ግጥም ብቻ 📘
63.5K subscribers
1.57K photos
31 videos
61 files
180 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሂድ!

አትጠራጠሩ እውነት ነው ነገሩ
አትደናበሩ ተስማምቷል አገሩ

ተረት ተተርቶ በምግባር ተፈትቶ መፅሐፍም ተፅፏል
ወደፊት ነውንጂ ወደኋላ ያየ ባምላክ ይቀፀፋል!

By @Lawyerly1

@getem
@getem
@getem
27🔥5
#ደብዝዞ_መወደድ

በልክ መሸፈን በልክ መገኘት፡
በልክ ጮሌነት  በልክ   መሞኘት፤
አቤት ስትችይበት!

በልክ ማወደስ  በልክ  መፎገር፡
መስመር  ያልዘለለ  ጨዋታና ነገር፤

በ ል ክ መቀበል በልክ መሸኘት፡
እ ኩ ል ሕብርና እኩል ብቸኝነት፤
አቤት ስትችይበት!
ኑሮና ቀለምሽ ወይነ~ደጋ መንደር፣
ለሰው አታሳዪ ካንድ ስምሽ በቀር።

ሳይሽቀረቀሩ ሳይሉ ወጣ ወረድ፣
ይገርማል ግን እኮ ደብዝዞ መወደድ!
አልተገኘሽም ስታሽካኪበት በየ በዓሉ
እንዲህም ሆነሽ~ታምሪያለሽ አሉ!
እቴ..

ሳትሽቀረቀሪ ሳትይ ክርትት ሰደድ፣
ማነው ያስተማረሽ?
                             ደብዝዞ     
                                     መወደድ!

አቤት ስትችይበት!

@myPoems396
@getem
@getem
@getem
30🤩6🔥3👍1
🦋ማያዬ🦋

በጨቅላ ቡረቃ
‎ፈንድቄ ምውለው፤
‎ስላንቺ ሳስብ ነው
‎ፈገግ የምለው፤

‎እፀ በለስ ወይን
‎የምሽት አዝመራ፤
‎የመለኮት እቅፍ
‎የፍቅር ደመራ፤

‎የጠዋት መዝሙሬ
‎ማለዳ ብስራቴ፤
‎ተጠግኗል ባንቺ
‎ደዌ ስብራቴ፤

‎ሀኪሜ ወዳጅሽ
‎ናፍቆሻል በጠና፤
‎ነይ መጥተሽ ደባብሽው
‎ይፈወሳልና፤

‎ብሌኔ ማያዬ
‎ስስት ቁንጅናዬ፤
‎ድብቋ ጀነቴ
‎ግልጧ መፅናኛዬ፤

‎ለውለታሽ ምላሽ
‎አሰናዳው ማጀት፤
‎ዝግጁ ነኝ ሁሌም
‎ካንቺ ጋር ለማርጀት፤

‎ፊደል ግምጃው ጠርቶኝ
‎ለክብሩ እጁን ስሜ፤
‎የሚመጥንሽን
‎አሰሳ ታድሜ፤

‎ድርሻዬን ዘግኜ
‎ድርሻሽን ለቅሜ፤
‎ይኼን ነው የምልሽ
‎እቺ ናት አቅሜ፤

‎የነፍስ ወይራ ነሽ
‎እጣን እና ከርቤ፤
‎ከፃፍኩልሽ በላይ
‎ይወድሻል ልቤ።

By @Abstruse12

@getem
@getem
@paappii
25👍3🔥1
እግዜር የኔው ይቆይ አስቀድማቸው..
.
.
መቼም እስከኖሩ
ሰው እንደ ፊቱ
መከራው ልዬ ነው
መቼም እስካሉ
እንደ አይን መጠኑ
ሰው ዕዳው ብዙ ነው

የኔ ስቃይ ባያንስ
ባይበልጥም አቋሙ
የኔው ስኬት ይቆይ
ሌሎቹ ይቅደሙ

በየ ቤተስኪያኑ
የሚፈሱ ዕንባዎች
ተራ ሲጠብቁ
ያለቀሱት ብዙ
አመታት በተስፋ
እየጠባበቁ

አስቀድማቸው
ለምን..?
ዕንባቸው ደርቋል
ከአይናቸው
ተስፋ ስላጣ
ፊታቸው

የኔው ይደርሳል
ተራዬ ይቆየኝ
አድርግላቸው
ችግር የለውም
እኔኑ ባታዬኝ

ልቤ ስለሚያዝን
ለመከረኛ ሰው
አልፎልኝ ካልደረስኩ
ይለፍብኝ በማልቅሰው

' በማለቅሰው ዕንባ
በተስፋዬ ካፊያ
ሰውን ካላኖርኩት
ምን ያደርጋል ጥድፊያ

እግዜር...የኔው ይቆይ
እናቶች ይቅደሙ
አባቶች ይቅደሙ
በልጅ ፊት አንሰው
ባለማኖር ውስጥ
ስለሚታመሙ

አባት አንሶ አይታይ
ግርማው አይጠውልግ
በልመናው ቃል
ተራው አስቀድመው
እንዲያደገድግ

ተራዬ ደርሶኝ
ስኬቴ ሁሉ ለሰው ካልደረሰ
ለሰው ኗሪው ይቅደም
መጨረሻ ልሁን
ዕንባን ካላበሰ

@geez_mulat

ይነበብ

ይህ ግጥም ፍፁም ከልቤ ያለውን ሀሳብ ያለምንም የቃላት ምርጫ የፃፍኩት ስራዬ ነው እስከ ሂዎት መጨረሻዬ የምወደው ስራዬ ነው  መታወሻ ይሁነኝ

@getem
@getem
@getem
60👍8😢6🔥3
ወጣቶች ነበርን
በእውቀቱ ስዩም
-----------------------------

ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ
ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ
ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ
ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤

ወጣቶች ነበርን
ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን
ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን
ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤
በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን
ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤

ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ
ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ

ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን
የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን
ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ
ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ
የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ
ምትቀበለን ፣ እየመሰለን
ከቁመታችን በላይ፣ የዘለልን፤

ወጣቶች ነበርን
ዛሬ እንደዋዛ
ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን፤

@getem
@getem
@paappii
44👍16😢9🔥3
40👍6🔥4👎3🎉1
ጠበቅሁሽ እኔማ፣ እዚያው ስፍራ ቆሜ፣
              በአክሱም ቁመና፣ በላሊበላ እድሜ።
                እግሮቼን ተክዬ፣ ቀኔን አስረዝሜ፣
               በሄድሽበት መንገድ፣ ልቤ እየነጎደ፣
               ስንት ነገር መጣ? ስንት ነገር ሄደ?
               ስንት ጊዜስ ነጋ? ስንቴ ጎህ ቀደደ?
               ስንት ጊዜ ዘነበ? ስንት ጊዜ አባራ?
             ትመጫለሽ ብዬ፣ በቆምኩበት ስፍራ።

       ስንቴ አድማሱን ማተርኩ፣ ስንትና ስንት አመት፣
             አንገቴን አስግጌ፣ በራስ ዳሽን ቁመት።
              በአክሱም ቁመና፣ በላሊበላ እድሜ፣
              በቀጠርሽኝ ስፍራ፣ ስጠብቅሽ ቆሜ፣
             ስንት ሳቅ አለፈ? ስንትና ስንት እምባ?
             ስንቴ ክረምት ሆነ? ስንቴ ፀደይ ጠባ?
                 ስንቱ ተገናኘ? ስንቱ ሰው ተጋባ?
            ሽል ስንቴ ልጅ ሆነ? ስንትስ ጊዜ አረጀ?
              ስንት ኮት ጨረሰ? ስንት እንጀራ ፈጀ?
        ስንት አይነት ሞት አየሁ? ስንት አይነት ፍፃሜ?
              በአክሱም ቁመና፣ በላሊበላ እድሜ፣
             በቆምኩበት ስፍራ፣ ስጠብቅሽ ቆሜ።

             ስንት ዉበት አለፈ? ስንት ዉበት ነጎደ?
          ስንት ትውልድ መጣ? ስንት ትውልድ ሄደ?
         ስንት እውነት ከፍ አለ? ስንት እውነት ወረደ?
             ስንት አለም ተሻረ? ስንት አለም ነገሰ?
ስንት ሀገር ፈረሰ? ስንት ሀገር ተሰራ? ስንት ሀገር ፈረሰ?
       ስንት ሺህ አመት ሸኘሁ? ስንት ሺህ ተቀበልኩ?
            እዚያች ስፍራ ቆሜ፣ አንቺን እየጠበኩ።

                እግሬን አስረዝሜ ቆየሁ፣ ቆየሁና፣
              በላሊበላ እድሜ፣ በአክሱም ቁመና፣
                ሳትመጪ ወደ እኔ፣ ሳላገኝሽ ገና፣
             ብዙ ነገር መጥቶ፣ ብዙ ነገር ያልፋል፣
               የራስ ዳሽን ራስ፣ አንገቱን ይደፋል፣
           አክሱምም ተንዶ፣ እንደ ጨው ይረግፋል፣
             ላሊበላም ወርዶ፣ ቁልቁል ይነጠፋል፣
                 ሰማይና ምድር፣ ያልፋሉ ታያለሽ፣
           እኔ ግን እዚያው ነኝ፣ አንቺ እስክትመለሽ።

By Elias shitawun

@getem
@getem
@paappii
88😢11👍8🤩4
🌿 MEET & MINGLE 🤝
One minute. Many connections.

Are you an artist, creative, cultural practitioner, organisation, or donor looking to connect, discover new opportunities, and explore potential collaborations?

Join us for an evening of quick introductions, meaningful conversations, and new connections with fellow members of the creative ecosystem.

⏱️ 1 minute to introduce your work
(For those interested)
🤝 Connect with new people
🔎 Discover new ideas and opportunities
🥂 Have fun and mingle

📅 29 July 2026
🕠 5:30 PM
📍 Creative Hub Ethiopia,
Old Post office, Piassa, Addis Ababa

🎟️ Registration: https://scan.page/5lJGCr

Come ready to share what you're working on, what you're looking for, and what you can bring to the table.
One minute. Many connections.
See you there!

#MeetAndMingle #CreativeEthiopia #Networking #CreativeCommunity #Collaboration #EUNIC #AddisAbaba

@getem
@getem
14👍2
=እኔ ነኝ የማውቀው =

አንዴ ብቻ ይድላኝ
አንዴ ብቻ ልረፍ
አንዴ ብቻ ልኑር
አንዴ ብቻ ልትረፍ
ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገው
እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማውቀው።

ሀብታሙ ሀደራ (እንዲህ ያለም የለ)
@getem
@getem
102😢20🔥17👍10
=ሶስተኛ አማራጭ =

'እኔ ወዲህ ማዶ አንተ ወዲያ ማዶ
አንገናኝም ወይ ተራራው ተንዶ'

ብለሽ የላክሽልኝ

ተራራው እንዲናድ ዞትር ከምንፀልይ
ከተራራው አናት እንገናኝና ዓለማችን እንይ።


ደሱ ፍቅርኤል(ሃገሬን ሰቀሏት)

@getem
@getem
23👍7
የሞኝ ታሪክ ✍️

ጊዜው ድሮ...ድሮ ፣ አስራሰባት ሰባ
ፍቅር ሳይወደድ ፣ ጥላቻ ሳይሰባ
ሃገር ባቢሎኗን፣ ገንብታ ሳትከፍል
እንዲህ አውግተናል፣ታሪክ ስንካፈል...
 
          * * * *
አንድ
የሀገር አትሌት፣ ኢትዮጵያዊ ጀግና
ተግቶ ያካበተ፣ ዝናን እስከቁና
ባንዲራን ወክሎ
ሃገርን አክሎ
ለሩጫ ይገባል፣ መስፈርት አጠናቆ
በድል ተስፋ ወኔ ፣ዓላማን ሰንቆ...
          .
          .
        እሽ
          .
          .
መንደርደሪያ መነሻቸው
የሩቅ መንገድ መሸኛቸው
ሲተኮስ ከነፈ
ፊትለፊት አለፈ...
          .
          .
        እሽ
          .
          .
ህዝብ አጨበጨበ፣ ላገር' ወኔ ሰጠ
ካሰለፈው' አብሮ፣ በምላስ ሮጠ።
* * * *
እሮጦ እሮጦ፣ ከፊት ሁኖ ከርሞ
ሃገር አጀብ እስኪል፣ ሯጮቹን ቀድሞ
ድሉን ሊረካከብ
ከደጁ ሲቃረብ
          .
          .
        እሽ
          .
          .
አንዲት ሸጋ፣ ከፊት ስትደግፈው
ለባንዲራ ነበር፣ ጨክኖ ያለፈው
ለሱ ይሁን ፣ላገር ባፏጨችው
ወኔውን ነበረ ከአፈር የፈጨችው።
የኋላ የኋላ
አቅም እየከዳው፣ ጆሮውን ይሰጣል
ላያት ሲከጃጅል ፣ ድሉን ይነጠቃል።
           
           * * * *
በእሩጫ መሃል ቆንጆ አይታይም፣
                    ፉጨትም አይሰማ
ቢከጃጅል እንኳን፣
                    ሽንፈት አያምርማ።
ለመሸነፍ ሳይሆን፣
                   ለመሸለም ጠንክር
በሩጫ ሜዳ ላይ፣
                  ባለም እንዳሰክር።

ጊዜው ድሮ...ድሮ ፣ አስራሰባት ሰባ
ፍቅር ሳይወደድ ፣ ጥላቻ ሳይሰባ
ሃገር ባቢሎኗን፣ ገንብታ ሳትከፍል
እንዲህ አውግተናል፣ታሪክ ስንካፈል

By ሰምረ የሽዋስ

@getem
@getem
@getem
18🤩3
⨳እናቴን በደልኳት⨳
ደካማዋን እንስት ፣ኡሚዬን በደልኳት
ስንቱን ችላችላ፣ እኔ መች ታገስኳት?!

ሚስኪኗን እናቴን ሀያቴን ጎዳኋት
ስትለፋ እያየው መች እኔ አገዝኳት?!
እንደው ቢጠናባት አቅሟ ቢደክም
❝አግዙኝ❞ ብትለን ትንሽ ከኔ ሸክም
❝ቁጭቱ አይቻልም ተዉ አቅቶኛል
ብሞትም አይገርምም ስቃይ በዝቶብኛል❞
ብትል!ብትለምን ብታስጠነቅቀን
ደግመን ስንበላሽ መች ሳምንት አለፈን?!
~^^^^^^^^^^^^^~
❝የቀን ተሌት ድካም ዃላ ተሰብስቦ
ሞት ሆኖ እንዳይመጣ በሀዘን ተከቦ❞
እያለች መከረች ደጋግማ ዘከረች
ደረቅ ልባችን ግን ዝም ብላ ቀጠለች!

ለቆሸሸው ህሊና ለደረቀ ልባችን
ምን ይሆን መፍትሄው መች ይሆን ነስራችን
መች ነው ምናስበው ለውዷ እናታችን
እረፍት የምንሰጠው  ሆነን ከልባችን?!
                              ❮መች ይሆን⁉️

አህያንኳ ስትወልድ በልጇ ታርፋለች
የኛ ነብሲያ ግን ማመፅ አላቆመች
የጌታዋን ቅጣት ክብደቱን መች ፈራች
                   ❮መች እሱን አሰበች?❯

እናቴን በደልኳት እናንተም እንደዛው
ፈጣሪን መች ፈራን መች ሆንን እንደሰው?
               ❮የእናትን ጥቅም መች ልኩን አወቅነው?!❯
ጀነት ከእግሯ ስር መሆኗን እያወቅን
ደነዝ ሆነን ኖርን ወደ እሳት ሮጥን።
           ~
ማማዬን በደልኳት ክብሯን አዋረድኩኝ
ስትለፋ እያየው መች ላግዝሽ አልኩኝ⁉️
    ⨳መች ለሷ ታገልኩኝ
                ⨳ መች ስለሷ ኖርኩኝ

  ~አሁን ግን~~
አሁን ግን እናቴ እንዳናጣሽ ፈራን
ደከመሽ መሰለኝ እኛንም ዝም አልሽን
                      ❮ ተስፋ ቆረጥሽብን!❯

             እነዛ ግን እማ.......
አዋቂ ጀግኖቹ ጎበዞች ያወቁ
ሰይጣንን ገፍትረው በግዜ የነቁ
ጀነትን ፍለጋ ያንቺን ሀቅ ጠበቁ
አንቺን አስደሰቱ አንቺን አከበሩ
ላንቺ ምቾት ሲሉ ስሜትን ቀበሩ
                           {ታድለው!!!}
ግዜ አላጠፉም እንደኛ ዘግይተው።

             እነሱማ~~~
መች እንደኔ ሆኑ አላዋቂ ደደብ
     'ምላሽ የሚሰጡ የማያንስ ከስድብ!'
መች እንደኔ ሆኖ ስሜት የገዛቸው
       ቁጭ ብለው የሚያዩ ስትለፋ 'ናታቸው
መች እንደኔ ሆኑ የማያዝኑ ጨካኝ
        አፍ ብቻ የሆኑ የሚመስሉ አማኝ
❪መች እንደኔ ሆኑ አስመሳይ አስኮናኝ!❫

ግን ምንም ቢሆንም ....
ምንም ቢሆንም ግን!አንቺን አላጣንም🤍
እኛ ብዘገይም ሞት አልቀደመንም
ስለዛ~
ጥፋቴን አውቄ ስተቴን አርሜ
ግዜው ሳይሄድብኝ እናቴን ኻድሜ
ከልብ አስደስቼ በስራም አግዤ
ብዙ ዱዐዎችን አፍሼና ይዤ
መሄድ አስባለው ወደዛኛው አለም
መቼም ፍጡር ሆኖ ሞት እማይቀምስ የለም❗️

        
``ድሮም```
     ❮የእናት ዱዐ ድሮም❯
መቼ አለው ግርዶ?
ሲሆን ታየዋለህ ወደ መሬት ወርዶ!


         እናት.......

ጀነት ከእግሯ ስር፤ እዝነት የተሰጣት
እናትኮ ማለት.........እውነትም እናት ናት።

    ~ኡሚዬ አታልቅሽ~
ኑሪ በፈገግታ~ፍክት!~ ድምቅ! ብለሽ
ደሰታሽ ብዝት ይበል ክፉ ሁሉ አይንካሽ

          አይዞሽ!!

ነገ ትካሻለሽ በኛ በልጆችሽ
                  ❮ጤና ብቻ ይስጥሽ❯
ግንኮ አውቃለው!
አፉ በይኝማ! ብዙ በድያለው።
ይቅርታ እስክትሰጪኝ እጠብቅሻለው
ለኔ ባይገባም አፉታን እሻለው
ከልብ እንድትምሪኝ እለምንሻለው
              (ያንቺ ልብ ለቅሶዬን አይቶ አያስችለው!
'''''''''''ግን ኡሚዬ'''''''''''''
ግን እናቴዋ ይህንን እወቂው.....
ካለፈው ስህተቴ በደምብ ተምሬያለው
ሀያቲ ስስቴ በ~ጣ~ም  ወድሻለው
                 ❮ጥሩ ልጅ ለመሆን ቃሌን ሰጥቻለው❯

By @Zoyaumumahi

@getem
@getem
@getem
21🔥4
#እኔም_እንደዚ_አንችም_እንደዚያ_!

ያንችው ጋ ንፋስ እኔጋ አይነፍስም
ያገርሽ ሰንደቅ ካገሬ አይገጥምም

ያይንሽን እምባ ከንግዲ አልጠርግም፣
ጉንጉን ፀጉርሽን አልደባብስም።

በይ አታማሪ ይሁን የሆነው፣
አንችም ተቀበይ እኔም ልቻለው!

የተከልነውም የሚያድግ አይመስልም፣
እንኳን ዛፍ ሊሆን፧
የሚያቆጠቁጥ ዘር አይታይም!

ተመልከች'ማ...

በሚሰባብር በሽኝት ዜማ፥
የጠራች ፀሐይ ማምሻ ስትደማ፣
ስታለከልክ በቀኑ መዝጊያ፣
አስታወሰችኝ፧
የኔና ያንችን አራራይ ማብቂያ።

መሸ ልግባበት እንደልማዴ
አንችም እንዳሻሽ እኔም እንደሆዴ።
በር መስኮቴን ከረቻችሜ፣
እናፍቃለሁ ላይሽ በህልሜ።

እንጃልኝ..

ሃምሌ መባቻው ቅር ቅር ይላል፣
ሳስበው...
የኔና ያንቺ ነሀሴ ደርሷል።

ይሄ ከሆነስ የመኖር ጣዕሙ፣
ሌትናቀኔ ሲያጉረመርሙ፣
ምን ተስፋ አለን ችለን ልንሽራት፣
ሕይወት እንዲ ነች በቃ እንተዋት!

በይ እንተወው፧
እምባና ኩርፊያ ይቅርብንማ፣
ማን ይሰማናል ብንጮኽ ብናማ?!

ይልቅ..

መኖር እንቀጥል ከንግዲም ወዲያ፣
እኔም እንደዚ...አንቺም እንደዚያ!
እንቀበለው አዲሱን መግቢያ...
እኔም ከወዲህ..አንችም ከወዲያ!🥀

@mypoems396
@getem
@getem
@getem
27🔥2😁2
=የምድረበዳ በረከት =

አንዲት ብርጭቆ ወይን
አንዲት ጤፍ እንጀራ እንዲት አሪፍ ቅኔ
እነዚህ ባሉበት በምድረበዳ ላይ ቁጭ ካልሽ ከጎኔ
ሌላው ምን ይሰራል
ምድረበዳው ሁሉ ዓደይ ለብሶ ያድራል።


በዕውቀቱ ስዩም (የማለዳ ድባብ )
መነሻ። ኦማር ካያም "Rubaiyat"

@getem
@getem
41🔥6😱2