ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የናፍቆት አለንጋ ሲያናውጣት ነብሱ
ለአይኑ ቦታ ለቆ ሳይከፈት ጥርሱ
በገፋሽው ፍቅር ቂም እንደነከሰ
ሰብአዊ አካሉ ዘውትር እያነሰ
እጅና እግሩ ደረትና አንገቱ
ምላሥ ጆሮ አፍንጫ የላይ ሰውነቱ
መቃብር ያልገቡ በድን አካላቱ
ከቁም ሞት ለመዳን ለነፍስ ሲዋትቱ
ግና
ዘለላ ውሀውን
መሬት እየረጨ
ከእንባ እጢዎቹ ውስጥ
ፍቅር እያመነጨ
የማይታይ ቀለም እያርከፈከፈ
በሽፋሽፍቱ ጫፍ ስምሽን እየፃፈ
ሞቶም ሳይለይለት
ወድቆም ሳይነሳ
ጊዜ ይቅበረው ተብሎ
በሰው እንደተረሳ
ጥላቻ እና ሀዘን
ፍቅር እና ደስታን እንደተንተራሰ
አይኑ
አይኑ ብቻ ቀረ እንባ እየፈሰሰ

ምንያህል ጥላሁን
12/08/2010

@getem
@getem
ማን ሊታመን አሁን


ባጣ ባይኖረኝም ባዶ ቢሆን ቤቴ
መኖር እችላለው በገዛ አካላቴ
ኖሮት ቢከዳኝም ትላንቱን ረስቶ
በዛች ጭንቁ ሰዓት መሬት ተዘርግቶ
አንስቼ አብልቼ እንደራሴ አይቼ
ዛሬ ለምን እረሳኝ ስወድቅ አጥቼ


ትላንት በዛን ግዜ አብረውኝ የበሉ
ምነው በጭንቅ ሰዓት አሁን የታሉ
መውደቄን አይተው አሁን የራቁኝ
ትላንት ይመለሳል ምነው አይዞህ አላሉኝ
ትላንት ይመለሳል ምነው አይዞህ አላሉኝ


DaDa coffee

@getem
@getem
#የተነጣቂው_ስንኝ

ከደረትሽ ልዉል ዛሬ ሰበብ ባጣሁ
የባልሽ ስጦታ ሃብል ሆኜ መጣሁ

ኢዛና

@getem
@getem
@lula_al_greeko
◉ ኢዲሞክራት ስሞች 

ግዛቸው ሸንቁጤ
በለው ድፋባቸው 
ቅጣው ግፋወሰን
ደባልቄ ያዛቸው 
ዳምጠው አስጨናቂ
አሸብር በላቸው 
ግጨው አያርገጤ
አሰግድ ጌታቸው 
እኔ እንዳስተዋለ
ሆኜ እንደተመልካች 
ብዬ መደብኩዋቸው
የሰው መብት ተጋፊ ወይም ገፋፊዎች 
ጭራሽ አምባገነን
ኢዲሞክራት ስሞች !!!


😊ከቶአታው

@Lula_al_greeko
@getem
@getem
👍1
ግጥም ብቻ 📘
◉ ኢዲሞክራት ስሞች  ግዛቸው ሸንቁጤ በለው ድፋባቸው  ቅጣው ግፋወሰን ደባልቄ ያዛቸው  ዳምጠው አስጨናቂ አሸብር በላቸው  ግጨው አያርገጤ አሰግድ ጌታቸው  እኔ እንዳስተዋለ ሆኜ እንደተመልካች  ብዬ መደብኩዋቸው የሰው መብት ተጋፊ ወይም ገፋፊዎች  ጭራሽ አምባገነን ኢዲሞክራት ስሞች !!! 😊ከቶአታው @Lula_al_greeko…
፪ በጎጠኘነት አይን ያየው ተመልካች
😒ዋኖሴ

የሥም ዝርዝሮቹን
ከዓስተዉሎትሕ ሳይ
ዕኔም አንድ ኃሳብ
ብልጪ አለብኝ ቆይ::
እኒሕ ከዚሕ በላይ
የደረደርካቸዉ ሥሞቹ በሙሉ 
አንድ ዘር ጠቋሚ
በእዉነት ይመሥላሉ::
እናም አካሄዴ!
ከርዕሥሕ ሳየው ኃሳብሕን በሾዴ
የዚሕ ስም ባለቤት ኢ-ዲሞክራት ነው
ለማለት ነዉ እንዴ?

@getem
@getem
ግጥም ብቻ 📘
፪ በጎጠኘነት አይን ያየው ተመልካች 😒ዋኖሴ የሥም ዝርዝሮቹን ከዓስተዉሎትሕ ሳይ ዕኔም አንድ ኃሳብ ብልጪ አለብኝ ቆይ:: እኒሕ ከዚሕ በላይ የደረደርካቸዉ ሥሞቹ በሙሉ  አንድ ዘር ጠቋሚ በእዉነት ይመሥላሉ:: እናም አካሄዴ! ከርዕሥሕ ሳየው ኃሳብሕን በሾዴ የዚሕ ስም ባለቤት ኢ-ዲሞክራት ነው ለማለት ነዉ እንዴ? @getem @getem
የቶታአው ምልስ ለ ዋኖሴ 😊

እኔ አላልኩኝም አልወጣኝ እንደሱ 
ምናለ ደርሳችሁ እሳት ባትለኩሱ 
እኔ ያልኩት ስሙን 
የግል መጠሪያዉን 
ደሞ እኒህን ስሞች ማን ላንዱ አረጋቸው 
አበሻ ጫፍ ከጫፍ ነው ሚጠራባቸው 
ፈልግ ብታደርግ ከሱማሌ አታጣም አንድ አሪፍ ጌታቸው 
እናም ብዙ አታዉኩዋት አትጥላችሁ ነፍሴ 
በተለይ ደሞ አንተን ወንድሜ ዋኖሴ 
የዋርካ ዉስጥ አምዴ ተጠሪና ዋሴ 
አንተም ዘር ቆጠራ ቁልቁል ልትወርድ 
እንዳትቀልብኝ በልኮ አትዋረድ 
እልቅ ዝም ብለህ ያዘው ገብስ ገብሱን 
ይቅርብህ በል ጣለው ተወው መተርጎሙን

ቶታአውኮትኳች

@getem
@getem
("ከዛፍ የተቀመረ ዜማ")

ካ'ለም እቅፍ ወጥቶ
ካ'ለም እቅፍ ሸሽቶ
ወደ ገዳም ሲሄድ
ደክሞት ተዝለፍልፎ
ብላቴናዉ ያሬድ ካ'ንድ ዛፍ ስር አርፎ
ከዛፉ ግንድ ሥር ትል ሲሸልል ሰማ
እንዲህ በሚል ዜማ

"ዛፍ ነዉ ህይወቴ
ቅጠልዋ እራቴ
ሰባት ጊዜ ልውደቅ
ሰባቴ እንድወጣ
የኀላ ኀላ 'ራቴን አላጣ"
ይህን ስትሰማ ቅጠሊቱ ራደች
መሸሽ ባይሆንላት ሙሾን አወረደች

"ዛፉ ህይወቴ ነው
ግን ኀያል ቢመስልም
ተራራ ቢመስልም
ተራራ ቢያክልም
የማታ የማታ
ከትል አያስጥልም"
ያሬድ ይሄን ሰምቶ
ትሉ በጥረቱ ራት ሲበላ አይቶ
ተስፋውን አጸናዉ
በቅጠሏ ዕጣ ግን ተነካ ልቡናው
ከዚያም ተመልሶ
የትሉን ፉከራ
የቅጠሏን ለቅሶ
ባ'ንድ ላይ ለውሶ
ዜማውን ቀመረ
ዜማው ተዘመረ
ከሰው ነፍስ ተስማማ
በሰው ድምፅ አማረ ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
።።።።እኔ አደለሁማ።።።።።
ባንቺስ ምን ሊፈረድ ነው እንጂ በነሱ
የወንድነት ክብሩን ረግጠው በረሱ
የተቆለፈን በር እያዩ 'ሚያንኳኩ
ሰሚ በሌለበት የሚለፈልፉ
ተራራን እንደ ኳስ ሊገፉ 'ሚለፉ
ፍቅር በልመና በገንዘብ የሚሉ
ምኑንም ሳዪዙት ልሞት ነው በሚሉ
ነው እንጂ በነሱ ባንቺስ ምን ሊፈረድ
እያሸረጋገዱ ለሆኑልሽ ገረድ


እኔ አደለውማ እንግዲ 'ደነሱ
እሺ ስትይ እሺ
እምቢ ስትይ እምቢ
ነው የልቤ መልሱ
መቻል ያውቅበታል ሁሉንም በሆዱ
ለፍልፎ እንደነሱ አይወጣም በጉዱ
በቃ እንዳጠብቂ ለቅሶ ና ልመና
ሁሌ የለም ፋሲካ አንዳዴም ነው ገና



ነባ

@getem
@getem
👍1
*ሄደች ያሉኝ ዕለት*
እግሬ እንደለመደው አይኗን ልየው ብሎ
ከሰፈርሽ ውሎ
ድንገት ብትቀሪበት ልቤ ሲጨናነቅ
የጎረቤት ጨቅላ ጠርቶ አንቺን ቢያስጠይቅ
ከሀገር ወታለች መባልሽን ሰማና
ምስልሽን አትሞ ትካዜን ተላብሶ ቀረ ከጎዳና።
አንቺ በሄድሽበት ጥላሽ ባረፈበት
አንችን ብቻ ስሎ
በድን ሰውነቱን ከኋላ አስከትሎ
ወድቋል ራሱን ጥሎ።
ኢማ...
ሄደች ያሉኝ እለት
እንደዚህ ሆኛለው
እንዳልሞት እንዳልድን
ባንቺ ቆስያለው ባንቺው ነፍሪያለው
መሬትን ሰማይ ነው ሰማይን ምድር ነው
ብዬ ተሟግቼ እብድ ተብያለው
የቀኙን ለግራ የግራውን ለቀኝ
ጫማየን አዙሬ ተጫምቼዋለው
ሱሪየን ገልብጬ አጥልቄልሻለው...

ሀ ወደላይ አይደል..በ መስሎ ታይቶኛል
እንኳንስ ትተሺኝ..
ስትርቂ ከጎኔ ነገር ይጠመኛል
ምድር ሰማይ መስሎ እንዳልቆም አርጎኛል
እውነት ለመናገር
ካገር ወጣች ሲሉኝ እንዲህ ተሰምቶኛል።
እባክሽ ቶሎ ነይ... ጓዴ ነይ...
ኢማ ነይ።

(ስምኦን)

ለማታውቀኝ ለማውቃት ኢማንዳ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
የባለጊዜ ሰዓት(ልዑል ሀይሌ)
.
ድልቡ ባለጊዜ
ሰዓቱ ማይሰራ
ሰኮንድ ደቂቃውን
ሰዓቱን ይቆጥራል
በድሃው መከራ
.
ደሃውም ይቆጥራል
በሃብታም ክንድ ላይ
ሰዓት ሆኖ ታስሯል
ህልሙና ምኞቱ
በሰዓትነቱ በቁጥር ውስጥ ታጥሯል

08-09-10

@getem
@getem
ናፍቆት መሞቴ ነው
ጠፋሽብኝ ብዬ 
የኢንተርኔት ፍቅሬ
እንዴት ነሽ ፋፊዬ 
እዚህ ዋርካ ቻት ላይ
ያኔ እንዳነበብኩሽ 
ወዲያዉ ነው የያዘኝ
አደገኛው ፍቅርሽ 
ያ መስተፋቅርሽ
የላክሽዉ በጽሁፍ 
በፍቅር የሚያስር
ደርሶ ሚያንከረፍፍ 
ልቤን ድንገት ወግቶ
ቢይዘው ቀስፎ 
አደባባይ ጣለኝ
ምንይሉኝን ገፎ 
መቼም ይህንን ስል
ተቃዋሚ አላጣም 
የዋርካ ወንድ ሁሉ
ይወድሻል በጣም 
ግና የሁሎቹም
አንድነት ቢደመር 
የኔ ለብቻው ነው
አይቀርብም ዉድድር 
እናም አንቺ ፋፊ 
እኔ ወድሽ አይደል
በናትሽ አትጥፊ

የግጥም ሳይበር ኔት

@getem
@getem
የናፈቁ ነፍሶች ደስ የሚል ግጥም (poem)
😔 የናፈቁት ነፍሶች 😔

@getem
@getem
◌◌◌◌◌ በብቸኝነት ◌◌◌◌◌
ከተማው ተይዞ ሲጣል ምድረበዳ
ሰው ከራሱ በቀር ለሌላው እንግዳ
ሆኖ ሲውል ሲያድር በብቸኝነቱ
ሞተች ያላል አለም
ውስጣዊ ፍጥረቱ።

በደበበ ሰይፉ

@getem
@getem
✧✧✧ ብዙ ተባዙ

የእናትነት እጣ፣ ያባትነት ውርሱን
የፍጥረትን ምስጢር፣ የቤተሰብ ቅርሱን
የትውልድ አደራ፣ የብዙ ተባዙን፤
ለአእምሮህ ሳይሆን ባሻው ለሚከንፈው
ለልቦናሽ ሳይሆን ስርአት ለሚገድፈው
ለፈቃድህ ሳይሆን እብደት ለሚለክፈው
ለህሊናሽ ሳይሆን ዓለም ለሚያጎድፈው፤
ሰጠው ለሽፍደትህ ጦር ለማይመልሰው
ለመግነጢስ ገላሽ ጾም ለሚያስፈርሰው
ጻፈው በገበናሽ በጉያሽ ትኩሳት
በማትሟገተው የጭንህ ዲን እሳት፤
በሰጣችሁ ርስት በወጉ አንድትረቡ
በሴስ አቆራኝቶ በወሲብ ቀለቡ
ምድርን በሰው ሞላት በኪነጥበቡ።

ፋሲል ይትባረክ

@getem
@getem
🖼📸📷🖼📸📷🖼📷📷
የፎቶግራፍ አድናቂ ከሆኑ በተለያየ መልኩ ሃገርኛ ምስሎችን በየቀኑ ለእናንተ እናደርሳለን ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉ
እናመሰግናለን ።
📸📷📸📷📸📷📸📷📸📷📸
@Mykeypictures
ባክህ ቶሎ አትምጣ...
--------------------------
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
.
ጥሩ እንዳደረጉ እንደሰሩ ደህና
ብለው ይፀልያሉ ጌታ ሆይ ቶሎ ና
እኔ ግን ምስኪኑ ሀጢያተኛ ልጅህ
ይችን ፀሎት ፀለይኩ ወድቄ ከደጀህ
አምላኬ፣
ካለሁበት ሀጢያት ነብሴን ሳላወጣ
በንስሀ ፀፀት እራሴን ሳልቀጣ
ባክህ ቶሎ አትምጣ!

@getem
@getem
@lula_al_greeko
ሰውን ግን ምን ነካው
በቶራህ
በስብዕናችን ቻናል ብቻ join @Abysinia @Abysinia
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 ግጥምን በጃዝ በነፃ

ውድ የግጥም ብቻ ወዳጆች እንሆ የሁለችንም ቤት በሆነው በብሄራዊ ቲያትር ነገ ዕለተ ረዕቡ ግንቦት ፲፭ በ 11:30 ሁላችሁንም ጋብዘናችውሃል። እንደው ጠሪ አክባሪ ነውና አደራ እንዳትቀሩብን ብለናል።
~~~ ወቸው ጉድ! ~~

ኣምሳለች
እሺ እያለች
ኣታለለች
እምቢ ብትል
ምን ታስከትል?

ልጅ ቅጣው
ለሽምጠጣው
ዘልሎ ወጣው
ኣለሁ ብሎ
ሄደ ጥሎ

ጋሽ ገመዳ
ዶፍ ኣራዳ
ያ ወራዳ
ተሽቀርቃሪ
ኣጭበርባሪ!

’ትየ ሙና
ከጋሸ ጦና
በጥሞና
ደጅ ካስጠኑ
ይኮነኑ

ኣባ ተክሌ
ኣልባሌ
ጨው ኣሞሌ
ጥምጥማቸው
ከበዳቸው

እሱን ጥሩት
ኣትቅጠሩት
ምን ትፈሩት
ባባ ዘውዱ
መጣ ጉዱ

በገመቹ
ላዩ ታቹ
ተሰላቹ
መሃል ሆዳቸው
ቡጢ በሏቸው!

ለልመና
’ትየ ሃና
የሉምና
ዘመድኩን
ያ ብኩን

ዘልዓለም
ሲፋለም
ያየ የለም
ና ኣሉት
ሊበሉት

ኣቶ ካሰው
ልጅ ጣሰው
በጣጠሰው
ኣስናቀ
ቦጨቀ

ዘበርጋ
ሳይረጋ
ተዘረጋ
ሲነጋ
ተዋጋ

ዳምጠው
ኣዳለጠው
ኣመለጠው
ኣሓዱ
ምጣዱ

ሓመልማል
ከጀማል
ስትማማል
ሙስጣፋ
ተንከራፋ

ኣቶ ያለው
ሞት ዘለለው
ምን ይሻለው
ልጅ ገለታ
እንጃለታ

ሳቢሳ
ከግሪሳ
ለቶሎሳ
ኣቶ ገቢሳ ያ ደሳሳ

ወልደሩፋኤል ያ ሳጥናኤል
በሚካኤል
ዓርፎ ይሥራ
ሰው ኣይጥራ

ጥላሁን እስኪ ኣሁን
ምን ይሁን
ባላባት
በቀረባት

እንደፎከረው
ኣከራክረው
ኣይምረው
ያጠረው
ኣበጠረው

ኣቶ ፈረደ
ተወራረደ
ተንገዳገደ
ኣቶ ረታ
መላ መታ

ኣቶ ፈለቀ
የልጅ ዘለቀ
ጥርስ ኣወለቀ
ዓለሙ
ድዳሙ

ለዓብደላ
ኣስኪጠላ
ስጡት ጠላ
ሲጠጣ
ይንጣጣ

ለቢራራ
ሳይጣራ
ስጡት ቢራ
እስኪነቃ
ይንቃቃ

ልጅ መርሻ
ከጥሻ
ምን ትሻና ውጣ
ዓይንህ ይውጣ

ኣድማሱ
ከትራሱ
መለስለሱ
ተቃቀፉ
ተናቀፉ

ይላላ
ፊት ኋላ
ሞላላ
ኋላ -ሸት
ጥላ -ሸት

’ትየ ምርጡ
ሲጠጡ
ምኑ ቅጡ
ለጠላቸው
ኣልከፍላቸው!

ዓለሚቱ
ከማሚቱ
ሲጓተቱ
ምሕረቱ
መሞቱ

ተማሪ
መሰሪ
ሰርሳሪ
ሲሰረስር
ይከስር

ሊበሉት
ሰለሉት
ደለሉት
ያ ነጋሽ
ተናካሽ

ከወርቁ
መዳረቁ
ይታረቁ
ለፀሎት
ማ’ ብሎት ብሎት

ፀሓዬ
ከታዬ
ተያዬ
ብድር
በምድር

ኣማረ
ዘመረ
ከበረ
ሲዘምር
ይደምር

ወንዳፍራሽ
ካምባፍራሽ
በኣዳራሽ
ተጣሉ
ሊባሉ

ለኣመሉ
ኣስካሉ
እያሉ
ምን መጣ
ገበጣ

ስብሓቱ
ከጫልቱ
ማንጋቱ
’ንጃለቱ
ያ ገልቱ

ልጅ ሃይሉ
ሳይከፍሉ
ሊበሉ
ብድራቸው
ስጧቸው

ልጅ መራራ
ሲንጠራራ
ተሰበራ
ወደቀ
ደቀቀ

ሰመረ
መከረ
ሰከረ
ሲሰክር
ይፎክር

ገ/ኢ. ጐርፉ።

@getem
@getem
ባክህ ቶሎ ይምጣ!
(ስምረት አበበ)

እንኳንና 40,- ሺህ አመት ቢሰጥህ
ዝንት አለም አትጸድቅም በወዝ በጥረትህ
ይልቁኑስ ይምጣ.....
ድካምህን ያገዘው
በጎልጎልታ ሞቶ ሀጢያትህን ያጠበው
ጽድቅ የለኝም ብለህ ራስህን አትኮንን
ጽድቁን ቆጥሮልሀል እሱን ያመንከው ቀን

("ባክህ ቶሎ አትምጣ" ለሚለው ግጥም የተሰጠ ምላሽ)

@getem
@getem
@poemmedia