ግጥም ብቻ 📘
63.1K subscribers
1.57K photos
31 videos
61 files
181 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ተኳረፍኩኝ ካገሬ ጋር
ተሳቅቄ ሆኜ ከዳር

ጀርባየን አላምነውም
ጠላቴንም አላውቀውም
ማውቀውንም አላውቀውም
ባውቀውም አልንቀውም

መተንፈሻ አጣ አገሩ
ኩፍ በዛ በየዳሩ
ሰቀቀን በርዞታል
አይጥምም አየሩ

ዘር በዛ ባገሩ
አዲስ ጠፋች በአበባ
ሚሰቴ አሏት ባለቤቴን
ቀለበቴን አይቶ አገባ

አገሯ ዳር ናት
ሰውም ወድቋል ጥጉጥጉ
ሬሳው ሳይነሳ
ዘሩን ዘሩን እየፈለጉ

አዲስ አመት ባክህ ና
አታብቅል አበባ
ኢትዬጵያን ሚሏት ሀገር
ባይሆን ይዘህ ግባ
.
.
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat

@getem
@getem
@getem
53😢17
ውደቅ እስቲ ላንዴ
እንደ ጥልያን ጦር፣
ገላህ ይሸለታል
በጦር በጎራዴ።


አንተ ባለ ክብር !

ላንዴ እስቲ አቀርቅር
መታሸት ያወዛው …
ጀርባህ ይነረታል ፣
በዱላ ና በትር።
:
ተገልጠህ ብታየው
        ትከ’ሻህ ተከፍቶ
አናትህ አይተርፍም
        በኮናኝ ተሞልቶ።
.
ፅጌረዳ የሰጠህ
በዘመንህ ወራት
እሾሁን ያስቀራል
ቅጠሏን አራግፏት።
:
ከፊት ስትቀርብ አይደል?
(እንደ ለቅሶ ንፍሮ)
ተዘግነህ ‘ምታልቀው
ልኬትህ ተሽሮ ?
:
ተሞልቷል ከተማው
በድንጋይ ፣ በምሳር
ዘንበል ያልህ ጊዜ
ተቋጥሮ ያመሻል
የፈካልህ ግንባር ።
:
ብቻ!
ወንዝ እንደወረደች
የገጠር ኮረዳ ፣
ላስቲክ ጫማዋ ስር
አዳልጧት በነበር
ረጢብ  እንግጫ ፣
-
ሚዛን ስተህ ውደቅ
በቋጥኝ ፣ በጭንጫ ፤

ያጨበጨቡ እጆች
ጉያህ ይሰርጋሉ፣
ደግሞ ለቁንጥጫ ።

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@paappii
57👍5🔥1🎉1
ትናንትን በዛሬ_!

ያቺ ትናንቴ ሀ--ሁ-- ዬ  የነበረች፣
የሆነ ቀን ዛሬ ነበረች።
             እንድያው ሳላስብ ዘንግቻት፣
             ይሄው ዛሬ አስታወስኳት።
ቁጭ ብዬ በዛሬ ፊት ስታዘባት፣
የኳተነች ጎስቋላ ፊት የነበራት፣
             በደስታ እና በፈተና የረሳዃት፣
              ይሄው አሁን በዛሬ ፊት አነሳዃት።
ከፊቴ ፊት ቁጭ ብላ ስትስቅብኝ፣
ስጠብቃት ብን ብላ እንዳጠፋኝ።
               ባትሆን ኖሮ የኔ ትናንት፣
                ይችን ዛሬ-- አሁን ባልል ታምኜባት።
መምህሬ የኔ ትናንት፣
መቆሚያዬ የዛሬ እናት፣
          የጉዞዬ እርሾ የነገዬ ርስት፣
          የጉልበቴ ሰደፍ የዘመኔ ሽበት።
                          
                     በ መ/ር ሰይድ: ነሐሴ 6, 2018

@getem
@getem
@getem
43👍1🔥1
🔔 ውድ የቻናላችን አባላት፣ አዲስ የምስራች አለን!

የተመረጡ ግጥሞችን እና ሀሳቦችን, ወጎችን የምናጋራበትን ጉዞአችንን የበለጠ ለማሳደግ እና ጽሁፎቻችንን ባማረ ሁኔታ ለማቅረብ አዲስ Substack ገጽ ከፍተናል!

📌 ግጥሞች ለማንበብ እና አዳዲስ ጽሁፎቻችን በኢሜይል እንዲደርሷችሁ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው Substack ገጻችንን Subscribe ያድርጉ፡
https://substack.com/@getembicha

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!!
@getem
22🤩3
ታግሼ እንዳላልፈው ፥
ክህደት ስላጠቃኝ
አበባ እሰጥ ብዬ ፥
እሾህ ስለወጋኝ
ሁሉንም ለመተው ፥
ትንሽ ነው ሚበቃኝ

By ሲራክ ወንድሙ

@getem
@getem
@paappii
117😢27👍9🔥5🤩2🎉1

      ቃና አልባ ህይወቴ
                     የፈሰሰ ሀሞቴ

   ጣዕም
   መልኩ ጠፍቶ ፡ የጠቆረ ወተቴ
                     ያ ‛መት ሙት አመቴ  𓏸  𓏸
  𓏸
                       ተሰርዮልኛል ! !
         ....ተሰርዞልኛል...
እናትነት ፍቅርሽ ፡ ያለፍኩትን አይቶ
                          ፤ አዝኖ ራርቶልኛል
ከአዘቅት እመቃት ፡ከባርያነት ግዞት
                              ለይቶ አንስቶኛል ⨳



   
ማህፀንሽ ሳለሁ ኪዳን ገብተሽልኝ
    ያንቺን መልከ ስጋ ˔ ከእግዜር ገዝተሽልኝ
   . . . አገልግለሽኛል
   ተርበሽ ተጠምተሽ አሳድገሽኛል ꨄ
𓏲 አፈር ግፈሽ ቅመሽ
  ርኩስ ፍጡር ወንድን በስራሽ አስንቀሽ
  ‟ቅድሚያ ላንተ” ብለሽ
            ከሰው እኩል አርገሽ
  አሁን ያለሁትን ፣
  ነገ ምሆነውን .  .  . ሰውነቴን ሰራሽ !
                 {  አበጀሽ !   አበጀሽ  ! }

𓏲 እናት ሴት እናቴ
  ኅቡዕ ቃለ~ጥበብ ˔ የፀሎት ቅናቴ
   ከፈራረስኩበት ፣
   ከወለገድኩበት ፣
  ደርሰሽ አንከብክበሽ ፥ በፍቅርሽ መቅናቴ ⨳

𖥔
    [ ምን ትባል ፅዕዱቴ ?
           . . . በምን ስም ትጠራ
   ምድራዊ የሆነች የሰማያት ጣራ ]

𓏲 ስላንቺ ማንሳቱን ˔ ላልፈፅም ሰደርኩት
                          ላላከትም ካደምኩት
ቢሆንም
ቢሆንም እንኳንም ጀመርኩት...


< ግዴም ሆኖ ቢገኝ  አበጀሁ >

by ሰምረ የሽዋስ

@getem
@getem
@getem
25👍7
«ናፈቅሽኝ አቦ !» ብዬ የፃፍኩት
ኩራት ሲሰማኝ - ቀድጄ ጣልኩት ።

«ናፈቅከኝ በጣም» ብለሽ የፃፍሽው
ልምምጥ መስሎሽ
ወርውረሽ ጣልሽው ።

የፍቅር ብርሃን እንዳልተሰማን
ቅር እንዳላለን እንዳልናፈቅን
በአዲስ ወረቀት - ፀብ ተላላክን ።

እንበልና ...

እኒያ ወረቀቶች ...
ቀደን የጣልናቸው
የክረምት ጎርፍ አገናኛቸው ።

እስኪ አስቢያቸው ...

ደራሽ ተሳፍረው
ሆነው ጎን ለጎን
እርስ በርሳቸው ተያይተው ቢሆን ?
ምን ይሉ ይሆን ?

By Habtamu Hadera

@getem
@getem
@paappii
128🔥4😢4🤩4👍3
59🔥12👍1👎1
48🔥14👍7
ድልድይ ናት ጳጉሜ ከዝያ ወደዚኛው፣
ከመጨረሽኛው~ወደ~መጀመሪያው
ሲታደል አይደል ወይ ቋጭቶም ለመደምደም፣
የዓመት ቆይታን በ5 ቀን መገምገም!

@mypoems396
@getem
@getem
@getem
53👍14🔥6
"እኔ
ባዲስ ቀን አላምንም
ቀን ከቀን አልለይም
አሮጌ መሆን ነው የቀረኝ አንድ አቅም!"
የሚል ድባቴያም ሰምተህ ግን አታውቅም?!

ካደፈ ልብሱ አልፎ ከርሞ ልቡናውን እያስተባበረ
መስኮት ግድግዳውን እያሰማመረ
ድባብ የሚጨምር ደርሶ ባያየውም
እንዲህ ያለውንስ አላስተዋልኸውም?!

ግን
ከዚ ሁሉ ረቅቀን መጠቅ ነጠቅ ብለን፣
ከአይደለም እና አዎ መሃል ወጥተን፣
ካዲስነት ጀርባ ምን ታምር ታይቶሃል?፣
እውነትም ብርሃን ያለው ይመስልሃል?!

...
መልስ ያበጀህ እንደው ያጣህም እንደሆን
ወዴት ትሸሻለህ ተቀባይ ከመሆን?!

ሰው ፍጡር ነውና የለም የሚዘልለው፣
ከሚሆነው መሃል እንዳይሆን ሚነቅለው!
መቼም አለመቻል አስካቆረመደው
ሰውነት አንድ እርሙ መቀበል ብቻ ነው!

እናም..
ከመፈለግና ከመመኘት በስቲያ
እንደፈቃዳችን ከመናፈቅ ወዲያ
አዲስ ቀን ያው ቀን ነው መምጣቱን አይተውም፧
ተአምር ቢያመጣልን ወይ
አንዳች ባይፈጥርም፣
ከመኖር አይበልጥም።
አደይ ታብባለች ጠሃይ ትወጣለች
ህይወትም አትቀልልም፣
...
(ወደሚቀጥለው ብናልፍ አይሻልም?)

ለምኑም ለምኑም:(

@mypoems396
@getem
@getem
@getem
44🔥6😱2
አዲስ አመት
.
.
ያ...ጠቢብ ሰለሞን..........
ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤
ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው?

ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤
ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው።

ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤
ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤
አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ።

የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤
ጸሎቷን ለማድረስ እጇን ለዘረጋች፤

ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው።

ዛሬም ለሀገሬ........
መከራ እንደ ሀምሌ ፀንቶ ላጨገጋት፤
ዉሽንፍር መባርቅት አብሮ ለሚንጣት፤

ቀለበትሽን አዉሻትና........
መከራዋ ያብቃ ነጭ ልብስ ትልበስ፤
ተስፋዋ ይለምልም በፍቅር ትታደስ፤
እንባዋ ታብሶ ብርሃን ይታያት፤
በዚ በአዲስ አመት ደግ ቀን ይዉጣላት።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ዔደን
@topazionnn
@getem
@getem
47👎1🔥1
ትዝ ይልሻል?

የዛሬው ዋዜማ በጳጉሜ 5 አምና

ከበርሽ ነበርኩኝ
የሀሳቤን ልኖር ደጅሽን ስጠና

አይገርምም?

ድሮ ልንል በቃን እኒያ ቀናት አልፈው

ትዝብት ሊሆኑን በፊደል ተጽፈው

ይሄውልሽ አለሜ ይሄንን እወቂ

እንዳለፈው ዘመን
ለእኔ ኑሪ እያለ
ደጅ ይጠናል ብለሽ እንዳትጠብቂ።

ባይሆን
እኔ የምፈልገው
ይሄን አዲስ ዘመን ንጹህ እንቁ'ጣ'ጣሽ
ለሚመጣው ዓመት
:
ከሀሳቤ አሻግሮ
:
ከስኬቴ ጀርባ አምላክ አንችን ያምጣሽ።

ጳጉሜ ፭ ፳፻፲፰ እኩለ ሌሊት

By ይክበር ፀጋዬ

@getem
@getem
@paappii
29🔥1🤩1
ብንሥቅም ፡ ባንሥቅም
አደይ ቀርታ አታውቅም።

by Seifu Worku

መልካም አዲስ ዓመት

@getem
@getem
@paappii
66😁12👍7😢1
ደርሷል ትዕዛዛችን ፣ እንብላ ከእህሉ
አዘን አዘን የተቀመጥን ፣ ዳስዳስ ያለን ሁሉ

እንደአበሻ ገበሬ ፣ አርሶ እንዳጨደ
ነዶን ከምረን ፣ እጃችን ሰብል ያዘ
የመብቃትን ማዕረግ ፣ የመድረስን ከፍታ
እጃችን ጨብጦ ፣ ክንዳችን ባይገታ

ግና
ግና ሆዳችን ፣ አልጠገበም ሞልቶ
ሰው ሰው ተርቧል ፣ ወዳጁን አጥቶ
የእራሱ ራስ ከዳ ፣ የሆዱን ሆድ ፈጀ
ፍቅር እየዘራ ፣ አሜከላ አጨደ

ሰውን ሰው ራበው ፣ ሰውን ሰው ተጠማ
አበሻ በታሪኩ ፣ ዛሬ ብቸኝነት ደማ።

By ናትናኤል_አበበ

@getem
@getem
@getem
24👎5