡ መጣሁ ብሎ ልኮብናል ገጣሚው
@getem
@getem
ብርድ የሰራው ወበቅ

ያው እንደምታውቂው
ዝናቡን ጠብቆ ጠፋብን መብራቱ
ነይ እስቲ እቀፊኝ
ብርድና ጨለማ እኔ አልወድም እቱ።

ብሎ አቀፋትና
ግላዊ እሳቱን ከጭኗ ለኮሰ
ደረቱ ላይ ቀልጣ
ከደረቷ በታች ፀሐይ ተፀነሰ።

የለኮሰው እሳት
በብርድ አመካኝቶ በፀሐይ ቀጠለ
ነደዱ እንደ እቶን ፍቅር ተቃጠለ።

በአንድ ፀሐይ ቀን
ሆዷን አሳየችው ታዘበ እንደገፋ
በቅፅበት በረደው
እሳታዊ አቅሙ ተሰለበ ጠፋ።
ቀስስ እያለ ራቃት
ብዙ ተከትላው ተጋባባት ብርዱ
ሁለት በረዶዎች
ጨለማ ላይ ጭረው ፀሐይ ልጅ ወለዱ።

ጨቅላ ሙቀት አዝሎ ጡቷ ስር ይስቃል
ማን ያውቃል
ለፍቅር ወግ ሳይደርስ
አባቴን ያለቀን በታሪክ ይጠልቃል
ካባቱ አስተያይቶ
ያፍላነቱን ሙቀት በለጋው ይንቃል
አሁን ግን ለጊዜው
በረዶ ታቅፎት በምቾት ይስቃል።
ፈገገገገግ
ወገገገገግ
ቦገገገገግ
ጨለማ የወለደው የብርሐን ሐረግ።

(ታምራት ሚሊዎን)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
1👍1
#ቡና_አማረኝ_ብትይ ...

ደክሞኝ ቢሆን እንኳን
መች እኔ ሰንፋለሁ
ብቻ አንቺ ከቆላሽ
ለመውቀጡ አለሁ

ኢዛና
@getem
@getem
@lula_al_greeko
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ግንቦት ፲፭ በብሄራዊ ቲያትር የተሳካ ምሽት አሳለፍን "ንባብ ለሂወት" በሚል መሪ ቃል ፕሮግራሙን በነፃ ላዘጋቹልን ለብሄራዊ ቤተመፅሃፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ ምስጋናችን የላቀ ነው። 🙏🙏🙏
Tsegaye Gebre-Medhin - "Abren Zim Inebel/አብረን ዝም እንበል"
~ አብረን ዝምም እንበለ ~

ጸጋዬ ገ/መድህን

@getem
@getem
~~~ ጠላቴን ስመርቅ  ~~~~

በስልጣን ከፍ ከፍ
በዝና ከፍ ከፍ
በሀብትም ከፍ ከፍ
ወደላይ ከፍ ከፍ
ከፍ ከፍ.... ከፍ ከፍ
ከዛ የወደቅህ ዕለት አጥንትህ እንዳይተርፍ::

ገጣሚ ታገል ሰይፉ

@getem
@getem
ልሰቀልልሽ?
..

እንዲህ ይመስለኛል
.... ክርስቶስ በምድር
ፍቅር ይገባን ዘንድ
.... ቢመላለስ ቢዞር
በእግሩ ተራምዶ አልገባን ስላለ
"ድንገት ካልታያቸው ከፍ ልበል" ብሎ
...በራሱ አምሳያ...ፍቅርን ሰቀለ።

እኔ እንደሚገባኝ......
ክርስቶስ አይደለም የተቸነከረው
ይታያቸው ብሎ...
ፍቅርን ሰቅሎልን...እሱ ዙፋን ላይ ነው።

..ደጅሽ ብመላለስ ሰርክ ብመጣ
..አንቺ እንደ አይሁድ አልገባሽ ስላል
..እኔ ተሰቅዬ ዙፋኔ ላይ ልውጣ

( ታምራት ሚሊዮን)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
ጠ-ረ*ጠ-ር*-ኩ-ሽ(ልዑል ሀይሌ)

ንፋሱ ገልቦሻል
ምን አስለምደሽው?
ፀሐዩን ስታዪ
ለምን ነው ልብስሽን ቶሎ ያወለቅሽው?
ምነው መራቆትሽ
ለወጪ ወራጁ ላማተረሽ ሁሉ
አሁን ጠረጠርኩሽ
የወጡ የገቡ አስወለቅናት ሲሉ

15-09-10
@getem
@getem
“እናቴ ትሙት አንላቀቅም!”


“ሰማህ የኔ ውድ . . . 
ሳፈቅርህ ከልቤ ባንተ ተረትቼ
ስላንተው ስባክን አቅሌን ነፍሴን ስቼ
በክንድህ እያሟሟህ ባፍህ እያቀለጥከኝ
ከማያውቁት ዓለም ወስደህ እየከተትከኝ
ነፍሴን አስክረሃት በሀሴት ዳንኪራ
እንዳልቆም እንዳልሄድ ያላንተ እንዳልሰራ
አድርገህ ጠፍረህ እንዲህ አሳስረኸኝ 
እሄዳለሁ ብትል ከመንገድ ጥለኸኝ 
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
እኔ በፍቅር ቀልድ አላውቅም!”

ስትይኝ ፈራለሁ 
አንዳንዴም ኮራለሁ 
አንዴ ደስ ይለኛል 
አንዳንዴ ይጨንቀኛል።


“እየውልህ ውዴ . . . 
እኔማ ስወድህ ሁኚ ያልከኝን ሆኜ
የኔን ዓለም ትቼ ባንተ ዓለም መንኜ
ጠቅልዬ ግብቼ ከገዳምህ ዋሻ
በስምህ ፀልዬ ሃጢያቴን ማስረሻ
እንደሆነ መቼም አንተም ታውቀዋለህ
ከቶ ያልሰጠውህ ኧረ እንደው ምን አለህ
ታዲያ ሁሉን ወስደህ ባዶዬን ቀርቼ
ኑሮዬን በሞላ አንተው ላይ ገንብቼ
ስታውቀው እንዳልኖር አንተን ተለይቼ
እሄዳለሁ ብትል ድንገት አንቺን ትቼ
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
እኔ በህወት ቀልድ አላውቅም!”

ስትይኝ ፈራለሁ 
አንዳንዴም ኮራለሁ 
አንዴ ደስ ይለኛል 
አንዳንዴ ይጨንቀኛል።


ሰማሽ የኔ እመቤት . . . 
እውነት አንቺን ርቄ
እምነትሽን ፍቄ
በፍቅርሽ ቀልጄ 
ሌላ ሴት ለምጄ 
ምኖር ይመስልሻል ?!
እውነት እውነት እውነት 
በእውነት ተሳስተሻል !
ደግሞ ፉከራሽን ዛቻሽን ፈርቼ
እንዳይመስልሽ ውዴ እኔስ ተረትቼ!

ይልቅ እኔም አልኩሽ . . . 
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
ካንቺስ ወዲያ ሴት አላውቅም። 
___
አብዲ ሰዒድ
2004 E.C

@getem
@getem
~~~ ጌሾና ፍቅር ~~~~

ቃሌን ተቀበይኝ በብቅል በጌሾ
ተጠርጎ እንዲወጣ የቂማችን ቁርሾ
ሰክረው ያስቀየሙት ማግስቱን ይረሳል 
በጨብሲ የገነቡት አይዘልቅም ይፈርሳል
ቢሆንም ዛሬን ነይ ነገ እንደሁ ይደርሳል።

ውዴ ሆይ ነይልኝ 
በይ ጠጪ እንጠጣ
ሰላምና ፍቅር ባገር እንዲመጣ !

ደግሞ ይሄን ጡትሽን እስቲ ሸፈን አርጊው
የባላገር ነፍሴን ሰው ፊት አታባልጊው። 

እናልሽ ዓለሜ . . . 
አፈር የሚገፋው ያ ሚስኪን ገበሬ 
ተስፋው እየፈጀው ልክ እንደ በርበሬ
አንጀቱን አጥብቆ ወኔውን ሰንቆ 
ለዓላማው ፅናት እግሩን ሰነጣጥቆ
በደደረው መዳፍ ላቦቱን ሞዥቆ …

“አንተ ስትደርስልኝ አደርጋለሁ ጫማ
ለክብርህ ለግብሬ ለስምህ ሚስማማ 
በል በርታልኝ ልጄ ዝመት ወደ አስኳላ
ቀለም የለየ ነው ደህነኛ ‘ሚበላ!” 
ብሎ የሸኘኝን ከዚያ ከገብስ እርሻ 
የጀግናው አባቴን ድህነት ማስረሻ 

እንዲሆነኝ ፍጠኝ 
ነይ ጠጪ እንጠጣ
ችጋር ድንቁርና ካገር እንዲወጣ !

ኧረ ተይ ጭንሽን አንሺው ከፊቴ ላይ
አልታይ ይለኛል ካንቺ ወዲያ ሰማይ። 

ደግሞም ብትፈልጊ ግብርና ማጥናቴ
በሰብል ምርምር ጥበብ መገብየቴ 
ያባቴን ገብስ እርሻ ላዘምን ላስፋፋ
በጉልበት ሳይደክም በእውቀት ላፋፋ
አልሜ ወጥኜ ግቤን አሰልፌ
ነበር የተማርኩት ከሰው ተጣድፌ
ቀረሁኝ ፒያሳ ቢራዬን ታቅፌ።

ኦሆሆይ ፒያሳ …
አሃይ ቼቺኒያ …
የደፈረሽ ይውደም እናት ኢትዮጵያ!
ዘራፍ ብሎ ገዳይ የጀግና ልጅ ጀግና
ድህነቱን ታቅፎ፣
እውቀቱን ጨንግፎ፣
ሽል ተስፋውም ረግፎ፣ ይጠጣል ያውና!

እኔ ምልሽ ውዴ . . . 
ባለፈው ከኮሌጅ የተመረቅሽ ለታ
መንደርተኛው ሁሉ ሲጨፍር በሆታ
እናትሽ በኩራት ኮንጎዋን ተጫምታ
ዘመኗን በዚያች ለት ሹሩባ ተሰርታ
በበለዘ መልኳ በቅን ልቧ ፈክታ …

“ብሞትም አይቆጨኝ አልቀረሁ ለፍቼ
አንቺን መሳይ ሃኪም ለቀበሌ አፍርቼ
የትልቋ እህትሽ የገነት መካሻ 
የከሰለ ልቤን ሃዘኔን ማስረሻ
እሷ እንደው ተቀጨች አዋላጅ ነርስ አጥታ
አምላክ ባንቺ ካሰኝ ለወገን መከታ”
ብላ እንደሳመችሽ ባስታወስኩት ጊዜ
ያንዘፍዝፈኛል የያዘኝ አባዜ። 

የቀዬው ሰው ሁሉ ዶክተር መጣች ሲሉ
ካዛንችስ ተገኘች ልጅት በመሃሉ 
ምነው በሌሊቱ?!
ምነው በውድቅቱ?! 
አይሻልሽም ወይ ቀን መርፌ መውጋቱ?! 

እያለ እንዳይዝሽ ይህ ነዝናዥ ህሊና
በይ ጨለጥ አርጊበት ደብል አስቀጂና
ውዴ ሆይ በይ ጠጪ
አይዞሽ እንጠጣ
እድገት ብልፅግና ባገር እንዲመጣ !

ኧረ ተይ አንቺ ልጅ …
ባጭር ቀሚስሽ ላይ ፍም ጭንሽ ተጋልጦ
እንደ እናትሽ ቅቤ ጨረሰኝ አቅልጦ።

ኦሆሆይ ካዛንቺስ …
አሃይ ቼቺኒያ …
ደህና ቀን ይውጣልሽ እናት ኢትዮጵያ።
____
አብዲ ሰዒድ 
2006 E.C

@getem
@getem
ግጥም (Facebook)

የሠቆቃ ጊዜ የሠቆቃ ዘመን፣
ዘንቦ ማያባራ ቢጸለይ ቢለመን።
ሠሚ ያጣ ጬኸት፣
እንቅልፍ አልባ ሌሊት፣
ኗሪ አልባ ወና ቤት፣
ጸደይ የለሽ ክረምት፣
ትንሣኤ አልባ ሥቅለት፣

አምላክ ዛሬ ይብቃን፤ በዝቷል ሠቆቃችን፣
ሥንሥም መነከሥ፤ ወርቅ ሥንሠፍር ጠጠር ሆኗል ምላሻችን።
@getem
@getem
……………ባንገናኝ እንጂ…………
(የአምልዬ)

መውደቅ መነሳትን ከትል የተማረ
ለነፋስ የሚስማማ
ድንቅ ድርሰት ድርሳን ውብ ዜማ አዋቀረ
ሰባት ጊዜ ወድቆ
ሰባቴ የተነሳን የደላው ትል አይተህ
በጥልቅ ተመስጦ
ለሩሕ የረቀቀ ዜማ ማበጀትህ

....…………እጅግ ይደንቀኛል .…………

ሰባት ጊዜ ሳይሆን
ሰባ ሰባት ጊዜ ወድቄ 'ምነሳ
በመነሳት ማግስት
ደሞ ሌላ ውድቀት ሲፈጥረኝ ለአበሳ
ባንገገናኝ እንጂ
ዘመን ባያድልህ ያሬድ ማህሌታይ
መገፋት መውደቄን
በድል ያልተቛጨ የኔን ጉዞ ብታይ
ለትል ያዘነ ልብ ላምሳሉ በደማ
ከዚህም የሚልቅ
በደረስክ ድርሳን ባዋቀርክ ዜማ።

@Bookkstore
@getem
@getem
…ልዩነት…
# በረከት_በላይነህ
.
ብዙዎች
አንደበቱ ባይጥም
ለጆሮ ባይመች ~ ትምህርት አሰጣጡ
“ኤዲያ”
የጋን ውስጥ መብራት
በማለት አድመው ~ ካዳራሹ ወጡ
.
ጥቂቶች
የመምህሩ ዕውቀት
የጋን ውስጥ መብራት ~ መሆኑን ያመኑ
አምነው የተግባቡ
አዳራሹን ትተው ~ ወደ ጋኑ ገቡ

@getem
@getem
እዚህ እና እዚያ

እዚህ ᎐ ᎐ ᎐

ነጋሪት፣ ከበሮ ፡ ሲጎሰም ሲመታ
ጋሻ ጦር ተሰብቆ ፡ ሲነፋ በእምቢልታ
መለከት፣ ጸናጽል፣ አታሞ ሻኩራ
በሕብረ ዝማሬ ፡ በመድፍ እያጓራ …
ሽለላ እየደራ 
ሻማም እየበራ 
ፉከራ ቀረርቶ ፡ ያፈኞች ቱማታ 
እዩልኝ ስሙልኝ ፡ ያድር ባይ ድንፋታ
ያደነቁረናል ፡ ያለ ቅንጣት ፋታ !

ስሟቸው !…
“የምልጃ ታቦቴ 
አድባር ጉልላቴ 
ምልክቴ ጌጤ 
ማተቤ ነህ ፈርጤ…” 
ሲሉ ሲባባሉ
በስም ሲማማሉ
ሲ – ሸ – ነ – ጋ – ገ – ሉ !


. . . ያ
. . . . . . ስ
. . . . . . . . . ጠ
. . . . . . . . . . . . ሉ !!!

እዚያ ᎐ ᎐ ᎐

እዬዬና መርዶ፣ የእድር ጡሩንባ 
ያስለቃሾች ዋሽንት፣ ያላቃሽ አዞ እምባ
ለዛ የለሽ ዜማ፣ ጣዕም የለሽ ንፍሮ 
ቅጥ የለሽ ንፍረቃ፣ ገጽ አልባ እንጉርጉሮ …

ዝርጠጣ፣ ፍርጠጣ 
የስሜት ሽምጠጣ
ልዝቡን ከግልቡ ብረዛ ቅየጣ . . .

ደራሽና ገስጋሽ ፡ ላይሆኑ ዘላቂ 
በጅምላ ሲነዱ ፡ ሕዝቤን አሳቃቂ 
ደግሞም አስጨናቂ 
“ስስ ብርሃን ፈንጣቂ” 
ግርዶሽ አሟሟቂ
ውዥንብር ናፋቂ . . .

ስሟቸው !…
“ተፋጀ ተጣላ 
እርስ በርስ ተባላ
ሞተ ተሰደደ 
ተቃጠለ አበደ …

አትነሳም ወይ አትለውም ጎኑን
ደምህን ታቅፈህ ከምትድህ ዘመኑን”
እያሉ እያስባሉ እሳት እየጫሩ
በስም ላይ ስም ጭነው እየተሞሸሩ…

“አዋቂው … ልሒቁ 
ረቂቁ … ምጡቁ 
ታጋዩ … አርበኛው 
የፍትህ እረኛው
አንተ ብቻ ዳኛው “

“ከኛስ ወዲያ ላሳር – ለሕዝባችን ግርማ
እጃችን ያልነካው – ሁሉም ነው ጨለማ።”
ሲሉ ሲፈርጁ በመንጋ ሲያስቡ 
ጽድቅና ኩነኔን ባንድ ገጽ ሲከትቡ
ሲያረቁ ሲያፀድቁ 
በቃል ሲያስመርቁ 
ሲ – ያ – ጨ – መ – ላ – ል – ቁ !


. . . ያ
. . . . . . በ
. . . . . . . . . ሽ
. . . . . . . . . . . . ቁ !!!

እዚያና እዚህ ሆኖ የህልማችን ጫፉ
ስንፋተግ አለን ቀኖች ሲቀጠፉ
እስኪ እንጠጋጋ ወፎቹ እንዳይረግፉ።

/ አብዲ ሰዒድ /

😊
@getem
@getem
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
——————
መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ!
አምባ ወጥቼ እኩለ-ሌት ፤ ስለት ገብቼ በስሟ
ከርሞ ሰይጣን በሷ አስቶኝ፤ ልገላገል ከህመሟ
ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ፤ ደጋግሜ፤ ማህሌት ቆሜ
ሆዴ ቃትቶ ባር ባር ብሎ፤እርቃኔን ከሷ ታድሜ
ደጀ ሰላሟን በአራት እግር፤ ተንበርክኬ ተሳልሜ
በስጋዬ እሚነደውን፤ በጸሎት ላቤ አጣጥሜ
እፎይ ብዬ አመስግኜ፤ ውዳሴዋን ደጋግሜ…
ገና ከደጅዋ እልፍ ሳልል፤ ደሞ ይምጣ የቁም ህልሜ?
ሌት በጥምቀቷ የነጣው፤ ነጋ፤ ደፈረሰ ደሜ።
ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘልኝ፤ አዬ የስለት አታምጣ!
በውጣ ውረድ በጠበል፤ ባሣር ወዜ ቢገረጣ
ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ፤ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ!

@getem
@getem
@lula_al_greeko
#እኔና_ቤቴ
.
በእንባ ለማራጨት ፥ ቀልድ መቼ ጠፋ?
ከእሬት የመረረ ፥ ከእናት ሞት የከፋ።
.
እንቀልድ ካልንማ ፥ ብዙ አለ ቁምነገር
በሳቅ አንከትክቶ ፥ ጥሎ 'ሚያንፈራፍር።
.
ጠላው በጋን ሞልቷል፥ ምንጭ ውሃም አላጣን
ይሁን ብለን አለን ፥፥ ቅ..ራ..ሪ እየጠጣን ።፡
--------------------------//--------------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@lula_al_greeko